Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

አዲስ ኢትዮጵያን ናፍቆት፡ ሰባቱ ዋልታ መሠናክልዎች

About Seven basic issues Ethiopia shall see deeply to basically civilize as of today.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 03rd 2021GC.,

Take this on PDF.

ኢትዮጵያ ገና አልተመሰረተችም። በጥንቱ ስልጣኔ ሀገር ነበረች ቢባል ትርጉምሰጭ ነው። በሂደት ግን ስልጣኔ በምድሯ ከጠፋ ወዲህ ዘመንአዊ የሀገር ትርጉም እማይገልጣት ሀገር ሆነች። ዘመንአዊው የሀገርነት ፍልስፍና በዘመነ አብርኆት ከተፀነሰ ወዲህ፣ ከጥንት ታሪክዎቿ የተፋታች እና ዘመነ ስልጣኔ የረሳች ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አልንበረችም – ማረጋገጫው፣ ዘመንአዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት – ማለትም ኢትዮጵያን ከአዲስ ለመስራት ከግልአጥፊው አፄ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ ምንይሊክ ካልእ ሲሞከር የነበረ በመሆኑ ነው። ዘመንአዊት ኢትዮጵያ ግን፣ በቀኃሥ. ዳግ-ተፀንሳ፣ መወለድ እንኳ ሳትችል ደርግ ከእዛም ኢህአዴግ. በማስተዳደሩ በመናጠቅ እየተቀባበሏት እዚህ ደረሰች፤ ዛሬ ድረስ ዘመንአዊት ሀገር የለችም።

ህዝብ የሀገርፍቅር አለው። ዘመንአዊ ሀገር ግን የለውም። በኢትዮጵያ የታጡ ዘመንአዊ ሀገር ዐብይ መነሻዎቹ ምንምን ናቸው?

፩) ወጥ የሀገር ድንበር አገነዛዘብ የለም

በዓለምአቀፍ ህግ እንደታወቀው፣ የድንበር እና የህዝብ አንድ ስነልቦንታ (psyche) መኖሩ ነው። ይህ በኢትዮጵያ የአልጠለለ ጉዳይ ነው። ከቀይባህር ተሻግሮ በዐረብ ምድር ኢትዮጵያ ነበረች። በህንድ መስመርም ኢትዮጵያ ምድር አድርጋ ትገዛ ነበረች። በሂደት ቀይባህር የተሻገረ ድንበር ራቀ። በሂደት ቀይባህር እራሱ ራቀ። ዛሬም፤ የመገንጠል ወሬዎች አሉ። ማለትም፤ ድንበር በወጥነት አልተመሰረተም። ህዋሃት. ትግራይን ሊገነጥል በጣረበት፣ የ2012-13 ውጊያ ይህ ሲታይ፣ ይህ የአልጠራ ጉዳይ እሚያስመለክተው፣ የፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም “በየት ዞረን በምን ተቀልብሰን እዚህ ቅዠት ደረስን [ከቀይባህር የተሻገረ ድንበር ትተን አሁን ወደ አለንበት ደረስን]?” (መስፍን ወልደማሪያም፣ ዛሬም እንደ ትላንት? ገ.16)፣ የሀገር በአስተማማኝ መንገድ ለዘመንአዊነት የአለመመስረትን ነው።

፪) ስነውሳኔ (politics) ወጥ አግጣጫ የሌለው ነው

ሁለተኛ ገና የጠለለ የስነውሳኔ አግጣጫ የለም። ሀገር በአንድ የሀገርነት እና ህዝብነት ቃልኪዳን አልተመሰረተችም። ስነውሳኔው በመከታተል በቅርብ አስተዳደርዎች እየታየ እንደ ቀጠለው ሀገርን ከማገልገል ለጥቅም በመሯሯጥ የተመረዘ ነው። ስርአተ ጭሰኛነት፣ በስርአተ ካድሬ ዛሬም የአለው ገሀድ ነው። አንዳንዱ ገንጣይ፣ አንዳንዱ ነፃ የአልወጣ ጎሳ አለኝ እኔ ለብቻዬ የተጨቆንኩ ነኝ ብሎ ነፃ አውጭ፣ አንዳንዱ ሀገር እኩል አልለማችም፣ አንድ መፍትሔ የአሻ አለ ብሎ ለሀገር ለመስራት ተጣጣሪ፣ ወዘተ. የእሚሆንበት የተንኮታኮተ ስነውሳኔአዊ አውድ አለ። ያም አምባግነና እና ኋላቀር ህዝብ ይዞት ማደግ የአልቻለ ነው። በአጭሩ፤ ፕሮፍ. መስፍን እንደአሉት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት ኖሮ አያውቅም፤ (ገ.55)፤ አንድ ድሀ ሀገር በብዙ ሺህ ፖለቲካ ድርጅትዎች መወከሏ የገንዘብ መሰብሰቢያ እንጂ ሀገር ማገልገያ ድርጅትዎች አለመገኘትአቸውን የአሳይ አለ ብለው ሲደመድሙ፤ በአንድ ወቅት አንዲት አፍሪቃአዊ እንስት፣ በአደጉ ሀገርዎች ሁለት ሶስት ፖርቲዎች አሉ፣ በእኛ አህገጀር ብዙ ተቃዋሚዎች በመቶዎች አሉ፣ የንፅውሳኔ (of democratic) ትግበራ የአለው እኛ ጋር ነው በማለት እንቀልድበት አለነደ ብላ ነበር፤ ያም የአፍሪቃ ንጽውሳኔ ጉዳይዎች ውይይት ላይ የተካሄደ ነበር። ኢትዮጵያም ድሀ ናት። ችግርዎቿን በአንድ አግጣጫ ሰብስቦ በሰፊው በእነዚያ ችግርዎች መደራጀት እንጂ ለእየጎሳ እና አግጣጫው ሁሉ መደራጀት ከፍተኛ የአለመጠንከር ለስነውሳኔ ጨዋታው የአደርግ አለ። እታች ደግሞ እምናየው ሲጠቀለል፤ የማህበረሰብእ ቀጣይአዊነት (of continuity) የለም እና ህዝቡ ለስነውሳኔ ዴንታአጥ ነው እሚሉትን ሁለት ነጥብዎች እናግኝ።

