Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የሰውልጅ አንድ-መሆኑን አሳይቷል እና፤ ለህዋሃት ምስጋና

About a military wonder made by TPLF – capturing “enemy” and wearing them its uniform and make them fight at front against their own locality or “people” they were captured from – that teaches a humanity lesson of wars, if not more.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, September 01st 2021GC.,

አንዳንድ ድንገተኛ ትርክትዎች፣ አንደምታአቸው (their implications) አስገራሚ ናቸው። ኀዋሃት. ኢህዴግ.ን መስርቶ የድሀድሃ-ህዝብ ሲያስተዳድር፤ ሰብእአዊነትን ከማበልጸግ እና ውህድአዊነትን ከማጠጠር፤ በጎሣ ቅርጫ የወጣች ሀገር መሰረተ፤ የዜጋ እና ብሔርአዊ ጥበብን ከፖለቲካ፣ አስተዳደር፣ እና ተመዛዥ እና ተያያዥ የህይወት አገባብዎች (contexts) በመሰንጠቅ አቆየ፤ በእዛም ክፉ-እውቅ ሆነ፤ ኩርማን-ትውልድ በኋላ ከውስጡ መፈንቅለ-አስተዳደር ገጥሞት እርምጃበእርምጃ እራሱም ግሉን ሽብርተኛ ዝርዝርን ተመዘገቦ አገኘው፤ ለስልጣን ዳግ-ውጊያ ክወና ገባ። አንድ የእዚህ የእራሱ የመከፋፈል እና ንፁሕ ሰብእአዊነት ላይ የእማይመሰርተውን ርእዮት – በወጭወራጁ የእሚረገምበትን ቋሚ-አዝማሚያው – ተፃራሪ-ትንግርት (አንደምታ) ግን፤ በነሃሴ 25ኛ 2013ዓም. በአንድ ዜና መሀከል ተደመጠ።
የአሚኮ.ው ዘገባ፤ ህዋሃት.ዎች (የትግራይ መከላከያ ኀይል ብለው ለዳግ-ውጊያው እራስ-ሰያሚ ሆነዋል)፤ አማራ ክልል ለሰርጎገብ ተብለው በክልሉ መገናኛብዙሃንዎች እሚጣጣል ዘመቻ ሲገቡ፤ ብዙጊዜ ወጣትዎችን ዘርፈው፣ በምርኮ ደምብ ይዘውአቸው ይመለስ አሉ። እነእዚህ ዜጋአዊያን (civilians)ን በመውሰድ፤ የእራስአቸውን መለዮ የአስታጥቁአቸው አለ። በቀጣዩ የእየአግጣጫ (ግንባር) አውድማ፤ ከፊት አድርገው ይበትኑአቸው እና በፊትወራሪነት ክልልአቸውን ወይም አጋር ክልል ሰራዊቱን (በቅርብ የአልተለመደ የሀገሯ ታሪክ ብዙ ክልልዎች የተለያዩ የኀይል ሰራዊትዎች አዘጋጅተው አሉ)፤ ወይም ማእከልአዊውን ጦር ይወጋ አሉ። ከወጡበት መንደር ተቃራኒ መስለው ፊትፊት ይዋጋ አሉ። ቢመለሱ ከጀርባ የእሚነካአቸው የተለየ ጠባቂ አለ። ወደፊት ቢዘምቱ የእራስአቸው ዘመድ ቤተሰብእ ወይም ክልል አለ። ያ ደግሞ ጠላት ብሎ የአጠቃአቸው አለ። ከፊትም ከኋላም ሲጠቁ ለመዳን በደመነብስ ምሪት የመዋጋት እድሉ ከተመረጠ ደንበኛ ፊት ወራሪ ይሆን አሉ። ይህ ሰቅጣጭ ነው። የአማራ ክልል አስተዳደር ራስ አቶ ተገኘሁ ተሻገር፣ በህግ ባይሆንም በድርጅትአዊ ገደብአያቅ የመወሰን አቅም ጦርነት እና የዘር-አማራ ማንነነት ጦርነት ብለው በማወጅ ህዝብአዊ ውጊያ ብለው ሰይመውት አለ። “የህልውና ዘመቻ” ተብሎ በመሰየምም በሀገርአቀፍ ደረጃ፣ ዘማችዎች ተመልምለው አሉ። የክልል አስተዳደሩ ራስ እንደ አወጁት፤ በሌላ ቀን፤ በእጅ፣ ድንጋይ፣ ስለት የእሚዋጋ ገበሬ፣ ወጣት፣ እናት፣ ከህዋሃት. ተዋግቶ የዘረፈው መሳሪያ ከአለ ክልል አስተዳደሩ በይፋ የማራኪው ንብረት ብሎ ይመዘግብለት አለ ብለው አለ። ማእከልአዊ አስተዳደርም፤ የትግራይ ክልል አመትአዊ በጀትን በብዙ በላቀ መቶ ቢሊየን ብርዎች ወጪ (በዋነኛነት ዉጊያ) ስምንት ወርዎች አካባቢ ክልሉን አስተዳድሮ፣ በመጨረሻ ተሸንፎ ከወጣ በኋላ ከትግራይ ክልል መደበቅ ወደ ዳግ-ማጥቃት የተመለሰው ህዋሃት.