Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ቋንቋ አማርኛው እና ለእሱ የአልተወጠነ ዳግምርምር ባህል

About how Amharic has to establish a research-language-culture for itself.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 22nd, 2021GC.,

ይህ አጭር ጽሑፍን በ ተአዶ. (PDF) የአንሱ። ———- (ሲጨርሱ ተያያዥ የሆነ ይህ ጽሑፍን አያይዘው ይፈትሹ።)

ቋንቋ አማርኛ በጥቂት ንግግር ባህልዎች እዚህ የደረሰን ነው። የንግግር፣ ስነቃል፣ ስብከት፣ ወዘተ. ወይም ያ ማለት አንደበት-አማርኛ (spoken Amharic) ትተንው፣ ጽሑፍ-አማርኛን ከሰነጠቅን፣ ቢያንስ በቅርብ ዘመንዎች (አንድ ምእት) ውስጥ በጥቂት ቅርንጫፍዎች የተለያየ ሆኖ አይተንው አለ። (ቅርንጫፍ እንጂ ወጥ ባህል ለማለት ከባድ ነው)። ። እነእዚህም መሀከል ወደ ባህልነት የተቀየሩ ነበሩ። ለምሳሌ የቤተእምነትዎች አማርኛ ወይም መንፈስአዊ-አማርኛ በወጥነት የአልተዛነፈ ባህል አለው። ባህል ለመሆን የከበደአቸው እንደ ተለዪ አማርኛ አስመልካችነትአቸው ግን ለይተን ማየት የእምንችልአቸው እሚከተሉት አሉ። የተጻፈ አማርኛ ብቻ በደፈና ቢመረመር፣ የፖለቲካ (በብዛት ፕሮፓጋንዳ) አማርኛ፣ የቀኃሥ. ዘመኑ የዳግምርምርዎች (researches)፣ የስነጽሑፍ (በተለያዩ ደረጃዎች የእሚለያዩ እንደሆኑት)፣ የህግ ድንጋጌዎች አማርኛ፣ የይፋ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነትዎች አማርኛ፣ የቀኃሥ. መንበር ዘመን ስነጥበብዎች እና መጽሐፍዎች አማርኛ፣ የደርግ አስተዳደር ዘመን መጽሐፍዎች እና የጽሕፈት አማርኛ፣ የኢህአዴግ. አስተዳደር ዘመን መጽሐፍዎች፣ የተለመደው የአለፉት ሰላሳ አመትዎች መደበኛ እና በእየወቅቱ እሚገጥሙን አጻጻፍዎቹ፣ ወዘተ. አማርኛን በተለየ መንገድ ጥቂትም ቢሆን ቀለም አበጅተው የተለየ አድርገውት አሉ።
እነእዚህ ወደ አማርኛ ባህልነት የአልተሻገሩ፣ ግን የአማርኛ ማንነትን ለመመስረት በሩቁ ቢሆንም እንኳ የተቀራረቡ የጽሑፍ አማርኛ ናቸው። ከእነእዚህ የደርግ ዘመን፣ ቀጥሎ የቀኃሥ. ዘመን፣ እና የህግ አማርኛ የተሻለ ወጥነት ወይም የመለት አቅም አለአቸው። ወደ ባህል ምስረታ የተቃረቡ ነበሩ። ለምን? ለምሳሌ፤ የደርግ ዘመን የጽሑፍ አማርኛ እጅግ ከተከተለው ዘመን የተሻለ የሰፋ እና የተደጋገመ የጽሕፈት እውነት ነበረው። በተለየ፣ ስለ ማህበረሰብእአዊትነት