Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የችሮታ ፖሊቲካ ለንጽውሳኔ (democracy) እንደ ተፃራሪ [Gift-politics as Contradiction to Democracy]

About how “gift-politics” of Prosperity Party is beginning practical anti-democratic moves of sham-administrative participation of opposing parties in the party’s few appointments.

Take this post on PDF.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, October 6th, 2021GC.,

ድኅረ አምባግነናውን (the post-dictatorship) – ከለየለት አምባግነና በማጭበርበር ንጽውሳኔአዊ (of democracy) ስርአት ነኝ እሚለው ሀዲስ-አምባግነና – በብዙ መልኩ ሲንጠፋለል እናገኝኘው አለን። ንጽውሳኔን (of democracy) እሚያታልልበት እና እሚያመልጥበት መንገድዎችን በመዘወር እንደ ተጠመደ ነው። በአለም ዝማኔ እና ስልጣኔ መሀከል ብዙ ለንጽውሳኔም ስርአትዎች ቢያብቡም፣ አሁንአሁን በተለየ፣ ንጽውሳኔ እምቅነቱ (its potential) በእሚለዋወጠው የአምባግነና መንገድዎች እየተቸገረ ይገኝ አለ። የጉስታቭ ሊደን (Gustav Lidén) አምባግነና በንዑስ አይነትዎቹ ተጠንቶ አልተሰደረም ገና ሃሳቡን አረጋጋጭ እውነት በቅርብ የኢትዮጵያው 2013ዓም. ምርጫ ዙሪያ ተከስቶ አለ።
ብልጽግና መሬትአንሸራታች ድል ከአስከፊው (በተለይ ነፃ ድምጽ መስጠት አንፃር በእየመንደር ቅስቱ እንደ ቡና-ጠጡ ተንበሽብሾ የተከወነ ድምጽመስጫ ጣቢያ አሰራር፣ ድምጽ ሠጪውን እጅግ አስግቶት በድብቅ የመምረጥ ስነልቦናውን ከትቶ ሰልቦበት ተመልክተን ነበር፤ በግል ተሞክሮ እና ቅኝት፤ ያም የአልጠነከሩ ተቃዋሚዎችን በእየጉራንጉሩ የመቆጣጠር አቅም እራሱ አለማገዙን ለአለመጥቀስ ነው፤ – በድምጽጣቢያ በነብስ ወከፍ በጥቂት መቶዎች ከሺህ በታች ድምፅ ሲሰጥ ውሎ ስለነበር የእየመንደሩ የቱ ግለሰብ ማንን መምረጡ በእሚመስል መቀራረብ ቁንጽሉ ሰፈር የእሚመርጠው በገሀድ አስቀድሞ በመታወቁ እጅግ ነፃነት የአጣ የአልተለመደ ድምጽ መስጫ አሰራሩ ነፃነት ገዳይ ስለነበር፤ በኢትዮጵያ ከተማዎች ተጠባብቀው በእሚኖሩ ቤትዎች እና ሰፊቤተሰብዎች የታወቀች በመሆኗ ትንሿ ሰፈር 1500ተመዝጋቢ በቀላሉ በመሸፈን ሰፈሩን የእሚወክል ምርጫ ድምጽ አሠጣጥ በመኖሩ፣ ለምሳሌ በጸሐፊው ሰፈር በአንድ አይን እይታ ሁለት ድንኳንዎች የተለያዩ ድምጽመስጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ፣ ቀኑን ሙሉ በተለይ ከምሳበኋላ ድምጽ እሚሰጥ አልነበረም ማለት ይቻል ነበር፤ በማግስቱም የአሸነፈው ድምጽ 108 ሰው የመረጠው እና በሰፈሩ ከ700 ጥቂት የበለጠ መራጭ ድምጽ የሠጠበት ነበር። በመላ ኢትዮጵያ ምርጫቦርድ የከወነው ስልት ይህ በመሆኑ በእየሰፈሩ የነበሩት ነዋሪዎች ማንን