Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

አዲስ ቃልዎች (ስያሜ) ዐማርኛ ቋንቋ ውስጥ፦ ስለ አራት መርኆዎች ትንተና

Four principles, some original for Amharic language, in naming. ስም ስለማውጣት (ስያሜ) አራት መርኆዎች ለአማርኛ ቋንቋ፨


Pick this piece in PDF.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 12th 2021,

አንድም ይታገል አለ አንድም ሲታገል ከጠነከረ ይቀራረብ አለ እንጂ፣ የተመዘገበ የቱም የሰው ቋንቋ እንኳንስ ሲወለድ አድጎም ሙሉ አይደለም። መጠነቃልዎቹ (its vocabularies)፣ አንድ ምስክርዎቹ ናቸው። በእየጊዜው፣ የቱም ቋንቋ አዳዲስ ቃልዎችን እንደ አበጃጀ ነው።
የጠነከረ ተጨናቂዎች ቋንቋው ከአሉት፣ ቃልዎች ከውጭ ቋንቋ ሲመጡ በቀጥታ ከመዋስ በእራሱ መንገድ ይተረጉም አለ። ብቻ፣ አዲስ ቃልዎችን ለማምረት ከፈለገ፣ ለእራሱ በየቱም ቋንቋ አዲስ ቃልዎችን ለማበጀት ብዙ ደንብዎች አሉ። ከእነእዚህ በአማርኛ የእሚገጥሙ መንገድዎችን እንመልከት።
አንደኛ፤ ከሌላ ቋንቋ እሚተረጎም ቃል ከሆነ የእዛ ቋንቋ ስርወ-ትርጉሙን (its etymology) ማጥናት ነው። ያ፣ የቃሉ መነሻውን አስታውቆን፣ ለቃሉ አዲስ አቻ ፍቺ መንገድ ይከፍትልን አለ።
ሁለተኛው፣ የእሚሰየመው ነገር ነገረስራ መውጫመግቢያውን አጥንቶ እሚገልጠው ቃል ማበጀት ነው። ይህን በሁለት እንሰንትረው። አንደኛው ቀላል የድምፀት፣ ባህሪ፣ ወዘተ. ጥናትዎችን ከውኖ በእዛ መሰረት ቃል ማበጀት ነው። ለምሳሌ፦ በረረ እሚለው ከወፍ የመብረር ወቅት ድምጽ ሲበርሩ ከእሚሰማው “ቱርር” እሚለው ድምጽ የአደገ ነው። ወይም፣ ሁለተኛው የነገሩን ባህሪይ በጠለቀ መንገድ ማጥናት እና ባህሪውን መግለጫ ቃል በማብሰልሰል ስራ ፍፃሜ በመፈልሰፍ ነው። ለምሳሌ፣ መደዴ ናሙና ለመጥራት፣ በር ይቀረቀር አለ። ያንን ድርጊት ከዋኙን ቁስ ከግብሩ የተነሳ፣ መቀርቀሪያ ቢሉት እንደ ማለት ሊሆን ይችል አለ። ሌላምሳሌ፣ ወታደር እሚለውን ወል ስም አንዲት አዛውንት “ወጥቶ አደር” ብለው ወጥቶ ውጭ በድንበር የእሚያድር ከእሚል እሳቤ መምጣቱን ሲናገሩ፣ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ኀዲስ) ደግሞ “ዋትትቶ አደር” በማለት ወጥቶ ከመልፋት በእየመልክአምድሩ ከመዳከም ስራው የመጣነው ብለውት አለ። በደፈናው፣ ቃሉ በየቱም ስርወትርጉም አመጣጡ ብንወስደው፣ የበለጸገው የእሚገልጠውን ጋርዮሽ-ስም በማጥናት ነገረስራውን ዝምብሎ በማስቀመጥ ብቻ ስም ሁን ብሎ ነው።