እና ማንኛውም ጉዳይ የተሻለ ህዝብአዊ የጽሑፍ ልውውጥ የተከወነበት ነበር። ዋናው ጽሕፈትአዊ የባህል መመስረት ማስረጃው፣ ከትንሽ የመልእክት ልውውጥ ሙከራ በላይ የጋለ የልውውጥ እውነት መኖሩ ነው። ያ በዘመኑ የተሞከረ ነበር። ሁለተኛ እና የበለጠ ዋናው አላባአዊ፣ ተመሳሳይ ቃልዎችን መገልገል፣ ተቀራራቢ ወይም ወጥ የአረፍተነገርዎች ቅርጽዎች መቅጠር፣ ወዘተ. እውነት ነው። ሶስተኛው እና የባህል ምስረታውን ወደ ጠነከረ ባህል አሻጋሪው፣ በአንድ ንቅአተህሊና ቋንቋውን በወጥ መንገድ ቀጥረው የእሚገለገሉት ህዝብዎች ወይም አንድአች ክፍልአቸው፣ ቋንቋውን በመገልገል ወደ ርብርብ እሳቤአዊ (of understanding) ጉዞ ለመድረስ መቻሉ ነው። ለምሳሌ አንዱን ቋንቋአዊ ትልም መርጠው የተለዋወጡት መረጃ ወይም እውቀትን ሌላዎቹ በተመሳሳይ የቋንቋ ቀለም ይዘትአዊ ምላሽ የአበጁለት አለ። ሌላውም የይዘት ቅጥያ ይጨምርበት አለ። አንዱ ወይም ሌላ አዲስ የሆነም ወደ ጋራ ልውውጥ አውዱ ተቀላቅሎ፤ ተጨማሪ ወይም አዲስ መንገድ የሆነ የእይታ አግጣጫ የአክል አለ። እንዲህእንዲያ ወየተባለ፣ በወጥ የባህሉ መንገድ የተከማቸ የእሳቤ (understanding) ወይም እውነት ግንባታ ይከወን አለ። ያ ከተደጋገመ፤ እውቀት እና መረጃውን ማመላለሻ እና መገንቢያ ብቸኛው መንገድ ከሆነ፣ አይነተኛ የቋንቋው አንድ ባህል ይሆን አለ።
በእዚህ መሰረት፤ የህግ አማርኛ ለምሳሌ ባህል የመሆን አቅም ነበረው። ነገርግን፤ ወጥ የቋንቋ ባህል መመስረቻ እድልዎቹን ፖለቲካ አጨናግፎበት አለ። የፍትሐ ብሔር፣ እና መሰል የተቀናጁ ትልልቅ ርዝመት የአገኙ ድንጋጌዎች፣ በተሰነጠቀ እና ለእራሱ በተለየ አማርኛ ባህል ይለዋወጡ ነበር። አዋጅዎችም የእነእርሱን ፈለግ መቀራረብ ይሞክሩ ነበር። በሂደት፣ የአማርኛው ልዩ መንገድ በተለይ በዘመነ ኢህአዴግ. የተዛነፈ ሆነ። ለምሳሌ ቋንቋው የእራሱን ቃልዎች ፈጣሪነቱ ጠፋ። በፊት አማርኛ አቻ የእማይፈለግለት ቃል ጥቂት ሆኖ ቢበዛ የተለመደው ፈረንሳይአዊ ቃሉን መገልገል ነበር። ቃል ሁሉ ወደ አማርኛ ተመልሶ የእራሱን ቋንቋ ባህል ይክብ ነበር። ለምሳሌ፤ ዛሬ ለአለው ወ ለዘመኑ እራሱ የተለየ አማርኛ እሚሰኘው “secondary residence” እሚለውን “ምክትል መኖሪያቤት” በማለት ቀይሮት ነበር። በዘመነ ኢህአዴግ. ህግ እንግሊዝኛ ቃሉን በቀጥታ ወደ አማርኛ ቃልትይብ (transliteration) መከወን ለምዶ አለ። ወደ ታች ሲወረድ ደግሞ፣ የፖለቲከኛ ወይም ይልቁን ካድሬ አማርኛ ወደ መመሪያዎች