Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ዉሃዉስጥ ዓሣ የትምህርት እውነት ኢትዮጵያን እንደጎዳው

About how education system of Ethiopia is not consistent in its manner of furnishing education for students from grade one up to degrees and is a henceforth a national disasterious system.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 03rd 2021GC.,


Pick this on PDF.

“ወጥ የሆነ የትምህርት መስመር ለህዝቡ በተጨባጭ የለም። የእማይናጋ እና እየተከማቸ ብቻ የእሚጓዝ፣ እውቀት ማሰሻ ሂደት ቢፈጠር “ሀገርን እሚጠቅመው” ዜጋ መመረት ይችል አለ። እየሆነ ያለው፣ ተቃራኒው፣ እውቀቱን መጨበጥ ሲሞከር ሁሌ ይለዋወጥ አለ፣ ቁልፉ ሳይደረስበት “ትምህርቱን አጠናቀቅሁ” ስነልቦና “ተመራቂዎችን” እየአበሳጨ፣ ሀገር እየጎዳ ነው። እስከእሚታወቀው፣ በእዚህ መንገድ የኢትዮጵያ ትምህርት የችግር አይነቱን የዳሠሠ ሙከራ የለም። የትምህርት አሠሳው ግን በእየዋናዋና ጉዞው በቀደመው እውቀት እየተደረበ እሚወፍር አይደለም።”

የኢትዮጵያ ትምህርት ስርአት እና እውነት በጠቅላላው፣ በብዙ መንገድዎች እየተተቸ የአለው ነው። በእርግጥ ይህ ተገቢ ነው። የተገባ ምርት ሆነው ዜጋዎች እየፈለቁ አይደለም። አንዳንዴ ግን፣ የትምህርት መበላሸት እሚብራራው በ መምህር፣ ተማሪ፣ ትምህርትቤት፣ ብሔርአዊ የትምህርት አስተዳደር፣ ቋንቋዎች፣ ይዘት፣ ወዘተ. በእሚጠቆሙ ችግርዎች ነው። ይህ ሞኝነት፣ ከትምህርት ውጭ የትምህርት አጋዥ ወይም በአንድ ወይም ሌላ መንገድ ተያያዥ አስተዋፅዖዎችን ለመጠየቅ የአፍር አለ። ትምህርት እውነቱ ደሴት ግን አይደለም። ብዙ ትስስርዎች ቢኖሩም፣ እነእርሱን ትተን፣ ሲብራራ በጥቂቱ ግን ከትምህርት ውጭ ከአሉ እውነትዎችም ጋር ሊያያዝ እሚችል አንድ እይታን እናዳብር። እይታውን ለመጫር እንጂ የጠለቀ ውይይት አይደረግም። ከተጫረ፣ ሀገር መመልከት የእሚገባት አሳሳቢ የተዘነጋ አግጣጫ ይመስል አለ። በትምህርት ስርአቱ ከእሚነሱ አንድ ችግርዎች ለአብነት ታች አንስተን እናዝግም።

አንዱ ችግር፤ በቅርብ አመትዎች በአሰልቺ መደጋገም ጥራት-አጥ እየተባለ የእሚገኝ ነው። ተማሪዎች እራስአቸውን ችለው ሃሳብዎች አያመነጩም። ስለ ትምህርቱም ቢሰለጥኑ፣ ፍሬነገሩ ወይም እውቀቱ የለአቸውም። አስተማሪዎቹም፤ ለ ኤስቢኤስ መስኮተድምጽ (radio) አማርኛ ክፍል አወያይ አቶ ካሳሁን ሰቦቃ ነገዎ በነሃሴ 2013ዓም. የቀድሞ የደብረብርሃን ኅዋአዊ ከተማ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ዲን ደረሰ አየናቸው (ዶር.)፣ አሳሳቢ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ጥራቱ ማሽቆልቆል በ”በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራት ውድቀት ምክንያት የራሳቸው ሃሳብ የሌላቸውና መፍትሔ የሚሰጥ ዕውቀት ያላዳበሩ ተማሪዎች ተፈጥረዋል” አርእስት ለግማሽ ሰዓት ሲወያዩ እንደተናገሩት፣ አጭር “ሃንድ አውት” ሰጥተው በመፈተን ትምህርቱን መጨረስአቸውን ነግረው ይለዩአቸው አለ፤ ያም እጅግ የወረደ መሆኑን ገለጡት።

እንዲህ የአሉ ችግርዎችን ነቃቅሶ መመልከቱ ተገቢ ቢሆንም ብቸኛ መሆን ከእማይገባው እይታ በተለየ የትምህርት እውነትን በጠቅላላ በኢትዮጵያው ስርአት ለመዳሰስ እንሞክር። የላዩ፣ ከታች ይመሰረት አለ። የታቹ ተፅዕኖ በላዩ ከመጥፋት የራቀ ነው።