ስለመምረጥአቸው አስቀድሞ ታውቆ ለነፃ ድምጽ አሰጣጥ የከበደ፣ ለማስፈራራት የቀለለ፣ ሲፈጸምም በገሀድ የቱ ቤት ማንን መረጠ በእሚል ደረጃ ስለእሚገመት ድምጽ አሰጣጡን የቀደመ የስነልቦና ጫና በማድረግ የተፅዕኖ ግብዣ በመስጠት፣ ህዝብ ነፃ ድምጽ የመክተት ፍላጎቱን በመቶበመቶ ደረጃ በቀረበ የአስቀረበት ወይም የነጠቀው አሰራር ነበር፤ ነፃ የአልነበረ ድምጽ በቀላሉ በእየመንደሩ ካድሬዎች “big brother is watching you clearly” እሚሉበት በመሰረትአዊነት የኮሮጆ እሳቤን የጣሰ ስለእዚህ የተበላሸ (foul) ነበር ማለት ነው፤ አሁንም በፉክክሩ የተገደሉ፣ የታሰሩ፣ ቅስቀሳ የተከለከሉ፣ ወዘተ. ተፎካካሪዎችን ለአለመጥቀስ ነው) ምርጫ ትግበራ ጀርባ ታወጀለት።
መንግስት ልመስርት ሲል፣ አምባግነናውን የፈራው መሰለ። ኢህአዴግ. እጅግ የበዛ ቁጥጥሩን የተቃወሙበት ወቅት፣ “አብሬ አሰራችሁ አለ” እሚል ቃል ለተፎካካሪዎች ይሰጥ ነበር። እስኪለወጥ፣ በአንደበቱ የደለለበት ስልት ሆኖ ቆየ። ከእናቷ ሆድ ወጥታ እናቷን እምትመታ በመሆን የአደገችው ብልጽግና፣ ምን ኢህአዴግ.አዊ ጥንካሬ በተለይ በአለምአቀፍ ግንኙነት እና ሰላም-ገበያውን በመቆጣጠር ብትወድቅም፣ በአንዳንድ ነገር ወደ ኢህአዴግ. የአምባግነና ስልት ካዝና በመግባት፣ መኮረጁ ተሳክቶላት አለ። የተረቱትን ዋናዋና ተፎካካሪዎች፣ አብሮ የማሰራት የኢህአዴግ. ካርድ ኢህአዴግ. አንስቶ አለ።
በአዲስ አበባ መራጭ ካርድዎች፣ የተባረረው የተፎካካሪ መንጋን – እንደ መርኁ ለአስተዳደር የአልተጠራ እና ረብ አትሠጠኝም የተባለ ተፎካካሪ – ብልጽግና ግን እየመራረጠ በኩሉ-ፈቃዱ፣ ማንም ሳይጠይቀው፣ አቅፎት አለ። አመክንዮው፤ የችሮታ ፖሊቲካ ነው። አዲሱ የአምባግነና ንዑስ ገጽታ ሲሆን፣ ተፎካካሪዎችን ለማድከም፣ ወይም አካታች ነኝ በእሚል ድኅረ-አምባግነና መስራች ሐሳዊ-መርኅ ሊከወን ይችል አለ። የችሮታ ፖሊቲካን ጉስታቭ መመልከት የአለበት፣ አዲሱ አምባግነና ሆኖ ግሉን በተግባር በኢትዮጵያ ስለአበቀለ ነው። በእዚህ መሰረት የችሮታ ፖሊቲካን በአጭሩ እንይ።
የችሮታ ፖሊቲካ ምንድር ነው? በፊትም እንደ አየንው፣ እንደ ሰላም ሻጭነት፣ አብይ የአውታረ አምባግነና ነው።
የችሮታ ፖሊቲካ (Gift-politics) እንዲገመት፣ እሚፈለጉ ፭ መስፈርትዎች ዝርዝር።
1 – ንጽ ውሳኔ የለም፤
2 – በምትኩ አምባግነና አለ፤
3 – አምባግነናውን እማይቀበል አዝማሚያ አለ፤
4 – ተፎካካሪዎች የመመረጥ እውነትአቸው እሚሰቃይ እድል ነው፤
5 – አንድ ወይም ንዑስ ወይም በጋራ የአሉ እና በህብረት እሚሰሩት ድርጅትዎች በላቀ አሸናፊነት ወደ ስልጣን ይመጣ አሉ።
በእነእዚህ ቅድመሁኔታዎች መሟላት መሀከል፣ የችሮታ ፖሊቲካ አስተዳደርአዊ ክንፉ ሆኖ ለመንግስት (ድኅረ)አምባግነናው ይጀመርለት አለ። አምባግነናው ሁለንተናአዊ ነው። ነገርግን፣ የችሮታ ፖሊቲካው በአስተዳደር ዘርፉ እሚዘረጋ አውታር ነው፤ እርሱም የጠቅላላ አምባግነና አብይ አሀድ ነው።
በምንነቱ ተቆንጥሮ የተገለጠው የችሮታ ፖሊቲካ ይህ ከሆነ፤ ክዋኔው እንዴት ነው?