፫) አንድ ማህበረሰብእ የለም

ዘመንአዊት ኢትዮጵያን በእሚወክለው በመሀከልሀገር (ገጠር የአልሆነ)፤ ወጥ ሀገርአዊ እና ዘመንአዊ ማህበረሰብእ የለም። ማለትም ተወራራሽ፣ ቀጣይነት የአለው፣ በበፊቱ የእሚቀጥል እና የእሚገባ የአንድነት እና ሀገርነት ጉዞ የለም። ተከትሎ፤ የስልጣኔ ጉዳይ የራቀ ነው። ስልጣኔ በቅብብሎሽ የእሚገነባ ሲሆን ሁለት ትውልድዎች እሚተካኩት ደግሞ በእየ አንድ ሰከንዱ ሲሆን በረዥሙም የጊዜ-መጠን ይተካካ አሉ ብለው እሚገነዘቡት አሉ። ያ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠት ነው እንጂ ቅጽበት ሁሉ የመተካካት ህግ ነው። ሀገር ሲሆን ይህ ጉዳይ አይቀየርም። አስርት (decade)፣ በእየሰከንዱ በቀደመው አስርት ላይ እየተተካ ይጓዝ አለ። ጠቢም (also future-generation)። የሆነው ሆኖ በሰባት ሺህ አመትዎች የእሚለጠጥ ታሪክ ውስጥ በቅርቡ ጊዜ፣ አንድ ወጥ የሀገር እሳቤ በአለመገኘቱ፣ ሀገር በዘመነ መንገድ የኢትዮጵያውን ማህበረሰብእ ወጥ አድርጋ መፍጠር አልተቻላትም። ይስማእከ ወርቁ ልናነጋ ተኛን ብሎ ሶስት ሺህ አመትዎቹ ጨለማ ዘመንዎች ናቸው ብሎ ደምድሞት አለ። ዛሬም የቀጠለው፣ በመሸጦነት፣ በጎሳ፣ እምነት ወዘተ. የተከፋፈለች ሀገር ስለጥቂትዎች ጥቅም መፍፈለጉ፣ አንድ ሰከንድ እንኳ ቀዝቅዞ ቢቆም እና የአለው ቢታይ፣ ሀገር ለመጪው እና ለአለው ትውልድ ወጥ በሆነ መንገድ እየተገነባችም እና በእየቅጽበትዎቹ እየተላለፈች እየተገኘችም አትገኝም። በትምህርት ትውልድ ከተቀረጸ፣ ዘወትር የትምህርት ጥራት ችግር ከተነሳ፣ ጠቢው እሚቀበለው ከአልተገነባለት አቅም ጎን ነው የአስብል አለ።

ወደ ላይ ታች ትውልድዎች ተትቶ፣ ወደ ወርድ ቢታይ አብሮ እየኖረ የተሳሠረ ማህበረሰብእ በእዚች አንዲት ሰከንድ እንኳ የለም። ሀገር እጅግ ጠንካራ፣ ዘርፈብዙ እና ከፍተኛ የሆነው ሉዐላዊ አካል እሚወክል የጸና አረዳድ ነው። በስሩ የእሚገኘው አንድ ማህበረሰብእን ግን ብንመለከት እንኳ ወጥ እና እየተተካካ እሚገኝ ማህበረሰብእ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ሠንሰለት ደግሞ ምን ቢጠነክር ጥንካሬው በአንዲቷ ዘለበት መርገብ ከጥቅምውጭ ይሆን አለ – እንደ ብሂሉ። የአልተሳሠረ ህዝብ ደግሞ፣ ሀገርን መመስረት አይቻለውም። የባህል አገነዛዘብም ወጥ ሳይደረግ የልማድ/ወግ አገነዛዘብ እንደ ባህል ተደርጎ ጎሳዎች ባህልዎች አሉአቸው በእሚል የተዛባ ትርክት ሀገር እንዳይመሰረት ተደርጎ አለ። ባህል ሀገርን አንድ ማድረግ ሲገባው፣ እጅግ የተበጣጠሠች ሀገር ለመፍጠር የተደረገ ሴራ ሆኖ አለ። የኢፌዴሪ. ህገመንግስት መግቢያውም አንድ ማህበረሰብእ እንገነባ አለን እሚለው ውስጡ ህዝቡን በመከፋፈል እና በአለማዘመን የተነሳ እውነት ከመሆን ይልቅ ከቶ የራቀ ነው። ጭራሽ በአስተዳደሩም ጎሳ የእውነት እና ሀገር ዋልታ ተደርጎ፣ “ለወላይታ የአክሱም ሀውልት ምኑ ነው!?” በእሚል አመለካከት አግጣጫ መለያየትን እንጂ፣ ዘመነ መሳፍንትአወከ በጎሳ መራራቅን እንጂ ወጥ ሀገርነትን እና ዘመንአዊት (ለምሳሌ እዚህ ከስብጥር እና አብሮነት የተነሳ) ሀገርን መመስረት አልተቻለም።

፬) አንድ የድሃድሀ ሀገር ውስጥ የአለው ሀገርአዊ እውነት እና የእዛ እውነት ክህደቱ አሰቃቂ ነው

“ማነህ ባክህ?”፤ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ግጥም፤ (እሳት ወይ አበባ፤)፤ አንድ ሀገር ለአለመመስረቱ ሌላው ማረጋገጫ ነው። የገጠር እና መሀከልሀገር ኢትዮጵያን ቁምነገር በአለው መንገድ ማስተዋል አልተቻለም። ገጠር ኢትዮጵያ ትክክለኛዋ ኢትዮጵያ ናት። ቢያንስ 80እጅ ኢትዮጵያ ያቺ ነች። ነገርግን፣ ሀገር ሳይሆን ቀዬ እና የተዳፈነች፣ የአልተዳሰሰች፣ የራቀች፣ ለምግቧ በቀረ የአልተፈለገች፣ ኢትዮጵያ ናት። መሀከልሀገር ኢትዮጵያ ገጠርን ማነህ ባክህ? እንጂ አንተ እማ እኔ ነህ አትለውም። እንግዳ ለእንግዳ። አስተዳደር፣ የስነውሳኔ አደረጃጀት፣ የስነምጣኔ አገልግሎት እና እቅድ፣ ይህን ሰፊ ኢትዮጵያ ከድቶ በማሽቀንጠር፣ መሀከልሀገር የአለውን ወይም ከተሜ እና ከተሜቀመሱን ብቻ ለማለት እስኪያስደፍር የቀፈፈ እውነት የሆነ ነው።

አንድአንዴ፣ ዳር ሀገር መሀከል ሀገር ተብላ ኢትዮጵያ ተሰንጥቃ እንድትታወቅ በስፋት የእሚጥሩት እጅግ ጥቂት አስተዋይዎች ጠቆም ከማድረግ ይልቅ ወደ ጉዳዩ አተኩረው አይጠልቁም። እነ በእውቀቱ ስዩም፣ ተስፋዬ ገብረአብ፣ ወዘተ. ጉዳዩን ስለመዘንጋቱ ቢጠቁሙም አስፈላጊ ስምጠትን አያስጮልቁም፤ ከመቆንፀል በዘለለ። ስነውሳኔ ላይ የእሚሳተፉ ስነውሳኔአዊያን (politicians) እምብዛም ለጉዳዩ ዴንታ የለአቸውም፤ ከአስታወሱም አንዳንዴ አንድአንድዎች እና ጥቂት በሆነች ትኩረት መጠን ነው። ለምሳሌ፤ በቀለ ገርባ አንድ ወቅት “ኢትዮጵያ ሲባል ሰማንያ እጁ ገጠሬ መሆኑን እንጂ ከተሜውን ብቻ አናስተውል” ብሎ ነበር። ይህ ዋና መሆን የእሚገባው አረዳድ በእዛ እሚቋጭ ጥቂት አንክሮት እንደ ቅምሻ ብቻ የእሚያገኝ ነው። በኋላ በትነሹ የታሰሩት የኢህአዴግ. ከፍተኛ ባለስልጣን በረከት ስምዖን፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እንዲበረታቱ በተደረገ ውይይት ላይ (የድርጅትዎች የጋራ መድረክ) ለምን ኢህአዴግ. እንደ እሚያሸንፍ ሲገልጡ፤ “የአላወቅአችሁት ኢህአዴግ. ሁሌ የእሚያሸንፈው፣ ገበሬውን ስለያዘ ነው! ወደ ገጠር ዘወር አትሉም።” ብለውአቸው ነበር። እውነታ የአለው መልእክት ነበር። በእርግጥ ይህ ሃቅ የድርጅትዎቹን አቅም ይፈትን አለ፤ ገጠር ድረስ ተጠያቂነት፣ ግልጠኝነት፣ እውቀትም ባይሆን ነቃ ማለት የለም። ለተቃውሞ አደገኛ እና አስቸጋሪ ነው።

