Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ወል-ንቃተህሊና መጥፋት፡ ኢትዮጵያ ግንባታ ህጸጽ ተውሳክ

About how Ethiopia is consistently missing its modern nation building chances because common psychology and consciousness are not germinated and every attempt seem to be doomed be a repeating of preceding generation’s attempts.

“የደጋውም መቶ እምዬ ይላታል፤የቆላውም መቶ እምዬ ይላታል፤ጣሊያን አልወረረ ተኩስ አልተተኮስ፤በግላችን ጉዳይ ቤታችን ፈረሰ፤ፍርጃ!”

የቆላውም መቶ እምዬ ይላታል፤ጣሊያን አልወረረ ተኩስ አልተተኮስ፤በግላችን ጉዳይ ቤታችን ፈረሰ፤ፍርጃ!”

(ኀይለየሱስ ፈይሳ፤ አልመስል አለኝ፤ ሙግ. (=ሙዚቃ ግጥም፤ 2012ዓም።)
—-

“ከዜሮ የመጀመር አባዜን ትተን በቀደመው ለመገንባት መልመድ አለብን።”

(ጠሚ. አብይ አህመድ፤ 2010ዓም.፤ የድሮ መንግስትቤት (4ኪሎ) ማስዋብን በተመለከተ)

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 27th 2021Gc.,

በኢትዮጵያ የመሻሻል ፍላጎት፤ ብዙ እንጭጭ ጉዳይዎች ይጀመር አሉ። እሚደርሱት አጭር ማብቂያ እንጂ ተገቢ ፍፃሜአቸው አይደለም። ከምንም በላይ፤ ሀገርን እንደ እሚታለመው እና ፍፁም ኢትዮጵያ እንደ እሚጠበቀው (ተምኔትዮጵያ) መመስረት ቀርቶ ከድሀነት እራስን መነጠል አልተቻለም። ስነምጣኔ፣ ስነውሳኔ (politics)፣ ባህል፣ ህግ፣ ወዘተ. በእየ ዘርፉ፣ ሀገር መለወጥ የእሚገባት የዘርፍ አይነትዎች ናቸው። ነገርግን፤ ለሁሉም በእየዘርፉ ለውጥን ሲታገል፤ የጋራ የሆነ አንድ ስህተት – ስለእዚህ እምቅ መፍትሔ – በመደጋገም ሲረሳ ይታይ አለ፤ በግልጥ። የወል ንቃተተህሊና ወይም ማእከልአዊ ወይም የአልተበታተነ ወይም አንድ ወጥ የአመለካከት እውነት ግንባታ አስፈላጊነት ነው።
ለምን ሁሌም ተመሳሳይ ችግር በሀገር አደባባይ ይደመጥ አለ? ለምን ወጥ የሆነ የመፍትሔ አግጣጫ እየተተነበየ እና እየታለመ ለውጥ ግን ይርቅ አለ? አጭር መግለጫ መሆን ከቻለ፤ ለምን በ ቀኃሥ. ዘመነ መንግስት አማርኛ ቋንቋ በብዙ ጎንዎቹ ይሻሻል ተባለ? ዛሬም ያው ጥያቄ ተነሺ ሆነ? ለምን እንደ ጃፓን ይሰልጠን እየተባለ ያኔ ተሰበከ? ዛሬም ሀገርአዊ ቀለም የአለው ስልጣኔ ይከወን ተባለ? ምንም የለውጥ ፍላጎት እሳቤ ሳይቀነስ ሳይጨመር፣ በመደጋገም ሁሉም በመነገር እና በመደገም ቀጠለ? ከህልም እቅድ በተረፈ ተግባሩም፤ አንዱ አስተዳደር ሲገባ ሌላ የቀደመውን ትትረት አፍርሶ እና ዘወትር ነቅፎ መሄድ ሆነ? ለምን የባህል ለውጥ እና ባህል ወረራ አለብን እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነገረ ለውጥ ግን ቀረ? ለምን ሁሉም ለኢትዮጵያ ዕድገት አላሚ ግን ምንም ለውጥ ጠፊ ሆነ?
እንደ አልንው፤ የእየዘርፍ ጉዳዩን ትተን፣ የእምንመለከተው የጋራ የዘርፍዎች ሁሉ እና የአንድ ባህል አላባአዊ የውድቀቱን አመክንዮ ነው። ያም፤ ቀጣይነት የአለው ሀገርአዊ ንቃተህሊና የመገንባት እውነቱን ነው። ምንም ቢሰራ፣ ያንን ከመርሳት አታላይነት መላቀቅ በምትኩ የቀደመውን ከዛሬ ማጣበቅ ጋር የእሚያያዝ የንቃተህሊና አላባአዊ ዙሪያ የአለ እሳቤ ነው። ማን ምን አደረገ? ለምን ዛሬ በሌላ ሰው ተደገመ? እነእዚህን በይፋ ግንኙነትዎች መዘርዘር የአስፈልግ አለ። አንድ አአዲስ ሃሳብ ሲመጣ፣ የቀደመ ተመሳሳይ የነበረውን ጉዳይ መልሶ መጥራት ይገባ አለ። የቀደመውን ማስታወስ ከተቻለ አዲስ መጪው ከዜሮ እሚያስጀምረን አይሆንም። የእምናውቀው ሃሳብን ነው የእሚነግረን። አዲስ ነገርን እንዲያክል እንጂ የጋራ ንቃተህሊናአችን የእሚያውቀው የሆነ ጉዳይ ነው። የጋራ እውቀት፣ ትንታኔዎች፣ ጥበቃዎች፣ ወዘተ. በእየዘርፉ ይኖሩን አሉመ የወቅቱን ችግር እና የአለንበትን አንድ የእድገት እርምጃ አንረሳውም። በእዛ የንቃተህሊና ደረጃ እኩል አብረን እንደ ሀገር እና ህዝብ ቆመን አለን።
ብዙጊዜ እሚገርመው የእየዘርፉ የይዘት ችግር አንዱ አንዳንዴ ዋነኛው ችግር ይሆን አለ። ለምሳሌ በስነውሳኔው፣ ገና መቶ አመት እድሜ የደለን ነን፤ ወይም ከሉሲ ጀምሮ የተመሰረትን ነን ወዘተ. እሚሉ ክርክርዎች ወደ አስተዳደር ጉዳይ ይፈስስ አሉ። ግን፣ እነእዚህን ማጥራት አንድ የሀገር ወጥ ስነልቦና የአለመመስረት ጉዳይ ነው። ሀገር በተፈለገው ደረጃ አልተመሰረተችም። ፕሮፍ. መራራ ጉዲና እንዲናገሩት፣ ሀገር ገና ከአዲስ በእሚፈጠር ዘመንአዊ የጋራ ቃልኪዳን መመስረት ባት። ይህ የሀገር ግንባታ አንድ ዘርፍ = ስነውሳኔ – ውስጥአዊ ችግሩ ነው። ግን፣ በተደጋጋሚ በእየወቅቱ የእሚነሳ ነው። በጉዳዮች ሁሉ የጋራ ንቃተህሊና ተይዞ መጓዝ ቢለመድ አንድ እሚታከምበት አማራጭ ከእዚህ አያያዝ ይመነጭ አለ። ለምሳሌ ቀጣዩ ሰው እንጭጭ እድሜ የደለን ነን ብሎ ሲነሳ ያ ሃሳብ ቀድሞ ጠልሎ ተብላልቶ ስለአልተቀመጠ ከአዲስ ተጭሮ ተወርቶ የእሚቋጭ ነው። እንጂ ከእዚህ በፊት የተባለው ተሰብስቦ በሙያተኛዎች ተወርቶ አንድ ነቢብ (theory) ወጥቶለት በስም የእሚጠቀስ የጋራ እውቀት የሆነ አይደለም። ለምሳሌ በተራ አያያዝ ለማብራራት፣ “መራራ ጉዲና ነቢብ” ተብሎ አልተሰየመም። ቢሰየም፤ የህዝብ እውቀት ይሆን አለ። የጋራ ጉዳይ በመሆኑ፣ ሁሉም በተራ በጥራዝነጠቅ ወሬ አስሬ አያነሳውም። መራራ ጉዲና ነቢብ ከተባለ፣ በአጭሩ የህዝቡ እሳቤ ጠልለፐ ሀገር በዘመነ መንገድ አዲስ ቋበት አጥልቃ ትሞሸር እሚል እሳቤ ይሆን እና ሁሉ የእሚያውቀው ይሆን አለ። የወል ንቃተህሊና ተመሰረተ። በእርሱ ቀጣዩ ጉዳይን መገንባት የእሚቻል ይሆን አለ። ቀጣዩ መሰል ሃሳብ የያዘ ሰው አዲስ ልፍለፋ እና ታጥቦ ጭቃ የሀገር ቀልድ ትግልን አይከውንም – በፊትለፊትአችን።
የመነሻሃሳቡ እሳቤ ከጠራ፣ አንድ አብነት እንድገም። ያም፤ የአማርኛ ቋንቋ ትግል ይሁን። ምእት የደረሰ ትግል አማርኛን ለማሻሻል ተደርጎ አለ። የጋራ ስነልቦናአዊ መመጣጠን በህዝቡ ዘንድ ግን የለም። ለምሳሌ፤ ብዙ የተለያዩ ሃሳብዎች በጉዳዩ ቢኖሩም አንድ ብለን የማጥበቅ/ማላላት ጉዳይን እንይ። ሃዲስ አለምአየሁ የአቀረቡት ሃሳብ አለ። ያንን ማንም አንድ ስያሜ ሰጥቶ አላጠራውም። ነገ ለሄላው ተነስቶ እሚመረምረው እና በግሉ ታግሎ እሚደርስበት ተመሳሳይ ጉዳይ ይሆን አለ። የሃዲስ ፊደል ሃሳብ በእሚሟም ለምሳሷሴ መሰየም የአለበት የሀገር ችግር የሀገር እውቀት ወይም አንድ ሃሳብ ነው። ጠርተፐ በጋራ እውቀትነት ተይዞ በቀላሏሉ የጋራ አመለካከት እንዲሆን ይህ ቢደረግ፣ የጋራ ንቃተህሊናው የእሚቆመው፣ አንድ የተሟላ የሙከራ ሃሳብ ተይዞ እንደ ተቆመ ነው። ቀጣዩ ሰው ወደ ጉዳዩ ከገባ ያ ስያሜ በቀላሏሉ እሚደረስበት (accessible) ይሆንለት አለ። በእዛ ጅማሮ መወያየት ከተቻለ፣ ሀገር አንድ ጉዳይዋን ወደፊት የመገንባት እንጂ በቀደመው ምትክ አዲስ ወለል የማበጀት ሞኝነትን አትከውንም፤ ሁሌ እንደ እምትሰራው እና በመሳለቂያነት ደረጃ የአለም ቂጥ እንደ ሆነችው። በተመሳሳይ ሁለተኛ ነቁጥ ብንነቅስ፣ የፊደልገበታ ጉዳዩ ለምእት ምሁር ከመፍቀሬ-ለውጥ የሆነውን አማተር ሲያነታርክ ቆይቶ አለ። ይህ በተሰናሰለ መንገድ ጠርቶ፣ ተመድቦ፣ ተጠንቶ አልተቀመጠም። የተጨነቀ ወይም ሀቀኛ ተማሪ አማርኛ ፊደልገበታው ግራ ቢያጋባው መልስ የለም። የጠለለ የውይይት እና ዳግምርምርዎች (researches) እውነት የለም። ደግሞ በግሉ ተዘፍቆ በችግሩ እና መፍትሔ ፍለጋው ይዋኝ አለ፤ ይህ ምስኪን ተማሪ። በመጨረሻ፣ የእሚደርሰው ቀድሞ የተሞከረው እውነት ላይ ነው። ከዜሮ ጀመረ። የጋራ ንቃተህሊና አልነበረም እና አዲስ ሊያቆጠቁጥ ሞመረ። ሀገር ግን በአንድ
