Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ትንቢተ ዐማርኛ፡ ለጥቂት ተጽዕኖው የአንዣበበ የመሀከልሀገር “አማርኛ በእንግሊዝኛ ቅርፅ” ለውጥ

About the prophecy that Amharic will have a budding distinct structure and culture shift strengthened in coming decades in central Ethiopia, among its English/Arabic speakers who are using English’s structures and cultures in their “new” Amharic.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 02nd 2021GC., Get this piece in PDF

ስለ አማርኛ መፃዒ፣ ብዙ ተተንብዮ ባይገኝም፤ አንዳንድ (ትንቢትዎች) ግን አግኝቶ አለ። ለምሳሌ፤ በቅርብ መጪ አስርታት፣ አማርኛ በእንግሊዝኛ ቃልዎች ተገጥግጦ ይገኝ አለ እና ከእስከአሁኑ በበለጠ “አማ-ሊሽ” መሰኘቱ አይቀሬ ነው።
የዲን. ዳንኤል ክብረት፤ አማርኛ በ2030 አካባቢ አጭር ወግ፣ እሙን ይሆን አለ ማለት ነው። ሌላኛው፤ ከእዚህ ተመዥራጭ ቀላል ድምዳሜ አለ። ከሽልፍኖት (technology) ግዛት በልጦ ይሰወር አለ፤ የእውቀት፣ ዳግምርምር (research) እና ጥበብ ቋንቋነቱ ብሶ ይደይም አለ። መደዴ መግባቢያነቱ ከፍቶበት ይቀጥል አለ ወዘተ. በአጭሩ፤ የስልጣኔ ባለቤት የአልሆነ የተገኘውን አጭር ስልጣኔም የእማይጠቀልል ለዑዋላዊነቱ የተገረሰሰበት ቋንቋ ይደረግ አለ። እነእዚህ ሁለቱን አንድ እሚያደርግ፤ ትንቢትዎቹ እውን ለመሆን የመንግስት እና ህዝብ ባህል በአለበት መቀጠል አለበት፣ ወይም በቂ የአሁኑን ችግርዎች ማከም መከወን የለበትም። ለቋንቋ አማርኛ ሶስተኛ ትንቢትን ግን እናበልጽግ። ይህ የበለጠ ስራ ጠያቂ ሲሆን፣ በእሚያንቀላፉ የተለመዱት መንግስት፣ ማህበረሰብእ፣ ባህል፣ ትምህርት፣ ወዘተ. አስተዳደርዎች አያያዝ ከቶ የእሚያስጥሉት አይመስልም። ይህ የአማርኛ ጠቢ፣ በመሀከልሀገር (በተለይ ዋናዋና ከተማዎች) አማርኛ-በእንግሊዝኛ-ቅርጽ ይሰኝ አለ። የአማርኛው የቅርፀት ከእንግሊዝኛው ቅርጸት ወስዶ አማርኛውን መንሻፈፍ እየተፈጠረ ነው። ይህ አዲስ የአማርኛ ጠባይ ሆኖ ወደ መደበኛው አማርኛ (ቢያንስ የንግግር) አንድ ቀለም ሆኖ ይታከል አለ። መዋቅርአዊ-አማሊሽ ነው።
በአሁኑ አስርት አመት አማርኛ አንድ እየአስተናገደ የአለው ለውጥ ነው። ሲብራራ በእንግሊዝኛ መግባባት የለመዱ ታዳጊ ተናጋሪዎች እየአጠነከሩት የአለው አዲስ የአማርኛ ቅርፀት ነው። ያ፤ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቅርፀት የያዘ አማርኛ እየሆነ ነው። እሚመስለው፤ በእንግሊዝኛ እየተናገሩ በአማርኛ በቀጥታ (literally) እየተረጎሙት የአለ ነው። የቋንቋው ቅርፀት ወደ አማርኛ ስለ አልተመለሰ ግን ውርስ ትርጉም አይደለም። ቀጥተኛ-እና-እጅግ-ቀጥተኛ ከእንግሊዝኛ ቅርፀቱ ሳይዛነፍ ወደ አማርኛ የእሚገለበጥ እንግሊዝኛ አይነት (አማርኛ) ነው። በውጤቱ፤ ያ በአማርኛ የእማይገኙ ወይም የአልተለመዱ ቅርፀትዎች አሉት። በተለየ ደግሞ የእዚህ አዲስ የመሀከልሀገር አማርኛ እድገት፣ የመወጠኛ እሳቤዎቹ፤ የስነምግባር፣ አመለካከት አግጣጫ፣ የባህል መስመር፣ ወዘተ. ማስመልከት የሚችል ቅርፀት ማግኘቱ ነው። ለትኩረት የማስመር፣ መግለጥ እና ማፍረጥረጥ፣ ወዘተ. አቅሙ፣ ከአማርኛ እነእዛን መከወኛ ዘዴዎች በመለየቱ፣ ቅርፀቱን ከአዲስ አጣምሞ ገንብቶት አለ። ይህ ቅርፀት፣ በእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የአኗኗር ባህል የእሚገኝ ነፃነት፣ እውቀት፣ ርእዮት፣ ወዘተ. የእሚንፀባረቅበት ነው። እንግሊዝኛ በእዚያ የማፍረጥረጥ፣ የማስተኮር እና ቀላል-ግልጥ የመሆኑ እድሉ የበዛ ነው። ማለትም፣ አማርኛ እንዲያ ለመሆን የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀም አለ እንጂ በተፈጥሮው እንዲያ ስለአልተቸረ ያ ቅርፀት (structure) ወይም ቅጽ (form) የለበትም። ቋንቋ እና ተናጋሪው ማህበረሰብእ የተሳሠሩ በመሆንአቸው፣ የአማርኛ ቅርጽ ቁጥብነት፣ ግድየለሽነት፣ የላይየላይነት (ከአንገትበላይነት)፣ ወዘተ. እንጂ አለማወላዳት የለበትም። በሰዋሰው ተፈጥሮውም በመዝረክረኩ ወጥነትን በማጣቱ ቆራጥ መለዋወጫ አይደለም። ሥነማህበረሰብ-ቋንቋአዊ (Sociolinguistics) ገጽታዎቹን ከቀነጨብን ወደ ሰዋሰው ገጽታዎቹ እንሻገር።