ሠበበ ችሮታ ፖሊቲካ፣ በዋነኛነት አምባግነናን መደበቅ ነው። ጉዳትዎቹን ስር (ታች እንደ አለው) አምባገነኑ ንዑስ ኢላማዎችን አስደርጎአቸው አብሮ መጉረስ እሚችል ነው። አከዋወኑ በእየእውነቱ ወይም አውዱ ቢለያይም በደፈናው እንደ እሚከቷው ነው።
አሸናፊ ነኝ ያለ/ሆነ የተባለ ድርጅት፣ ንጽውሳኔ በአለመኖሩ አምባግነና ይጠቆምበት አለ። የአሸነፈአቸው ተፎካካሪዎች ምንም ወይም እሚረባ ስፍራ የለአቸውም። የሁሉን ተቆጣጠርክ ጫናዎች ይበረክትበት አለ። አሸናፊነቱንም ለመቀበል ይከብድ አለ። ስለእዚህ፤ በአስተዳደሬ መዋቅር አንዳች መካን-ጊዜ በመፈለግ እከትትአችሁ አለ እሚል ህገወጥ እሳቤ ይወለድ አለ። የተካተቱ ተቃዋሚዎችም፣ በስሩ ሆነው በአልተገለጠ አካሄድ ይሰሩለት አለ። ስለእዚህ ልክ የተሸነፈን ቀጥሮ የማሰራት የአክል፣ ነው።
የችሮታ ፖሊቲካ ጎጂ ጎንዎች ምንድር ናቸው? በአብነት ደረጃ እሚከተሉትን እንይ።
ሀ – አምባግነናአዊ ተቃውሞ ሊፈነዳ ሲል የማርገብ ጉልበት አለው፤
ህዝብ የአነገበው ተቃውሞ ሞላጎደል ዘወትር እሚወክሉ መሪዎች ብቅብቅ ይል አሉ። በተፎካካሪ ድርጅት ደረጃ ከተቀናጁ፣ እነእርሱን ከመሀከልአቸው ወደ አምባገነን ድርጅቱ በመውሰድ፣ ህዝቡን በራቀ ተዘዋዋሪ እንደምታ የማረጋጋት እውነትን እንዲአገኙ የእሚከወን በመሆኑ ይህ ሊከሰት ይችል አለ።
ለ – በቀኑ ፍፃሜ እንደ ስልቱ ፍፃሜ አምባግነና የአግዝ አለ፤
በመጨረሻ፣ አምባግነናውን የፖሊቲካ አስተዳደር እና ሀገር እውነቱን ፈጽሞ ለመቆንጠጥ አዲስ በሩን (ሌላ የለበሰ አምባግነና በመሆን) ይከፍትለት አለ። ስለእዚህ፣ የእውነት ቢከወን እንኳ ከመዝሩጥ እንደ ማንሾለላ ጥቂት (ተረቱ ከምግብ ወደ ነፃነት ይቀየር እና) የማጋራት እውነት ነው። ማለትም፤ ተፎካካሪዎችን በመሰብሰብ ሰበብ ምላሹ የመጠቅለል ህልምን ማሳካት ነው። ልክ እንደ ሐሳዊ-ህግአዊነት (rule by law)፣ በተፎካካሪህ ግዛ (rule by (your) opposite parties) የአለ ነው። ያ፤ ከፍተኛ ደረጃው ማለትም ሊሰበር የተቃረበ የማጭበርበር እሳቤ ነው። ሐሣዊ-ህግአዊነት (rule by law) ወደ ህግአዊነት (rule of law) የተቃረበ ልእለኃያል ማጭበርበሪያ እንደ ሆነው፣ ይህ ችሮታ ፖሊቲካም፤ ለንጽውሳኔ የተቃረበ መስሎ እሚታይ ነው። ጭራሽ ተርታውን (the mediocre) ንፁሕ የንጽውሳኔ ተግባር መስሎ ሊታየው እሚችል ነው። ዘንድ፤ አጭበርብሮ አምባግነናን የማቋቋም እድሉ የተለጠጠ ነው።
ሐ – የፖሊቲካ ተፎካካሪነትን ይጎዳ አለ፤