ይህ በኢትዮጵያ የመለወጥ ህልም አንዱ ራሱን የቻለ አዲስ መሰናክል ሆኖ አለ። ያም አአምርኩሎነት (I-Know-it-all) ማንነትን ለሁሉ የሰጠ ሆነ። ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም እንደ ተናገሩት፣ ሁሉ ተናጋሪ፣ ምላስ የደለው አውሪ፣ የተማረ ሁሉ አዋቂ፣ በሆነበት ሀገር ጥራዝነጠቅነት በዝቶ፣ ሀገር መሰማማት አልቻለችም። (ዛሬም እንደ ትላንት)። ይህን ነቢብ መሰየም ተገቢ ነው። አአምርኩሎነት ብለን ብናጠናው፤ ማከሚያው የቀደመ እውቀት እና ውጥን አለ ብሎ የተነሳውን ጀማሪ መመለስ ነው። ለተሻለ ቀጣዩ ደረጃ ስራ ይነሳሳ አለ እንደገና መጥቶ የአለፈን አየደግምም። አንድም ሁሉ አዋቂነት የበዛስ ይህ ወል ንቃተህሊና ስለአልዳበረ እና በጋራ መጓዝ ስለሌለ ነው። የቀደመ ትውልድ የሰራው ለእዚህ ትውልድ በዓድ ነው። ከዛሬ ሙለራዎች አልተጣበቀም። የቀደመውን ማከም፣ ጭራሽ መንተራስ አይታሰብም። አንዳንዴ፤ እንደ ኗሪ አልባ ጎጆነት ነው። የቀደመውን ንቆ መተው አንዱ ገጽታው በመሆኑ። ግን የእሚናቅ ለሆነ አብራርቶ ገልጦ፣ ሰይሞት ተናግሮ የጋራ እውቀት ቢያደርጉት ሀገር አኩሪ አካሄድ ነው። ለጠቢ (for posterity) አዲስ ትግል እንጂ ድግግሞሽ አይፈቅድም። የሙከራ ሞግሼ ከመከወን፣ ታካይ አሻራ ማከል ትውልድአዊ ቅብብሎሽ አስርፆ ሀገርን ወደፊት የአስፈነጥር አለ።
አንዳንዴ፣ ተራ የአካደሚክ ትትረት ነው። በእየዘርፉ የተከወኑትን እዚህ ከእዚህ በሆነ እሳቤ (ሀገርአብቅል_እውቀት) ማጥናት ነው። ሀገርበቀል እውቀት ሳይሆን ያ የአለ ልማድ ነው እና ሀገር ገንባ እሚሰኝ እውቀት ነው። ያንን አንዳንዴ በነፃ መንገድ ሀገርን ከማጥናት እና ከተለመደ የአንቀሳቃሽ (machine) ማስተማሪያ መንገድ መውጣት እውነትን የእሚናገር ነው። የሀገር እንቅስቃሴዎችን አጥንቶ በአደራስ ነቢብ እና ስያሜ እየአጎሩ እንቅስቃሴዎችን ማደርጀት እና ለቀላሏል ልኮት (reference) ማዘጋጀት የተራ ትምህርት አለም ስራ ይመስል አለ። ስርአተትምህርቱ የሀገር እውነትን አካትቶ አያስተምርም። የተደጋገመ እና መሰረትአዊ እውቀት እንጂ የሀገር ጥናት እና ሀገርን በተለየ ገሀዷ መሰረት እንዲአጠኗት አስቻይ አግጣጫንም አያስጨብጥም።