የተራዘመው የ2013ዓም. ስድስተኛው ሀገርአቀፍ ምርጫ እንኳን በአንድ ትንሽ ከተማ እንኳ በተንበሸበሸ እና በእየቅያሱ አካባቢ በተነዛ የድምፅ ጣቢያዎች ድምፅ መሰብሰብን ከውኖ ምርጫው እንዲበላሽ ሆኖ አለ (የእሚመርጡ በእየሰፈርአቸው ስለተሸነሸኑ የነፃ ድምጽ በምስጢር መስጠት ጉዳዩን ተጠራጥረው በፍራቻ መርጠው ነበር፤ ድርጅትዎች ደግሞ፣ ተጋዳይ ተሟሟች ምስክር ወይም ታዛቢ በእየመንደር ጉራንጉሩ አበጅተው መከታተል አልተቻለአቸውም ነበር።) ስለእዚህ፣ አቅም በእሚፈትን የምርጫ አተገባበር ሂደት ወደ ገጠር መዝለቁ ለደካማ ድርጅትዎች ተራራ መግፋት ነው። ቢሆንም በሰፊ መደራጀት የተሻለ አቅም ይገኝ ነበር። ገጠሩን መመልከት ከአልተቻለ ሀገርን ማወቅም መመልከትም አይቻልም። ቀላሉ ሂሳብ ሰማኒያ እጅ ኢትዮጵያ ገጠር ናት ከተባለ ሃያ እጁ ቁንጽል ኢትዮጵያ ብቻ ነው ብሎ ግንዛቤውን መተርጎም ነበር። ያ እስከአሁን የለም። የኢትዮጵያ አረዳድ ድፍን እሚሆነው፣ ገጠርን በየዋህነቱ እና “ቱባ ባህል”ኡ በማንቆለጳጰስ ወቅት ብቻ ነው። በቀረ፣ ገጠሬ የከተሜ መጋቢ እንደሆነ እንኳ ትርጉም በእሚሰጥ ንቃተህሊና መጠን አይታወቅም – ገጠሬ ተንቋሻሽ፣ የአልሰለጠነ፣ የተዋረደ፧ ድሃድሃ፣ ወዘተ. ነው። ሰብእአዊነቱን የተሻለ ደረጃ አለኝ ሰለጠንኩ ባዩ ከተሜ አይገነዘብም። በከተማ ገጠሬ ይንቋሸሽ አለ። ሰው መሆንን ልጅዎች ተምረው እንዳያድጉ የገጠር ዘመድ እንኳ እንደ እንስሳ በራቀ ደረጃ መስተንግዶ ይሰጠው አለ። ለድግስ የእሚጠራ ገጠር ኢትዮጵያአዊ ጓዳ ተደብቆ ተስተናግዶ ይባረር አለ። ልጅዎች ሰውን የእሚረዱት በልብሱ ብቻ ሆኖ በተቃወሰ ሰብእአዊ ግንዛቤ በማደግ ስነልቦናአቸው ቶሎ ይጎዳ አለ። ሰውን በሰውነቱ የመመልከት ልማድ የይዳብርም። መንግስት ሰውን የመናቅ አመሉ ከእዛ ይመዘዝ አለ። ጠንክሮ የእሚኖር ዜጋም አይመሰረትም። ከተሜ በመሆኑ ብቻ የተሻለ እንደሆነ አስቦ ወርዶ ነትቦ የመለወጥ ርእዮቱን ይቀማ አለ።

የኢትዮጵያ ወካይንም ተደርጎ አይወሰድም። ይህ የአልተወጠነ ስነልቦናአዊ ብሔርአዊ አገነዛዘብ ነው። የተማሩትም ያንን በመድገምአቸው አሳዛኝ ቢሆንም፣ ሀቁ ዞሮዞሮ ወደ ዋልታው ኢትዮጵያ መመልከት እና ሀገርን ከእዛ አረዳድ አስፍቶ መገንባት ነው። ያኔ ፕሮፍ. መስፍን የአሉት በአጭር ጊዜ ስንበዛ ወዮልን የአሉት ለመታከም አይቸግርም። እንደ ዙምራ በእየመንደሩ የሰለጠኑ የገጠር ማህበረሰብእዎች የስራ እድል እንኳ ከፈጠሩ፣ ሀገርም ይበለጽግ አለ። ለእዚህ ሀቅ ኋኝ ብሔርአዊ መስተንግዶ የአስፈልግ አለ። ደርግ፣ በመሰረተ ትምህርት ጉራንጉር እንደ ደረሰው፣ ፊደል የአልቆጠረ እንደ ጠፋውከ የእዛ አተገባበር በብዙዎቹ ነገርዎች የአለማቋረጥ መተግበር አለበት። የኢትዮጵያን ከፍታ ከገጠር ከአለበት ከገነቡት ብቻ እውን ይሆን አለ። ከተማዎች በቆሸሹ እና በተጨናነቁበት ዘመን፣ ገጠሬ እየፈለሰ በእየከተማው ዳር መሬት በመቀራመት በአልሰለጠነ አካሄድ ከተማዎች በማስፋት እና የከንቲባ አገልግሎትዎች ሳይዳረሱ በራቀ እና ተልከሰከሰ መዘመን ከመጓዝ፣ አሁን እንደ አለው፣ ወጥ ይህን የእሚመለከት እና ለሁሉ ኢትዮጵያአዊ የእሚሆን መስተንግዶ መዘርጋት የግድ ይለው አለ። ኢትዮጵያ ሀብቷ ገጠሯ ነው። ሰማንያ እጅ ዜጋዎቿ፣ ሰራተኛ ጉልበት እና ከፍተኛ ተተኪ እምቅ አቅሟ፣ ዋልታ የስነምጣኔ ግብዓቷ ግብርና፣ ተፈጥሮ ሃብትዎቿ፣ ወዘተ. የእሚገኙት – ከትኩረት በቀረ – በገጠር ኢትዮጵያ ነው።