በዋነኛ መገለጫው ከእዛ በአሻገር፣ ለ ተውላጠስምዎች ነፃ እውቅና ይቸር አለ። ግንባርስጋ ህላዌአቸው ወንጀል ሆኖብአቸው በስውር ከእየቃሉ የእሚጣበቁ ወስፋት ተውላጠስምዎች በአማርኛ ቢኖሩም፣ ይህኛው ልማድ ውስጥ ተውላጠስምዎችን ለግልአቸው ይገለገል አለ። ሐረግዎችም፣ በእንግሊዝኛ እንደ አሉ ታዋቂ ሀረግዎች በቅርጸት ተመሳስለው የእሚመሰረቱ ናቸው። የአረፍተነገር አንኳር ወይም አጽም ማረፊያ ግስዎችም ተለውጠው በእንግሊዝኛ አቻዎችአቸው ተተክተው አሉ። እንዲገባን አስከትለን በአብነት ዝርዝርዎች እንመለከትአቸው አለን።
ለምሳሌ፤ ጎረቤት የአገኘኋት ገና-ታዳጊ፣ በእንግሊዝኛ እና አረብኛ ፊልምዎች ስታድግ ከርማ፣ አማርኛ ብቸኛ አፍመፍቻዋ አይመስልም። አማርኛዋ እንዲሁ የእነእዛ ቋንቋዎች ቅርጽ የተከረበተበት ሆኖ አለ።

ለምሳሌ፤ “እኔ ዳቦ እፈልግ አለሁ።” እንጂ “ዳቦ እፈልግ አለሁ” አትልም። “እኔ እምፈልገው አንተ ከረሜላ እንድታመጣ ነው።” እንጂ “ከረሜላ አምጣልኝ” ወይም “ከረሜላ እንድታመጣልኝ እፈልግአለሁ።” አትልም። “ያን እሱ እኔን የነገረኝ መቼ ነው?” እንጂ “መች ነገረኝ?” አትልም። “ዉሀ አግኝልኝ!” (ጌት ሚ ዎተር ከእሚለው) እንጂ “ዉሀ አቀብለኝ/ስጠኝ/አምጣልኝ” አትልም። “ለእራት ምን እናገኝ አለን?” እንጂ “እራት ምንድነው እምንበላው?” አትልም። ወዘተ.

አማርኛ በእንግሊዝኛ ቅርፀትዎች ይነገር አሉ። የእንግሊዝኛ ባህል እና ከእዛ በላይ ደግሞ ቅርፀት ለአማርኛው መሰረቱ ሆኖት አለ። እሚመስለው፣ አመለካከት እሚከወነው፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው። ወደ አማርኛ በቀጥታ ይተረጎም አለ። ወይም፣ እሚመስለው፣ በፊልምዎቹ ባህል ይኖር አለ። እሚወራው እንደ ገጸባህሪዎቹ ነው። ስለእዚህ አማርኛው ለእዛ መሰል አረዳድ ብቁ አይደለም። ይህ በልጅዎች እሚመሰረት የአማርኛ ባህል አይደለም። በእነእርሱ እየቀረ አይደለም። ስለእዚህ አንድ ትንቢት ሆነ። አንደኛ ልጅዎቹ በእዛ ባህል ሊያድግ ይችል አሉ። ሁለተኛ ከፍ የአሉ ሰውዎችም፤ ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ እና የመኖር ባህሉ በመኖርአቸው የተነሳ እጅግ አድርገው፣ ይህን ልማድ አሁንአሁን ይገለገሉበት አለ። ከእዚህ የተነሳም፤ በትልልቅ ሰውዎችም (ከተሜ፣ ዳያስፖራ፣ ወዘተ.) የእሚገለገሉት ቋንቋ ባህል እየሆነ አለ። ከእዚህም የተነሳ፣ ይህ ለወደፊት እየበዛ በመሄድ፣ አንድ የቋንቋ አግጣጫ የመቅረጽ አቅሙ ትልቅ እየሆነ የመጣ ነው። እሚመጣ ይሆን አለ። አዝማሚያውን ለአስተዋለ የቋንቋ ባለሙያ ይህ አዲስ የአማርኛ ልማድ ነው። ለምሳሌ፤ በ ኢቢኤስ. ሄለን ሾ የእሚከታተል በእዛ እሚኖር ሀበሻ ውይይት ሲከውን ይህን ባህል ለማደን አያቅትም።
ጥቅም ወይስ ጉዳት አለው? እሚመስለው በደፈናው ጠቃሚ ነው። የአማርኛ ባህል መለወጥ አለበት። በተለይ በመሀከልሀገር የአለው አማርኛ ባለቤት የአጣ ክፉ ሰዋሰው እንደወረሰ በባህሉ በመሞት የእሚገኝ የቋንቋ ነገር ሆኖ አለ። ያንን ማስተካከል ተገቢ ነው። ማንም ጠልቆ አያያውም። ቢበዛ የሞግሼ ፊደል ይቀነስ ወይስ አይቀነስ፣ አማሊሽ አማርኛን ወረሰ፣ ወዘተ. ከፍተኛዎቹ የአማርኛ ላይ ክርክርዎች እየሆኑ የቀደመው ምእት የተከተለው ደግሞ በተለይ በቅርብ ገንኖ አሉ እንጂ አማርኛ መሰረትአዊ ስህተትዎቹን ስለተሸከመ እናክመው እሚሉ ውይይትዎች ገና ናቸው። በዘመንአዊው ሚዛን የስልጡን ህዝብ ቋንቋ ግን እንደ አልሆነ ገሀድ የወጣ ነው። (በተለይ መሀከልሀገር የአለው አማርኛ እንጂ የገጠር አማርኛ እጅግ የተሻለ እውነት በእርግጥ አለው።) ከእነእዚህ ስህተትዎቹ፤ አማርኛ እንዲላቀቅ ከፍተኛ ትግል ይጠይቅ አለ። እንደ ሰለጠነ ህዝብ መኖር የተቻለ ቀን የእሚነሳሱ እነእዚህ እልፍ ችግርዎቹ፣ ዛሬ ተትተው፣ አማርኛ በእዚህ የእንግሊዝኛ ቅርጸት ጥቂት ተንፈስ ሊል ይችል አለ። ብቸኛ ጉዳቱ፣ አማርኛ መሰል እድገትን በእራሱ ማበልፀግ ከቻለ ያንን መከተሉ መመከሩ፣ ነው። ያ የእራሱ ሰፊ ዳግምርምር ይጠየቅበት አለ። የቋንቋ ስውር ባህልንም በአማርኛ ከእሚገኘው የአማርኛ ተናጋሪ መሆን ስውር ተፅዕኖ ወደ እንግሊዝኛ የተነሳ ከእናገር ተናጋሪ ባህል ከደባለቀው እንጂ ሌላ ነገርዎች አይታዩም። ለምሳሌ አማሊሽ የአለው የአእምሮ አቅም ማነስ፣ የአንደበት አለመጥራት፣ የአስተሳሰብ በልጅዎች ጠርቶ የአለማደግ፣ ወዘተ. በእዚህ የለም። እንደውም፣ በተጠቀሱት ጉዳይዎች የተሻለ ጥቅም ከተገኘ የእሚገመት ነው። በደፈናው፤ አማርኛ ግልጠኛነት፣ አማያወላዳነት፣ ነፃነት፣ ወዘተ. በተግባቦት ልማዱ ስለሌለ እነእዛን ልማድዎች ወደ ማህበረሰቡ ለማምጣት ይህ አማራጭ ሊሆን የእሚችል ነው። ቋንቋ እና ባህል በመቀራረብአቸው፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋው ተያያዥ ልማዱ ወደ አማርኛው ተናጋሪ ሊጠራ እሚችልበት ይሆን አለ።

One reply on “ትንቢተ ዐማርኛ፡ ለጥቂት ተጽዕኖው የአንዣበበ የመሀከልሀገር “አማርኛ በእንግሊዝኛ ቅርፅ” ለውጥ”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s