Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ጸረ-ዜሮጅማሮ ኢትዮጵያ [Anti-Zero Ethiopia]

About steps to delve into in knowing how to stop “zero-beginning” culture of Ethiopia in almost every aspect.

Take this generic piece on PDF.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 30th 2021GC.,

መተዋወቅያ

ከዜሮ መጀመር በብዙ ዘመንዎች ጀርባ የተጣባ ኢትዮጵያአዊነት እንደሆነ አለ። ያም፤ እኔ እሻል፣ የቀደመው አይረባ፣ ወዘተ. ከእሚል የኀሳብ አተያይዎች እሚከተል ተግባር ነው። የዘመነ ህላዌ የመሰረተ ህዝብ በቀላሉ እሚያሸንፈው የአጥንትአዊነት አብነት ነው። የጊዜ ጽንሰሃሳብን የአለመረዳት እና ለነገ አለመጨነቅ የሰፋበት አኗኗር የእሚያስከትለው የቀጣይአዊነት ስርጉደት ወይም ቅወሳ ነው።
በኢትዮጵያው ህዝብ፤ ዜሮጀማሪነት የአለ ትልቅ ጉድፍ ተደርጎ በደፈናው ይወሰድ አለ። በተለይ በቅርብ ወቅትዎች ይህ እየተደጋገመ ይገኝ አለ።

፩) ጠቅላላአዊነትን መሻገር

ዜሮ ለጠቅላላ እኩሌታ ለመሆን የቀረበ ነው። በደፈና የእሚደረጉ ደመነብስአዊ ነገርዎች ናቸው። ደፈና/ጠቅላላአዊነት ስለእዚህ፣ የአለመብሰል እና በኀሣብ እና ድርጊትዎች የአለመስረግ ዕዳው ናቸው። ለምን ጠቅላላአዊነት ተለመደ? የአልተዘረዘረ (not-detailed)፣ እና በልዩአዊነት (specialization)፣ የአልጠጠረ ጉዞ አለ ማለት ነው። ከእዚህ የተነሳ፣ የአልተከማቸ የማእዶት (transformation)፣ ኀርየት (journey)፣ በቀጣዩ አፍራሽ ሊፈርስ ውስብስብነቱ አይታየውም። የተወሳሠበ እውነትን የተመለከተ አፍራሽ ግን ከዜሮ ለመጀመር እንደ ጠቅላላአዊ ሙከራዎችን አፍራሹ ነፃነትም ሆነ ሞራልአዊ ጥንካሬ አያገኝም። በአኗኗር፣ ፍልስፍና፣ ቋንቋ፣ አሠራር፣ በደፈናው በእውነት ሁሉ፣ ወደ ሠመጠ እና ሠፋ አገነዛዘብ መስፋፋት አስገዳጅ የጸረ-ዜሮጀማሪነት መሰረት ናቸው።

፪) የትውልድ(ዎች) ቀጣይነት የአለው አስተዋፅዖ

አንድ ዘመን የወጡ የትውልድ ምልክትዎች ወዲያው ተተኪ ሲመጣ ይሠርግ አሉ። ወዲአው ይረሳ አሉ። የትውልድ(ዎች) ቁንጮ የእየዘርፉ ገላጭ ግለሰብእዎች፣ ከተሰለቡ፣ ቀጣይነት ይገረሰስ አለ። ቀጣይነት ከጠፋ፣ መጪው ከአዲስ ለመጀመር ይገድ አለ። ክፉቱ፤ ኢትዮጵያ ድኀ ናት። በየቱም ዘርፍ እመርታ የሞከረ ዜጋ ውጭ የመውጣት ብሎም በእዛው የመቅረት እድል አሉ። በእዛው ትውልዱ የሞካከረው ከህዝቡ ንቃተህሊና ይሰለብ አለ። መጪው ለመፈንጨት ወይም ቢያንስ ከዜሮ ለመጀመር እና ሃይባይ ለማጣት ይገድ አለ። ለገሀዱ/ህዝቡ እና ንቃተህሊናው የተንጠለጠለ የትውልድዎች አንድአንድታ (መዳህዎች)፣ መጣሁባይን የማረጋጋት አቅም ይኖረው አለ። ይህ ዘርፈ ብዙ ውጤትዎች አሉት። ለምሳሌ፤ ሀገርንም በጊዜ መስመር አንድ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው። ትውልድዎችን የማጠባነቅ እና አዋህዶ የማስዘገም ገጸበረከቱ ምትክየለሽ የብሔርአዊ እመርታ ምስጢርም ነው።

