Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ኢትዮጵያን የእሚያተራምሳት የባህል እና ቋንቋ ዝብአረዳድ[The Misunderstanding of Culture and Language that Stirs up Ethiopia]

About how Ethiopians shall see Culture and Language in a proper and powerful way it really is.

፨ሀሰተኛ የባህል እና ቋንቋ አግጣጫዎች በመንግስት አስተዳደርዎች እንደ ቀጠለው ነው፨

————————– ——————— ———————– ——————– ——–

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 04th 2021GC.,

Take this on PDF.

በባህልም፣ ሀገር ብዙ ባህል አላት ብሎ መንግስት አስተዳደሩ ለሰላሳ አመትዎች ህዝቡን መበታተኛ አደረገው። ዳንስ እና ቋንቋ መለያያ ድንበርዎች ሆነው በስነልቦናአዊ አሉታ ውጤት መከፋፈልን ሰርተው አሉ። ባህል ግን የአኗኗር ፍልስፍና እንጂ ዳንስ አይደለም። ዳንስ እና አመጋገብ ወዘተ. እጅግ ተራ እና ንዑስ የባህል አላባአዊ ናቸው። ባህል የሰውልጅ ከተፈጥሮ ጋር የአለው አገነዛዘብ እና ግንኙነት መገለጫው ከባድ የሰውመሆን ጥበብ ነው። በማንም ዘንድ የእሚለያየው እንደ ዳንስ ወይም አለባበስ በአሉ ተራ ጉዳይዎች አይደሉም። በትግራይ ወይም ቆላ አማራ የአሉ አጭር ቁምጣ ቢለብሱ ስለተራራማ ጉዞአቸው ልብሱ እንዳይጎዳ፣ ጭቃ እንዳያገኘው፣ ሙቀት እንዳይወብቅ ወዘተ. እንጂ ስለማንነት ተብሎ አይደለም። ለአስተዳደሩ ግን ያ ማንነትህ ነው ተብሎ ከሌላው እንዲነጠል እና እንዳይዋሃድ የተሸረበ ሴራ የሆነ እውነት ነው።

የመልክአምድር እና አየርጠባይ፣ የዶርዜ ወይም ራያ ቤት አሰራርን ከጎንደር ቢለየው፣ (ወደ ደቡብ ቀርከሃ አለ፣ ወደ ሰሜን ሰንበሌጥ አለ፣ ቤትዎችአቸው በእነእዚህ የተነሳ ሲገነቡ እሚይዙት ገጽታ የተለያዩ ናቸው)፣ አስተዳደሩ ግን ባህል ማለት ያ ነው – ከእዛ ውጭ ለእዛ ጎሳ ማንመሆን የለውም – በእሚል ወጥ ትርክት ዜጋዎችን መከፋፈያ አደረገው። በደቡብ እንሰት በቃይ ነው በሰሜን ጤፍ በቃይ ነው። መልክዐምድሩ በአለያየው ሰብል የተነሳ ማንመሆንአችሁ የተለያየ ነው እምትበሉት የተለያየ ነው እና በእሚል መንግስት መከፋፈያ አደረገው። አለባበስም፣ ፈጽሞ ለእየብሄረሰቡ አልነበረውም። መንግስት መከፋፈሉን በመቀጠል፣ በእየቀለማቱ መለያየት ለእየብሄረሰቡ አዳዲስ የልብስ አይነትዎችን ፈጥሮለት አለ። ለምሳሌ ጉራጌ እማያውቀውን ቀለል የአሉ ቀለምዎች የእሚጣሉበት ሱፍን አዘጋጅቶ የእናንተ ልብስ ደህ ነው፤ ሌላው ያ ስለሌለው የእናንተ ማንመሆን ይህ ልብስ ነው አንድ አይደልአችሁም፣ ፕሮፓጋንዳውን ነዛበት አሰጸበት። ብዙ ብሄረሰብዎች፣ በኢህአዴግ.ኡ አስተዳደር እንዲህ አዳዲስ የእማያውቁአቸውን ልብስ አግኝተው ከሌላው የተነጠሉ ሆነውበት አሉ። ባህል፣ ቆሻሻ አመለካከት ሆኖ ከሌላው መነጠያ ማንኛውም ምክንያት ነው ተብሎ አለ፤ በማይታበል አንደምታው እንኳ።

