Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ህገወጥ፣ ሙያወጥ፣ ስነምግባርወጥ፣ ሀገርአዊ ክብርነክ፣ ብርቱ-ሰነፍ አማርኛ፣ እና ቀውሱ ህልውና ዘመቻ

About the continued national foul by TPLF and all formal administrators in using illegal, unethical, hopeless, worst propaganda terms.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, October 05th 2021GC.,

ስልጣን በተለወጠ ቁጥር ወንመማማችዎች መሀከል መዋጋት አይኖርም…በእሚል እሳቤ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንደገለጡት በመፈንቅለ ኢህአዴግ. ጀርባ፣ ፍቅር እና መደመር” ተብሎ ሁሉም ፖለከቲኛ መሰባሰብ ጀምሮ ነበር። የአረጀ አመል ቶሎ ቀርቶ ከትቶ አልጠፋ ብሎ ወዲያው አፈናና እና እስር ከተትሎ፣ ወዲያው የስልጣን-ቅሬታ ወለድ ጦርነት መጣ። ብሔርአዊ-ቀውስ ይፋ “ውጊያ”፤ ከ2013ዓም. ጀምሮ አሁን አመት ሊሞላው ሆነ።

ሁሉን ትተን የተሰለቸ “የዛቻ ዘገባ” እና የቋንቋ ክሽፈትን በአጭሩ እንቆንጽል።

___________________

“መደምሰስ” እንደ ቀዳሚ መርኅ ተደርጎ በአስተዳደርዎች ሲሠራበት እና ሲሠበክ የተለመደ ነው። ይህ የዘገባ ስርጭት መሀል ምስል ዜናው “መደምሰስ” እሚቻልበትን መንገድ አግጣጫ ስለመስጥት ሲሆን፤ በመቀባበር፣ ሳያስተርፉ በመግደል፣ ወዘተ. ዛቻዎች ይጠናከር እና ይዘቱን የአዳብር፣ ይከተሉትም አለ። [የመደምሰስ ርብርብ ጽሑፍ ዜና የ2021.8.21እኤአ. አሚኮ.]

__________________

በእየመገናኛብዙነኑ (የህዝብ/መንግስት)፣ “ህዋሃትን/ጀንታውን/ ወዘተ.እንቀብረው አለን!!”…ፀያፍ ታሪክ ጀርባ አቻ ፀያፍ አማርኛ እየተነዛ አለ። በጋዜጠኛዎች፣ ሰራዊት፣ ነፃ ወይም ፈቃጅ-ዘማች፣ ወጪ ወራጅ፣ መንግስት አስተዳዳሪዎች፣ ህገወጥ፣ ሙያወጥ፣ ስነምግባርወጥ፣ ሀገርአዊ ክብርነክ፣ ብርቱ-ሰነፍ አማርኛ፣ ቀውሱ “ህልውና ዘመቻ” ጀርባ እየተደመጠ አለ።

ቀደም ብሎ ለአዲሱ አመት፣ በመስክ ከሰራዊቱ ጋር በዓል የአከበሩት ዶር. ጠሚ. አብይ አህመድ “እሚገነባው ዘመንአዊ የተሰኘው ሰራዊት” ነው ቢሉም፣ የውትድርና እና አስተኔሰብእ ህግዎች (military and humanitarian laws) በ መሠረትአዊ ደረጃ የአልሰለጠነ ለመሆኑ አሳባቂ ነው። የተጠቀሰ አባባሉ፣ በመንግስት መገናኛብዙሃንዎች ሁሉ – ከ”ህግ ማስከበር ዘመቻ” ወደ “ህልናውና ዘመቻ” የተቀየረው ዉጊያ ከተጀመተ በመጀመር – አለማቋረጥ የእሚያስተጋባ ሆኖ ወራት ሲቆጠር፣ “ከገባበት አማራ ክልል ወያኔ በነብስ አይወጣትም!” “እንዳሉ እንደመስስአቸው አለን!” “ፈጽሞ እንጨርስአቸው አለን!” “ልንቀብርአቸው ነው!” “ግብአተ መሬቱ እዚህ ይፈጸለተት አለ!” “መቃብሩ አማራ/አፋር ክልል ነው!” ወዘተ. እየተሰኘ አለማቋረጥ ሲሠማ ነበር።

ከመደበኛ በድንጋይ እና ዱላዎች ለመዋጋት የተነሳ እስከ ክልል ፕሬዝደንት አገኘሁ ተሻገር የተደጋገመ መፈክር መሰል ወደ ግጭቱ የተንሰራፋ አቀራረብ ሆኖ አርፎት አለ። የረዥም ዘመን ታሪክ ባለለቤት ሀገር አተዳደር ኃላፊነት የተሸከመ፣ የታሪክ አላባአዊ የሆነ፣ የትልቅ ሀገር ይፋ አስተዳደር፣ ዘፋኝ እንደ አለው “…ወራሪ ሳይመጣ በግልዘችን ጉዳይ…” የእራስ ወገኑን በእዚህ መንገድ መግለጡ ከፍተኛ የስነምግባር ውድቀት፣ የቋንቋ እና ሀልዎቴ (attitude)፣ ህግዎች፣ ወዘተ. ጥሠትዎች ነው።

