Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

በተጨናገፈ ታሪክ ማግስት ዛሬም ብሔርአዊ ፖለቲካን የበለጠ-አስፈንጣሪ እድል ለሀገር ይጣራ አለ

About the new even better (also drowned/betrayed and was the direction three years ago) opportunities of politics and nation building in Ethiopia behind the crazy war since 2020GC., between TPLF and central administration that is being criticized and urged to end in peace talks/negotiations.

Take this piece on PDF.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 23rd 2021GC.,

የአብን አደረጃጀት ኃላፊ፣ አቶ ጋሻው መርሻ በየኛነገር ዝግጅት ላይ፣ ለአሃዱ ትመ.ው አዘጋጅ አቶ ዘላለም ደረጀ እንደ ነገሩት፣ ህዋሃት በብረት እጁ 27ዓመትዎች ቀጥቅጦ ሀገር ገዝቶ አለ። አሁንም፤ እኩልነት አይፈልግም፤ ወይም ሀገር መምራት ወይም አማራጭ የለም ባይ ነው…አሉት። “ጦርነቱ እኩልነት በእሚፈልግ እና እኩልነት በእማይቀበል ጎራዎች መሀከል ነው!” በማለት ገልጠውለት አለ።
የተአግ. መንግስት አስተዳደር ደግሞ፣ ከህዋሃት ጋር ስምምነት እንዲሰፍን በመሀከል አስተዳደሩ ጫና እየአደረገ ነው። ጭራሽ በቅርቡ ማእቀብ በመሀከል ሀገር፣ አማራ እና ትግራይ ክልልዎች፣ በኤርትራም የውጊያው ተሳታፊዎች ላይ ማእቀብ ለመጣል ፕሬዝደንትአዊ ብይን (order) ተላልፎ አለ፤ አለምአቀፍ ተቋምዎች፣ ኢመንግስትአዊ ተቋምዎች፣ የአፍሪካ ‘ኢንተለክቹዋልስ’፣ ወዘተ. ከመዋጋት በሰላም ተደራደሩ ጥሪዎች እየበዛ ነው።
የአለውን ብሔርአዊ-ቀውስ ውጊያ እንዴት ቢታለፍ የተሻለ ነው? ሀገር የበዘበዘ አምባገነን ህዋሃት በውጊያ ወይስ በሌላ መንገድ ይያዝ? ምንም ይሁን፤ ውጊያ ግን ተገቢ አግጣጫ መሆን አይችልም። የአስተዳደር ስልጣን በተለወጠ ቁጥር የለየለት ንፁሐን ጭምር የህዝብ ፍጅት የሀገር ታሪክ ዑደት ሆኖ አለ። ሀገር ግን ከቀደሙት መሰል ውድቀትዎች ተምራ ለመዘመን መሞከር ግዴታዋ ነበር። ያንን ለመከወን የተለወጠው አስተዳደር በመጀመሪያ ሰሞኑ ላይ ቃል ገብቶ ነበር፤ ጭራሽ ተቃዋሚዎች ሁሉ በልዩ ይቅርታ ወደ ሀገር ገብተው፣ ወደ ተደላደለ የፓለቲካ ድባብ መንደርደር ነበር። ይህ በእርግጥ የአስተዳደሩ ስጦታ ሳይሆን የወጣትዎች ሞት፣ እና የረዘመ ፀረ-ኢህአዴግ ትግል ልጅ ነበር።
