Categories
Uncategorized

ወደ መሸጦነት እየተከረበተ የእሚገኘው “ምሁርአዊ አስተያየት”

About how academicians are being unprofessional in Ethiopia and comment helping the government as a well and widely growing culture.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 28th 2021

(ተያይዘው) ለአለፉት 3 ዓመትዎች – ድህረ ኢህአዴግ. – ከተገለጡ አዲስ የለውጥ መንገድዎች መሀከል፣ አንዱ የምሁርዎች የስነውሳኔ (politics) አስተዋፅዖ ነው። እንደ ቀደመው አስተዳደር የተማሩትን እና የእሚቃወሙትን ከማሰቃየት፣ ማሰር፣ ወዘተ. ወደ ያንያን አለመከወን ተመጥቶ አለ። የመሰለው፣ ሲጀመር አካባቢ፣ እንዲያውም ሹመት፣ ተሳትፎ፣ እና ነፃነት ለእነዚህ የማህበረሰብእ አባት-ሚና አንድ ተጫዋችዎች ቀን የወጣ ነበር። በሂደት፣ የተለየ ዘዴአማአዊነት (strategy) እንጂ ከልብ የፈለቀ ለውጥ አልሆነም። ከማሰር፣ ማሰቃየት፣ ማበሳጨት፣ እና ህዝቡን በአስተዳደሩ ከማነሳሳት፣ መምህር እና ምሁር እሚሰኙትን ቀጥሮ በእራስ ጎን ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው ተብሎ የታሰበ ነው። በእየስፍራው ሰው የእሚያውቅአቸው መምህርዎች እና ግለሰብእዎች በሹመት ወደ አስተዳደሩ አጋዥነት ዞረው አሉ። አሁን፣ ምንም የረባ ሊቅአዊ ተግባርዎችን ሲከውኑ አይስተዋልም። የአስተዳደሩን ክፍተትዎችም ከእራስአቸው ሚና በመደመር ይንከባከቡት አለ። ከምንም በላይ፣ ወደ ሙያአዊ፣ እውቀት-አዊ፣ እውቅናአቸው እሚያስጠብቀው፣ ወዘተ. አስተዋፅዖ ለመሻገር አልተቻለአቸውም። ሙያአቸው፣ እና እውቅናአቸው አስተዳደርአዊ ጠለፋ ላይ አድርሶአቸው ከእዛም እጅ ሰጪነትን አስከትለው በሙያ ማገልገል ግን ሳይችሉ ቀርተው አሉ። ይህ አንቀጽ፣ እዚህ ነጥቡን ይግታው። ተጨማሪ ፈላጊ መነሻ እይታ እና አንድ የርእሱ ጉዳይ እንጂ ዋናው ጉዳይ አይደለም። ያ ተከታዩ ብቻ ነው።

በእየዋናዋና መገናኛ-ብዙሃንዎቹ፤ በተለይ ትእይንተመስኮት እና መስኮተድምጽ ጣቢያዎች፣ የምሁርዎች አስተያየት በብዙ ጉዳይዎች ይቀርብ አለ።

“…ከእዚህ ኅዋአዊከተማ (university) የእዚህ ትምህርት-ክፍል መምህር በጉዳዩ ይህን ያንን አክለውልን አሉ…”

ችግርዎቹ ብዙ ናቸው።

፩) እሚቀርበው የምሁር ሃሳብ መንግስት የእሚከውነው ስራ ወይም የዘገባው ሃሳብ ተገቢ መሆኑን እሚናገር አስተያየት ነው።

፪) ቢያንስ፣ ያንን የእሚቃረን ሃሳብ ከአለ ሌላ ተቃራኒ ወይም ገለልተኛ ሃሳብም ከእከሌ መምህር ገጥሞን አለ እሚል ምሁር አስተያየት ፍለጋ የለም። እውቀት ግን የተለየ ክርክርቴ አለው።