ን በሀገርአዊ አዋጅ ለማንኛውም ዜጋ ሁሉ በተደረገ ጥሪ እየመለሰ መውጋት ጀምሮ አለ። ነጥቡ፤ የዘመተው፣ ከእየመንደር የወጣ መደበኛ ዜጋ ነው። ከምንም በላይ በእየቀኑ እሚተላለፉ ስርጭትዎች፣ ውጊያው በተለመደው የጦርነት ህግ መሰረት በሰራዊት ከመከወን በእየመንደርተኛ፣ በድል እስኪመለስ በሌላ ሰው እና ጎረቤት ማሳው እየታረሰለት በእሚቆየው ገበሬ፣ ወዘተ. እሚከወን ነው። እጅግ የእርስበእርስ ጦርነት ሊመስል እና የትልቅ ታሪክ ባለቤት ነን በእሚል ህዝብ ሳይሆን፣ በመንግስት-የለሽ አኗኗር የወደቀ ህዝብ እሚከውነው ውጊያ ይመስል አለ። ነጥቡ፤ ይህ ጦርነት በተጨባጭም፣ በይፋ በአማራ ክልል እና ማእከልአዊ አስተዳደርዎችም እንደ ተገለጠው፣ ህዝብአዊ ጦርነት የተሠኘ ነው። ማለትም፤ መንደሩን ለመጠበቅ በእሚመስል መልኩ ብዙ ሰው – ከወጣት እስከ ሽማግሌ – ከእየገጠሩ ወጥቶ በአቅራቢያው ነቅተህ ተዋጋ፣ ጠብቅ በእሚል ክተት እንደ ተፈለገ እሚዋጋበት ውጊያ ነው። ድምዳሜው፤ ስለእዚህ ቤተሰብእ ከቤተሰብ እየተዋጋ ሊሆን ይችል አለ። ምርኮ የተወሰደው ወጣት በህዋሃት ውጋ የተባለው የመንደሩን ሰው ነው። ሴት ወንድ ሳይል የዘመተ ህዝብ እሚያጠቃው ከሰፈሩ የተሰረቀ ወጣትን ነው። የተሰረቀው ወጣትም በመገደድ እሚተኩሰው ወደ መንደሩ – ከመንደሩ ወደ ተውጣጣ ሰራዊት አጥ የቀውስዎች ጦርነት ነው።
ፀማኮ፤ በአዳራሽ በመመረቅ የመጀመሪያው አማርኛ እና ኢትዮጵያአዊ ፊልም የተሰኘ የዘካሪያስ ሐይለማሪያም ገጽማያ (screen) ጭብጥ፣ የእነ ፀማኮ አይደለም ይሰኝ አለ። የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጦርነትን ለመተቸት የተሰራ ትርክቱ፣ ወንድማማችዎች በተራ መለያያ ነጥብ ተቧድነው ሲገዳደሉ አስመልካች ነው ይባል አለ። በእርግጥ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እጅግ አንድ የሆኑ ናቸው። ይህ አሁን እየሄደ የአለው ታሪክ ግን የጦርነት ጫፉ እርስ በእርስ መተላለቅ ነው ለእሚለው እጅግ የገዘፈ ምፀት ነው። ህዋሃት. በአንድ ወገን፣ በተለይ አማራ በሌላ ወገን የእሚዋጉት የአንድ ህዝብ ውጊያ ነው። እጅግ አስጸያፊ የታሪክ አዙሪት ነው። ለስልጣን ህዝብ ከመዋጋቱ እና መስዋእት ከመደረጉ በአሻገር፣ ዞሮዞሮ ውጊያው እርስበእርስ እሚከወን መሆኑ ነው። ያንን ንፁህ የስልጣን ጠብ ህዝብአዊ አድርጎ በእዚህ ዘመን ተራበተራ መተላለቅን ማስቀጠል እጅግ የከፋ ብሔርአዊ ጎልማሳነት መጥፋትን ማረጋገጫ ነው።
