Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

“ህልውና ዘመቻ” ላይ የጋዜጠኛዎቹ ከባድ ተኩስዎች

About how Ethiopian journalists fake war scenes in battle correspondence with fake heavy military machine shots behind them bursting in the historically and nationally crazy Hilwuna Operations.

በመጀመሪያ፣ እስከ ሰባት ወርዎቹ ቀውሱ “የህልውና ዘመቻ” በተለመደ የፕሮፓጋንዳ አዘጋገብ ቢሮክፍል ተቀምጠው ይዘግቡት ነበር። የተነገረአቸውን፣ ሁሉም መገናኛብዙሃንዎች ወደህዝብ የአስተጋቡ ነበር። የተለየ ጋዜጠኛነት ከመስኮተድምጽ (radio) እና ትመ. (Tv)፣ የአየሁት የተለየ አዘጋገብ በመረጃ ትመ. ብቻ ነበር። ያም በዲን. ዘመድኩን ነጭነጯን መርሐግብር ላይ አንዳንዴ የተሰረቁ የተስ. (ተንቀሳቃሽምስል) ቀረጻዎችን የአሳይ ነበር። (ለምሳሌ፣ “ወታደርዎች” ተብለው በአጭር ቀንዎች ስልጠና የዘመቱት መሳሪያ ሳይይዙ ከፊትከፊት ሆነው ሲዋጉ ነበር፤ ከጀርባ ዋናው ሰራዊት በትልልቅ መሳሪያዎቹ ተኩሶ ከፊት ለአሉት በሉ ሂዱ ተመትተው አሉ ጥይት (ል)ቀሙ ይሉአቸው እና ሲሄዱ የተደበቁ የህዋሃት. ተዋጊዎች በጥይት (ትልቅ መሳሪያዎች አልነበሩአቸውም) ይለቅሙአቸው ነበር። ይህን አሳዪ የአሉትን ምስል የቀውስ ውጊያው ድንገት ተዋጊዎች ቀርፀው ሰጡኝ ብሎ የአስመለከተው ተስ. በ ሐምሌ ወር ነበር። በተረፈ፣ ምንም ምስል በተለይ በቀጥታ ዘገባ አልተመለከትንም።