፫) ቋንቋ እና ተግባቦት ዝማኔአቸው ጸረ-ዜሮጅማሮ ነው

የቋንቋ አቅም መድረቅ፣ ተግባቦትን መደዴ አድርጎ የአስቀር አሉ። በተደጋገመ የተግባቦት ስልት በተለይ በቋንቋው የደከመ አያያዝ ሲከወን፣ ተግባቦት አእምሮን ፈጣሪ አያደርገውም። የተደጋገመ አተያይ ደግሞ፣ አእምሮን በቁም ይቆልፍ እና ግለሰብእዎችን ቁምሽልብ የአደርግአቸው አለ። ደመነብስአቸው በእላይአቸው ነግሶ፣ ሰብእአዊው የህላዌአቸው አላባ፣ ይሰለብ አለ። እዛ ቸልተኛ ኑባሬ ውስጥ ሲከረም፣ አለም እሚሰድበው ህዝብ የመሆን እድል ይያዝ አለ። ለምሳሌ አማርኛ ቋንቋን ሰድበው የፈጠራ ነገር አያስጽፍም የአሉት እእነ ስብሐትለአብ ገብረእግዚእአብሔር በእነ ዳኛቸው ወርቁ እና ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ውጥንዎች በደፈናው የከሸፈ አገነዛዘብ፣ ዛሬ ወደኋላው ከቅጥውጭ ተሽቀንጥሮ የወደቀ ሆኖ አለ። አማርኛንም ሆነ ሌላውን ቋንቋ ነቃነቃ አድርጎ መገልገል፣ አለሙን አስፍቶ፣ የማንም አላወቀም እኔ ልጀምረው ከአዲስ እሚለውን የዜሮጅማሮ ገሀድ ይጻረረው አለ፤ ሌቋሆ. (ሌላነገርዎች ቋሚ ሆነው)።

፬) እሪና፣ እና ነፃነት፣ ከ ዝሙን አስተሳሠብ

ሰው/ቡድን፣ እኩልነትአጥ፣ እና ነፃነትአልባ፣ ዝሙን አስተሳሰብም ከሌለው ማህበረ ሰብእ ከበቀለ የቀደመውን የመደምሰስ ፍላጎቱ ተጠባቂ ነው። የአውሬአዊ/ደመነብስአዊ ክፍሉ በእዚህ የአገኘው እና የበላይ የአጣ እድሉ ይጠራ አለ። የተጀመረውን ደምስሶ የዳግ-መመስረት የአልተማረ ጉጉቱ እሚጸናው፣ የበታችነት ስሜቱን ማጣጫ፣ ቂሙን ማወራረጃ አድርጎ የቀደመውን ስለእሚንቅ፣ ስለእሚአወድም ነው። የወያኔ ወታደርዎች፣ በእየከተማው ሲገቡ የእየ ቢሮውን ማህደርዎች በስሜት የአወድሙ ነበር። ይህን መሰል የነፃነት አጥ፣ እሪና አለመኖር፣ ወዘተ. የወለዱአቸው መታፈንዎች እሚፈጥሩአቸው የእየተራበተራ አምባግነናዎች ናቸው። በአንድ ብሔርአዊ መግባባት፣ እሪና፣ አርነት፣ ወዘተ. የተመሰረተች ሀገር፣ አንድም የመካበት እውነትን ትከተለው አለች፤ በሌላም የአፍርሶ ገንቢ እድሉን ታደባይበት አለች። እኩል እና ነፃ ህዝብ የእሚአውቀውን የማዋጣት እና የማስተጋበር እንጂ የማበላለጥ ወይም እኔእሻል ባይነቱ በጎጂ መንገድ በአደባባዩ አይወጣበትም። የዘመነ ሀገር በ ቋንቋ ሁሉን አቅፋ በመራመዷ፤ ዜሮጅማሮን በስውር መሳለመሳ ደምሳሽ አሻራዋ ድልትነሳው አለች።

) ትውልድአዊ መጋመድ

የአቶ ጌታቸው. .. መጽሐፍ፤ የትውልድ ቅብብሎሽ እንደ እሚከራከረው፤ የትውልድ ቀዳሚ ከተከታዩ አልተሳሠረም። ሀገርን ከመጉዳቱ ሰፊ አሉታው በዘለለ፤ የዝግመት ማከማቸት ትትረቱንም ይሰብረው አለ። ይህ ከቀደመው የሰፋ እና የሰመጠ ጉዳይ ነው። ይህ መሰረትአዊ የወጥ ህዝብአዊ ዝግመት መኖርን ፈላጊ ግን እጦቱ የእሚሰጠው ተፅዕኖ ነው። ወጥ ሀገርአዊነትን አበላሽቶ፣ በደፈና ሀገርን እንደ እሚጎዳው ለዜሮጀማሪነትም ግብዣ አቅራቢ ነው። ጭራሽ የጎልማሳነት ገጽታን ከማህበረሰብእ በመግፈፍ፣ ናዋዥ ትውልድአዊ ውድቅ-ነፃነትን ይተው አለ።