ሀገርን ማበልፀግ በእዛ ሰፊው ህዝብ ላይ የእሚነሳሳ ህልምም አይደለም። የተዛባ እሚመስል እና መሀከልሀገር ከመገኘት የተነሳ ብቻ እንደ ዋናው ኢትዮጵያአዊ የመቆጠሩ ነገር እጅግ የከፋ ኋላቀር እና ለመለወጥም እንዲችል አስተኩሮት ቀርቶ ከማዳበሪያ እዳዎች ማካበት እና ጥቂት አገልግሎትዎች ማሽቀንጠር በዘለለ ቁብ የእማይቀበል ነገር ሆኖ አለ። እንኳን በራቁ ገጠርዎች፣ ከአዲስአበባ ሁለት መቶ ኪሜ.ዎች “ራዲየስ” ውስጥ፣ ገንዘብ ስርአት ወድቆ፣ እቃበቃ መነጋገድ በ2012ዓም. በሰፊው አለ። መለኪያአቸው እንኳ ዘመንአዊ አይደለም። ግማሽ ቁምጣ ማሽላ ቆንጆ ቀሚስ ይቀይር አለ። ይህ ለእነእርሱ ደግ ነው። መንግስት ቀረጥ አይወስድብአቸውም፣ ሃብትአቸው እዛው ይዟዟር አለ፣ ግን የመረሳትአቸውን ነገር ለማስተዋል አብነት ነው። ይህ ሰፊ ኢትዮጵያ እንደ ዙምራ የእራሱ መሪ ከአላገኘ በእዛው ቀርቶ የስነምጣኔ፣ ባህል፣ ስነውሳኔ፣ ተጠቂ ሆኖ በመረሳት የእሚቀር እና ሀገርን በትልቁ ደረጃ አሳድጎ ለመመልከት የእሚታሰበውን ሁሉ የእሚጻረር ጉዳዩ ነው።

፭) ተምኔትዮጵያአዊ ቅዠት

በመጨረሻ፣ አሁን የአለው እውነት እንደሆነው፣ ብዘጀ ኢትዮጵያአዊ መደዴ (mediocre) – አንድአንድ “መደበኛ ልሂቅዎች”ም ጭምር እሚያስቡት የአለምጭራ ሀገር በድሃድሀነት መጎሳቆሏን፣ ተስፋዋ ዘወትር እየመነመነ መሄዱን አይደለም። በተለይ በተለመደው የሙዚቃ ዘርፍ ኢትዮጵያ ታላቅ፣ ወደፊትም አንደኛ ወዘተ. እሚሉ መፈክር መሰል ሙግ (ሙዚቃ ግጥም)ዎች አሉ። የጎደለን የለም ባይ ሰውም ትንሽ አይደለም። እናምር አለን፣ ከሁሉ እንሻል አለን፣ የነገርዎች ነገር መነሻ ነን፣ ወዘተ. ብሎ እሚኩራራ እና ሌላ ነጥብ አይመለከተኝም ባይ ቀላል ቁጥር የአለው አይደለም። ይህ ተምኔትዮጵያ (a UtoEthiopia) የቅዠት በሽታ ስሙ ነው። ፍፁም የሆነች ሀገር እንደ አለው እሚያስብ ትውልድ አባል እጅግ ብዙ ነው። ያ ግን የተምኔትዮጵያ በሽታ ነው። የግእዝ ቁጥር(ዎች) የተፃፈበት ልብስ መልበስም የ ወደ ጥንቱ ታላቅነት – በኢህአዴግ. አስተዳደር ዳግ-አክሱምአነት እንበለው (በእየመገናኛብዙሃኑ የአክሱም ሃውልት እየታየ ወደ ቀደመ ስልጣኔ ማማአችን እንወስድአችሁ አለን እሚል የኢህአዴግ. ፕሮፓጋንዳ ይንቆረቆር ነበር) – የእሚደረግ ጉዞ ማብቂያው ይመስል አለ። ያ እርካታ ነው። በቂም ነው። እንደ አየንው እላይ ገጠሩን በማንቋሸሽ እና በመናቅ ግእዙን በልብስ መለጠፍ ግን የስልጣኔ አገነዛዘቡ ማብቂያ ነው – ቢያንስ እንደ እሚመስለው እና እሚቀርበው። ሀገርን እስከ መጨረሻው ማስታወስ መቻልም ነው። ትርጉሙ ግን ገና የአልተወጠነ ተራ ተግባርነት የተቃረበ ነው።

ምክንያቱም፤ ወደታላቅነት ለመጓዝ አስፈላጊው በሽበሽ ትግል ነው። ፕሮፍ. በቃሉ በለጠ ለ ኢዜማ. ድርጅት ለመወዳደር ከተመዘገቡ በኋላ አጀንዳዎች አንድ ወቅት በ2013ዓም. ሲያስተዋውቁ፣ “…እኛ ትልቅ ነን! ትልቅ ነበርን! ቅብጥርሴ! ምናምን! (በማፌዝ ድምፀት እና አካልአዊ ምልክትዎች (gestures))፤ እሱ አይደለም ጨዋታው! እጅአችንን አንስተን ወደ ስራ መግባት አለብን!” ብለው ነበር። ይህ እሚገርመው ከቶ አዲስ ትችት እና ትልምአግጣጫዎች (policies) መሀከል መገኘት የነበረበት ጉዳይ አይደለም፤ ገና አሁን የተገኘ ባይሆንም። በአሉ ግርማ፣ ብሉይ-ደራሲ የተሰኘ (considered classic author) የህሊና ደወል ጭብጡ፤ “ኢትዮጵያ እሚያስፈልጓት የቆሸሹ እጀደዎች ነው!” በእሚለው እውቅ ገደልማሚቶ መፈክሩ ይታወቅ ነበር። በአጭሩ፤ ሀገር መመልከት ባትችልም፤ ዋና ጉዳይዋ፣ ለስራ በአዲስ ባህል መንቃት ነው። ማንም ያንን መመልከት አልቻለም፤ ሀገር የአንቀላፋች የሆነች እንደ ሆነች የባሰ ጊዜ ውስጥ እራሷን በቅርቡ ታገኘው አለች፤ ሌቋሆ. (ሌላነገርዎች ቋሚ ሆነው)።

ስነውሳኔው የ ፕሮፍ. በቃሉን እና በዓሉን ገና ወጣኝ እይታዎች ማየት አይችልም። የካድሬዎች ሰንሰለት፣ (የውሻ ፖለቲካ፣ ለደራሲ ሰሎሞን ሙሉቀን፣ የውሻ ፖለቲካ) በስነውሳኔው ተለምዶ፣ ሀገር እና ህዝብ ማገልገል ሳይሆን አስተዳደሩን ማገልገል (መሸጦነት ለፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም)፣ በመሥረፁ፣ የችግሩ-ላይ እውርነት በዝቶ አለ። አስተዳደር እና ተቋምዎች እራስአቸውን እንጂ (ስርአቱን) ሀገርን ለማገልገል አያስቀድሙም። ተምኔትዮጵያ ስለእዚህ፣ ለመንግስት አስተዳደርዎች (ኢህአዴግ. እና ብልጽግና) ቀኝ እጅ ነው። ስለእዚህ በታላቅ ነበርን ታላቅ እንሆንአለን ፕሮፓጋንዳ የተቀየረ ይህን ቅዠት ማስተጋባት ዳግማስተጋባት በመብዛቱ፣ ሀገር በቅዠቱ ለመዋጥ እንድትበቃ እና እንድትቀጥል አግዞ አለ። ለምሳሌ፤ በተለይ ዘፋኝዎች ለአለፉት ሰላሳ አመትዎች ታላቅ ሀገር እንደ አለችአቸው፣ እሚመስልአቸው አለመገኘቱን፣ ወዘተ. በመደጋገም አሰልችተው አሉ። ሃይባይ የለም። ቤንዲ ዌልቸር እንደ አለችው፣ ከሶስት ሺህ አመትዎች በፊት ታላቅ ነበርን ሲሉ ኢትዮጵያዎች ዛሬም ይሰማ አሉ ግን ትክክል ቢሆኑም፣ ዛሬ ሲሉት ግን ፈገግ የአሰኝ አለ…በማለት አስተያየት የሰጠችው፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዋ፣ ይህን ቅዠት አስተውላ ነው። የጥንት ዘመን በመካከለኛው ዘመን ተተክቶ ነበር። ያኔ ዘመነ መሳፍንት ነበር እንጂ ያ ታላቅነት አልቀጠለም። መኩራራቱ ያኔ ማብቃት እና ተዙሮ መምመልከት ነበረበት። ቅዠት ሆኖ ግን ቀጠለ። ጭራሽ መካከለኛው ዘመን ሲቋጭ እና ዘመነ አብርኆት (enlightenment) እና ዘመንአዊ ስልጣኔ ሲጀመር ኢትዮጵያም ዘመንአዊ ታሪኬ ጀመረ ብላ ተሸወደች። ምንም አብርኆት እና ዝማኔ ዛሬም የለም። እነእርሱ የባህል እና ስርአት ለውጥ ናቸው እና እነእርሱም የአልተገኙት ገጽታዎች እንደሆኑ ዛሬም አለ እና።