ወዲአው፣ ህዋሃት ለዝቦ፣ ስልጣኑን ለተወዳጅ አባሉ ቢያስረክብም፣ ፕሮፌሰር መስፍን እንደ ገለጡት ህዋሃት ከውስጡ ተፈንቅሎ እየሸሸ እና እየተገለለ በመጨረሻ ወደ ክልሉ ጡረታወጣ። ስልጣኑን ለመመለስም መፈንቅለ መንግስት ወዲያው ሞክሮ ነበር ይባል አለ። ከፍተኛ ደረጃ ግድያዎች እና የግድያ ሙከራዎች ተከውነው ነበር። ዞሮዞሮ፣ የስልጣን ጠብ ተከሰተ። ዛሬም ሀገርአዊ እና ህዝብአዊ ጉዳይ የማድረግ ፕሮፓጋንዳ ቢንሰራፋም፣ ውጊያው የስልጣን ሆኖ እንደ ቀጠለ አለ።
ብሔርዊወ-ቀውሱ ነገር ግን፣ ወደ ለየለት እና የተራዘመ ውጊያ የአንድ ድርጅት ስልጣን ጠብ ጉዳዩ መዞሩ ነው። ይህን ለማስቀረት፣ ከምርጫው ቀድሞ፤ እነ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እንደ አሉት አዲስ ሀገርአዊ ውል (social contract) ሁሉንም በማካተት መመስረት ነበረበት። ሀገር መዘመን እና ከግድየለሽ ሀገር ናቂ ፖለቲካዋ መንፃት ሲገባት፣ ወደ ተለመደው “ተረኛነት ፖለቲካ” የተሰኘ ስልጣን ተተካክቶ ሀገር የመምራት ጉዳይ በምትኩ ተከወነ። በተለይ በአማራ ክልል እና በኋላ በሁለተኛው ዙር የመሀከል ሀገር አስተዳደር የውጊያ ጅማሮ ላይ የስልጣን ጠብ ወደ ህዝብ ጠብነት ተለወጠ። አማራ ክልል እንደ ዋና የትግራይ ክልል ጠላት ሆነው በእየተራ (መጀመሪያ አማራ ቀጣይ ትግራይ) ተጠቃቁ። ከማእከልአዊ ወደ ክልልአዊ ስልጣን ጠብ ወርዶ፣ ከክልል ወደ ህዝብአዊነት ደግሞ በገሀድ ይፋነት ወረደ። አቶ ተገኘሁ ተሻገር በእየወቀኑ በክረምቱ 2013ዓም. በሁለተኛው ዙር የህዋሃት ማጥቃት ወቅት፣ “ህዝቡ ወጊያው ህዝብአዊ እንደ ሆነ ተገንዝቦ እንዲነሳሳ ስንሰራ ሰንበተን አለ። አሁን እየተሳካልን ነው። ጦርነቱን ህዝብአዊ ለማድረግ የበለጠ እንሰራ አለን” ይሉ ነበር።
ውጊያው ቀጥሎ ከጦርነት ለረዥም ጊዜ ወርዶ የክሂሎትአማአዊ ኢደህንነት (technical insecurity) ብቻ የሆነ ሆኖ፣ እጅግ ሰግጣጭ የንፁሐን መሞት፣ መፈናቀልን አስከተለ። ቅርስዎች፣ እምነት፣ ትምህርተወ፣ ህክምና፣ ወዘተ. ተቋምዎች በሺህዎች ተቆጥረው ወደሙ። እንስሳዎች እና ተክልዎች በሆንብሎንታ ወደሙ። ብዙ ንብረት (ለምሳሌ በአንደኛው ዙር ማእከልአዊ መንግስት “የህግ ማስከበር” የአለው ብሔርአዊ-ቀውሱ ውጊያ መቶ ቢሊየን ብርዎች እንደ አስወጣ እና ከፍተኛ ክስረት እንደሆነ ለትግራይ ክልል ወዙ አመትዎች በጀቱን እንደ ፈጀ ወዘተ. ተነግሮ ነበር። ብዙዎች ሞተው፣ ብዙዎች ቆስለው፣ ብዙ ገንዘብ፣ ንብረት እና አውታረልማትዎች ወድመው፣ አመት ልደቱን ለማክበር ውጊያው እና የተከተለው የስልት ፀረ-ሰላም ቆይታ እዚህ መጥቶ አለ።