አፍንጫአችን ስር ጦርነት አመት ልደቱ ሲከበር የአስመለከተን መገናኛብዙሃን አልነበረም። ግን በሃምሌ ወር አካባቢ አንዳንድ ትመ. ጣቢያዎች ወደ መስክ ዘገባው ተላኩ። ጦርነት ከእየአለበት ለመዘገብ ብለው ቢነሱም ለወር የተመለከትንው አስቂኝ ነገርዎችን ብቻ ነበር። ይህ ውጊያ በሁለተኛ ዙሩ (ማእከልአዊ መንግስት ተሸንፎ ከመቀሌ መውጣት ጀምሮ)፣ መደበኛ ውጊያ ከቶ አልነበረም እሚሰኝ ነው። (ህዋሃት. ትግራይ ክልል ተለቅቆለት ተረክቦ አለ፤ ሰርጎገብ ህዋሃት (TDF)፣ ጥቂት ሰዎች ድንበር አስዘልሎ ወደ አማራ እና አፋር ክልልዎች እየላከ በእየከተማው ደርሰው፣ መንግስት በማበሳጨት ቀድሞ በተገለጠ ኢላማ መሰረት ደራሽ አደጋ ጥለው አያይዘው እንደ አበሳጭ ፕሮፓጋንዳ ብቻ፣ ከተማውን ተቆጣጠርን በእሚል ወሬ የአስነግር አሉ፤ እቃዎች ሰርቀው ይሰወር አሉ፣ የቀረውን ከብት ሳይቀር ገድለው አውመድው ይሰወር አሉ። የመሀከልሀገር “ህዝብ” (በተጨባጭ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደአሉት የገዥ ድርጅት) መገናኛብዙሃንዎች ለአስርቀን ከተማ መቆጣጠሩ ውሸት ነው በማለት ለመሀከልሀገር ለማረጋገጥ እና ድሉን ተቀብለንው አለ በማለት ከክስረቱ በኋላ ህዝብ የአደነቁር አሉ። ጋዜጠኛዎቹ ከሃምሌ ጀምረው በሰርጎገብ ጥቂት ቡድንዎች ከተያዘ በኋላ የተለቀቀ ከተማው በመሄድ “ይኸው በወታደሩ፣ በአካባቢው ወታደር ትግል ነፃ ከተማ ነው!” በማለት (በውጊያ) ከበባ ተይዞ የተፈታ ከተማ ይመስል እንደ ታላቅ ድል ይዘግቡት አለ። በአለማቋረጥ፣ ለቀንዎች። አራት ሰርጎገብ ቡድን ከተማውን ድንገት በማድፈጥ ገብቶ በተኩስዎች አምሶት የወጣ ነበር፣ እንደ ብዙወወ አጋጣሚ እውነቱ ግን። ሰርጎገብ አንድ ተቋም ላይ አደጋን ሲጥል፣ ወይም የመረረ ሆኖ ደራሽ-አደጋው በሆነ መደር ንፁሀንን ሲተኩስ እሚዘግብ የለም። ቆይቶ ሰላም ሲሆን “ተሸንፈው ሄዱ…”፣ ወይም “በጭካኔ አጥፍተው ሄዱ…” ብለው አሁን ዋናው ነፃነት ነው መከላከያ ከተማውን ተቆጣጥሯት አለ በማለት ለአንድ ሁለት የማህበርአዊ ድረገጽ “ህዋሃት ከተማዋን ያዘ!” ማበሳጫ ወሬ ሳምንት ድረስ ውሸትነቱ ይዘገብ አለ። ይህኛው አንዱ የመስክ ዘገባ ሆኖ እየቀጠለ ነው። በእዚህ መስክዘገባ ትርጉም ሰጭ ጋዜጠኝነቱ የለም ማለት ይቻል አለ። ሊያውም አልፎአልፎ እንጂ ወደ ደራሽ-ተጠቂ መንደር በግርግሩ መሀከል ድርሽም ማለት የለም። ህዝብ የቀረጸውንም፣ የአየውንም ማቀበል እማኝ ጠቀሳ የለም። ለምሳሌ ጳጉሜን 04 በኢቢሲው. ኢቲቪ. ምሽት ዜና ዘገባ፣ በዋግኽምራ ብሔረሰብእ አስተዳደር ዞን ፀአግብጂ ወረዳ እጅግ በከፋ መልክአምድር ተቆርጦ ከመሀከልሀገር በመገለል በእሚገኝ መንደር አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የአስገነባው ትምህርትቤትን ህዋሃት. ሰርጎገቦቹን ልኮ አፈረሰው በእሚለው ዘገባ፣ ለውስጡ አትሌቱ በቤቱ ቃለመጠየቅ ተደርጎለት ይህን ለኢዜአ. ተናግሮ ነበር፤ (ታች የዘገባው ትይብ ከማንበብ እዚህ አድምጡ)

“[የዋግኽምራ አካባቢ ለረዥም ዘመናት ልማት ርቆት የተረሳ አካባቢ ነበር]…መንገዱ ስትሄድ ሳት ካልክ ገደል ብትገባ ሬሳህ የእማይወጣበት መንገድ ነው። የሄድንበት! በተለይ ከሰቆጣ ወደእዛ [ዋግኽምራ ብሔረሰብእ አስተዳደር ፃዓግብጂ ወረዳ] የሄድንበት ወደ 50ኪሜ.ዎች የእሚሆነው በጣም ዘግናኝ የሆነ ቦታ ነው። እዛ የአለ ህብረተሰብእ፣ እዛ…ያ ህብረተሰብእ ‘ኦልሬዲ’ ጥቃት ከደረሰበት፣ ያ ህብረተሰብእ ‘ኦልሬዲ’ ከወደመ ቆይይቶ አለ። አሁን በእዛ በእንትኑ … ቁስሉ ላይ… እንደገና እንዳይነሳ የእምታደርገው እንጂ እኔ በሄድኩ ጊዜ በጣም አዝኜ ነው፦ ‘እውነት ይሄ ህብረተሰብእ የኛ አካል ሆኖ(?) እውነት አደገች በምትባል ሀገር እንደ እዚህ አይነት ነገር አለ ወይ?’ እምንልበት ነው። እና፤ ‘ሪሊ’ በጣም ይነካ አለ።”

