Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ኢትዮጵያአዊ የትምህርት ፍልስፍና

About attempting a home grown education philosophy / policy for Ethiopia – written in Amharic. ለኢትዮጵያ ሀገርበቀል የትምህርት ፍልስፍና ወይም ፖሊሲ ለመሞከር የተጻፈ አጭር መነሻ ጽሑፍ።

—————————————————————————————————————- በ ተዶአ. (PDF) ይህ አጭርጽሑፍን ይጋሩ።

—————————————————————————————————————–

“ድንቁርና ይጥፋ፤ እውቀት ይስፋ፤ ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ!”

፨ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሔረ ቡልጋ፨

bY Binyam Hailemeskel Kidane, August 23rd 2021GC.,
* በጽሑፉ መሀከል አንድ ቃልን ሙሉ ቅንፍ፣ – () – ከተከተለ፣ ለቃሉ እንግሊዝኛ አቻ ቃል በጽሑፉ መጨረሻው ይገኝ አለ ለማለት ነው፤ ንባቡ የአንባቢዎች ዓይንዎች እንዳይጎረብጥ ይህ ተደረገ።
* እነእዚህ ቃልዎች ላይ የአተኩሩ፦ ሀገርበቀል እውቀት፤ #ሀገርአብቅል_እውቀት፤
* አጽሕሮተጽሑፍ፦ ስለ ስለአልጠለለ የተደናበረውን “ሀገርበቀል እውቀት” በዘመንአዊ ትምህርትስርአት ማካተት ጉዳዩን አጥርቶ ወደ #ሀገርአብቅል_እውቀት)- ሙሉ ወጥ ኢትዮጵያአዊ የትምህርት ፍልስፍና – የማሳደጊያ መንገድን መቀየስ።
* ቃልዎች ብዛት 3,000+ ፤ ቁምፊ() ኒያላ፤ ለመካከለኛ አንባቢ፦ ፲፭ደ. ንባብ።
—————————————————————————————————————-

፩) ሀገርአዊ የሆኑ የትምህረወት ጉዳይ ናፍቆትዎች

፩ሀ) ኢትዮጵያ ባለ ዘመንአዊ ትምህተት ስርኣት ነች

አንዱ ለቅርብዘመንዎቿ-ኢትዮጵያ የአልተሳካ እውነት፣ ለእራሷ ብጁዐውድ()፣ ስርዓተ-ትምህርት እና ዳግ-ምርምር()፣ እና ስነግብር()፣ መመስረት ነው። በዐዋጅ ሀገርአዊ የእውቀት ልማት ማስተናገጃ ፍኖት አልተወለደም። የሀገር እውነትን መመርመር ብቻ ኢላማው የአደረገ ንጥል (ወጥ) የእውቀት አካል ማከማቻ፣ ማሰሻ፣ እና ወደ አገልግሎት መጎልጎያ ስርዓት የለም። ኢትዮጵያ በተለይ ከ ሃያኛው ክዘ. መባቻ ጀምሮ በዘመንአዊ ትምህርት ይዘት እና ስርአት እየተቋቋመች የአለች ናት። ቤተክህት እና ለቤተንጉስ/መኳንንት/መሳፍንት እሚሰጡ ትምህርትዎች እየተገሸሹ በዝሙን የትምህርት ይዘት እና ስርአት ግዝግቤት() እየተቀየሩ መጥተው አሉ።

፩ለ) ሀገርአዊ የእውቀት ማእድ/ስርአት-እና-ይዘት/ ወሬው ጮርቃ ነው

ስለእዚህ፤ ይህ ሀገርአዊ የእውቀት ማእድ ስርኣት እውቅና እና ቀጠራ ጉዳዩ፤ በገጠጠ መንገድ የተወለደው በቅርብ አስርታት() ነው – የገነነው በተለይ ከ ቀኃሥ.()፣ ጀምሮ ነበር። መስፍን ወልደማርያም (ፕሮፍ.)፣ ዛሬም እንደ ትላንት? ላይ በዘመንአቸው፣ ዘመንአዊ ትመህርት የእሚማሩት የመኳንንት ልጅዎችን በአብነት ተማሪዎች “አስኳላ” ብለው ይነቀፉ እና ይጠሉአቸው እንደነበር ይናገር አሉ (ገ.123)። ያኔ ለረዥም ዘመንዎች በአገልግሎት የአረጀው የሀገር ውስጥ እውቀት ገበያ ስርአቱ እና ይዘቱ፣ በገሀድ በአደባባይ ትምህርት() ውስጥም፣ ቦታ ይፈለግለት ይባል የጀመረበት ዘመን ሆነ። ቀኃሥ. እራስአቸው፤ የሀገርበቀል ጥናትዎችን መተው እንደእማይገባ፤ ዘመንአዊ ትምህርቱን ሀገር ከኖረበት የእውቀት ስርአት ውጭ ማሳደድ “…በድቡሸት ላይ ቤት እንደገነባው ሰው መቀለጃ ለመሆን ነው።” በማለት በአንድ መጽሐፍ መግቢያ የከተቡትን አንብቤ አለሁ። ሲደመደም፤ ገና ለይፋ ስርአት ዛሬም ባይበቃም፣ እስከእዚች ሠአት፣ እድሜጠገቡ የሀገር እውቀት ማእድ ስርኣት በዘመነው ወንድም ስርአቱ የመስተንግዶ ስፍራ እንዲያገኝ ብዙ እየተባለ ነው። የዘመነው ሙሉኛ ይቅር ባይ ነቁጥ አልገጠመም። ነገርግን፤ ይህ ለሀገር የእውቀት ስርአት እና ይዘት (ግእዝ-መር ጥናትዎች) የመታገል አመጣጡን ስናይ አጭር እድሜ የአለው ትግል ነው። በቅርብ ደግሞ የእየ ጎሳዎችን ልማድአዊ ተግባርዎች ወደ ሀገር የአፈራው የእውቀት ማእድ በእሚል ከግእዙ በመቀየጥ በደፈናው ግእዝ እና የባህል ልምምድዎችን “ሀገርበቀል እውቀት” በማለት ሰይሞ ለማጥናት የመሞከር ጉዳይዎች ብቅብቅ እየሉ ነው። ይህ “ሀገርበቀል እውቀት” ተብሎ የተጠራ፤ ጉዳይን ሰንጎ በደንብ የአብላላ እምብዛም የለም። ገና ሹክሹክታ እና ጉርምርምታ፣ ወይም በተቀላቀለ መንገድ እንጂ መደበኛ እና ከምንም በላይ ይፋ አተያይን አላገኘም። ለምን? እሚመስለው ተከታዩ ነው።

