Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ሀቀኛ ኢትዮጵያአዊነት ከ|ሀ|እስከ|ፐ| ትርጉምዎቹ፡ አንድ ቢጋር [The 26 Meanings of Actual Ethiopianism: an Outline]

The 26 meanings of being an Ethiopian.


Take this on PDF if you whim it.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 19th 2021GC.,


በቅንጭብጭብ ደረጃም ቢሆን ይህ ኢትዮጵያአዊነትን ለማሰስ የተተነተኑ ደራሲዎች ሉለ። ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፣ ይስማእከ ወርቁ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ በእውቀቱ ስዩም፣ በአሉ ግርማ፣ ጌታቸው ታደለ፣ ከበደ ሚካኤል፣ አብድልፈታህ አብደላ፤ ወዘተ. ናቸው።


፩) መተዋወቂያ

ኢትዮጵያ በዓለም በህዝብ ብዛቷ፣ በኋላቀርነቷ፣ በድሃድሃነቷ፣ በረዥም ታሪኳ፣ በነፃነቷ፣ በመካከለኛ ርቀት ሯጮቿ፣ በምስራቅአዊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት፣ ወዘተ. ታዋቂ ናት። ግን፣ ኢትዮጵያአዊነት (Being an Ethiopian) ምን ፍቺ(ዎች) አሉት? ከአኗኗሩ ገሀድ፣ ከታሪኩ ውርስ፣ ከጠቢው እድልዎች፣ ተጨምቆ ኢትዮጵያአዊነት ለጋራው እውነት ምንምን የእሚከትት እውነት ነው?
ገሀድን ለመሰብሰብ በመሞከር፣ ሙከራዎቹን በአጫጭር አንድመስመሬዎች ለመግለጥ የአክል በቢጋር መጠን ይህን መንደፍ ከተቻለ ለመሞከር እንሆ። ይህ መቶበመቶ ሙሉ ሠንጠረዥ አይደለም። ከሃያ ስድስት የግእዝ ሆሄዎች ዝርዝሩ በተጨማሪ፤ የቀረ(ሩ) የኢትዮጵያአዊነት ትርጉም(ዎች) ከአሉ ከአለቅድመሁኔታ የእሚታመን ነው።

፪) ተጨባጭ ናሙና ኢትዮጵያአዊነት ፍቺዎች በወፍበረር (ቢጋር) ደፈናዎች።

ሀ – የፖለቲካ አንዲት-ኢትዮጵያ አለመኖሯ ኢትዮጵያአዊነት ነው

ቢያንስ ከረዥም ዘመንዎች ጀምሮ ኢትዮጵያ በሀገር አስተዳደር ፖለቲካ እና ስልጣኑ ወጥነትአጥ ሀገር ነበረች። ከአስተዳደርአዊ ስልጣን ጀምሮ የመፈራረቅ ጉዳዩ ዛሬም በጎሣ እና ንዑስ ኋላቀር መመዘኛዎች እሚመሰረትበት ሀገር ናት። ዛሬ እንኳ፤ ህዋሃት ትግራይ ክልል እና ኢትዮጵያን በመምራት 27ዓመትዎች ቆይቶ፣ ስልጣኑን ሲቀማ፣ ክልሉን ለመገንጠል እንቅስቃሴ ጀምሮ ለአመት የአላባራ አሰቃቂ እና ጥንትቀር ውጊያ ነበር። የተካው ድርጅትም “የተረኛነት ፖለቲካ” በተሰኘ ጽንሰሃሳብ ሀገር እንድትታወቅ የፈቀደ ሆነ። ሁሉን የአስማማ አንድ አገዛዝ እንደ ተናፈቀ አለ። አንዳንዴ፣ እንደ ምንይልክ ካልእ የደሉ አሰባጥረው፣ መንግስትን አከፋፍለው ለማስተዳደር የጣሩ ይኖር አሉ። በደፈናው፣ ሀገር ተብሎ በሀገሩ እኩል የማስተዳደር ጉዳዩ የውሀሽታ የሆነ ጉዳይ ነው።
ለ – አንዲት-ኢትዮጵያ በአኗኗር አለመኖሩ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ሀገር ለህዝቡ የተሰናሰለ አንድነት የአለበት እውነት ነው። በኢትዮጵያ ቢያንስ ሁለት ዐብይ ኢትዮጵያአዊ ህዝብ አለ። አንዱ መሀከልሀገር (ከተማዎች) ነዋሪው ባይተዋር ህዝብ ነው። ሌላው ገጠሪቱ-ኢትዮጵያ እሚሰኘው ልእለብዙሃኑን እሚወክለው ገጠር ኢትዮጵያአዊ ነው። ፈጽሞ የተገለለ እና የተረሳ ህዝብ ሆኖ፣ ገጠሩ ሲገኝ፣ ከተሜውም በአልተመሰረተ ወጥነት ምክንያት የተዘበራረቀ ግድየለሽ መሀከልሀገሬ ሆኖ በደፈናው ኢትዮጵያን በሁለት በመሰንተር ለምእት አካባቢ ኢትዮጵያአዊነትን በአዲስ መንገድ የጀመረ ሆኖ አለ።
ሐ- ትላንት ቤቴ [ወይም ወል ንቃተህሊናየለሽነት] ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኑሮ በትዮጵያ ውስጥ በደፈናው በትላንት ውስጥ የተወተፈ ነው። በተለይ መሀከልሀገሬው፣ አኗኗሩ ወደ ነገ ለመግባት ይፈራ አለ። ገና ከመንጋቱ ዛሬው ሮጦ ወደ ትላንት የአፈገፍግበት አለ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ በዛሬም እንደ ትላንት መጽሐፍአቸው ይህን ለመግለጥ ሞክረው ነበር። ለውጥን መፍራት ኢትዮጵያአዊነት ነው፤ አዲስ ነገር ይፈራ አለ፤ እንደ ጻፉት። ሲደመደም፤ ህዝቡ በመሀከልሀገር አዲስ ስርአት፣ አስተሳሰብ፣ ወዘተ. ሲሞክር በወሬ ነካነካ የአደርጋት እና ወደ ለመዳት ትላንት ይወተፍ አለ። ለውጥን ገፍቶ አይደርስባት፤ ትላንቷን ፈንቅሎ አይጥላት፤ የትላንት ቤቴ እውነት የተስማማው ነው። ዝማኔ፣ ሀገርበቀልነት፣ ስልጣኔ፣ ነፃነት እና እኩልነት፣ ትምህርት፣ ስነምጣኔ፣ ወዘተ. እንዲአዘግም በእየጊዜው አቅም እና ገንዘብ (ህይወት ጭምር) ይሰዋ አለ። መሀከልሀገር ሀገር ግን ተመልሳ ወደ ትላንቷ ማፈግፈግ ልማዷ እና ስለእዚህ መገለጫዋ ማለትም ኢትዮጵያአዊነቷ ነው።
መ – አትጨናነቅ፣ ግን በምኞትህ እለቅ፣ ወይም ጥን የዋኅነት
ኢትዮጵያዎች፣ እንደ መገለጫ በአለመጨናነቅ የመኖር ፍላጎትን ለማስመር ሲሞክሩ ይታይ አሉ። ቢያንስ ከፍተኛው መሀከልሀገሬ ህዝብ ያንን አንፀባራቂ ነው። ሲአድግ አጭበርብሮ ወይም በአቋራጭ ወደ ፊት ለመድረስ ፈላጊ ነው። ሲማር ኮርጆ እና አጭበርብሮ ለማለፍ፣ ስራ እና ንግድም ቢሆን በውለታ ተሳስሮ ፊት ለመሆን ቋማጭ ነው። እከሌ የተሻለን ነው እሱ ይገባው አለ እኛ እንረጋጋ በመደበኛው መሀከልሀገሬ የለም። ገጠር ኢትዮጵያ ደግሞ የለየለት እጅግ ጥንትአዊ ህይወት በመሆኑ፣ በግብርና እና ንግድ ታግሎ አንዲት ማረፊያ በማዘጋጀት መኖር የህይወቱ ማብቂያ ነው። ከአንዲት ነገር መፈለጉ እና ኑሮውን ለማስደገፊያነት ማሰቡ በቀረ፣ ገጠር ኢትዮጵያ፣ ሁሉን የቀረውን ለአምላክ ትቶ መጨናነቅን አውግዞ ኗሪ ነው። በየዋኅነት የተሰራ ህዝብ ሆነ። መሀከልሀገሬ፤ በአገኘው መንገድ አንድ ስፍራ ደርሶ፣ በመደሰት መኖር ፈላጊ ነው። የዋኅነት ከመሆኑ የተነሳ እንደ ህዝብ ይህ አልተሳካለትም። ቁንጽል ጋርዮሽአማ (communal) ስኬት በድሬዳዋ ወይም ጨርቆስ ሊኖር ይችል አለ፤ ከመጨናነቅ የራቀ አኗኗርን በድህነቱ-መጋራት ለመኖር የመሞከሩ ነገር በእነዚህ አካባቢዎች አልፎአልፎ ይሰማ አሉ። በቀረ፣ በአትጨነቅ ፈሊጥ የረባ አረዳድ አልከተወነም። ከእዚህ የተነሳ፣ ብዙሀኑ አትጨነቅ ባይ ሆኖ የተሻለ ነገር እና ነገን ግን ቋማጭ ነው። መሀከልሀገሬ አትጨናነቅ እያለ ሲያጉተመትም በእየድንበሩ በስደት መሞት፣ በእየሀገሩ ለጉልበት ስራ መሰማራት፣ በድህነት መማቀቅን ማስቀጠል፣ እውን ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ሠ – ለሀገር ብቻ እሚነሳ አዘማኝ አስተሳሠብ፣ ርእዮት፣ ወዘተ. አለመኖር ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ከፍተኛ የለውጥም ሆነ አኗኗር እውነቱ ከሌላው ህዝብ የእሚጎተት ነው። ከረዥም አመትዎች ጀምሮ፣ ከውጭ ስርአትዎችን፣ ልማድን፣ እውቀትን፣ ወዘተ. ማስገባት የተለመደ ነው። ከውስጥ መንጪ ርእዮት፣ (እምብዛም) ለጆሮ እንኳ አይሰማም። (ሁሉን) ከሌላ ለማስገባት መሞከሩ፣ ኢትዮጵያአዊነት የአረጋገጠው አንድ መለያው ነው።