ባህል ግን ማንመሆን ነው። ሰው ደግሞ የሆነው ሰውን ነው። ባህል ሰውን ከእንሰሳዎች እሚለየው ገጽታዎቹ ናቸው። እንደ አንድ ዘረፍጥረት (species) ዓስተኔሰብእ (mankind) ለተፈጥሮ፣ እራሱ፣ እና ወደፊቱ የአገኘው አገነዛዘብ እና በእዛ መሰረት የእሚከውነው ድ ወደ ልማድነት ተቀይሮ ልማዱ ወደ ወጥ ፍልስፍና ሲመጣ የእሚታየው የማህነረሰቡ ህላዌ-ምላሽ (answer to existence) ነው። ለሰው ከባሀል ወዲያ ህላዌ እምብዛም የለውም። ባህል መንፈስአዊነትንም ወደ እራሱ ግዛት በአንድም ሆነ ሌላ ተያያዥነት የተነሳ መንከር ስለእሚሻ መነብስ ጉዳይንም መጨመር የእሚችል ከሆነ እጅግ መሰረትአዊ ጽንሰሃሳብ ነው ማለት ነው። ከህላዌ-ምላሽ ከተገናኘ፤ ህላዌ ደግሞ ለሰውልጅ አንድ እና ብቸኛ ነው። ሁለት አይነት የህላዌ እውነት ታይቶ አይታወቅም። ስለእዚህ፣ ሰው እሚለያየው በባህሉ ሳይሆን በልማድ፣ ወግ፣ ልማድአዊ ልምምዱ (traditional practices) ነው። አለባበስ፣ አመጋገብ፣ አጨፋፈር፣ ቋንቋ፣ ወዘተ. ተልካሻ የልዩነት ምንጭዎች እሚሆኑት ለእዚህ ነው። በዘመንዎች እሚዘምኑ፣ በተለያዩ ምክንያትዎች የተፈጠሩ እና የእሚቀያየሩ፣ የእሚዋዋሱ፣ የእሚጠፉ፣ የእሚበረዙ፣ ወዘተ. ጉዳይዎች ናቸው። ባህል ጭቂት ጭቂት ቢገለጥብአቸው እንጂ፣ በዋነኛነት አይመሰረትብአቸውም። ከእዛስ የራቀ ነው (far from it!)!

በባህል ሰው ሰውነትን ይለምድበት፣ ህላዌውን የአመቻችበት ዘንድ የእሚሰራው አረዳዱ ነው። ከተፈጥሮው ተሳስሮ፣ የመገኘት ኢላማውን እና እውነቱን የእሚቋደስበት፣ የእሚያሳካበት ምጡቅ ሀቅ ነው። ሰው ማን እንደሆነ፣ ከየት እንደመጣ፣ የት እንደ እሚነጉድ፣ ከአወቀ የባህሉን ምስጢር ደረሰበት ማለት ነው። ሰው ለመሰንበት እና ለመሻሻል፣ በሰፊ መንገድዎች ከቁስ፣ መንፈስ፣ የእማይታወቀው ሁሉ፣ የእሚነካካበት ስነስርአት ነው። ባህል ለሁሉ አንድ ነው። ዝርዝሩ፣ እንደ መልክአምድሩ፣ እንደ አሰለጣጠን ስፋት እና ጥልቀቱ፣ እንደ ልማድ እና ወጉ፣ ታሪክ፣ ተፅዕኖ፣ እንደ እምነት፣ ፍልስፍና፣ ወዘተ. ይበታተን እና ጥቂት የተዛነፈ የቀለምዎች ገጽታን ይጨብጥ አለ እንጂ ዲበ ህላዌው አይነካም። ባህል ማንነት ከሆነ፣ ባህል መበረዝ እና ባህል መለወጥ ወይም ባህል ወረራ እሚሰኙ ሃሳብዎች ፈጽሞ ሃሰት ይሆኑ ነበር። ማንነት አይበረዝም። አይቀየርም። አይለወጥም። ሰው ሰው ነው። ባህል ሲቀየር፣ ሲበረዝ፣ ወዘተ. ሰውየው ለምን አይናውዝ፣ አይሰክር፣ አያብድም። ማንነቱ ከተነካ ያ ተጠባቂ ነው። ማንነቱ አልተነካም ማለት ነው እንጂ። የሰው ባህልን በተዛባ መንገድ መረዳት ስለተከወነ እንጂ የአኗኗር ዘይቤ፣ ወግ፣ ልማድ፣ ወዘተ. ቢነካ፣ ቢቀየር፣ ቢበረዝ እንጂ፣ ከቶ አይለወጥም። ባህል ማንነት ከሆነ ማንነት ከቶ ከአልተቀየረ ስነአመክንዮአዊነቱ (its logic) ያን የአክል ፌዝ ነው። ባህል አይለወጥም፣ በጊዜም፣ በቦታም ወጥ ነው፤ ባህል ሰው መሆንን መለማመጃ እና ተለማምዶ መኖሪያ የአገነዛዘብዎች ሁሉ አከርካሪት ነው። ባህል ከተቀያየረ እማ፤ ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ከቡስካስ በስተጀርባን ምን ብሎ ጻፈው? ከሎ እና ነጭ ተመራማሪዋ ስለምን በሀመር ተዋድደው በአንድነት ተላምደው ቆዩ? ስለምን ጋልታምቤ አማራው የሀመር ሰው ሆኖ አረፈው? ስልምን ከሎ አዲስ አበባ ተስማምቶት ኖረ፣ ውጭስ ሀገር በአንድ መንፈስ ሆነው ከነጫ እንስት በመጨረሻ ተገለጡ? ሁሉም ቢዘዋወር እና ቢበረዝ፣ ዞሮዞሮ ከአውሮፓ፣ ሀመር እና አማራ ጎሳዎች ወጥ ሆነው በአንድ ነጥብ ውስጥ ተገናኝተው ተሳስረው አሉ። ባህል አንድ በመሆኑ፣ ተግባብተው ኖረው አሉ።

