Categories
miniArchiver

የችሮታ ፖሊቲካውን በቀና ስለማገዝ

About how the “Gift-politics” of prosperity party should be at minimum reality be conducted like.

Take this piece on PDF.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, October 6th, 2021GC.,

በችሮታ ፖሊቲካ፣ ብልጽግና ከቆነጸለአቸው የድርጅት ተፎካካሪዎች መሀከል እጅግ በነፃ ፈቃዱ ለግርምታ (surprise) የቆነጸለአቸውን ጥቂት የተፎካካሪ ድርጅትዎች ግለሰብእዎች በሹመት በመክተት የ”አካታች ፖሊቲካ/አስተዳደር” በእሚል ቅብ አምባግነናን ተግባር ጀምሮት አለ። ያም በሩቁ በኢህአዴግ. አስተዳደር ሲያንዣብብ የከረመ እቅድ እና ቃልመግባት ነበር።

የሆነው ሆኖ ይህ በተጨባጭ ከተከሰተ፣ ምርጡ የአቆያየት ሂደቱ እንዴት ቢሆን ነው? በደፈናው አብሮ መስራት/ሀገር መውደድ/በተገኘው መጠቀም/ወዘተ. መርኅዎች አይደሉም። አዲስ ትግበራ በመሆኑ የጠራ አካሄድ ይፈልግ አለ። ከአስተዳደር በላይ የህዝብ ጥቅም የተጣባው ሁነት ውልደት ነው። ከአስተዳደር በዘለለ የህዝብ ነፃ የመደራጀት መብትዎችን እና ደፈና ንጽውሳኔን (democracy) ሂደትን የእሚያጎሳቅል እምቅ አደጋነት አለው። እና የአልሰለጠነ ውጥን ቢሆንም፤ የሰለጠነ አያያዝ መፈለጉ ግንባርስጋ ነው።
ወደ እንዴት ይያዝ ስንሻገር፤ እስከ አሁን የታወቀው ምንም አለመታወቁ ነው። ለምሳሌ፣ የኢዜማ. ከፍተኛ አመራር፣ አቶ ግርማ ሰይፉ (በፊት አምደኛ፣ የግል ተወዳዳሪ ሆነው በመለስ ዜናአዊ ጀርባ በእሚዘረፈጠው የ”እንደራሴ” ስብስብ ዳር ላይ ለመቀመጥ የተመረጡ) በተሰየሙ ምሽት የአወቁት እንደአልነበረ እና “…የፖሊሲ ማቻቻል ውይይት እንከውን አለ…” ብለው ለኢሳት. እለትአዊ ዝግጅት መሳይ ወንድሜነህ ነግረውት ነበር። ሌላ የችሮታ ፖሊቲካው ሹመት ስጦታ ተቀባይዎችም እስኪሾሙ የአወቁት ጭምጭምታ አልነበረም።

ታዲያ እንዴት ነገርዎች እንደእሚከወኑ የታወቀ ነገር የለም ማለት ነው። ምን እንጠብቅ?

