Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ስለ አጽሕሮተቃልዎች ቀላል አፃፃፍ ምክረሐሳብ

A new way suggested to write acronyms in Amharic.

Take this piece on PDF. [Also read]

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 17th 2021GC.,

አጽሕሮተቃልዎች (ግእዝ ‘አጽሕሮተቃላት‘)፥ ሁለት ወይም በላይ ቃልዎች እራስአቸውን ከርክመው አንዳች ሆሄዎችአቸውን በማዋጣት የፈጠሩት – ምንጊዜም ከእነርሱ ሙሉአካል ድምር የአጠረ – አዲስ ቃል ነው። በጋራ ሁሉም ቃልዎቹ ይወከሉበት አለ። ልክ እንደ “የብዙ ቃልዎች ተወካይ ሆሄዎች” ቃል ነው። ኢላማው፣ ረዥም የቃልዎች አጠራሩን ማሳጠር ነው።
በፊት፣ እጅግ እስከ ቅርቡ፣ አጽሕሮተቃልዎች በነቁጥዎች ወይም ይዘት (.) እርዳታ ይጻፍ ነበር። ተወካይ ሆሄዎች በእየመሀልአቸው ይዘቱን በመክተት ይታወቅ አሉ። አሁን ድረስ በይፋ እሚታወቅ አማርኛ ሰዋሰው ህጉ ይህ ነው። በቅርብ የቋንቋ አማርኛ አጻጻፍ ዝግመት፣ ነጥብ ሳይጨምር እራሱን የአቀርብ አለ። የሰዋሰው ደንብ እና አዲስ ልማድ የሆኑትን፣ ሁለቱን ምሳሌዎች እንይ፤ (ቢቢሲ አማርኛ እና ብርሀኑታዬ17 እሚል ጦማር ውስጥ ከተገኙ ዜናዎች የተወሰዱ ተከታታይ ምስልዎች)፦

የሁለቱ ምስልዎች ድህረገፅዎች ከሰሩ እነሆ፦ አንደኛ፤ ሁለተኛው

ከእነእዚህ አጽሕሮተቃልዎች የቢቢሲ.ው እሚያሳየን፣ አሁንአሁን የሰዋሰው ደንብ በአለመከተል በአጽሕሮተቃልዎቹ መለመድ የተነሳ እንደ እንግሊዝኛ ከአለ ይዘት መጻፍ እየተለመደ መሆኑን ነው። አጽሕሮተቃልዎች በበፊት ደንቡ ደግሞ፣ እጅግ አታካች በሆነ መንገድ ይተየብ እንደ ሆነ የጦማሩ ምስል የአስመለክተን አለ። በእየሆሄው ይዘትን መመልከት ለዓይንዎች አስቸጋሪ እና ጎርባጭ ነው። ይህ ሰዋሰው እጅግ ሰነፍ ደንብ ይመስል ዘንድ ይህ በቂ አመክንዮ ነው። አማራጭ የተደረገው ይዘት ከቶ አለመጠቀም ደግሞ አደጋ አለው። አማርኛ እንደ እንግሊዝኛ፣ የሆሄዎች አነባበብ ደምቡ ነፃ አይደለም። ሆሄ ሁሉ በቃል ውስጥ ከተገኘ የመነበብ እድሉ ከፍተኛ ነው። በእንግሊዝኛ ሆሄዎች ተሰባጥረው በጋራ አንድ ብቻ ድምጽ ሊያበረክት ይችል አሉ። ይህ ደንብን መመልከት ከቻልን፣ አማርኛ እንደ እንግሊዝኛ መቶበመቶ በንባብ እና መናገር ወቅት የተሳካለት አጽሕሮተቃልዎች የማቅረብ አቅም የለውም። በእንግሊዝኛ በተለይ ላእላይ ሆሄዎችን በመገልገል የተፃፈ አጽሕሮተቃልዎች በቀላሉ የአጠሩ ቃልዎች መሆኑ ይታወቅ አለ።
እንግሊዝኛ የአለው ይህ እድል በአማርኛ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የተበላሸ ነው። ሆሄዎች ልማድአቸው ቃል መመስረት ብቻ ነው። አጻጻፍ ወቅት አጽሕሮተቃልዎች በነቁጥዎች መገጥገጥአቸው ለእዛ ነው። ሆሄዎቹን ከይዘት ውጭ ቢደረድሩ አንድ ቃል መስለው መቀመጥአቸው ይገመት አለ፤ አጽሕሮተቃልዎች ናቸው ብሎ የመገመቱ ነገር ከፍተኛ ኢኋኝነትአዊነት (impossibility) የአጥለቀለቀው ነው። እውቅ ለሆኑ ነገርዎች ልክ እንደ ‘ተመድ’ የከፋ ላይሆን ይችል አለ። እንደ ቋንቋ ግን፣ አማርኛ ከአለ ነቁጥዎቹ መገጥገጥ አጽሕሮተቃልዎች ጽፌ አስቀመጥኩ ቢል ለታሪክ ወይም የዛሬውም አንባቢ ከፍተኛ ችግር እንጂ ሰዋሰው የአዳበረው ቋንቋ አይሆንም። እንደ እንግሊዝኛው መሆን ስለእማይችል ነቁጥዎችን መገልገል የሰዋሰው ደንቡ ሆኖ ተሰርቶ አለ። ነገርግን፣ ይህ ደንብ አታካች ነው ከአልን አማራጭ መመልከት ተገቢ ነው።
የአጽሕሮተቃልዎች የማሻሻያ ሃሳብ
አማርኛ ቀላል በሆነ መንገድ አጽሕሮተቃልዎችን መጻፍ መልመድ አለበት። ‘ተመድ’ ከአለይዘት የቀረበው በእየሆሄው መሀከል ይዘት ላለመሰንቀር እና የድርጅቱን ድረገጽ ንባብ አታካች ላለማድረግ ነው። ነገርግን፣ ‘ተመድ’ ሲነበብ አጽሕሮተቃልዎች እየተነበበ ለመሆኑ ቋንቋው ማረጋገጫው ምንድር ነው? ቃሉን አስቀድሞ ለአላወቀ አጻጻፉ አደጋ ነው። ቋንቋው መረጃ የማቀባበል አቅሙን የአደክምበት አለ። መፍትሔው የአመረ እና የእማይጎረብጥ ክሂሎትአማነት (technique) አበጅቶ መቅጠር ነው።
በእዚህ መሰረት፣ አንድ ይዘትን በማንኛውም ቃል ፍፃሜ ላይ አጣግቶ ማስቀመጥ የቀደመው ሆሄ ሁሉ አጽሕሮተቃልዎች መሆኑን ማስረጃ መደረግ ይችል አለ እሚለውን ሃሳብ እንውለድ። አጽሕሮተቃልዎችን ይዘት እሚያገለግለው በተሻለ እና ተዋበ ወይም ቢያንስ የአነሰ አስቀያሚ መንገድ ይሆን አለ።
ለምሳሌ ዓመተ ምህረት ወደ ዓ.ም. ከእሚአጥር ወደ ዓም. ቢመለስ ማለት ነው። ይህ አንዳንዴ ጭራሽ የተለመደ መንገድ ነው። ዞሮዞሮ ቋንቋው የአፈጀ አካሄድ መያዙን በዘልማድ ዝግመት እንመለከተው አለ። ቀጥሎ የቀረቡትን እናስተውል።