የአለያየአቸው ቋንቋ፣ ስልጣኔ መጠን (ያም ነገርን ሁሉ ቅኝ ወይም ይልቁን ቀጥታ የመግዛት አቅም ነው)፣ ቆዳቀለም፣ ወግ፣ ልማድ፣ ወዘተ. የእሚያለያይአቸው መሆን አልቻለም። በመሰረተ እውነት፣ ሰው አንድ ነው እና። የሰው ፍላጎ፣ ተፈጥሮ፣ ዘረመል፣ ወዘተ. አንድ ነው እና። በብዛት መልክአምድርአዊ ገጽታ የልዩነት መሰረት ነው እና። ለምሳሌ፣ በከፍተኛኛ የጉራጌ ተራራዎች የእሚገኝ ጉራጌ ከጉንችሬ ወደ አሳይታ ቢሄድ ቆጮ የአካባቢው ምግብ አይሆንለትም። የግመል ስጋ እና ወተት በተወዳጅ እንግዳ ደምብ ይቀርብለት አለ እንጂ፣ አፋር የኖረውም ጉንችሬ ቢመጣ ፍየል በእዚያ ስለእማትኖር ስጋዋን አያገኘውም። ይህ መለያየት ከቶ ባህል አይሰኝም። አመጋገብ ዘይቤ ወይም ስልት ብቻ ነው። ያም፣ በአካባቢው ተገኝቶ ለመበላት የበቃው ምግብ ማለትም ተፈጥሮ የእሚወስነው እንጂ ባህል ጋር የእሚገናኘው ነገር የለውም። ቢበዛ ልማድ እና የማህበረሰቡ መገለጫ እስኪሆን የተዘወተረ ልምምድ ነው። ባህል አይደለም። ቢበዛ የባህል ጥፍር የአክል የአነሰ አላባአዊ ነው። ያም፣ በዋናው ባህል ላይ የአነሰ እውነት አዋጪ’ ነው። አቶ ሙሐመድ ሰኢድ፣ በመቅደላ አምባ ኅዋአዊከተማ (university) የብዝሃ ባህል እና የልሳነ ብዙነት ጉዳዮች ትምህርት ሊቀጉባኤ (lecturer) የአዘጋጁት የክፍለትምህርቱ (subject) ቢጋር (outline) እሚከተለውን ይል አለ።

