Categories
Quotes

Quote#6 [ጥቅስ#፮]

Getachew Abdi on disappointing Ethiopian theatre.

ብሔርአዊ ቴአትር መስከረም 13ኛው ቀን 2014ዓም፣ ጌታቸው አብዲ ሲሰግዱ እና ሲሳለሙት ከባለቤትአቸው እና አጃቢዎች ጋር። ከኢሳት. ትመ. ዜና የተወሰደ።
ጌታቸው አብዲ ከባለቤትአቸው ጋር በብሔርአዊ ቴአትር የእንኳን ደህና መጡ ዝግጅት ላይ ተሰይመው ስጦታዎች እና ዝግጅትዎች ሲኮመኩሙ።

“…

(በስቱዲዮ:-) የእዚህ ሀገር ቴአትር ዛሬ ስመለስ ሞቶ አግኝቼው አለሁ፤ ያ ከአየሁት ሁሉ የአሳዘነኝ ነገር ነው። የእዛ ዘመን ቴአትር በነበረበት ቢቀጥል ኖሮ የዛሬው የተበታተነ የሀገር ፍላጎትዎችአችንን የአስቀር፤ አንድ ሀገር እና ህዝብ የአደርገን ነበር። ሌላው የሰለጠነ አለም ቴአትር ጫማ አራግፎ ለሀገር አንድነት ምልከታ የእሚገቡበት ነው። ያኔ፣ የእነዮፍታሔ ንጉሴ ስራዎች እና መሰልዎቹ በተለየ፣ አንድነትን አጥባቂ እና ማህረሰብእ አሰባሳቢ ነበሩ። ዛሬ ይህ በእኛ ቴአትር የለም። አሁን እኔ በተለየ እምመክረው በእየ ስፍራው… በመላ ሀገሪቷ… የቴአትር እንቅስቃሴ ኢንስቲቲውት ተመስርቶ እንዲሰራጭ ነው። የቴአትር ኢንስቲትዩቱ ለእየ ባህሉ፣ ቋንቋው ለኢትዮጵያ ሁሉ የአስፈልጋት አለ። ይህ ለእኔ እጅግ ወሣኝ ነው። (በመረድክ ደግሞ:- [ስር የአልሰደደ አይበቅልም! በጽናት እሚታገል ታዳጊ ከስር ጣወትዎች ማብቀል ከአልጀመርን እየተሞ የአለው ቴአትር በላጭ አደጋ የእሚያገኘው ኪነጥበብ ሆኖ ሀገር የበለጠ የአከስር አለ። አንድ አመለካከት የለአበት ሀገር መፍጠር የባሰ የስአቸግረን አለ።]