ሀረግ ወይም ረዥም ስም
የበፊት ሰዋሰው አጽሕሮተቃልዎች ደንብ
ግራአጋቢ አማራጩ
አዲስ ምክረሃሳብ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
ታ.ኢ.ህ.ግ.
ታኢህግ
ታኢህግ.

ጠቅላይ ምኒስቴር
ጠ.ሚ.
ጠሚ
ጠሚ.

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካይዎች ምክርቤት ምልዓተ ጉባኤ
ኢ.ሕ.ተ.ም.ቤ.ም.ጉ.
ኢሕተምቤምጉ
ኢሕተምቤምጉ.

የመጨረሻው በተለየ፣ በፊት ተሰምቶ እማይታወቅ አጽሕሮተቃልዎች ነው። አመክንዮው፣ እንዲህ ለአንባቢው በሙያውም ሆነ በአንዳች አመክንዮ የእማይታወቅ አጽሕሮተቃልዎች ሲገጥም የእሚቀርበውን መወሳሰብ ለማሳበቅ ነው።
በእነእዚህ መሰረት፣ አማርኛው የቀረበው በአንድ ነቁጥ ሲሆን፣ በቀላሉ የአንድ ረዥም ቃልዎች ህብረት አጥሮ መወከያው መሆኑን እንረዳ አለን። ቃሉ እንኳ ለመበተን ባይቀልለን፣ ሃሳቡን እንረዳ አለን። ዓይንዎችም የአልቀፈፈ አጻጻፍ ተመልክተው አይረበሹም።
መደምደሚያ
ቋንቋ አማርኛ እንዲዘምን እና ለተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲቀርብ ኁልቆመሳፍርት መሻሻልዎች ይፈልግ አለ። በተለይ የመሀከልሀገር አማርኛ። ነገርግን፣ ይህ ከእነእዛ ከቶ ለማለት በቀረበ መንገድ የእሚደረደር ማሻሻያ ምክር አይደለም። እጅግ ቁንጽል ችግር ነው። ቢሆንም እየተፈጠረ የአለው እና የእሚፈቀደው መቅለል ግን አይናቅም። ብዙ እና የተስተመቅለ ጥናትም ይጠይቅ አለ፤ በሀገር የመጨነቅ እና ግድአለሽነት መጠን የእሚመለከቱት እንደሆነው፣ ይህም ከማንም የእማያንስ አንድ አጭር ግን ቁምነገር የሆነ ውይይት ነው፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “ስለ አጽሕሮተቃልዎች ቀላል አፃፃፍ ምክረሐሳብ”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s