Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ብሔርአዊ ድሀነትን በአዲስ ጎዳና፡ ትምህርት እና ስራን ድሀነት ተኮር ስለማድረግ

About how Ethiopia shall reassign administrative and education-work world in accordance with contextual truth of the poorest nation.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 10, 2021GC.,

Get this on PDF.

ከትምህርት እና ስራ ፈጠራ አንጻር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግርዎች አሏት። እነእዚህም፣ ወደ ተሻሻለ አኗኗር እንዳይደረስ አድርገው አሉ። የሰላሳ አመትዎች ጉዳይዎችም እጅግ የአላጠገቡ ጉዞዎች ነበሩ። የተለየ መንገድ መፍጠር አስፈላጊነቱ ግልጥ ነው።
መንግስት ተማሪዎቹን ሰነፍ ጎበዝ በእሚል ምዘና ወደ ተግባር እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋምዎች ይሰነጥቅ እና የአሰለጥን አለ። እነእዚህ ተመራቂዎች ሲመረቁ የእሚሰሩት ስራ ፍለጋ ሲሆን በአሉ ግርማ እንደ አለው “እስክናድግ በቤተሰብ ትከሻ ስናድግ በመንግስት ትከሻ እንንጠለጠል እና እንኖር አለን።” (ከአድማስ ባሻገር)። ይህ ተመራቂን ስራ ሲሻ መንግስት አንድ መወተፊያ ስፍራ የማበጃ አመራር ትልምአግጣጫ( policy) አለው። ስራ ፈጠራ በእሚል መስሪያቤት እና ካድሬ ሁሌ ይገመገም አለ። ለዜጋው ስራ አመቻችቶ በቢሮው ሰው የአስቀጠረ የመስሪያቤት አስተዳዳሪ የእሚጠቀም ነው። ካድሬዎችም ወለፀጥታ በእሚል መናኛ እና ሙያ የእማያማክል ተራ ስራ ቦታ ማስፈለግ ወዴታአቸው ነው። ይህ ሀገርን እየሸወደ የአለ ተርታ ድል ነው። አስተምሮ ማስመረቂያውን ጉዳይ ለኢትዮጵያ በተቻለ የተለየ አግጣጫ መውሰድ ተገቢ ነው። ሀገርበቀል ትምህርት ከማስተመር በተያያዘ ሀገር አብቅል ትምህርትም (build-nation education)፣ መከወን አስፈላጊ ነው። በስነልቦና ለምሳሌ በሺህዎች በእየአመቱ ቢመረቁም በስነልቦናው አገልግሎት የእሚሰሩት የቱን የአክሉ ናቸው? በሌላ ሙያዎቹስ? ይህ ሀገርአዊ ክስረት፣ ስነልቦናአዊ ውድቀት፣ ሙያአዊ ውርደት ነው። መንግስት ለስነልቦና ምሩቅዎች እሚሆን የተለየ አግባብነት የአለው ስራ ዘርፍ እንኳ እንደ አለው አይታይም። በግል ዘርፍም ስንልቦናአዊ አገልግሎት ንግዱ የወረደ ሀገር በመሆኑ ይህ ሁሉ ተመራቂ የት ይገባ አለ? እንደ ብዙው ትምህርት ዘርፍ በተገኘው ስራ አጊንቶ ደመወዝ መፈለግ እንጂ ሀገርን አገልጋይ ስርአት የለም።