ሦስተኛው፣ አዲስ የአልተለመደ ቃልን አማርኛ ማበጀት ከፈለገ፤ የእምንፈጥርለት አንድ መንገድ፣ ቅጥያዎችን በመገልገል እንዲገለገል ነው። የተለያዩ ቅጥያዎች በአማርኛ አሉ። በስፋት የአጠና እና የዘረዘረአቸው አልገጠመኝም። ግን፣ ብዙ ተቀጣይዎችን በተለያየ መንገድ በመሞረድ፣ አዲስ የስያሜ ቃሉን እንዲያግዙት እና እንዲቆረቁሩት ለመከወን የእሚቻል ፈጠራአማ አማራጭ ነው። የእሚፈጠረው አዲስ ቃል የነጻ አዲስ ቃል መሆኑ በእርግጥ አይጠበቅም። ግን፤ ደግ አዲስ ትርጉም የእሚበጅለት ቃልን ለማብቀል እሚቻል ነው። ለምሳሌ፣ ጮርቃ እሚለው ለጋ በእሚለው እሚተካ ነው። የተለያዩ አጋጣሚዎችን ከእዚህ ቃል አንፃር ከአገኘን፣ በእዚህ ቃል ቅጥያ ሰፍቶበት መፈልሰፍ እሚቻል ነው። ምሳሌ፣ ጮርቃበል (እንጭጭ የእሚመገብ ማለት ነው)፤ ጮርቃጠል (እንጭጭ ወይም በፍካሬ ፍቺ ጅማሮ ወይም ውጥን የእማይፈቅድ እሚል ፍቺ አበጂ ነው)፤ ማእዶት-ጠል፣ ጋዜጣ-ጋዜጠኛ፣…። ከአሉት ብዙ የአማርኛ ቅጥያዎች አንጻር አማርኛ ይህን መንገድ ገና አልተገለገለውም። ብዙ ቃልዎች ይህን መንገድ ቢቀጥሩት፣ በተሻለ ጥራት የቋንቋውን የአግባቢ እና አስተሳሰብ ረጂነት እሚያግዙት ይሆን አለ።
አራተኛ፣ ግስን ወደ ስም የማዞር ሂደት ነው። አማርኛ ደስ የእሚል ብልሃት በእዚህ ውስጥ አለው። ነገርግን፣ ግስን ወደ ስም አዙሮ ስምዎችን ማዘመን፣ ማብዛት እሚቻለው፣ መንገዱን አስፍቶ በመጠቀም ነው። እንጂ ይህ የአማርኛ እውነቱ እጅግ ቁንጽል ነው – ቢያንስቢያነስ በመሀጀልሀገር አማርኛ የአለው። ነገርነግን እንደአልንው፣ ይህኛው አካሄድ እጅግ የተዋበ (ሳቢ) ስለእዚህም አነቃቂ (አእምሮ አብሪ) አቅምን ለተናጋሪዎቹ ይለግስ አለ። ችግሩ፤ እንደ ሼል ሲልቨርስቴይን ለጋሷ ተክል፣ ከቋንቋው መጠቀም እንጂ የአለውን ሲጨርስ ዳግ-ልማት ስለእማይከወን የአልበዛ የአማርኛ አቅም እንዲኖር ሆኖ አለ። ይህኛው መንገድ፣ ቋንቋንመ ለምሳሌዎች ገባ (ግ.) = ግባት (ስ.) (ፀሐይግባት)፤ መጣ (ግ.) = መጡልሽ (ስ.)፤ ራስምታት፤ ወዘተ.። በእዚህ መንገድ የእሚሰየሙ፣ ጠንካራ የትርጓሜ ልማድን ማስረጽ እሚችሉ ናቸው። አማርኛ ገና ብዙ እሚሰይምአቸው ቃልዎች ይፈልግ አለ። የመጠነቃልዎች ገና እንጭጭነት በአማርኛ አለ። ምክንየሰቱም፣ አማርኛ ውልደት እና የአሁን እድገቱ ሀጠር ነው። በእዛ የአሉ እንደ “መራዥ፣ ሰግ” መሰል ቃልዎች፣ በመሀከገልሀገር አማርኛ የሉም። ማለትም አማርኛን ተገልጋይ መሀከልሀገሬው የአማርኛ መደበኛ ብቃት እንኳ የለውም። ወደ መደበኛ አማርኛ የገጠሩን ለማዝመት፣ አስቸጋሪው ነገር ጥቂት ማሻሻያ አንዳንዴ ማስፈለጉ ነው። ያም፣ ለዘመኑ የእሚሆን ቋንቋ እንዲሆን ቢያንስ ታካይ ፍቺ ማጉረስ ማስፈለጉ ነው። ለምሳሌ፣ ሰግ እእምትለውን “እሳትሰግ = firewall” ብሎ መሰየም የአስፈልግ ይሆን አለ። ሁለተኛው ገጠር አማርኛ ምን ቢፋፋ ለዘመነ ነገር ሙሉለሙሉ እማይሆን ይሆን አለ። ለምሳሌ፣ በስፖርት ፉክክርዎች የገጠር አማርኛ የከበደ ዘመቻ ማድረጉ አይቀርም። ከእነእዚህ ሁለት ችግርዎች የተነሳ፣ አማርኛ በመሀከልሀገር ተቸግሮ አለ። ለምሳሌ፦ በአማራ ትመ.