ረ – መሀከልሀገሬ ባህልየለሽ መሆኑ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ገጠር ኢትዮጵያ በእየጉራንጉሩ፣ ትንፍሽ-ሳይል፣ በጭምት ባህል ያም ብዙ ጊዜ ጥንትአዊነቱ የሰገገ ነው – ባህል የሰመጠ ነው። መሀከልሀገሬ የተመሰረተው በአንድ ምእት የአልሞላ ትትረት ነው። በተለይ ከድል በኋላ ከተሜነት እየተጀመረ፣ ሁለተኛ በተለይ ደግሞ በቻይና ተፅዕኖዎች ከተሜነት በግድየለሽ አያያዝ እየተከማቸ መጥቶ፣ ዛሬ በመደረሱ፣ የባህል ወረራም በመንግስት አስተዳደርዎች በመፈንገሉ፣ ወጥ አኗኗር ከገጠር አብሮ ወደ ከተማ አልገባም። ከተማም ለራሱ ወጥ ቀለም አላበጀም። ከተማ የተበታተነ የእየጎሳውን ባህል እሚሰኝ ልማድአዊ ተግባርዎች (traditional practices) እና እምነትአዊ ተግባርዎች እየቀነጫጨበ በእየፊናው በመኖር ላይ ነው። ወጥ ኢትዮጵያአዊ የባህል ቀለም የለም። ጉራማይሌነቱ ሀቅ ቢሆንም፣ በከተማ የገጠሩ ባህል ስለአልመጣ፣ የእራሱም ስለአልተመሰረተ፣ እንደ ደሴት ባህል አጥ የሆነ ህዝብ የአለበት ነው። በተለየ ደግሞ፣ ሀገር የአልፈጠረው የተለያዩ ቁሳቁስዎች እና ተያያዥ ዘይቤዎች በአለማቋረጥ ስለእሚገቡ ከተማ ሲገባ የገጠሩ ባህል ይሰለብ አለ። ከተሜነት ደግሞ ከውጭ በእሚገቡ ቁሳቁስዎች እና ተያያዥ ዘይቤዎች በመዥጎርጎር ወጥነትን የአልመሰረተ፣ የዘመንአዊው አለም ኋላቀር ባህል ሆኖ አለ። ወጥ ባህልየለሽነት ለመሀከልሀገር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ሰ – ግድድየለሽነት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
በገጠርም ሆነ መሀከልሀገር ኢትዮጵያ፤ ዓለም በስልጣኔ ስትገሰግስ የማየቱ ነገር አለ። አንዳንዴ ሰው በትጋት እና ብልሀቱ የጊዜን ጽንሰሃሳብ ልቡን ተረድቶ እና ስለእዚህ ተገልግሎት ተለውጦ ቢያዩም ያን መመልከት አፋሽአማነቱ (of its inspirational reality) ለመስራች ህዝቡ ግን ኦና ነው። የጀንከር አውሮፕላን ለመጀመሪያጊዜ በኢትዮጵያ ምድር እምትበርር አገልጋይ አውሮፕላን ሆና የተመለከታት ህዝብ፤ በመሰል ጉዳይዎች ለመሰልጠን ከመነሳሳት፣ አውሮፕላኗን ትክ ብሎ ተመልክቶ፤
“አያሳየኝ የለ ይሰሩትን ያጡ፤ ጠንቀቅ በል ጌታዬ ደሞ ወደ አንተ መጡ!” በማለት ገጥሞ ይጨዋወት ነበር። ጥቅሙ ምንድር ነው? በምን ተሰራ? እኛስ? ወዘተ. እሚለው ወሬ ከጎልማሳዎች አልመጣም። ሀገር በዘመነ መንገድ እንድትገባ የመጨነቁ ነገር በተግባር የለም። ነገው አስፈሪ እና አስጊ ነው፤ ዛሬው ሆኖ በተጨባጭ እንደ ተገኘው። ጃፓንዎች ከምእራብ የኮረጁት ስልጣኔ ግድ በመስጠት ነበር። ኢትዮጵያም በዘመነ ቀኃሥ. ብርቱ ጅማሮ ጠንስሳ ነበር። ዛሬ የአለው የሀገር ዝማኔ ቅርጽ የእዛ ዘመን ውርስ ነው። ምን ይዘን በአለም መድረክ እንቅረብ፤ ነገስ ምን ይውጠን እና ስፍራአችን የት ይሆን አለ፤ አለም ሲገሰግስ ልጅ እና ልጅልጅዎችአችንስ የት የደረሰ አለምን ከድህነትአችን አዋህደው ሊቀበሉን ነው፤ እኛስ ለውጥን ለምን አንቆረቁርም?? ወዘተ. አለመኖርአቸው፣ ብርቱ እና የሰላ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ቀ – ገሀድን ከተረዱ በኋላ ገዳቢ-ሰንባች ፍልስፍናን መከተል መርጦት መቀመጥ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
የቱም ማህበረሰብእ የእየራሱ ፍልስፍናአዊ መሰረትዎች አሉት። መነሻው፣ ምድር፣ ኑሮ፣ ገሀድ፣ ወዘተ. ምንድር ናቸው ብሎ መጠየቁ ነው። መልስዎቹን የታከከ ፍልስፍና ወይም ባህል ይመሰረት አለ። በኢትዮጵያ ደግሞ፣ የአለው ፍልስፍና፣ ኑሮ አዲስ ነገር የለውም፤ አትጨናነቅ፤ አለም ዘጠኝ ነው፤ ወዘተ. ነው። ገሀዱን የአየው ህዝብ፤ በህይወት እማየው አዲስ ነገር የለም መሰለኝ ብሎ መዋለድ፣ ተክቶ መሞት የቁምነገርሁሉ ጥግ ሆኖ አቁሞ አለ። ወግ እና ማእረግ ወልዶ፣ አሳድጎ፣ ድሮ፣ ዓይንበአይን አይቶ መሞት ነው። ይህ በመሰረቱ ሰብእአዊ፣ እንስሳአዊ፣ እፅዋትአዊ፣ ብቻ ለሁሉ የተቸረ ተፈጥሮአዊ ገሀድ ነው። ዓለምን ግዙ ለተባለው እና ብቸኛ ሀያሉ ፍጥረት ሰው ግን በቂ አይደለም። በእዛ መቅረት ግን ኢትዮጵያአዊነት ነው። አንዳንድ ድሀድሀ ሀገርዎችም ይሄ መገለጫአቸው ነው። ግን፤ ኢትዮጵያአዊነት በእዚህ ብቻ የእሚገኝ ነገር ነው የእሚሰኝ አይደለም። እዚህ የእሚገኝ አብይ እውነት ኢትዮጵያአዊነት ነው። በእዛ መሰረት፤ የኢትዮጵያ ሙሉው ህዝብ ተለቅ የአለ ሰው መሆንን (ማንነትን) የእሚመጥን ፍልስፍና የአላበጀ ነው። እጅግ ስንፍና የተጣባው እና ከጥንትአዊው ዘይቤ መንፏቀቅ የተሳነው ነው። ሺህ አመት አይኖርም፤ የልጅልጅ ግን ለእዛ ዘመን ሩቅ አይደለም፤ እንደ ብዙ ሀገርዎች ድንገት ህዝብ ጨራሽ መቅሰፍ ወይም አደጋ ቢገጥም ሀገርን ማስቀጠያ ህቡእ ስርአት መዘርጋት ባይቻል፤ የነገ ኢትዮጵያ ከዛሬዋ’ እንድትሻል የማድረጉ ነገር ከትቶ ለኢትዮጵያ ጎልማሳዎች አልታየአቸውም። በልጅነት በጨቀየ አስተዳደግ በቸልታ መምጣት፣ በትዳር በእየቀብሩ በመመላለስ መኖር የእዚህ ፍልስፍና ውጤት ሆኖ አለ። ልጅዎችን በነገ ባለመብትነት አይቶ በእሚቀበል፣ ሀገር ገንብቶ በእሚያሳልፍ ፍልስፍና መጠመድ አልተቻለም። ስርአትን ማቆም አይታቀድበትም። የአሉ ችግርዎች ቀላል መፍትሔዎችን ማግኘት እንደእሚችሉ በማወቅ እንኳ ጀርባ የጠና ግድየለሽነት በመኖሩ፣ የሰነፈ አኗኗር ሀገርን አዝቅጦ ለማስቀረት በቅቶ አለ።
ነገርን በአምላክ ለማላከክ ይህ ኢትዮጵያአዊ የኑሮ ፍልስፍና ይረዳ አለ። ሁሉን ለአምላክ ለመተው ይህ ፈሊጥ ሰበብ ይሆን አለ። በግድየለሽነት ከልደት ከአራስቤት ገንፎ፣ እስከ ሙት አመት መታሰቢያዎች በጠና መራር አውሬአዊ ክፍሉን ሰብእአዊነት እሚያክምበት ስርአት ተሰንቅሮ የቀረ ማህበረሰብእ በስፋት በመላ ሀገሪቱ ይታይ አለ። ሀገርን አልሚ ስርአት መፍጠር ሰማይ የተሰቀለ ይመስል የራቀ እውነት ሲሆን፣ በምትኩ ፍላጎትዎችን በመካድ የተነሳ ወደ መሰራተቅ ተገብቶ እሚኖርበት ሀገር ሆኖ አለ።
ገሀድን ሲረዱ፣ አለም ዘጠኝ ነው ለካ፤ አዲስ ነገር የለም ለካ፤ ወዘተ. ብሎ ከመሽመድመድ፣ ወደ ፎኮ አመለካከት መድረስ አልተቻለም። አውሮፓአዊው ፈላስፋ ግን፣ እሚያስደስተንን ፈልገን በመከተል ለመንበልበል እንድንጋበዝ ከገሀድ አሰሳው ጀርባ መክሮ አለ። ሀገር፤ ገሀድ ምን የከፋ ቢመስላት፣ ነገ አዲስ ሆኖ ይመጣ አለ፤ ታሪክ ይገኝ አለ፤ የገነባሁት ለእኔም ይደርስልኝ ለልጅዎቼም መንደርደሪያ ሆኖ የአስኮበኩብልኝ አለ አትልም። “እንደተኾነው” መሰንበት በቂ ፈሊጤ ነው ብላ፤ ለሰላም በመደዴ አረዳድ በማቀንቀን ሌላውን ነጣጥላ፣ ገንጥላ፣ ጥላ፣ ህዝብን ማበልጸግ በአለማቻሉ በተረጋገጠለት ዴንታየለሽ አንገትበላይ አኗኗር ዘይቤ መኖሯን ከቀጠለች፤ ይህችስ እሙን ኢትዮጵያአዊነት ነች።
በ – ለልጅዎች ምንም የተለየ ጭንቀት አለመገኘቱ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ልጅዎች የሀገር ወለል ናቸው። መሀከል ላይ ወጣት የሀገር ጫፍ ደግሞ አዛውንትዎች ናቸው። ያ በዘመንዎች ሲተካካ ይኖር አለ። ልጅዎች ወጣትከ ከእዛ አዛውንት ይሆን አለ። ይህን ርእዮት ግን፣ ኢትዮጵያአዊነት አያውቀውም። መደዴ የመቼት (space-time) አገነዛዘብ የሌለበት ሀገር በመሆኑ፤ ልጅዎች የተሽቀነጠሩ እድል አዳኝዎች ናቸው። እድልአቸውን የቀደመ ትውልድ አይከውንልአቸውም፤ አያ1ናልአቸውም። ለአስተዳደግአቸው መጨነቅ የለም፤ ለወደፊቱ ሀገር መጨነቅ የለም። የህግ፣ አኗኗር ስርአት፣ ወዘተ. ልጅዎችን ተንከባካቢነት የለም። እሚያድገው ሀገር ወራሽ አይመስልም። አቅሙን አጎልበቶ።፨፣ አንፆ፣ አበልጽጎ፣ በለመለመ አካሄድ ልጅን ማብቀል ፀረ-ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ሀገር በልጅዎች ላይ ትገነባ አለች። ኢትዮጵያ ልጅዎቿን በእድልአችሁ ኑሮ በእሚል ፈሊጥ ተጠምዳ አለች። በእድሉ እማያድግ ዛፍ እና ቁጫጭ እንኳ የለም። ሌላው የሰለጠነ አለምም በእድሉ እንጂ ልጁን በአዲስ እድል መግዛት እና ከፈጣሪ በመዋዋል አያሳድግም። ነገርግን፤ እንደ ነቃ ማህበረሰብእ የሰጠሁት ይመለስልኝ አለ በእሚል ለልጅዎቹ ነፃ እና የተመቻቸ አለም የአመቻች አለ። በምላሹ የበረታ ነገን እየአጠነከረ ነው። በግድየለሹ መናኛ አኗኗር ልጅዎችን በአለመጨነቅ እንደ እንሰሳ ከአዋቂ አብሮ እንደ አዋቂ በማሳደግ እየተታለለ እና በምላሹ ከሃዲ እና አስቀድሞ የከሰረ ትውልድ እየአበለጸገ ቢኖርም ጥቂት ለመሻሻል እማይዛነፍ ህዝብ ነው።
ተ – ቋንቋን አበልጽጎ ቢጀምሩም፣ አንደበትን አለማጥራት እና በቆሻሻ ተግባቦት ደረጃ የማጉረምረም ተግባቦት ላይ ተሰንቅሮ መቅረት እና ያንን ማባባስ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
በአፍሪቃ ብቸኛው በእራሱ የተፃፈ የእዚህ ዘመን ቋንቋ ግእዝ እና መሰል የሴም ቋንቋዎች አሉ። ይህ ታላቅ የጥንት ማእዶት፣ ዛሬ በቋንቋ ሙያ መስፈርትዎች የተዘረፈጠ ህዝብ የወረሰው እውነት ነው። አማርኛ ዋናው ቋንቋ ቢወሰድ፤ ዶክተር ምተወኩ ዑርጌሳ በየካቲት መጸፀሔት 1979ዓም. እትም ወይም በቀደመ የህዳር እትም ጀምሮ፣ ወይም በቀደመ ዘመን ሁሉ ማለት በእሚቻል ይስተካከል የተባለ እና ከእነችግርዎቹ ወዚህ የመጣ ቋንቋ ነው። የመሀከል ሀገር መግባቢያ በመሆኑ አፍመፍቻ ሳይሆን ከእየብሔረሰብእ ቋንቋ በመቀጠል ተምረውት እሚናገሩት በመሆኑ፣ ከገጠር ወደ ከተማ በአለመምጣቱ፣ አጻጻፍ ጉዳይዎቹ በኋላቀርነት በመጓዝአቸው፣ እንግሊዝኛ ስለቦረቦረው እና አመሊሽ ወደ መሆን በመቋቋሙ፣ የእነ ጋሽ ስብሃት በአማርኛኛ አይፃፍም ሃሳብን የአስቀየረ የ አደፍርስ ልብወለድ አማርኛ ጅማሮው በአለ ማደጉ፣ እና ዝሙን አማርኛ በአለመመስረቱከ የእውቀት ቋንቋ በአለመደረጉ፣ ወዘተ. ከፍተኛ የችግርዎች ትብትብ መፈናፈኛ የአሳጣው የድሀድሀ ቋንቋ እየሆነ የሄደ ቋንቋ ሆኖ አለ። መንግስትዎችም በፕሮፓጋንዳ አግጣጫዎችአቸው ብቻ እየነዱት ከፍተኛ ውድመት አድርሰውበት አለ። ሌላ ቋንቋዎችን ደግሞ ከእዚህ ዋናው መግባቢያ መውደቅ ተከትሎ ግልጥ ግምትን መስጠት የድሚቻል ነው። የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አቅም እንደ እሚቀጠሩት ከሆነ ከቅርብ የአለፈ ታሪክ አንፃር እንኳ የተንሸራተቱ ናቸው። ደማርኛ ፕሮጋንዳ ሲደመር መናኛ የእንደምን ዋልአችሁ አቅም እንጂ የአለምን ጥበብ መዳሰሻ ቋንቋ አይደለም። ግእዝ ታላቁን የጥበብ ቋንቋ እንኳ በስነተወ ዘመንም ቀዳሚነቱ መስካከል አልተቻለውም። አማርኛ የበሽተኛ አእምሮ ምልክት የሆነ ቋንቋ እንደ መሰለ በይፋ ይነገር አለ። የሰዋሰው ደንብ ጥሶ በመገናኛብዙሃንዎች ይውል አለ። አንድ ቀን ሙሉዋን ከአማርኛ ሰዋሰው መከበር ጋር በመገናኛብዙሃን ስታልፍ ማስተዋል አይቻልም ቢባል የእየለቱ ተጨባጭ ጥናት አለመኖር እንጂ ተሞክሮው ግን አለ። አረፍተነገርዎች የቁምአሽልብ አቅም የያዙ የአልዘመኑ ናናቸው። በእዚህ ጽሑፍ እንኳ የተሳሳተ አረፍተነገር አይጠፋም። ይሃ ተራ ስህተትዎችን በመዘንጋት በትልቁ ሚዛን ሲመዘን የእሚገጥመው ስህነተት ነው። በእዚህ ጥበበ ፍጥረት፣ ፍልስፍና፣ አንክሮትከ ወዘተ. አይገኝም። በሌላ ቋንቋዎችም መሰል ውድቀት ይይገመት አለ። ቋንቋን እማይገለገል ማህበረሰብእ ተብሎ በሰለጠኑት አለምዎች መነቀፉም አንዱ እውነት ነው። የሀገር አንደበትን በአልዘመነ እና እንደ አደፍርስ ልብወለድ እንኳ በጥበብ አለሙ ሁሉ መድገም አለመቻሉ፣ የባሰ የቋንቋ የአልጠራ ገሀድን በማሽቆልቆል ጉዞዎች ማካበቱ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኀ – የድሀድሀ አስጸያፊ ቅንጡነት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
እጅግ ብዙ ኢትዮጵያአዊ ስራ አጥ ነው። የህዝብ ብዛት እየናረ ነው። ዛሬም ግን፣ ሀገር መሰረትአዊ ቁሳቁስ ጨምሮ የእምትገለገለውን ቁሳቁስ እና አገልግሎት ሁሉ ማት ይቻል አለ ከውጭ ገዢ ናት። የረባ ሀገር ውስጥ ምርት እንክብካቤ ወይም ስራ ፈጠራ ትልምአግጣጫዎች (policies) የሉም፤ ተግባሩ ኦና ነው። እሚበላ እና የአናት ጣሪአ ለዜጋዎች በሌሉበት፣ ቅንጡ ነገርዎችን በውጭ ምንዛሬ መግዛት አለ። ኃይሌ ገብረስላሴ (ሻለቃ አትሌት) እንደ አለው ሰሊጥ ለውጭ ገበያ ሸጦ በምላሹ ዘይት ይሸምት የአለ ግራአጋቢ ህዝብ ነው። ሀገር ወደግ እሚለው ዝባዝንኬ ዝብዘባ፣ ተራ መሰረትዎችን ስቶት፣ በአየር ላይ ሀገር የሚገነባ የአክል፣ እንደ ህንድ-ኢትዮጵያአዊው በዓሉ ግግርማ “ኢትዮጵያ የእሚያስፈልጓት የጨቀዩ እጅዎች ነው” ከማለት ወደኋላ ተሽቀንጥሮ፣ ጭራሽ እጅ ለማቆሸሽ ሳይሆን በተሻለ ከአለም ለመሸመት እና ለመንፈላሰስ ፈላጊ ህዝብ አለ። ገብረህይወት ባይከዳኝ እንደ ተፀየፈው፣ ይህ እውቀት የማጣት ጉዳይ ነው፤ ቅጣቱም የሀገር ሀብትን ወጪ አድርጎ የውጭ ስራ እና ልፋትን መሸመት፣ ለመጪው ትውልድ ነው ያም በአነሰ የተፈጥሮ ሀብት በባዶ እድገት አለሙን እንዲቀላቀልበት እየተፈረደበት ነው። ቅንጡ እና የእማያመርት ህዝብ ነገውን ዛሬ በመስነፍ ባለእዳ እየአደረገው ነው። እነ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እንኳ የማህበረሰብእ ውል (social contract) ገና አላሰርንም፤ እነ መለስ ዜናአዊ ከመቶ አመት ወዲያ ኢትዮጵያ አልነበርንም፤ ወዘተ. በእሚሉበት ማለትም በግልጽ እንደ እሚታወቀው የሀገር በዘመነ መንገድ መመስረት ገና የወደፊት የቤት ስራ በሆነበት ሀገር፤ ስራዎቹን ሁሉ ለመጪው ትውልድ በመጠቅለል ከምሮ ማሳለፍ እውነት ሆኖ፣ ሀገር ግን በጸና የቅንጡ አኗኗር ሲራወጥ ማየት ፀሐይ የሞቀው ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ነ – ዜጋዎች ግልአዊ አኗኗር እና ጥራት የሉአቸውም ኢትዮጵያአዊነት ነው።