ትምህርትቤት በሁለተኛ ዓመቱ ከተጠቃ እና ፈረሰ በኋላ፣ “ህልሜ ተሰብሮ አለ፤” በማለት እጅግ በመረረ ሀዘን ለመንደሩ ማዘኑን ሲገልጥ የቀረበ ምስሉ ግን ተማሪዎች የከበቡት ደስ የእሚል ትምህርትቤትን ማስመልከት ነበር። ወድሞ የተተወ ምሰሉን ለማሳየት ወደእዛ የሄደ የለም።

ይህ ተትቶ ዋናው የውጊያ ዘገባውን ሲያስተላልፉ በወጥነት የእምንመለከተውን እንይ። ያም፤ ዘገባውን ዘግበው፣ ሲያበቃ አካባቢ ቆመው በፊትለፊትአችን ይናገር አሉ። ህዋሃት. እየተሸነፈ ነው፣ ወዘተ. ከአሉ በኋላ፣ ከጀርባአቸው ወይም አጠገብአቸው ትላልቅ የጦር መሳሪያዎች ይታዩን አሉ። ከባድ መሳሪያ ኃላፊ ወታደሩም፣ ከጓደኛዎቹ ወደ ጋዜጠኛው ይመለከት አለ። ልክ ዘገባ ሊጨርስ ሲል ግንባር ነኝ ለማለት እንዲመቸው ከምስሉ ውጭ በተስማሙት መሰረት አንዴ በትልቁ ቢኤም ከባድ መሳሪያውን ወደ ሰማይ ይተኩስለት አለ። ሽሽሽሽ…ድድድድምምምምምም!!! ለእዚህ ጦርግንባር ዘገባ ለእከሌ እከሌ ነኝ ብሎ ፈገግ እየአለ ይቋጭ አለ። (ለምሳሌ አሚኮ. በጳጉሜ አምስት ዜና ስርጭት አንዱ ዘገባ፣ በ”ወሎ ግንባር” “አሸባሪው ትህነግ እንዳይወጣ እየተሰራ ነው፤” አርእስቱ ሁሉን አሳዪ ነው። [ስር ‘ጋለሪ’ውን ይዩ] ሰርጎገቡ ቡድን ሳይታይ ሰርጎ አለ። ውጊያ የለም። እንደ ተለመደው ተደብቆ ደራሽ አደጋውን ጥሎ ሊወጣ ሲያስብ አድፍጦ በመጠበቅ በአለበት በህገወጥ መንገድ ጨርሰው ለመግደል እና ለመቅበር የአስብ አሉ፤ (በእዚ ሳይሆን በእየዘገባው አማራ ክልል መቀበሪያው ነው፣ አናስወጣውም፣ አናስተርፈውም፣ እንደመስሰው ብቻ አለ በማለት ከውጊያ ህግ ውጭ የማንም አይተርፍም ፈሊጥ የተንፀባረቀበት ዘገባ ነው)። ዘገባው በአጭሩ ዘጋቢው ደጀን አምባቸው፣ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ማእከልአዊ እዝ 6ኛ መካናይዝድ አባላትን በወሎ “ግንባር” አግኝቶ በሰላም ድባብ ከብበውት በእየተራ በከባድ መሳየያው በ ቢኤም ላይ የቡድን ሃላፊነት ወስደው በጋራ እንደእሚሰሩ ወዘተ. ገልጠው የገቡ ሰርጎገብዎች እንዳይወጡ የአቅምአቸውን በርትተው ስለመስራት ግዳጅአቸው ነገሩት። እንደ ቀደመ ዘገባው፣ ያ ዘገባ ሲቋጭ ግን በከፍተኛ መሳሪያ ተኩስ መዝጊያ ነው። ምንም በሌለበት ለዘገባው ማሞቂያ።