፩ሐ) ሀገርበቀል እውቀት የአልጠራ እውነት ነው

“ሀገርበቀል እውቀት” እሚለው ውይይት ስር፤ የአልጠራ ፍላጎት እና ቁጭት፣ እንጂ ወጥ ፍልስፍና አይገኝም። አንዳንዴ፣ በዓለም መድረክ ሀገርአዊ “አለሁኝታ” ማሳያ እሚደረግ ጥረት ሆኖ እሚገኝ ነው። የአልጠጠረ ሀገር-ፍቅር መግለጫ መንገድ እንጂ ሌላ ደንዳና ፍልስፍና አብዝቶ የአልኮተኮተው አውድ ነው። ምን ማለት ነው? ለምሳሌ፤ የጎሳዎች ባህልዎች እና የእምነት እውቀትዎች፣ በኢትዮጵያ በዘመንአዊው መንገድ በፊትም ይጠና አሉ። በአለምአቀፍ ደረጃም በኢትዮጵያም፤ ዘመንአዊ ትምህርት በ ተለያዩ ስነሰብእ እና ማህበረሰብእ ጥናትዎች፣ ባህል፣ ልማድ፣ ወግ፣ እምነትዎች፣ ወዘተ. የአጠና አሉ። ከእዚህ አንጻር የተነሳው “ሀገርበቀል እውቀት” ብቻ የእነእዚህ ጥናትዎች ዝርዝር እንጂ ግልቋሚ አዲስ አውድ አይደሉም። ሌላው ነጥብ፤ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋምዎች ወደ ህዝቡ በወሬ ደረጃ ሀገርአችን እውቀት አበልጻጊ ነበረች በእሚል አርእስት ውይይት ለመጫር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋምዎች የተመዘዘ ውይይት እና ስለእዚህም ህዝብአዊ ግንኙነት() እንጂ የሠመጠ ፍልስፍና እና ስነግብር የአለው ወጥ ትምህርትአዊ መንገድ ሆኖ አናገኘውም። ሶስተኛ ደግሞ፤ የሀገር ባህል “መበረዝ” የአሳሰበው ተቆርቋሪነት ትምህርት ስርአቱ ዳግ-ቅኝት() አድርጎ የሀገር ልማድ፣ ወግ፣ ባህል፣ ልምምድዎች፣ ወዘተ. ቢጨምር የተሻለ ነው እሚል የክርክርቴ() መስመር ሆኖ የቀረበ መንገድ ነው እንጂ እንደ አልንው የተወሳሰበ ወጥነት የአለው ግልቋሚ አማራጭ አይደለም። ከእዚህ በተያያዘ ተጨማሪ አመክንዮዎች ሊነሱ ይችል አሉ። ለምሳሌ፤ አንድ ተቆርቋሪ፤ ጠሚ. አብይ አህመድ (ዶር.) አግኝቼ ላናግር ብለው በ ፋና ትመ. (Tv) በ 2011 ቀርበው ሲናገሩ፤ የአቀረቡት ሃሳብ፣ ህዝቡ፣ ስራአጥ እየሆነ የአለው በትምህርት ስርአቱ ክሽፈት ነው፤ የሀገር እውነታን አብሮ በተግባር-ተኮር እውቀት እና ክሂሎት ሸመታ መማር አለበት። ለምሳሌ፤ ግብርና፣ እርሻ፣ ፈትል፣ ወዘተ. ቢማሩ፣ በዘመንአዊው ትምህርት ቢወድቁ ወደ ገጠር ገብተው ለመስራት የአግዝአቸው አለ እና የሀገር ባህል እውቀት እና ልምምድ ተግባርዎች በትምህርት ስርአቱ ይካተቱ። ያኔ ስራፈጣሪነት እና ስራአጥነት አንድ እገዛ የአገኝ አሉ ብለው ነበር። ከእዚህ ነቁጥ እንደ እምንረዳው፤ አዲስ ወጥ የሀገር ትምህርት ፍልስፍና ማበጀት ሳይሆን አላማው ስራነክ ጉዳይዎችን መርዳት ነበር። ስንምጣኔአዊ ውድቀትን ለመርዳት እንጂ የሠፋ የትምህርት ሁለንተናአዊ ፍልስፍና ሰበበሃሳቡ() አልነበረም። የሀገርበቀል እውቀት በእሚል አርእስት ግን የተደረገ ልውውጥ ነበር።
በደፈናው፤ ሀገርበቀል እውቀት፣ ኢትዮጵያም የእውቀት ምንጭ ናት እሚለውን – ሌላው ሲሠለጥን ኋላቀሪ ብንሆንም ቀድመን ጀማሪ ነበርን ለማለት የአክል ቁጭት አስተጋቢ የንግግርዎች አውድ – እንጂ የነጠረ() ወጥ ፍልስፍና የለውም። ይህ አንድም ተምኔትዮጵያ (ኢትዮጵያ ፍፁም እና ወደርየሌላት እሚል መደዴዎች() እሳቤ ነው፤ ዌንዲ ቤልቸርን የአስፈገገ የጥንቱን ሀገርአዊ ድልዎች የመዘብዘብ አመል ብቻ ነው የተባለ ነው። ከማንአንሼ እይታ ወይም እውነትም የእውቀት እና ልማድ ሀብትዎች አሉን አስብል መደምደሚያ ለማጫር እንጂ ሀገር ለማቅናት የተመነዘሩ ወይም የተገለገልንብአቸውም ጉዳይዎች አይደሉም። በእርግጥ፤ በእዛም አለ በእዚህ፤ እነእዚህ “ሀገርበቀል እውቀት” በእሚል የተዛባ ስያሜ ተጠርተው አሉ። እውቀት ሰብእአዊ እና የፍልስፍና ጥናትዎች ወገን የሆነ ድንበርአያቅ ባህሪይ ነው። ከለብአዊነት ተፈጥሮው ለአዳምዘር ዘረፍጥረቱ() የመነጨ ስጦታው ነው። እውቀት ድንበር የለውም ከአልን፣ “ሀገርበቀል እውቀት” የመሰረትአዊ ስህተት የአፈነው ስያሜ ነው። እውቀት በአንድ ድንበር ዙሪያ ይጀመር፣ ይበለጽግ የአድግ አለ። ያ ደግሞ እንደ አልንው የአካባቢው ልማድአዊ ልምምድ ተብሎ ከየትምይምጣየት በመላው አለም የእሚጠና ነው። ይህን ተራምዶ መቅደም ከአልተቻለ ወደኋላ እራስን ጎትቶ የመፍጨርጨር ጥረት እንጂ የዳበረ ንጥል እና ንፁህ ጉዳይን አያስመለክተንም።
የኬንያ፣ ብራዚል፣ ወይም ሌላ ሀገር እውቀትም፣ ለተራ ስያሜ እና ኩራት-መር ውይይት ከሆነ ሀገርበቀል እውቀት ነው። የትም እውቀት ቢወለድ፣ የሰብእአዊነት ጥበብ እና ለማንም የእሚበጅ እስከሆነ፤ የሰብእዓስተኔ() ሃብት ሆኖ በአለም የታወቀ እና የተጠና እየተጠናም የእሚቀጥል ነው። ሀገርበቀል እውቀት በእሚል የኩራት ምንጭ እንጂ ባይተዋር ፍልስፍና አይሆንም። የሀገሩ ባህልአዊ (ወደ ዘመነ አብርኆት የአልተሻገረ እና በዘመነ ስነግብር የአልተጠና፤ ቀጥሎ የአልተወሳሠበ እና ወደ ተዘርዛሪ አዳዲስ የስርአት መዋጮነት የአላደገ፤ ልማድአዊ ድግግሞሽ ስለሆነ ከማንነት እንዲጣበቅ የተደረገ) የልማድ አይነት ነው – በደመነ መልኩ እየተጠና የከረመው እና የአንድ ሀገር ብሄረሰብእ ልማድ መሆኑ የታወቀው የጎሳዎች ተሞክሮ። የግእዝ እውቀትዎች ደግሞ፤ ከዘመነው እየተቀላቀሉ ከምንም በላይ በዘመነው ስርአተትምህርት ታቅፈው እየተጠኑ የእሚገኙ እንጂ የግልአቸው ስርአተ ትምህርት የሌለአቸው (አብነት ትምህርትቤት ወይም መንፈስአዊ ትምህርትቤትዎች በቀረ)፣ ነው። ሲደመደም፣ የ”ሀገርበቀል እወቀት” ከእሚሰኘው፣ የጎሳዎች ልማድአዊ ተሞክሮው()፣ በእየክፍለትምህርቱ በሰፋ እና ጠለቀ መንገድ ከምንም በላይ ዳግምርምርአዊ ስነግብር በመገልገል የልማድ ተሞክሮዎች ወዘተ. በእሚል በዘመነ መንገድ የእሚጠና ነው። ሀገርበቀል እውቀት ሲባል የስነውሳኔ()፣ ልማድ እና ቅጥአጥ ኩራት ይሆን አለ እንጂ ቀድሞም በአለም ሁሉ የእሚጠና እና ስያሜ የአገኘ እውነታ በመሆኑ ይህን ራሱን የቻለ ስርአተትምህርት ወይም ንጥል ሀገርአዊ የትምህርት ይዘት ለማድረግ መሞከር በዐድ ትትረት ነው። በሌላ አገላለጽ፤ “ሀገርበቀል እውቀት”፣ የአልጠራ እና በግሉ የእውቀት ማእድ ስርአት ሆኖ የአልተበጀ ነው።

