Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

መሠረተልማት፡ አስተዳደርአዊ መጥፎ ቃል

About how the past 30yrs have purposefully been erroneous for narrowing the notion of “fundamental development” into physical infrastructures building and ditch human and administrative developments.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 07th 2021GC.,
ኢህአዴግ. አስተዳደር፣ ሸዋጅ እና መጥፎ ተፅዕኖ የአለው ቃል አስለምዶ ነበር፦ መሠረተ ልማት። ይህ ለሰላሳ አመትዎች የተደጋገመ ቃል ነበር። እዚህ ጎሣ ግዛት ላይ መሠረተ ልማት አናሳ ነው። እዛ ደግሞ መሠረተ ልማት እየገነባን ነው። ወዘተ. ቁልፍ ቃል ነው።
በመሠረቱ፣ ይህ ቃል ትርጉሙ ምን ነው? መሠረተ እና ልማትን ከመግጠም ቀድሞ እንደ ምእላድነትአቸው እንፍታአቸው። መሠረተ የመሠረት ውላጁ የአንድ ግንባታ አካል ማረፊያው የመነሻ አካሉ ነው። የነገር ሁሉ ውጥኑ ወይም ጅማሮው ማለትም ነው። ይህ በቂ ነው። ልማት፣ ማለት የኑሮ ሚዛንን በመድፋት ወይም የአኗኗር ደረጃ (living standard) ለውጥን በማሳካት እውነት ውስጥ መገኘት ማለት ነው።
መሠረተ ልማት፣ በኢህአዴግ. አስተዳደር ትርጓሜው ከ ግንባታ ጋር የተቆላለፈ ነው። የመኖሪያ ቤትዎች፣ መንገድዎች፣ ህክምና ጣቢያዎች፣ ትምህርትቤትዎች፣ ወዘተ. የመሠረተ ልማት ማሰሪያ ትርጉም ናቸው።
ይህ እጅግ ሰቅጣጭ አወዳደቅ ነው። መሠረተ ስህተትዎች የታቀፈ አረዳድ ነው። ሆን ተብሎ የተዛባ ከፍተኛ ሀገር ክህደት ነው።
ለምን? መሠረተ ልማትን በሰፊው ለአለመቀበል የተደረገ ዝብአረዳድ ነው። የኢህአዴግ. አገነዛዘብ በእንግሊዝኛ፣ “infrastructure” ነው። በእንግሊዝኛው የቀረበው፣ የመሪያም-ዌብስተር (2020ግዓ.) ፍቺ

“the basic equipment and structures (such as roads and bridges) that are needed for a country, region, or organization to function properly”