ስልጣንን መልቀቅ፣ ስልጣንወ መመለስ እና ማግኘት፣ እዚህ ሀገርን አድርሶ አለ። ከሞትዎቹ በዘለለ፣ ቀፋፈከ የውትድርና እውነትዎች ተስመልክተው ነበር። መሳሪያ የአጡ በእጅ እንዲዋጉ ሲደረግ፣ ከመላ ኢትዮጵያ በእሚያስብል ከእየጥቃቅን ከተማው ጭምር በተለይ ስራ አጥ ወጣት እንዲዘምት ሲደረግ እና በቀንዎች ውጊያ ልምምድ ወደ ለየለት ውጊያ ገብተው እንዲዋጉ ሲደረግ እና መሳሪያ ሳይሰጥአቸው መማረክ የቻሉት ለአብነት በተደጋጋሚ ሲንቆለጳጰሱ ነበር። በተጨማሪ፤ ብዙዎች በተለይ በትግራይ ክልል በረሃብ እየተፈጁ ወቅቱ ሲአዘግም፣ ማእከልአዊ መንግስትም በሽንፈት የመጀመሪያ ዙር ውጊያውን የአጠናቀቀው “የክልሉ ሰውዎች ይረሱ” በእሚል ነበር። በኋላ፣ አማራ ክልል በተለይ ወደ ወሎ ርሀብ እና መፈናቀሉ ወደ ግማሽ ሚሊየን ህዝብ አካባቢ አጥቅቶ የምግብ ርዳታ ጩኸት በተቃውሞ ሰልፍ ሁሉ (ፋኦ ደጅ በመሰለፍ) ተከውኖበት ነበር።
በአጭሩ፣ ከወንበር የውጊያው አመክንዮ ሆኖ መነሻነቱ፣ ወደ ክልልዎች መውረዱ፣ ቀጥሎ ወደ ህዝብዎች መውረዱ፣ ቀጥሎ ማእከልአዊ አስተዳደር “የሳምንትዎች ህግ ማስከበር” ከአለው ወደ ለየለት ረዥም ውጊያ፣ ከውጊያነት ወደ ተራዘመ ጸረ-ሰላምአዊነት እና ስልትአዊ (በተለይ ሰርጎገብ) እና የውጤትአምጣአዊ (tactical) በተለይ ደራሽ አጭር ግን አጥፊ ውጊያዎች ተመልሶ አለ። ለምሳሌ ድንገት በአፋር፣ ወይም አማራ ክልል ብዙ መቶ ንፁሕ ዜጋዎችን ገድሎ፣ ከተማ አውድሞ፣ ዘርፎ መመለስን ህዋሃት በሁለተኛው ዙር ሲከወን እንደ ከረመ አለ። አስገድዶ መድፈር ከትግራይ ክልል የመጀመሪያው ዙር ውጊያ ጀምሮ እስከ አሁን በስፋት ይከወን አለ ተብሎ በእየወቅቱ እየተገለጠ ነው።
ሂደትበሂደት፣ የስልጣኑ ጠብ ንፁሑ (የአልታጠቀ) ህዝብን አውድሞት አለ። ቀጣይ ታሪኩ ደግሞ የጨቀየ ሆኖ አለ። ቂም እና ቁርሾ በእየስፍራው ተቀብሮ አለ።
ይህ ብሔርአዊ ቀውስነት ሆነ። በአዙሪት የአልሰለጠነ ፖለቲካ መርገምት ሰምጦ አስተዳደርአዊ ለውጥን ከፍተኛ አጥፊ እውነት አድርጎት አለ። ሲጀመር የተጠቀሱት የአብን. ኃላፊው፣ ህዋሃት ከአልገዛ መገዛት እማይፈቅድ የአሉት፣ የ2014ዓም. ዘመኑን የመሳፍንት ዘመንን የአስመስል አለ። ቀደም ሲል፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በዛሬም እንደ ትላንት? መጽሐፍአቸው፣ በእየክልሉ የተለየ ሰራዊት ለመሆን የደረሰ ልዩ ሀይል የተሰኘ ወታደር እየተቋቋመ ነው፣ ዘመነ መሳፍንት ይመስል ክልልዎች አቅም በማካበት ላይ ናቸው በማለት ማእከልአዊ መንግስትን የእሚቃረኑበት አቅም መስሎአቸው ያ ከሆነ መልካም ብለውት ነበር። የእሚመስለው፣ የአብን.ኡ ኃላፊ ዘመነመሳፍንትን ህዋሃት ፈላጊ ነው። እእደ ምንይልክ ካልእ ሀገር በአንድ አስተዳደር ለመውደቅ አስተዳደሩ ቀድሞ ፈጽሞ በውጊያ “ክልልሉን” ማሸነፍ አለበት። በእርግጥ ከእዛ ዘመን የወረደው እውነት የተሸነፈ ክልል ቢኖር፣ ክልልዎች እና ማእከልአዊ መንግስት እንደ እሚሉት “ህዋሃትን ማጽዳት! መቅበር!” በመከወን አዲስ በተዋረድ ተቀጣይ መንግስትአዊ አስተዳደር ይበጅ አለ እንጂ እንደ ምንይልክ ካልእ አስገብሮ ራስህን ግን አስተዳድር ብሎ መመለስ የለም።