አንድ ኢትዮጵያአዊ መደበኛ ግለሰብእ፣ ከሌላው እሚለየው ምንም የለም ማለት ይቻል አለ። ጥቂት የካበተ ሀብት የአለው፣ ድሃው፣ ሰነፉ፣ ጎበዝ እሚሰኘው፣ ወዘተ. ብቻ እንደ ሀገር-ህዝብ፣ ሰዉ ተመሳሳይ ነው። ያ በመሰረትአዊ እንደ ሰው የመገኘት እውነት ነው። በሀገር እውነት ደግሞ፣ የአደባባይ እውነቱ የጠበቀ ሙያአዊነትከ ልዩአዋቂነት፣ ወዘተ. አያበረታታም እና ንቃተህሊናው፣ ሁሉንም እኩል አደፍጥጦ የአስቀረ በጽኑ የወረደ ነው። ስለእዚህ፣ ማንም የተደበቀ፣ የግልአዊ (individual) ህይወት የለውም ማለት የእሚቻል ነው። ማንም ለማንም ትንግርት አይሆንበትም፤ በጥቂት እና መናኛ መመዘኛዎች ከአልሆነ በቀረ። የተወሳሰበ አኗኗር የለም። አንዲት ከልጅነት በኋላ የመጣች ሀበሻ ጎብኚ፣ በ2007ዓም. ከኢትዮጵያዎች መግባባት የአንድ ቀን ስራ ነው። ማናቸውም አይለያዩም። ሰላምታ በቂ ነው፤ ከእነእርሱ መግባባት የእሚቻለውም በመሰረትአዊው የሰብይአወከነት ደረጃ ነው ብላ የፃፈችውን በበይነመረብ ማንበቤ ይታወሰኝ አለ። ትክክል ነበረች። ፈጽሞ። የተለያዩ ሰዎችን ማግኘት አይታሰብም። በጥራዝነጠቅ፣ መናኛ፣ ግድየለሽ፣ የአልተወሳሰበ፣ ሰነፍ፣ ወዘተ. አኗኗር፣ ረጋ እና ቅዝቅዝ፣ ብሎ እሚኖር ህዝብ የአላት ሀገር ናት። አንዱን ምሁር እእንኳ አንድ በል ቢሉት የተለመደው ምሁር ከሆነ አሰልቺ ተርታ ነገር ቢተፋ እንጂ የሰመጠ የተለየ ማንነት አይታይም። አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ወይም ዶክተር ዙምራ የተለዩ ለመሆን እሚጥሩ እና ምንአልባት የእራስአቸው የተለየ ምንመሆንን የአበጁ ወይም እየአበጁ የአሉ ናቸው ልንል እምንልአቸው ናቸው። በቀረ፤ እንደ ጳጉሜ ሰባት እንጂ የምንመለከትአቸው በተለየ ደረጃ ውስጥ ሰምጠው የእሚያስደምሙን ዜጋዎችን አንመለከትም። ሁሉም በጋራ ውድቀት አብሮ በመሃይምነት ሰምጦ የእሚገኝ ህዝብ ነው። በጋራ ዉዳቂ ህላዌ ኑባሬ እንጂ በዘመነ እና ስልጡን አኳኋን አለመገኘት ግንባርስጋ ኢትዮጵያአዊነት ነው። ይህ በእርግጥ በአሳፋሪ ሁኔታ በኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር የተመሰረተ እና የተንበለበለ እውነት ነው። በቀደሙ በተለይ በቀኃሥ. ድል መልስ ኢትዮጵያ ህላዌ በክብር፣ በማእረግ፣ በጋራ ንቃተህሊና ማዝገም-መጀመር እሚዘምን ህላዌ ጅማሮ ላይ ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በተጠቀሰው መጽሐፍአቸው አንድ ምእራፍ ኢትዮጵያአዊነት በእኔ ወጣትነት ዘመን ክብር ነበር፤ ኩራት ነበር፤ ዛሬ ኢትዮጵያአዊነት መሸጦነት (ለጥቅም የአለ ነገርን መስዋእት ማድረግ) ነው ብለው መዋረድ የበዛበት ትውልድ ብለውት አለ። ከያኒ ጌታቸው አብዲ ለመታሰቢያ ቀጸላ የእኔ ዘመን ቴአትር አንድ ህዝብ የፈጠረ ነበር አሁን ብትንተወኑ የወጣ ማንነት የበዛበት የተንኮታኮተ ሀገር ነው ብለዋት አለ። በደፈናው፤ ዘመኑ ከበፊቱ አባት ዘመኑ የተቆረጠ ነው፤ በተለይ በሌላ ምእራፍ “የትውልድ ቅብብሎሽ” በእሚለው እንደ ጻፉት። አንዱ፤ የእዚህ ትውልድ መገለጫው ይህ የግለሰብእ ቀለም አለመበልፀግ ነው። ግለሰብእ በጥንካሬ ማንነትን አይመሰርትም፤ አይወሳሰብም፤ አይከባበርም። ኑሮን በፀና የውድቀት ደረጃው ተረድቶ ሁሉም በሰነፈ ቅርርብ ተጠጋግቶ በአወቅሁሽ ናቅሁሽ ደንብ ሳይዋደድ ሳይከባበር፣ በአዲስ እሚማሩበት ሰው በእየመንደሩ ማብቅል ማጣት ለህዝብ እንደ ግለሰብእ ነጥሮ በመውጣት ለኑሮው እና ስልጣኔው ጭማሬ ከማበርከት ተፋትቶ በቸልታ የእሚገናኝበት ሆኖ አለ። ግልአዊ ብቃት በህላዌ የከሰመበት ህዝብ መሆን ኢትዮጵያአዊነት ነው።
አ – ዘመንአዊ ህይወት የለም፤ መሰረቱ አልተጣለም።
ዘመንአዊ ህይወት ገሀድን ሁሉ በሰው ቁጥጥር ውስጥ ይሰበስብ አለ። ከልጅ እስከ አዛውንቱ መጨጊያ እንዲአገኝ፣ ስደተኛ እንኳ ቢመጣ አብሮ በነፃነት እንዲኖር፣ ለችግር እና ለአልታወቀው ሁሉ እውቀት ፍለጋ እሚከወንበት፣ የህግ፣ እውቀት፣ ነፃነት፣ ወድሰጪነት፣ ወዘተ. አላባአዊዎች ዘመንአዊነትን ይመሰርቱ እና ተሳስረው በእሚፈጥሩት ጫወታ ብርቅርቅታን አጎምዥተው ይፈጥር አሉ። እንደ ቀደመው የጥንት ዘመን አለሙን ለማወቅ እና ለመቆጣጠር መመራመርን ንጉስዎች እንኳ በመከወን ይቆጣጠሩት እና ትልልቅ አለሙን ይገነቡት ነበር። አሁን መንግስት እእውቀትን በመገልገል ሀገርን አይገነባም። በመዝረፍ የደለውን ሀብት በመቀራመት የጠነከረ ወርሮበላ የእሚፈነጭበት ስርአት ነው። ማንም ግድ አይሰጠውም። ሀገር ማልማት ቀላል በሆነበት አብዛኛው አለም አብዛኛው ህዝብቡን በአጭር አመትዎች በእሚያለማበት እና በእሚያሻሽልበት ወቅት፣ መንግስትዎች ግን አስተዳዳሪዎችአቸው የሹመት እንጀራ አሳሽ፣ ከእየመንደሩ ለተሻለ ተስፋ በመነሳሳት እና በጎሣ በመመረጥ የድሚንጠላጠሉበት የማስተዳደርን አቅም እንጂ ሀገርን የእማያገለግሉበት ቢፈልጉም የድማይችሉበት እውነት የአለበት ነው።
ከ – የጋራ ማህበረሰብእአዊነት ወይም ጋርዮሽአዊ ህብረተሰብእነት አለመኖር ኢትዮጵያአዊነት ነው።
የቻይና ኢትዮጵያን በኢህአዴግ. አስተዳደር ግንባታዎች እና የመሰረተ ልማት አላባ የሆኑት አውታረልማትዎችን (infrastructures) የመገንባት እውነት ገሀድ ነው። ቀኃሥ. ከእዛ ደርግ፣ ከእዛ ቻይና በኢትዮጵያ ከተማነት ጉዞ የእሚጠየቁት ባለቤት ናቸው። በእዚህ ሂደት እውቅ የቻይናዎችን ግንባታ ካምፕ መስረቅ ወሬ በእየመንደሩ ይሰማ ነበር። ያንን ችለው፤ እሚሰሩት ትጉህዎቹ፣ የሰኩት የመንገድ ብረት ተዘርፎ ሲጠብቅአቸው፤ አንዱ “ቆይ ኢትዮጵያዎች ሌላ ሀገር አለአቸው?” ማለቱ በስፋት ትውፊት ይወራ ነበር።
እንደ አውራምባ ማህበረሰብእ በጋራ አስተሳሰብ መድመቅ እዚህ መገለጫ አይደለም። ተሰራርቆ መደሰት መርኅ ሆኖ በግልጥ የእሚሰበክበት ሀገር ነው። በእውቀቱ ስዩም እንኳ “…ሁሉ የሌሊት ወፍ ሲሆን…ጨለማህን ሸጠህ ብላ!” በማለት የበመመነታተፍ የመኖር ኢትዮጵያአዊነትን ተመልክቶ የአንተም አትስነፍ ተቧጨቅን ምክር አስምሮት አለ። የጋራ አንድ ንብረት አለን ብሎ የሀገር ሀብትን ለጋራ በፍትህ እና እኩልነት መገልገል ጸረ-ኢትዮጵያአዊነት ነው። መሰራረቅ እና ድንዛዜ ከመብዛቱ የተነሳ ይህ የቀወሰ ህዝብ ይመስል አለ። እቤቱ በር ላይ መንገድ አዳሪ እማይተኛበት ከተሜ እየቀነሰ እመመነመነ ነው። ሃላፊዎች ሀገር አያስተዳድሩም። ይዘርፍ አሉ፤ በህዝብ መርህ እና ቸልታ ይበረታታ አሉ።
ወ – ስልጣን የአምላክ ነው፤ ሰላም ለሰውልጅ ልኩ ናት መርሕ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኋላቀርነት ጥጉ እዚህስ አይታወቅም። ስልጣን የአምላክ ነው፤ ሹመት ከሰማይ ነው፤ ማንም ምንም አያገባውም እሚለው፣ መርኅ የህዝቡ ሁሉ ነው ለማለት ይዳዳ አለ። ሀገርን እሚያስተዳደርን ለፈቃዱ መተው በገጠር የተለመደ ቢሆንም፣ በከተማ ከቀኃሥ. ጀምሮ ደየበረታ ሄዶ በኢህአዴግ. ዛሬዛሬ ማንም ምንም ዴንታው እስከ አይሆን ድረስ ተደርሶ አለ።
