Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የብልጽግና ችሮታ-ፖሊቲካ እና ተመዥራጭ ቀልድዎቹን በቁምነገር ስለመመርመር

About how a gift-politics (a dictator’s gift of administrative positions for his defeated political rivals) has lurked around Ethiopia during EPRDF and now Prosperity Party has successfully adopted the sham politics in Ethiopian history of dictatorship and administrative governance.

ይህ ጽሑፍን በ ተአዶ. (pdf) ይጋሩ።

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 29, 2021GC.,

ቁልፍ መጠነቃልዎች (key vocabularies)፦ የችሮታ-ፖሊቲካ፤ ንጽውሳኔ፤ ኢህአዴግ.፤ ተጠያቂነት


አዳነች አበቤ፣ የመጀመሪያዋ የአዲስአበባ እንስት ተመራጭ ከንቲባ ሆነው የእራስአቸውን የአልተመረጡ እንስት የአዲስአበባ ከንቲባ ፈርማህደር (record) በማሻሻል በ18ኛ መስከረም 2014ዓም.፤ ሲመረጡ፣ አስተዳደርአቸው የብልጽግና ድርጅት 100እጅ የመናገሻዋን 6ኛው ብሔርአዊ ምርጫ ማሸነፍን ተከትሎ የተቋቋመ ነበር። ካቢኔ ሲመሰርቱ፣ ሲቀድም የህግ ተመራቂ እና የአዳማ ከተማ ከንቲባዋ፣ ሁለት ተፎካካሪ ድርጅትዎች (አብን. እና ኢዜማ.) አንድአንድ ተወዳዳሪዎችአቸውን እንዲአቀርቡ በመጠየቅ፣ ከ18 ካቢኔዎችአቸው መሀከል በመክተት ሾሙ። አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም (የአብን አደረጃጀት ኃላፊ) የመንግስት ንብረት አስተዳደር ቢሮ አቶ ግርማ ሠይፉ የአአ. ኢንቨስትመንት ቢሮዎች መራሔዎች ተደረጉ።
ሠበበድርጊቱ፤ ‘መቶበመቶ ምርጫ ስለአሸነፍን አስተዳደሩን ለአለመጠቅለል ነው!’ ተብሎ አለ። ይህ እንዴት መታየት አለበት?
መጀመሪያ፣ ምርጫ በፍሬጉዳዩ፣ ህዝብአዊ ለዑዋላዊነትን መተግበሪያ መሣሪያው ነው። የተመረጡ፣ አስተዳደር እንዲከውኑ በውድድርዎች ጀርባ የተጠሩ ናቸው፤ እንደ እሚገመተው እና መርኁ። የአበቤ ድርጊት ይህ ቁልፍ መርኅን የበጠሠ ነው። “ሁሉን የመክተት የዲሞክራሲ ጉዳይን ለማሻሻል እንተጋ አለን” ብለው በሹመት ንግግር ድርጊቱን ለማብራራት የተናገሩት፣ ፈጽሞ ለመቀበል የእማይቻል ነው። ንጽውሳኔ (democracy) ህዝብ ከአስተዳደር የአሰናስል አለ እንጂ እንደራሴን ከመረጠው ቁንጽል ተሸናፊ ተፎካካሪ እሚያነካካ አቋራጭ የለውም፤ ኖሮት አያውቅም፤ ከስር እናየው አለን። እውቀት እና አቅም እስከአለአቸው ይስሩ እሚባለው፣ ተከትሎ እሚደመጥ አመክንዮ ደግሞ ህጻጼአዊ (of fallacy) እና ተርታ (mediocre) አመክንዮ ነው። ብዙዎች ይህ መስፈርትን የአሟላ አሉ። የቀድሞ ጠሚ. ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በሂደት አስተዳደርአቸው እየተገነደሰ ሲሄድ፣ በዶር. አብይ አህመድ ከመተካቱ የለየለት ለውጥ ቀድሞ፣ ከእየ ኅዋአዊከተማው (the universities) ምሁርዎችን አድኖ ለአጭር ወቅትዎች በመሾም፣ ተቃውሞአዊ ማእበልን ለመቋቋም ሞክረው ነበር። አፍታዎች መተንፈስ ቢችሉም የአልተሳካው የድርጅት ትልምአግጣጫዎች (policies) እና ከችግሩ መክፋት የተነሳ የድርጅቱ መጥፎ ታሪክ እና ፍልስፍናዎች በመሆኑ እስኪወድቅ፣ ካቢኔው ነፃውን የእውቀት መር አሿሿም ተከትሎ ለመትረፍ በማኔቴቄልፋሬስ ደንብ ጥሮ ነበር፤ በአዲስ የ”ኦሊጋርኪ” ስልት። በእውቀት ከአሉአቸው ተሹመው የአገልግሉ እሳቤ አስሳብቦ፣ ከተፎካካሪዎች የተጋበዙ ባለስልጣንዎችን መጥራት ግን፣ በአንደምታው ሁሉ በተለየ መንገድ(ዎች) መተንተን አለበት። ንጽውሳኔአዊ (democratic) ልምምድ አይመሰርትምም፣ ሙያተኛመርነት (meritocracy)ንም አይገልጥም። ሁለቱም እንደ ተርታአቸው፣ በህዝብ መሾም እና በእውቀት ውድድር መሾም ብቻ ናቸው። የአልተጣበቁትን በስመንጽውሳኔ እና/ወይም ስለእውቀት መጠራት ስምዎታ ስለእዚህ ህጻጼአዊ ክርክርቴ (argument) ሆኖ ይጠልል አለ።
ሁለተኛ ተጠያቂነትን ይሠብረው አለ ፩። የቆየው ህገመንግስት፣ የተመረጡ ለህሊናአቸው፣ ህገመንግስቱ እና ለመረጠአቸው ይጠየቅ አሉ፣ ሲል፣ እነእዚህ እንግዳ ካቢኔዎች፣ ህገመንግስት የጣሠ የተጠያቂነት ድንበር ይበጅልአቸው አለ። መች ተመረጥኩ? እሚል መርኅ ሊገዛአቸው፣ የህዝብ መርጦኝ አለ ድንቅ ፖሊቲካል ስነልቦና አይነካካአቸውም።
ተጠያቂነት ይሰብራል ፪፤ ተጠያቂነትአቸው ለጋበዘአቸው ድርጅት እና ድርጅት ብቻ በመሆን፣ ከፍተኛ የታማኝነት ቀውስ ይቀሰቅስ አለ። በግብዣ ስልጣኑ የመቆየት እና መነሳት ጉዳዩ መቶ እጅ በሿሚ ድርጅቱ በኩል በመሆኑ፣ የታማኝነት ጉዳዩን ጤናአማ አያደርገውም፣ ሌቋሆ. (ሌላ ጉዳይዎች ቋሚ ሆነው)።
አራተኛ፣ የአልተመረጡ የአዋቂነት ግርማ የያዙ ካቢኔዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ የተመረጠ ድርጅት እነእርሱን በማካተት መከወን የእሚችለው፣ በልዩአዋቂነትአቸው የተነሳ ነው። ያንን መርኅ የጣሠ የካቢኔ መዋቅር ይሆን እና ይህ እንቅስቃሴ፣ አስተዳደር ጎጂ በውጤቱ ህዝብ ጎጂ ይሆን አለ። የተፎካካሪዎች-ማካተት ትርክት፣ በርግጠኝነት አዲስ የካቢኔነት መስፈርት ነው። ስለእውቀት የተቀጠሩ አይደሉም። ስለአካታችነት በእሚል፣