፫) እጅግ ደካማ እና ማንም መመስከር እሚችለው ሃሳብ እንጂ የተወሳሰበ እና ዘገባውን ምሁር የቃኘው አያስመስሉትም። የወጪወራጅ፣ መንገደኛ፣ ወይም ተማሪ አስተያየት ቢባል እና ቢቀርብ ያው ነው እንጂ ፍፁም የተመነጠረ እና የሰመጠ (detailed) አተያይ አይቀርብበትም። ለምሳሌ፤ ቁጥርአዊ፣ ንጽጽርአዊ፣ ወዘተ. መረጃዎች የሉም። የሰመጠ እይታዎች የሉም። ዘገባውን ብቻ የተማረ መሰከረለት እንዲባል ተራ ታካይ ሆኖ የሚቀርብ እንጂ ብሩህ ነጥብ የለውም።

፬) ምሁርአዊ አስተያየቱ አንዳንዴ ብቻ ለመጥቀስ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ወይም ሁለት አረፍተነገርዎች እንጂ በቂ ትንታኔ አይሰጡበትም።

፭) በደፈናው፣ ቆንጽሎ እቅጭ የጋዜጠኛው ዘገባ ነቁጧን አጠንክሮ ለማቅረብ፣ የህዝብ መገናኛብዙሃንዎች፣ “የምሁር አመለካከት” በእየዜናዎችአቸው ወይም ትንታኔዎችአቸው መሀከል ለመክተት የአስብ አሉ። መምህርዎች እሚከውኑአቸው የምሁር አተያይዎች፣ የተለመደ ኢላማአቸው፣ መንግስትን ደጋፊ እና ደጋፊ ብቻ አስተያየት መቸር እየሆነ ነው። ከሙያአዊ እውቀቱ እና መርኁ የተቦጨረ እንጂ የእሚፈስስ አስተያየትን አይሰጡም።

፮) የተለየ አመለካከት የሌለ ይመስል፤ ተቃራኒ አስተያየትዎችንም አይጠይቁም። የፕሮፓጋንዳ ኢላማውን ለማሳካት የተሰራው ዜና እሚጠይቅው ድምዳሜን ደጋፊ አስተያየት ለመሰብሰብ እከሌን አነጋግሬ አለሁ አይነት አካሄድ በተጨባጭ ሲመዘን የአለው እውነት ነው።
በፊት፤ ኢህአዴግ. የእዚህ ቀበሌ፣ ገጠር መንደር ሰውዎች ይህን ያንን ዓለም አቀፍ ውሳኔ በትጋት እንደ እሚጻረሩት ገለጡ ብለው የጉዳዩ እውቀት የሌሉአቸውን ሰውዎች ዳግምላሽ (reaction) በማስተላለፍ የተሰለቸ እና አቂያቂይ ልማድ በመከተል፣ ዘገባዎችን አሰልቺ እና አታካች ቀለም ይሰጥ ነበር። ብዙዎች ይቀልዱበት ነበር። በአስተዳደር ገልባጩ ብልጽግና አስተዳደር ስር ደግሞ፤ ያ የተለመደ ማታለያ ግብረመልስ ዘገባ የአለ እንደ ሆነ ቀነስ ግን ብሎ አለ። በምትኩ ግን የተቋቋመ መሳይ ይህ ዘገባ-አዘገጃጀት እየተከወነ ነው። የምሁርዎችን ስም በመገልገል፣ ለፕሮፓጋንዳ ጠንካራ ድጋፍን መሰብሰብ መወገዝ የእሚገባው ይመስል አለ። እየተቋቋመ የአለ ልማድ በመሆኑ ዳግ-ሊቃኙት ይገባ አለ።