ፈጽሞ የቱም በሰውልጅዎች መሀከል የእሚከወን ውጊያ ማብየያ ኢላማው መጨራረስ እና መጠፋፋት አይደለም። የውጊያው ተልእኮ ግብ (operation goal) ጥቅም ወይም መብት ይገባኝአለነት ብቻ በመሆኑ ያንን ማሳካት ውስጥ መድረስ እንጂ ጠላንት ፈጽሞ መደምሰስ ፍፃሜው (የወደ ፍፃሜው አካሄድ) እንዳይሆን አለምአቀፍ የውጊያ እና ሰብአዊ ህግ ይከለክለው አለ። የውጊያ መብትዎች ጥሠት፣ ዘርማጥፋት፣ ወዘተ. ጉዳይዎች በጣሽ አያያዝ ይነን አለ።

እነእዚህ የጭካኔ ጥግ እና መሰል አስተያየትዎችን በእየቀኑ ፳፬/፯ በእየ “ህዝብ” መገናኛብዙሃንዎቹ መለፈፍ፤ “የቢራ ማስታወቂያዎች ስርጭቱ ህፃንዎችን በቤትአቸው እንዳይኖሩ ይረብሽ አለ” ብሎ ከመገናኛብዙሀንዎች ከከለከለ (ገና ሲሰየም ሰንሞ) አስተዳደር የእማይጠበቅ ነው። ዳር እስከ ዳር የእሚያስተጋባ የመቀባበር አፈር የመገባባት መደማሰስ፣… ዛቻዎች፣ የሙያ እና የህዝብ መደበኛ ህይወት መሰንጠቅንም የአላከበረ ኋላቀር አያያዝም ነው። ህሊና አደንዛዥ የዛቻ መዓት ብሔርአዊ ጎልማሳ-አጥነት በዝቶ በነፃ በእየቤቱ በመንቆርቆር እንደ ተደመጠ እና አስተጋባ፣ ብሔርአዊ-ቀውሱ – የተለመደ አስተዳደር ለውጥ ጀርባ እሚቀጣጠል የስልጣን ሽሚያ ውጊያ – እንደ ቀጠለ አለ።

በእርግጥ ህዋሃት አለምአቀፍ የውጊያ ደንብዎችን በመጣስ በከፍተኛ መጠን አስቸግሮ አለ። በፊትም በልእለብዙዎቹ የተጠላ አስተዳደርአዊ ህላዌ ነበረው። አሁንም ጥግ የአጣ የውጊያ፣ በቀል፣ ማበሳጨት፣ ወዘተ. ስልቱ የውጊያ እና ሰብእአዊ ህግዎችን በይፋ በወፍራሙ የጣሠ ነው።

ነገርግን፤ የማእከልአዊ መንግስት አስተዳደር ሀገርን እና ነገን በትክክል ወካይ በመሆኑ፣ ከሯጭ (fugitive) እና “አሸባሪነት” የታወጀ ድርጅት አቻ ዝቅጠት አይፈቀድለትም። በአቻ ውድቀት ሁለቱም ከታዩ ሁለቱም “አስተዳደርዎች” ከታሪክ እና ኃላፊነት እውነትዎች እኩል አይወገዙም። የቀደመው፣ በይፋ፣ ሀገር ወክሎ ሁሉበእጁ በደጁ ሆኖ፣ ደረጃን (of standard) እየሰራ እሚጓዝ በመሆኑ ይህ ውድቀትን አይጠብቁበትም፤ የክልል አስተዳደርዎን ጭምር። ይህ ፀያፍ እና ህገወጥ የንግግር መልክን ፈር እሚያስይዝ ከመጥፋቱ ባሻገር ከፍተኛ ቁርሾ (ከጦርነቱ ጎን እና በኋላ) የእሚያክል በመሆን ነገን የበለጠ ከውጊያው በላይ የእሚጎዳ ሆኖ እሚታይ መሆን አለበት። ነገ እንደ ዛሬው ንፁሕዎችን የአጋጭ አለ። ከኢላማው በላይ ግልአዊ ጠብ የነበረ የአክል ነገር ፈጥሮ የአኖር አለ።

እነእዚህን ቀለል እና አንገትበላይ መሰል እነውትዎችን ጥሶ በቀጣይአዊነት መንቀሳቀስ የሀገር ቋንቋ፣ ስነልቦና፣ ክብር፣ ማእረግ፣ ውበት፣ ህዎች፣ ስነስርአትዎች፣ ውህድአዊነትዎች፣ ተስፋዎች፣ ታሪክዎች፣ ሙያአዊነትዎች (ቢያንስ ህገደምብዎች (protocols))፣ ወዘተ. “ግብአተመሬት” ይከትት አሉ። በእዚህ አስተዳደር፣ ለአለፉት ሶስት አመትዎች እንደ ድንጋይ የበረታ መደበኛአዊነት (being regular) ርሀብ በመቀጠል ላይ ነው፤ ይህ የይፋአዊነት ተግበቦት መሀከል መደበኛ መስመርን መሳት ብቻ አንዱ መገለጫው ነው፨
By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s