፪) የሀገር-ትምህርት ግንኙነት አዲስ እድል

፪ሀ) ዘመንአዊው ስርአት ገዢ ነው

ኢትዮጵያ ለአለፈው ምእት ዘመንአዊ ትምህርት ስርአትን ለእራሷ በይፋ እና በስፋት ቀጥራው የእምትገለገል ሀገር ሆና አለች። ጎንለጎን የጎሳዎች ተሞክሮዎች፣ ጠቅላላ የሰብእአዊ እውቀት፣ እና የእምነት ትምህርትዎች በህዝቡ መሀከል አሉ። በደፈናው ግን፤ ዘመንአዊው ስርአተትምህርት ሀገርን በዋነኝነት አገልጋይ ነው። ስርአተትመህርት ስንል፤ በውስጡ የይዘት ውጤት፣ የስነግብር ዘዴ፣ የስነሂደት() ዝግመት ወይም እርምጃዎች፣ እና ከሌላው የሀገር ስርአትዎች (ለምሳሌ ይፋ ስራ፣ ምዘና፣ ንግድ፣ ወዘተ. ስርአትዎች) ጋር ተስማምቶ የመቀነባበር አቅም ተሰጥቶት የእሚገኝ ዋናው የዜጋዎች አእምሮ ማበልጸጊያ ይፋ አማራጭ ነው። ሀገር ከትምህርት የአላት ይፋ ግንኙነት ጥራት ከአጎደለ በቀረ አለምአቀፍአዊ እና ዘመንአዊ ነው። ከላይ (፩ሀ) ላይ የሰፈረ ውይይት ዳግ-ማስመሪያ ነው።

፪ለ) የትምህርት ስርአትን ኢትዮጵያአዊ ማድረግ ወይም ከሀገር እውነትዎች ማገናኘት

ከላይ እንደሰፈረው ቀድሞ (፩ለ) ፤ ሀገርን ከዘመንአዊ ትምህርት ለማስተሳሰር ሶስት የሙከራዎች እውነት ተገኝተው ተጠቅልለው አሉ። አንዱ ሀገርአዊ ኩራትን ለማንፀባረቅ፤ ሁለተኛው የሀገር አኗኗር ዘዴ ሀገርአዊ ቀለሙ ወይም ባህሉ እንዳይደበዝዝ፤ ሶስተኛው ስነምጣኔአዊ ትርፍ ለማግኘት የእሚከወን የ “ሀገርበቀል እውቀት” ውይይት አለ። እንደ አየንው ደፈናአዊ፤ የአልተጠቀለለ፤ ወጥነት የጎደለው፤ ነው። ስርአተትምህርቱን ኢትዮጵያአዊ ማድረግ አይችልም። ቀጣዩ ጥያቄ የእዚህ ንዑስ ውይይት ከእዚህ ይወለድ አለ። ሀገርን ከሀገርአዊ የትምህርት ፍልስፍና ማስተሳሰር ይቻል አለ ወይ? በየትኛው አካሄድ (እንዴት)? ለምን?