ይህ አጭር ቁንጽል የመነሻሃሳብ ነቁጥ፣ እሚያተኩረው አንድ ሃሳብን ለማስጮለቅ በማሰብ ነው። ይህ እሚሆነውም፤ ትምህርትን እንደ አንድ አለም – ከሀ ሁ ቆጠራ ጀምሮ እስከ ልህቀት ደረጃው ድረስ (ምን አልባት ለምሳሌ ሀ ሁ አስብዬ በፊደልዎች ስነልቦና ህክምና እሰጥ አለሁ እሚል ወይም ሀ ሁ በእዚህ መንገድ ለአማርኛ ቋንቋ ይሻሻልለት ወዘተ. በእሚለ ወዘተ. ደረጃ ትምህርት ቢቀረጽ (በስነልቦና ዘርፍ፣ በስነቋንቋ፣ በስነልቦናአማቋንቋ (Psycholinguistics)፣ ጠልሰም ጥናቶች፣ ወዘተ. ሀገርበቀል ክፍለትምህርት ቢዘጋጅ እንበል እና) በእርግጠኝነት ከ ሀ ሁ ጀምሮ እስከ “ፍፃሜ” የትምህርት እውነትን በአንድ የተያያዘ ወጥ እውነት ወይም ዓለም በረዥሙ ለይቶት ስለአንድ አካሄድ መመልከትን ማሰብ ይጀመር አለ። ትምህርት የኢትዮጵያ ህዝቡ አንድ ገጽታ ነው፤ በመሰረቱ ሀ ሁ -ዎችን A B C -ዎችን ከመልቀም ይጠነሰስ አለ። እስከ አራተኛ ክፍል የሮጠው ትምህርት በዋና መስጫ ቋንቋው ድንገት ለማለት በእሚያስደፍር ደረጃ ተቀይሮ በእንግሊዝኛ መሰረትአዊ እውቀትዎች ሁሉ ለማለት ይቻል አለ ይጠኑበት ይጀመር አለ። በክፍል ክፍል መዛወር ከፍተኛ ትምህርትቤትዎች ተደርሶ ወደ ከፍተኛ ተቋምዎች ከፍተኛ እውቀት አሰሳ ክወናውን ይዛወሩበት አለ። በመጨረሻ፣ በተለያየ ስምጠት ደረጃ ሰልጥነው ከእዚያ ተቋም ወደ ማህበረሰብ ዳግ-ይቀላቀል አሉ፦ ለፍቱን ልዩነት ፈጣሪነት።

ይህ ከ ሀ ሁ የእሚነሳ የትምህርት እውነትን ወይም ገሀድን እስከ ፍፃሜው አዋህደን ወይም ነጥለንው መመልከት በመጀመር፥ ቀጥለን፣ መድሐኒቱ እንዲገለጥ ወደ ችግርዎቹ ዳግ-እንመለስ።

