Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics) ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

Propaganda Vocabularies Goes Too Bad for Ethiopian Public Media And Causes Further Worries [የፕሮፓጋንዳ መጠነቃልዎች በኢትዮጵያ ህዝብአዊ መገናኛብዙሃንዎች ጨፈገጉ እና ታካይ ጭንቀትንም ጎለጎሉ]

About the awkward propaganda Amharic vocabulary of Prosperity Party’s rule.

bY Binyam HAILEMESKEL Kidane, August 21, 2021GC., [እባሪዎች እና ምስልዎች የአካተት የእዚህ ጽሑፍ ተአዶ. (PDF) ስሪቱን ይውሰዱ]

“ጎሠኛን፣ ሸረኛን፣ ሴረኛን እና መሸጦን በቁጥጥር ስር ማዋል እና ደካማን እና ደሀን የእሚያጠቃ ጉልበተኛን እየተቋቋሙ ማሸነፍ፣… አገሩን የአስቸገሩ ጉልበተኛዎችን ሰብስቦ እድፍ ዉሃ ውስጥ መድፈቅ እና መቼም እንዳያንሰራሩ በላይአቸው ላይ የአክሱምን ሐውልት መጫን! ይኽ ከንዴት የእሚወጣ ስሜት ነው፤ ሰው ሲናደድ የእሚናገረውም ሆነ የእሚያደርገው ወደ እንስሳ ደረጃ ወርዶ ነው። እንዲህ የአለ መልክ የእሚገለጠው እንስሳአዊ ንዴት የእሚሰነዘርበትም መልስ የእዚያው ዓይነት እየሆነ ወደሰውነት ደረጃ ለማደግ በጣም አስቸጋሪ ይሆን አለ። [ይቺን ሀገር መልካም ጎኗን ከክፉው ገጽታዎቿ ጋር አብሮ ተረክቦ በተስፋ ለተማሩ ወጣትዎች ማስረከብ እሚችል አመራር የአስፈልግ አለ]

መስፍን ወልደማሪያም፤ “ዛሬም እንደ ትላንት?” ገ.19-20፤ አልፋ አታሚዎች፣ ሐምሌ 2012ዓም።

ቋንቋ አማርኛ፣ በመሀከልሀገር ለሰላሳ አመትዎች ዘግናኝ አፍጢም አወዳደቅ እየአሰቃየው ነው። ድኅረ-አብይ አህመድ (ዶር.) አስተዳደር መጀመር – ልክ እንደ ሌላው የአስተዳደር ቅርጽ፣ እና ቅፅ (administrative structure and form) አወዳደቁ – ከኢህአዴግ. አስተዳደር ባሽ የፕሮፓጋንዳ ቋንቋ አሰራሩም ደፍርሶ አለ። የመንግስት መገናኛብዙሃንዎች፣ በእውቅ የአስተዳደር (ካድሬ) አማርኛ (አማሊዝኛ) እንደ አሰለቹ እና አደነዘዙ የአብይ ከህዋሃት. ውስጥ ገልብጦ መውጣት (መስፍን ወልደማሪያም (ፕሮፍ.፣) ዛሬም እንደ ትላንት፣ ገ.43)፤ የተሻለ እውነት ቢያስጠብቅም፣ በብዙ ሃቅዎች ግን ከፊ ውድቀትዎች አሉ። አንዱ፤ መንግስትአዊ የመገናኛብዙሃንዎች አገልግሎት ቋንቋአቸው ተቆጣጣሪ ማጣት ነው። ንቁ የአካባቢ ማህበርአዊ/ፖለቲካአዊ ትችትዎች ተከታታይ ባልሆንም፤ ተቆጪ አባትአዊነት-መር ሃይባይዎችም ከአሉ አላስተዋልኩም። ከእምንመለከተው፣ እምንሰማው፣ በደፈናው፣ ፕሮፓጋንዳአዊ አማርኛ እጅግ አቅለሽላሽ ሆኖ አለ።
በተለይ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ.)፣ አንዳንዴ ኢቲቪ. የእሚደመጠው አማርኛ “ህፃንዎች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣትዎች፣ ሌላ ማንም ጤነኛ ሰውም…አያዳምጠው!” ከእሚል ማስጠንቀቂያ ተከትሎ አይከወንም። ቢሆንም፤ ውስጡ ግን የእማያልቅ የመጠነቃልዎች (vocabularies) መንከርፈፍ አለ። እጅግ አስከፊ በሆነ ደረጃ፣ የስድብ፣ ንቀት፣ ማጥላላት፣ ጸያፍ፣ ብልግና፣ ኢስነምግባርአዊ፣ ዘግናኝ፣ በብዙ መልኩ ተተርጓሚ (ለምሳሌ አንዱ ባለሀገር ሌላው ከአቋሙ የተነሳ ሀገርየለሽ ሆኖ፣ ከፍርድ ውጭ በመኮነን “ባንዳዎችን ማጽዳት…” ተብሎ ከፍተኛ ወንጀልአዊ እንደምታ ተጠቂ መሰኘት)፡ ወዘተ. ቃልዎች አሁንም አሁንም ይደመጥ አሉ። በተለይ ለልጅዎች አድማጭ/አዪዎች ግን አስፈሪ እና ሽብር-ነዢ ቃልዎችን በአስገራሚ ቸልታ ሲተላለፉ እናደምጥ አለን። ለምሳሌ፤ “ህዋሃት.ን ይኸው ልንቀብረው ነው”፤ “መቀበሪያውን እዚህ ልናደርገው ነው፤” “መቃብሩ ተቆፍሮለት አለ፤” “ላንዴ እና መጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬቱን ልንፈጽም ተዘጋጅተን አለ፤” “እዚህ ይድረሱ እንጂ አፈር ሣሣንጨናነቅ ልናለብስአቸው ተዘጋጅተን አለን (የደቡብጎንደር ብልጽግና ጽቤት. ኃላፊ፣ ነሃሴ 15ኛ ቀን 2013ዓም፣ አሚኮ. ዜና የመጨረሻውን፣ የወንድምማማችዎች ጠብ ቀርቶ የአለምአቀፍ ውጊያ እንኳ እማይፈቅደው አንድም ሳያስቀሩ የማጥፋት/መግደል ህገወጥነትን ለተሰበሰበው ህዝብ ሲሰብኩት) ተናግረውት አለ።)፣ ወዘተ. ለልጅዎች ትንግርት እና ረባሽ፤ ለአዋቂ ደግሞ እብድ ከአልሆኑ በቀረ ስነስርአትአጥ፣ ርቆ ማስተዋል ከግልጽስንፍና የከበደአቸው፣ ናቸው። ለሙያአዊ መዛኝዎች ደግሞ፣ መደበኛአዊ (of regular) ወይም ይፋ ወይም አደባባይአዊ (official or public)፣ አማርኛ መሆን እማይችሉ ናቸው። እነእዚህ አማርኛዎች የማህበረሰቡ መግባቢያ እና ትልቅ ዐውድ ወይም እውነትን መለዋወጫ ከሆኑ፣ መደበኛ፣ ጤነኛ እና ተስፋአለሽ አካሄድ በስምጡ ደፍርሶ አለ ማለት ነው።
ለነገሩ፤ ጠንካራው እና ጠርናፊው የኢህአዴግ. አስተዳደርአዊ እውነት ዛሬ የለም። ከእዚህ አንጻር እሚሻል የነበረው የፕሮፓጋንዳ መጠነቃልዎች ልማድ (አስቀያሚ ግን እንዲህ የአልተዝረከረከ እና መሳቀቂያ የእማይሆን) ከኢህአዴግ. ግልበጣ ጋር አብረውት ተሰውረው አሉ።