ሰርስሮ በስፋት ገብቶ አለ። አዋጅዎችም እሚረቀቁት ሌላ አዋጅ በጎን ይዞ በመገልበጥ ደካማ ማርቀቅ እንጂ በእራሱ የቋንቋ መብቃት እና ፈጠራ አይደለም። ይህ በመሆኑ፤ የህግ አማርኛ ቋንኗቀ ባህል እድገቱ የተደረመሰ ሆኖ አለ። በደርግ ዘመነመንግስት ተመሳሳይ የተሻለ የአማርኛ ባህል ከየት መጣ? ዘመኑ በተሻለ የተማሩ ዜጋዎች የታጨቀ ነበር። ልውውጥን በእየጋዜጣው፣ መስኮተድምጹ (radio)፣ መማሪያ አውድዎች፣ ወይም መገናኛብዙሃኑ ይከውኑ ነበር። ይህ ከአንድ ቋንቋ ወደ አንድ የጠበበ ወይም ዐውደብጁ (customised) አንደበት አደረሰው። ይህ ባህሉን ሲወጥንለት፣ የእማይናቅ የልውውጥ እና ሃሳብ ክምችት ድግግሞሽ በመኖሩ፣ ወደ አንድ ባህልነት የማደግ ቅድመ እድልን ቸሮት ነበር። ይህ ዘመን፤ ከእራሺያ በተመለሱ መጽሐፍዎች፣ የትምህርት ቃልዎች ወደ ህዝቡ መፍሰስ፣ የፖለቲካው ወደ ትምህርቱ (ርእዮተአለሙ) መቀላቀል እና ፕሮፓጋንዳው ለርእዮቱ ሀቀኛ ሆኖ በቋንቋ በመተሳሠሩ፣ ዘመኑ የተለዋወጠው አማርኛ ወጥ ባህልን የመመስረት አቅም ጀምሮ ነበር ለማለት እሚጋብዝ ነው።
ይህ ንዑስ ነቁጥ ሲጠበለል፤ ወጥ የአማርኛ ባህል የአከማቸ ክፍለ ልውውጥአዊ አለም እምብዛም አመመገኘቱን መደምደም ይሆን አለ። የመንፈስአዊ አማርኛን ግን ለማስመር የአክል፣ ትልቅ ወጥነት እንደ አለመው ማስመር የአስፈልግ አለ። ባህሉ የተቋቋመ ነው። አማርኛው እምብዛም አይዛባም። አቀማመሩ፣ በተለመደ መንገድ የመቅረብ እድል የአለው ነው። በተረፈ፤ ሌላዎቹ የአንድ ባህል ምስረታ እድልን ማንኳኳት እንጂ የመክፈት እውነትን አልፈጠሩም። በደፈናው፤ በተለመደ መደበኛው የአማርኛ አመጣጥ መንገዱ ግን ወጥ የሆነ የአንድ ባህል አመጣጥ በአማርኛ ታሪክ የለም። መነሻ ሃሳብ ከአስጨበጠን በማመን፤ ይህ ሰፊ ነጥብን ተሰናብተን፣ መነሻሃሳብ ደረጃ ለውይይት ወደ እሚቀመጥ ጠባብ ሰበበሃሳብአችን (our premisses) እንግባ። ያም፤ ይልቁንም፣ ወጥ የዳግምርምርዎች (researches) ባህል ቋንቋ አማርኛ ውስጥ የለም እሚል ነውታ (claim) ነው።
ለመመርመር ሳይሆን አጥርቶ ለመፍታት፣ የቋንቋ አጻጻፍ ባህል ምንድነው? በተለየ፣ ለእዚህ ለጥናት-ወጠኝ ጽሑፍአችን እንዲአግዘን የዳግምርምር (research) ቋንቋ ባህል ደግሞ ምን ነው? ይህ ከእሚያያዘው ጉዳይ መብራራት ቢጀምር፣ ዳራው መሰረቱን የአብራራው ስለሆነ እንዲህ አጥሮ ይታይ። አንድ ማህበረሰብእ፣ ለምን በጽሑፍ ቋንቋ ይግባባ አለ? እጅግ የአጠረ መልእክት ለማስተላለፍ፣ መልእክቱም ተነብቦ በእዛው ግንኙነቱ ሊቋጭ ከታሰበ፤ በእዚህ ጽሑፍ ልውውጥ ባህል ማዳበር እማይታሰብ ነው። የጽሑፍ ቋንቋ ባህል ገኘት፣ አንደኛ የጽሑፍዎቹ አንድአዊነት አለ። ማለትም፤ ብዙ ጽሕፈትዎች እና ቅጽዎች ቢኖርአቸውም፣ የሁሉም ኢላማአቸው አንድ እንዲሁም የተለየ ንቅአተህሊና፣ እውነት ወይም እድገት/ለውጥ ለማምጣት የእሚከወኑ ከሆነ ነው። ሁለተኛ፣ ለእረዥም ጊዜ የእሚከወን ተደራራቢ ጽሕፈት ሲገኝበት ነው። ሶስተኛ፣ ይህ የጽሕፈት መደራረብ ወጥ የመጠነቃልዎች (vocabularies) አመራረጥ፣ የቃልዎች አሰካክ ደምብዎች መሰል ልማድዎች፣ የፍሰት መንገድ ወይም ስልት፣ ተገቢ ለእራሱ ተስማሚ የቋንቋ ፈጠራ ሲያገኝ፣ ወዘተ. ይህ እውነትም ተደጋግሞ ሲገኝበት ነው። ሰፊ፣ ዘላቂ እና ተደጋጋሚ ልውውጥ ማበልጸጊያ መንገድ እና ሂደት መሆኑን እናስምርበት። የጽሑፍ ልውውጡ እንደ እዚህ ባህልን የእሚያሳድገው፣ ለእዛው አላማ አይደለም። ለይዘትአዊ ግብ ብቻ ነው። በይዘቱ፣ ልውውጡ አንድ ተግባቦትአዊ ልእልና ወይም ጫፍ ላይ ተለዋዋጭዎቹን ማውጣት የአስብ አለ። የእዛ ጥረት የቋንቋው ገጽታ ደግሞ የባህልነት ደረጃን የመመስረት እውነት አለው።
በእዚህ መሰረት፤ የዳግምርምር አማርኛ ባህል ምን ይመስል አለ? አስቀድሞ ከእዛ በተዳሳሽ መጠን አለስ? መላምቱ፤ አሉታአዊ ነው። ቋንቋ አማርኛ ዳግምርምርአዊ ገጽታው የአልተመሰረተ ነው። ዳግምርምር በእርግጥ፣ በአማርኛ የመከወን እድሉ ከቀኃሥ. ዘመን ወደ እዚህ በመጣ ቁጥር ቁልቁለት የወደቀ ነው። ወደታች መውረዱ በተለየ በኢህአዴግ. ዘመን የፈጠነ እና በእዚህ ወቅት ግብዓተመሬቱ የተከወነ እውነት ነው። የዳግምርምር አማርኛ ባህል የእማይገኝ ሆኖ ተረጋግጦ አለ። በአንድም ሆነ በሌላ አመክንዮ፣ ጥናትዎች እና ዳግምርምርዎች በአማርኛ የመከወን እና መቅረብ አቅምአቸውን እረስተውት አለ። ሙሉለሙሉ የእንግሊዝኛ ምድር ሆኖ አለ ለማለት የአስደፍር አለ። ያም፣ በትምህርት ስነግብር (methodology) አግጣጫው የተነሳ ነው። በነሃሴ 12 ቀን 2012ዓም. በተካሄደ የቋንቋ ፖሊሲ ውይይት ላይ፣ ናሁ ትመ. በዜና ቀንጭቦ እንደ አሰራጨው፣ አንድ ተሳታፊ (ስሙን ከቶ የአላስተላለፉት)፣ በእንግሊዝኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የእሚጠናው “ፍልስፍናው፣ ህጉ፣ ትምህርቱ፣ እውቀቱ…በእንግሊዝኛ ስለእሚገኝ ነው…” በማለት አብራርቶት አለ። በእርግጥ አማርኛ እንደ አንድ ጥናተ-ትምህርት (subject) እንጂ እንደ ዳግምርምርአዊ እና ትምህርትአዊ ቋንቋ የአልታወጀ ነው። ቢሆንም እንኳ፤ አማርኛን በእዚህ መጠን መዘንጋቱ ከፍተኛ ውድቀት ነው። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አንድ ወቅት እሚፃፈው ሁሉ በእንግሊዝኛ ሲሆን ተናድደው እሚከተለውነ ብለው ነበር። “ገንዘብ ለመሰብሰብ የተፈጠሩ በመሆንአቸው ቋንቋአቸው ወደ ፈረንጁ የአደላ አለ [የፖሊቲካ ድርጅትዎች ስም ዝርዝርን በእንግሊዝኛ በማግኘትአቸው ነው] …የስልጣን ጥመኛዎችም ሆኑ ምሁራን ሲናገሩም ሆነ ሲጽፉ ለኢትዮጵያዎች ጀርባአቸውን ሰጥተው ነው።” (መስፍን ወልደማርያም፣ ዛሬም እንደ ትላንት? ገ.60)። ይህ በእርግጠኝነት ሙሉ አመክንዮው አይደለም። የታወቀው የታላቁ ፕሮፌሰር የቸልተኛነት ንዴትም የአለበት ይመስል አለ። ነገርግን፤ በደፈናው እውነትም አለው። አማርኛ በእዚህ መጠን ከዳግምርምሩ አለም መባረር አልነበረበትም። በፊት የተሻለ መስተንግዶ ማግኘቱ እጅግ አንክሮት ፈጣሪ ነው። አስጊ ትልምም መከተል ነው። መነሻሃሳብ አቅራቢ ጽሑፉን ለመደምደም፤ እጅግ በቁንጽል በአማርኛ የመመራመሩን ነገር ስለማስፈለጉ በመጪው አንቀጽ አስምረን እንዝጋ።
አማርኛን በጥናትዎች እና ዳግምርምርዎች ማካተት፤ ሀገርን የማበልጸግ ሰፊ አስተዋጽዖ አለው። በተያያዥ ተጽዕኖዎች (ripple effects) ደግሞ፤ የህዝብ በንቅአተህሊና መሻሻልን አጋዥ ነው። ብሔርአዊ ኩራት፣ ማንነት፣ ስሜት (ስነልቦና)፣ ክብር፣ ወዘተ. አጋዥ ነው። በእንግሊዝኛ ለእሚያጠናው አእምሮውን አበልጻጊ ነው። (በተለይ ዎልፈር እንደ አረጋገጠው፣ እብስልስልታ እና አረዳድ-ፈጠራ (contemplation and cognition)፣ ሁለት ቋንቋዎችን ከማወቅ የተነሳ የእሚለማ እውነት ነው። በተለመደው የአለፉት ሰላሳ አመትዎች አካሄድ ግን፣ አማርኛ ተትቶ በእንግሊዝኛ ብብቻ አትኩሮት በመኖሩ ብዙ ቃልዎችን በአቻ አማርኛ ማግኘት አልተቻለም። ይህ ከሆነ፣ የተለመደው የእንግሊዝኛ ከአማርኛ ተሰባጥሮ የመነገር እና መጻፍ (አማሊሽኛ) ልማድ መሆኑ ይቀጥል አለ። ይሄኔ፤ እንግሊዝኛ አጥኚ ሁለተኛ ቋንቋ የማወቅ ትንግርት እና ብልጭታው ይሰለብበት አለ። ብዙዎቹን እንግሊዝኛዎች ከአማርኛ በመመለስ አልተማረም። የተለየ እይታን አልቀሰመም። የርእዮት-ትንግርት (of perspective puzzle) አምልጦት አለ። ስለእዚህ፤ ግንባርስጋ ነቢቡ (the theory)፣ አማርኛ ከተጣባው መዛነፍ አለመታጠቡ ለተማሪ፣ ዳግተመራማሪው ሁሉ የአሳሳቢ ችግር ምንጭ ነው። ይኽ ማብራራት በሰፊ እና ከእዚህ በበዛ ትንተናዎች፣ አመክንዮዎች እና ነቢብዎች የእሚሰፋ ነው። እና፤ በቅምሻ በእዚሁ እንበጥሰው።
ወደ ቀደመ ነገር ተሰፍተን ለመጠብለል፣ የዳግምርምር አማርኛ ባህልን ለመመስረት፣ አማርኛውን መሞረድ ተገቢ መሆኑን እንወያይ እና እናብቃ። የእሚፈለገውን መጨረሻ ለመጠቆም እንድንበቃ፣ “አማርኛ ዳግምርምርአዊ ባህል” ብንመሠርት ኖሮ በመንታ መንገድ ተበትኖ የእሚዳስሡት መሆኑን እንተንብይ። አንደኛ፣ የእየሙያው አንድአች ቀለም መገኘቱ ነው። ምሳሌ ለማምረት፣ ህክምና፣ ሒሳብ፣ ወይም ስነፈለክ ክፍለትምህርትዎች፣ በእየ ሙያቃልዎችአቸው የተለየ ድባብን ለዘርፍአቸው የዳግምርምር አማርኛ ባህልዎችን እንደ እሚያበለጽጉ ግልጥ ነው። ሁለተኛው፣ በደፈናው ወል የጥናትዎች አማርኛ ባህልን እንገምት። ይህ ከስነግብር፣ ቋንቋአዊ እና ወጥ የዳግምርምር ጽሕፈት እና ተግባቦት ገሀድዎች የእሚጨመቅ ዉጤት ይሆን አለ። በደፈናው፣ ለማንም አጥኚ እሚሆን አማርኛ ባባህል ነው። ለአብነት የአክል ዉስጡ እሚገኘው፣ የልህቀት እና ጠቅላይ አእምሮአዊ አድማስ ለጣጭ፣ ብልጭታ ጠሪ፣ ወዘተ. የቋንቋ ቅጽ ነው እንበለው። ግን እነእዚህ ለየቱም የዳግምርምር ቋንቋ ገሀድ ሲሆኑ አማርኛን ከበረቱበት አንድ መጨመር ይገባው አለ። ያም፣ በጠለቁ የሰዋሰው ደንብዎችም ላይ ከፊል-ደንብ ሊጎርስ መቻሉ ነው። ለምሳሌ፤ “-ን”ን አለአግባብ እንደ ተርታው አማርኛ ትርፍ ሆና ሳለ አለመሰግሰግ እና አረፍተነገርዎችን በአነስተኛው የሰዋሰው ደንብዎች ስብጥር ለማሟላት መጣርን ሊያቅድ ይችል አለ። አማርኛ በእዚህ የተዝረከረከ ሰዋሰው በመያዙ ይህን መሰል ቋንቋውን የአሻሻለ አካሄድ የባህሉ መገለጫ ሊሆን ይችል አለ። በተረፈ፤ ንዑስ ባህልዎች ተጠባቂ ናቸው። ለምሳሌ አንድአንድ ጸሐፊዎች፣ በአጭር እና ቀላል አማርኛ፣ ሌላዎች በረዥም እና ልእለውስብስብ ስልትዎች ሊቀርቡ ይችል አለ።
በአማርኛ የዳግምርምር ጽሕፈት አይሞከርም ለእሚሉት ደግሞ፤ የስብሃት ገብረእግዚአብሔር እና ታላቁ ብሔርአዊ ቅርስ ዳኛቸው ወርቁን መጠቆም በቂ ነው። አማርኛ የዳግምርምር ባህሉ ሞቶ እንዲሁም በደግ ደረጃ ሲቀድምም ሳይመሰረት የአለ ነው። እነሆ ችግርዎቹን እየቀመለ፣ ባህልን ከፈጠረ፣ ማንነት ለግሉ አነፀ ማለት ነው። ያ፣ ቀድሞ ስለ አልተጎዘጎዘ በአማርኛ አጥንቶ መጻፍ አይታሰብም ማለት እኔ እንድጽፍ ቀድሞኝ ሌላው እየጻፈ ጎኅ ይቅደድልኝ እንደ ማለት ነው – ጥቂት የድኩምነት አመክንዮ፨

—– —– —— —– —– ——

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s