የባህል መነሻው ግለሰብ ቢሆንም ባህል ለመሆን ማህበረሰቡ ሊቀበለው ይገባል። ከሰው ልጅ ጋር እጅግ የተቆራኘ በመሆኑ፣ የሰው ልጅ ብቻ ሃብት ነው ማለት ይቻላል። የባህል ባለቤት መሆን የሚቻለው የማህበረሰብ አባላት መሆን ሲቻል ነው። ባህል በደም አይተላለፍም።

ይህ፤ እሚነግረንን እንይ። ባህል ከግለሰብእ ይጀምር አለ ይል አለ። ያ ከሆነ። ግለሰብ ባህልን ከየት አመጣው? ማን አቀበለው? እንዴት ወለደው? የእሚመስለው፤ ባህል ማለት የመገኘት እና እንደ ሰው ነኝ በቃ በእሚል የእሚዳብር የአረዳድ ሁሉ አንኳር እውነት ስለ ሆሆነ ነው። ቀጥሎ በደም የለም ይይለን አለ። ባህል በደም ከሌለ፣ ለምን ባህልን እና ቋንቋን (እሱም በደም የለም) የሰው መለያያ ብሎ እንደ መሳሪያ በልዩነቱ በማተኮር መለያየት ማመንጫ ተደረገ? ሀገር ቀርቶ ሰውዘር ሁሉ ባህሉ አንድ ነው። ያም ባህሪው ነው። ባህል ከባህሪይ የእሚወለድ ነው። የሰው ባህሪ ወይም ግብር ባህሉን ውለድ ይለው አለ። እርሱም የአበጀው አለ። አረዳዱ አንኳር በሆነ ደረጃ ሲዛነፍ ይህ ባህሉን የአዛንፍበት አለ። እንጂ የባህል መሰረትአዊ ለውጥ ተከውኖ አያውቅም። ይህ ማለት ባህል የስልጣኔ ዋና አላባ ነው። ሰው በሰለጠነ ቁጥር ስልጣኔውን እሚያንፀባርቅ ባህል ያቀልም አለ። ባህሉ ግን አይለወጥም። የሰው ባህል ለአለመለወጡ፣ ማረጋገጫው፣ ሰው አለመለወጡ ነው።

ሰው ሰው እንጂ መቼም በድህነት፣ በኋላቀርነት፣ በልህቀት፣ ሁሌም አንድ ነው – ሰው። ይህ፣ እንኳ እሚዛነፈው፣ ሰው ከግብሩ በተለየ አዲስ ባህል” ሲያዳብር ነው። ያም የባህል ለውጥ ይሰኝ ቢሆን እንኳ የሰፋ ለውጥ ግን እንዳይሆን እሚያስችሉ አጋጣሚዎች ይነገር አለጀ። ለምሳሌ የምወግሊ (ማን ከብ) ትርክትን ከ ሩድያርድ ኪፕሊንግ ዘ ቡክ ኦፍ ጀንግል ወይም ከታርዛን ትርክት መመልከት ይቻል አለ። ሁለቱ ገጸባህሪዎች፣ ሰው ሳሉ በሰው ግብር እንደ አሉ ከእንሰሳዎች ባህል ውስጥ ጠልቀው በመገኘት እና አብረው በመኖር እንመለከትአቸው አለን። ያ የባህል መበረዝ ነው። ሰው ባህሉ ማንነቱ ነው። ማንነቱ ሰው መሆን ነው። ዉሻ፣ ፍየለበግ፣ ወዘተ. ለእየራስአቸው ባህል አሉአቸው። ሰውም ከጥበበኛነቱ የተነሳ አብሮአቸው ባህሉን በማዛነፍ ሆኖ እንመለከተው አለን። ሁለተኛ፣ አዳም በገነት ከእንስሳዎች በተለየ አብሮነት ኖሮ አለ። የእዛ ባህል የተለየ ነው። በምድር ግን፣ ባህል ሰው መሆን ብቻ ሆኖ አለ። ሰው በመሆን የሰውመሆን ምንነት ይመሰረት አለ። እንደ አካባቢው፣ ስልጣኔው፣ ወዘተ. ይህ የእሚለያይ ይሆን አለ። ያ የባህል ቀለሙን ይለዋውጠው አለ። ባህል ግን ሰው የመሆን ጥበብ ብቻ ነው። ሰውዎች ልጅነትአቸው ስለእሚናፍቁት ግን በስህተት ባህል ተቀየረ ብለው ይገነዘቡት አለ። ጥቂት ይህ በትንሹ ቢሆንም እሚሳበቀው፣ ለምሳሌ የአክል በ ተስፋዬ ገብረአብ የስደተኛው ማስታወሻ አንድ አጭር ትርክት ነው። የኦሮሚያ ክልል እውቅ ሴቷ፣ ወደ አዲስ አበባ ገብታ ተራ ሰው ሆነች። ያ የባህል ቀለም መለወጥ የድሚፈጥረው የቀለምዎች ግጭት ነው። ሲበዛ ደግሞ፣ የሀገር (አዲስአበባ) አለመሰልጠን እና መደዴነት (mediocricity) ነው። ሁሉን አቃፊ ማህበረሰብእ አልተወጠነም እና።