አምስተኛ፣ ህዝብአዊነትን መፃረር ነው። የኢዜማ. እና አብን. ተጋባዥ-ባለስልጣንዎች፣ በእየድርጅትአቸው ተፎካክረው፣ በተለይ ኢዜማ. በእየአንዳንዷ ወንበር ላይ በከተማው ተፎካክሮ፣ መራጭ ህዝቡ፣ የአላመነበት ነው፤ እንደ መርኁ። ህዝብ ይህን ከወሰነ፣ እንደ መርኁ፣ አመክንዮው፣ በቂ እና ብቁ አለመሆንን መመልከቱ ነው። በተጓዳኝ፣ ብልጽግናን መቶእጅ መምረጥ፣ እንደ መርኁ፣ መቶእጅ የተገባው፣ በቂ እና ብቁ፣ ተሰኝቶ ነው። ይህ ከምርጫ ተወልዶ በገሀድ ሲተገበር፣ እሳቤው፣ ተሸናፊዎችን ከአስተዳደር ድራሽ ማጥፋት እና አሸናፊውን የመሾም እውነት ነው። ከተሸናፊዎች ጎራ የህዝብ አተያይ፣ እንደ መርኁ፣ የአለመብቃት እና አርኪ የአለመሆን እውነት ነው። አንዲት ድምጽ የተነፈገ እንደ መርኁ በቂ እና ብቁ የአለመሆን ጠባይን ህዝብ የተረዳለት ተፎካካሪን፣ መራጭ አቧራ የአለበሰ ተፎካካሪን፣ የእኔ ጉልበት ፈርጥሞ አለ እኔ አጽድቼ በአስተዳደሬ እከትትህ አለሁ ብሎ የህዝብ አቧራውን ማራገፍ፣ ለመርኅዎች የእማይገጣጠም እንቅስቃሴ ነው። ህዝብ አትክልም ብሎ የጣለውን፤ ህዝብ ትሆነኝ አለህ ብሎ የወከለው፣ በጎን ከአነሳው፣ ህዝብአዊነትን (የህዝብ የበላይ ወይም ለዑዋላዊነትን) መፃረር ነው። ህዝብ ለአገልግሎት የአላመነት ዞሮ ህዝብ ፊት መግቢያ ከተቸረ፣ የህዝብ ፍፁም ልእልና ብጠሣ ወይም ክህደት ተከወነበት። የኢዜማ. አንድ ተወካይ እንኳ፤ ስለተሸነፍን አንበታተንም፣ እዚሁ በህብረት ተቀምጠን እየታገልን ግል እየአስተካከልን እስከ ቀጣይ እንቆይ አለን፣ እንደ አሉት፣ ህዝብአዊ ክልከላው መቶእጅ እንደ መርኁ እሚከበር እንጂ፣ በናጠጠ አሸናፊ መሆን የተነሳ እሚቀለበስ ዐውድ ማበጀት አልነበረበትም።
ስድስተኛ፣ ሀቀኛ ሳይሆን ከፍተኛ መጥፎ ሠበብን (not good-faith but in bad-faith) የተከወነ ስለመሆኑ ማስረጃ የለም። መቶበመቶ በምርጫ ማሸነፍ እጅግ ፀያፍ ልምምድ ነው። ያግንታዎች (exceptions) ቢኖሩም፣ በተለየ ሁለት አመትዎች የሰነበተ ዳኺ ድርጅት – “ገና የቀደመውን ድርጅት ስለ አልተካሁት ችግርዎች ይገጥሙኝ አለ እንጂ እኔ ከአሁኑ እምተች አይደለሁም!” የእሚል –
ሰባተኛ፣ ለትግበራ የእማይመች ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። መቶእጅ የአሸነፈ ድርጅት አንድ ስፍራ ለተፎካካሪዎቹ ፈለገ ማለት ምን ነው? እንዴት የአለ ነፃነት ለተጋባዡ አለው? ተፎካካሪ ድርጅትዎች፣ የእየራስአቸው ዐቅድ በእየዘርፉ አሉአቸው። በተሾሙበት ዘርፍ መቶእጅ አርነት ወጥተው አለን? በድርጅት የእሚከወን ማንኛውንም ጉዳይ በእዛ ዘርፍ መከወን ይችል