“ኢህአዴግ. አስተዳደር ዘመንዎች ውስጥ ከነበረው ጠንካራ የአምባግነና ስልት፣ ረገጣ ዘዴዎች፣ እና የፕሮፓጋንዳ እማይዛነፍ ወጥነት፣ ለማንም ማፈንገጥ ከባድ ነበር። እንኳን ለካድሬ እና ሰራተኛው፣ ህዝቡም በእጥበተአእምሮ አቅለሽላሹን ቋንቋ ተላምዶት ነበር።”
በደፈናው፣ ከውስጡ ለተፈነቀለው ለኢህአዴግ. (ገ.24፣ 55) አስተዳደርአዊ ጭቆናው እርጋታ እና ወጥነትን በአስተዳደርአዊ ወደርየለሽ ጭካኔው (ገ.29) እና ኋላቀር ቅርፀቱ ተጨባጭ ቅፅ አላብሶት ነበር። የነበረው ቆንጣጭ የድርጅት ትድድር (party management) እና ሰንሰለት፣ ወጥ ኢህአዴግ.አዊ የአማርኛ ባህልን – ከሌላነገርዎች መሀከል – አስፍኖት ነበር። ከመፈንቅለ ድርጅቱ በኋላ፣ የአመራር ሰንሰለቱ በመበጥበጡ፣ የወረሱት ካድሬዎች፣ የፕሮፓጋንዳ አቅም – እንደ ሌላ አስተዳደአርዊ ወጥነትዎች እና ግብዓትዎች – ገና ስለአላበለጸጉ፣ ሶስት አመትዎችንም አልፎ እጅግ ድሃ የብሄርአዊ ትድድር የአልተሳኩ እና እጅግ ኋላቀር ስራዎችን የአስመለክት አሉ። አንዱ እና ጉልኁ፣ የዲፕሎማሲ በአፍጢም የወደቀ እውነቱ ሆኖ ሰንብቶ አለ። የኢህአዴግ. እናት እና አባት ህዋሃት. እንኳ በእየጫካው ተሸሽጎ የተሻለ የዲፕሎማሲ እና ከምንም በላይ ህገደምብ (protocol) እውቀቱ የተሻለ ሆኖለት የማእከልአዊ መንግስት አስተዳደሩን እየአበሳጨ፣ እየተሳለቀበት፣ እየተሻለው ተገልጦ አለ። የእሚያያዘው፣ የህዝብ ግንኙነት እና የይፋ ቋንቋ አጠቃቀም እውነቱ፣ አብሮ ከኢህአዴግ. ዘመንዎች ንጽጽሩ አንጻር እንዲሁ ክፉኛ የተዘረፈጠ ሆኖ አለ። እውቀት እና ክሂሎቱ ወደአደባባይ ከእሚደርሱት ግለሰብእዎች ከመሰወሩ በአሻገር፣ በቀላሉ የፕሮጋንዳ እና አስተዳደርአዊ ግንዛቤዎች ላይ ተበልጠው ይገኝ አሉ። ይህን፣ በመረረ የአማርኛ ውድቀት ለመድፈን ሲሞክሩ የአመራር (አምባገነን ቢሆን እንኳ) ጥበቡን የተጣሉት ይመስል አሉ። ያንን፣ በጠንካራ የድርጅትአዊ ጥርነፋ እና ስርአት፣ ኢህአዴግ. በቀላሉ ይቆጣጠረው ነበር። አሁን ግን እኳን በታች ሰንሰለት፣ በትልቁም አመራር ደረጃ የብልጽግና ካድሬዎች አማርኛ ከፖለቲከኛ ቀርቶ ከአላፊአግዳሚ የእማይጠበቅ ሆኖ አለ።
ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ ለመደበኛ ህዝብ ህዋሃትን ከሙያአዊ ቋንቋ ውጭ በማፈንገጥ እየተሳደቡት እና እየከሰሱት በህፃን ቋንቋ ውጊያውን ለህዝብ-ገለፃ (press release) እንደእሚገልጡት፣ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊቀመንበር ታላላቅ ሀገርዎችን እንደ ሰነፍ-ልጅ-አውሪ ተሳደቡት (ለፋሲል ከነማ ብር ሲያዋጡ ነበር – ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኛው ዲና ሙፍቲ በኋላ ለቋንቋው አትቀየሙን ይቅርታ እንደ አሉት፣ መልሰው ራስአቸው ስለሱዳን የ40ኪሜ.