ባህል አይቀየርም። ግን በተዛባ መልኩ የእሚቀየረው ባህል እሚሰኘው ለምሳሌ በአንድ ማህበረሰብእም የለም። አንድ ህዝብ በፊት ባሪያን በመያዝ ይገለጥ ከነበረ ቀጥሎ ከተወው፣ ባህሉ ተቀየረ ማለት ነው፤ በተሳሳተው አተያይ። ኢትዮጵያም፣ በጠለፋ እና ልጅ-ጋብቻ የታወቀች ሆና እስከ ቅርቡ ከመገኘቷ የተነሳ፣ ድፍረት ፊልምን ከውጭ እስከእዚህ ተመጥቶ ተመልክተን አለ። ዛሬ በአለምአቀፍ ጫናዎች እና ስልጣኔዎች የተነሳ ሴት ግርዛት፣ ህፃን-ጋብቻ ወዘተ. ከመደበኛው ሀገር እውነት እየተሰወረ የአለ እውነት እየሆነ ነው። ባህል ግን አልተለወጠም የአኗኗሩ ዘይቤ ተዛንፎ ነፃነት፣ እሪና፣ ወዘተ. እየተከበረ ስለመጣ ነው። ይህ ወጥ “ባህል” በጊዜ ለውጥ እንደ እማይገኝ የአሳየን አለ። በዘመነ አሃዝአዊነት (digitalization) እንኳ አኗኗር ተቀይሮ አለ። ባህል ግን አልተቀየረም። የአኗኗር ዘይቤ እንጂ።

ምክንያቱም ባህል ማንነት ከሆነ፣ ማንነት በለውጥዎቹ አልተለወጠም። የተለወጠው ማንነት የእሚጓዝበት 1ለም ብቻ ነው። ያም ዘመንአዊነት ነው። ስልጣኔ ባህል እሚቀይረው እሚሰኘው፣ አኗኗርን የአዘምነው አለ በእሚለው አተያይ እንጂ ማንመሆንን የአዛንፈው አለ በማለት አይደለም። አደፍርስ ልብወለድም፣ እንደ ቀሩት የወቅቱ አንድአንድ ድርሰትዎች የሰለጠነ ሀገር ለመመስረት ኢትዮጵያዎች ውጭ ተምረው ሲመጡ ሀገሩን የእማይስማማአቸው ሆነው ሲያገኙት አሳይቶን አለ። አደፍርስ ላይ የአደፍርስ አጎት አቶ ጥሶ ግን ደግ ማስታረቂያውን ሲቸሩ፣ መስማማት፣ መተጋገስ፣ አንድ ነን ዞሮዞሮ ብሎ በእየአግጣጫው ዉህድአዊነትን ማተኮር ደግ ነው … በማለት ይጠቁም አሉ። የዘመንአዊ ባህል አረዳድ ሰብእአዊነት ብቻ ነው። አንድሰው ለብቻው ቢኖር እንኳ፣ ሰው መሆንን ከከወነ፣ ሂደቱ ባህልን መማር ን ይከትትተ አለ ማለት ነው። ለእዛ ነው። ዘመንአዊው አለም ላይ ባህል ሁሉአቃፊነት ሆኖ የተለያዩ ግለሰብእዎች አንድ ላይ የእሚኖሩት። መንግስትአዊ አስተዳደርዎቹ ግን፣ ከኢህአዴግ. ጀምሮ፣ ባህልን እንደ ዘመነ ህዝብ መፍጠሪያ ከማድረግ ይልቅ፣ መልክአምድርዎች፣ አየርጠባይዎች፣ ቀለም፣ ወዘተ. የፈጠሩአቸውን የአኗኗር ዘዴ መለያየትዎች አድርገው በማስተኮር፣ ወደ ልዩነቱ ህዝቡ እንዲያማትር ብቻ እና ወደ መነጣጠል ስነልቦና እንዲያዘነበል የእሚሯሯጡት። ባህል እና ቋንቋ በእሚል ደግሞ፣ በአንድነት የቋንቋንም መለያየት እንደ ለጠጡት እና አበላሹት ባህል መከፋፈያ ማድረግ ይፈልግ አሉ።