ድርጅትዎች ለመቃወም የነበረአቸው ተነሳሽነት፣ ህልም፣ ፍላጎት፣ የአቅም መሰብሰብ፣ የትኩረት መከማቸትን፣ የአደክምብአቸው አለ። መከፋገልን፣ አለመተማመንን፣ ወዘተ. ሊወልድም ይችል አለ። በአተገባበሩ ደግሞ፣ ከፍተኛ ቀውስን ፈጣሪ ነው፤ የአልተጎረጎረ ጫካ (unchartered territory) በመሆኑ፣ ለሙስና፣ ጥቅመኝነት (በ ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም ቋንቋ መሸጦነት)፣ በቀኑ መጨረሻ፣ ክፉ ተፅዕኖው የአየለ ይሆን አለ። ተፎካካሪዎችን ሰባብሮ በመነጠል፣ አድክሞአቸው የማፍረስ ሁሉ እምቅ ኀያል ጎጂነት አቅፎ እሚንተከተክ ገሀድ ነው። በተግባር ወቅትም፣ ድርጅትዎችን ከትልምአግጣጫአቸው (from their policies) ሊያለያይ ወይም ሊያስከፍል (to be compromised) እሚችል ነው። ከዋና ተቃውሞ ስልት፣ ዘዴ፣ ወዘተ. በመለየቱ፣ በተፎካካሪ ተቋምዎች አደጋጣይ ነው።
መ – የንጽውሳኔ ልምምድዎችን (democratical practices) በከፍተኛ ደረጃ የአከስም አለ፤
የህዝብ ድምጽ ዋጋው ሉዓላዊ ነው። ከእርሱ በላይ የለም። ዘንድ፤ የተመረጠ ድርጅቱ በአሸነፈ መጠኑ ወኪል ሉዓላዊ እንዲሆን እና እንዲሰራ የተጠነቀቀ ውክልና ይሸከም አለ። እንጂ ሶስተኛ አካል የለም። ይህ ግንደ ንጽውሳኔ ብቸኛ መርኁ ነው። አምባገነኑ ከደረመሰው፣ መሰረት መርኁ ተናጋ። የተሸከመውን ቀጥተኛ ተዋረድ የአለው ኀላፊነት ወደጎን ወደ ህዝብ የአልመረጠአቸው በማዛወር፣ የከበደ ደባ በውክልና ጽንሰሃሳብ እና ተግባሩ ይወትፍበት አለ። አስቀድሞ፤ ለይስሙላ ከአልሆነ፣ አምባገነኑ የአሻውን ወደ አስተዳደሩ ከወሰደ ምርጫ መከወኑ ስህተት ይሆን አለ።
ሠ – ህዝብአዊ ለዑዋላዊነትን የአከስም አለ፤ (የህዝብ ድምጽ መከበር የንጽውሳኔ አንድኛ መርኅ ነው። በተለየ፣ የእንደራሴ ንጽውሳኔ አይነት፣ እሚተገበረው፣ የህዝብ ድምጽ በማክበር ብቻ ነው። የአለው፤ ያ እሚከወንበት ብቸኛ አንድ መንገድ ነው። ህዝብ ወኪልዎቹን ከእንችል አለን ብለው ቀረቡ መሀል መርምሮ በመምረጥ ስለእዚህ እሚሾምበት ነው። ምንም በቀረትአዊነት (exception) ለእዚህ የለውም።
ረ – የህዝብ የፖሊቲካ ነፃነት ያም መሰረትአዊ መብት ነው በከፍተኛው ደረጃ ይገረስስ አለ፤
ተቃውሞ ፖሊቲካ መሰረትአዊ እሳቤው፣ በሃሳብ ልዩነት ህዝብን ማደራጀት ነው። ድርጅት እሚመሰረተው፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንደ አሉት (በ ዛሬም እንደ ትላንት?) ለገንዘብ ማግኘት ወይም ደግሞ የውሸት ህዝቡን ለማታለል (በእጅአዙር የአምባገነኑ መሳሪያ ለመሆን እሚመሰረት ተቋም) ከአልሆነ በቀረ፣ አንድ ድርጅት መነሻ እና መፈጠሪያ የህላዌ አመክንዮው አንድ ሃሳብ በተለየ መንገድ በመያዙ ነው። ህዝብም፤ በስሩ እሚደራጀው እና እሚሰበሰበው፣ እሚደግፈው እና ማህበረሰቡን ወደ እራሱ ለመጎተት እሚታገለው፣ የሃሳብ ልዩነት በመኖሩ ነው። ይህ መሰረትአዊ ገጽታ፣
ሰ – ተተንባይ፣ መደበኛ፣ የፖሊቲካ ልምምድን ይጣረስ ቀጣይ የፉክክር ወቅትዎችንም ይጎዳ አለ፤