፪ለ፩) ዐብይ ሀገርአዊ ስርአተትምህርትአዊ ለውጥ ቅዠት ነው

በአሁን እውነት፤ ሙሉለሙሉ ኢትዮጵያአዊ ስርአተትምህርት ማበጀት አይታሰብም። የአንድሀገር ብቸኛ ስርአተትምህርት የለም። ምእራብአዊ ስርአተትምህርት የእሚሰኘው እጅግ ወጥ፣ ገሀድተኮር()፣ እና የተለመደ ከምንም በላይ በኢትዮጵያም የሰረጸ ነው።
ቀጣዩ የነበረው ጉዳይ፤ የሀገር ውስጥጣ ልማድአዊ ሙከራዎችን እና ተግባርዎችን ለተማሪዎች እስኪያድጉ በትንንሹ የመስጠት፤ በከፍተኛትምህርት ደረጃ ደግሞ በሰፊው የማስጠናት መንገድ ሶስተኛ ደግሞ ህዝቡን የመስበክ ጉዳይ ነው። ሁለተኛው አስቀድሞም በስፋት እየተከወነ ነው። ሶስተኛው፣ ለህዝቡ የማስተማር፣ የማሳወቅ፣ ወዘተ. ነጥብዎች እንጂ ስርአተትምህርት የመሆን እድሉ አናሳ ነው፤ ጉዳይነቱም ህዝቡን ማሳወቅ ብቻ ነው። የመጀመሪያው ደግሞ፤ የአለን ጎሳዎች ልምምድዎች እና እምነትአዊ እውቀትዎችን ቀነጫጭቦ ማሳወቅ ነው። በደፈናው ሲደመደም፤ የቱም መሰረትአዊ አዲስ የአጠናን ዘዴን አይፈበርክም። በተገኘው የዳግምርምር እውቅ መንገድ ወይም ስነግብር እንጂ የተለየ መንገድን እሚከተል ስርአተትምህርት የለም።
ነገርግን፤ መቶበመቶ ይህ ሩቅ አይደለም። በተጠና መንገድ አዳዲስ መንገድዎችን ማቋቋም እና ኢትዮጵያአዊ ስርአተትምህርት መቅረጽ የእሚቻል ነው። ለምሳሌ፤ በሌላ ጽሑፍ (ስለ የቋንቋ እንግሊዝኛ ትምህርት በተሻለ ፍኖት እንዲሰጥ ማሠብ) እንደ ዳሰስንው፣ እንግሊዝኛን እና ቋንቋን ብቻ አንድ አመት ለምሳሌ አራተኛክፍልን መስጠት የእሚቻል ነው። እስከእማውቀው ይህ ልምድ በሌላ ሀገር የለም። ከስምንተኛ ክፍል በኋላ ደግሞ፤ የተግባር ስራ ትምህርትን ማከል እና አመቱን በመሙሉ የስራ ትምህርት መስጠት የእሚቻል ነው። ወይም አብሮ፤ በአብነት ትምህርትቤት ስነግብር መልክ የተቀረጸ ትምህርትአዊ ስርአትን ማቀነባበር የእሚቻል ነው። በተለይ መዋእለህፃናትን ደግሞ እንደ አንዳንድ ሀገርዎች ለምሳሌ የጨዋታ ብቻ ጊቢ ማድረግ ወይም ስነምግባር ወዘተ. መስጠት እሚቻል ነው። በፍፃሜው ለእዚህ ሀገር የእሚበጅ የእራሱ ለመሆን የቀረበ የትምህርት ስርአት ማበጀት እሚቻል ነው። ግን፤ በእዚህ ደረጃ ለማሰብ እና ለመንቀሳቀስ እሩቅ ቀን ዛሬ ነው። ከዛሬ ይልቅ ወደፊት ቅርብ ነው። ወደፊት ስለትምህርት በአንክሮት ሲታሰብ፤ እነእዚህ ጉዳይዎች መንፈስ ይችል አሉ።

