Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ስለ አአምርኩሎን በኢትዮጵያ ማከም፡ የ ሀገርአብቅል ጥናትዎች እና ስልጣኔ ጉዳይዎች

About the challenges of know it all social information exchange world in Ethiopia with basic ways out.

በ ተአዶ. (PDF) ይህ አጭር ጽሑፍን ይጋሩ። ጉድራይቭ ወይም አካደሚያ ወይም አርካይቭ

—-

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 20th 2021

በተለይ በአለፉት ሁለት አስርታት (decades) ሁሉአዋቂነት ወይም አእምርኩሎ (I know it all)፣ በኢትዮጵያ እጅግ የከፋ በሽታ ሆኖ አለ። በቀላል መገናኛ መንገድዎች፣ ብዙ ጉዳይዎችን ብዙዎች በተሳታፊነት ሲካፈሉበት የተስተካከለ እና የጠራ አተያይ ይጎድል አለ። የተዛባ አተያይዎች፣ ስህተት መረጃዎች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጉዳት የአደርስ አሉ። በመሰረቱ፣ የነቃ የማህበረሰብእ ተሳትፎ ትልቁ ዋጋ የአለው ጉዳይ ነው። አስፈላጊም ነው። ነገርግን ዋናዋና ጉዳይዎችን እና ትክክለኛ መረጃ መምራት የአስፈልግ አለ። አአምርኩሎ በአብይ ጉዳይዎች ላይ የእሚመሩ ተገቢ ዜጋዎች በአለመኖርአቸው ክፍተቱን ማንም መሳተፍ የፈለገ ብቻ በደረሰው፣ በአለው፣ በአወቀው መጠን አዋጥቶ የእሚዘውረው የመረጃ ልውውጥ ነው።

ለምን አእምርኩሎ በዛ?

1) በኢትዮጵያ መሀከልሀገር ወጥ የአኗኗር ባህል የለም። የማክበር እና አዋቂዎችን የመስማት ልማድ ገጠር የቀረ ነው። ይህ የጠራ ማህበረሰብእአዊ ውይይትዎችን ለመከወን አንዱ መሰናክል ነው። ለምሳሌ፤ በአንዳንድ ብሔረሰብእዎች፣ መረጃዎች በጠራ መንገድ ተላልፈው ማህበረሰብእ አባል በተሳካ መንገድ ነገርዎችን ይከውንበት አለ። የወልደአማኑኤል ዱባለ ታሪክ ከ ቀኃሥ. ጋር የእሚወራውን እወነት ከያዘ መረጃዎችን በገጠር በተሻለ መንገድ እንደእሚዘወሩ መረዳት የእሚቻል ነው። በገጠር ኢትዮጵያ መረጃዎች በአዋቂዎች እጅ እና ቁጥጥር አሉ። ያ የተሻለ መንገድ ሲሆን፣ ታናናሽዎች ለቁጥጥር እማያስቸግሩ መሆንአቸው ሌላው ተጽዕኖ ነው። ባህሉ ሲደማመር፣ የከበደ የመረጃ አገልግሎት ስርዓትን ሊያገኝ ይችል ይሆን አለ፤ ለአጥኚዎቹ ይህ እውነት እንደሆነ ግልጥ ነው። በመሀከልሀገር ግን፤ ከተሜነት ስለተጀመረ፣ የተለያዩ አመለካከትዎች በትክክል አልተገነቡም። ስለእዚህ፣ የመረጃ ቅብብሎሽ እና ማህበረሰብእአዊ ተሳትፎ በባህል የእሚገኘውን የማእከለ-ትውልድዎች ግንኙነትዎችን አላጠሩትም። የተማሩ አሉ፤ ተምረው ብዙም የእማይገፉ አሉ። የበሰሉ የተማሩ አሉ። ግድየእሚልአቸው የአልተማሩ አሉ። ተምሮ ግድ የእማይልአቸው አሉ። ለወጥ የንግግር ባህል መታደል አልተቻለም እና ማንም ምንም ከልካይ ያለበት አይመስልም። የተማሩ እና አዋቂዎችን አድምጦ ማክበር እምብዛም የለም። የተማሩ እና ትልልቅዎች ሲጀመር ግን ለአዋቂዎች መነጋገሪያ መድረክ የለም። ለምሳሌ የሀገርሽማግሌ የተሰኘ አንድ አዋቂ አንድአች ነገር በመገናኛብዙሃን ቢናገር ሌላው ሰምቶ በራሱ ይወያይ አለ እንጂ ይፋ ወይም ከፊል-ይፋ ወይም ጭራሽ ኢይፋአዊ አቻ እውቀት እና ብልኀት የአለው ግለሰብእ መልስ የእሚሰጥበት ልምምድ እና አውድ የለም። በእየፊናው መነጋገር እና በአልሰለጠኑ ጋዜጠኛዎች አንድአች ነገር ለመመለስ የመጋበዝ ጉዳይ ቢገጥም እንጂ ወጥ አቀራረብ አለም። ቀጣይነት የአለው ጅማሮም ስለእማይኖር የንግግር ባህልን በአዋቂዎች እየመሩ ለማስኬድ እድል አይፈጠርም። ገና በአልተመሰረተ እና በአላደገ ሀገር፣ ምንም ወጥ የክርክር፣ የፉክክር መድረክ፣ የእውቀት መለዋወጫ አውድ፣ እና የጥበብ መከፋፈያ መንገድ አገኝም። ይህ ሆኖ ሳለ፤ ወጣትዎችን በቅርበት እየተቆጣጠረ እሚያሳድግ ሀገርአዊ ልማድ በመሀከልሀገር የለም። አዋቂዎች በእድሜ እንጂ በዘመኑ እውቀት እና ጥበብ አይበልጡም። ትውልደ ወጣቱ እና ታዳጊው አባትዎቹ የአልተማሩትን እሚማር እና እሚሰራ በመሆኑ፣ ተሞክሮም ሆነ ብልኀትን ከወላጅዎች እና አዋቂዎችም አይረከብም። በእራሱ ለስራ ፍለጋ የእሚናውዝ ሃይባይ የሌለው ባይተዋር ነው። ስለእዚህ የአሻውን ለመናገር እና መረጃዎችን ለማሾር የበላይ የለበትም። የአዋቂ ወይም ጎልማሳ ዜጋዎች ተሳትፎ የነተበ በመሆኑ፣ የተዥጎደጎደው ፈርቀዳጅ የሌለበት ተቆጣጣሪም የእማይሰርጽበት የንግግር እና ልውውጥ ባህል ነው። ወጣትዎች መምራት ባለመቻሉ እና ወጣትዎቹ ግን ከድህነት እና ግድየለሽነት የተነሳ የእሚያውቁት ነገር እምብዛም በመሆኑ የእሚያጡት ባለመኖሩ የአሻአቸውን ለመዘወር እና በመረጃው አለም አዋቂነትአቸውን ለማስደመጥ ምንም አይገድብአቸውም። የሠለጠነ እና የተወሳሰበ አኗኗር ስለአልተጀመረ፣ ከተሜነቱ ኮሳሳ ውጥን ስለሆነ፣ አብሮት ግን ገደቡ የነተበ የልውውጥ ስርአት ስለአለ፣ ለትውልዱ ጉዳት የሆነ ኑባሬ ተቋቁሞ አለ። በመሀከልሀገር የሰለጠነ አኗኗር እምብዛም አይገመትም። ይህ ማለት የመረጃ እና ወሬ (ዜና) ልውውጥ እና ተሳትፎ አብሮ ደካማ ነው ማለት ነው።
2) ግን አዋቂን ቢሰሙት የለውም የእሚሰሙት። ዘመኑ ተለውጦ አለ። እውቀት በዝቶ አለ። አዋቂዎች አዛውንትዎች ገብተው በፈጠነው አለም ታጋይ ከአልሆኑ፣ ምንአቸው ይሰማ አለ? እድሜ ብቻ ለዛሬ ቀልቃላ-ስልጡን (hyper-civilized) አለም ዋጋዋ ቀንሶ አለ። የአዋቂዎች አለም ከወጣቱ አልተለየም። አዋቂዎች ያው የተለመደ ቆሻሻ ኑሮ ነዋሪ ናቸው። ማንም ወደእነእርሱ አይመለከትም። ማንም ቢገምት፣ ቢያወራ አዋቂዎች እኛ እናቅ አለን፣ በእድሜህ እኩል እውቀት አለህ አይሉትም። እድሜአቸው ቁጥር እና መናኛ ወግ እንጂ የተከማቸ እውቀት የለውም። ማንም ልናገር ቢል ከባድ አይሆንም። የተሻለ አዋቂ የለም። ትልልቅ መፍራትን እንኳ የእሚቀንስ አኗኗር በመሥረጹ ፍሬነገር ከጠፋ እማ ምን የአክል ይቸግር። ወሬም ለጨዋታ እና ጉንጭ ማልፋት የአክል (ለመዝናናት) እንጂ ለትርፍ አይከወንም። ምንም የጠራ እና የተመረመረ ወሬ ቀረበ ወይም አልቀረበም የከበደ ዋጋ አይጣልበትም። እሚያተርፍ ወሬ ሳይሆን የጊዜማሳለፊያ አይነቱ መደበሪያ ወይም መሰል ጭንቅ-ንፁህ አያያዝ የአለበት መንገድ ተከትሎ መነጋገር የተለመደ ልማድ ነው። ያ ልማድ ወደ ማህበረሰብእ ወሬ ልውውጡም ቀርቦ አለ። እንደተባለው የአንድአርግአቸው ጽጌ ቅኔ አኗኗር እየጎዳን ነው አተያየትም፣ ይህ አንድ መገለጫው ነው። የጠራውን እና ቁምነገሩን ከመውሰድ፣ በቸልታ እዚህም እዛም ለመሳቅ የአክል መነጋገሩ ተለምዶ፣ ወደ ይፋ ልውውጡም ይህ እየገነፈለ የእሚመጣ ልማድ እየሆነ ነው።

መፍትሔዎች በአብይ አገላለጥ ሁለት ናቸው።

1) ብሔርአዊ ጥናትዎች ወይም #ሀገርአብቅል_ጥናትዎች

ታላቅ የአኗኗር በተለይ እዚህ የመረጃ እውነት ለውጥ የአስፈልግ አለ። የስርዓት ለውጥ የአሻ አለ። በተሳሳተ መንገድ ሀገርበቀል እውቀት ይጠና እሚሉ ሰዎች አሉ። ግን ያ ኢትዮጵያን አያድንም። ሀገርበቀል እውቀት የእሚሉትም የእየጉራንጉሩ እና ጎሳው ልማድ፣ ወግ፣ ወዘተ. እና የእምነት እውቀትን ነው። እነእዚህ ለብቻአቸው የእሚጠኑ አንድ ክፍል እንጂ ሁሉን ስልጣኔ መስራች አይደሉም። መጠናት አሉብአቸው። አስተዋጽዖ ማበርከት አሉብአቸው። ግን ሀገርን ሙሉለሙሉ አይገነቡም። ሀገርን ሙሉለሙሉ እሚገነባውን እሳቤ በሀገርውስጥ እናብቅል ከአልን ሀገርበቀል እውቀት ድሮ ከአለፈው ጊዜ ጀምሮ መንቀስ እና መለቃቀም አይደለም። ሀገርበቀል እውቀት ትተን ወደፊት ለእሚሆን ሀገርአብቅል እውቀት በእሚል ጽንሰሃሳብ አዲስ መንገድ እናብጅ። ሀገርበቀል እውቀት የአለፈ እና የአለ (የተከማቸ) አካልን አጥኚ ጽንሰሃሳብ ነው። በተለይ በእነ አብድልፈታህ አብደላ “ጥለት ኢትዮጵያ” የተሰኘ የ ኢሳት. ትመ. (Tv) እውቀትን ከእየጎሳው እና እምነቱ መዝዞ የማሳደግ ጥረትዎች ውይይትአቸው አለ። ይህ ጽንሰሃሳብ፣ የአለፈውን ታሪክ አንኳኪ ነው። አንድ የጥናት ክፍል ነው። ኢላማው በኢትዮጵያ በፊት አስቀድሞ የተገኘውን እውቀት ዛሬ ለመገልገል እንዲቻል ነው። በተቃራኒው ሀገርአብቅል እውቀት ግን፣ ከምእራብ የመጣው ስርአተትምህርትን፣ ይህ ሀገርበቀል እውቀትን እና የእሚታወቅ የትምህርት እና ጥናት መንገድዎችን በሙሉ አስተሳስሮ ከሀገር እውነታ ፈላቂ የፍልስፍና እና ርእዮት ፍኖት መገንባት አላሚ ነው። ከእዛ፤ ሀገርን በእራሷ ማጥኟ መንገድ እሚያጠናት ነው። ይህ አሁን ከአለው የማስተማር ስርአትም ሆነ የሀገርበቀል እውቀት እንቅስቃሴዎች የተለየ አካሄድ እና ትልምአግጣጫ (policy) የአለው ነው። እውቀት በተለይ በቀኃሥ. በኢትዮጵያ በዘመንአዊ መንገድ ሲሰጥ፣ በዓድ እንደነበር ይገለጥ ነበር። ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማሪያም እንደተናገሩት ከሆነ፤ “አስኳላ” (ገ.126) ተብሎ በመደበኛ ህዝቡ ጭራሽ በንቀት እስኪጠራ ትምህርት እና ትምህርትስርዓቱ ተጠልቶ ነበር። (በእርግጥ እንደአብራሩት አማርኛ እና ግእዝ ስለአልቻሉ እንጂ የመኳንንት ተማሪዎቹ ይህን የአክል ስለአጠፉ አልነበረም። እንዲያውም፤ ሀገርን የአገለገሉ ትውልድዎች እንደወጡብአቸው (እራስአቸውን ጨምሮ) በእየቦታው ይጠቁሙት አለ። ማለትም የይዘት ሳይሆን የሀገር-መምሰል ጉዳይ አስኳለን የአስፈጠረ ይመስል አለ)። አንድአርግአቸው ጽጌ አንድ ወቅት (2013ዓም.) በ ኢሳት. ጥለት ኢትዮጵያ ዝግጅት በሁለት ክፍል በቀረቡ ጊዜ ይመስለኛል (ወሩን አላስታውሰውም)፣ እርስአቸውም የዘመንአቸው ትምህርት የውጭ ሀገር እውቀት ብቻ እንደ ነበረው እና የሀገር ታሪክ ሳያጠኑ የ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ የቅድስት ሄለና ደሴት ንግግርዎቹን ጨምሮ ሙሉ ታሪኩን ተምረው ይሸመድዱ እንደነበር ገልጠው አለ። ስለእራስአችን እንድናውቅ ስለእዚህ ብንፈትሽ ተቀራራቢ፣ የተሻለ፣ የማይተናነስ፣ ወዘተ. እዚህ የመነጨ የእውቀት አካል እና ታሪክ አለን እና እናተኩርበት በማለት የእሚነሳ “የሀገርበቀል እውቀት” ነጥብ አለ። ከእዚህ ተነስተን ስንደመድመው፤ በሀገርበቀል ጥናት ማለት፣ በእዚህ የነበሩትን እውቀት ነክ ልማድዎች እና ውጤትዎች ከዘመንአዊው ትምህርት ማስታከክ የአልም አለ። በሀገርአብቅል ትልምአግጣጫ (policy) ወይም ፍልስፍና ግን እዚህ እንደ ምክረሃሳብ እንዲሆን ማንሳት የእምፈልገው፤ የዘመንአዊ ትምህርት ስርአቱ ሀገርበቀል እና የወግ እውቀት እና ተሞክሮዎችን ቢጨምር እንኳ አያያዙ ተገቢ አይደለም ብሎ እሚጀምር እሳቤ ነው። በመሰረቱ፤ ኢትዮጵያ እምታስተምረው የተሰለቸ አለምአቀፍአዊ ይዘቱ መናኛ እና መነሻ የሆነውን ደረጃ ትምህርት ነው። ጥናትዎች በተለመደ መንገድ ተከውነው መመረቅ እና ስራ ፍለጋን ማመቻቸት የተግባሩ እውነታ ነው። ተመራማሪዎች ደግሞ፤ በአለምአቀፉ ደረጃ በአለምአቀፍ፣ አህጉርአቀፍ፣ ወይም በእነእሱ ደረጃ በሀገር በእሚዘጋጁ የምርምር ምርት ማውጫ ማሳተሚያዎች የእሚያሳትሙ ወይም መሰል ውይይትዎችን የእሚከውኑ ናቸው። ነገርግን፤ ያ ችግር-ተኮር ወይም ችግር-ፈቺ እሚሰኘውን እሳቤ የራቀ ነው። ሀገርበቀል (nation-grown) እውቀት ቢጨመርበትም አያያዙ እስከአልተለወጠ ያው ነው። ስለእዚህ፤ ሀገርአብቅል (grow-nation) መንገድን እንይ። ይህ፤ ፈጽሞ እውቀትን በንፁህ መንገድ ለኢትዮጵያ እንዲሆን አድርጎ የማበጀት መንገድ ነው። ወደ ባህል እና እምነት ተጉዞ ወይም ወደ ውጭ ስርአትዎች እና ንጽጽርዎች ተጉዞ እንደልቡ የእሚማረውን ይማር አለ። ግን ይህ ነበረን ብሎ ከሀገር ልማድ ማከል ወይም ከውጭ አሰራር ወይም ነቢብ ተነስቶ አንድ ነገር ማብራራት እና መተንተን ከእዛ መደምደም አይደለም። በእዚህ መንገድ የእሚገኘው እውቀትን ገና አዲስ አድርጎ ለኢትዮጵያ ማበጀት ነው። ከአዲስ እና በርግጠኝነት ገና ስለአልተከወነ (ቢያንስ ከጅማሮ ትትረት በቀረ) ከአዲስ መከወን ነው። በሀገርበቀል እና ዘመንአዊ መንገዱ ሁሉ፤ የአልተጠናች ኢትዮጵያን ማጥናት እሳቤው ነው። አዳዲስ ቃልዎችን፣ ጽንሰሃሳብዎችን፣ ፍልስፍናዎችን፣ መርኆዎች፣ ወዘተ. ለማጥናት እና መፍጠር እሚያልም ነው። ሀገር እንድትበለጽግ ተጨባጭ በገሀድ የተመሰረተ የውስጥ ጥናት መከወን ነው። ለምሳሌ፤ አዳም ረታ (ደራሲ) እንጀራ በመልኩ፣ ቅርጹ፣ ሽታው፣ ጣዕሙ፣ ስነአሰራሩ እና ደፈና ተፈጥሮው፣ ሲታይ የእራሱ ፍልስፍና አለው ይል አለ ሲሉ ተሰምቶ አለ። ይህ አተያየቱን ሕፅንአዊነት ብሎት፤ ከአንጀራ እውነት ወደ ተቻዩ-ሰፊ-የእውነት አገነዛዘብ ለማጥለል እሚደረግ ትትረት ነው። ቴዎድሮስ ገብሬ፤ ስለ አዳም ረታ የተናገረውን መጥቀስ ለጊዜው ይብቃ። “ከአገረሰባዊ እሴቶች – ከእንጀራ፣ ከጉርሻ፣ ከልቃቂት፣ ከአደይአበባ፣ ከተረት፣ ወዘተ. ቅርፅ እና ጨመቅ በመነጩ ርዕዮቶች አማካይነት፣ ተናጥላዊ (ኢትዮጵያአዊ) ንፅረተዓለምን ለመቅረጽ ወደመሞከር ተሸጋግሯል።”
ለመጠቅለል፤ ይህ ወይም ይህ መሰልን አዲስ ርእዮት ከኢትዮጵያ ተነስቶ መሞከር እና ማብቀል፣ ሀገርበቀል እውቀት አይደለም። ሀገርአብቅል እውቀት ወይም ሀገርአብቅል ጥናት(ዎች) ነው። ብቻ ብሔርአዊ ህልውናን በብሔርአዊ የአስተሳሰብ አዲስ መገንድ ወይም ስልት ዳሳሽ፣ ከእዛ አንድ “ብሔርአዊ” እርእዮት አመንጪ ፍላጎት እና አካል ነው። ወይም ታች እንደ አለው፤ አንድአርግአቸው ጽጌ የቅኔ አኗኗር አንድአች የስነልቦና አለመጥራት ተፅዕኖ በሀበሻ ሳይኖረው አይቀርም ብለው እንደ ገመቱት፤ ይህ መነጽርአቸው ቢብራራ “ቅኔ እና የሀበሻ ስነልቦና” በእሚል ነቁጥ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ብቻ እሚሆን የስነልቦና ፍልስፍናን (የቅኔ ከነስልቦና እውነታ፣ መነሾዎች፣ ግንኙነት እና የተጽዕኖ ትስስርዎች፣ ዉጤትዎች እና ትርፍዎች፣ ወዘተ.) የእሚያጠና እና ወጥ እና ሙሉ አንድ የእውቀት መንገድ አመቻቺ ነው። ወይም በእዚህ ጽሑፍ እንደ አለው፤ አንድ ነቁጥ (point) ከአንድ ቃል ማብቂያ ላይ ከተገኘች፣ አማርኛ ራስቻይ አጽሕሮተቃልዎች ወይም ምህጻረቃል ማሳወቂያ መንገድ ስለሌለው ነቁጡን ቃሉ ፊት የአየ የአጠረ ቃል መሆኑን እንዲሀነዘብ ማድረጊያ መንገድ ይሁን በእሚል ለእዚህ የእሚሆብ ነጥብ ማበጃ ሀገርአብቅል ጥናትዎች (grow-nation studies) እንዲህ፤ የአሉ የኢትዮጵያ በተለይ የድንበሯን ክልል ገሀድ በዋነኛትተ ወይም ብቻ የእሚያጠና (ምንአልባት ከድንበር በሂደት የእሚዘልል ነው – ልክ ሀገርበቀል እውቀትን አብረው እሚያተኩሩት “ለባዊ አካዳሚ”ዎች የአለም እውቀት ከኢትዮጵያ እውነት ብለው አለሙን ከሀበሻ አንፃር ብቻ ለመመልከት የእሚያደርጉት ኢላማ ተከታይ ክፍሉ እና ልህቀቱ ነው – ) እና ከእዛው ተነስቶ የበለጸገ ለእዛው አገልግሎት የእሚቀር ነው። ሀገርበቀል እውቀት ግን አለምአቀፍ ነው። የኢትዮጵያ ገዳ ስርአት ወይም ግእዝ የከተበአቸው ጥበብዎች ለአለም የእሚሆኑ ናቸው። ሀገርአብቅል ጥናትዎች ግን እምብዛም ለሌላው ሀገር አይሆንም። ስለጤፍ፣ ቅኔ፣ የኢትዮጵያ መልክአምድር ከ ኢትዮጵያአዊ ስነልቦና፣ የኢትዮጵያ ሰማይ (ለምሳሌ ላሊበላ እና የላሊበላ ሰማይ እንደ ቺሊ እና የቺሊ ሰማይ የተለየ ስነፈለክአዊ እውነት አሉአቸው እንደ እሚባለው) ከኢትዮጵያ አኗኗር እና ተፈጥሮ ተፅዕኖ፤ የኢትዮጵያ አመትአዊ ወቅትዎች ከአስተዳደግ ስነልቦና፤ በስነምጣኔ ለምሳሌ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በቀለ (ኢሳት. ኢኮኖሚያችን