[ለመጀመር እንዲረዳን ተከታዩን መንደርደሪያ አንቀጽ እንይ፤ ውስጡ ከእምናነሳው ቅንጭብ ሃሳብ ተያያዥ የሆነ ነገርን ለማየት እንሞክር። የኢትዮጵያ ትምህርት የጥራት ጉዳዩ የእሚወድቀው የቱ ጋር ነው? በእርግጠኛነት፣ ከተማሩት ኢትዮጵያዎች፥ ልእለብዙሃኑ (the super majorities) ሀ ሁ በትክክል አያውቁም! ከ ሀ ሁ ጀምሮ የተበላሸ ትምህርት ለዜጋዎች ከተሰጠ እውቀት የእሚገነባው በውሸት ስርአት እና መሰረት ላይ ነው ማለት ነው፤ ሌላ ውይይት ሳያስነሳ ግልጥ የሆነ ነጥብ ነው፤ ፊደልገበታ በንቀት ታልፎ እሱን ተጠቅሞ በመመራመር የምን እውቀት እንዲገኝ ይጠበቅ አለ? የንግግር ቋንቋ ብቻ በመገልገል እንጂ በጠለቀ አፃፃፍ ስርአት የመመራመሩ እውነት ተጠያቂ ይሆን አለ። አማርኛ ባናውቅም በእንግሊዝኛ እናጠና አለ ቢባል፣ በአደግንበት ስርአተትምህርት፣ ስለ ድርሰት፣ አፃፃፍ ዘዴዎች፣ ወዘተ. በአማርኛ ውስጥ አጥንተን ነው – በእስከ አሁኑ የኢህአዴግ. አስተዳደር ስርአት የመጣንው፤ ሌላ ቋንቋ ላይ የሌሉ ክሂሎትዎች እና እውቀትዎችን በአማርኛ አጥንተን ነበር። ከ ሀ ሁ አለማወቅ ተያይዞ ምንአይነት ጥራት ከእዚህ ይጠበቅ አለ? ይህ ትርክት-ዳራ መዛዥ አብነት ነው። እሚያሳየው በደፈናው ትምህርት ሲጀመር አካባቢ፣ ማለትም ታች ላይ የአለው፣ እውቀት ገበያ፣ ለትልልቁ እውቀት አብቂ አይሆንም፤ ይዘቱ አሰልቺ፣ አሰጣጡ ግድየለሽ፣ ፍሬነገሩ እጅግ-እጅግ ጠባብ ወይም ቁንጽል ስለእዚህ በክፉ ደረጃ የተበደለ ነው። ይህን ነውታ (claim) ለማጠንከር ለምሳሌ፤ ስለ አማርኛ ቀደም ብለው ህፃን-ታዳጊዎች በፊደል ገበታው መስራት እሚችሉአቸውን የቃላት ጨዋታዎችን አንድ ወይ ሁለት እንኳ አያውቁትም። ከፊደልገበታው ወደ ጽሕፈት ሲመጣ፣ የ40 አመትዎች ቀድሞ የነበረ የእጅ ጽሕፈትን ብንመለከት ወጥ የሆነ እና ለማንም እሚመበብ፣ የብራና ጽሑፍ ቁንፊ (font) የመሰለ እጅ ጽሕፈት በማንም ባይማርም እስከ ጥቂት ደረጃ ፊደል በቆጠረ አዛውንት ይገኝ አለ። የጽሕፈት ጉዳዩ መዝቀጥ፣ በእዚህ ዘመን ፊደልን ከማጥናት እንኳ የወረደ ትምህርት የእሚሰጥ ለመሆኑ ምስክር ነው። ፊደልዎቹን በበቂ ደረጃ ደጋግሞ መጻፍ ለመምህሩ ማስጻፉንም በተማሪዎቹ አይሞከርም ማለት ነው። ማንም ታዳጊ እንደ ልቡ ፊደልዎቹን በሆነ አመት ላይ ነው አጥንቶ የእሚፈጽመው፣ አጻጻፉን መልክ እሚያስሰጠው። ለምሳሌ፣ ከፊደልገበታው በተያያዘ ብዙ ችግርዎች ቢኖሩም፣ የአእምሮ ብስለት ለልጅዎች በጊዜ ለማስጀመር የፊደል እና ተያያዥ ብልሃትዎችን ለህፃንዎች መስጠት የእሚቻል ስርአተትምህርትአዊ ህልም የለም። (ለምሳሌ፦ ከ ሀ ለ መ… ፐ ድረስ በግእዝ ቤትዎች ብቻ ቃልዎችን፣ “ሰነፈ” “በረታ” ወዘተ. ብለው መፍጠር እና መጫወት፤ በሳድስ ሆሄዎችን ሳይደጋግሙ “ሂጂ”፣ ራብእዎችን “ማሳ”፣ “ሣጣራ”፣ “ቃታ”፣ “ማታ” (ቃታ ላይ ታ ስለአለ ማታ አይሆንም) ወዘተ. ብለው ወዘተርፈ በመሰሉ ጨዋታዎች እንኳ አያድጉም። ከፍቅረ ፊደል፣ ቋንቋ ደምለደም መግባባት፣ አእምሮ ብስለት፣ ትምህርትን በመዝናናት ስነልቦና መተዋወቅ፣ ፈጠራአዊ ትትረት ልማድዎች/ ንዑስ ባህልዎች መግባባቱ የአመልጥአቸው አሉ። የጧት ዓይንኣሩን የአልጠረገ አማርኛ ተሸክመው ክፍልዎችን በወል በመዘዋወር ከፍ ሲባል ሁሉም ትምህርት ለምሳሌ በደቡብ ክልል በታላቁ በቋንቋ እንግሊዝኛ ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ ይጀመር አለ (ጸሐፊው ሲማር ከሰባት ይጀምር ነበር)፤ ከአማርኛ ክፍለትምህርት (subject study) በቀር። አራተኛ ክፍል ድረስ ግን፣ ልጅዎች የተማሩት በአማርኛ ብቻ ሲሆን እንግሊዝኛ በአንድ ክፍለትምህርት ይሰጥ ነበር፤ ያም ገና እንጭጭ መሰረትአዊ የቋንቋው ክሂሎቱ እንጂ ገና የአልተመሰረተ ክሂሎት ሆኖ አራተኛ ክፍል የእሚጠናቀቅ ነበር። ከአምስተኛ እስከ አስራሁለተኛ ክፍልዎች በእንግሊዝኛ የጠጠረ ፍሬነገር ትውውቅ ጅማሮውን መማር ቢከወንም (በሂሳብ፣ ታሪክ፣ ወዘተ.) እንግሊዝኛ ቋንቋ ግን፣ 12ኛ ክፍል ላይ ተደርሶም እንደ መነሻ ደረጃ የእሚሰጥ ነው። አማርኛ ደግሞ ከቶ በመዘንጋቱ፣ ደርግ አስተዳደር እንኳ በአማርኛ “biology” ይተረጉም እና የአሳትም እንደ አልነበረ፣ አሁን ዶር. ደረሰ አየናቸው እንደ አሉት፣ በሌላ ቋንቋ ተምሮ ሌላው ችግር አሁንም ይደቀን አለ፦ በአሌላ ቋንቋዎች ወደ ስራ ይገባ አለ። (ለምሳሌ፤ እንግሊዝኛ እና ተያያዥ ክሂሎትዎችን ብቻ አምስተኛ ክፍል ላይ ሌላ ምንም ትምህርት ሳይሰጥ፣ እንዲማሩት እና ቋንቋውን አጥንተው ስድስተኛ ክፍል ወደ ፍሬነገርዎች እንዲገቡ አጭር ምክረ ሃሳብ ተነግሮ የአለው አንዲት መነሻ መውጫ መሆን የእሚችል ነው፤ እንደ ደርግ አስተዳደርም፣ አማርኛ መጽሐፍዎቹን እስከ ከፍተኛ ደረጃ ድረስ በመተርጎም በጎን በአንድ አቀራረብ መስጠት መከወኑም ሌላው እውነት ነው)]

አሁን ወደ ዋና ጉዳይአችን እንግባ። ጥቂት ከተገለጠ፣ ሙከራው፣ ወጥ የእውቀት አሰሳ እውነት አለመገኘቱን ለማሳየት ነው። ይህ ድምዳሜ በርትቶ በመገለጥ እንዲተባበረን የትምህርት-ውጭ አለሙን እናስምር። በሉሉ፣ ስልጣኔ ፈጥኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አለ። ይህ ስልጣኔ ወደ አልተመሰረተበት ወይም መዋጮ ወደእማያገኝበት ኢትዮጵያ በተለያዩ መጠንዎች እየተገዛ ወይም በእርዳታ ወይም በግንኙነት አይነትዎች የተነሳ ወደ ኢትዮጵያአዊ ጭምር ይፈስስ አለ። የገጠር ብዱል ታዳጊ እንኳ የሉል ስልጣኔ ጫፍዎችን ተሸራርፎ የማግኘት እድል ሁሉ አለው። በከተማዎችም ሆነ ገጠርዎች፣ ትምህርት በኢትዮጵያ ሲከወን የእሚታሰበው የእዚህ ስልጣኔ እውቀትን ማስጨበጥ ተብሎ ነው። ለምሳሌ፣ ኪነህንፃ የሃበሻ እውቀት የለበትም። እሚሰጠው የተለመደው የውጭው ደረጃ እንዲደረስበት ተደርጎ ነው። ሁሉም ትምህርት ከአማርኛ ወይም ሀገር ውስጥ ጥናትዎች በቀረ፣ ህልምአቸው አለሙን መምሰል ነው ወይም መኮረጅ ነው ተብሎ ይታሰብ አለ። መንግስትም ከሩቅ ምስራቅ አባቢ ኩረጃዎቼ ከፍተኛ ናቸው ብሎ በኢህአዴግ. አስተዳደር በተለየይ ይለፈፍ ነበር። ታች የደሉት ትትምህርትዎች ስለእዚህ ከ ሀ ሁ ሲጠነሰሱ ኢላማው በእነ ኤሲያ ነብርዎች ደረጃ ሀገር መስራች እውቀት ላይ ለማድረስ ነው። አንድአንድ እድለኛ ትምህርትዎች ይኖር አሉ፤ በተረፈ አብዛኛው ትምህርት ግን ከፍተኛ የእየሰዓቱ ለውጥን ይከውን አለ። አዳዲስ ግኝትዎች አቀራረብዎች፣ ወዘተ. ስለ አሉ፣ ትምህርቱ እነእዛን ማካተቱ የግድ ነው።