፪ለ፪) ሀገርአብቅል_እውቀት እንደ ኢትዮጵያአዊ የትምህርት ፍልስፍና

ዘመንአዊው እጅግ የተቋቋመ ነው እና፤ የስርአተትምህርት ኢትዮጵያአዊነትን በእዛ ደምድመን፤ ወደ ኢትዮጵያአዊ የትምህርት ፍልስፍና ውይይት እንግባ። ይህም እጅግ እየራቀ ከእምንመለከተው የአንድአንድ ጉዳይዎች (ለምሳሌ ታች እምንመለከተው ሕጽንአዊነት) ውስጥ አንስተንው፣ እምናበለጽገው ወይም እንደ ወጥ ፍልስፍና እምንገነባው ነው። ይህን #ሀገርአብቅል_እውቀት ብለን ስም በማውጣት ተምሮ ከአደገበት “ሀገርበቀል እውቀት” ውይይት አንፃር ከስር እንመልከተው።
ሀገርን ሙሉለሙሉ እሚገነባው እሳቤን በሀገርውስጥ እናብቅል ከአልን ሀገርበቀል እውቀት ድሮ ከአለፈው ጊዜ ጀምሮ መንቀስ እና መለቃቀም አይደለም። ሀገርበቀል እውቀት ትተን ወደፊት ለእሚሆን ሀገርአብቅል እውቀት በእሚል ጽንሰሃሳብ አዲስ መንገድ እናብጅ። ሀገርበቀል እውቀት የአለፈ እና የአለ (የተከማቸ) አካልን አጥኚ ጽንሰሃሳብ ነው። በተለይ በእነ አብድልፈታህ አብደላ “ጥለት ኢትዮጵያ” የተሰኘ የ ኢሳት. ትመ. (Tv) እውቀትን ከእየጎሳው እና እምነቱ መዝዞ የማሳደግ ጥረትዎች ውይይትአቸው አለ። ይህ ጽንሰሃሳብ፣ የአለፈውን ታሪክ አንኳኪ ነው። አንድ የጥናት ክፍል ነው። ኢላማው በኢትዮጵያ በፊት አስቀድሞ የተገኘውን እውቀት ዛሬ ለመገልገል እንዲቻል ነው። በተቃራኒው ሀገርአብቅል እውቀት ግን፣ ከምእራብ የመጣው ስርአተትምህርትን፣ ይህ ሀገርበቀል እውቀትን እና የእሚታወቅ የትምህርት እና ጥናት መንገድዎችን በሙሉ አስተሳስሮ ከሀገር እውነታ ፈላቂ የፍልስፍና እና ርእዮት ፍኖት መገንባት አላሚ ነው። ከእዛ፤ ሀገርን በእራሷ ማጥኟ መንገድ እሚያጠናት ነው። ይህ አሁን ከአለው የማስተማር ስርአትም ሆነ የሀገርበቀል እውቀት እንቅስቃሴዎች የተለየ አካሄድ እና ትልምአግጣጫ() የአለው ነው። እውቀት በተለይ በቀኃሥ. በኢትዮጵያ በዘመንአዊ መንገድ ሲሰጥ፣ በዓድ እንደነበር ይገለጥ ነበር። ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማሪያም እንደተናገሩት ከሆነ፤ “አስኳላ” (ገ.126) ተብሎ በመደበኛ ህዝቡ ጭራሽ በንቀት እስኪጠራ ትምህርት እና ትምህርትስርዓቱ ተጠልቶ ነበር። (በእርግጥ እንደአብራሩት አማርኛ እና ግእዝ ስለአልቻሉ እንጂ የመኳንንት ተማሪዎቹ ይህን የአክል ስለአጠፉ አልነበረም። እንዲያውም፤ ሀገርን የአገለገሉ ትውልድዎች እንደወጡብአቸው (እራስአቸውን ጨምሮ) በእየቦታው ይጠቁሙት አለ። ማለትም የይዘት ሳይሆን የሀገር-መምሰል ጉዳይ አስኳለን የአስፈጠረ ይመስል አለ)። አንድአርግአቸው ጽጌ አንድ ወቅት (2013ዓም.) በ ኢሳት. ጥለት ኢትዮጵያ ዝግጅት በሁለት ክፍል በቀረቡ ጊዜ ይመስለኛል (ወሩን አላስታውሰውም)፣ እርስአቸውም የዘመንአቸው ትምህርት የውጭ ሀገር እውቀት ብቻ እንደ ነበረው እና የሀገር ታሪክ ሳያጠኑ የ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ የቅድስት ሄለና ደሴት ንግግርዎቹን ጨምሮ ሙሉ ታሪኩን ተምረው ይሸመድዱ እንደነበር ገልጠው አለ። ስለእራስአችን እንድናውቅ ስለእዚህ ብንፈትሽ ተቀራራቢ፣ የተሻለ፣ የማይተናነስ፣ ወዘተ. እዚህ የመነጨ የእውቀት አካል እና ታሪክ አለን እና እናተኩርበት በማለት የእሚነሳ “የሀገርበቀል እውቀት” ነጥብ አለ። ከእዚህ ተነስተን ስንደመድመው፤ በሀገርበቀል ጥናት ማለት፣ በእዚህ የነበሩትን እውቀት ነክ ልማድዎች እና ውጤትዎች ከዘመንአዊው ትምህርት ማስታከክ የአልም አለ። በሀገርአብቅል ትልምአግጣጫ ወይም ፍልስፍና ግን እዚህ እንደ ምክረሃሳብ እንዲሆን ማንሳት የእምፈልገው፤ የዘመንአዊ ትምህርት ስርአቱ ሀገርበቀል እና የወግ እውቀት እና ተሞክሮዎችን ቢጨምር እንኳ አያያዙ ተገቢ አይደለም ብሎ እሚጀምር እሳቤ ነው። በመሰረቱ፤ ኢትዮጵያ እምታስተምረው የተሰለቸ አለምአቀፍአዊ ይዘቱ መናኛ እና መነሻ የሆነውን ደረጃ ትምህርት ነው። ጥናትዎች በተለመደ መንገድ ተከውነው መመረቅ እና ስራ ፍለጋን ማመቻቸት የተግባሩ እውነታ ነው። ተመራማሪዎች ደግሞ፤ በአለምአቀፉ ደረጃ በአለምአቀፍ፣ አህጉርአቀፍ፣ ወይም በእነእሱ ደረጃ በሀገር በእሚዘጋጁ የምርምር ምርት ማውጫ ማሳተሚያዎች የእሚያሳትሙ ወይም መሰል ውይይትዎችን የእሚከውኑ ናቸው። ነገርግን፤ ያ ችግር-ተኮር ወይም ችግር-ፈቺ እሚሰኘውን እሳቤ የራቀ ነው። ሀገርበቀል() እውቀት ቢጨመርበትም አያያዙ እስከአልተለወጠ ያው ነው። ስለእዚህ፤ ሀገርአብቅል() መንገድን እንይ። ይህ፤ ፈጽሞ እውቀትን በንፁህ መንገድ ለኢትዮጵያ እንዲሆን አድርጎ የማበጀት መንገድ ነው። ወደ ባህል እና እምነት ተጉዞ ወይም ወደ ውጭ ስርአትዎች እና ንጽጽርዎች ተጉዞ እንደልቡ የእሚማረውን ይማር አለ። ግን ይህ ነበረን ብሎ ከሀገር ልማድ ማከል ወይም ከውጭ አሰራር ወይም ነቢብ ተነስቶ አንድ ነገር ማብራራት እና መተንተን ከእዛ መደምደም አይደለም። በእዚህ መንገድ የእሚገኘው እውቀትን ገና አዲስ አድርጎ ለኢትዮጵያ ማበጀት