በችሮታ ፖሊቲካ የተሰናሠለው፣ በተፎካካሪዎች ህገመንግስትአዊ ነፃ ድንበር የሰረገ የአምባግነና ደባ፣ ቀጣይ ፉክክርዎችን የአደበዝዝ አለ። ጠንክሮ እሚመጣውን፣ አስጊ የእሚሆነውን፣ አስቀድሞ በማቀፍ ፉክክርዎችን የአደበዝዝአቸው አለ። ለሙሉ ትግል የእሚከወነውን (ለመንግስት ምስረታ) መርኅአዊ መሰረት የእሚገነባው ነፃ ፉክክርን የአበሳጨው አለ። ባላሸንፍ፣ ከአሸናፊው ልግባ ከአሁኑ ልስራ እሚል የፖሊቲካ የስነልቦና ቀውስ የአወርስ አለ። በሙሉአቅም የመደራጀት፣ የመፎካከር እና መንግስትነትን መስርቶ ሀገር የማሻሻል እድልዎችን ይጣረሰው አለ። በጎን ሴራዎች ግብዣ አላስፈላጊ ንክኪዎችን እና እውነት/ሁነትዎችን በመጥራት፣ ሴረኛ ፖሊቲካን የአስተናግድ አለ።
ሸ – ተጠያቂነት ይኮስስ አለ፤
ይህ የተዛባ ርእዮተ ፖሊቲካ በመሆኑ፣ እሚጠየቀውን አካል የአግበሰብሰው አለ። ብልጽግና እንደ ድርጅት የወደቀ ክወና ሰራ ቢባል እንደምን በመቶ እጅ ኀላፊነቱን ይቀበለው አለ? በጋራ ሆነን ሰራን አብረን እንጠየቅ ወይም እነእርሱ አሳሳቱኝ ወዘተ. የማለት እድሉን ማን ይከላከለው አለ? እንደ ተጠቀሰው ለማነካካት እና በምላሹ አምባግነናአዊ ትርፉን መዛቅ እንጂ፣ ተጠያቂነትን የእሚያኮስስ ርምጃ ነው። ተፎካካሪዎች ቢጠየቁ እንኳ ከህዝብ ይሁንታ በተሳሰረ እውነት አልተሾምንም ስለእዚህ አንጠየቅም፤ ወይም ሌላ ነጥብዎች የመፈጠር እውነትአቸው ፈጽሞ አይዘጋም።
በደፈናው፤ የችሮታ ፖሊቲካ፤ በሙሉ መጠን ወይም ከፍተኛ ቅርርብ የአሸነፈ ተፎካካሪዎቹ ጋር ሄዶ በነፃ ፍቀዱ (አለ ደንብ እና ህግ፣) እየመራረጠ እሚወስድበት እውነት ሲሆን፣ አምባገነኑ በቸርነቱ እሚከውነው ነው። በርቀት የህዝብ ተፅዕኖ መነሾው ነው። አሰራሩ ግን ፈጽሞ ነፃፍቃድ እና ሁሉን ዘዋሪነት ነው። ግፊትዎችን ብቅብቅ ሲሉ የመቆጣጠሪያ ወቅትአዊ ስልትም ሆኖ መታየት እሚችል ነው። የንጽውሳኔ እና መሰረትአዊ የፖሊቲካ እውነትን እሚያበላሽ ጠንቀኛ ገሀድ ሆኖ የተገለጠ ነው፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “የችሮታ ፖሊቲካ ለንጽውሳኔ (democracy) እንደ ተፃራሪ [Gift-politics as Contradiction to Democracy]”

[…] በችሮታ ፖሊቲካ፣ ብልጽግና ከቆነጸለአቸው የድርጅት ተፎካካሪዎች መሀከል እጅግ በነፃ ፈቃዱ ለግርምታ (surprise) የቆነጸለአቸውን ጥቂት የተፎካካሪ ድርጅትዎች ግለሰብእዎች በሹመት በመክተት የ”አካታች ፖሊቲካ/አስተዳደር” በእሚል ቅብ አምባግነናን ተግባር ጀምሮት አለ። ያም በሩቁ በኢህአዴግ. አስተዳደር ሲያንዣብብ የከረመ እቅድ እና ቃልመግባት ነበር። […]

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s