በኢትዮጵያው ተማሪ እግሮች ገብተን ወጥ የእውቀት አሰሳ ግን ተጨባጩ እውነት ለመሆኑን እንይ። ከታች እስከአራት ክፍልዎች፣ ፊደልዎችን፣ እንጭጭ መነሻዎችን እና መሰረትአዊ ትውውቅዎችን በደካማ አካሄድ እና ይዘት ይሞከር አለ ብለን አለ። አያያዙ ደግሞ በተግባሩ መታየ፣ በእዛ እድሜ ገደብ ማንም ትህርትን ከቁብ አይከትትም፤ የህዝቡ ልማድ ከታየ። ትምህርትቤት መዋል ከተቻለ በቂ ፍጻሜ ነው፤ ለብዙዎች በተለይ ልእለብዙሃን ለእሚሆኑት በእየገጠር እና አነስተኛ ከተማ ለእሚኖሩት ኢትዮጵያዎች። ትምህርቱ ጥራት የለውም ስለተባለ፣ ለጠነከረውም እንኳ የእሚያጀግን መነሻ አይሰጠውም። ብቻ ፊደልዎች ጋር መተዋወቅ፣ በከፊል ማንበብ፣ መጻፍ፣ እንግሊዝኛ ማንበብ መሞከርዎች፣ መጻፍ መሞከርዎች፣ ይከወን አሉ። በምኑም ሆነ ምኑ በጠነከረ መንገድ በስሎ መውጣት እና ወደ አምስተኛ ክፍል በስሎ በአራቱ ክፍልዎች የመመረቅ እድል የለመም፤ አንድም ትኩረቱ በማንም ዘንድ ማለት ይቻል አለ አናሳ ነው አንድም ጥራተ ትምህርቱ ደካማ እና ይዘትየለሽ ማለት የእሚቻል ነው

ከአምስት እስከ አስረኛ ክፍል፣ የታቹ መሰረት ጋር አይጣጣምም። ታቹ እስከ አራት አሰሳው አማርኛ ውስጥ ነበር። ጎበዝ የሆነው፣ በእንግሊዝኛ ከደከመ፣ በጉብዝናው ከቶ አይቀጥልም። የቋንቋ ክሂሎት በአለመገንባቱ ብቻ ከጨዋታው ውጭሆን ይጀምር አለ። በአማርኛ አጠናን ዘዴው፣ ሂደቱ፣ ወዘተ. በመናጋቱ፣ የትምህርት እውነቱ መናጋት በብዙዎች ይደርስ አለ። እሚጠቀም አለ፤ እሚጎዳ አለ። በእንግሊዝኛ የበረታበታ ከአምስት ጀምሮ የመንሰራራት እውነት ይከውን አለ። እንግሊዝኛን ብዙዎች ግን ይደክሙበት አለ። በእየጉራንጉር ትህርትቤትዎች የእሚያድገው ኢትዮጵያአዊ በርትቶ ለመማር እሚያግዝ እውነት የለውም። ማለት ይቻል አለ በተቻለው ብቻ ለመጓዝ ይገደድ አለ፤ ከእሚፈለግበት በታች፣ በቻለው ሁሉ። የተቻለውንም እማይከውን አለ። ይህ ከግለሰቡ፣ ቤተሰቡ፣ የአቅራቢያ ማህበረሰቡ እውነት፣ ትምህርትቤቱ፣ ወረዳ ወይም ቀበሌ አስተዳደሩ፣ ወዘተ. አንጻርዎች ነው። በከተማዎች አስጠኚ መቅጠር፣ እንግሊዝኛ ቅላፄ ወደ እሚያምርበት ትምህርትቤት ማስተማር ቢዘወተር እንጂ ስለይዘቱ መጨነቅ የእማይከወን በመሆኑ እገዛ ይደግ ቢሉ እኒህ የተማሪው አቅራቢያ አካልዎች አቅምም የለአቸውም፤ ማዳበርም አያስቡም። በእየገጠሩ እና አናሳ ከተማዎች ደግሞ፣ ተማሪዎች ሲመረቁ ብሔርአዊ ከፊል-ህግ በሆነ ባህል “…አስታውሳት እማማን..ሳይደላት…” ይባል እና በመመላለስ እንጂ በሰለጠነ አያያዝ ተማሪው አለማደጉን ይመሰከርለት አለ።