ነው። ከአዲስ እና በርግጠኝነት ገና ስለአልተከወነ (ቢያንስ ከጅማሮ ትትረት በቀረ) ከአዲስ መከወን ነው። በሀገርበቀል እና ዘመንአዊ መንገዱ ሁሉ፤ የአልተጠናች ኢትዮጵያን ማጥናት እሳቤው ነው። አዳዲስ ቃልዎችን፣ ጽንሰሃሳብዎችን፣ ፍልስፍናዎችን፣ መርኆዎች፣ ወዘተ. ለማጥናት እና መፍጠር እሚያልም ነው። ሀገር እንድትበለጽግ ተጨባጭ በገሀድ የተመሰረተ የውስጥ ጥናት መከወን ነው። ለምሳሌ፤ አዳም ረታ (ደራሲ) እንጀራ በመልኩ፣ ቅርጹ፣ ሽታው፣ ጣዕሙ፣ ስነአሰራሩ እና ደፈና ተፈጥሮው፣ ሲታይ የእራሱ ፍልስፍና አለው ይል አለ ሲሉ ተሰምቶ አለ። ይህ አተያየቱን ሕፅንአዊነት ብሎት፤ ከአንጀራ እውነት ወደ ተቻዩ-ሰፊ-የእውነት አገነዛዘብ ለማጥለል እሚደረግ ትትረት ነው። ቴዎድሮስ ገብሬ፤ ስለ አዳም ረታ የተናገረውን መጥቀስ ለጊዜው ይብቃ። “ከአገረሰባዊ እሴቶች – ከእንጀራ፣ ከጉርሻ፣ ከልቃቂት፣ ከአደይአበባ፣ ከተረት፣ ወዘተ. ቅርፅ እና ጨመቅ በመነጩ ርዕዮቶች አማካይነት፣ ተናጥላዊ (ኢትዮጵያአዊ) ንፅረተዓለምን ለመቅረጽ ወደመሞከር ተሸጋግሯል።”
ለመጠቅለል፤ ይህ ወይም ይህ መሰልን አዲስ ርእዮት ከኢትዮጵያ ተነስቶ መሞከር እና ማብቀል፣ ሀገርበቀል እውቀት አይደለም። ሀገርአብቅል እውቀት ወይም ሀገርአብቅል ጥናት(ዎች) ነው። ብቻ ብሔርአዊ ህልውናን በብሔርአዊ የአስተሳሰብ አዲስ መገንድ ወይም ስልት ዳሳሽ፣ ከእዛ አንድ “ብሔርአዊ” እርእዮት አመንጪ ፍላጎት እና አካል ነው። ወይም ታች እንደ አለው፤ አንድአርግአቸው ጽጌ የቅኔ አኗኗር አንድአች የስነልቦና አለመጥራት ተፅዕኖ በሀበሻ ሳይኖረው አይቀርም ብለው እንደ ገመቱት፤ ይህ መነጽርአቸው ቢብራራ “ቅኔ እና የሀበሻ ስነልቦና” በእሚል ነቁጥ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ብቻ እሚሆን የስነልቦና ፍልስፍናን (የቅኔ ከነስልቦና እውነታ፣ መነሾዎች፣ ግንኙነት እና የተጽዕኖ ትስስርዎች፣ ዉጤትዎች እና ትርፍዎች፣ ወዘተ.) የእሚያጠና እና ወጥ እና ሙሉ አንድ የእውቀት መንገድ አመቻቺ ነው። ወይም በእዚህ ጽሑፍ እንደ አለው፤ አንድ ነቁጥ ከአንድ ቃል ማብቂያ ላይ ከተገኘች፣ አማርኛ ራስቻይ አጽሕሮተቃልዎች ወይም ምህጻረቃል ማሳወቂያ መንገድ ስለሌለው ነቁጡን ቃሉ ፊት የአየ የአጠረ ቃል መሆኑን እንዲሀነዘብ ማድረጊያ መንገድ ይሁን በእሚል ለእዚህ የእሚሆብ ነጥብ ማበጃ ሀገርአብቅል ጥናትዎች እንዲህ፤ የአሉ የኢትዮጵያ በተለይ የድንበሯን ክልል ገሀድ በዋነኛትተ ወይም ብቻ የእሚያጠና (ምንአልባት ከድንበር በሂደት የእሚዘልል ነው – ልክ ሀገርበቀል እውቀትን አብረው እሚያተኩሩት “ለባዊ አካዳሚ”ዎች የአለም እውቀት ከኢትዮጵያ እውነት ብለው አለሙን ከሀበሻ አንፃር ብቻ ለመመልከት የእሚያደርጉት ኢላማ ተከታይ ክፍሉ እና ልህቀቱ ነው – ) እና ከእዛው ተነስቶ የበለጸገ ለእዛው አገልግሎት የእሚቀር ነው። ሀገርበቀል እውቀት ግን አለምአቀፍ ነው። የኢትዮጵያ ገዳ ስርአት ወይም ግእዝ የከተበአቸው ጥበብዎች ለአለም የእሚሆኑ ናቸው። ሀገርአብቅል ጥናትዎች ግን እምብዛም ለሌላው ሀገር አይሆንም። ስለጤፍ፣ ቅኔ፣ የኢትዮጵያ መልክአምድር ከ ኢትዮጵያአዊ ስነልቦና፣ የኢትዮጵያ ሰማይ (ለምሳሌ ላሊበላ እና የላሊበላ ሰማይ እንደ ቺሊ እና የቺሊ ሰማይ የተለየ ስነፈለክአዊ እውነት አሉአቸው እንደ እሚባለው) ከኢትዮጵያ አኗኗር እና ተፈጥሮ ተፅዕኖ፤ የኢትዮጵያ አመትአዊ ወቅትዎች ከአስተዳደግ ስነልቦና፤ በስነምጣኔ ለምሳሌ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በቀለ (ኢሳት. ኢኮኖሚያችን እይት() ላይ) ለኢዜማ. በ2013ዓም. ዘግዪ ምርጫ ከእጩነትአቸው ቀድሞ እንደ ተናግገሩት 40እጅ የኢትዮጵያ ወጣት አልሚ በአለመመገብ የተነሳ በመቀንጨር እውነት አምራች ዜጋ አይሆንም እንደአሉት፤ ወይም ቻይናዎች ተሳደቡት እንደ ተባለው የአመጋገብ እና ሽሮአዊ የስነልቦና እና ስነአካልአዊ() ግንኙነት፣ ወዘተ. በተገኘው ስነግብር (ለምሳሌ ሀገርበቀል እውቀት እና ስርአትዎችን ከዘመነው በመደባለቅ ኢትዮጵያአዊ ትምህርት እና ዳግምርምር ስነግብር (Ethiopian educational and research methodology) በእሚል በማበልፀግ ከተፈለገ በአውደብጁ ማጥኛ መንገድ፤ የሀገር ከባቢ እውነት ቢጠና ለሌላው አለም በአብይ ደረጃ ይዘቱ ይህን የአክል በቀጥታ አይረባውም። የ መስፍን ጎንለጎን የስነልቦና ልብወለድ፤ 2012ዓም. (በጽሑፉ ጸሐፊ) ውስጡ ይህ ሃሳብ እና አብነት የአክል አለ)። ዘመንአዊው ስርአተትምህርት ለኢትዮጵያ ጥቂት ክፍሉ እንዲህ ዋጋው የአነሰ ይዘት ሰጪ ነው። ይበልጥ የስነግብር() እንጂ ይዘቱ የራቀ ይሆን እና በሀበሻ ህዝብ ህይወት ማሻሻል ቀጥተኛ ተተግባሪነት የራቀ ትግበራን ይይዝ አለ።