፣ አንዲት ወጣት ጸሐፊ በባህርዳር በ2012ዓም መጽሐፏ መመረቁን የዘገ ጋዜጠኛ “…የደራሲዋ ከአጭር ልብወለድ የረዘመ ከረዥም ልብወለድ የአጠረ ልብወለድ መጽሐፍ ባለፈው እእሁድ በሙሉአለም አዳራሽ ተመረቀ” ብሎ ዘገባ ጀምሮ ነበር። በእጅግ ቅርቡ፣ በዘአንድ ዓመት ዘግዩው 2012ዓም. ኦሊምፒክ፣ የአየውን ዘገባ በእዚሁ ትመ. ሲዘግብ ጋዜጠኛው የአለው እሚከተለውን ነበር። “…ተስፈንጥሮ በመዝለል አካልን አሽከርክሮ ወደ ውሃ በመዘፈቅ ውድድር…”
እነእዚህ አብነትዎች እና የአማርኛ ከተማ እና ዝሙን ሽልፍኖትአዊ (technological)፣ ህይወት፣ አማርኛ አዳዲስ ቃልዎችን እንዲያበለጽጉለት ህዝቡን እና መንግስትን ይፈልግ አለ። ይህ ሲከወን፣ ስያሜ ማብቀል ጋር ይኬድ አለ። እነሆ፤ እነእዚህ መርኆዎች እና መንገድዎች መነሻ ሊሆን ችል አሉ።
አዲስ-መጠነቃልዎች፣ በአማርኛ ስያሜን ሲያበጁ፣ እነእዚህን መርኆዎች መገልገል የእሚችሉ ናቸው። በተለይ በአንክሮት ነገርን በመመርመር አዲስ ተስማሚ ቃል ቢፈለስፉለት አእምሮን አልሚ እሚሆን ነው። በአነሰ ግን ማለት ይቻል አለ በአቻ መጠን የቅጥያ ቃልዎችን አክሎ ቃልዎችን ማበጀት አንዱ ትልቅ መንገድ ነው። አማርኛ በአደገ የቃልዎች መጠን የእሚገኝ ነው። በተለይ ከግእዝ የእሚዋስአቸው በአገልግሎት እንዲውሉ ከተፈቀደ። ነገርግን፣ በተለመደ አማርኛ እሚደመጡ ቃልዎች እጅግ ትንሽ እና የቋንቋው አነስተኛ አቅሙ ብቻ ነው። ይህ ውድቀትን ለመርታት እና ቋንቋውን በትልቅ መጠን የልህቀት መገልገያ ለማድረግ፣ የአሉትን የራቁ ቃልዎች መቅጠር አንዱ መንገድ ሲሆን፣ ሌላው በእዚህ መንገድ አዳዲስ ቃልዎችንም ማበጀት ነው። በተያያዘ፤ ከሌላ ቋንቋ የእሚገኙ ቃልዎችን መዋስ አደገኛ በመሆኑ ይህ አካሄዱ ተመካሪ ነው። የሌላ ቋንቋ ቃልዎች ወረራን በባህል መበረዝ፣ በብሔርአዊ ስሜት፣ በሀገርበቀልነት ስነልቦና፣ ወዘተ. ስጋትዎች መዝነው ቢከራከሩብአቸውም፤ ዋናው የስነቋንቋ አመክንዮ ግን፣ አንድ ቋንቋ በእራሱ መንገድ ሙሉኛ በመቆም ቃልዎችን ለምሳሌ ከአላበጀ ለቋንቋው ተገልጋይዎች የአእምሮ ነፃ አመለካከት አያመቻችም። [ሁለት ቋንቋ ማወቅ በመንታ ምላስ መግባባት ብቻ ሳይሆን – ዎልፈር እንደ አረጋገጠው – አመለካከትአዊ አቅምን ያጠራ አለ። ቢያንስቢያንስ ለመናገር-ማሰብ (thinking before speaking)፣ ላይ የተለያየ አመለካከት እውነትን እንድንሞክር የአደርገን አለ። ቃልዎች ከአንዱ ቋንቋ ወደሌላው መጥተው ሁለቱን ቋንቋ በማወቅ ጊዜ ተመሳሳይ የአንድ ቋንቋ ቃልዎችን በሁለቱ ቋንቋዎች ከአገኘ፣ አእምሮ በተለየ መንገድ አንዱን ነገር የመመልከት እድሉ ይዘጋ አለ።] ስለእዚህ፣ አንድ ቋንቋን ቃልዎችን ከመዋስ መፍጠር አእምሮን አብሪ የአደርገው አለ። ይህ እንዲሆን፤ ከብዙዎቹ ፍኖትዎች መሀከል፣ የተዘረዘሩት አጋዥዎች ናቸው፨


By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s