Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ከቋንቋ መዋስን ወደ ከቋንቋ መስረቅ ማምጫ በቂበላይ ምክንያትዎች ምናሌ

About how borrowing from languages is a bad expression and stealing from languages is a better expression.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 16th 2021GC.,

Take this on PDF.

“መዋዋስ” እሚለው ቃልዎችን፣ እና ሀረግዎች፣ ከሌላ ቋንቋ የመበደር ሃሳብ ስለመግለጥ የታሰበ ስነቋንቋአዊ ጽንሰሃሳብ ነው። ከመጀመሩ ቀድሞ ለነገሩ፣ ቋንቋ ቅርጸት (structure) የመሰራረቅ እውነትም አለው፤ በሌላ ጽሑፍ እንደ አየንው። ወደ ጉዳዩ በዳግ-መመለስ፣ እሚከተለው ምናሌዎችን በመዘርዘር እንቀሳቀስ።
አንደኛ፣ መዋስ እሚለው የተዋሱትን ተገልግሎ በመጨረሻ ወደ አዋሹ መመለስን ስለ እሚነግር፣ የተሳሳተ ስመሜ ይሆን አለ። ቋንቋ ተዋዋሰ ቢባል ተመላለሰ ስለእማይባል ዝብአገነዛዘብ (misunderstanding) ነው። እውነት ከሆነ አንዱ ቋንቋ ከሌላው ወስዶ የአስቀር አለ። ማለትም መስረቅ ነው። ቃል/ሀረግን ለእራሱ ሳያበጅ ነጥቆ በመውሰድ ከቋንቋ ደንብ ውጭ መገልገል በመጀመሩ ስርቆት ነው። ይህ በአዎንታአዊ (in positive) ስነቋንቋ ጥናት አተያይ ሳይሆን በይሁናታ (in natural/normative) አተያይ ነው። በቂ መርኅዎች የወለዱት እሴትአዊ-ብይን (value judgment) ነው።
ሁለተኛ፣ ድርጊቱን አቅልሎ ‘መዋዋስ’ን መገልገል ከላይ የተጠቆመውን አዎንታአዊነት (positivism) ማበልጸግ ነው። ያ፣ ከፍተኛ ደሃነት ፈጣሪ ነው። ቋንቋ መሆን ከእሚችለው ይልቅ በቀጥታ አሁን የአለውን (አለ? አዎ-ንታ) ሰነፍ መንገድ እንዲከተል የአደርገው አለ።
ሶስተኛው፣ ከሁለተኛው የእሚቀዳ እና ከቀደሙት ይልቅ ሰፊ ነው። ተሰብስበው ንዑስ ነገርዎች ይመሰርቱት አለ። ‘መዋዋስ’ ከአልተበረታታ፣ የቋንቋ ንፅህናን በመጠበቅ ለመጓዝ ጥቂት በርን ይከፍት አለ። ለአንድ ቋንቋ ቃልዎችን በእራሱ ማበልጸግ ለተገልጋይ የህሊና እና የቋንቋ ቅድስና፣ የንቃተህሊና መስፋት እና መጠጠር፣ ሌቋሆ. (ሌላነገርዎች ቋሚ ሆነው)፣ የአንጎል መጎበዝ አንድ ምንጭ ነው። ቃል መሰራረቅ ከእነእዚህ ሁሉ ፀር ነው። ብዙ ችግርዎች በጀርባው ታዝለው አሉት። ሀ) የቋንቋ ስር/ቤተሰብን ይበርዝ አለ። አንጎል የለመደው የቋንቋ ዘሩ ከተበረዘ አንጎል ይሰክር አለ። ቋንቋ በራሱ ሰዋሰው ደምብዎቹ እና አዳዲስ ቃልዎች ማበልፀጊያ መርኆዎች (ከእነሱ መሀከል ቀንጭበን በቁንጽል ጽሑፍ አይተን ነበር) መሰረት ቃልዎች ከላዳበረ በተሰራረቁ ቃልዎች ተገልግሎ ለእሚያስብ ሰዉው የፈጠራ አቅም፣ የአመለካከት ብቃት ክወና፣ የአንጎል ነፃነት፣ የቋንቋ ሉዓላዊነት፣ ወዘተ. ከፍተኛ እድልን ነፋጊ ነው። ለ) ሁለት ቋንቋዎችን ማወቅ የማሰላሰል እና የግንዛቤ አቅምን የአመጥቅ አለ፤ ዎልፈር እንደ አረጋገጠው። መሰራረቅ አንጎል እንዳይመነጥቅ ጸር ሆኖ ይገጥም አለ። ለምሳሌ በተለየ መሀከልሀገር አማርኛ የእንግሊዝኛ ቃልዎች እና ሀረግዎችን በከፍተኛ መጠን ሰርቆ እናገኝኘው አለን። ማለትም፣ እንግሊዝኛ የማወቅ ተረፈ ጥቅም (ለአንጎል መበልጸግ) አቅሙ ይጫጭ አለ። ይህ ዝርዝሩ ብዙ ነው። በጥቆማ እንዝጋው። ሐ) የቋንቋ ዘር/ቤተሰብ፣ መበረዝ፣ በቃልዎች መሰራረቅ ይከወን እና የድምፀት ሁሉ መናጋት ሆኖ እብስልስልታን የአንገጫግጭ አለ። የተለየ ቃል በአንድ ቋንቋ ሲገኝ የመሳቅ እድል ሁሉ አለ። ለምሳሌ፣ ለአማርኛ ቋንቋ አዋቂው የዙሉ ቋንቋን ለመጀመሪያ ጊዜ ማድመጥ የ ጠ ዘር አብዝቶ የአስገርም፣ የእስራኤል ቋንቋን ማድመጥ የ ሸ ዘር በዝቶ የመደነቅ ነገር፣ ወዘተ. አለ። በእነእዚህ ቋንቋዎች ‘መዋዋስ’ ቢከወን ትንግርት ይሆን አለ። ያ፣ የአመለካከት መንገጫገጭ ለመኖሩ አስረጂ ነው።
በደፈናው፤ አመለካከት በጠራ መንገድ እሚከወነው በአንድ ወጥ የቋንቋ ፍሰት ነው እሚለው የቋንቋ መሰረትአዊ አረዳድ መበረታታት አለበት። ከመፍጠር ወደ መስረቅ ገብቶ ቋንቋ እንደ አይባልግ ተገቢ በመሆኑ ‘መዋስ’ በእሚል ነገሩን በማቅለል አበረታች ማድረግ አይገባም። በዘመነ አመለካከት የቋንቋ ከፍተኛ ጥቅምዎችን ሳይሸርፉ መገልገል እንዲቻል በተቻለ ሁሉ መታገል ከአንድ የቋንቋ ዳግጥናትዎች (re-studies) ይገባ አለ። እንደ ሀቁ መሆን እና በተቻለ ለነገሩን ማስጣል ክብረነክ አጠራር ቢደረግ ተገቢ ነው። ጠቃሚነቱ ዞሮ ለግሉ ቋንቋ ነው። ‘መዋስ’ ቋንቋን በመበረዙ እና ህሩይ የቋንቋዎች መሰረት ላይ የእሚበቅል የሉዓላዊ ቋንቋዎች መስተጋብርዎችአቸውን ገጸበረከት በመከልከሉ ስለእሚተባበር ተገቢ መርኅ እንደ አይደለው ለማሳወቅ አያበረታታም። ተገቢ ለውጡ ከተፈለገ፣ ቋንቋዎች ተዋዋሱ ከማለት ፣ ፍላጎቱን አይገልጠውም፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s