በሶስተኛው የታሪክ ክፍል ዘመንአዊ ታሪክ (modern history) ጭምር ግን ሀገር ወደ ጥንት ታላቅነቷ አልተመለሰችም። ዘመንአዊ ታሪክ ከንፈዘመን (era) የላትምም። ከፊውዳል መላቀቅ ከሆነ ገና ያ ድሉ አንድ ምእት አልቆጠረም፤ ምትኩም የውሻ ፖለቲካ የተሰኘው (ሰሎሞን ሙሉቀን፥ ደራሲ)፣ የካድሬ ስርአት እንደ ጭሰኛ ስርአት ነው። ለሮዞሮ መሬት የህዝብ ከአልሆነ ጭሰኛነት አልተባረረም፤ ማንም መፈናቀል የግዴታው መሰረት ነው። መንግስት (state) በህገመንግስቱ የመሬት ባለቤት ነኝ ብሎ አለ። ህዝብም ሃብቱን ይቋደስ አለ ቢልም፣ ከህዝብ እና መንግስት አቅም የአለው እና ሁሉን ዘዋሪ መንግስት በመሆኑ፣ በተጨባጭ መሬት እንደ ፊውዳል ስርአት ኪራይ እንጂ ባለቤት የእማይኮንበት ነው። ወደኋላ በመኬዱ፣ ዘመንአዊ ታሪክ የት ተመሰረተ? ሁሉም ነገር ማለት ይቀልል አለ፣ ከእውቀት እስከ ቁሳቁሱ፣ ውጭ ተመርቶ በገበሬ ሃብት የእሚገዛ ነው። የአምራችነት (industrialization) ስነስርአት በአውራምባ ከአልሆነ የትም የለም። የውጭ ተቋምዎች መጥተው የእሚገጣጥሙትም ለተሻለ ትርፍ እንጂ ሀገር በመዘመኗ አይደለም። ርካሽ ሰራተኛ፣ ነፃ እሚሰኝ ጥሬ እቃ፣ ከፍተኛ ጥቅማጥቅምዎች ጥበቃ፣ ለእራስአቸው ደግሞ የተሻለ የሽልፍኖት ስነምጣኔ ትኩረት እና ተራ ተራውን የማምረት ነገር ማስወገድ፣ ወዘተ. እድልዎች አሉት። ሀገርን ግን እምብዛም አያገለግልም።

ዘመንአዊ ታሪክ ባይጀመርም፣ ታላቅነት እና ፍፁምነት አለን ለእሚሉት በኋላቀሩ ስልት እና ሚዛን ታላቅነት ከአለ ቢጠይቁአቸው የእሚገባ ነቁጥ አለ። የማይጠይቁት ነገርም፣ የጥንቱ ታላቅነት ዛሬ አይሰራም፤ ያኔ ሴት እና ወንድ እንኳ ቀርቶ ወንድዎችም መሀከል እሪና አልነበረም። ንጉስዎች ለገነቡአቸው ግንባታዎች ብቻ ታላቅነት ማለት ዛሬ ይቻል አለን? አዲስ ኢትዮጵያ ይገነባ አለ፤ በጥንቱ ይቀጠል አለ እንጂ ወደ አልዘመነው ጥንትአዊ-ስልጣኔስ ዳግመመለስ እሚል ትርክት ተራ የፕሮፓጋንዳ ቀልድ ብቻ ነው፤ ስለራበው ጉርስ ፍለጋ ፕሮፓጋንዳ ለእሚያስተጋባ እና ሀገር ላይ ለእሚያላግጥ ካድሬ እሱም “የጠላት መሳሪያ ነው” (መስፍን፣ ገ.27፣ 28) ውብ ተረቱ ነው፤ ስለ ገሀዱ መርምሮ ወይም ተምሮ የተነሳ፤ ፕሮፍ. በቃሉ እንደ አሉት ያ ቅዠት ነው ተነስተን እንስራ እሚል አግጣጫ ቀራጺ ይሆን ነበር። መንግስት ወደ ጥንቱ ታላቅነት እየ ዳግ-ገሰገስን ነው ብሎ ለሰላሳ አመትዎች ምንም ረብአለሽ ለውጥ አልታየም። ዘመንአዊት ኢትዮጵያ አለች ይባል እና አፄ ቴዎድሮስ እና መድፍአቸው ይነሱ እንጂ፣ እርስአቸው ቄስዎችን እና መነኩሴዎችን ከአውሮፓ ወንጌል ለማስተማር ቢመጡ አስረው መድፍ ስሩልኝ ስለአሉ ዘመንአዊ ሀገር መስራች የተሰኙ ሆነው ነበር። ዛሬም፤ መሳሪያ ስሩልኝ ብሎ መንግስት ማሰር የቻለው የቻይና ወይም ሌላ ሀገር ጎብኚ ወይም ነጋዴ እንኳ የለም። የቴዎድሮስ የመለወጥ ፍቅርም የዘመንአዊነት መሰረት መሆኑ በፍቅር ደረጃ የቀረ ሆኖ ይከበር ይዘከር አለ እንጂ ተጨባጭ መሰረት የለውም።