አሉን? ዘርፉን በፖርቲአቸው መርኅዎች መሰረት ማስተዳደር ይችል አሉን? ይህ ጥርጥር የለውም። አዎንታአዊ ምላሽ አለው። አንድ ዘርፍን ለመምራት በተጋባዥነት የተጠራ ተፎካካሪ፣ በእራሱ ዐቅድ፣ ቁጥጥርዎች፣ መዋቅርዎች፣ ህግ እና አፈፃጸም መርኅዎች፣ ስነግብር (methodology) እና ተግባርዎች መከወን እሚጠበቀው ገጽታ ነው። ተቀጣሪ ሆኖ አገልግሎ ምንዳ ተቀብሎ አንዱ ግለሰብእ ከተመለሰ – የአሸናፊ ድርጅቱን ስራዎች ከሰራ – ስምህን ልግዛው ነው እንጂ፣ አንዲት ስፍራዋንም ሰጠሁህ አይደለም። ከአቧራ አንስቼ ህዝብ የለቀለቀህን የፈትበቃኝም አልበቃህልኝም ውሳኔ ገፍፌ ስሾምህ፣ እኔ የመቻቻል/መገባበዝ/መዋደድ/ወዘተ. ፖሊቲካ አብረሕኝ እንድትጫወት ጠራሁህ ማለት፣ አንዲቷን ስፍራ በነፃነት ሰጠሁህ ማለት ነው። አደጋ የአለው አሰራር ቢሆንም፤ ተጠባቂ ሀቁ፣ የአልተገደበ ነፃነት ነው። ብልጽግና፣ ለምሳሌ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስፍራውን አልመራውም፤ አንድ ተፎካካሪዬ ይምራው ከአለ፣ ከእራሱ ውጭ ስፍራዋን አደረገው ማለት ነው። ለአነሰ ትርጉም፤ ይህ ቀልድ ከተከወነ፤ ከፍተኛ ውድቀት ነው፤ ለሁሉም። ፖሊሲ ትግበራዬን ትቼ (forgone) የንተን ተካሁህ ማለት – በእዚህ ደረጃ በመቶእጅ ነፃነት ከተከወነ – ጥቂት ጉዳዩን የሀቀኛ ሠበብ (good-faith) ሠበቡን ሊያንጨላጭልለት ይችል አለ። አስተዳደር ጠቅልል በህዝብ ብባልም ክፍት ሁለት ጠጠርዎችን ለአብጅ የአለ ሀቀኛ ግብዣ ከሆነ፣ ሀቀኛ ትግበራው፣ በጥሪው ጎን ሙሉ አርነት መስጠት ነው። በእርግጥ ማብራሪያ ለህዝብ መስጠቱ ይጠበቅ አለ። የህዝብ ድምፅ ጉዳይዎች (በአንድም በሌላ በዘረዘርንአቸው ነጥብዎች በኩል) የመሳተፍ እድል አሉአቸው። ጉዳዩን ስለእዚህ ማብራራት ግዴታ ነው። ይህ ለኦዲት ወይም ተጠያቂነት ደግሞ አጋዡ እና ህዝብንም ጥቂት ማክበሪያው መንገድ ነው። በቀረ፤ የይስሙሉ ወይም ክፉ ሰበብ (bad-faith) የመሆን እድሉ ይንር አለ።
ነፃነቱን እስከጥግ አስቀድሞ ግምት በመውሰድ፣ የተደረገውን ግብዣ በመመልከት፣ ወደ ተጠባቂ ትግበራው እንግባ። አንድ አስተዳደር ፈጽሞ አሀድአዊ ነፃነት በእየዘርፉ የለውም። የኢንቨስትመንት ጉዳዩ ከቤተእንደራሴው ህግዎች፣ ካቢኔው ጠቅላላ ዕዝዎች/አግጣጫዎች እውነታ፣ ከጠቅላላ መዋእለንዋይ ትልምአግጣጫዎች (economy principles) የእሚጋመድ ነው። በተሟላ አርነት የእሚከወን የአንድ ዘርፍ ኃላፊነት ከሌላው ዘርፍ የአልተሰናሠለ ትልምአግጣጫዎች ወይም መሰል መመሪያዎች የመፋተግ እውነቱ በመደበኛ ቅድመንቃት ተጠባቂ ነው። ከተጠባቂው (the conventional) ወይም ተፈላጊው አርነት ጀርባም እንኳ፤ አሁን የፖሊሲ እና መሰል መመሪያዎች አንፃር የአስቸገረ ቆይታ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። የኢዜማ.