Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ራስ ሳይጠና ጉተና፡ ስድ ይፋ ኢትዮጵያአዊነት በማቆጥቆጥ ላይ

About reality of sheer administrative poverty under Prosperity Party and its potentially nation-hurting process.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 23rd 2021Gc.,
ይህ አጭር ጽሑፍን በ ተአዶ. (PDF) የአንሱ።


ይህ አጭር ጽሑፍ፣ ከሀፍረት ተነስቶ የተጻፈ ነው። ይህም፤ በአልተቀደመ መንገድ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ወደ መገናኛብዙሃንዎች የእሚሾልኩ ከባድ ስህተትዎች በመገኘትአቸው ነው። ጉዳዩ ዓለምአቀፍ ግንኙነትን ይመለከት አለ።
በነሃሴ 17ኛው 2013ዓም. አንዲት ጎልማሳ እመቤት፣ በደቡብ ትመ. (Tv.)፣ የአስተያየት ማስታወቅያዎች መሀከል ቀረበች። በጎዳና ቆማ በመጮህ ይህን አለች።

“…የእኛ ምርጫ ሰላምአዊ ነው! መቀበል ግዴታአቸው ነው። እኛ የአሜሪካ ምርጫ ፍትህአዊ እና ነፃ አይደለም ብንል እነሱ ይቀበሉን አለ?”

አንዲት መንገደኛ የቤት እመቤተወ (ከሀዋሳ አካባቢ?)፤ ነሃሴ 2013ዓም.

ቀደም ብሎ፤ ሁለት ወርዎች ገደማ ፊት፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ አንድ ከፍተኛ ሆቴል ውስጥ ለ ፋሲል ከነማ ማሻሻያ ገንዘብ ሲለመን፣ “…የነቀዘ ስንዴአቸውን አንፈልግም…” ብለው ተመሳሳይ ሀገር እና የእማይረሳ ባለውለታ በመዋል የአሳደጉንን ጎረቤትን ተሳደቡ። (ይህ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ፣ ቀንዎች ቆይቶ ይቅርታ ተጠይቆ አለ)። በእዛው ሰሞን፤ “Hands off Ethiopia” በእሚል ትእይንተህዝብ፣ በመስቀል አደባባይ፣ ጥቂት ዜጋዎች በመፈክር ወጥተው ግድቡ ይሞላ፣ ጫና አታድርጉብን ብለው ወጡ። ብዙ ተመሳሳይ የተጻፉ መፈክርዎች ተነበቡ። ለምሳሌ፤ “ትህነግ.ን አታስታጥቁ፣ እኛም አስታጥቀን እንዳንልክ አሜሪካ!”፤ ወዘተ. እሚሰኙ መፈክርዎች ነበሩ። ይህ ወደ ሰሞኑ ፕሮፓጋንዳ ሲያመራ፤ ያም የአብይ አህመድ አስተዳደር፣ መንግስትአዊ አስተዳደር እና የህዝብ ህይወትን በቀይ መስመር መሰንጠቅ የአልቻለበት ብቻ አንዱ ከኢህአዴግ. የባሰ ውድቀት የወደቀበት እውነት ነው። ተራ ወይም የእለት ከእለት አስተዳደርአዊ ስራዎችን ወደ ህዝቡ ማፍሰስ የአለ እውነት ሆኖ አለ። የእሚቀረው ይህን በልተን ቢሮ ልንገባ ነው ወሬ ነው። መነገር የሌለብአቸው ወሬዎች ከአስተዳደሩ ግዛት ወደ ህዝቡ ይፈልቅ አሉ። የዲፕሎማሲ እና ህዝብ ግንኙነት አሰራሩ እንደ ሃይቲ ርእደመሬትዎች ተናግተው አሉ። በእርግጥ በቅርቡ ከተደጋገመ አለመጠንከር በኋላ ብሌነ ስዩም.. እምትሰኝ ቃልአቀባይ ተቀጥራ በሙያአዊ አያያዝ የመንግስት ወሬዎችን ለማቀበል እየሞከረች ነው። ቢሆንም፣ ባለስልጣንዎች ብቅ ከአሉ፣ የማይባል ነገር ተናግሮ፣ የመመለስ ነገሩ እንደ በዛ ነው።
ከእዚህ በተያያዘ፣ እጅግ የሰነፈ እና መስመሩ የጠፋበት ነገርዎቹ ማምለጥአቸው እንደ አለ ሆኖ፣ ይህ ልክ ከማጣቱ የተነሳ የቀሸመ ዓለምአቀፍ ግንኙነት እና ንግግርዎች አሉ። እሚመስለው በሩቅ ግምት፣ ግንኙነት ስራውም በተግባር የተደበላለቀበት ነው። አስተዳደሩ በቅርቡ በተሻለ መንገድ ዲፕሎማትዎችን ለማሰልጠን እና ለማሳደግ ከምሁርዎች ውትወታ በኋላ እንቅስቃሴዎች ጀምሮ ስለ አለ። አሳዛኙ ነገር፤ ወጪወራጅ እየጠሩ ሰላም እንፈልግ አለ ብቻ ሌላው ቀርቶ ሰላምአችንን መንግስት የአረጋግጥልን የአስብሉአቸው እንደ ነበረ (በኢህአዴግ. ተቃውሞ ተከውኖ ጥቂት ግርግር ከተነሳ)፣ አሁን አዛውንትዎችን፣ ልእለ ሃያል ሀገርዎችን ማስናቅ ጀምረው አለ። ከአቀራረብአቸው ማህበረሰብቡ የአልተማሩ ቢበዛ መሰረተትምህርት የገቡ የቤት እመቤት መሳይ እናት ይህን ከተናገሩ፤ እጅግ የአለምአቀፍ ግንኙነት ክሽፈት ነው። በእርጋታ እና ብልሃት፣ ከእነ ቶማስ ወልድ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ. መፈንቀል፣ ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ግንኙነት የሰነፈ ውርደት በእዚህ መጠን ቀርቦባት እሚያውቅ አይመስልም። ህዋሃት. በአሸባሪነት ዝርዝር ተከትቶ የተሻለ ዓለምአቀፍ ግንኙነት አቅም እና ልምዱ ለ ህዋሃት. ወየአገዘው እና ማእከልአዊ አስተዳደሩን እየአበሳጨው ነው። እጅግ ተራ ጉድለትዎችአቸውን ለህዝብ በእየቀኑ ይነግሩት አለ። ለምሳሌ፣ በ ኢሳት. ም በ እለትአዊ ዝግጅት እንደ እሚደጋገመው፣ የተገዙ ጋዜጠኛዎች ህዋሃት.ን ይደግፍ አሉ ይባል አለ። ይህን ለህዝብ በመደጋገም ከመግለጥ፣ እና እማይረባ ወሬ መንዛት፣ አንድ ባለሙሉ ኃይል መንግስት፣ በተገቢው አካሄድ ተዋግቶ እሚጥለው ተራ የዲፕሎማሲ እለትከእለት ስራው መሀከል የአለ ይመስል አለ። ይፋ እና መርኅዎችን የተከተለ፣ የእማይደናበር እና የበሰለ አያያዝ ግን ነገሩ በአለመቸሩ በአንዴ በንዴት እየጦፉ፣ ሰራተኛነትአቸውን በመተው፣ ወደ ህዝቡ ፕሮፓጋንዳ ተክቶ በትርክት ውድቀትአቸውን ለመሸፈን ይሞክር አሉ። ይህ እና መሰል ስህተትዎችን በአሉበት ማፈን እንኳ አይታሰብም። እማይነገርን ከማስቀረት ለህዝብ መንገሩ መፍትሔ አይሆንም። ህዝብ ተክቶ አስተዳደሩን ነገሩን አያስተካክልም። ብቁ ተብለው ወይም ነን ብለው የተሰየሙት እነእርሱው ናቸው።