ከፍ እየተባለ ሲመጣ፣ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ከመግባት ቀድሞ፣ አብዛኛው ትምህርት እና ተማሪ ጎበዝ ከተሰኙት እሚልቁት ቁጥርዎች በሽምደዳ ጽንሰሃሳብ ወይ ፈሊጥ የእሚመጡ ናቸው። ሽምደዳ፣ ቋንቋውን አብዝቶ አያቅም። እንደ ስልክ ቁጥር፣ መረጃውን መመዝገብ በቂው ነው። መረጃ ደረጃ እውቀት ይወድቅ አለ። እውቀት ከማሰስ በመረጃ ደረጃ እውቀቱን አውርዶ በማነብነብ በደህና ውጤት የመጓዝ እውነት አለ። ይህ የብዙሃኑ ጎበዝ ተማሪዎች ምስጢር ነው። በሌሊት ተስቶ ለማስታወስ እንዲቻል ደጋግሞ የመማር እውነታ የአለው ገሀድ ነው።

የሰነፈ፣ ያንን አይከውንም። የጎበዘ፣ መረጃ በእሚሰኝ ደረጃ ተምሮ የአዘግም አለ። ጥቂቱ እውቀት እንዲሆነው የተማረውን፣ በእውቀት፣ አንፋሽአዊ ደረጃ (inspiration level)፣ እብስልስል (contemplation)፣ ወዘተ. በመከወን ለማወቅ በመጣር ይነሳሳበት፣ ይሞክርበት አለ። በሶስት ረድፍ፣ ተከማችቶ ከፍተኛ ትህርት ተቋም ይደረስ አለ ማለት ይቻል አለ። በሶስት አይነትዎች የትህርት እውነትን ማሰስ ገሀዱ ነው ማለት ነው። የትምህርት እውነቱን በወጥ እና አንድኧዱ ከሁሇሁ ጠቃሚው መንገድ ማስኬድ የለም። ይህ ከቶ እውነት ነው። ዳግምርምር (research) ለልኮት (refernce) መጥቀስ አይቻል ይሆን አለ። ግን ይህ መመርመር የእሚችል እውቅ ፀሐይየሞቀው ሀገርአዊ የትምህርት አሰሳ እውነቱ ነው።

በከፍተኛ ትህርት፣ የእሚሻል ውይይት እና ዳግጥናትዎች አሉ። ጥራት የለም የእሚለው ወሬ ከፍተኛ ነው። አስተማሪዎች አያበቁም። ግን ከተማሪው እግርዎች ሳይወጣ እውነታው ከእሱ አይንዎች አንፃር ይታዩ። አሁን፣ የከፍተኛ ትምህርቱ የጠበበ ወይም የአተኮረ ነው። አብዛኛው ሽምደዳአዊ አመጣጥ በትኩረት የተነሳ የእሚሰምጥ ትምህርትን መያዝ ይከብደው አለ። የበረታ መሸምደድ፣ መፈተን ይቀጥል አለ። እውቀት አሁንም መረጃ ነው። ላይ የተጠቀሱት ዶክተር እንደ አሉት ይህ ዋና ገጽታ ነው። አጭር ጽሑፍ ተሰጥቶ ያንን አንብቦ ማስታወስ ከብዙዎቹ ይጠበቅ አለ። ይበቃ አለ ተብሎ ይደመድ አለ። ያ በመምህሩ ይከወን አለ፤ ከላዩ ያንን መሰል እውነት ተቆጣጣሪ አይታይም። ያ ክፍተት ነው። ቢሆንም፣ አብዛኛው እውነት ያ እንደ ሆነ፣ አንዳንዴ በተለይ በአንድ ወይም ሁለት እና መሰል ተቋምዎች፣ ወይም ደግሞ በአንዳንድ መምህርዎች ብቻ፣ ከፍተኛ የእውቀት መንገድን እሚከተል አስተምህሮት ለተማሪው ይገጥመው አለ። ያ የተለመደ አመጣጡን ዳግመኛኛ የአናጋው አለ። ለምሳሌ፣ ተማሩዎች ለመጀመሪያ ጊዜ እውቀት ማደን ከጀመሩበት ሀ ሁ ለቀማ ወዲህ እራስአችሁ አንድ ነገር አድርጉ ይባል አሉ። ወይም መምህሩ የእሚያስተምረውን ቀንሶ ውይይት ይጀምር አለ። ይህ በዐድ ነው። ትንግርት ነው። ለኢትዮጵያው ተማሪ፣ ጎበዝ ለተሰኘው እና እየተሞካሸ በማስታወስ አቅሙ እየተመዘነ በመሸለም ለእዛ ደረሰው ይህ አዲስ መናጋት ነው። እሚሸመድደው እሚያስታውሰው፣ በእዛም ተመዝኖ እሚያገኘው እውቅና አዎንታአዊነት የለም። ግራአጋቢግራአጋቢ የትምህርት አሰሳ እውነት በኢትዮጵያ።