ጦነርቱን እንዳይለምዱበት በማግለል ይመስል፣ ሴት ዘጋቢዎች የሉም። ወንድ ዘጋቢዎቹ ግን፣ በእየ ተገኙበት “ግንባሩ” እየተሽሎከሎኩ በአውዱ የአለነን እውነት በመዘገብ አያሳዩንም። “አሁን የኛ ወገን ተኮሰ…!” ወይም “አሁን ወታደሮቹ እሚያልፉት ወደ እሚመቱበት ድብቅ ስፍራ ነው እየተከተልኩአቸው ነው….” አይነት ዘገባ የአሉአቸውም። የአለውን ተግባርአዊ ውጊያ ከቶ አያስመለክቱም።

ማንም፣ ምንም በሌለበት ወደ ሰማዩ አስተኩሰው ዘገባ መጨረስ ለምደውት አለ። ይህ ብዙ ስጋት ይጭር አለ። አንደኛ ለ”ጋዜጠኛው ልቤን ነካው…” እውቅ የአስራዘጠኝዘጠናዎቹ ዘፈን እሚመጥን የውጊያ ትክክልኛ ልብአንጠልጣይ ዘገባ የለም፤ ህዝብ-አታሎት (public deception) አለ። ኢስነምግባርአዊ። ኢሙያአዊ። ሁለተኛ፣ አለአግበብ የህዝብ ሃብት መቀነስ አለ፤ ተኩሱ ከፍተኛ ወጪ ይወስድ አለ ተብሎ ይገመት አለ፣ በውጭ ምንዛሬ ይገዛ አለ። እነእዚህ አይነትዎቹ ተኩስዎች የውሸት ናቸው! ለህዝቡ ማታለያዎች ናቸው። አታላይዎቹ ሰራዊቱ ጭምር በጋራ ቢሆኑም በዋናነት ለህዝብ እናሳይልአችሁ ተኩሱልን ባይ ሰነፍ ጋዜጠኛዎቹ ናቸው። ተገቢ ዘገባ እንደ ሙያው ፍላጎት ከአልሰጡ ወደ መስክ መሄዱ ለክስረት ፍፃሜ እየሆነ ነው። የጋዜጠኛዎቹ ከባድ መሳሪያዎች ተኩስዎች ኦዲት ቢደረጉ ተገቢ ነው። ለሰራዊቱም ሆነ ለጋዜጠኛዎቹ ኢስመምግባርአዊ ተግባርዎች (unethical practices) ናቸው። ውጊያ ዘገባ እውነት ውጊያ መዘገብ እንጂ ማታለያ ተኩስ አይደለም። ያ የጋዜጠኛዎቹ ተኩስዎች ናቸው። ወደማን? ቀውስ ጦርነት፣ ቀውስ ዘገባ፨

—– & —–

ምሳሌ፤ ታች የእሚታየው የተስ. ገጽማያተኩስ (screenshot) ዜናውን አበበ እሸቱ ሲያነብብ፣ ያው የጽሑፍ ዜና በውይይት ሲዘገብ ያው ጽሑፍ ዜና በተኩስ ቡንን እያለ ሲደለባቅ የአሳይ አለ ያም ከላይ የተጠቀሰው ዘገባ ነው።

This slideshow requires JavaScript.

Also read this article of Berhanu Gebremariam.

2 replies on ““ህልውና ዘመቻ” ላይ የጋዜጠኛዎቹ ከባድ ተኩስዎች”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s