አንጋፋ ከያኒ ጌታቸው አብዲ፤ (ፀሐፌ-ተውኔት፣ ኬሮግራፈር፣ ዘፋኝ፣ አዘጋጅ፣ ቴአትርቤትዎች አስተዳዳሪ፣ ወዘተ.) ለመታሰቢያ ቀፀላ፣ በምን አለሽ መቲ ኢሳት. ትመ. (ቴቪ) መስከረም 12ኛው 2014ዓም.፣ በመቅረብ ከውጭ ሀገር 26ዓመትዎች ኑሮ ጀርባ ተመልሰው፤ ደሴ ተወልደው፣ በማሲንቆ ከእናትአቸው በመደበቅ ለልጆች ሠብስበው በመዝፈን ሱአድጉ፣ እነ መርአዊ አቅርበው አሳድገውአቸው ከሙያ በላይ እንደ ወንድም አቅርበውአቸው ስለነበር፣ “የጥበብ መምህሬ እና እንደ (ወንድም) ስጋዬ ሆኗል”፣ ብለው፣ እውቅ የሆነ ተስፋዬ አበበ (ባለ የክብር ዶክተር እና የኪነት ቡድን በስሙ የእሚገኝለት፣) ቴአትር እየደረሰ በቴአትር ቤቱም ከቆሙ ሀውልትዎች ጋር የተያያዘ የግል ትግል ከነበረው እና ዛሬም ወጣትዎች እየሰበሰበ ማስተማሩን ክብር ችሩት ብለው፤ ሁለት አመትዎች ሀገር ፍቅር ቴአትርን በመሪነት፣ ቀጥለው (በ1959ዓም.፣ ለአዲስ አመቱ፣ እፈልግሻለሁ አታመልጭኝም የእነ መራዊ፣ ዘፈንን በብሔርአዊ ቴአትር በመዝፈን የተወዋቀው ቴአትር ቤትን) በኋላ ለ ሰባት አመትዎች የ ብሔርአዊ ቴአትር ቤት አስተዳዳሪ ተብሎ ለመጨረሻ ጊዜም በገረር ሳለ የ አገልግለው፣ (አብረው በብሔርአዊ ቴአትር “ትእይንተ ጥበባት” ተከታታይ የደራሲዎች እና ጸሐፊዎች እውቅ ዝግጅት እና ለብዙዎች መተንፈሻ የሆነው ዝክረ ኪነጥበብ፣ ዝግጅትን እና አንድ ቴአትር ከሰኞ እስከ አርብ እየተደጋገመ እንዲታይ ወስኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የአስጀመረ፣ የተጠቀሱ ዝጅቶጀቹን በመወጠን እና ማስኬድ እያገለገለ)፣ ከቀይ መስቀል ጋር ከእነ ደበበ እሸቱ ጋር ለተራቡ ዜጋዎች ምግብ ርዳታ ፍለጋ ውጭ ሀገር ወጥተው – በአዲሱ የህወሃት አስተዳደር 1984ዓም. ሁለት ወርዎች ሳያገለግል (ቀደምሲል?) ከቴአትርቤት ስራው በደብዳቤ ስለተቀነሱ – በእዛው ዲሲ. ቀርተው በስደተኛነት በዳግ-ኑሮ መመስረት፣ በኪነጥበብ ዙሪያ በተለየ የኢሳት. ትመ. (ቴቪ)፣ አባል ሆነው፣ (በጥበብ ዝግጅት እይት (show) ህዝብ ሲያነቁ የቆዩት) ስለእዚህ ጥቂት ከውጭ ሆነውም ሀገር ለማገልገል በመሞከር የቀጠሉት፣ ስለ ሚስትአቸው ወሮ. ወርቄ ማግባት ብለው የፀና ማጨስ ልማድን 20 ዓመትዎች ትተው “አንተ ብትተው አለምም ማጨስ ይተው አለ” የአለ ታማኝ በየነን የአስገረሙት፣ በውጭ ሳሉም በሙያው ለመስራት ኢትዮ-ሜሪካዎችን በወጥ መንገድ ማሰባሰብ አቅቶአቸው በግል ኑሮ በስፋት ተገድበው ለመስከን የተገደዱ መሆንአቸውን የነገሩት፤ ከሰባ አመትዎች በላይ ብሆንም ለማገልገል ዝግጁ ነኝ የአሉት፣ ለመታሰቢያ ቀፀላ ሲአወያዩአት፣ ስለ ዛሬው የሀገር ቴአትር መውደቅ፣ መኢሶን. ተብለው ከእነ ብርሀኑ ዘሪሁን