በእዚህ ተገቢ እሚሰኝ፣ እንደ ተገቢው አያያዝ፣ ግብረመልስአዊ አሰጣጥን እሚከተለው መምህር ከቶ በታች ደረጃዎች የእማያገኙት ነው ማለት ይቻል አለ። በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትዎች እሚገኘው ደካማ ትምህርት “አሰጣጥ” ወደ ትምህርት “ፍለጋ” ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርስ አለ። አንዳንድ መምህር ርህራሄ አጥ ሆኖ በቃ አንብቡ በቃ አድምጡኝ አይልም። ተገቢውን ነገር ብትዘገዩም እዩት ይል አለ። ያኔ ጎበዝ የተሰኘው እንኳ ሰነፍ ነው። ነፃ አመለካከት፣ ስነአመክንዮአዊ እውቀት አፈላለግ፣ ይበረታታ አለ። መጠየቅ ይበረታታ አለ። ይህን ከዋኝዎቹ እጅግ ቁንጽል መምህርዎች የትምህርት አሰሳ እውነት በኢትዮጵያ ውስጥን አዲስ እና ከፍተኛውን ደረሃ ይዘው ከስንት አንድ እንደ መስቀል ወፍ ይመጣ አሉ። ተማሪዎች በመምህሩ ከአመኑ የተማርኩት ሁሉ ከፍተኛ ክስረት ደረሰበት ይል አሉ። የአልተማርኩ መሆኔን አሳሰበኝ እሚሉት መምህር ብዙ ባይሆንም አለ። ያ ከፍተኛ እና መናቅ የእማይገባው ሀገርአዊ ህፀፅ ነው። የተማሩትን ዞሮ መናቅ ማለት የመጡት የሀሰት ነበር ማለት ነው። የጎለመሰ በአለበት ሀገር እውቀት አስስ ተብሎ በልጅነቱ በተጠራው ንፁህ ዜጋ ገና እውቀት ማሰሱን አንድ ምእራፍ ሳያደርስ በእዚ ደረጃ መክሰር ከደረሰ በስርአት እና ሀገር ተደጋፊ ሀጢያት ነው። ተማሪነት በጉብዝና ተለይቶ እየተንቆለጳጰሰ ሽምደዳ ሲባረር ያ ድል ከሌለ ምን አይነት ወጥ መንገድ የአለመዘርጋት እውነት ተማሪን እየአስጨነቀ ነው? አንዴ በአንድ ቋንቋ ሲያስሱት ከመቅጽበት መቶ እጅ በእሚሰኝ ለውጥ እውቀቱ ወደ ሌላ ቋንቋ ይሰደድ አለ። የውሃውሥጥ ዓሣ ሆኖ ትምህርቱ ይከዳ አለ።.የአሟልጭ አለ። የአልጠጠረ እድሜ የአለው ተማሪ ይህን ማጥመድ እንዲችል ምንም ግብዓት በመደበኛነት አያገኝም። ዳሩ፦ አሁንም ፀንተው ግን ቢይዙት፣ መምህር እና ስርአቱ አንብቦ ለአስታወሰ መቶ ከመቶ እሸለመ የትምህርት አግጣጫውን ወደ ሽምደዳ የአስኮበልለው አለ። በአዲስ ምዘናው እየጎበዘ የፈረጠጠውም፣ ጎበዝ ነኝ ብሎ በተቀነሻሸቡለት መረጃዎች ማስታወስ አቅሙ ከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ሲደርስ፣ ህሊና ከአለው የእማይዘነጋው ገሀድ ተለውጦ ይቀበለው አለ። ማስታወስ ችሎ የሸመደደውን ሲያወጣ፣ እንዲመራመርበት እና በአገኘው መረጃ አንዳች እይታ አብጅ ይባል አለ። የአልገጠመው ሆኖ ዞሮ ወቃሽ፣ ተናዳጅ ይሆን አለ። እስከ እዚህ ስንማር ምነው አላስተማሩን አስብል እውቀት አሰሳን ሊመለከት ይችል አለ።

ወጥ የእውቀት አያያዝ ጠፍቶ፤ በሸዋጅ አካሄድዎች “ተምሮ” ከተመረቀ፤ ወደ ስራው አለም ይገባ አለ። ያኔ፤ በየትኛው የትምህርት ቅርፅ እውቀቱን ይመነዝር አለ? ስራ ፈጣሪነት እሚለው ቅዠት እንደሆነ አለ። ለእዛ አብቂ ትምህርትም የለም ይባል አለ። የአለውም ግን እንደ አየንው በወጠ3 የትምህርት ባህል አይሰጥም። በአንድ መንገድ የአላደገ ዛፍ ደግሞ የምን ተጠባቂ ስኬትን ይሰጥ አለ? ስራ ፈጠራን ደግሞ ከሀገር አውድ መመልከትም የለም፤ እንደ አኗኗር እውነት፤ እንደ አጠናንም። ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም በ ዛሬም እንደ ትላንት? ስለ ትምህርት በአነሱበት ምእራፍ ተማሪው፣ ለአካባቢው ችግርዎች መፍትሔ አፈላለግ እየተማረ አያድግም ይል አሉ። ያ፤ ፈጠራስራን እምናይበት መንገድን ይነሽረን አለ። ከምንም በላይ መንግስት አስተዳደርዎቹም ፕሮፍ. መስፍን በመጽሐፉ በተለያየ ቦታ ደንቆሮ እንደ አሉአቸው፤ አንድ ቦታ ተማሪው ስራ አይፈጥርም ይሉ እና አንዱ ቦታ ዞረው ከውጭ እሚገቡ ምርትዎችን ከለላ በማለት እንዲቀሩ ህዝቡም ስራ ፈጣሪውም ተማሪ አስተማሪውም ቀለል በአሉ ምርት እና አገልግሎትዎች እንኳ በሀገርቤት እንዲሞክር አያደርጉትም። ይህን አስተዋይ ትልምአግጣጫዎች (policies) ከፈጣሪነት መጥፋት ትችቱ አይገጣጠምም።