ብዙ ኅዋአዊከተማዎች() በኢትዮጵያ አሉ። ነገርግን፣ ስለ ተናቀው የድህነት ልማድ እና ጠቢው፣ ስለህዝቡ ከቶ አያጠኑም ማለት እሚቻል ነው። የተለመደ የመመረቂያ ጽሑፍዎችን ማስጻፍ እና አአዩ. እንኳ አደረገ እንደ ተባለው ቦታ ይዞ ክፍሉ ከሞላ ጥናት ጽሑፉም የእሚወረወር ነው። ያ፣ እንደ ግዴታ ለመመረቅ ብቻ የግድ የእሚሰራ ጥናት እንኳ ለሀገር እሚደግፍ አይደለም። የስርአተትምህርት እውቀቱን መፈተኛ እንጂ የሰመጠ የሀገር ጉዳይ ጥናት አይደለም። ለምሳሌ፣ ስለ ህዝቡ ድህነት፣ የፖለቲካ ጉዳይ፣ ማንኛውም እለትከለት ጥያቄ፣ ወዘተ. ምርምርዎች አይደረጉም ማለት ተቻይ ነው። ለምሳሌ ህጻን እና ሴትዎችን ወደ እውነትአቸው ሰምጦ በእራስአቸው አለም ስለእነእርሱ አኗኗር ለመገንዘብ ማጥናት የለም። ሁኔታዎችአቸው እንዴት ይሻሻል? ስለ ማጥባት ልማድአቸው ምምን ይታወቅ አለ? ከአጥኚዎች ይልቅ፤ ተራ የፖለቲካ ትእዛዝ እና መንግስትአዊ መዋቅር ወይም ስራ የበለጠ የእሚያውቅ ነው። መንግስት ከየት አምጥቶ በሚኒስቴር መስሪያቤትዎቹ የእሚያስተናግድ ሆነ? የሴት እና ህፃናት ጉዳይዎችን በአለምአቀፍ እውቀቱ እና ስርኣቱ እንጂ በሀገር ጥናት ስለእማይከውነው ነው። ከተቋምዎቹ የተሻለ የአወቀ የእሚመስለው ስለእዛ እንጂ እራሱም አጥንቶ አይመስልም። እንጂ ሀገርን በሠመጠ መጠን ለመምራት ከተቋምዎቹ ህዝቡን የተመለከቱ ነገርዎች ምርምር አይከወንብአቸውም። ትልልቅ እሚወጡ ጽሑፍዎችም ለአህጉር እና አለምአቀፍ ውይይት እንጂ ለሀገር ፍጆታ እሚውሉት ጥቂት ናቸው። ለምሳሌ በስነልቦና እና ፍልስፍና ብዙ ጥናት ቢከወንም ሀገርበቀል ፍልስፍና እና ስነልቦና ጥናትዎች ከቶ አላደጉም። ግን ብዙ ለሀበሻ በምርምር ተጠንቶ ከበለጸገ በፍልስፍና እና ዝርዝር እውቀትዎች ተመንዝሮ መራባት የእሚገባው የእየጎሳው ምርጥ ልማድዎችቻ አሉ። ለምሳሌ በጉራጌ ውስጥ የአለው የልጅዎች አስተዳደግ በስነልቦና የረቀቀ ደቂቅ ስነልቦና() ጉዳይዎች አሉት። ልጅዎች እራስበመቻል እሚያድጉበት መንገድ ጃን ፖል ሳርተ የሰበከው ሀገር ይመስል እንደ ፈረንሳይ አስተዳደግ ይመስል አለ፤ በደፈናው። ከልጅነት በመተው፣ በመምረጥ፣ በአለመታቀፍ፣ አለመጨነቅ እና እራስን በማስተዳደር እራስአቸውን ነጥለው በሃላፊነት መውሰድ ህላዌአዊ ነፃነት() ወይም የህልውና ጥገኝነት ሳይይዝአቸው – በግል-ቻይ() እና ራስ-ተደጋፊ() ስብእና – የአድግ አሉ። በቀላሉ ወደ ስራ እና እራስ ማስተዳደር የመግባት ልምምዱ ምንአልባት ከእዚህ ከማጥባት የእሚጀምር ይሆን አለ። የህላዌ ፍልስፍና በእዚህ ማህበረሰብእ ትልቅ እውቀት፣ ተግባር እና ጥበብ የአለበት ይመስል አለ። ይህንን መሰል ጉዳይዎች አልተጠኑም። እንደ ጅማ ዩንቨ. “በማህበረሰቡ ነን” እሚሉ መፈክርዎች እና መሰል ህልምዎች በእየተቋምዎቹ ቢገኙም ለከባቢው ግን ብዙም ንጹህ አካባቢያዊነትን አይሰጡም። ሀገርአብቅል ቀርቶ ሀገርበቀል እንኳ አይደሉም። የባህል ህክምና ትምህርትቤት ተነጥሎ ከአለአቸው? የሀገር ጎሳዎች፣ ልማድ፣ መንፈስአዊ፣ ወዘተ. ህክምና ጥበብዎች እና ታሪክዎች አጥኚ ክፍለ ትምህርት ከአሉአቸው? ወይም የንግድ እንቅስቃሴ ጥበብ ጥናትዎች MBA ወዘተ. የጉራጌ ነጋዴዎችን አነጋገድ ጥበብዎች አጥንተው ከአስተማሩት እንጃ? ወይም የእረኝነት ጥበብዎችን እና ብልኀትዎችን፣ እውቀት እና ተሞክሮዎችን ከአጠኑ እና ከአወቁት እንጃ? ወይም አረቄን እና ዘይትን በእንስራ የእሚወጡበትን መንገድዎች ከአጠኑ እና ከአሻሻሉ እንጃ። ወይም ለምሳሌ ለሀገር እውነታ የእሚሆኑ ገሀድዎችን አጥንተው የሀገርአብቅል ጽንሰሃሳብዎችን እና ነቢብዎችን ለምሳሌ “ሀገርአብቅል ትምህርት” ብለው አይነት እሚሰበስቡ ከሆነ እንጃ። ወይም በሀገርአብቅል ጉዳይዎች ዙሪያ በእየደራሲው፣ ጋዜጠኛው፣ ተመራማሪው፣ ወዘተ. የእሚሞከሩ ጉዳይዎችን ሰባስበው፣ አንድ የሀገርአብቅል እና ሀገርበቀል ስርአተ ትምህርት ለማበጀት ወደ አንንድ ነቢብ ለመድረስ እሚታትሩ ከሆነ እንጃ? ወይም ከፍተኛ የሀገር ጉዳይ ለመለወጥ እሚችል መንገድዎች የአሉት ለምሳሌ በስነምጣኔ ነባር ወይም ሀገርበቀል እውነታን ተንተርሶ መንግስትን እና ህዝብን ለመግፋት ለናሙና የአክል ስለሸክላ ጥበብ፣ እድልዎቸ ችግርዎችአቸው እና ታሪክአቸው፣ ከእየማህበረሰብ መሀከል የእሚወጡ የምርምር ተቋም ውይይትዎች የሉም። ስለሽመና፣ ጠላ፣ አረቄ እና እርሻ፣ ወዘተ. በአልተቋረጠ እና ዋና በሆነ መንገድ የማጥናቱ ስራ ለተቋምዎች የተሰጠ ተልእኮ እና ፍፃሜ አይደለም። ጠላ እና አረቄን ወይም ነጠላን ግን የእማይጠቀም እምብዛም በአለመኖሩ፣ የተመራማሪ ተቋምዎች ፍፃሜ ምኑን በማህበረሰብእ ውስጥ ነው የአስብለው አለ? ስለጠጅ አይነትዎች የተብላላ ቋንቋ እና ፍልስፍና መድቦ የእሚዘውር ተቋም አይታይም። በአለምአቀፍ ጥናት፣ መረጃ እና እርዳታ እንጂ ስለህዝቡ የጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት ወይም ሌላ መሰል ጉዳይዎችም መረጃ አይታይም። በእነእዚህ ጉዳይዎች ሁሉ፣ የህይወት እርምጃ አባል ናቸው እና መወራት ከአለበት የእሚነፍሰው መረጃ የማንም የተናጋሪው አመለካከት ይሆን አለ እንጂ የእውቀት እና ምርምር ስጦታ መረጃ እና ወሬ የመሆን እድል የለውም።