ፐድንሄድ ዊልሰን የዘር ለሰውልጅ ውድቅ መስፈርት መሆኑን አስተዳደግ አንድ አድራጊ መሆኑን በምፀት የተሰበከበት መጽሐፍ ነው። ሀገርም በተለይ አማራ እና ትግሬ አንድ የሆነ ነው። ተስፋዬ ገብረዓብ፣ እንግሊዝኛ በመሰለ አማርኛ የስነጽሑፍ-ቋንቋ አቅሙ እሚማርከው፣ ምንም በጭብጥዎቹ በአንድአንድዎች ቢተችም፣ የስደተኛው ማስታወሻ አንድ ነጥቡ፣ የሁለቱን ጎሳዎች ፍቅር እና አንድነት ይተርክበት አለ። በአጭሩ፤ ጎሳአዊ እንዲሆን የተፈለገው ጦርነት ስልጣን በያዙት በኩል ሲሆን፣ በህዋሃት. በኩል ህዝብአዊ ጦርነት አልተከወነም። እንደ ድርጅት፣ እሚዋጋ ተቋም ነው። ሁለቱም፣ በተለይ ይፋ ባለስልጣንዎቹ ይህን ውጊያ የማስቀረት ሁለንተናአዊ ኀላፊነት ነበረብአቸው። ቢከፋ፣ በሙያ እና ሰራዊት ብቻ መከወን ነበረበት። ህዝብአዊ የተደረገ እና ያ ድል የተደረገ ውጊያ፣ አንድ ህዝብ ከማጣላቱ በተረፈ፣ የለየለት የአንድ ህዝብ ከእዛ ወርዶም የደንድ ጎሳ ውጊያ ሆኖ አለ። የቤተሰብ ደረጃ ውጊያ ለአለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ህዋሃት.ዎች እሚያዋጉት ሰው እንደ ሌለአቸው ይወቅ አለ። በዓለምአቀፍ ደረጃ ህፃንዎችን በማሰለፍ ሁሉ እየታወቁ ነው። ይህ አዲሱ ስልትአቸው ያንን ማርገብ ለመቻሉ ጥርጥር የሌለው ነው። ከእዛ በአለፈ ግን፤ የወታደር እጦትአቸውን ለማቃለል የተገለገሉት ስልትም በውትድርና ጥበብ የእሚጠና ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ሁሉንም ብንተወው ግን፤ ህዋሃት. ሰው በሰውነቱ አንድ ነው፤ ኢትዮጵያአዊ ሁሉም አንድ ነው፤ የእሚለውን መርኅ ሲጥስ ኖሮ፣ ዛሬ በጭንቅ – ወታደር ቁጥር ማነስ – ጊዜ የአመጣው ብልኀት፣ ዘግይቶም ቢሆን፣ በዘገባው ተመላክቶ አለ እና፤ አማራ ክልል እና ማእከልአዊ መንግስትዎች አስተዳደርዎችን አጣብቂኝ ከታች ነው። ስምምነት እንጂ፣ ይህ ውጊያ፣ የጎልማሳ ደምብ የእሚገዛት ሀገር ለአለመመስረቷ አስረጂ ነው። እርስ ለእርስ ውጊያ እየተካሄደ ነበር። ዛሬ ደግሞ በዘግናኝ የሆነብአቸው ደረጃ ጦርነቱ ተለውጦ ተገለጠልአቸው። ሲቀድም መደረግ የአልነበረበት ጦርነት፣ በእራስ ሲደርስ ጭንቁ በዛ። የእሚከወነውን ለማወቅ እድል የለንም። ጨክኖ ስለስልጣን አሁንም የአማራ ክልል እና ማእከልአዊ መንግስት ሰራዊትዎቹ የአጠቁ ከሆነ ይህ ትንግርት ነው። ህዋሃት.ም የእሚከውነው የአንድ ህዝብ ውጊያ ቢሆንም፣ መልሶ ደግሞ የበለጠ ደረጃን የእሚራመድ ጥቂት የከፋ ዘዴ ነው። የጦርነት ህግ ለእዚህ ምን አይነት አተያይ እንደ አለው ለጊዜው ዳግምርምር መከወን አልተቻለም። ቢሆንም፤ በእንደምታ፣ ሰብእአዊነትን ለማክበርከ ጦርነትን ለመጠየፍ፣ አንድ ህዝብ መሀከል ጠብን ለማስቀጠል መሞከር፣ እንዲወገዝ፣ ይህ ደህና አብነት ሆኖ ለታሪክ የእሚቀር ነው። የሰመጠ የጉዳዩ ዝርዝርዎችን እንጠብቅ አለን። ለእዚህች የተለየች ትምህርትም ህዋኀት.ን ማመስገን ተገቢ ነው። ከውድቀትከ ከአሉታ ተነስቶ የበለጠ ቀና ነገር ለመገንባት የእሚቻል ነው። ያ በሩ ተከፍቶለት አለ። የአንድዎች መሀከል ጦርነት፣ እዚህ ከደረሰ፣ በትልልቁ የአስተዳደር ደረጃ ለመስተካከል እና ሁሉን እኩል አቃፊ ምድር ለማበጀት ሸመገለ ስህተትን ለመመልከት ይህ ሌላ እድል ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s