፮) ሀቀኛ ወለል

ሀገርን የመሰረተ ተገቢ ወለል አለመኖሩ፤ በግልበቂ አመክንዮ ዜሮጅማሮን መስራች እና አስክሂያጅ ነው። በእርግጥ ላይ የደለው ዝሙን አስተሳሰብ እና የጊዜ ግንዛቤ ከአለ፣ የጎዳ ትላንትንም ከመደምሰስ ሙከራ የ ታሪኩን ማንበር (maintenance) ጉዳይ ይከውን አለ። ተገቢ ወለል ከአለ ግን፤ ምንጊዜም ወደፊት የመጓዝ ጉዳዩ እንጂ የማፍረሱ ነገር እድሉ ይቀንስበት አለ።

ዝብግንዛቤዎች

፩) ዜሮጅማሮ የቀደመውን የግድ ማቀፍ አይደለም

ለውጥ አስፈላጊ ይሆን አለ። ምንአልባት ገና የአልተገነዘብንው እውነት ገና አለ። እንደ ኋላቀር ሀገር ምንም ቢደረግ ገና ፍፁምነት ላይ አልተመጣም። ስለእዚህ፤ ለውጥን መከወን ተጠባቂ ነው።
በሂደቱ ሁሉ ግን የቀደመውን መከተል ማለት ተደርጎ ዜሮጀማሪነት መወሰድ የለበትም። አዲስ ጅማሮ ከአስፈለገ፤ እንደ ዘርፉ መከወን ተቻይ ነው። ዳሩ፤ ዜሮጅማሮን ከአዲስ ጅማሮ ማጋጨት አያስፈልግም። ዳሩ፤ የተለየ ለውጥ ሲከወንም፤ ዜሮጅማሮ ተደርጎ እንዳይታይ ደግሞ፣ ከማህደር አያያዝ አንፃር ምንም ክፍተት መደረግ የለበትም። የፈለገ ለውጥ ቢደረግ፤ የተደረጉ ነገርዎችን መሰወር፣ እና ማውገዝም ከአስፈለገ ከማህደር እና ተያያዥ ማናቸውም (የቀደመ ድርጊቱን ከዋኝዎች ማጥፋት፣ ወዘተ. ጭምር)፤ ጋር ማያያዝ ተገቢ አይሆንም።

፪) ዜሮጅማሮ በጎጎንዎች አሉት

ጭፍን ወይም ደፈና አረዳድ ለዜሮጅማሮ አያስፈልግም። በእየራሱ መንገድ ከዜሮ መከወን እሚፈለግብአቸው ጉዳይዎች አሉ። የአልተመሰረቱ ነገርዎች ብዙ ናቸው። ያንን በመመስረት ዜሮጅማሮን መጥራት ተገቢ አይሆንም።
ከዜሮ መነሳት፤ እሚገናኘው ከ እኔ ብቻ፣ ማለት፣ አምባመግነን፣ ሀቀኛ ስርአት አለመወጠን፣ ወዘተ. ነው። እነእዚህን በማከም፤ ቀጣይአዊነት (continueity) የአለው ህህላዌን ማበጀት ለሰው ስልጣኔው እና ዝግመቱ አስፈላጊ ነው። እንደ ሂደት ዋጋ የአለው አካሄድ አይነት ሲሆን ለይዘቱም አስተዋፅዖ አለው። ታጥቦጭቃ፣ ከመሆንን ማከም፣ አካልንም ማገዝ ነው ማለት ነው። አብሮ ዝብአረዳድዎችን ማስታገስ አስፈላጊ ነው።

መደምደሚያ

በደፈናው፤ ህይወት በእየ ዘርፏ ኢትዮጵያ ውስጥ ዜሮጅማሮን አበረታች ናት። ጥንትአዊ፣ ደመነብስአዊ፣ ነገን ቸላባይ እጅግ ገልቱ የጊዜ እና ዝማኔ አረዳድ በመኖሩ፤ ነገረወ የመደምሰስ እና የመናቅ እድሉ ከፍተኛ ነው። በደፈናው እንደሆነው። ከትድድር (management)፣ ጉዳዩ በላይ፣ የአመለካከት፣ ህልም ማለም፣ እውነትን የመረዳት፣ ወዘተ. አቅምዎች ሁሉ እሚያጠያይቅ ወይም እሚነካካ ለመሆኑ እምብዛም ጥያቄዎች የሉም። ጸረ-ዜሮጅማሮ ኢትዮጵያ፤ የእሚጠልፋትን አጥንታ ለማከም ደዌዋ እንደሆነ እንድትረዳውም የአስፈልጋት አለ። ልክ ይህን ስትዘነጋ ከርማ፤ ሀቀኛ መሰረት የጣለች እለት ቀና ከዜሮ-ጅማሮ እምትከውንበት አንዱ ፍሬነገር ጸረ-ዜሮጅማሮነቷን ማስታመም ይሆን አለ፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s