የጋዜጠኛዎች እና አርታዒዎች አቅም ዘግናኝ ደካማ መሆኑ ይታወቅ አለ። የሙያ ስራአቸውም ህዝብን በሰላሳአመትዎች አንቅቶ አለ ከተባለ ባለጌ-ቅዠት ነው። የአስተዳደር ሰውዎች ጣልቃገብነት ሳይሆን ሙሉለሙሉ ቁጥጥር በህዝብ መገናኛብዙሃንዎች አለ (አንድአርግአቸው ጽጌ በተለይ የክልል ትመ. እና መድ. ጣቢያዎች የፓርቲዎች ነው እንጂ የህዝብ አስተዳደር የለብአቸውም ብለው በ2012ዓም. ኢሳት. ትመ. ተናግረው አለ)። ስለእዚህ፤ የዘገባ እና ጋዜጠኛነት አቅም እንደ ላሸቀው ሁሉ፣ የፓርቲ ልሳን የሆኑት እነእዚህ ተቋምዎች የማያወላዳ አስተዳደር-ዘመምነት የእዚህ አዲስ መጥፎ ባህል መንታ መነሻ ችግርዎች ናቸው። ይህ ባህልን ለመግታት አሁኑኑ እነሆ ማስተዋል ይጀመር። ነፃ የመረጃ እና ትንታኔ እውነት የንጽውሳኔ (democracy) እና ማእዶት (transformation) ወለልአቸው ነው። የነቃ ማህበረሰብእ ነፃ መረጃ ይመገበ አለ። ይህን በአደገኛ አካሄድ የማርከሱ አካሄድ አሁን እንደ ተመሰረተው መቋቋም ግን የለበትም። ትልቅ አህዝብ አደጋ እዚህ ተመስርቶ አለ – ሳይቃጠል በቅጠል።

የከፋው አንደምታ ደግሞ፣ ከፍተኛ ትምህርት-ተኮር ተቋም ውሥጥ፣ ተደጋጋሚ የግልጥ እውቀት ሳይሆን አስተዳደር ፍላጎት አርኪ ሃሳብዎችን ከእየኅዋአዊ ተቋሙ መስጠት እና መሰብሰብ ተቋምዎቹ ገለልተኛ የመሆንአቸውን ነገር የአበለሻሸው አለ። አስግቶ የእሚጠየቅ የነፃ አካደሚአዊ መረጃ እና እውቀት ምልልስዎች የአለመኖር ጥያቄ ደግሞ ዘገባዎቹነወ ብዓ ሳይሆን ትምህርት ተቀለምዎቹንም የአስጠይቅ አለ።

ከመምህርዎቹ ራስ ዳግመቃኘትን በዘለለ ለተቋምዎቹ፣ ይህ ጉዳይ አሳሳቢ እንዲሆን እነሆበእዚህ (hereby) ይታሰብ። በስመ ዳግ-ምርምር (research) ተቋም፣ ሀገርን ለአስተዳደር ሃሳብዎች አጋዥ መሆኑን ቢያንስ እንዲህ የአጥኑት። ጋዜጠኛነት አስተምረው ይህን ኢገለልተኛነት-አጥነትን ቸላ አይበሉት። በዘለለ፤ እንደ ተቋም ለከፋ ተፅዕኖ አይንቀሳቀሱም ተብሎ ይጠበቅ አለ እና ከጉዳዩ መራቅአቸው የከፋ ጉዳት በሀገር በመሰንዘሩ ስራአቸውን አይርሱት። ከትምህርት እውቀት ተጣራሽ፣ አስተዳደር ደጋፊነትን አስማሪ፣ ኢገለልተኛ፣ እና ነፃሜዳ የአልሆነ (ተቃራኒ ነቁጥዎችን/እይታዎችን እኩል አወዳድሮ ፍርዱን ለተደራሲ ብቻ እማይተው) ጋዜጠኛነትን አግዘው የእማያግዙ አስተያየትዎች ከሀገር አመንጣቂ እና ስራፈጣሪ ጠቢ አውጭ ተቋምዎች – በከበረ ስምአቸው የጦፈ መሸጦ – መስፍንወልደማሪያምአዊ መጠነቃል (vocabulary) – ነት ሲከወን ዝምታ ሀገር ክህደት ነው – ሙያ እና ቤረሙያ (ረቋም) ማርከስም። አስተዳደር አቃፊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህር አተስያየትን ለማከም ሀገር ትረባረብ፨


Leave a comment