ይል አለ።
መሠረተ ልማት ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ሲመለስ “foundation of development” ነው። የልማት መሰረቱ ደግሞ፣ ቁሳቁስአዊ ትኩረት አይደለም። የስርአት፣ የአእምሮ፣ ባህል እና ተያያዥ ጉዳይዎች መልማት ይቀድመው ወይም የግድ በከፍተኛ መጠን ይመሰርተው አለ።
መሠረተ ልማት፣ በቁሳቁስ ስነስርአት አይገኝም። መሠረተ ልማት በንቃተህሊና መበልጸግ፣ ሰብእአዊ መብትዎች መከበር፣ ተጠያቂ እና ግልጥ መንግስአትአዊ አስተዳደር በመኖር፣ ፍትህ እና እሪና በመስረጽ፣ እውቀት እና ነፃነት በመከማቸት፣ የእድልዎች መስፋፋት እና መገኘት፣ ወዘተ. የእሚገኝ እውነት ነው።
ኢህአዴግ. መሠረተ ልማትን በግንባታ ቋንቋዎች የቀየረው፣ በፍፃሜው የጠራ የዜጋዎች ለአለማምረት ነው። ዞረው የስልጣን ቁንጢጡን ይነጥቁት ስለሆነ የአሉትንም ይጸየፍ አለ።
መሠረተ ልማት የአእምሮ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ እውቀት፣ ንቃተህሊና (በተለይ የጋራ/ህዝብአዊ)፣ ነፃነትዎችከ ወዘተ. እና የስርአትዎች መስተካከል ከሆነ፣ መንግስትአዊ አስተዳደሩ እነእዚህን ለመካድ እና ለአለማልማት፣ መሠረተ ልማትን በ ግንባታ አጀማመር (infrustructure) ለውጦ አውቆታአዊ ዝብአረዳድ (itentional misunderstandig) ከውኖበት አለ።
መሠረተልማት ተዛንፎ እንደእሚተረጎመው፣ በብልጽግናም በመቀጠሉ ከፍተኛ አደጋ በሀገር ግንባታ ትትረቱ አለ። ለአንድ ህዝብ የልማት መሰረት በባይከዳኝ ገብረህይወት (ነጋድራስ) እንደተገለጠው፣ እውቀት ነው። ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያምም፣ ወጣት ትውልድ በእውቀት ለምቶ ሀገር እርሱ የአልማ የአሉት፣ (ዛሬም እንደ ትላንት)፣ እውቀት የልማት መሰረት በመሆኑ ነው። በእውቀት ደግሞ አለም ብዙ የደረሰበት ደረጃ አለ። ንጽውሳኔ (democracy)፣ ስልጣኔ፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽ አሰራርከ ህዝብአማነት (republicanism)፣ ወዘተ. መሰረተ ልማት ናቸው። በንጽውሳኔ የእማይታወቁ የምስራቅ ሀገርዎች እንኳ ለሰብእአዊ መብትዎች፣ ባህል፣ ስነምጣኔ፣ እውቀት፣ ወዘተ. ከፍተኛ ትኩረት ስለሰጡ የልማት መሰረት ፈጥረው አሉ። እራስአቸውንም በከተማዎች (infrastrucres) ለመገንባት ችለው አሉ። ንጽውሳኔ ባይኖርአቸውም ከፍተኛ የሀገር ፍቅር የለአው፣ ከንጽውሳኔ በላይ ምእራቡ ይማረው የድሚሰኝ የተጠያቂነት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ባህል ተቆጣጣሪነት፣ ስንምጣኔአዊ ተቆጣጣሪነት፣ ወዘተ. ይዘው ንጽውሳኔአዊ ጉድለቱን ተክተው አሉ። መሰረትአቸው ከቶ ግንባታ አይደለም እና መሰረተ ልማት እሚሉት ኢህአዴግ. ልኮርጀው የአለው የእውቀት እና ትምህርት ስርአት ጭምር ነው። መሰረተ ልማት ተብሎ በኢትዮጵያ ግን፣ ሀብትን በመበዝበዝ በከፍተኛ ወጪዎች፣ እዳዎች እና እርዳታዎች አንዳንድ ነገርዎችን መገንባት ነው።
የእውቀት እና ጥበብዎች መሰረት የነበረች ሀገር፣ የረዥም እድሜ የተጫጫናት ድረስ የሸመገለች ሀገር፣ መሰረተ ልማት ብላ ግንባታዎችን በማስተኮር አመለካከት ማዛባት መሞከሯ ከፍተኛ ታሪክአዊ ጸያፍነትም ነው። የጥንቱ ከፍተኛ ስልጣኔ፣ በግንባታ አንድ ዘርፉ አደገ እንጂ (ያም ለእዚህ ትውልድ መሰረተልማትዎችቻ አያያዝ ትንግርት የሆነ ነው፣ የእነ ላሊበላ ውቅርዎች ከፍተኛ ጥበብ በመሆኑ ቆሻሻአቸው እንኳ አልተገኘም የዛሬ መሠረተ ልማት እሚሉ ከተማዎች ግንባታአቸው ቆሻሻ በቆሻሻ የሆነ ነው ብሎ ዲን. ዳኔል ክብረት፥ ሙዐዘጥበባት፥ እንደ ተቸው፣ የ”መሠረተ ልማት” አቅምአቸው የበፊትዎቹ ከፍተኛ፣ ሀገርበቀል እና ታሪክመሪ እንደሆነ አለ) ትኩረቱ እውቀት፣ ጥበብ፣ ልህቀት ነበር። ዛሬም፣ ለመላው አለም ትንግርት ሆኖ የእሚጠና እውቀት የአበረከተ ስልጣኔ ነበር። ለእዚህ ትውልድም የኩፋት ምንጭ የሆነው፣ የጥንቱ ሀገር የለማው በእራሱ የእውቀት እና የግንባታ አቅም ነበር። አሁን ልማት መሰረቱ፣ ከውጭ በእሚገቡ ስነምጣኔ አኮምሻሽ ወጪዎች እና እዳዎች ጥቂት ነገርዎችን መገነባባት ከሆነ፣ ይህ ከፍተኛ ዝቅጠት ነው።
መሰረተ ልማት፣ ፊቱ በዋናነት ወደ ህዝብ እና አስተዳደር እንደ ዞረው ወደ ግንባታ አይዞርም። ከቶ ከእዛ የራቀ ነው። ራስንበራስ ማስተዳደር የልማት ሁሉ መሰረት ነው። እኩልነት እና ፍትህ የልማት እናት ናቸው። ሀገር ለምቶ በጥንቱ ዘመን የነበረው ከመንገድዎች እና ውስጥአቸው መሳለቂያ ከሆኑ ትምህርት ጊቢዎች ውጭ ነው። ቀድሞ መተኮር በእገቡአቸው፣ የመሰረተልማት አላባአዊያን ሀገርን መጥመድ ሲገባ አስተዳደሩ ያንን ማከናወን አይችልም። በሙስና እና እጅግ ደካማ አስተዳደርአዊ አፈፃፀሙ ብቻ በስልጣኑ ለመቆየት ኢላማው በመሆኑ፣ መሠረተ ልማትን በቁስ ግንባታ ጉዳይዎች የአስተኮረ ሆኖ አለ።
መሠረተ ልማትን በአግባቧ እና አግጣጫዋ ፈትቶ መስተካል አስገዳጅ ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s