እይት (show) ላይ) ለኢዜማ. በ2013ዓም. ዘግዪ ምርጫ ከእጩነትአቸው ቀድሞ እንደ ተናግገሩት 40እጅ የኢትዮጵያ ወጣት አልሚ በአለመመገብ የተነሳ በመቀንጨር እውነት አምራች ዜጋ አይሆንም እንደአሉት፤ ወይም ቻይናዎች ተሳደቡት እንደ ተባለው የአመጋገብ እና ሽሮአዊ የስነልቦና እና ስነአካልአዊ (physiological) ግንኙነት፣ ወዘተ. በተገኘው ስነግብር (ለምሳሌ ሀገርበቀል እውቀት እና ስርአትዎችን ከዘመነው በመደባለቅ ኢትዮጵያአዊ ትምህርት እና ዳግምርምር ስነግብር (Ethiopian educational and research methodology) በእሚል በማበልፀግ ከተፈለገ በብጁ (customised) ማጥኛ መንገድ፤ የሀገር ከባቢ እውነት ቢጠና ለሌላው አለም በአብይ ደረጃ ይዘቱ ይህን የአክል በቀጥታ አይረባውም። የ መስፍን ጎንለጎን የስነልቦና ልብወለድ፤ 2012ዓም. (በጽሑፉ ጸሐፊ) ውስጡ ይህ ሃሳብ እና አብነት የአክል አለ)። ዘመንአዊው ስርአተትምህርት ለኢትዮጵያ ጥቂት ክፍሉ እንዲህ ዋጋው የአነሰ ይዘት ሰጪ ነው። ይበልጥ የስነግብር (methodology) እንጂ ይዘቱ የራቀ ይሆን እና በሀበሻ ህዝብ ህይወት ማሻሻል ቀጥተኛ ተተግባሪነት የራቀ ትግበራን ይይዝ አለ።
ብዙ ኅዋአዊከተማዎች (universities) በኢትዮጵያ አሉ። ነገርግን፣ ስለ ተናቀው የድህነት ልማድ እና ጠቢው፣ ስለህዝቡ ከቶ አያጠኑም ማለት እሚቻል ነው። የተለመደ የመመረቂያ ጽሑፍዎችን ማስጻፍ እና አአዩ. እንኳ አደረገ እንደ ተባለው ቦታ ይዞ ክፍሉ ከሞላ ጥናት ጽሑፉም የእሚወረወር ነው። ያ፣ እንደ ግዴታ ለመመረቅ ብቻ የግድ የእሚሰራ ጥናት እንኳ ለሀገር እሚደግፍ አይደለም። የስርአተትምህርት እውቀቱን መፈተኛ እንጂ የሰመጠ የሀገር ጉዳይ ጥናት አይደለም። ለምሳሌ፣ ስለ ህዝቡ ድህነት፣ የፖለቲካ ጉዳይ፣ ማንኛውም እለትከለት ጥያቄ፣ ወዘተ. ምርምርዎች አይደረጉም ማለት ተቻይ ነው። ለምሳሌ ህጻን እና ሴትዎችን ወደ እውነትአቸው ሰምጦ በእራስአቸው አለም ስለእነእርሱ አኗኗር ለመገንዘብ ማጥናት የለም። ሁኔታዎችአቸው እንዴት ይሻሻል? ስለ ማጥባት ልማድአቸው ምምን ይታወቅ አለ? ከአጥኚዎች ይልቅ፤ ተራ የፖለቲካ ትእዛዝ እና መንግስትአዊ መዋቅር ወይም ስራ የበለጠ የእሚያውቅ ነው። መንግስት ከየት አምጥቶ በሚኒስቴር መስሪያቤትዎቹ የእሚያስተናግድ ሆነ? የሴት እና ህፃናት ጉዳይዎችን በአለምአቀፍ እውቀቱ እና ስርኣቱ እንጂ በሀገር ጥናት ስለእማይከውነው ነው። ከተቋምዎቹ የተሻለ የአወቀ የእሚመስለው ስለእዛ እንጂ እራሱም አጥንቶ አይመስልም። እንጂ ሀገርን በሠመጠ መጠን ለመምራት ከተቋምዎቹ ህዝቡን የተመለከቱ ነገርዎች ምርምር አይከወንብአቸውም። ትልልቅ እሚወጡ ጽሑፍዎችም ለአህጉር እና አለምአቀፍ ውይይት እንጂ ለሀገር ፍጆታ እሚውሉት ጥቂት ናቸው። ለምሳሌ በስነልቦና እና ፍልስፍና ብዙ ጥናት ቢከወንም ሀገርበቀል ፍልስፍና እና ስነልቦና ጥናትዎች ከቶ አላደጉም። ግን ብዙ ለሀበሻ በምርምር ተጠንቶ ከበለጸገ በፍልስፍና እና ዝርዝር እውቀትዎች ተመንዝሮ መራባት የእሚገባው የእየጎሳው ምርጥ ልማድዎችቻ አሉ። ለምሳሌ በጉራጌ ውስጥ የአለው የልጅዎች አስተዳደግ በስነልቦና የረቀቀ ደቂቅ ስነልቦና (child psychology) ጉዳይዎች አሉት። ልጅዎች እራስበመቻል እሚያድጉበት መንገድ ጃን ፖል ሳርተ የሰበከው ሀገር ይመስል እንደ ፈረንሳይ አስተዳደግ ይመስል አለ፤ በደፈናው። ከልጅነት በመተው፣ በመምረጥ፣ በአለመታቀፍ፣ አለመጨነቅ እና እራስን በማስተዳደር እራስአቸውን ነጥለው በሃላፊነት መውሰድ ህላዌአዊ ነፃነት (existential freedom) ወይም የህልውና ጥገኝነት ሳይይዝአቸው – በግል-ቻይ (autonomous) እና ራስ-ተደጋፊ (self-reliant) ስብእና – የአድግ አሉ። በቀላሉ ወደ ስራ እና እራስ ማስተዳደር የመግባት