፫) መደምደሚያ

ለኢትዮጵያ ዘመንአዊ ስርአተትምህርት ተበጅቶላት በእማያስመነድግ መንገድ እየተገለገለችው አለች። መገለጫው፤ አለምአቀፍ ውድድርዎች ላይ የከሸፈ፣ ስራፈጣሪነት ላይ የወረደ፣ ማህበረሰብእአዊ ለውጥ ላይ የእማይበረታ አገልግሎትን አቅራቢ ፍፃሜ ብቻ ነው የአገኘው። ይህ በጥራት ዘመንአዊውን ስርአት እንደአለው አሁን ቢከውኑት እሚሻሻል ነው። ነገርግን ተፈላጊ ፍፃሜን አያስመለክተንም። አማራጩ ሀገርአዊ ስርአተትምህርተን በአውደብጁነት ማዘጋጀት ከአልሆነ የትምህርቱን አሁን የእሚገኝ ፍልስፍና እእና ትልምአግጣጫ እንኳ ኢትዮጵያአዊ ማድረግ ነው። ያም፤ ኢትዮጵያን ከችግርዎቿ ተነስቶ እሚገነዘብ መሆኑን መስፍን ወልደማርያም (ፕሮፍ.) ገልጠውት አለ። በመቀጠል ግን፤ ከችግርም ጀርባ ልህቀት እና ውድድር አለ። ለእዛ እሚያስብ ችግርን አብሮ ይወቅጠው አለ፤ ከኑግ የተገኘ ሠሊጥ ነው እና። ስለእዚህ፤ ትምህርት በሀገርን በሀገሩ አመለካከትአዊ መንገድዎች ማጥኛ ስርአት በማበጀት ወደፊቷን ማገዝ እና መመስረት የእሚቻል ነው። ይህ አርትዖት የአልተከወነበት አጭር አጽሕሮተጽንሰሃሳብ ገላጭ ጽሑፍ ነው። በመመለስ በአርትእ ካልዕ ለማጥራት እሞክር አለሁ። ለጊዜው ውይይቱን ለመጎልጎል እነሆ መነሻነቱ ይበቃ አለ፨
—————————————————————————————————————-

፬) የቅንፍ ቃልዎች

 1. ቁምፊ = Font
 2. ብጁዐውድ = Customized
 3. ዳግምርምር = Research
 4. ስነግብር = Methodology
 5. ግዝግቤት = Importation
 6. አስርታት = Decades
 7. ቀኃሥ. = ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
 8. ለአደባባይ ትምህርት = Public Education
 9. ህዝብአዊ ግንኙነት = Public Attachment
 10. ዳግቅኝት = Revision
 11. ክርክርቴ = Argument
 12. ሰበበሃሳብ = Premesiss
 13. የነጠረ = Quantitative/quantifiable
 14. መደዴዎች = Mediocre
 15. ዘረፍጥረት = Species
 16. አስተኔሰብእ = Humankind
 17. ልማድአዊ ተሞክሮዎች = Traditional Practices
 18. ስነውሳኔ = Politics
 19. ስነሂደት = Procedure
 20. ገሀድተኮር = Objective
 21. ትልምአግጣጫ = Policy
 22. ሀገርበቀል = Nation-grown
 23. ሀገርአብቅል = Grow-nationl
 24. እይት = Show
 25. ስነአካልአዊ = Physiological
 26. ስነግብር = Methodology
 27. ኅዋአዊከተማ = University
 28. ደቂቅ ስነልቦና = Child Psychology
 29. ህላዌአዌ ነፃነት = Existential Freedom
 30. ግልቻይ = Autonomous
 31. እራስተደጋፊ = Self-reliance

———————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————————-

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s