ዎች ሰርስሮ በኃይል የሀገር መሬት መውሰድ ለህዝብ ሲያወሩ ክፉ የቋንቋ ስህተት ሰርተው በሳምንቱ ለእኔም ቋንቋዬ ይቅርታ እንደ አሉት)፣ ወዘተ. ብዙዎቹ የብልጽግና ዘመን ፕሮፓጋንዳ እና ዲፕሎማሲ መጠነቃልዎች እጅግ የህፃን መለማመጃ አማርኛ መስለው አሉ።
የመንግስትአዊ እና ብሔርአዊ ጉዳይዎችን ይህ ከውጭግንኙነት አንፃር እየጎዱ እንደ አሉት፤ ወደ አሰልቺው ፕሮፓጋንዳ አማርኛ ስንመለስ፤ መገናኛብዙሃንዎቹ፣ የአነሰ ዘግናኝ አማርኛ ለህዝብ እና ታዳጊዎች ማቅረብ ቢችሉ በግልጥ ይመከር አለ። የቋንቋ ጥናት፣ የስነምግባር ምክር፣ አርትዖት ከዋኝ/አከዋወን፣ ወዘተ. ለሁሉም ሰራተኛዎች ማለማመድ ተመካሪ ነው። የልጅዎችን ስነልቦና፣ የጤናአማ ጭንቅላት አዋዋልን፣ ድንገት የማጨፍገግ አቅምአቸውን ማስጣል እንዲችሉ ይሞክሩ። ጦርነት፣ ግጭት፣ ወዘተ. በስነምግባርአዊ አቀራረብ፣ በዘመነ ቋንቋ፣ ከምንም በላይ ዲፕሎማሲአዊ አያያዝ መቅረብ ይችል አሉ። ከእውነት ርቆ፣ በግል-እውነት አስማሪ መንገድ ያም ፕሮፓጋምዳ ነው መኬድ ከተመረጠ ያም በ ኢህአዴግ. እንደነበረው ዘግናኝ ወጥነት እንጂ ከፊ ማንምየለብሽም አቀራረብ መምጣቱ አስጠዪ ነው። በሰለጠነ ምድር ስለመኖር፣ ነገን ከዛሬ አብሶ ላለማለፍ፣ ነገርን ማቅለል እና በለዘበ ቃል መግባባት የተለመደው ባህል ከሆነ ሰምብቶ አለ። ከእዚህ ተራ ግን ወሳኝ ዝግመትአዊ ስጦታ መመለስን ማን ያብራራው? ከምንም በላይ ከአለቅድመማስጠንቀቂያ ጸያፍ የመብል ሰዓት ምስልዎችን ሁሉ እሚያስመለክቱት ለወርዎች የተደመጡት የቆሸሸ የአርበኛ-ነኝ ህዋሃት.ን ልቅበር ቋንቋ፣ የስነልቦና እና አእምሮ አግጣጫ መናጋት አስመልካችዎች ናቸው። ምን የውጥንቅጥ እና ጎልማሳአጥ አመትዎች ሊከመሩ እያሎበኮቡ ቢሆንም፣ በተቻለ ሁሉ የትልልቅነት ማሳያ ድርጊቶቹን አብሮ የትንንሽነት መገለጫ በሆኑ አማርኛዎች ማጠልሸቱ አብጋኝ ነው። የአእምሮ እና አሳቢነት ቢሰወር፣ መገናኛብዙሃንዎች ጥቂት ከተጨነቁበት የአማርኛ ጥሩ ግን አለው። ይህን መሳት፣ መንገዱን ወደ ደቦፍርድ የአዞረው አለ፤ (አማራ ፖሊስ ኮሚሽነሩ፣ ተኮላ አይፎክሩ፣ ይህ ሲያሰጋ ተዉ ብለው በ አሚኮ. ነሃሴ 15 ቀን 2013ዓም. የተሰራጨ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡት)። ይህ ደቦ ፍርድ ደግሞ አውሬአዊ ጭካኔ ነው፤ ያም አዙሪት አመንጪ ነው፤ (መስፍን ወልደማሪያም ለኢትዮጵያ ለውጥ ከፍተኛ አንዱ ፀር አውሬአዊነት ነው፤ በክፋት የቀደመውን ክፉ አገዛዝ መመለስ የአጠፋን አለ እንደ አሉ እና አስምረው እንደ አስጠነቀቁት፤ ገ.19 – 20)።