ው ተሿሚ “የፖሊሲ ማቻቻል ለማድረግ እንጥር፣ ህዝብን አርክተን ለመታየት እንታገል አለን” ብለውት ነበር፤ ኢሳት. እለትአዊ ዝግጅት በመሳይ ወንድሜነህ በኩል ሲአናግርአቸው በእዛው በምሽቱ ላይ። እንደእሚጠበቀው፣ የድርጅትአቸውን ፖሊሲ(ዎች) በነፃነት አይተገብሩትም ማለት ነው። ድርድርዎችን አቅደው አሉ። ያ መገለጡ አስፈላጊ እንደ ሆነው፤ የትግበራ ሀቀኛነት መቶእጅ አይጠበቅም ማለት ነው። ይህ ከሆነ ሀቀኛ የተፎካካሪ ድርጅትዎች ግብዣ ወይም፣ የተሸናፊዎች ሀቀኛ ዳግተመልሶ የማገልገል እውነት አይጠበቅም። ዞሮዞሮ እሚጠልለው፤ ጉዳዩ ተርታ የአምባግነና (መቶእጅ ነፃ መሆን) እምቅ ፍራቻ ወይም ስጋትን የተከተለ መደዴ የፖሊቲካ ግርግር ነው። የአብረህኝ አስተዳድር እዚህግባ እማይባል ተፅዕኖ የአለው እና ምንአልባት ሲጀመር የተገደበ ትግበራው የእሚጠበቅ አዲስ ልምምዱ፤ መናኛ/ልክስክስ የፖሊቲካ ዝባዝንኬ ነው። ተያያዥ ወደ ሆነው ጉዳዩ እንለፍ።
ስምንተኛ፣ የመደዴ (mediocre) ፖሊቲካ አስተሳሰብዎችን ለ ማጭበርበር/ማታለል/መግዛት/ ወዘተ. የተከወነ፣ መቶእጅ የበላይነትን ፍራቻ፣ የስሞታ እንኳ ቢሆን “አካታችነት”ን ኀሠሳ፣ የስጋት-ውጤት፣ ታእታይ ቅንጭብጭብ (infra-fractional) በተፅዕኖው (virtually) ኦና ትንግርት ነው። የመራጭ/ህዝብ ስነልቦና መበዝበዣ ውጤትአምጣአዊነት (tactical) እርምጃ ብቻ። ይህን ክፉ ውጤት አለው። ነፃ ተፎካካሪነትን፣ ነፃ ህዝብአዊነትን፣ የህግየበላይነትን፣ የፖሊቲካ ልማድን፣ የለዑዋላዊነት ጽንሰሃሳብን፣ ወዘተ. እሚአደፈርስ ነው። የእዚህ ማረጋገጫው፤ አንድ ጉዳዩ (የአዳነች አበቤ) አለመጠበቁ ነው። በኢሳት. እለትአዊ የምሽቱ ዝግጅት ተጠባቂ የክልል እና ማእከልአዊ መንግስትዎች ምስረታ ላይ (ድሬዳዋን ጨምሮ)፣ ይህን መሰል የስልጣን ግብዣ እንደ እሚጠበቅ እና ንጽውሳኔአዊ (democratic) ተሞክሮዎችን አጋዥ እንደ እሚሆን በድጋፍ ተመልክተውት አሉ። ይህ ከሆነ፤ ወደ ለየለት ቀልድነቱ ጉዳየጀ የአመራ አለ። ምርጫ፣ መንግስት ምስረታ፣ አገልግሎት፣ (የህዝብ ዳግ-ጥሪ)፣ ሌላ ፉክክር ለአዲሱ ምርጫ፣ የሆነውን ገሀድ አካሄድ አግበስብሶ የማጥቃት እና ጨዋታውን ገና ሳይዘምን እና ነፃነት ሳይልድ ወደ ውሽልሽልነት ማጠጋጊያ ልምምድ ይሆን አለ። ባራክ ኦባማ፣ ተፎካካሪአቸው እንስትን ቢሾሙ፣ ከሚሊየን አንድ ጉዳይ ሲሆን በልዩልዩ (አይነተኛ እጥፋት (hallmark)) አመክንዮዎች የእሚከወን ጉዳይ ነው። ሌላ እንዲህ የገጠመ ጉዳይ ቢገኝ፣ በመሰል አመክንዮ ከሆነ ይታለፍ ዘለ። በቀረ፤ ተፎካካሪዎች መቶእጅ ወይም እንዲያ ለመሰኘት ስንዝር በቀረው ሀገርአቀፍ ምርጫ ጀርባ አንድ እና ሁለት ለአተገባበር የእማይሆኑ አስተዳደርአዊ “አካታችነት” የእሚጠይቅ ጉዳዩ ሀገርን እና ፖሊቲካዋን ጎጂ ነው። የበረታ እና እንደ ኢዜማ. ቀጣዩ ምምርጫን ለመርታት እዚችው ኩስኩስ እንል አለን መርኅ እና ተጋዳይነት አስፈላጊ ነው። የጸና አም ማግነናአዊ “የምርጫ አሸናፊነት”ም በአለበት በርትቶ መጓዝን መፍራት የለበትም።
በኢህአዴግ. አስተዳደር ይህን ለመከወን መዳዳት እንደተከወነ ነበር። ብናሸንፍም እናሳትፍአችሁ አለን እሚሰኝ ወሬ ይስተጋባ ነበር፤ ከውስጡ ተፈንቅሎ ዐብይ አመራሩ በአፍጢሙ እስኪገለበጥ። አሁን ይህ መተግበሩ፤ ተመሳሳይ አስተዳደርአዊ ውድቀትን ለመከላከል ቢሆን እንጂ የህዝብ ድምጽ (democracy) የማክበር እርምጃ፤ ላይ እንደአየንውም የሙያተኛመርነት መርኁም አይደለም። ድምጽ ከስር እስከቤተመንግስት ከተከበረ በመርኁ፣ ንጽውሳኔ እና ህዝብአዊ ለዑዋላዊነት አለ። ሙያተኛዎችን ካቢኔ ማድረግ ተጠባቂ ክፍለ እውነት ነው። ተፎካካሪዎችን በችሮታ ማካተት እና ቀናምላሽዎችን መፈለግ እጅግ ከንቱ ፖለቲካአዊ ኢስንግባርአዊነት፣ የተፅዕኖ-ሸመታ ክፉ ሠበብአዊነት (bad-faith bargaining) ነው። እሚጠና የእሚሆነው፤ አስቀድሞ ግን በአሉታአዊነቱ እሚገምቱት፤ የድርጊቱ በ ተፎካካሪ ድርጅትዎች እሚጥልብአቸው ተፅዕኖም እሚከታተሉት ይሆን አለ።
ሲደመደም፤ ተወዳድሮ የአልተመረጠን ማለትም የተሸነፈን፣ ህዝብ ከአባረረው፣ እንደ መርኁ፣ በኋላ እንደ አምላክ በፍፁም ኃይል እና ችሮታ አቅርቦ መሾሙ፣ ዘርፈብዙ አሉታአዊ ቀልድ/ሹፈት መሳይ እይታዎችን እየመዠራረጠ ጋባዥ ነው። የተዘረዘሩት እንደአየን፣ ዳግ-መሰመር (re-underlined) የአለበት እውነት ግን፤ (በእዚያምአለበእዚህ፤) ሙሉ ነፃነትአቸውን ለሁለቱ አስደንጋሪ ካቢኔዎች አያይዞ መለገስ ከተቻለ አንዲት ቁንጽል ብትሆንም ቀናነት በከፊል ማግኘት የእሚችል ጉዳይ ይሆን አለ፤ አንደኛ መርኅዎችን ስለማክበር ሁለተኛ አምባግነናአዊደግነት (dictatorial benevolence) ለብቻው ተበረታች እና ስለእዚህ ሙሉ ቀናአዊነት ስለሌለው፤ ጉዳዩ ሙሉ ቀናነት ሊቸረው ከቶ አይቻል። ቀጥሎ፤ ህዝብንም በከፊል እንኳ አክብሮ ለምን የአባረርክአቸውን ሾምንብህ? እንዴትስ በአልመረጥክው ትልምአግጣጫዎችአቸው (their policies)፣ ይሰሩል አሉ? ወይስ እኛ እንመራህ አለ፣ ነእርሱን ለስምዎታ እና ምንአልባት አለምአቀፍ ገጽታአችን ስንል ስለሆነ የጠራንብህ፤ የእኛን ስራ ሰሪዎች ናቸው ስለ ምንዳአቸው ብቻ የተፎካካሪ ስም ይዘው ይቀመጡልህ አለ? ወዘተ. ብሎ ዝርዝሩን መግለጥ፣ የተዳፈነውን በይፋ መግለጥ ተገቢ፣ አስገዳጅ ነው። የምርጫ ህግዎችንም የእሚበጥስ በመሆኑ፣ ማብራራቱ አስገዳጅ ይሆን አለ። የምርጫ ህግ ተፎካካሪዎችን አወዳድሮ የአሸነፈውን የመንግስት አስተዳደር አቅምን መቸር ብቻ ነው። ያግንታ (exception) አያውቅም፤ የህዝብ ድምጽ በእንደራሴነት አሰራር ወደ ህዝብአዊ አስተዳደር ብቻ እሚመለስበት ክፍተትየለሽ ፍልስፍና ነው። በምርጫ ረትቶ፣ እንደ መርኁ፣ መንግስት መመስረቱ ግንባርስጋ ተግባር ነው። በኋላ ከአለው የአምባግነና እና ዴንታየሽነት እውነት ቀጥሎ ሂደትዎቹን እየተከታተሉ ለፀሐይየሞቀው ወይም ተጠያቂነት የአለበት አስተዳደርአዊ እና ህዝብአዊ መስተጋብርዎች የመግለጡ ልምምድ ቢሰወርም፣ አሁን በእዚህ ጉዳዩ መሰረት ግን፣ የችሮታ-ፖሊቲካ ስጦታ ተቀባይ የሆኑት ካቢኔዎቹ፣ ለዘርፉ ድርጅትአቸው በአበጀው/እሚያበጀው ዐቅድአቸው አስተዳደር እንዲመሩ የተገመተ ነው። የአሸናፊ እንደ ቃሉ ይመራ አለ ቋንቋ፤ መንገጫገጭ በጠጠር ለዝሆን ደረጃ ቢያገኘውም፣ ዝርዝሩ የህዝብ እውቀት እየሆነ እንዲታይ ከፍተኛ የህዝብ ፍላጎት (interest) ይሆን አለ። ሌላው ዳግ-መሰመር የእሚጠይቅ፣ ጉዳዩ፣ ችሮታ-ተኮር ፖሊቲካን ኢህአዴግ. እንደ አንዣበበት ሳይሞክረው የተፈተለከ ሂደት ላይ የነበረ የልእለቅዠት ቅዠት (surrealistic illusion) መሆኑን ነው። አምባግነና ጠረፉ ሲረዝም፣ ወደ ልእልና የመጣው አምባግነና የዐቀደው አይንበጨው ስልት ችሮታ-ፖሊቲካ ነበር። ይህ የእሳቤ ታሪኩ እየታወቀ፤ (ድርጅት) ገድሎ-ወራሹ ብልጽግና ሊሞክረው ሲገባ፤ መታወቅ የአለበት ደግ ነገር አለመሆኑን ነው። የችሮታ-ፖሊቲካ የጽንፍ አምባግነና መታያ አውዱ ነው። የአምባግነና ጥግ (በተለይ ድኅረ ብሔርአዊ ምርጫ ፫ኛ) የሆነው ዐቅድ ሆኖ የቆየውን የገናአባት ስጦታ መሰል ሸርፎ ስልጣን ማጋራት፤ ከቀልድነቱ በዘለለ፣ ከሰላምሻጭ (peace-selling) ፖሊቲካነት [ከልማት፣ ፍትህ፣ እሪና፣ አርነት፣ ዝግመትአዊ ለውጥ፣ ወዘተ. በመከለል፣ ሰላምን ማረጋገጥ ብቻ መንግስቱ በመከወን አምባእሚገንንበት ስልት ነው] የእሚቀጠል የአምባግነና መገለጮ በመሆኑ ከእዛም ቢሆን ግን በመዝለል፤ በዝርዝሩ አተገባበሩን እንድናየው መደረግ አለበት። እንደ ዝርዝርዎቹ፣ የእዚህ ችሮታ-ፖሊቲካ የጉዳይ ይፋአዊነቱ እና ከእዛ በአላነሰ መረንየለሽ ዘርፍአዊ አርነቱን ለማየት ህዝብአዊ፣ ፖሊቲካአዊ፣ ህግአዊ፣ ታሪክአዊ፣ ምንአልባት ችሮታአዊ-፣ መብትዎች እና ጥቅምዎች ሀገር ኢትዮጵያ አላት፨
Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s