ከእዛ እሚሻል ግን አለመፈጠሩ የባሰ ከርፊ ታሪክ ነው። በማፈግፈግ ጉዞው፤ ተቀጥሎ በቄስዎች እነ መነኩሴዎች ለመሰልጠን መሞከሩ እስከ ቀኃሥ. ዘልቆ፤ ፕፎፍ. መስፍን፣ በህንድአዊ ቄስ፣ በፈረንሳይአዊ መነኩሴ፣ በሌላም ፕሮቴስታንት ፓስተርዎች አማርኛን ጨምሮ ትምህርትዎች በትልቅ ክፍያ እየተከፈሉአቸው ሲሰጡ “ታሪክአችን እማ የሚሲዮንአዊያን መጫወቻ ነው የሆነው” (መስፍን ገ.126) ብለው አስሰምረው ይህን የስልጣኔ ጉዞ በምፀቱ ገልጠውት አለ። ሰሞኑን እንኳ፤ ይህ ጥገኝነት አልቀረፍ ብሎ፤ ሀገር ልትቆረስ ነው በእሚል ህዋሃት. እና ማእከልአዊ አስተዳደሩ ጦርነት ከጀመሩ ብዙ ወርዎች በኋላ ከየቱም ዉጊያ እለትዎች በበለጠ ወደ 5,600 ሰውዎቹን የተገደለበት ዘገባ፣ የነጭነጯን መርሐግብር በመረጃ ትመ. እሚያቀርበው ዲን. ዘመድኩን ሙስናን ለማሳበቅ የብረታብረት ፋብሪካ ሊከፍቱ የ”ኢንቨስትመንት” ፈቃድ አወጡ ባላቸው፣ በሌተ. ጀነ. ባጫ ደበሌ፣ የቀረበው፣ ጠሚ. አብይ አህመድ ቱርክ ሄደው ስምንት የውጊያ “ድሮን”ዎች ተሰጠአቸው ከተባለ በሳምንቱ ገደማ ነው። ይህን በእርግጥ ጠሚ.ሩ በተሾሙ ወቅት ከአረብ አንድ ሀገር የተወሰነ ገንዘብ ይዘው ሲገቡ “እንደ ለመደአችሁት ለምኜልአችሁ መጣሁ” ብለው ጥቂት ተገቢ አረፍተነገር ተናግረው ነበር። ማለትም፤ ለሰላሳ አመትዎች ማጭበርበሪያ-ፕሮፓጋንዳ እንጂ ወደ ጥንቱ ታላቅነት ጥቂትም አልተኬደም ነበር። ጭራሽ ማሽቆልቆል አለ።

ከመሳሪያ ማምረት ሙከራዎች ወደ መግዛት እና መለመን መደረሱ ጉዞውን ወደኋላ አድርጎ እንደሆነው የአስመለክት እንጂ ሰላሳ አመትዎች እንደተዘከዘከው ፕሮፓጋንዳ ወደ ታላቅነት የመራመድ ተስፋን አያስመለክትም። የአለም በከፍተኛ መጠን ማደግ ወደ እዚህ ሀገርም ፈስሶ ጥቂት የስልጣኔ በረከትዎችን ለመግዛት ተቻለ እንጂ ሀገርን በማሳደግ ሚዛን ወደኋላ የተኬደ ነው። ያንንም ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣ በታላቁ በአማርኛ የአልተደገመ መጽሐፍአቸው፣ ህዝብ ከሰነፈ ሌላው እየበረታ በቀላሉ የአመረተውን የተፈጥሮ ሀብቱን በመሸጥ እየገዛ ይኖርበት አለ፤ ያም ለሰነፈው ህዝብ ጠቢ አደገኛ ነው ብለውት እንደ ነበረው የአለ እድገት በኢትዮጵያ ታይቶ አለ፤ በአለፉት ሰላሳ አመትዎች። የመንግስት ውጭምንዛሬ ለአለፉት ሰላሳ አመትዎች የተገኙት እና ወደ ሶስት ቢሊየን ዶላርዎች የደረሱት፣ በብዛት ለነገው ትውልድ በአለመጨነቅ ከተፈጥሮ ሀብት እየመዘዙ መሸጥ (የግብርና የአልተቀነባበረ ምርት ውጭሽያጭ = export) እና የሰውሃይል (diaspora) ጉልበት ሽያጭ (remitance) የእሚገኝ እንደሆነ አለ። ዋናው የሀገር ገቢ እራስ እና ሀብትን ከመቸብቸብ እንጂ ሰልጥኖ ከማምረት ወይም እንደ ሌላው የአደገ ሀገር ከተስማሚ ንግድ ምንጭ እሚመዘዝ አይደለም።

በባህልም፣ በቋንቋም፤ ሀገር ብዙ ባህልዎች እና ቋንቋዎች አላት ብሎ መንግስት አስተዳደሩ ለሰላሳ አመትዎች ህዝቡን መበታተኛ አደረገው። በጎሳ ርእዮት ሀገርን መሰነጣጠቂያ እና ለውጥን፣ ህብረትአዊነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ወዘተ. መከላከያ አደረገው።

ከስነውሳኔ፣ ባህል፣ ኪነጥበብ፣ እና ስነምጣኔ በዘለለ፣ የኢትዮጵያ ፍፁም ናት ቅዠቱ የትምህርት እና ባህል ቀለምን ማድመቅ ዝግመት ላይ የነተበ እንዲሆን ሆኖ ቀርቶ አለ።

፮) ተገቢ ኢትዮጵያ መሰረትዎቿ ተረስተው አሉ

ሌላው ዋልታ የኢትዮጵያ ችግር፣ ትላንቷን ሀገሪቷ ማሽቀንጠሯ ነው። ትላንት ከሌለ፣ በምን ጊዜ ላይ ተቆመ? ዛሬ የትላንት ወለል ላይ ከአልቆመ የእማይገኝ የጊዜ አይነት ነው። በእማይገኝ ጊዜ ላይ የቆመች ሀገር ሆና አለች። ዘፋኝ እንደ አለው “…የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ..”። የጊዜ አረዳድ በህዝቡ የወረደ ነው። ፕሮፍ. መስፍንም ያንን ተችተውት አለ። እዚህ እምናተኩረው ዘርዘር ብሎ በቅንጭብነቱ ሲቀርብ ግን፣ በአጭሩ፣ የተሞከሩ የትላንት የኢትዮጵያ ደግ ሙከራዎችን መሰብሰብ እና መያዝ አልተቻለም እሚለውን የጊዜ እንደምታ ችግር ማንሳት ብቻ ነው። ለኢትዮጵያ ትልቅ የአደረጉት፣ የት ናቸው? ስራዎችአቸውስ? አስተዋፅዖአቸውን፣ ለማወቅ ከባድ ነው። በእየዘርፉ፣ ሀገርን ለመጥረብ እኣ ማሳመር ሀ ወይም ሁ የሉ አሉ። ዘርፍአቸው ግን አያወሳአቸውም። ሀውልት፣ ሽልማት፣ ማእረግ፣ መንገድ፣ ዳግ-ህትመትዎች፣ አውደ ውይይትዎች፣ ተዝካርዎች፣ ወዘተ. አይታዩም።