ሀገር፤ በተለመደ የስልጣን ፍልሚያ አዙሪት ተሽከርክራ ወድቃ አለች። ቀውስ ውጊያ በንፁሕዎች ዙሪያ እየከረመ ነው። ህዝብአዊ ውጊያው በብዙ ዘርፉ ህዝብን እየአወደመ ነው። የሀገር ታሪክ በመቆሸሽ ቀጥሎ አለ። ከምንም በላይ ለነገው ትውልድ አዲስ ምእራፍ ተከፍቶ ሁሉን አቀፍ ፖለቲካአዊ ዝማኔ (update) መከወን አልተቻለም። ሀገር፣ በዘመነ መንገድ ሳትመሰረት፣ በተገኘው የስልጣን እድል አለርህራሄ በመጠቀም ወደ አስተዳደር ጫፍ ለመድረስ ምንም የአልተገባ ቢሆን ምንም በመክፈል ላይ እየተቀጠለ ነው።
ይህ ብሔርአዊ-ቀውስነት መጀመር አልነበረበትም። አሁንም ዘግይቶ፣ ማብቃት አለበት። ህዋሃት በብዙ ኢትዮጵያዎች አይወደድም። ለእዛ ሲባል አብዮት-ጫፍ በደረሰ ተቃውሞ ወደ መውደቅ ተቃርቦ ነበር፤ በሂደት በሰጠው ግብረመልስአዊ መሻሻል እራሱ እስኪባረር ድረስ። ዞሮዞሮ በላጩ መደበኛው ዜጋ ህዋሃትን ቢመለስ አይደግፍም።
ነገርግን፤ የከረመው የመሳፍንትአዊ ከፍተኛ ትግል ሀገርን በማበላሸት በመቀጠሉ፣ ጉዳዩም በተቻለው ፈጣን መንገድ ማርገብ ተመካሪ ነው። ይህ እሚሆን ከሆነ ግን፣ ፈጽሞ ብቻውን መከወን የለበትም። እንደ አዲስ ሀገርን ለመመስረት እድል ሆኖ መወሰድ አለበት። የታሰሩት የኦሮምያ እና ብሔርአዊ ዘመም ፖለቲከኛዎች አብሮ መጠራት አሉብአቸው። የአሉ ተቃዋሚዎች መካተት አሉብአቸው። ሀገር በአዲስ መንገድ ወደ አዲስ ሀገርአዊ አስተዳደር ለመቅረብ አዲስ ግን ተገቢ መንገዱን መጀመር አለባት። የዘገየውን በመመልከት፣ ሁሉን የከተተ፣ ስርአት ማበጀት ተገቢ ነው። በቅርብ አመትዎች ርቀት የተወደደ ልብወለድ የነበረው Gone Girl, ሲጠናቀቅ፣ ቤን አፍሌክ በተወነበት ገጽማያ ውርሱ (its screen adaptation) አታላይ ወንጀለኛ ሚስቱን በይቅርታ እሚቀበላት በመጨረሻ ከእነስህተቷ ለወደፊቱ ለአረገዘችው ልጁም ሲል ነው። ስለ ጠቢው (the posterity)፣ ሀገርን አዲስ አግጣጫ ውስጥ ስለማስገባት እና በምላሹ የዘገየ ተገቢ ህዳሴ ለማግኘት፣ ብሔርአዊ ሰላም እና እርቅ፣ ቀጥሎ (ሁሉን) ጠቅላይ ስምምነትዎች እና ወል ስምምነት (social contract) ተመካሪ ነው።