ልምምዱ ምንአልባት ከእዚህ ከማጥባት የእሚጀምር ይሆን አለ። የህላዌ ፍልስፍና በእዚህ ማህበረሰብእ ትልቅ እውቀት፣ ተግባር እና ጥበብ የአለበት ይመስል አለ። ይህንን መሰል ጉዳይዎች አልተጠኑም። እንደ ጅማ ዩንቨ. “በማህበረሰቡ ነን” እሚሉ መፈክርዎች እና መሰል ህልምዎች በእየተቋምዎቹ ቢገኙም ለከባቢው ግን ብዙም ንጹህ አካባቢያዊነትን አይሰጡም። ሀገርአብቅል ቀርቶ ሀገርበቀል እንኳ አይደሉም። የባህል ህክምና ትምህርትቤት ተነጥሎ ከአለአቸው? የሀገር ጎሳዎች፣ ልማድ፣ መንፈስአዊ፣ ወዘተ. ህክምና ጥበብዎች እና ታሪክዎች አጥኚ ክፍለ ትምህርት ከአሉአቸው? ወይም የንግድ እንቅስቃሴ ጥበብ ጥናትዎች MBA ወዘተ. የጉራጌ ነጋዴዎችን አነጋገድ ጥበብዎች አጥንተው ከአስተማሩት እንጃ? ወይም የእረኝነት ጥበብዎችን እና ብልኀትዎችን፣ እውቀት እና ተሞክሮዎችን ከአጠኑ እና ከአወቁት እንጃ? ወይም አረቄን እና ዘይትን በእንስራ የእሚወጡበትን መንገድዎች ከአጠኑ እና ከአሻሻሉ እንጃ። ወይም ለምሳሌ ለሀገር እውነታ የእሚሆኑ ገሀድዎችን አጥንተው የሀገርአብቅል ጽንሰሃሳብዎችን እና ነቢብዎችን ለምሳሌ “ሀገርአብቅል ትምህርት” ብለው አይነት እሚሰበስቡ ከሆነ እንጃ። ወይም በሀገርአብቅል ጉዳይዎች ዙሪያ በእየደራሲው፣ ጋዜጠኛው፣ ተመራማሪው፣ ወዘተ. የእሚሞከሩ ጉዳይዎችን ሰባስበው፣ አንድ የሀገርአብቅል እና ሀገርበቀል ስርአተ ትምህርት ለማበጀት ወደ አንንድ ነቢብ ለመድረስ እሚታትሩ ከሆነ እንጃ? ወይም ከፍተኛ የሀገር ጉዳይ ለመለወጥ እሚችል መንገድዎች የአሉት ለምሳሌ በስነምጣኔ ነባር ወይም ሀገርበቀል እውነታን ተንተርሶ መንግስትን እና ህዝብን ለመግፋት ለናሙና የአክል ስለሸክላ ጥበብ፣ እድልዎቸ ችግርዎችአቸው እና ታሪክአቸው፣ ከእየማህበረሰብ መሀከል የእሚወጡ የምርምር ተቋም ውይይትዎች የሉም። ስለሽመና፣ ጠላ፣ አረቄ እና እርሻ፣ ወዘተ. በአልተቋረጠ እና ዋና በሆነ መንገድ የማጥናቱ ስራ ለተቋምዎች የተሰጠ ተልእኮ እና ፍፃሜ አይደለም። ጠላ እና አረቄን ወይም ነጠላን ግን የእማይጠቀም እምብዛም በአለመኖሩ፣ የተመራማሪ ተቋምዎች ፍፃሜ ምኑን በማህበረሰብእ ውስጥ ነው የአስብለው አለ? ስለጠጅ አይነትዎች የተብላላ ቋንቋ እና ፍልስፍና መድቦ የእሚዘውር ተቋም አይታይም። በአለምአቀፍ ጥናት፣ መረጃ እና እርዳታ እንጂ ስለህዝቡ የጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት ወይም ሌላ መሰል ጉዳይዎችም መረጃ አይታይም። በእነእዚህ ጉዳይዎች ሁሉ፣ የህይወት እርምጃ አባል ናቸው እና መወራት ከአለበት የእሚነፍሰው መረጃ የማንም የተናጋሪው አመለካከት ይሆን አለ እንጂ የእውቀት እና ምርምር ስጦታ መረጃ እና ወሬ የመሆን እድል የለውም። ምንም የተናገረ አዋቂ ለመሆን የተሻለ አዋቂ በተቋምዎች እና ሙያተኞች አልተፈሩም። የአንድ አካባቢ ፖለቲካ እና ምድር ምርምርንም እሚመረምሩ መታተምያዎች፣ ይህ ሁሉ አካሄድ በምርምር ተቋም ብቻ ሳይሆን በጋዜጠኛነት እና ጽሑፍ ገበያውም የአለ ነው። የህዝቡን ችግር መርማሪ መጽሐፍዎች በግለሰብእዎች አይታተሙም። ልብወለድዎች እና ግጥምዎች ይበዛ አሉ። ከእነሱ እሚገዳደር ህትመት የለም። ምርምር አይጠይቁም፣ የልብ ፈጠራ ተብለው በትንሽ ብር ማንም ሊያሳትምአቸው የእሚችል ናቸው። እንጂ ስለህዝቡ አኗኗር፣ የእራሱ ጉዳይዎች በስፋት አይጻፍም። ቀሪውም ትርጉም ነው እና የአፍንጫስር እውነት እና ችግር መወያያ አይደለም። ጋዜጠኛነቱም አብይ ወሬዎችን በሩቅበሩቁ እንጂ የተዘረዘረ ወሬ አይከታተሉም አያቀርቡም። ለነገሩ ለምሳሌ ጋዜጣ እና መጽሔትን በተመለከተ፣ ንቁ አንባቢ በከተማዎች ስለሌለም አንዱ ችግር ነው ብለው ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም ህዝቡን ገሥጸው አለ (ገ.31፤ ዛሬም እንደ ትላንት?፣ 2012ዓም.)