ለሀገር ከሁሉ ምርጥ ጥቅም ታግሎ ከአለም መድረክ ግንኙነት መመለስ ግዴታዎችአቸው ነው። አስተዳደርአዊ ቡድን እንጂ ሀገር አይደለንም በእሚል የአልተበሳጨ ግንኙነት ማውረስ አለብን ብለው ለነገው አስተዳደርም ሆነ ሀገር አያስቡም። ለነገው ሀገር ቢቀር፣ ለዛሬውም አልታሰበለትም። አለማወቅ፣ አለመሰልጠን (በነገሩ)፣ ወይም ብልኀት ማጣትን፣ ወደ ግንኙነትዎች አበላሺነት እና በምትኩ ህዝቡን ለማባባት ችግሩን መዘርገፍ ከፍተኛ የኢሙያአዊነት (un-professionalism) መገለጫ ነው። ይህ ወደ ብዙ ነገርዎች እየፈሰሰ የእሚገኝ ክፍተት ሆኖ ወደ ሶስት አመትዎች እየተጠጋ ነው። ለምሳሌ፤ የህዋሃት. ሰዎችን በዉጊያ እና አሸባሪነት ህግዎች እና ፖለቲካ ማስተናገድ እንኳ መገናኛብዙሃንዎች እና ሹሞች አቅቶአቸው አሉ። ስለ ማጽዳት፣ መደምሰስ፣ መቃብር መክተት፣ ወዘተ. እሚሰኙ የጎልማሳ የአልሆኑ ቃልዎች እና ምግባርዎች እንጂ ወደ ተገቢ እና ልምድ የአለው ወይም አርቆአሳቢ አያያዝ መውጣት አልቻሉም። በእየስፍራው የአሉ ስህተትዎች እንዲህ አስጨጋጊ ከሆኑ፣ ለሌላውም ነገረ-አስተዳደር አስጊ ነው።
ይህ እንደሆነ፤ ዋናው ጉዳይ፣ ታላላቅ እና አጋዥ ታሪክ የአሉአቸውን የአለም መሪ ሀገርዎችን፣ ቢቻል መግባባት፣ ባይቻል በጥበብ ዝም ማለት እና በስውር ማስተናገድ እንጂ፣ በይፋ የመሳደብ ጉዳዩ በታሪክ የነበረ የእማይመስል፣ ወደ ፊት ለትውልዱ (ማሰብ ከተጀመረለት) ጥሩ ቅርስ አይሆንም። ክብርን ዞሮ ሀገርን ይነካ አለ እንጂ ለትልልቅዎቹ ሀገርዎች ይህ ጎጂ አይሆንም። በባዶ ሜዳ ከእራስ ተፋትጎ ሌላን ሰድቦ ግልን-የማቅለል እንጂ እርግጥ ይህን በእዚህ ምስጥ እና ተቶ የተወሳሰበ ሙያአዊ የዲፕሎማሲ አለም ማንም ቁብ አይሰጠውም። መንግስት አስተዳደሩም፤ የፕሮፓጋንዳ አዲስ አግጣጫ መቀየስ ይሻለው አለ እንጂ፣ ህዝቡን ትልልቅ ሀገርዎች ተሳደብ፣ የእኔ አፈጻፀም ከብዶኝ ስለሆነ በእርጋታ እእና ጥሞና ሁሌ የወረደ አሰራሬን ስነግርህ የማድመጥ እና መባባት ጉዳዩን ተያያዘው በእሚሉ ሁለት የፕሮፓጋንዳ አግጣጫዎች የመግባቱ እና መቆየቱ ነገር መተው የአለበት ነው። ሌላ ንድፍ ስህተት እና ክፍተትዎችን መሸፈን ይችል አሉ። በአነሰ የጉዳት ስፋት መቀራረብ ተቻይ ነው – በኢህአዴግ. አስተዳደር እእንደ ነበረው። በተራ እና ተራ ምሳሌ፤ መለስ ዜናአዊ፣ አምስት ሳንቲም ባንቀበል ይ አለ መዋቅርአዊ የስነምጣኔ ጫናን የተቀበለ እርዳታ ግን ይቅርብን ብለው ለፓርላማ ይናገሩ ነበር። ይህ ችግር ገጥሞአቸው፣ እርዳታ ዎች ግን በብስለት በመንቀሳቀስ ቢሆን ነው ቀርተው አያውቁም። አሜሪካ ግን፣ እርዳታ እስከማዘግየት ደርሳ እንደ ነበር በእዚህ አስተዳደር ግማሽ እድሜ ገደማ ይታወስ አለ። ተግቶ፣ በቅድመንቃት የመከታተሉ ነገር አልቀደመውም። ቢሆንም፤ ይህ ነጻ ድርጎ አልቀረም፤ ወዲያው ተፈቅዶ አለ። የከፋ ጥያቄ ቀርቦ ሀገር አስጨንቁ ሳይባል በጥቂት ነገር በርግጎ ዞሮ እነእዚህን ሀገር መሳደቡ እጅግ በጮርቃነት ታልፎ፣ ከመንገደኛ ሰው ጠቅላላ እውቀት ባሽ የሆኑ አስተዳደርአዊ የለምአቀፍ ግንኙነትዎች እና ህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለአስተዳደሩ ፈትጎ ማጥራት ይጠበቅ አለ። አስተዳደርአዊ ግድየለሽነት ቢኖር እንኳ ስለ ጠቢ ይህ ተገቢ እሚሆን ነው። እራስን አጥንቶ መቅረብም፣ የጠኑ ጊዜም ስነስርአት የአለው ሆኖ በስነምግባር መገኘትም፣ ከነገወዲያ ዞረው ሲቃኙት የእሚሰለብ ቅርስ አይሆንም። መስፍን ወልደማሪያም፣ ሀገርአዊ የፖለቲካ እውነትን ጠቅልሎ በቀነጫጨበ ጠቋሚ መጽሐፍአቸው – ዛሬም እንደ ትላንት? ላይ፣ ኢትዮጵያአዊነት በዓለም መድረክ በእርስአቸው ዘመን ኩራት፣ ማእረግ እና ክብር እንደ ነበር እና የጥቁርነት ጌጥ እና ፈርቀዳጅነትም እንደ ነበር በአጭር ምእራፍ ቆንጽለውት አለ። (ገ.119-128) ይህ የፖለቲካ አለምአቀፍ ኢትዮጵያአዊነት እና መገለጫው ወደ ተከረበተ ዘግናኝ እውነት፤ የዋህነት፣ ብሎም ብልግና እየተቀየረ ነው። ምንአልባት፣ እንደ ፍራንክ – ዕውቁ ቼክ አጭበርባሪ፣ በፍርድ ታስሮ በመንግስት ኀላፊዎች እየተጠራ ለሀገሩ ቼክ አጭበርባሪዎችን በማደን በእውቀቱ ወደ ማገልገል እንደ ተመለሰው – በፊትም ሆነ ሰሞኑን የእሚታሰሩ የህዋሃት. ሰራተኛዎችን ለአስተዳደሩ ሲባል ቢሆንም ሀገርም እየተጎዳች በመሆኑ፣ ከታሰሩበት ሆነውም ሆነው እንደ ፍራንክ በጥብቅ ቁጥጥር እየወጡ፣ ፕሮፓጋንዳ አሰራር እና መሰል በአንጻርአዊነት የተሻሉ ሆነው በተጨባጭ የተገኙብአቸውን ልምድዎችን እንዲያጋሩ ቢደረግ ከእሚሄደው የአፈነገጠ ዝግመት የተሻለ አማራጭ መሳይ ነው። ይህ ተመርጦ ባይሆን፣ መደበኛ ወልስሜትዎችን (common sense) በመገልገል፣ በተሻለ የሙያአዊነት እና አዲስ አስተዳደርአዊ የግንኙነት ቀለምዎች መለወጥ አስፈላጊ ነው። የአስተዳደሩ ጉዳይ በብዙ ነቁጥዎች ተሻሽሎ አለ እየተባለ አንድአንዴ ሲነገር ይሰማ አለ። ይህ እውነት ከሆነ የተሻለ እየተሰራ አቀራረብ ግን ከተበላሸ የእሚገለጠው ሌላ መልክ በመሆኑ፣ ይህ ጉዳይ አመድፋሽ አድርጎ አስተዳደሩንም ይጎዳው አለ። በደፈናው ሲደመደም፤ ህጸጸኛ (erroneous) የአለምአቀፍ ግንኙነት፣ ህዝብግንኙነት፣ እና ፕሮፓጋንዳ እውነት በኢትዮጵያ በአልተቀደመ ታሪክ እየአቆጠቆጠ ይገኝ አለ። ይህን ሁሉም መመልከት ይገድድ ዘንድ አንኳር አመክንዮዎች ተዘርዝረው አሉ፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s