ዋናው ነጥብአችንን ዳግ-እናንሳ። የተማረው ተማሪ የት አገልጋይ ነው። እውቀት አሰሳው እየአሟለጨ አለመገኘቱ በመቀጠል ሀገር ማወናበዱን ይከውን አለ። አንዳንዱ በእየመደበኛው (ስራአጥ ቁጥር ቅነሳ) በእሚል አስተዳደርአዊ እርምጃዎች ስራ ተፈጥሮለት ለጥቂት ደሞዝ የሆነበት ይሸነቆር አለ። አንዳንዱ፣ እውቀቱ እማይበቃው ስራን የአገኝ አለ። በሙያአዊ ስፍራዎች አንቱታ የእሚያተርፍ እንዲሆን አብቂ መነሻ አላገኘም እና በሙያው አለም ባይተዋር ይሆን አለ። ይህ ተግባር ተኮር ትምህርት ከቶ ባለመኖሩ፤ የኢትዮጵያ ትምህርትዎች ፍልስፍና ምክኑያዊነት (rationalism) እንጂ ተሞክሮአዊ (empiricism) በአለመሆኑ ነው። የቱም አስተማሪ ተቋም እኔ ተግባር የእሚትነው ተግባር የእሚመራው የትምህርት ፍልስፍና እከተል አለሁ አይልም። ሁሉም አስነብቦ፣ አስሸምድዶ፣ ማስታወስ አቅምን ብቻ በእሚያሰኝ መንገድ ፈትኖ እና መዝኖ ቢበዛ አንዳንዴ በተገቢ ምክኑያዊነትን ተግብሮ በመጠይቅአዊ አተያይ ተማሪ አምራች ነው።

ያንን ገትተን ወደ ቀደመ ነጥብ ዳግእንመለስ። አንዳንድ ተመራቂ፣ በአስተዳደር ጉዳይዎች መድከም የተነሳ፣ ከሙያ ነፃነት ይጋጭ አለ። ያም ሌላ መንገጫገጭ ነው። እውቀቱን ለመተግበር እሚከልለው ብዙ መሰናክል አለ። በተለይ በህዝብ ማገልገያ ሙያዎች እንደ ምንም አውቆ የወጣው ለምሳሌ አቃቤህግ ቢሆን በህግ እና ስርአት ለማገልገል ከፍተኛ የመንግስት አስተዳደር ጣልቃገብነት ስለእሚኖር ይህ ችግር ይበዛ አለ።

በሽልፍኖት (technology) የተመረቁ ደግሞ፣ ወጥ እውቀት በአለመታደኑ ሲወጡ፣ በእየቀኑ እሚጓዘው የፈጠራ አለምን ብዙዎቹ ለማወቅ እንኳ ይቸገር አሉ። ከእዚህ አንፃር የአለው መጋጋጥ ከፍተኛ ነው። አንዳንድ እውቅ እና ታጋይ መምህርዎች አለም ዛሬ የደረሰችበትን የክፍለትምህርትአቸውን እውቀት መቸር ይፈልግ አሉ። በከፍተኛ ጥረት ጥቂት እውቀት ከሰጡ፣ ሲወጣ ግን እውነቱ ሩቅ ነው። ሀገር ገና ኋላቀር ናት። በለጋ እድሜ ሰርቶ ከእውቀትአቸው ሀገሩን ለማስታረቅ ይቸገር አሉ። በልምድ መሪ ደረጃ ሲደርሱ እውቀትን ትተው ለእንጀራ ሲል አገልጋይ በመሆን ይቀር አሉ። እውቀቱ ይባክን አለ። ተያይዞ፣ እሚማሩት ለድሀ ሀገር እውነታ ሳይሆን ለረቀቀ ቅንጡ ሀገር ይመስል እውነታውን ትምህርትቤትዎች አያስተምሩም። እውቀቱ ቅንጡነትን የአመቻች አለ። እውነታውን አያንጸባርቅም። ተመርቀው ስራ አጥተው የተመቻቸ እረፍት የአለው ከፍተኛ ብር ከፋይ፣ የተረጋጋ ወዘተ. ተብሎ በእሚገለጥ መንገድ ስራ ከአላመጣ የእሚተገበር እውቀት የለንም ባይ ትውልድ በዝቶ አለ። ትምህርቱ መሰረተ እውቀት በአለማስጨበጡ፣ ከስር ጀምሮ የመስራትን ጥበብ አብሮ አያቀብልም። የተሰጠው እውቀት ታች ወርዶ መስራትን አያካትትም። “የደሞዝ ይስጡአቸው ማመልከቻ” ብቻ እስኪ መስል፣ ተቀምጦ ደመወዝ መፈለግን እሚያበረታታ እውቀት እሚታደንበት የሀገር እወነት እንደ በዓሉ ግርማ አገላለጥ “ቆሻሻ እጅዎች መፈለግ” ሆኖ ሳለ ይህን እውነት ጆሮዳባ የአለ እውቀት አደና ነው። የኢትዮጵያ የትምህርት አደና እውነትን የካደ ነው።

የትምህርት እውነቱ፣ መልሶ ረብየለሽ እሚሆንበት ሌላ አጋጣሚ በሰለጠነ አለም የትምህርትአቸው ሙያ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ተመርቀውበት ትምህርቱን ግን የእማያውቁት የአክል ተግባሩ ይርቅአቸው አለ። በሌላ መሰል ክስረት፣ በስነልቦና ተመርቀው ለምሳሌ በስነልቦና ሙያ ለመስራት እድል እሚያገኙት ግን እጅግ ቁንጽል ይሆን አሉ። በአልሰለጠኑበት ሙያ ለመስራት ይገደድ አሉ። የእውቀት አደና እማይጨበጥ ዓሣ ሆኖ ጭራሽ ትምህርት ትግበራው ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይሆን አለ።

ወጥ የትምህርት እውነት በሀፖ (ሙሉበሙሉ ወይም ከመጀመሪያ እስከ ፍፃሜ) የሹፈት፣ ማላገጥ፣ ይመስል አለ። ሀ ሁ መቁጠሩ እና መተየቡ ሳይጠጥር፣ እንደ ተኬደው ተኬዶም አንድ የትምህርት ፍፃሜ ሲደረስ፣ ሌላ ገሀድ ገልባጭ ክስረት ይከተል አለ።