ጋር በዛሬው አንድነት መናፈሻ የቀድሞው አራትኪሎ ቤተመንግሥት ለሰባት ወርዎች የታሰሩት፣ ውጭ ሀገር 1961ዓም. ለትምህርት መስኮብ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ በኩል ተልከው፣ ተምረው ሲመለሱ በሀገር ፍቅር ቴአትር የሰሩት (ሁለት አመትዎች በአስተዳዳሪነት)፣ የባህል ሚኒስቴር ውስጥ የጥበብ እና ባህል መምሪያ ክንፉን መሪ የነበሩ፣ የ ስንታየሁ፣ ቁልፉ፣ መስታወት፣ ምሽት፣ 1929 (ስለ አርበኛዎች)፣ ወዘተ. ተውኔትዎች ደራሲው፣ የስድስት መቶ በላይ ከያኒዎችን (ከቅዱስ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርትቤት ኳየር፣ ኦርኬስትራ፣ ብዙ ተዋንያወዎች፣ ወዘተ. በአንድ መድረክ አስተባብሮ እይት የማዘጋጀት የበፊት ዝና ቁልፉ (ያ እውቅ ብዙ ከያኒዎች የአሳዩት ትርዒት ለኢሕድሪ. ምስረታ ሲሆን መቶዎቹን ዳንስ ኬሮግራፍ አድርጎ በአቀረበው ዝግጅት፣ በሌጎስ ናይጄሪያ እና ኩባም በአያሌው እውቅ እና ታዋሽ መሰል ስራዎችን የአሰናዳ እና አቀረበው፣) የእነዚህ መሰል እና ስራዎቹ በደፈና ስኬት ምስጢሩ፣ ‘ከፍተኛ ዲሲፕሊን’ እና “ስራ፣ ስራ ብቻ ነው! ጸጥበሉ ከአልኩ መቶዎች ሲንጫጩ ስፒል ሲወድቅ ተሰሚ ዝምታ ለመፍጠር እስክፈራ በስራ ዋዛ የማላበዛ ነበርኩ!” በማለት እና በመሰል መርኅዎች፣ እና ሙያአዊነት መሆንአቸውን፣ ወዘተ. ሲነግሯት፣ አርቲስትዎች እነ ችሮታው ከልካይ፣ ቴዲ፣ ከተማ እና ሰሎሞን “የአሳደገን እጅግ ሙያተኛ፣ ሠው ስለእሚያሳድግ የገባው (enlightened) ወይም ተገቢው አራዳ፣ ሰው እማይንቅ ሙያተኛነት ብቻ እሚያጠብቅ ሠው ነው!” ብለው በዝግጅቱ ሲቀበሉት በየተራ የመሰከሩለት (ችሮታው ከልካይ “18 ጊዜ ቃለመጠይቅ ስደረግ በአንዱም የአልረሳሁት እና በብልሃት አመራሩ ግሩፕ የማያውቅ ሆኖ የአሳደገኝ፣ ግሩፕ እማያውቅ የመጨረሻው የቴአትርቤቱ ሰው የሆነብኝ ብሎ የአመሰገነው፤ ቴዲ ደግሞ በ ትእይንተ ጥበባት ድራማ ሰርቼ አይቶ ቀጠረኝ ያን ያክል የአገዘ ዝግጅት ነው የሰጠን የአለለት)፤ እጅግ ሰፊ ሙያተኛ ውለታውን ሁሉም የጠቀሱለት፣ ቃሏን በመደጋገሙ “ስልተ ዘይቤ” እሚል ቅጽል የተሰጠው፣ በእዛው ሰሞን መታሰቢያ አቅርባው ሲወያዩ ከቀረበው የተቀነጨበ፤ በማግስቱ በብሔርአዊ ቴአትር የምስጋና ዝግጅት ላይ የተስፋዬ አበበ ኪነት ማእከል ቡድን፣ የጎንደር ኪነት ቡድን፣ የብሔርአዊ ቴአትር ደናሽ ቡድን፣ ስለ 1929 ቴአትሩ የአርበኛዎች አመስጋኝ ቡድን፣ ወዘተ. ተሰብስበው ሊያመሰግኑ ከተዘጋጀው ዝግጅት ሲገቡ በቴአትር ቤቱ መገወቢያ ሰግደው ሲሳለሙ ቀድሞ ተቀርፆ ከተሰራጨ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s