ይህ አዙሪት የፈጠረው ምንጭ ነው። የእማይታወቁ ታላላቅዎች፣ በመዘንጋትአቸው፣ ማንም የተነሳሳ ቢኖር ከአዲስ ነገሩን ለማጥራት ይጥር አለ። ከዜሮ የመነሳት አባዜው የሰነበተው እና ኢትዮጵያአዊ የሆነው ለእዚህ ነው። ተጨማሪ ኢትዮጵያአዊ ቀውሱ ደግሞ፣ አአምርኩሎ (ማንም አዋቂ ነኝ የእሚልበት እውነት) የእሚፈልቀውም ከእዚህ ነው። የተሰሩት በገሀድ በሀገር አደባባይ፣ በሙያ፣ ትምህርት፣ በወል ብሔርአዊ ንቃተህሊና፣ ወዘተ. ስለእማይታዩ ማንም ቁንጽል የታየው፣ ያችን ቢያበረክት፣ አዋቂ ነው። የበለጠ ወይም ተመሳሳይ የሰሩት አልተገለጡም፣ ሜዳው ባዶ ነው። በነበረው አክሎ መካብ የለም። ይህ ሀገርን የማእማያሰለጥን አምካኙ ድንቁርናው ነው። ዘመን በቅጽበት ሲተካ፣ ትላንት ግን የተረሳበት ሀገር ነው። ከእነ ጥንትአዊያኖች ጀምሮ፣ ዛሬ እስከ እሚታትሩት የተገመደ ገሀድ መጽደቅ አለበት። ከ”ዘመንአዊው ታሪክ” ቢወሰድ፣ ከእነ ተስፋ ገብረስላሴ፣ በቀለ ሞላ፣ ወዘተ. የእሚታከል እውነት ማደግ አለበት። ይህ ለምሳሌ፣ በትድድር (management) ትምህርት የሀገርበቀል ስኬትአማዎችን መዝገበአእምሮ (encyclopedia) ደረጃ አጥንቶ ዳግማስጠናት ልማዱ ቢሆን፣ የበቀለ ሞላ ትርክት በቀላሉ የታወቀ በቀላሉ የእሚያነሳሳ ትምህርት ሆኖ በየትም ደረጃ እና በተለይ በሆቴል ትድድር እና ንግድ ትድድር ትምህርትዎች ይበቅል ነበር። ጥቂት ተቆንጽለው ከእሚበተኑ ነገርዎች በዘለለ፣ የሀገር እውቀትን ማበልጸግ እምብዛም የለም።

ይህ ሲሆን መነቃቃት ሰጭ፣ አንፋሽአዊ (inspirational)፣ እውቀት ንግድ ከመኖሩ በዘለለ፣ ተጨባጭ ጉዞን ማፋጠኑን የአግዝ አለ። የቀደመው የመሰልጠን ትትረት ተንጠልጥሎ ለትውልዱ በእየጉራንጉሩ ህላዌ (ንቃተህሊና ሁሉ) ክፍት ሆኖለት ከአለ፣ ዞሮ ወደ ወጣኝ እውነት ሃሰሳ እና ህክምና አይንባጫረቅም፤ ውሃወቀጣ ይታከም አለ። በምትኩ በቀደመው ተገልግሎ በስኬቱ ወዲያው ወጥቶበት ወደ ላይ የመገስገስ እውነት ይጀመር አለ። በተያያዘ፣ ጠቅላላአዊነት ይከስም አለ። የተዳፈነ እጅግ መነሻውን ነገር ደጋግሞ ከመንገር፣ የተሞከረ እና አሁንም የተደረሰበት (ወደኋላ እና ወደጎን) ጥረት ሁሉ ከተሳሠረ፣ ወደ ዝርዝር ችግርዎች፣ ቋንቋ፣ ትትረትዎች፣ ርእዮትዎች ወዘተ. መጓዝ ይቻል አለ። ተሞክሮ፣ የጊዜ ምስጢርን መግቻ አንድ ቁልፍ ነው። ከአለማቋረጥ ጊዜ ሲፈስስ፣ ትውልድዎች ሲተካኩ፣ የጊዜ በደል ይደርስብአቸው አለ። አብረው በመገኘት አይነጋገሩም። ተሞክሮዎችአቸው ከተንጠለጠሉ ግን፣ ትውልድዎች ሲሄዱ መጪው አሻራዎችአቸውን ሁሉ ይወስደው አለ። የኗሪ አልባ ጎጆዎች ግጥም ከትውልድዎች መተሳሰር አለመቻል የመጣ ገሀድ ነው። የቀደመው የሰራው በኢትዮጵያ ዛሬ በእዚህ ዘመን ከመኖር እውነት አንፃር መገኘት የእሚገባው እውነት ነው። ያ የተዘነጋው ትስስር ነው። የተሞከረ እውነቱ አለ፤ ነበረ፤ ባይታይ ካመም ይቆይ አለ። ወደ እዚህ ግን ተገልጦ እንዲበተን በስርአት ሁሉ የመክተቱ ስራ የትም ወይም እጅግ በራቀ መጠን በቀረ የለም።

፯) ህዝቡ በእሚገባ ግድየለሽ ነው

በገብረህይወት ባይከዳኝ፣ የኢትዮጵያው ህዝብ ተዘልፎ ነበር። የእማይጨንቀው ህዝብ ነው፤ ወደፊቱ አስጊ ነው ብለው ነበር። አመክንዮው ሌላው አለም አለማንቀላፋቱ ነው። ስለእዚህ፣ ዛሬውን አላጠነከረ ነገውን አላበሰለም። ዛሬ እንደ ተሆነው የእሚኖርበት ማህበረሰብእ ነው። ነገ አይገድደውም። እንደመጣው ይኖር አለ። ገጣሚ ሜሮን ጌትነትም፤ ይህን ገጽታውን ሌላው የሰለጠነ አለም ህዝብ የአማ የሰለጠነ በልቶ ጠጥቶ ሲተኛ አምላክን ማዘኑን ነግሮ ይተኛ አለ፤ ሀበሻ ቆሎውን ቆርጠም አድርጎ ተመስገን ብሎ ይተኛ አለ፤ አምላክ የአልተደሰቱትን ለማስደሰት ሁሌ ወደ እነእርሱ የእሚሄድ ነው በማለት ገልጣው አለች።

መረር በአለ መልኩ ደግሞ፤ ፕሮፍ. መስፍ ወልደማሪያም፤ ይህ ህዝብ ዴንታ የለውም፤ ብዙዎች ሲሞቱለትም፣ የአጨበጭብ አለ እንጂ አይገድደውም ብለው ገልጠውት በጥቅስ አስደግፈው ወደፊት የእሚቀጣ ህዝብ ነው ግድየለሽነቱን በማብዛቱ አምላክ ይቀየመው አለ ብለው አሉ፤ (ገ. 31)።

አንድአንድ ሃሳብዎች ለህዝቡ በተነጠለ መንገድ የመዳበር እውነትን እየቸሩት ጅማሮ ለመለወን እየአሳሰቡ ነው። ለምሳሌ፤ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ የቅኔ አኗኗር ህዝቡን እንዲህ እንደ አደረገው ይናገር አሉ። ስነልቦናው መንታ ሆኖ በአንድ ወገን ተቆርቋሪ በሌላ ወገን ቸልተኛ ወይም ባለይሉኝታ ይሆን አለ። በእርግጥ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንም፤ ወይ እሳት ወይ አበባ እንሁን ብለው በአልለየለት መንገድ የእምንኖር መሆኑን ይናገር አሉ። ወደ አንድ የመንበልበል የህልውና መሰረት ወይም ግጣጫ መቀየስ አልተቻለም – እንደ ህዝብ – በማንቀላፋት እንደ ተኖረው አለ። ሰብእአዊነትን እና ግልን በጥን ጥንትአዊነት (ቅድመ አዳም ወይም አዳም) ደረጃ የተገኘውን ቀምሶ እስከሞት እንደ ተኮነው በመሰንበት አማርኛ የተዘዋወረ ሀገር ነው። አንድ ንጉስ መጥቶ ሀገር የአሳድግ አለ የአኔ ይትረፈረፍልን አለ እሚል የዋህነትም አለ። ምን አንድ ንጉስ ተቀብቶ ቢታትር በተለየ ጊዜ ሀገር ወደ አመዷ መውረዷ ነው። ህዝብ መነሳት እና መሰልጠን አለበት እንጂ ተቀምጦ አምላኩን መጠባበቅ እና ያንን ከትውልድ እስከ ትውልድ እየተናገረ መሰንበት የለበትም። ግድን እና ታሪክአዊ ተጠያቂነትን ወደ “ባህሉ መበረዝ” አለበት። ሆድ እንደሰጡት ነው፤ አእምሮም። እንጂ በራቀ የለውጥ ጥበቃ ላይ ነኝ በእሚል የሰነፈ እውነትም ብዙሃኑ የተተበተበ ነው። ደህና ሀገር በደም እና በላብ እንዲገነባ እንጂ ከሰማይ እንደ እሚወርድ ፍርፍር አድረገው መሳልአቸው የስንፍና ወደሩ ነው።