ለምሳሌ፣ አፋርኛ ስለ ግመል ስድሳ ቃልዎችን በልዩነት ይገለገል አለ። ጉራግኛ ስለ እንሰት ወደ ሃምሳ ስድሳ ቃልዎችን አበጅቶ አለ። እንግሊዝኛ ስለ ሽልፍኖትዎች (technologies) የእማይቆጠሩ በሌላ ቋንቋ የሌሉ ወይም እምብዛም የሌሉ ቃልዎችን አከማችቶ አለ። ግእዝኛ፣ አምላክን የእሚጠራው በእማይቆጠሩ ልዩልዩ የቋንቋው ብቻ በእሚመስሉ ቃልዎች ዝርዝር ነው። ይህ የእሚያሳየን፣ ቋንቋም፣ የማንነት ምንጭ ወይም ከቶ ማንነት አለመሆኑን ነው። መልክአምድር እና አኗኗር አግጣጫ ቋንቋን በሰፊው ይገልጠው አለ። እንጂ አንድ የተለየ ማንነት በቋንቋው እምብዛም የለም። እንደ ህዝቡ አግጣጫ ሁሉ እንጂ ቋንቋ የማንመሆን ማስመሪያ አይደለም። አንድ ሰው፣ ኦሮምኛ እሚናገሩ ሰውዎች ቢወልዱት እና ቻይና ገብቶ ከልጅነቱ በማንዳሪን አፍ ፈትቶ ቢመለስ፣ ማንነቱ አልተቀየረም። አንደበቱ ግን በማንዳሪን የአወራ አለ።

ይህ ስህተት አረዳድ የእሚያዛንፈው እውነት ነው እንጂ እራሱን የቻለ እውነት ቋንቋን ከማንነት አያያይዝም። ሀገርን ይህ አረዳድ የእሚረብሻት መንግስት አስተዳደርዎች፣ በቋንቋ ላይ የእሚፈልጉት የመከፋፈልን ውጤት ስለሆነ ነው። ቋንቋዎች እጅግ የአነሰ አቅም ነው አሉአቸው – አንዱን ከሌላው በመለያየት። ቋንቋ ቀላል ጉዳይ ተደርጎ በአንድነት ወደ ውህድነት መቀራረብ ይቻል ነበር። አስተዳደርዎቹ የመከፋፈል እንጂ የማዋሃድ ሰበዝዎችን ከጋራው ህላዌ አይወስዱም። በቀላሉ በተርጓሚዎች የቱንም ግልጋሎት የቱም ቋንቋ እየአገኘ፣ በጋራ ግን እንደ አማርኛ፣ ግእዝ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረብኛከ ፣ እና ጣሊያንኛ በአለጀ ቋንቋዎች መስራት እና መወከል እሚቻል ነው። ፈጥኖ በአለም ውስጥ ለመስረግ እንድንችል፣ ፈጥኖ በሌላው አለምም ግርድና እንኳ ለመቀጠር ከሌላ የድሃድሃ ህዝብዎች ለመፎካከር እንዲሁም ፈጥኖ ለመማር እና በቀላሉ አለሙን ለማወቅ ይህ ይረዳን ነበር። አለም በየቱም ቋንቋ ሰልጥና ንግዷን በገዢው ቋንቋ አስማምታ በማቅረብ ታቀላጥፍ አለች። ያንን ደረጃ ግን፣ ቀርቶ፣ በአንድ ቀላል መንገድ ለመግባባት እድሉንም ስነውሳኔአወከ (political) የማድረግ አዝማሚያ ይበዛ አለ። የቋንቋውን ከፋፋይነት አቅም ማጎልበትን ግን አስተዳደርዎቹ ሆንብለው ይደግፉት አሉ። ውህደትን አያፈጥንም ሲጀምርም አይቀበልም። ቢያንስ የእዛ እንደምታው የተረጋገጠ ነው።