ግብር ከሃሳብ እንዲመጣ፣ ሃሳብ ከቃልዎች እንዲወለድ እና ተላለፍ፣ የአማርኛ አጠቃቀሙን ወደ ሰለጠነ ቋንቋ መመለሱ፣ ሃገሩን ወደ ሰለጠነ አስተሳሰብ ከእዛም ወደእሚመዘዝ የሰለጠነ ግብር ሊጎትተው ይችል አለ። ይህን እድል እረኛ እንደተሰወረበት አንጋፋ ጠርናፊ-አጥ መንጋ፣ ደንብአልባ የቋንቋ ዝቅጠት እና እሽክርክሪቱ ውስጥጣ ገብቶ ማበላሸት፣ ሌላው የሀገር አሳፋሪ (የአልተቋረጠ) ውድቀት ነው። ቆምብሎ ይህን ማስተዋል አንድ እርምጃ ይሁን፨

——– ክፍተት ——–

ታች በአለው ምስል፣ ከስሩ የመገናኛብዙሃኑ (አሚኮ.)፣ ከፍርድውጭ ዜጋዎችን “ባንዳ” ብሎ የመበየኑ ነገር ይነበብ አለ። ምንም አሸባሪ ተብሎ ህዋሃት ቢታወጅበትም፣ ተይዞ፣ ተመርምሮ የአልተረጋገጠበት በተለይ የእስር ማዘዣ በአሸባሪነቱ የአልተለቀቀበትን ባንዳ ማለት ከፍተኛ እርምጃ እና የተሳሳተ ለመሆኑ ጥርጥርየለሽ ነው። የህዋሃት. ዋና መሪዎች እና ተቋሙ ብቻ አሸባሪ ተሰኝተው አሉ። እሚያዝዙት ህፃናት ሆነው፣ አሽሽ አጠጥተው ከፊትፊት እሚልኩአቸው እንደነበር እና ተገድደው እእንደነበር እየተማረኩ ገልጠው አለ። በተደጋጋሚ ያ ሆኖ ሳለ፣ እነእዚህን የህግ-ፊት ልጅዎች ጭምር፣ ወይም ቅጥረኛ ብቻ የሆነን፣ ወይም ከእየቤተሰቡ ሁለት ሰው ግዴታ ተብሎ ከትግራይ ተገድደው የዘመቱ መሆኑን ተናግረው አሉ እና ተገድዶ የመጣውንም ሁሉ ባንዳ ብሎ የመበየኑን ህገወጥ ዘገባ እየከወኑ ነው። ባንዳ ተራ ቃል አይደለም። ይህ የመረረ ቃልን በማንም ላይ መወርወሩ ነገን የአለማስተዋል ነው። አሳፋሪው ነገር፣ ያ ብቂያ አለመሆኑ ነው። ” ማጽዳት” አለምአቀፍ ወንጀል ነው። “cleansing” አቻ ትርጓሜው ሲሆን፣ ይህም በሉልአዊ የሰላም እና ደህንነት፣ ሰብእአዊነትም (human rights) ሆነ ሰብእአማነት (humanitarian) ደንብዎች የጣሠ፣ በአለምመድረክ አስጠያቂ ድርጊት ነው። ወደ ዘር እና ጎሳ ግጭትዎችም የመቀየር ወይም እንደምታአዊ መንሻፈፍ ወይም አውድአዊ አጨቃጫቂነት መፍጠር እንኳ የእማይሳነው አማርኛ ነው – ከአለው ስሱ የሰላም እና ደህንነት – የፓለቲካ እና ጠብ እንደአለው ሆኖ – ጉዳይዎች አንፃር። ይህ በሆነበት፣ ማእከልአዊ መንግስት ወይም የክልል መንግስት(ዎች)፣ አሸባሪ በተሰኘ እና በተወገዘ ቡድን ላይ የለዘበ የስራ ማስፈጸም ተራ እንቅስቃሴ እና ከምንም በላይ እዚህ እንደእምንመለከተው አማርኛ መገልገል ሲገባ(አቸው)፣ ማጽዳት፣ የእሚለው ምህረትየለሽ፣ ህግየለሽ፣ አጨቃጫቂ፣ ግድየለሽ፣ ከደረጃው የወረደ አማርኛ ሆኖ እናገኘው አለን። ለምሳሌ አንዲት ብቻ ዘገባ ብንቀነጭብ፤ ነሃሴ 18ኛ ቀን 2013ዓም. የተዘገበው የአሚኮ. “”የእሚያቆመን ድል ማድረግ ብቻ ነው።” የወሎ ግንባር ሰራዊት አባላት፤” እሚለው ዘገባ፣ ከወታደር እስከ ሚሊሺያ የአሉት፣ እጅግ በተገለጠ ቋንቋ ደጋግመው፣ በመግደል ወይም መደምሰስ ብቻ “ጠላት”ን እየገፉት እንደ ሆነ ቃለመጠይቅ የአደርግ አሉ። አንድአንዴ ተገቢውን የውጊያ ቃል “ድል ማድረግ” ቢጠቀሙም፤ ያም መማረክ፣ ገድሎ አለመጨረስ፣ ኢላማ ብቻን ማሳካት ወዘተ. ቢጠይቅም፣ መልሰው በእየቀኑ የእሚነገረውን የመደምሰስ እና መግደል ብቻ ፍላጎት ይመሰክሩት አለ። ከተጠቀሙአቸው ሀረግዎች መሀከል፦ “…ከምድርአቸው እየአፀዱት ነው።” “እየተዋጋን እየደመሰስን ነው።”፤ “አሸባሪው ቡድን ወደ ትግራይ ክልል ተመልሶ እንዲሄድ ሳይሆን አሁን በገባበት ስፍራ መቃብሩን ማዬት እንደ እሚፈልግም [መሰረትአዊ ወታደር ገመቹ በዳሱ] ነግሮን አለ።” “…በአጭር ጊዜ ደምስሰን…”፤ “፤ “ትህነግ. እየደመሰስን…እየአጸዳን”፤ “..እንደ አይመለስ አድርገን እእንቀብር አለን።”፤ “ደምስሶ..” [የዜናው ጽሑፍ ስሪት ታች እባሪ ተደርጎ በምስል አለ።] አንድ ለማከል የአክል፤ ተደጋግሞ ከእሚወጣው መግለጫ መሀከል፤ ብቻ አንዱ ላይ እንዲሁ የእሚደጋገሙ የፈጽሞ መጠፋፋት ህገወጥ እና ኢሰብእአዊ ትእዛዝዎችን እንልቀም እና እንጠቁም። ይህም በአማራ ክልል መንግስት ግንኙነትዎች (Communications) ጉዳይዎች ራስ ግዛአቸው ሙሉነህ የተሰጠ ልማደኛ የመንግስቱ ሀሳብዎች መግባቢያ መግለጫ ነው። ዉስጡ ከአሉት ለታሪክ ፀያፍ፣ ለህግ ጣሽነት፣ ለህሊና እና ስነምግባር ከፍተኛ ውድቀት፣ የሆኑ ሐረግዎች መሀከል፦ “…ከምድረገጽ ለማጥፋት”፤ “የማጽዳት …”፤ “እስከ አልተወገደ ድረስ…”፤ “እየተቀበረ ይገኝ አለ…”፤ “ተጠርጎ እስኪወገድ ድረስ”፤ “ክፉዎችን በመቅበር…”።
እነእዚህ አገላለጥዎች፤ ህግ እና ዘመንአዊ አስተዳደር ቢያንስ ሰብእአዊነትን አያውቁም። አጥፊ፣ ክፉ፣ ወዘተ. በመታረም እሚሻሻል ከአልሆነ በህግ ቁጥጥር ስር እሚከርም ነው። ይህ የሰውልጅ የረዘመ ትግል እና እውቀት የአካበተው አገነዛዘብ ነው። መሰረትአዊ የሰውመሆን ጥበብ መሀከል በዓለምአቀፍ ባህል የተጠበቀ እውነት ነው። ጦርነት እና ዘግናኝ ውጊያም፣ በአሸባሪ ቡድን እንኳ ቢከወን፣ ድል እና መንግስት አስተዳደሩ ሲጀመር ጀምሮ እንደ አለው “ህግ ማስከበር” ይከወንበት አለ እንጂ፣ የፈጽመለ ላጥፋህ እና ልቅበርህ፣ ከፍተኛ የአእምሮ ሚዛን መበላሸት ነው። አሸባሪ የተሰኘው ቡድን፣ ለምሳሌ፣ አላማው መንግስትን ማበሳጨት መሆኑን ቀደም ብሎ መቀሌን