ይህ ከሆነ፣ ወሬን ማንም በኢትዮጵያ አጥርቶ እና ተጨናንቆ ሊናገረው አይችልም። ማንም አዋቂ መምሰል ይችል አለ። የተገኘውን በመሰለ መንገድ ለማውራት ቀላል ነው። ተቋምዎች በሀቅ በህዝቡ ውሥጥ የሉም፣ አጥንተው እሚነገረውን ነገር አልመሩትም። ማለቱም ወሬ የእሚዘውረው አያያዝ ነገሩንሁሉ ይገልጠው አለ። በተያያዘ ጽሕፈት እና ህትመት እጅግ የነተበ አገልግሎቱ በምርምር እና ጥናት የተደገፈ የአካባቢ ጉዳይዎች፣ ቢያንስ በንጽጽር ቢያበጁ፣ አአምርኩሎ (የእኔአውቅአለሁ) ወሬዎች ይቀንስ አሉ። ሶስተኛም፣ ጋዜጠኛነት በተጨባጭ የሞተበት ዘመን አሁን አለ። ጦርትዎችን ለመዘገብ ጋዜጠኛዎች አደጋ እየተጋፈጡ በመከታታተል ለመዘገብ አይቀሩም ነበር። የ “ጋዜጠኛው ልቤን ነካው” ዘፈን እስኪዘፈን ይህ በኢትዮጵያ በፊት የታወቀ ነበር (በሀገር ውስጥ በወቅቱ እውነታው ቢያረጅም፤ ህዝቡ ግን በዘመኑ በመገናኛብዙሃንዎች አማራጭ ማጣት የተነሳ በመገናኛብዙሃንዎች ይመለከት የነበረው አንድ ወጥ ትንግርት በተለይ በእስራኤል ፍልሥጤም ዉጊያዎች የድሚሰሙትን የዘገባ ጀብዱዎች ነበር፤ ቴዲ አፍሮም በእዛ ጦርነት ወሬው መግነን የተነሳ እየሩስአሌምን ተቀኝቶላት ነበር)። በፊት ግን ኢትዮጵያም እውነታዋ ይህን ይቀራረብ ነበር። የድሮ ጋዜጠኛዎች ከጦርነት አውድማዎች ለእከሌ ጋዜጣ ብለው በጽሑፍ የዘገቡት ለልኮት (reference) አሁን ወዲያው ባላገኝም የአነበብኩ እንደ ነበር ትዝ ይለኝ አለ። ተጨማሪ ኦሮማይ ዛሬ ቢጻፍ ግን የነበረበት ወቅት የጋዜጠኛዎች እውነት አንፀባርቆ እሚገልጥ ስለነበር ዛሬን ግን አልገልጥ ብሎ የለየለት ፈጠራ እንጂ እውነት የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይን የታከከ ትርክትነ ትንግርት ይሆንብን አለ እና ከእዚህ እምንረዳው ጋዜጠኛነት በግብሩ ለአለፉት ሰላሳ አመትዎች በከፍተኛ ማዳጥ የአሽቆለቆልን መሆኑን ነው። የተስፋዬ ገብረዓብ የትግል ጋዜኤኛነት እውነት እንኳ ይህን ይመሰክርብን አለ። ዛሬ ከደርግ አስተዳደር እንኳ በወረደ መንገድ ጋዜጠኛነት ቢሮ ተቀምጦ ግለሰብእዎችን ማናገር እና የተላከ ማስታወቂያ ወሬን (press release) ለህዝብ ማስተጋባት ብቻ መስሎ በከሸፈ ሃቁ ተቋቁሞ አለ። ያም ጭራሽ ከፕሮፓጋንዳ አንጻር ብቻ እሚቃኝ እንጂ ነፃነት እና ህዝብአዊ አገልግሎት እማያውቅ ነው። የተስተካከለ ወሬ እሚደመጥብአቸው እና ንጥር መረጃዎች እሚብላሉበት እነእዚህ አውታረግንኙነትዎች በአቅም ኮስሠው እና ጫጭተው መጥፋትአቸው፣ ወሬን ማንም መንዛት የእሚችልበት መንገድ የበዛ እንዲሆን ፈቅደው አስችለውት አለ። ይህ ውድቀት መረጃን እና ዝውውሩን ከሙያአዊነት ፈልቅቆት በመቅረቱ የተነጠፈ ጨርቅ መንገድ በዘመንአዊነት ለአልተገራው ህዝብ የመረጃ ሰነፍ አያያዝ ሆኖለት ሠርግ እና ምላሽ አድርጎለት አለ።

2) ስልጣኔን መመስረት