በዋናነት፣ ቁንጽል ሃሳቡ ወጥ የትምህርት ጉዞ ወይም አያያዝ በመጥፋቱ፣ በኢትዮጵያ የመማር እውነት የወደቀ ሆኖ መማር ሂደቱ ይፈጸም አለ። ወጥ አያያዝ በመጥፋቱ፣ ጎበዙ ሰነፍ፣ ሰነፉ ጎበዝ የመሆን እድሉ በከፍተኛ ደረጃ አለ። ያ፣ የግጭቱን ነውጠኛነት የአሳይ አለ። ሽምደዳ የእሚቀናው፣ ፈጠራአዊ አመለካከት ወይም እይታ ከእሚቀናው፣ ቋንቋ ለመማር የእሚከብደው፣ ቋንቋ እንደ ተራ ክሂሎት ከእሚሰርጽለት፣ የተለየ በጎ መምህር ከእሚገጥመው ግድየለሹ እውቅ አስሸምዳጅ መምህር ከእሚገጥመው፣ ወዘተ. በተምታታ አካሄድ ወጥ የትምህርት እውነት ማጣቱን ይከውን አለ።

መውጫው ግንባርስጋ ነው። ይህ የኢትዮጵያ የእማይታይ ቢታይ ቁብ የእማይቸር ገሀድ ነው። ውጤቱ ቋሚ ክስረት ነው። እንደ ሆነው። እንደ ተለመደው። ማስተካከያውም በወፍበረር ተመዥራጭ እንጂ አዲስ አይሆንም።

ከልጅነት እስከ ፍፃሜ የተሰናሰለ አስተምህሮት (ይዘት እና ስርአት) ይፈልግ አለ። በእየመልኩ ደግሞ፣ እውቀት አተገባበሩ መሰናሰል አለበት። አያይዞ አጋዥ እና ግዴታም የሆነው የሀገር እውነትንም የማካተት ጉዳይ አስገዳጅ ነው።

ተመርቆ መደበኛ ዜጋ የሆነ ስለ ሀገር ውስጥ መሰረትአዊ እውነት እና እውቀት የማወቅ እድልን ማግኘት አለበት። ፕሮፍ. መስፍን እንደ አሉት፣ ከአካባቢ ችግርዎች የእሚበቅል እና ሀገርአዊ እውነትዎችን እየአመራመረ የእሚያሳድግ ትምህርት የአስፈልግ አለ። የታቹን የትምህርት ገበያ ከመካከለኛ ያን ከከፍተኛ ደረጃዎች ወጥ አድርጎ ማሰናሰል የአስፈልግ አለ። ምዘና ከሽምደዳ መንገድ ወደ እብስልስልታአዊ (of contemplation) እና ሀቀኛ ምክኑያዊነት፣ ተሞክሮአዊ እና ሀገርአብቅልአዊ ጎዳናዎች መመለስ አለበት። ነካሪ (immersive) አስተምህሮት ከታች እስከ ፍፃሜው መዘርጋት አለበት። የትምህርት ይውሰዱታ (takeaway) ወይም ይዘቱ ከድህነቱ እና ከፍተኛ እድሉ ተያያዥ መሆን አለበት። አለምም ከደረሰበት የእውቀት ማማ እሚታከክ ትምህርት ባይሰጥ፣ የተቀራረበ አለሙን እሚያስተዋወቅም ትምህርት ግዴታ ነው። ተመርቆ፣ አለሙን በርቀት መመልከት የተማሩበትም ትምህርት ሆኖ ለወቅቱ አለም ለአላት የሙያው ደረጃ እንግዳ መሆን ትምህርቱን አለሙን የእማያስጨብጥ የአደርገው አለ። እውቀቱ አሁንም ዓሣ ነው አምላጭ ነው። ለቀልድ እና ማሟያነት እሚሰጡት በቁምነገር የንቃተህሊና ግንባታ እድል ሆነው ማለፍ አለብአቸው። ድህረ ምርቃት በስራ ደግሞ ከእዚህ ጉዳይ ውጭ ቢሆንም፣ ወጥ እውቀት አደና ከተደረገ ወጥ ወደ ስራ ወይም ትግበራ ቅልቅል እውነታው እንዲሆን ከትምህርቱ ውጭም ብዙ መከወን አለበት፤ ምንም የአክል ጠቅላላ አስተያየት እንደ ሆነው፤ ጠቅላላ እንቅስቃሴ እጦት ገላጭ ጭምር ነው።

ውሃውስጥ ዓሣ የትምህርት እውነት ኢትዮጵያን እንደ ጎዳው አለ። ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ተምሮም ሀገርን አላበለጸገም። ለታሪክአዊ አንዳንድ ከፍታዎቹም መጣኝ እውነት በትምህርቱ አልተመረተም። ሊጨበጥ የድሚችል በወጥነቱ የእማያታልል ትምህርት መፈለግ አለበት። ሀገርን፣ አለምን፣ እና ሙያን የእማይከዳ እውቀት አደና ሂደት መቋቋም አለበት። በአጭሩ፤ አንድ ኢትዮጵያአዊ ተማሪው፤ በልጅነቱ የእሚያገኘው ትምህርት ከመካከለኛ ትምህርቱ፣ “ከከፍተኛ ደረጃ እውቀት አደናው” እጅግ የተራራቀ ነው። በመመረቅ እውነት አለሙም በተማረበት ቦታ ከፍተኛ ርቅቀት ይዛ ትቀልድበት አለች። አስተዳደርአዊ ኋላቀርትም፣ የአለ ጥቂት መብቃትዎችን የአኮሽሽ አለ። እነእዚህን መሰናስልዎች በማረም፣ ተገቢ ውጤት እና ተፅዕኖ ከትምህርት አለም መጥራት የእሚቻል ነው፨


By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s