ዳግ-ሲቆጣጠር ገልጦ ነበር። ይህ ተራ ተልካሻ የማበሳጨት እና ክብሩን የመባጨር የተገለጠ ኢላማ መንግስት መንግስት በከፍተኛ መነቃነቅ ህዝቡን አዝምቶ መከላከል ቢያውጅም፤ ድል ማድረግ ነገሩን ማክሸፍ እንጂ መበሳጨት ከምንም በላይ ከአሸባሪ ዘዴአማአዊነት (strategies) ወርዶ፣ በብስጩ ምላሽ ከህግ ማፈንገጥ ብዙ ታሪክ ከአላት ሀገር እና ጤነኛ አስተዳደር አይጠበቅም። የጦር ጥል ሲጠነሰስ ጀምሮ በህግማስከበር ሐረግ ሲገለጥ የነበረው ዘመቻ፣ እንዲህ ገደቡአጥ መንቦጫረቅ እና አስተዳደርአዊ የአያያዝ ክሽፈት ገጥሞት አለ። የምንይሊክ ካልእ እስኪገብሩ ብቻ ተዋግቶ እጅ ከሰጡ፣ ከእራስ የንጉስ ማእረግ ወርዶ የወጉት ቁስለኛን አክሞ፣ በስርአት ከትቶ የማለፍ እና እንዲህ የእሚተረክ ታሪክ የመተው፣ ወራሪዎችንም እንኳ ሲሸነፉ በሰላም የመመለስ እና ሀገርአቸው የማስገባት ቀድሞ-አሳቢ ጥበብ፣ በዘመነ ቀን፣ ተዋርዶ፣ አንድ ትንሽ ጨዋታን በተደናበረ ህገወጥ እና ኢስነምግባርአዊ አያያዝ ታሪክንም አበላሽ አስተዳደርንም አዋራጅ አያያዝ መያዙ መቃኘት የአለበት ጉዳይ ነው።

በህግ የታወጀው አሸባሪነት፣ ቢበዛ የአፈጻጸም ገደቡ የታወጀብአቸውን ይዞ በህጉ መክሰስ እንጂ በየተገኙበት ነፃፍርድ ማጽዳት አልነበረም። ይህ የይፋ ጦርነት እንኳ የእማይቀበለው አካሄድ ነገን አብሮ ለመኖር ወይም በሰላም ለመኖር ከእሚያስብ አስተዳደር አይመነጭም። ሀገርን በዛሬ ቸልታ እና በነገ ንቀት ማስተዳደር ነው። ከአምባገነንአዊ ስርዓት እንኳ አንሶ መገኘት ነው። ይህም በዋነኛነት ወጥ ስርአትን ገንብቶ ለአስተዳደር ትድድር (management of administration) ማበጀት የአለመቻል ነው። የእሚያሰጋው፣ ለሙስና እና ኢተጠየቅአዊ ስርአት እጅግ ክፍት የመሆኑን ነገር ማስገመት መቻሉ ጭምር ነው። ወጥ የመንግስትአዊ መዋቅርዎች እና አሰራርዎች ቁጥጥር ከሌለ፣ በምትኩ ነፃ እና ፍትሕአዊ የምርመራ እና ቁጥጥር ስርአትዎች በሙሉ (ገለልተኛ እና ጠንካራ ጋዜጠኛነት፣ ለዲት፣ ቤተእንደራሴዎች፣ መገናኛብዙሃንዎች፣ ፊሽካነፊዎች፣ ወዘተ.) ከአልተቋቋሙ፣ ሀገሩን የእሚቆጣጠረው ማን ነው ታዲያ? የመንግስትአዊ መዋቅር እና ቁጥጥሩ፣ ወጥ አሰራሩ፣ ቅፅ እና ቅርፁ፣ ይዘቱን (ነፃ ወይም አምባገነንነቱን) ትተው ሲመለከቱት እጅግ የቀለለ ሆኖ የአገኙት አለ። ወጥ የአስተዳደር ቅፅ እና ቀለም እጅግ ወሳኝ እና ከይዘቱነጽቶ ለስርአቱ መኖር ማረጋገጫ የሆነ ጉዳይ ነው። እንደተጠቆመው፣ የእዚህ መክሸፍ፣ ለቋንቋው መዘበራረቅ አንድ እድል እንደሆነለት ለብዙ ነገርዎችም ክፍተት ለመፍጠሩ ወይም አለመፍጠሩ ማረጋገጫ የለም። መነሻ ጥርጣሬ ግን በጉልህ ይጫር አለ። ከአማርኛው ባለማቋረጥ ለወርዎች መላሸቅ የተነሳ ተጨማሪ አስጨናቂ ስጋትዎችን ለማከልም ወደማስገደዱ እየተመጣ ነው። አስተዳደርአዊ ህላዌ በርትቶ ከአለ፣ ቀድሞም ይህ ስህተትን አንመለከተውም እና።