አንድአንድዎች፣ ህዝብ አለሽ መሪ አጣሽ እሚሉት ለእዚህ ይሆን አለ፤ “ሰው እንጂ ህዝብ አላጣሽም” ባይ መጽሐፍ ነበር። ስለየቱ ህቡዕ ህዝብ የእሚናገር ነው? ህዝቡ ቸልተኛ ነው። አውሮፕላን አይቶ፤ የስራፈት ነገር የእሚል (አያሳየኝ የለ ይሰሩትን ያጡ፥ ጠንቀቅ በል ጌታዬ ደሞ ወደ አንተ መጡ፤ ብለው በጀንከር አውሮፕላን) ብሎ ስነቃል እሚገጥም ነው። The Gods Must be Crazy ፊልም፣ የአሳየው ሀበሻን ባይሆንም፣ እሚያስፈግገው ህዝቡ እንደ አበሻ ሁሉ በስልጣኔ የእማይታወቅ መሆኑን ነው። በደርግ ዘመን፣ እከሌ ይገደል ሲባል፣ እሚቃወም ሳይኖር በሆታ እሚያጨበጭብ ፈሪ ነበር። ፕሮፌሰር እንደ ገሰፁት፣ በቀኃሥ. ጀግናዎችን የአስገደለ ህዝብ ነበር። በኢህአዴግ. መመስረት ሰሞን ጋዜጣ እና መጽሔተወ ሲበዛ አንባቢ አልነበረም – ግድየለሽነት – ስለእዚህ በአምላክም የተጠላ ህዝብ ነው፤ ፕሮፍ. መስፍን እንደ ገሠፁት፤ (ገ.31፣ 147)። ፕሮፍ. ብርሃኑ ነጋ፣ በህዋሃት. መባረር ማግስት ምርጫ ሲቃረብ፣ አሁን ምሁር እና ሃብታም ልሂቅ ሁሉ ይቀላቀለን፣ ወደ ስነውሳኔው ግቡ ቢሉም ይህ እሚሰኝ ተሳትፎ ሳይታይ ምርጫው ወዲያው በአስተዳደሩ የተለመደ ሙሉበሙሉነት የቀረበ ማሸነፍ ተፈጸመ።

በእየ መንግስት ግልበጣው፣ የሆነ ቡድን እድሉን የአጨናግፈው አለ። ህዝቡ በደሙ መንግስትአዊ አምባግነናን ሲሰለቸው ጥሎ ወዲያው የተመሰረተው አስተዳደር ባለጌ ሲሆን ሌላ ትውልድ ጠባቂ ነው። እንደ ፈረንሳይአዊ አብዮቶች ተደጋግሞ ተገቢ መንግስት እና ስርአት እስኪፈጠር መታገልን እና አንዴ ሀገር ማቅናትን፣ አይከውንም። ዴንታየለሽነቱ ቅጡ እየጠፋበት ነው። አንድ አስተዳደር በጎሳ ተመርኩዞ ቆይቶ ሲወድቅ ሌላውም በጎሳ ተንተርሶ “የተረኛ-ፖለቲካ” ተብሎ እየቀጠለ እሚገኝ እና አካሄዱ ተስፋየለሽ የሆነ ነው። ህዝብ ንቃተህሊናው ጨምሮ፣ ለሀገር ሟች እና ታጋይ ሲሆን፣ የሰነፍ ልማዱ ሲረግብ ይህ ይቀረፍ አለ። ኢትዮጵያአዊ አስተደሰደር እና ኢትዮጵያን ከአዲስ ምስረታ ይበረታ አለ።

ደርግ የማህበረሰብአዊት ኢትዮጵያ መጀመሩ ከእዚህ አንፃር የተሻለው አካሄድ ሆኖ ከአሁኑ በበለጠ እናገኘው አለን። በእዛ ስርአት አረዳድ ሰውን አስገድዶ መለወጥ ከፍተኛ እድል ስለነበረው የተሻለ መንቃት ነበር። ስለሀገር የማወቅ እና የመለወጥ እድሉም የተሻለ ይሆን አለ። አሁን ግድየለሽነቱ በነፃ የተተወ ነው። የዜጋዎች አለመሰልጠን ሀገር ጎጂ መሆኑን እሚያስተውል አገነዛዘብ የለም። የዜጋዎች መበልጸግ የሀገር መበልጸግ መሆኑን የእሚነግር አሰራር አይታይም። አንደምታው፣ ህዝብ ጎልማሳ ስርአት አጥቶ እንደ ፈለገ ይኑር እሚል አካሄድ እንደ አለ ይነግረን አለ። የጠበቀ ሀገርአዊ ጉዞ እና የዜጋዎች ከጉዞው የመተሳሰር እውነት የለም፤ ወይም በልሉ አይገኝም። ግድ አለመስጠት ኢትዮጵያአዊ ነው። በእራስ መለወጥ እና ለእዛ አስፈላጊውን አንዴ አስተካክሎ በስርአት ውስጥ መክተት አለመሞከር ብሔርአዊ ተዳሳሽ ገጽታ ነው።

በደፈናው፤ በብዙ ችግርዎች ወደ ዘመንአዊነት መሻገር እሚሳናት ሀገር እንደ ቀጠለች ናት። ብዙ ችግርዎችም የከበቧት ናት። ከፊው ነገር ነጠላ፣ መስቀል፣ የተክለ ሃይማኖት ፃድቅ ምስል፣ ወዘተ. እንኳ ከቻይና ተመርቶ እዚህ በውጭምንዛሪ እሚሸመት ነው። የስነምጣኔ አረዳዱ በአስተዳደርም ሆነ ህዝቡ እንደ ህፃን ወይም ቀውስ እንጂ እንደ ፊደል አለኝ ባይ አይደለም። ሌላው ሀገር ደግሞ ለምኑም ነገር እጅግ እየሰለጠነ ደግሞም በስልጣኔ እየነጎደ ነው እና አሳሳቢነቱ ሁሌነጓጅ (exponential) በመሆኑ ሃያል ነው። በደፈናው ህዝቡም ሀገሩም፤ ችግርዎቹም፣ እድልዎቹም፣ የአንዣበቡ እምቅ አደጋዎቹም ብዙ ናቸው። እነእርሱን በመዘርዘር በማከል ማደን አስፈላጊ ነው። ፈጽሞ አዲስ ባህል፣ አዲስ አግጣጫዎች፣ አዲስ ኢትዮጵያአዊነት፣ ወዘተ. እንጂ የተለመደው መቋረጥ የአለበት አካሄድ ነው – ጅጁ ኢትዮጵያ፨


Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s