በኢትዮጵያ የዛሬ እና የአለፉት ሠላሳ አመትዎች አኗኗር መሰረት፣ መረጃ ዋጋው ተራ ነው። አንዱ ሰበብ፤ ወሬን ለማጥራት ሰሚው የሰማው ወሬ እርግጠኛ መሆኑን እንዲጠይቅ እሚያስገድድ እውነት በመራቁ ነው። መረጃ እውቀት እና ሃይል እሚሆነው የሰለጠነ ግብይት እና አኗኗር ሲኖር ነው። ያኔ ስህተት መረጃ አክሳሪ ይሆን ነበር። የተስተካከለ መረጃ ማፈላለግ ይፈለግ አለ። ዳሩ፤ በዘፈቀደ ስለእሚሰራ እና እሚኖር፣ መረጃን ከማጥራት ‘በአሉ’ እና በተወራው ለመንቀሳቀስ ቀላል ሆነ። ገና ጋርዮሽአዊ ጥንትአዊነት በአልተወሳሠበ እና ነገወዲያን በአማተረ ጥበብ አልተሰበረም። የበዛ ወደ ማህበረሰብእ ወጥቶ በገሀድ ተንበልብሎ በእሚነድድ ማህበረሰብእአዊ ዝሙን ትስስር መመንደግ አልቻለም። የአኗኗር መንገድን፤ ግድ እንደ እሚሰጥ እና እሚጨነቅ ፍጡር፣ በጥራት እና በስምጠት ለመከወን ፍላጎት የለም። በልቶ በእሚያድረው፣ ነገን እንደ እንስሳ ከዛሬ ለይቶ በእማያውቀው፣ ትውልድን ጠቢ ማንነቴ ብሎ ማመን ከእማያውቀው፣ ገጣሚ እንደ ገለጠው ሺህዘመንዎችን አንግቶ ለማምሸት ደጋግሞ ወደ መኝታ በእሚሄደው (የወንድ ምጥ) በጥቂቱ እና በቆሻሻው አኗኗር ለመኖር ዴንታ የሌለው ህዝብ በ ተምኔትዮጵያ (UtoEthiopia) አገነዛዘቡ የአለም ቁንጮ ነኝ ብሎ የቸልታ ህላዌውን እንደቀጠለ አለ። ትምህርት በአለመዝለቁ፣ ህዝቡ እንዲህ ነጋድራስ ባይከዳኝን እንደ አስጨነቀው የተበደለ ሆነ። ይህ በሁሉ አውደህይወት እንደ ተገለጠው በእዚችው የመረጃ ልውውጥ አለም እና እውነቱም የተዘረዘረ ስህተት ሆኖ አለ። ለምሳሌ፤ በአለምአቀፍ ውድድር እና እውቀት የጠገበ አስተዳደር እና ትምህርት መገንባት ቢቻል፣ የተሻለ እውቀት ተገኝቶ ለመረጃ ዋጋ እሚሰጥ ሀገር ማበጀት ይቻል ነበር። ነገርግን፤ ጭንቀት ለነገ እማይደርስበት ሀገር ነው። ከእነ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ እስከ 2012ዓም፤ ህዝብ ዴንታአለሽየለሽ (carelessness) አጽንቶ፤ ሰነፍ ተብሎ እንደ ተገሰጸ ነው። 2012ዓም. ፕሮፍ. መስፍን ወልደማርያም አገላለጥ፣ እስከመቼ በአለመለወጥ የእሚረካ መሆን እንደ አለበት፣ ህዝቡ እራሱን መጠየቅ አለበት። የኢትዮጵያ ፖለቲካ እውቀት ታጋዩ፤ “…ምላስ የአለው ሁሉ ተናጋሪ በሆነበት፣ ፊደል የቆጠረ ሁሉ የተማረ በእሚባልበት ሀገር…” (ገ.23)፤ “በ2035ዓም. 250 ሚሊዮን ግድም ህዝብ እንሆን አለን፤ እግዜር ይሁነን” (ገ.102)፤ ብለው የመንቃት እና የመሰልጠኑን ነገር እንደ ገሠጹ እድሜአቸውን የአስረከቡን የሀገር-አባት ሰው ሆነው ተለይተው አሉ። በመረጃ እና የማህበረሰብእ ተሳትፎ ለተግባባ እና ወደፊት ተጓዥነት ብቻ ሳይሆን ለመዳንም ጭምር ይህን የማእዶት ግብር መከወን ግድድ የእሚል እየሆነ ነው። መረጃውን የመገልገሉ መንገድ ወደእዛ የእሚየደርስም፣ ሲደረስም የእሚመራ እና ወደ ተካቢ ልህቀት የእሚየስዘግመው መንገድ እንደ ሆነ አለ። እነሆ የተሻለ ዜጋአዊ የበላይነትን በትውልዱ በእውቀት መገንባት አዋቂዎች መገንባት እና በስልጣኔ ሀገሩን መንፏቀቅ ማስጀመር የጉዳዩ መነሻም መድረሻም ነው፨

One reply on “ስለ አአምርኩሎን በኢትዮጵያ ማከም፡ የ ሀገርአብቅል ጥናትዎች እና ስልጣኔ ጉዳይዎች”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s