አንዳንዴ ደግሞ፤ የመወያየት እና የዘመነ ልውውጥ (exchange) በህዝብ መሀከል የመከወን እውነት ነው። ሀገር እምትገናኝበት መደበኛው የጋዜጠኛነት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ ወዘተ. መንገድዎች፣ በእዚህ እሳቤ አይመሩም። ወቅትአዊ ወሬውን የመግለጥ ጉዳዩ በቂ ተደርጎ ይወሰድ አለ። አዋቂ ጠያቂ አዋቂ አውሪ አዋቂ ዳግተመራማሪ ከላይ የለም። ጎልማሳዎች ገና የአልተማሩ እንጂ መጪውን ታዳጊ ተቆጣጣሪ አይደሉም። የመደማመጥ ባህል ኦና የሆነው፣ በእውቀት እና አተያይ ወጥ ሀገርአዊ አግጣጫ ስለሌለ ነው።
ሀገር በቅብብል ትገነባ አለች እሚለው ተራ የሆነ እና መሬት የመምታት የአክል የተሳተ እውቀት፤ ትልቅ አንድ መገለጫው ይህ ነው። በደፈናው፤ የጋራ እውቀት፣ ስነልቦና፣ የምርመራ አግጣጫ፣ ወደ የጋራ ህልም፣ አንድነት፣ የመሰልጠን ትልም፣ ወዘተ. ከታች ናቸው። እነእዚህ ወል ንቃተህሊና የእሚፈጥሩት ነገርዎች ትውልዱ ተመሳሳይ ነገር ከተነጋገረ እውን እሚሆኑ ናቸው። ቀጣዩ ቀን፣ በቀደመው ሀገርአዊ እውነት ወይም ኑባሬ መቀጠል አለበት። የእዛ አካሄድ፣ ተሞክሮን ዋጋ ወሰጥ አለ። ከተሞክሮ ሁሉ አዲስ ግኝት ከተጨለፈ፣ የሀገር ትላንቷ ተሞክሮ አዲስ ሀገር ለነዋ አቀጣጣይ ኋኙ ነው። ሰበበእውነቱ፣ እጅግ መሰረትአዊ ነው። ነገን በዛሬ መርፌ ከነገወዲያ መስፋት ማለት ይህ ነው። የአለፈውን ዋጋ መስጠት ማለት ይህ ነው። በእርሱ ላይ መካብ ማለት ነገን ማክበር ነው ማለት ይህ ነው። የቱም ማህበረሰብእ፣ በአቋራጭ አይገነባም፤ ይህን የጋራ ስነልቦና የአንድ ማንነት ፍኖትን መፍጠር እጅግ ዋልታው ነው። የአለፈውን ሙከራ ሁሉ ማንጠልጠል እና ቀጣዩ የሀገር ቀን እንዲመለከተው ማስቻል ግዴታ ነው። አማራጩ፤ መዝረክረክ፣ የውድቀት ድግግሞሽ፣ ጥራዝነጠቅነትዎች፣ ስንፍናዎች፣ ዞሮ ማፈርዎች ናቸው። የጎልማሳ ወይም አባትነት (አባትነት ከፆታ ውጭ የአለ እሳቤ ነው) የ ሀገር አፈጣጠር ነገር እንዲኖር፤ ሙከራዎችን፣ ተሞክሮዎችን ለልጅዎች ማውረስ እነእርሱን የግል የግድ ቅጥያ ማድረግ የደፈና ጉዳዩ ስሩ ነው። አንድ የህይወት ዘመን ዋጋውን ቢያገኝ፤ ማንም ከዜሮ አይጀምርም። የአለፈውን ዋጋ መስጠት፤ ዛሬ አብሮ ወደ ኋላ ተመልሶ የነበሩትን በመተንተን፤ ዘፋኝ “…የኛ ጥበብ መሰረቱ…የኋላው ከሌለ የሌም የፊቱ…” እንደአለው፣ የአሉንን ኢትዮጵያአዊ ስህተትዎች ደና ስኬትዎች ወደ አሁን መጥራት አስፈላጊነቱ በግዴታውዴታ ደረጃ ነው፨

—–

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s