ይህ የእራሱ ሌላ ምርመራ ለመፈግ የእሚችል አስጊ ጥያቄ ነው፤ ከኢህአዴግ. መፈንቀል በኋላ አስተዳደርአዊ ክፍተቱ በስፋት እና ስምጠት አለ። ዋና እና የከበሩ የነበሩ የኢህአዴግ. አመራርዎች ተሰውረው፣ ተገድለው፣ ታስረው፣ ተሰድደው፣ በደፈናው ተገልብጠው እጅግ ታች በፒራሚዱ ቂጥ የነበሩት የተለመደ የሃያሰባት አመትዎች የተለመደ ጽን መሰላሉን ሰብረው የበላይዎችአቸው አሽተውአቸው ሳያስተምሩአቸው እና ከአንድአች ጥፋት በኋላ ወደተሻለ ስፍራ (በተለይ ወደ አምባሳደርነት) ሳይገለሉልአቸው እና ሳያወርሱአቸው በድንገት ወደ ከፍተኛ ሹመት የተመዘዙ ናቸው። (ለምሳሌ የአአዩ. መሪ ቢሊየን ብርዎች በአንዲት ናሙናአዊ ኦዲት ስስትጠፋበት ወደቻይና አምባሳደርነት፣ ወይም የሲዳማ ክልል መሪው ሲዳማ ህዝብን በደለ ሲባል በስፋት እና ድርጅቱን ብቻ አገለገለ ሲባል ወደ ደቡብኮሪያ አምባሳደርነት፣ ወይም ገነት ዘውዴ ተማሪ አስገደለች ሲባል ወደህንድ አምባሳደርነት፣ ወዘተ. እንደእሚሸጋሸጉት፣) የበላይዎች በመፈንቅለ ኢህአዴግ. ከመቅጽበት ተወግደው፣ እጅግ በወረደ ደረጃ (ለምሳሌ ትንንሽ ከተማዎች ውስጥ የተለያየ ስራ ሲሰሩ የነበሩ እንጭጭ ካድሬዎች ወደ ክልል እና ክልልን ሳይረግጡ ደግሞ ወደ ፌደራል መንግስት ሹመት ሲመነደጉ (ለምሳሌ ሙፈሪያት ከሚል፣ አህመድ ሽኩሪ፣ ወዘተ. ከእየወረዳ እና ዞን ወደ ማእከልአዊ አስተዳደር ጫፍ ሹም የተስፈነጠሩ ናቸው) ሌላዎችም ታች ከመቅጽበት በእነእሱ ምትክ በቅለው ስለ አሉ፣ ይህ አስተዳደርአዊ ትድድር ከፍተኛ ስንጥቃት እንዲገጥመው ይገመት አለ። የአምባግነና እና ጥርነፋ ወጥነቱም ይዛባ እና አንድ ቀለምነቱን ይረበሽ አለ። የቁጥጥር አቅሙም ይደክም አለ። የትእዛዝ ተዋረዱም ይረግብ አለ። ይህ ሲሆን፣ ከቋንቋ አቅሙ (ፕሮፓጋንዳ አማርኛው) ድርጅቱ (ብልጽግና) መላላቱ በላይ፣ የሌላ ችግርዎች ተሰቃዪነቱ ተተንባይነቱ አመክንዮአዊ ወደመሆን ይሸጋገር አለ። ይህ ሀገርአዊ ጉዳይነቱን የአበለጽገው አለ። የአስተዳደር አቅም – ከይዘቱ ውጭ – በህላዌው እና ኑባሬው ጠንክሮ አለመገኘቱ፣ የቋንቋው እና ተያያዡ ዝርክርክነት ብቻ ሳይሆን ተያያዥ ሌላ ዝርክርክነትዎችን ሊያስተናግድ ይችል አለ፨

ሁለት የዜና ዘገባዎች የጽሑፍ ስሪት (version) እባሪዎች በተከታታይ ታች ተቀምጠው አሉ [በ PDF ስሪቱ]፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s