ሰላምን ህዝቡ እንደ አንዳች ልዩ ነገር የአመልከው አለ። ከሰላም በላይ አይመለከትም። ሰላም ግን እጅግ መሬት ላይ የወደቀ የአኗኗር ስር እንጂ ፍፃሜ አይደለም። ፍትሕ፣ አርነት፣ እሪና፣ እና ብልጽግና ወዘተ. በዘመነ ማህበረሰብእ ከሰላም በላይ የእሚኬድብአቸው ዋልታዎች ናቸው። ፖለቲከኛዎች በቀላሉ ሰላምን በማደፍረስ እና በማስከበር፣ ኢትዮጵያን የማስተዳደር ስራን በቀላሉ እሚከውኑት፣ ህዝቡ የሰላም-ገዢ ሆኖ በመቅረቱ ነው። ሰላምን እሚወድደው ግግ እንደ ብልህ አይደለም። ሰላም ከአለፍትህ፣ ብልጽግና፣ እኩልነት፣ ህግበላይነት፣ ወዘተ. እፍዬገላ የአክል ጠንካራ ነው። ሰላም የቅጽበት እውነት ነው፤ የዛሬ የሰፈነ ሰላም ነገ አይደርስም። የረዘመ ሰላም፣ ብቻውን አይገኝም። በሀገር መሀከል ብልጽግና፣ ፍትህ፣ ወዘተ. ሲገኙ፣ ሰላም ቀጣይነት ይዞ መስፈኑ ገሀድ ነው። ሀገር ይህን ከትቶ አይቀበልም። መንግስትን ሰላም-ሻጭ እራሱን ሰላም-ገዢ አድርጎት አምባግነናም በማበልጸግ ቢጠመድ፣ እራሱም የእማይጸና እና ነገ የእማያገኝኙት ቢሆንም እንኳ ቢሆንም፣ ሰላምሻጭነት እና ገዢነት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ዐ – ጥራት የአለው የህይወት አገነዛዘብ ስለሌለ አኗኗር ጥራት አያውቅም።
በመናኛ አመጋገብ፣ በመናኛ ዳስ፣ በመናኛ መንገድዎች፣ በመናኛ አኗኗር ዘይቤዎች፣ ወዘተ. በቀፋፋ መንገድ መኖር መሰረተ ኢትዮጵያ ነው። የለውጥ፣ ዝማኔ፣ መሻሻል ጉዳይዎች ተገፍትረው አሉ። ሸማችነት ከሽሮ፣ ሽንኩርት እና ጤፍ (በመሀከል ሀገር እና ሰሜንአዊ ገጠር) አይዘልልም። በቀረው አብዛኛ ሀገር-ክፍሉ ፈጽሞ ለማለት የደረሰ ሸመታ የአለመኖር እውነት በሙሉ ታሪኩ አለ። ከልብስ፣ ጫማ፣ በዘለለ እምብዛም አይገዛም። ሀገር በደፈናው፣ ወደተሻሻለ ሽልፍኖትአዊ (technological) እና ቀላል አኗኗር መሆን የእሚችል ስልጣኔ ለማዝገም አይፈልግም። እጅ በማጣጠፍ፤ አለሙ ሲዘምን “ዋናው ሰላም እና ጤና፤ እናይአለን ብዙ ገና!” ብሎ ማቀንቀንን መድረስ እና አለመተቸት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ዘ – አለምአቀፍ ህይወት እማይታወቅ የሆነበት አኗኗር ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ከጥቂት ስፖርት ውድድርዎች በቀረ፣ ኢትዮጵያ ቅኝ የአልተገዛች ነች በቀረ፣ አለምአቀፉ ህይወት ለመደበኛው ኢትዮጵያአዊ ምንነቱ አይታወቀውም። አለምን በትጋት የማወቅ እድል የሀገር መንቃትን ይፈጥር አለ። ሀገርን የአስተባብር፣ የአነቃቃ፣ ልምድ ይሰርቅለት አለ። አለሙ እንዴት እንደ እሚገኝ ማወቅ ግን አይታሰብም። ሀገር ስለአለም እንዲያውቅ በነተበ ትምህርት ስርአት ጥቂት ከመሞከሩ በዘለለ ትርጉም የአለው ነገር ሲሞከር አይታይም። ጭራሽ ውጭ ሀገርዎች ሽንትቤት እየአጸዳ የኖረው ሁሉ እዚህ ዳያስፖራ በመሰኘት መጥቶ መኩራራተጀ ውጭው አለም ወርቅበወርቅ እና ተግቶ የእማያፈጋ በነፃ የእሚሰጥ እንዲመስል ለመደበኛው ህዝብ ተደርጎ አለ። ይህን በስደት እና መዘዙ ጭብጥ እና የማህበረሰብ ምክንያትአዊነት አለመኖር ልብወለዱ ሙሉጌታ አረግአዊ፣ ዲቪ ሎተሪ (ልብወለዱ ላይ ቀንጭቦ አስቀምጦት አለ)። ከአለም የተገጣጠመ ህላዌ በኢትዮጵያ መደበኛ አኗኗር አይታወቅም። የተማሩ እንኳን አለሙን እንዲአውቁ ቢጠበቅም፤ ገብረህይወት ባይከዳኝን እራሱ አውሮፓአዊ ብሎ “ዩትሮጲያን” ብሎ መሰየም የተለመደ ነው። ከሀገር አንፃር አለሙን መረዳት አለመቻል ኢትዮጵያአዊነት እውነቱ መሀከል የሰገገ ነው።
የ – ባዶክብ ብሔርአዊ ኩራት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
የከበደ ሚካኤል፤ “አለም የማንም ናት ጉልበተኛ የትም ሄዶ የአስገብር አለ!” እምትለው የተረትና ምሳሌ ግጥም ለኢትዮጵያዎች ተረስቶ አለ። አለምን አምላክ ፈጥሮት አለ። ሰውም ተበትኖባት አለ። በኢትዮጵያ ግዛት ሳይመርጡ መወለድ አለ። ያኔ፣ በተራ ኩራት መገኘት ነፈዝነት ነው። በመወለድ መኩራት እንስሳአዊነት ነው። መደበኛው የከተማ ኢትዮጵያአዊ አይነተኛ ስነልቦና በኢትዮጵያአዊነት መኩራት ነው። በአባትዎች ትግል፣ በድሮቀሩ የስልጣኔ ባለቤትነት ውርሱ መኩራት ነው።
(በፊደል ባለቤትነት፣ በታሪክ ርዝማኔ፣ በጥንቱ ዘመን ከፍታዎች፣ ወዘተ. ከፍተኛ ስሜት በብዙ መደበኛው ዜጋ አለ። ግን፣ ብዙዎች ይህ ዛሬ ተጠቅሶ የኩራት ምንጭ ሲሆን ስቀውበት አለ። ዌንዲ ቤልቸር፣ የኢትዮጵያ ታሪክም እንዲሁ እምትመራመረዋ፣ ስቃበት አለች። “አንድ ኢትዮጵያአዊ መናገር ሲጀምር ‘ከሶስት ሺህ አመትዎች ቀድሞ እኮ ታላቅ ነበርን’ ሳይል አፉን አይከፍትም… ያ ፈገግ የአስብል አለ” ነገር እንደ አለችው እሚቋጭ ነው። ኢትዮጵያአዊነት እጅአጨቅይቶ መስራት እና ሞላጫ ድህነት መታገያ መሆን ሲገባው በእማያውቁት እና ጠንቅቀው በእማይገነዘቡተወ የድሮቀር ውብ ስልጣኔ የሩቅ ወሬ እና ተራ የሀገር ፍቅር መንበላጠጥ ነው። የቅብብሎሽ ህፀፅ መጽሐፍ ደራሲ፣ አቶ ጌታቸው ታደለ በ2012ዓም. ማብቂያ በአፍሪ ትመ. ሰበዝ ዝግጅት ላይ ቀርበው፣ ስለመጽሐፍአቸው ሲአብራሩ፣ “እኔ ናይጄሪያ አምስት አመት ሰንብቼ አለሁ። ኢትዮጵያአዊ በሀገሩ አይኮራም! ናይጄሪያዎች በናይጄሪያ ሲኮሩ ይገርም እና ከእኛም የእሚሻል ሆኖ ይገኝ አለ! እኛም ወጣቱን በማቅረብ ከቀደመው ትውለድ እንዳይበጠስ እየተንከባከብንው ሀገር መገንባት አለብን!” ብለዋት ነበር። ምክንያትአዊ እና ዘመንአዊ አርበኝነት አለመኖር እና በባዶ ክብ ደረጃ ለማንም መሆን በአቃታት ድሀድሀ እና ጠሚ. አብይ አህመድ በተሾሙ ሰሞን “እንደ ለመድአችሁት ለምኜልአችሁ መጣሁ!” እንደ አሉት፣ በጠና ኋላቀርነት ውስጥ የሻጡዋት ሀገርን በተምኔትዮጵያ (በህልም ፍፁም ኢትዮጵያ አለችኝ እሚል ቁምሽልብ ወይም መደበኛ ኢትዮጵያአዊ እሚከተለው የሀገር አረዳድ ምስሉ ወይም ርእዮቱ ሲሆን በተለይ ምንም ትልቅ ሀገር ቢኖር እንኳ እንደ ቤልቸር አተያይ ዛሬው በአለመበልጸጉ አስቂኝ የሆነ ልፈፋ የእሚሆንበትን አግጣጫ አንጥሮ እሚያወፍር እቅድን የእሚፈጽም ቃል ነው፤) ተሸብቦ፣ ከመሻሻያ እቅድ ሳይገናኙ ብቻ በባዶ መኩራራት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ደ – እድሜአዊ መርነት በስልጣኔ ፍላጎቱ በአለመኖሩ ስልጣኔ እና ኢትዮጵያ መገጣጠም አልችል ሲሉ አሁንም ያንን አለማከም ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የመሰልጠን ህልም ልክ እንደ ህልም አለ። ግን ፍሬ ሰጥቶ አያውቅም። የእዚህ ውድቀት ዋናው አንድ መነሻው ሽማግሌ እና ጎልማሳዎች የስልጣኔው ጠንሳሽ መሆን በአለመቻልአቸው ነው። ፈጽሞ ወጣቱ ውጭ ተምሮ ወይም እዚህ ተምሮ ለውጥ ይፈጥር አለ ተብሎ የእሚጠበቀው ህልም እንጂ ሀገርን አዛውንት አስቦበት፣ አቅዶበት፣ አውጠንጥኖበት የአሰለጥነው አለ አይሰኝም። ያ የትትረቱ ወይም ህልሙ አከርካሪት እውነት ነው፤ ዳሩ የለም። አባት እና እናትዎች ሀገር አያሰለጥኑም፤ ሳይማሩ የአስተምር አሉ። የተማረው ሲወጣ አባትዎች እና እናትዎችቻ አያገኙትም። እንደ ልቡ፤ ልብ በአርባ ገንዘብ በሃያ እንደ አለው ደግ አቀንቃኝ አቤል፣ እራሱን መንከባከብ እእንኳ ሳያውቅ በቅንጦት እየተታለለ ሀገር ይዘነጋ አለ። እድሜው ሲገፋ ይደክም፣ ምቾት ይለምድ አለ እንጂ ሀገርን ማስቀደም አያልማትም፤ እንደ ደፈና ገሀድ አሰሳ። ይህን እነ ፕሮፌሰር መስፍንም ነካክተውነት አለ። ይህ ከእርስአቸው ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው። የእነ አደፍርስ፣ ከአድማስ ባሻገር ጭብጥዎች በዘመነ አለም ተምሮ በመመለስ ሀገርን የተለየች ሆና አግኝቶ መታረቅ አለመቻልን አስመልካች ነው። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያም እንደ አሉት፣ “እኛ ተምረን ተለውጠን እንደ ተላክንወወ ተመራምረን ስንመጣ ንጉሱ እና መኳንንትዎቹ ትላንትን አዝለው ጠበቁን!” እሚለው ይህን መሰንጠቅ በመሰንበቱ ሀገርአዊ መገለጫ መሆኑን የአስመለክት አለ። መሰልጠንን እሚያልሙት በልጅዎችአቸው እንጂ በእራስአቸው በኩል የአልሆኑ ጎልማሳዎች የአሉበት ህዝብ በመሆን የቆየ ሆኖ አለ። የቀረው አለም መሀከል የሰለጠኑ ሀገርዎች ስልጣኔን ከላይ ጀምረው ነበር። በአውሮፓ ለምሳሌ ታላላቅ እናት እና አባት የሆኑ ጎልማሳዎች በምርምር እና የእውቀት ትግል ሀገር እየመሩ ህዝቡ በእውቀት እና በተበጀለት ስርአት ከስር ጀምሮ እየተኮተኮተ ማደግን አሳክቶ አለ። ማደግን ከሌላ ስለአልኮረጁት ልጅዎችአችን የአሳድጉን አለ እሚል መርኅ አልተፈጠረም። ልጅ የጎልማሳዎቹ መስታወት ነው። ቀድሞ በኤሲያም መንግስት ትልልቅዎቹን ዜጋዎች እየለወጠ ሀገርን አዘምኖ በአዲስ ባህሉ ጠቢውን ትውልድ እየመራ ተቀበለው እንጂ ልጅዎቼ ሲአድጉ ሀገር የአሳድግ አሉ አልተባለም። በኢትዮጵያም ይህ ሙከራ ተሞክሮ ፈርቀድዶም ነበር። ጎልማሳዎች ትልልቅ የእውቀት እና ጥበብ ስራዎችን ለመስራት ይሞክሩ ዘንድ በቀኃሥ. ተደርገው ነበር። ልጅዎችም ሀገር የአሳድግ አሉ ሲባል በከፍተኛ ትኩረት እና ጥራት እንዲአልፉ በማድረግ ዛሬ ድረስ የአልተተኩ ትውልድዎችን መፍጠር ተችሎ ነበር። እድሜ የገፉ ፀሐፊዎች፣ ባለሙያዎች፣ ወዘተ. ለሀገር ዝማኔው ከፍተኛ ትንቅንቅ ይከውኑ ነበር። ከስከስር በልዩ ትኩረት የአደገው ትውልድ ግን ሀገሩን ከማሻሻል ንጉሱን ከድቶ ነገርን አበለሻሽቶ ከእዚህ የከፋ ውድቅ ዘመን አድርሶ አለ። በእርግጥ የተነሳበት እሳቤቤ ያ ትውልድ ድንቅ፣ በአፍሪቃም አቻ የአልበለጸገለት ታላቅ ነበር። ግን፣ ተጠልፎ፣
ገ – ዘመንአዊውን አለምን ለመቀላቀል አለማቀድ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ኢትዮጵያ አለም ሲዘምን ተመልክታ አለች። እራሷ በድሮቀሩ ስልጣኔ አንድአች ከፍታ ላይ ደርሳ ነበረች። አሁን ያ የኋሊት በመጓዝ ተቀይሮ ከዘመንአዊ ተጨባጭ ሰፊ የቀኃሥ. ለውጥ በኋላ ማፈግፈጉን ተያይዛ ዛሬ የለየለት ማፈግፈግ ወርሷት አለ። ከሽልፍኖት (technology) በመርከሱ የተነሳ ወደ ሀገር በተፈጥሮሀብት ሽያጭ ምትክ እየፈሰሰ ቢገኝም፤ በአለም መሰልጠን የተነሳ በትምህርት እና ሉልአዊ ስነስርአትዎች ጫና የነተሳ አኗኗር መሰረቱ ጥቂት ቢለወጥም (ለምሳሌ የሴት ግርዛት ቀንሶ አለ)፣ ሀገር ግን፣ የኋሊት እየሄደች ነው። ከንጉሡ እና ደርግ እንኳ የባሰ የኋሊት ጉዞ በርህራሄየለሽ ሉልአዊ አምራችአለም የተነሳ ኢትዮጵያ በወደኋላ ጉዞ በርትታ አለች። አንድ የኦሮሞ ተኮር ፖለቲከኛ በአንድ ትመ. ቀርበው ከኢህአዴግ. ህገመንግስትአዊነት የንጉሡ የተሻሻለው ህገመንግስት እጅግ ተሻለ እና በልጦ የተተገበረ ነበር ብለው ነበር።
አለም ሲዘምን ሀገር ጭራሽ ወደኋላ በመጓዝ ተጠምዳ አለች። በእርስበእርስ ግጭትዎች እና ሌባ ስርአት የመለወጥ ተስፋ የመነመነ እየሆነ ነው። አለም የበለጠ ስትመጥቅ የእሚቀጥለው ጠቢ የበለጠ ከፊ እንደ እሚሆን ይገመት አለ።
ሁሉ የሀገር ላሳድግ ፍላጎት ውሸት መሆኑ እሚታወቀው – በአስተዳደር መንግስትዎች ላይ – ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ለዌንዲ ቤልቸር በአዲስአበባ ጉብኝቷ በ1992ዓም. እንደ ነገሯት፤ የአለም እድገት መሰረት ኢትዮጵያ እና ጥቁር-ምስር ሀገር ናት፤ ብለው፤ ዛሬ ኋላ የቀረችው ስልጣኔዋን ወደ ሽልፍኖት (technology) አለሙ ማምጣት ስለአቃታት ነው እሚል እንደምታ ነግረዋት ነበር። አሁንም፤ ሀገር፣ ፈጽማ ወደ ስልጣኔ ማማ ለመዳሕ እንዳትችል የሀገርበቀል እና የሀገር እውቀት መሰረት የአለበት ሽልፍኖትአዊ (technological) ሽግግር አይከወንም። ያ ከሆነ፣ የሎሬት አስተሳሰቡን እንኳ የአልተደረሰበት መርኅ ሀገርን እሚያሸጋግረው እንዴት ሆኖ ነው? ከእነከበደ ሚካኤል የጃፓን መሰልጠን ኩረጃ እቅድ ጀምሮ፣ እስከ አሁን፣ መዛግ እንጂ ለመሰልጠን መሞከሩ እየባሰ በሄደ ወደኋላጉዞ የተነሳ አልተመሰረተም። አለሙ በስልጣኔ ሲንቀለቀል ለመቀላቀል አለማቀድ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ጠ – እንኳን ለእሚያመልጠኝ ለ ነገም ግድየለኝ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
እስከአሁን በእድሜ ዘመንአቸው ኢትዮጵያዎች የተመለከቱት ድህነት ነው። ኩሩ ህዝብ እንደ አልነበሩ ድህነት በእማያውቁት የተጋ አለም መሀከል ባሪያ እና ውጭ ሀገርን ናፋቂ አድርጎአቸው አለ። ግን ልምድአቸው ዋጋው ዜሮ ነው። አሁንስ ይህ ይስተካከል አይሉም። መስዋእት ከፍለውም እንደ የቱም ወይም ልእለአብዛኛው ሀገር በመስዋእት አዲስ አለምን ማቆም አይፈልጉም፤ አይመኙም።
የሽማግሌነት ወይም ጎልማሳአጥነት ማህበረሰብእ የተራበው እውነት እንዲሆን ይኼ የፈጠረው ነገር ነው። የልምድ ዋጋ እማይቆጠርበት ሀገር በመሆኑ፣ ህዝብ የአረጁ እና የአገለገሉ አባት እና እናትዎቹን ታሪክ እና ትርክት እንኳ ለመፃፍ፣ መሳል፣ መዝፈን፣ ብቻ መሰደር እና ለቀጣይ ትውልድ መማሪያነት ማንጠልጠል አለመቻሉ አለ። የቀደመው ትውልድ ምን እንደ ሰራ በቅጡ ለማወቅ አይቻልም፤ እንደ ህዝብ ይህ የእማይታይ ጉድለት በመሆኑ። ነገው ጨለማ ነው። ተስፋው የመነመነ ነው። ኢትዮጵያ 230ሚሊየን ዜጋዎችን በ2035ዓም. ስትይዝ “ያኔ እግዜር ይሁነን!” የአሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ለነገውም መነሳሳት በአለመኖሩ ነው። ለነገው፣ ነገ የአስብለት አለ፣ የድሀ ኢትዮጵያ መርኅ ነው። ያንን ቁጫጭም ታውቅ ዘንድ አለች። ለነገው ግን እንደ ግል ቢደከም እንደ ሀገር አንዳንዱ እንኳ አሳቢ ጉዳይዎችን መነካካት የለም። ነገን ለማበልጸግ ዛሬን መገንባት ግድ ሆኖ ሳለ የአመለጠ እና እየአለፈ የአለ ብዙ ወርቅ እድል ሳለ፤ በአለመጨነቅ ነገንም ዛሬ ገና አጨልሞ መቀበል፤ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ጰ – አብሮ አለመኖር ወይም በሩቅ እንኑር ፍልስፍና ኢትዮጵያአዊ ነው።