በደፈናው፣ ህዝብን በባህል እና ቋንቋ አገነዛዘቡ እንዲከፋፍሉት እማይደረጉ መፈንቅለድንጋይዎች የሉም። ቢሆንም፤ ባህል እና ቋንቋ ዘመንአዊ አያያዝን አግኝተው አዲስ የኢትዮጵያ ሀገር መመስረትን እውነታ ማድረግ ይቻል ነበር። ኢትዮጵያ መመስረት የእሚገባት፣ በአንድነት ብቻ ነው። በተረፈ፣ አንድ ሀገር ሆኖ ሳለ የተገጣጠበ ህዝብ ሆኖ፣ በመጎዳዳት እና መጠላለፍ ትርፍ ብቻ መኖር ከንቱነት ነው። ለአዲስ ኢትዮጵያ ደግሞ፣ የጎሳ ጉዳይዎችን የእሚለጥጡ እና ወደር የእሚያሳጡ አካሄድዎች ሀ መታጠፍ አለብአቸው። ባህል አንድ ነው። አብሮ ሰው በመሆን መኖር የእሚቻል ነው። ባህልን በዝብአረዳድ (misunderstanding) ሀገርአዊነት ማብረሻ ማድረግ፣ ከፍተኛ የጎልማሳአዊነት በሀገር መጥፋቱ ዐብይ ምልክቱ ነው። ባህል፣ ቋንቋም ሰውን አይበትኑትም። ቋንቋ አለሙን ለመረዳት ሰው የአበጀው መሳሪያ እንጂ፣ እኔ የተለየሁበት ነው ብሎ እሚፈጥረው መሳሪያ አይደለም።

ቋንቋን የእሚገለገለው ሃሳብ ለመግለጥ እና መቀበል እንጂ የተለየ መሆኑን ለማስመስከር አይደለም። በቋንቋ እና ባህል ሀገር የአሰራር ስምምነትዎችን እንጂ ወጥ ልዩነትን አትመሰርትም፤ በዘመነ ዘመንአዊ ታሪክ። ስት አገነዛዘብ ሀገርን የእሚመራበት አካሄድ ተቀልብሶከ እውቀት ወደ ብሔርአዊ መስመር እንዲወጣ ሀገር ትገደድ። አማራጩ፤ ፕሮፍ. መስፍን እንደ አሉት ፈጥኖ ከአልተስተካከለ በቁጥር ጨምረን ስንበዛ እና አመለካከትአችን እና ሀገርአዊ ስርአትአችን ስት እንደሆነ ሲቀጥል እውነትም እግዜር ይሁነን አስብል ነው። ሰው በጉራጌ ተራራዎች ድንገት ደርሶ ለምን ግመል የለምከ ለምን ሀመርኛ አይነገርም ብሎ የተለያየን ነን ከአለ፣ ሀገር የለችም። ኢትዮጵያ አልተመሰረተችም። የአዲስ ኢትዮጵያ ናፍቆት ይንበልበል ያም ቢያንስ ለሰውዘር ቤት እንደሆነችው ባትሆንም ለዜጋዎች ግን ቤት እንድትሆን እሚታስችል ሀገር የአስፈልግ አለ።

ጠሚ. አብይ አህመድ፣ የተሾሙ ሰሞን ገና አፍላ ጠሚ. ሳሉ (እጅግ በጥቂት ወርዎች ውስጥ) “አትተኙ” ብለው ዜጋዎች እንደተናገሩት፣ አስተዳደር በአለመተኛት ማገልገል እና ይህን መምራት የእሚገባው ዋናው ሰውነት የተሰጠው አካል ነው። ኦዲት የእሚደረገው በሌላ ዘመን ይሆን አለ፤ ግን የውድቀት ዝግመት አሁንም እንደ ቀጠለ ነው። ወደ ዘመንአዊ ሀገር ምስረታ መጓዝ አስገዳጅ ቢሆንም እንደ ጨቅላ ጠራጊ ዋናው ቆሻሻ – የቋንቋዎች እና በተለየ የባህል ዝብአረዳዱ – እየተቆረፈ ነው። ዛሬም እንጉርጉሮ!

—–

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s