የመጀመሪያ ነጥብ፤ ነገርዎችን እስከ ፍፃሜአቸው አስቀድሞ በመንደፍ ማሳወቀወ ተገቢ ነው።
በተቻለ የተሰጡት ኮታዎች የተወሰዱት ግለሰብእዎች በአንድነወቅት ባይገኙ፣ ለመጡበት ድርጅት እንዲሾመደ አስቀድሞ ቢገለጥ መልካም ነው።
ቀጥሎ የተመረጡ ግለሰብእዎች በእራስአቸው፣ ወይም ብልጽግና ስር ከመንቀሳቀስ በድርጅትአቸው መሰረት እንዲንቀሳቀሱ፣ የቅጥር ናቸው ነውታ (claim) እንዳይበዛ ከእነእርሱ ይልቅ ድርጅትአቸውን መሾም ተገቢ ነው። የተሾሙበት ቢሮ/ተቋም በእርስአቸው ስር ሳይሆን በድርጅትአቸው ስር ተሰጥቶ አለ ከተባለ፣ የታቀደ ደባ ላለመኖሩ እንዲሁም ሀቀኛ የማካተት ፍላጎት ለመኖሩ እጅግ ማረጋገጫ ነው።
በስሩ እንዲሰሩለት እና አስፈፃሚ አካሉ መሀከል እንዲገኙ ሲአደርግ – ያም ተፎካካሪ ድርጅትዎቹን ሳይሆን ከመሀከልአቸው አንድ ግለሰብ ብቻ መሾም ነው፤ ለምሳሌ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮን ግርማ ሰይፉ መራሔነት ተሾሙበት እንጂ በደፈናው ቢሮውን ኢዜማ. የአስተዳድር ተብሎ አልተጋራም፤ እና፣ የመሾም እውነቱን ከተራ ስሞታ ወደ ሀቀኛ ተለያይቶ የመስራት መንገድ እሚያመጣው፣ ሙሉ ተቋም ወይም ንዑስ አስተዳደሩን በነፃነት እንደ ተፎካካሪ ድርጅት ለማስተዳደር እድሉ ከተመቻቸ ነው።
የፖሊሲ ማቻቻል መስራት፣ ብለው ግርማ ሰይፉ የጠየቁት እሚሰምረው ከተከታዩ አተያይ ነው። ከአዲሱ የ2014ዓም. የሕተም. (ሕዝብ ተወካይዎች ምክርቤት) በመጀመሪያ ልዩ ስብሰባ አጀንዳ የተለመደ የአስፈፃሚ አካልዎች ፈርሶ መስራትን ጠሚ.ሩ ሲከላከሉ አንዳንድ ዘርፍ በይነዘርፍአዊ (cross-sectional) ነው እንደ አሉት መንግስትአዊ እውነት በእየዘርፉ የተጋመደ ነው። ያንን የመነካካት በይነዘርፍአዊ ንክኪ ማመቻቸት እንጂ መሰረትአዊ የተቋም መምሪያ ፖሊሲ እና አቅምዎች ግን ለተፎካካሪ ድርጅትዎቹ መተላለፍ አሉብአቸው። ለምሳሌ የትምህርት ምኒስቴር ስራዎች ከወጣትዎች እና ሴትዎች አስተዳደር ተቋም መነካካቱ አይቀርም። ያንን ለማቻቻል እንጂ የትምህርት ትልምአግጣጫዎችን (policies) ብልጽግና ከአብን፣ ኦነግ ወይም ኢዜማ. ተነፃፃሪ ትልምአግጣጫዎች ማቻቻል እንዳይከውን ተጠባቂ ነው። አመክንዮው፣ ፖሊሲ መተግበር፣ (ቢያንስ በህግ በተሰጠ ተቋምአዊ አቅሙ መሰረት እንደ ተፈቀደለት ንዑስ ህግዎችን ማውጣት፣ የተለቁ አዋጅ ድረስ ህግዎችን ማስነሳት፣ ወዘተ. አቅሙ) የአስተዳደር እውነት ነው። ያ ከተጣጣበት፣ ተፎካካሪው በተገደበለት የስጦታ መንደር እራሱ አልተንቀሳቀሰም ማለት ነው። ሀቀኛ “ማካተት” አልተከወነም።
አጭር ነጥቡ፤ ድርጅትአዊ ሹመት እንዲተኮርበት እና ትግበራው በእዛ ትልም እንዲሄድ ስለመምከር ነው። ያ፤ የመጨረሻው “ተፎካካሪ ድርጅትዎች ማካተት” ሆኖ ሊመለከቱት እሚገባ ነው። በቀረ፤ የአነሰ አቅም የያዘ “የተፎካካሪ ድርጅትዎች ማካተት” ወደ ለየለት “የተፎካካሪ ድርጅትዎች መቅጠር” እና በስምአቸው የመግዛት አምባግነና ነጸብራቅ ሆኖ ይጠልል አለ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s