ኢትዮጵያ ለመሰልጠን የመጀመሪያ እርምጃዋ የባህል ለውጥ ነው። ባህል መጨረሻው ምሰሶዎቹ ደግሞ፣ ሰውን እንደ ማህበረሰብእ ጠፍንጎ የማሰር አቅሙ መገለጡ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፈጽሞ በባህል ዘመንአዊ በአለመፈጠሩ፣ የተጠባበቀ ስነልቦና የለውም። አንድነት ቀድሞ በወልነት ስነልቦና ይበለጽግ እና ወደ ሌላ መገለጫዎቹ በመፍሰስ ነው አንድነት ሆኖ እሚገኘው። በቀለለ ቋንቋ ለመጠቅለል፣ አንድነት መሰረቱ፣ የስነልቦና አንድ ሆኖ መገኘት ነው።
የትዮጵያ ህዝብ ስስነልቦናአዊ አንድነቱ በከፋ ዘመንዎች ርዝመት ተራርቆ እሚገኝ ነው። እግርኳስ ከተገኘ፣ ሩጫ በኦሊምፒክ ወቅትዎች ላይ ሲመጣ፣ ታሪክአዊ ጉዳይ ለምሳሌ አባይ ይገደብ ሲባል፣ ወዘተ. አንድ ሆኖ ሀገሬ፣ ሀገሬ እሚል ህዝብ ነው። በተረፈ፣ አንድ ስነልቦናአዊ ገመድ በእለትከለቱ እንቅስቃሴ በሀፖ (ከመጀመሪያ እስከፍፃሜ) ህይወቱ ሁሉ የለውም። ይህ ማለት የህዝብ በሀገሩ እና በኑሮው ሁሉ ተሳትፎ ደካማ ነው ማለት ሊሆን ይችል አለ። ወይም፤ በኢትዮጵያ ከሩጫ እና ወሳኝ ብሔርአዊ አንዳንድ ጉዳይዎች በቀረ ህብረትአዊነት የለም ማለት ነው። ማለትም፤ ሰው ሰርጎ በግል አኗኗሩ ይጠመድ አለ ማለት ነው። ያም ውሎ ማደር እንጂ አምራች ወእም ተንበልባይ ህይወት አይደለም። ለመሻሻል እሚኳትኑበት እና ፋታ የእሚያጡበት አይደለም። ሀገር እሚዋረድበት ምስጢር አንድ ቅጥያ ወይም መነሻ የሆነው የአገኙትን ተቀራምቶ ወደ ቤት ገብቶ እንደ አቅም በእሚል መርኅ ሰንፎ ውሎ ማንተወ በንጋታው ያንንው መድገም፣ እስከ ልጅልጅ ስርአቱ ያ እንዲሆን ማድረግ ኢትዮጵያአዊነት ነው። በአጭሩ፤ የይስማአደከ ወርቁ።፨፤ ልናነጋ ተኛን (የወንድ ምጥ መደብል ላይ ግጥም ኢትዮጵያአዊነት በቀንመቁጠሪያ መሰረት እስኪነጋ መተኛት ነው ብሎት አለ)። እውነትም፤ በህብረት ወጥቶ የማለምለም እውነት የለም። የራቀ፣ ሰነፍ እና የእማይተነባበር፣ የእማይገነባ፣ እሳትም አበባም አልሆንም ብሎ የእማይፈነዳ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አገላለጥ አጉል ጨዋነት ኢትዮጵያአዊነት ነው። (ፕሮፌሰሩ እስከመቼ? ብለውት አለ)።
ጸ – ኢትዮጵያአዊነት ለችግር መፍትሔ የሆነው አንድ እርከኑ ብቻ (ወይም ቁጫጭአዊ) ርእዮት መብዛት እና መደበኛ ሆኖ መገኘት ነው።
አንድ እርምጃ ላይ ብቻ ማተኮር እሙን ኢትዮጵያአዊነት ነው። ቁጫጭ፣ በእጅ ቢያነሷት መዳፍን ዝምብላ ስትሽከረከር ትውል አለች። ኢትዮጵያአዊው መሀከልሀገሬ በአለፉት ሰላሳ አመትዎች፣ አንድ ችግር ሲገጥመው ለእዛ እንደጮኸ እና ያቺን ማከም የመጨረሻ ጉዳዩ እንደሆነው አለ። የረዘመ ቅኝት፣ አስተሳሰብ፣ ከምንም በላይ እንቅስቃሴ አያጋጥምም። ፍቱን መላ (panacea) ከመመልከት ወደ አሁኗ አንገብጋቢ ጉዳይ ሁሉም አቅሙን እንደበተነ ነው። ይህ የትል አመለካከት ነው። ንጉሡን ከመገርሰስ ጀምሮ፣ በፖለቲካውም ቢሆን ርቆ አይቶ አሁን ወይም ቀድሞ እሚመሰረተው ይታቀድ የአለ ህዝብ አይደለም። የአስቸገረው ከተወገደ በቂው ሆኖ የተገኘ ህዝብ ነው። ደጋግሞ መንግስት አስተዳደርዎችን መገልበጥ የእሚከውነውም ለእዚህ ነው። አሁን የቸገረውን ከፈታታ የአለም መጨረሻው ይመስለው አለ። ሀገርን በስርነቀል አመለካከት ከመመልከት ክሽፈቱ የግል አኗኗሩንም በአንክሮት (critically) የመመልከት አቅሙ ኦና የሆነበት የተደናበረ ህዝብ ሆኖ አለ። የሩቁን አስቀድሞ የእማያይ አንዳንድ እንስሳ ብቻ ነው። ብዙ እንሰሳዎች በረዥሙ አይተው እስከ ልጅልጅ ለእሚሆነው ኑሮ በመተባበር እንደ ጉንዳን የደሉት በተለየ፣ እሚኖሩ ናቸው። ኢትዮጵያአዊነት እንደ ህዝብ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንደ ገለጡት የልጅዎቼ ሀገር ብሎ እሚኖርበት የአኗኗር ተጨባጭ እና አንኳር እውነት የለውም። ችግር ከአለ፤ ለመፍታት እንጂ የችግሩን ምንጭ አይቶ አንዴ ለማድረቅ አለመሞከር ሀገርን እና ተስፋዋን ከአሾራት ያ ኢትዮጵያአዊነት መገለጫው የአልተቋረጠ እውነቱ ነው።
ፀ – የእድሜ መሰላል ቢኖርም የእድሜ እርከን (ማለትም ትስስር) ገላጭ አኗኗር በቅጡ አለመገኘት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
የገ ስርአት ላይ የእድሜ እርከን ምን የንጽውሳኔ (democracy) ፀር ቢሆን ውብ ገጽታዎችም አሉት። እድሜ እየአዘገመ በተለያዩ ደረጃዎች እንዲኖር ይጠበቅበት አለ። በኢትዮጵያ መሀከል ሀገርም ሆነ ገጠር ግ የበሰለ የእድሜ ክፍፍል የለም። የማህበረሰብእ መላላት የተከሰተው አንድም በእዚህ ለ ማህበረሰብእአዊ እውነት መቀደድ ነው። ልጅ መሆን የእድል ፍለጋ ጨዋታ ቤተሰብእ ማገዣ ተማሪቤት ከተቻለ መሯሯጫ ዘመን፣ ወጣትነት ከአድማስ ባሻገር እንደ ገለጠው፣ ከቤተሰብ ትከሻ ወደ መንገስት ትከሻ ለቀረው እድሜ መሸጋገሪያ ዘመን እርጅና እና ጎልማሳነት የቀብር እና ሰርግ ዝግጅትዎች አደና መከወኛ ዘመን ነው። አትራፊ የእድሜ ሰንሰለት ወይም መሰላል አንድ ማህበረሰብእን አሰናስሎ አልመሰረተም። ልጅዎች በማወቅ፣ መትጋት፣ አዋቂ በማድመጥ፣ ታሪክ እና እውቀት በመሸመት፣ ፕሮፌሰር መስፍን በተጠቀሰ መጽሐፍአቸው ስለ ትምህርት ስርአት ሲከራከሩ በጻፉት መሰረት ድሀድሀ ሀገር ተኮኖም ችግርዎችን አጥንቶ ለማከም በመማር ሂደት አያድጉም። ወጣት እና ጎልማሳ የአዋቂ ትውልዱ አካል እና ብብትስር ሆኖ እያገለገለው አይኖርም። አዋቂው የተገለለበት ምክንያት ከስልጣኔ መፍጠን እና ሀገርን እየተቀነጫጨበ መጥቶ የመውረር እውነት የተነሳ እየበዛ ሄዶ አለ። የተገለለ አዋቂ እና ሽሽማግሌ በመኖሩ ወጣቱ የሀገር እንቅስቃሴው በተለይ ማህበረሰብእን በተመለከተ ፊትወራሪ ሆኖ እንዲንቀዋለል አመቻችቶለት አለ። ልምድ በመጥፋቱ የተነሳ፣ ፕሮፌሰሩ እንደ አሉት፣ ወጣቱ ተምሮ ሲአበቃ በአንድም በሌላም ምክንያት ሀገር ህዝቡን ይጠላ ውጭ ናፋቂ ይሆን አለ። የትውልልድ ቅብብሎሽ ከእዚህ የተነሳ የለም ብለው አለ። ከፊው ነገር እየላላ የሄደው የትውልድዎች መሰበጣጠር ነው። እድሜ በእርከኑ ዋጋ እና ከፊል ይፋ ገጽታ ይዞ፣ ከስነስርአትአዊነት በዘለለ በይዘትም (beyond being procedural also in substance) መስተካከል እና አዋቂዎች ወጣትን እየመሩ ልጅዎችን እያሳደጉ ለሀገር በተለይ ማህበረሰብእአዊነተ ወጥ እውነት መፍጠር አለመቻል ላይ ሆነው፤ ከኩርማን ምእት በላይ እድሜ እርከንአዊ ትስስር በወጥ መንገድ አለመፍጠር እና ተበጣጥሶ በመገኘት መቀጠል ኢትዮጵያአዊነት በገሀድ የእሚነግረው አቻው ነው።
ፈ – ኢትዮጵያአዊነት ህዝብ ጉራማይሌ ሆኖ ተዘርዝሮ እንኳ ግን የአለማለቅ፣ ከምንም በላይ ወደ ስንስል ወይም ስብጥርነት የአለመምጣት ቸልተኛነት ነው።