ቀላል ጉዳይ ለመንካት የአክል፤ ይህን ጉዳይ ከትምህርት እንጀምረው። ከሙያ እና ከፍተኛ እውቀት ትምምርትዎች አንጻር ብቻ ተማሪው የእሚገጥመው የመደልደል ጉዳይ ጎጂ ነው። ሀገርአዊ ትልቅ ገሀድን አይመለከትም። ነገርግን፣ የተማሪዎች አቅም መለያየቱ የታወቀ ነው። የተለያዩ ትጋትዎችን እንዲያመነጩ ማሰልጠንም ተጠባቂ ነው። ግን፤ አሁን የአለው ሀገርን ለማሳደግ አይችልም። ምደባው ድህነት ተኮር ትምህርት፣ መካከለኛው አገልግሎት ትምህርት፣ የከፍተኛ ትምህርትዎች ተብሎ በመሰረትአዊ ደረጃዎች መከፋፈል አለበት። ይህ ሁለተኛ ደረጃን ትምህርት ሲጨርሱ የእሚገኘው አስተምህሮትአዊ አማራጭ መሆን አለበት። ከፍተኛ ትምህርት ውስጥ የተለዩ ደረጃዎችንም ማበጀት ተቻይ ነው። ለኢትዮጵያም ገሀድ ግድ ነው።
ለምሳሌ፣ ከየትም የተመረቀ ትልቁ የከፍተኛ ደረጃ ተማሪ አንዳንዴ በግል ብቃት ከአልሆነ በቀረ አለሙ የደረሰበትን እውቀት አያገኝም። የሀገር አሰለጣጠን፣ በተደረሰበት ደረጃ እንጂ አለም የአለውን እውቀት ሰጪ አይደለም። ለምሳሌ በሳይንስ ዘርፉ፣ ስለ ሮቦትዎች፣ አንድሮይድዎች፣ ወዘተ. እሚመራመር እእና ዛሬ በዘርፉ የተደረሰበትን አለምአቀፍአዊ ጫፍ የእሚቀላቀል ተማሪ ማፍራት አይታሰብም። በህክምና ምርምርም፣ ካንሰር ወይም ቫይረስን መመራመር እና አለም በእነዛ ዘርፍዎች የደረሰችበትን እየመሩ የእሚገኙ ተማሪዎችን ማፍራት አይታሰብም። ተማሪዎች፣ ቢጎብዙም በመደበኛነት፣ ተቀጥሮ በደህና ደረጃ ለማገልገል እንጂ አለሙ የአለበትን ደረጃ እሚመሩ እና እሚቀላቀሉ አይሆኑም። ይህ ሀገርአዊ ተጨባጭ ሀቅ ነው። ግን፣ ሀገር ይህን ተማሪዎች ማፍራት የአልቻለችው ጎበዝዎች አጥ ሆና አይደለም። የአለም ሙያዎች ማእከል በአለመሆኗ ነው። እንደ አንደኛው አለም የአንድ ትምህርት ዘርፍ ፈርአመራር አይደለችም። በየቱም ዘርፍ ቀዳሚነቷን አልያዘችም። ምርጥ ተማሪዎች እሚወጡት ተጓዳኝ የንግድ፣ ምርት እና ባህል አመራር በአሉብአቸው ሀገርዎች ነው። ምርትም፣ የአገልግሎት (ለምሳሌ አረብ በህክምና አገልግሎት ትልቅ ቱሪዝም በመፍጠር በመምራት ደረጃ ነው)፣ በሌላውም ደረጃ አለሙን ሀገርአችን አትመራም። መሰረት፤ ጎበዝ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ አለምአቀፍ የኢትዮጵያ ጉዳይዎችን እንዲበረቱበት ማሰልጠኛ የተለየ ተቋም ቢገኝ ይመከር ዘን እነሆ ነው። በእዚህ ተቋም በእየሙያዎቹ ሁሉ አለም የደረሰበት ደረጃ ላይ ኢትዮጵያዎችን እንዲገኙ እና የሀገር ብሌን መሆን እንዲችሉ እና አለሙን ከሀገር አንጻር እንዲደርሱለት የእሚሰለጥኑ ቢሆን በጎ ነው። እነእዚህ ልዩ ተማሪዎች፣ በየቱም ሙያ አለሙ የደረሰበትን አውቀው፣ ተመራምረው በመማር እንደሀገር ለአለሙ ጉዞ በማንአንሼ ደረጃ ቢሆንም አቅም ማበርከትም ለመቻል ይችሉ ይሆን አለ። ወይም፣ ለአስተዳደርዎች፣ ወቅትአዊ አዝማሚያዎች፣ ወዘተ. በተለየ መንገድ፣ አሁንአዊ ጉዳዩን በመመርመር ምክር ለማቅረብ ይችሉ ይሆን አለ። ለተቋምዎችም ማማከር ይችል አሉ። የተቀሩት ምሁር እና ተማሪዎ በአሉበት ይቀጥል አሉ ብለን እንሻገር።
በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አቅምአቸው አነሰ ተብሎ ወደ ከፍተኛ ትምህርት እና ዕድ መካነእውቀት (vocational colleges) ይገባ አሉ። አቅም የአለው የሌለው ብሎ በውጤቱ ከመለየት፤ አካሄዱን ማስተካከል የአስፈልግ አለ። የውጤት ልዩነት እንደ አለው እና ምርጫዎችም እንደ ተጠበቁ፣ ስርአቱ ግን በተግባረ ዕድ እና ከፍተኛ ትምህርት ከመከፋፈል፤ ወደ ጊዜ የእሚገድበው ክፍፍል ይምጣ። ሀገር በስነምጣኔ እና አስተዳደር አቅሟ እስክትነቃቃ፣ መሠረትአዊ ትምህርት ክፍልዎች ወይም የድሀነት ተኮር ትምህርትዎች ተብለው ታች የአሉት ይለወጡ። በስሙ መቀየሩ ከቅርጽ እና ፍልስፍናው መለያየት ይቀጥል ዘንድ የሆነ ነው። በእዚህ፣ እሚማሩት ሀገርን በመሰረትአዊ ጉዳይዎች ወደ ተሻሻለ አኗኗር ለማምጣት ይሆን አለ። ከለየለት ድሀነት ለማላቀቅ እሚያገለግሉ እንጂ አለም በቅንጦት ደረጃው በደረሰበት ደረጃ እና መርኅ፣ ወይም ይዘት ተምረው ወደ ተደላደለ ተቀጣሪነት ጉዞ ለመውጣት ከእሚያስቡ፣ ወደ ስራ ፈጣሪነት ይጓዙ። ያም የግልአቸው ሳይሆን፣ የመንግስት ስራፈጠራ ነው። መንግስት እና ህዝብ ሀገር ለእየእለቱ እንዲያስተዳድሩ የእሚያሰለጥንአቸው ናቸው። የእሚሰሩት ቀድሞ ይታወቅ አለ። ያም ሀገርን እና ደሀ ህዝብን ከወደቀ አኗኗሩ ማነቃቃት ነው። ለመደበኛው የአገልግሎት መስመር አይማር አይመረቁም። ህዝብ በማስተማር፣ በእየኑሮ ችግርዎቹ በንቃት በአጠገብ መሆን በመርዳት፣ መሰረትአዊ ቁሳቁስዎችን በርካሽ በማምረት (እንደ ወንፊት፣ ማንደጃ፣ ወዘተ. የአሉ መሰረትአዊ ቁሳቁስዎች እነእሱም ምንም ለሌለው የእሚያግዙ ናቸው። በረዥም ጊዜ ህዝቡ ከለየለት የከፋ ኑሮ ሲላቀቅ፣ እጅግ መሰረትአዊ ፍላጎትዎች ተብለው የተጠኑትን እንዲያስተናግዱ ተደርገው እኒህ አግዘው ለውጥ ሲገኝ ወደቀጣዩ ማማተር ብሔርአዊ ጤነኛነት ነው።
አብሮ፣ መንግስት የተለያዩ ተቋምዎችን ማዘጋጀት ይገድደው አለ። የመሰረትአዊ አኗኗር ቁሳቁስ አምራች ተቋምዎች፣ የመሰረትአዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተቋምዎች፣ ወዘተ. በእየመንደር ጉራንጉሩ አስፈላጊ ናቸው። ተማሪዎቹ በእነእዚህ በማገልገል፣ ሁሉ ኢትዮጵያአዊን ከከፋ ድህነት እንዲአላቅቁ መስራት እንዲችሉ ህዝብ ይቀጥርአቸው አለ ማለት ነው። እሚሰሩአቸው መሰረትአዊ ስራዎች ግን ለተለመደው ከተሜ አይሆንም ቢያንስ በመደበኛነት እና ሲጀመር። ለእየዜጋው – በተለይ ለተገለለው – ከሽንት ጨርቅ፣ ማንኪያ፣ ጀበና፣ ማንደጃዎች፣ ወንፊት፣ ሽሽትቤት እቃዎች፣ ቁሳቁስዎች ወዘተ. ጀምሮ በማምረት በረከሰ ዋጋ መሸጥ አሉብአቸው። በብዙ ምርት ትርፍ ስሌት ሀገርን ከለየለት ድሀድሃ አኗኗር ለማስተካከል እንዲችሉ መስራት እሚችሉ ገሀድ ተኮር የድሀነት ተኮር ትምህርት አግጣጫውን ተከትለው በመመረቅ የአገልግሉ። ወደ መደበኛኛ ደረጃ ገቢዎቹ ወደ ተለመዱ ተቋምዎች በመግባት የተለመደ አገልግሎትን ይስጡ። የተጠቀሱት ልዩ ተማሪዎች ደግሞ፣ ሀገር እጅግ ኋላ በመቅረቷ አለሙ እንዳያመጣት በጥቂቱ ለመካሪነት፣ አማካሪነት፣ ሀገር አንቂነት፣ ወዘተ. ተለይተው በመብሰል የአገልግሉ። ይህ ሁሉ ተጨፍልቆ በመሰጠቱ ግን ሀገርን በእየዘርፏ ለማገልገል አስቻይ ትምህርትአዊ ስርአት አለም። ብዙው ኢትዮጵያአዊ ስኳርን አያውቅም። ከሰልማንደጃ የለውም። ሽንትጨርቅን አይሸምትም። ጥቀከት ኢትዮጵያአዊ በውጭ ምንዛሬ ውድ እቃዎችን ይሸምት፣ ቅንጡ ኑሮ ይሞክር አለ። መደበኛ ከተሜው የተዘበራረቀ ስንምጣኔአዊ አቅም ይዞ አለ።
ትምህርት ስርአቱ፣ ከሀብታም እስከ ድሀድሃውን እኩል አገልግል ይባል አለ። የሀገር ደረጃን ለማዘመን ይህ አዋጪ ሳይሆን የቆየ ነው። ትህርትንም ከተግባር የአላስተሳሰረ ማታለያ እንደ ሆነ ነው። ሙያን አገልጋይ ህብረተሰብ ውስጥ እሚገባ ተማሪ አስመራቂ ስርአት የለም። ሙያአዊ ተገልጋይ ህዝብ አልተመሰረተም። ስልጣኔ ኋላቀር የሆነበት ሀገር ነው።
ህዝቡ፣ እሚፈልገው መሰረትአዊ ጉዳይዎች ሳይሟሉለት ከቀጠለ ሙያ እማይጠይቅ ነው። በልቶ ማደር ብርቅ በሆነበት ሙያአዊነት ዋጋ አጥ ሆኖ አለ። አቅምም የለም። ሸመታው ታች የቀረ እውነት ነው።