አቶ ጋሻው የአሉት የእሪና ናፍቆት ከአለ፤ አንዱ ተተኪ ባለስልጣን ቀዳሚውን እየአደባየ ለብቻው ዞሮዞሮ የመግነኑ ነገር መሰበር አለበት። እኩልነት እና ነፃነት ገደብ የለሽ ከአልሆነ፣ የመንግስት ስጦታ ብቻ ነው። ስለእዚህ፣ ከአልመራሁ እንጂ እኔ አልመራም የአለውን እንኳ መክተት እና ማስተናገድ ከአልተቻለ ትክክለኛ ነፃነት እና እኩልነት አይኖርም። አስሮ፣ የአልታሰረውን አሸባሪ ብሎ፣ ውጭ የአለውን ሞት ፈርዶ፣ ሁሉን ተቆጣጥሮ መግነን መቀየር የእሚገባው ተራ እውነት ነው። ስለስልጣን ብሎ ድሀድሀ ህዝብን በማነካከስ እና ማሰቃየት መቀጠል፣ ከታሪክ አስቀያሚ ብሔርአዊ-ቀውስ በተስተካከለ መንገድ አሻሽሎት ለማለፍ ይህ ሌላው እድልም ነው። እኩልነት በደቡብ አፍሪቃ የመጣው አፓርታይድ ይቅር ተብሎ አብሮ በመሆን ነው። አሁንም ስለህዝብ እና ታሪክ፣ ፖለቲከኛ ነን ባይዎች፣ (በየቱም የተባለ ጎራ ቢሰለፉ)ለሀገር ክብር እና ታሪክ በማለት ነገሩን ወደ አዲስ ግን ዘግይቶ የአረጀ ጉዞው መግባት አለበት። እርቅ ከተከወነ፣ ህዋሃት ከማእከል ሳይሆን የታሰሩት ሁሉ ከቀልድ መሰል የስድስተኛው ብሔርአዊ ምርጫ ተሸናፊዎች (ነፃነት አጥ ድምፅ አሰጣጥ ሆኖ በትንንሽ ከተማዎች እንኳ የበዛ ድምፅ ጣቢያ ተበትኖ ለተፎካካሪዎች ለመቆጣጠር እና ለድምፅሠጪዎች ደግሞ በእየቤቱ ደጅአፍ ድምፅ በመሰጠቱ ነፃ ምርጫነቱን የአባከነ ምርጫ የነበረ በመሆኑ)ሁሉን ነገር እንደ እሚገፋፋው፣ በብሔርአዊ እርቅከ ስምምነት፣ ሁሉን አካታች ስርአት ጅመራ ለመጀመር ተያያዥ እድል አምጪ እውነት ነው።

ከመፈራረጅ እና እርስለእርስ ከመበላላት፣ ወደ አንድ ለውጥ ለመሻገር አዲስ ታሪክ ለመፃፍ እጅግ አመቺ ቀዳዳ በህዋሃት እና ህልውና ዘመቻው የአብቃ ተስማመጀ ጀርባ አለ። ከስምምነት በላይ ከይቅርታ በላይ፣ ሀገር መመስረትም ለእዚህ ጉዳይ ምላሹ መሆን ይችል አለ። የሰላም ፍጠሩ ውትወታው አንድ አምባገነን ፊት ከእሚሆንበት የዘላለም ሀገርአዊ ልማድ ወደ ተለያዩ እና እማይስማሙ አካልዎች ሀገር በጋራ የማስተዳደር ሀቀኛ እድል መክፈት አዲስ ኢትዮጵያን መመስረት ነው። ዳሩ፣ ከእዛ በላይ በአንድነት እሚያስፈነጥረን እድል አለ። ህዋሃት ከተመለሰ፣ ፈጽሞ አብሮ መሆን የአለበት እውነት ሽግግር መንግስት ወይም በጋራ የአሉ ፖለቲከኛዎች ሁሉ ከአዲስ ለሀቀኛ ውድድር መቅረብ እውነቱ ነው። ምንም ሲደረግ፣ እሚታየው ከሁሉ በላይ ስለሆነው ስለ ወደፊቱ ነው። ከቀውስ-ጉዞ ወደ ዘገየው ጠቅላይ ፖለቲካ በውጤቱ አንድ ነፃ እና እሪናአዊት ሀገር መንደርደር ይቻል አለ። ከሁሉ መልካሙ ወደፊት ህዋሃትን “መቅበር” ሳይሆን፣ ከጥቂት ጤናአማ አማራጭዎች መሀከል ወደ ሀገርአቀፍ ጥቂት አመትዎች በተቀባባ ለውጥ ተይዞ የዘገየው ሀቀኛ ማእዶት መሸጋገር ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s