ጉራማይሌ ከእየአይነቱ ሆኖ መሰብሰብ ማለት ነው። ስብጥር ማለት ግን፣ ከመለያየት ቀጥሎ አንድ መሆን በመቻል፣ የተጣጣመ ውህደትን መፍጠር ማለት ነው። የተዘበራረቀነት እና የተሰናሰለ ዝብርቅርቅነት እንደማለት ናቸው፣ እንደ ቅደም ተከተልአቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ከሀመር ጨቅላ እና ሀመር እናት አያትዎች፣ ከአፋር ወንድ ወጣት እና ወንድ ሽማግሌ አያት፣ ከፃግብጂ ታዳጊ ሴት ልጅ፣ ከቀብሪደሃር የአርባ አመት እመቤት፣ ከአሰንዳቦ ሽማግሌ ወንድ አያት፣ ከቦዲቲ እና ሀይቅ ታዳጊ ወንድ ወጣትዎች፣ ከጨርቆስ ወጣትዎች እስከ ጎሬ አዛውንትዎች፣ ወ…ዘ…ተ…፤ አንድ አድርጎ ወይም የሀገር የአክል አቀራርቦ ወይም በመቀራረብ እና በእድሜአቸው መጠን የተለካ የአኗኗር መስተጋብር ተይዞ፣ አንድ ኢትዮጵያአዊ የሆነ አኗኗር አሉአቸውን? ቢለያዩስ የእነእዚህ እና ብዙዎቹ ጉራማይሌ ህዝብ አላባአዊዎች ይተዋወቅ አሉን? ምንም አዎንታአዊነት በመልሱ ቢኖር፣ ሀሰት ነው። ኢትዮጵያአዊ ኢትዮጵያአዊን አያውቀውም። የኢብሳ ጉተማ ግጥምን ለመድገም ወይም የእነ በእውቀቱ ስዩም የተረሳች ገጠር ሴት ወይም የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን ማነህ ባክህ? ግጥምን ወዘተ. ለመድገም አይደለም። እነእዛ ቁንጽል ናቸው። መሀከል ሀገሬ መሀከል ሀገሬን እንኳ አያውቀውም። ገና የአልተሰናሰለ ጉራማይሌነት ኢትዮጵያአዊነት ነው። በወልንቃተህሊና የአልተሰበጣጠረ እና የአልተጋመደ እምቅ (potential) ኢትዮጥለትአዊነት (ኢትዮጥለትአዊነት ዶር. አብድልፈታህ አብደላህ የኢሳት. ትመ. ጥለት ኢትዮጵያ አዘጋጅ “እኛ ኢትዮጵያአዊያን ልክ እንደ ጥለት የተሰባጠርን የተጋመድን ነን” ብሎ ከእሚገልፀው ሃሳብ ተነስቶ ለማደግ የእሚሞክር ጽንሰሃሳብ ሲሆን፤ በጉራማይሌ ገሀድ ሲገኙ ተሰናስሎ በልዩነት ውስጥ የመለምለም እና የመጽደቅ እውነትን አስመልካች እንዲሆን የእሚታሰብ ነው) እንጂ ሀቀኛ ወይም የተተገበረ ኢትዮጥለትነት የለም። የተለያዩ ጋርዮሽዎች (communities) አንድ ሆነው ኖረው አያውቁም፤ ገና አይተዋወቁም እና። በሰለጠነ የትምህርት እና ጥናት፣ መዝናኛ እና ስብጥር ትልምአግጣጫዎች (policies)፣ የእሚንተከተክ ዘይቤ እና ዝማኔ የለም። በእየተራራቁበት ሳይተዋወቁ እንኳ ዳገት አኗኗርን መግፋት የተለመደ እውነት ነው። በመለያየት አንድ ድንበር ተጋርቶ ተራርቆ በአለመተዋወቅ እና በአለመተባበር፣ ተራርቆ ሲኖር፣ ጉዳቱ ቢበዛም፣ ሀገርን ከጉራማይሌነት ወደ ጉራማይሌ መገማመድ ማምጣት አለመቻል እና ይብስ እየተራራቁ መሄድ ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ፐ – ለነገር ሁሉ ድንዛዜ እና ነፈዝነት ኢትዮጵያአዊነት ነው።
ምንም ቢፈጠር ከትቶ የአልሰሙ፣ የአላዩ፣ የአላሸተቱ የአክል፣ ዝምታ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሆኖ አለ። ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማሪያም፣ በ ዛሬም እንደ ትላንት? ላይ፣ የደርግ እና ቀኃሥ. አስተዳደርዎች ዘመን ላይ የነበሩትን ዘግናኝ ድንዛዜዎች ኮንነውት አለ። ብዙዎችን ህዝብ አስገድሎ በማጨብጨብ አሳልፎ አለ በማለት ተናድደውበት አለ። የኢህአዴግ. መግባት ሰሞንም ንጽውሳኔ (democracy) አኮብኩቦ፣ ብዙ ሲፃፍ አንባቢ ጠፍቶ ስለነበር፣ ቸልተኛ ህዝብ ነው፤ ብለው ኮንነውት ነበር። ገብረህይወት ባይከዳኝም፣ በመንግስት እና የህዝብ አተዳደር፣ ዋና አንድ የአባባው የህዝቡ ከቶ ዴንታየለሽ ማንነት መሰል ገጸባህሪው ነበር። ይህ ድንዛዜ ለወደፊቱ ጎጂ ነው፤ ዛሬ የተፈጥሮ ሀብቱን ተቀምጦ በመሸጥ ነገ ለመጪው ትውልድ እዳ የአወርስ አለ ብሎ አስጠንቅቆት አለ። እንደ አየንው ይህ ግድየለሽነት በቅንጦት እየተደገፈ፣ ሀገር ተፈጥሮ ሀብቷን በመሸጥ ዘመንአዊ ቁሳቁስዎች በምትኩ በመሸመት ለጠቢዋ በእዳ ማውረስ አግጣጫው ቸልታዋን በመቸር ላይ ናት። ከሰው(ዎች) በገሀድ መገደል፣ ከፍትህማጣት፣ መጭበርበር፣ ወዘተ. የተፈጠረ አዲስ ነገር የሌለ ይመስል፣ በቁምአሸልብ አኗኗር መቀጠል ኢትዮጵያአዊነት ነው። የዘመንአዊ ሀገር፣ አብርኆት የለወጠው ህዝብ፣ ዋና መገለጫው አንተ እኔ እኔ አንተ በእሚለው መርኅ መኖር ነው። በሰብእአዊነት ድርድርን ማጥፋት፣ በእኩልነት እና ነፃነት አለመደራደር ናቸው። የፈረንሳይ አብዮትም ሆነ የዘመነው አብዛኛው አለም፣ የሰለጠነው በመጀመሪያ በእነ አሌክሳንድር ዱማስ አንዱ ለሁሉ ሁሉ ለአንዱ መርኅ ነው። ህዝብ በጋራ አንድ ሆኖ ሰንሰለት ከአልሆነ አምበገነን መንግስትን እና ድህነት ወይም መሰል የኋላቀር አደጋዎችን ማሰር አይቻለውም። የአብሮ መኖር አቅሙ ከእንስሳዎች በብዛት ከፍ የአለ አይደለም። የእስራኤል ዜጋው ዳግተመራማሪ (researcher) ዩቫህ ኖህ ሀራሪ እንደ እሚከራከረው የሰው ልጅን ከእንሰሳ የነጠለው አብይ ነገር በጋራ የመተባበር አቅሙ ነው። ለእውቁ ኖህ ሀራሪ የእማይተባበር ማህበረ-ሰብእ የሰውዎች ማህበር አይደለም። የኢትዮጵያ ማህበረሰብእ ደግሞ በመተባበር ገና ነው። በጎሣ ይተባበር አለ ይባል አለ እንጂ እንደ ጎሣ እንኳ የጠነከረ ትብብር የአሳየ ኢትዮጵያአዊ ጎሣ የለም ማለት የእሚቻል ነው። ሀገርን ቀርቶ ቤተሰብእን ከትብብር ውጭ ማበልጸግ ከፍተኛ ዳገት ነው። ከመተባበር ይልቅ ነፈዝነት፣ ግድየለሽነነት እና ግልጎጂ የአለመተባበር እውነት በጠና መሰረቱ ከተገኘ ኢትዮጵያአዊነት ነው።

፫ መደምደሚያ

ኢትዮጵያአዊነት በደፈናው እጅግ የጸና ጥንትአዊ ማህበረሰብእአዊነት ሲሆን፣ ከአስቀያሚ መዝረክረክ እና ደንዳና ግድየለሽነት የእሚአሾረው ነው። እጅግ ሰቅጣጭ አጫጭር አስተሳሰብ የእሚገዛው ሲሆን፣ ብዙዎች ተስፋውን እየባሰ እየጨለመ እየመጣ ነው ይሉት አለ። ከተገለገሉበት ግን ከፍተኛ እምቅ ለውጥ እየተንቀዋለለ እንደ አለ የአለ ነው። ስለ ተለያዩ ነገርዎች እሚጽፉ እውቅ የኢትዮጵያ (ኢትዮጵያ ላይ) ጸሀፊዎችን በመከተል እና የተሰወረ ወይም ግንባርስጋ አስተያየትዎችአቸውን በመለቃቀም፤ ወጥ የሀገር እይታ እና የኢትዮጵያአዊነት ወይም፤ ሌላ፤ ጉዳይዎችን እንዲህ መሰብሰብ ይቻል አለ።
ኢትዮጵያአዊ ማን እንደ ሆነ ከኢብሳ ጉተማ “ኢትዮጵያአዊ ማንነው?” ግጥም ጎን ዛሬም ብዙዎች ህዝቡ የተሰናሰለበት የማርከስ ጋርቬይ ለሁሉ ሰው ተስፋ የእምትሆን ኢትዮጵያ እስክትመሰረት ብዙዎች ቢታገሉም መልሱ እስኪበጅ ድረስ፣ ኢትዮጵያአዊ ማንም ይሁን ማን፤ በእየጉራንጉሩ ባይዞርም፣ በተቻለ የሰፋ አተያይ ግን፣ ኢትዮጵያአዊነት የቀደመውን ፳፮ (ከ ሀ እስከ ፐ) ዝርዝር ይመስል አለ። የታላቅነት አንድ ጫፍ ደርሶ የነበረ የጥንት ስልጣኔ ጋር ተጠባብቆ በመዋሀድ እንደ ሎሬት ፍላጎት ማሻሻል ቀርቶ በጥፍር እንኳ መነካካት ሳይቻል፤ ዛሬ መላቅጡ የጠፋው አግጣጫውን የእማያውቅ ህዝብ ይመላለስ ዘንድ እየተቋቋመ ነው። ኢትዮዮጵያአዊነትን በተሻሻሉ መስፈርትዎች ለማግኘት ይስማእከ ወርቁ በ ደህንነቱ እንደ ገለጠው “አሜን አስተምሮ ይማረን!”። እስከ እዛ ግን፤ ኢትዮጵያአዊነት ይህ ወይም በከፍተኛ መመሳሰል እነእዚህን መሳይ መሳዩ ግድአልሰጥነት ነው። እውነትም ይማረን፨
Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s