እንዲህ ከሆነ፣ ለእዚህ እውነት ተመጣጣኝ ትምህርት ስርአት ተገቢ ነው። ተመራቂዎች መስሪያቤትዎችን በፖለቲካ ጫና አለአግባብ እየቀጠሩ ሊፈነዱ ከእሚደርሱ፣ በአሉበት ጥራትን በማደን እንዲጓዙ በመተው፤ አቅሙን ወደ ድሀነት ተኮር ህዝብአዊ ንግድ መመለስ ተገቢ ነው። በአጭር አመትዎች የሁሉም ኢትዮጵያአዊ አኗኗር ከለየለት ድንቁርና-መር-ድንቁርና-ወለድ አኗኗር ወደ ተሻሻለ አኗኗር መመለስ ይችል አለ።
የሀገር ልማድአዊ እውቀትዎችም በሂደት ወደ ዘመነ ደረጃ እና ከፍተኛ አምራችነት መለወጥ ይችል አሉ። በሂደት አምራች ህዝብን መፍጠሩ አጭር ጊዜ ውስጥ ይሳካ አለ።
አስፈላጊው ነገር የምርት በውጭ ገንዘብ መንዝሮ መግዛቱን በከፍተኛ ደረጃ ማስጣል ነው። ይህ ለተመራቂው እና ቁጥሩ ለበዛ ሀገር አስገዳጅ ነው፤ እንኳን ድሀድሀ ለሆነው ህዝብ። መንግስት ድሀድሃ የሆነ ህዝብ በኑሮ ሲቸገር፣ ብርም አጥቶ መሰረትአዊ ቁምነገር መግዣዎችን (እንደ መድሃኒት) ሲያጣ፣ ዘይትን እና ነጠላዎችን እንኳ ከውጭ በምንዛረሀ እንዲገዛ አድርጎት አለ። ምንም ስነምጣኔአዊ አቅም የሌለው ህዝብ ተምሮ ይቀመጥ፣ ከሙያውጭ ይታፈን አለ። አገልግሎት ምርት ይበላሽ እና ይቀር አለ። ተማሪውን አምራች ማድረግ አማራጭ የለውም። አምራችነት ከተፈጠረ፣ ስራአጥነት ይቀንስ አለ። አምራችነት እእንዲጠነክር ሀገርን ከአለምአቀፍ ንግድ መከልከል ከፍተኛ እርምጃ ነው። ስራአጥነቱ የበዛው፣ በፖለቲካ ጣልቃገብነትም የውሸት የእሚታከመው፣ ተገቢ የትምህርት እና ስራ ትስስር ስለሌለ ነው።
መሰረትአዊ ቁስዎች በዶላር ከእሚገዙ እና ስራአጥነት ከእሚቀጥል፣ መሰረትአዊ ቁስዎችን ለማምረት በመሰረትአዊ የድህነት ተከፐር ትብርትዎች ተምሮ በህዝብ ቀጣሪነተወ ወደ ስራ መግባት ቢቻኧእ፣ ብሩም ተቆጠበ፣ ስራም ተፈጠረ፣ ሀገርም በተጨባጭ ከፍታ አገኘ።
ትምህርቱ እንዲሰምር፣ ከውጭ መግዛት ጉዳዩ ይገታ። የተማረው አምራች ሆኖ ይጠመድ አለ። በሂደት ውጭ መሸጥ እንዲቻል ድሃድሃነቱ ሲረግብ፣ ትምህርቱ ከድሃድሃነት ተኮር መሰረትአዊ ትምህርት ወደ መካከለኛ ማህበረሰብ ተኮር ትምህርት መቀየር ይችል አለ። ሂደቱ በግሉ እየታረመ ከፍተኛኛ ደረጃን መድረስ ይችል አለ።
ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም በዛሬም እንደ ትላንት? እንደ አሰመሩት በ”2030ዓም. 250ሚ. ህዝብ እንሆን አለን። ያኔ እግዘሀር ይሁነን”፤ ያንን መቅሰፍት መሰል ጠቢ በእዚህ አያያዝ ከመጓዝ እና መጠበቅ፣ ትምህርትን እና ስራን ለሀገር ገሀድ ብቻ አገጣጥሞ ዳግ-መቃኘት ይቻል አለ። ሁለንተናአዊ ለውጥ ከእዚያ ይመዘዝ አለ፨


Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s