Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

በመሀከልሀገር ኢትዮጵያ ባህል የአለመፈጠር፡ ስለ እሚገናኝ ሆኖ የአልተገናኘውን ከአልተገናኘ የእማያገናኘውን ማገናኘት

About how it is late but necessary for Ethiopian culture to develop at central Ethiopia.

ይህን አጭር ጽሑፍ ከማስፈንጠሪያዎቹ ቢጸዳም በ ተአዶ. (PDF) አውርዱት። ከ ጉድራይቭ ተጋሩ። ከ አካደሚያ.ኮም አግኙ።

“ተከታታይ ትውልድዎች በሰላም እና ፍቅር እየኖሩ ባህልአቸውን እና የኑሮ ስርአትአቸውን እየተወራረሱ ይቀጥል አሉ፤ የቀደመው ትውልድ ለእሚከተለው ትውልድ የአለውን የአቀብል አለ፤ እየ አንድአንዱ ትውልድ የወረሰውን ብቻ ሳይሆን እሱ የጨመረበትን አክሎ ለተከታዩ የአስረክብ አለ፤ እንዲህ እየተባለ በትውልድ ቅብብሎሹ ሀገር ይገነባ አለ፤ ስለእዚህም የቅብብሎሽ መሰላሉ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፤ በኢትዮጵያ የትውልድ ቅብብሎሽ መሰላሉ ተሰብሮ አለ”፨
ፕሮፍ. መስፍን ወልደማሪያም፤ ዛሬም እንደ ትላንት? ገ.113

“አባት የአበጀው ለልጅ ይበጀው”፨
አፈወርቅ ታረቀኝ፤ አንጋረ ምሳሌ ዘግእዝ፣ (2001ዓም.)፣

 

መነሕፈት

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 7th 2021,

ብቸኛ እና የአልታደሉ፤ ዋና የኢትዮጵያ መገለጫ ባይሆኑም (መስፍን ወልደማሪያም፣ ገ.105) በኢትዮጵያ የአሉት የመሀከልሀገር ዜጋዎች ናቸው። ባይተዋርነቱ ማለት ይቻል አለ ከሁሉም ነገር እና ዓለም ጭምር ነው። ከምንም እና ከእራሱም አልገጠመም። ከዘመን-ርብራብ የአልተሰናሠለ ይህ መሀከልሀገር ማህበረሰብእ እሚመሠለው፦ መሪው ጥሎት እንደ ተሰለበ ብቸኛ የባህር ማእከል ላይ በተገኘው ማእበል ሁሉ እሚራወጥ ታንኳ ነው። እየተንገላታ ነው። የት እንደእሚሄድ አያውቅም። ከክፉው ሁሉ በላይ፣ ዴንታአለሽ የለም። ይህ ክፉ-ግን-መልሶ-ደግ-ነገሩ፤ ማንም ዴንታው አይደለም ወይም ዴንታው ችግር ለመቀልበስ እስኪበቃ አይረዝምለትም ማለት፦ ይህንንም እውነት እራሱን የሚመለከቱ እምብዛም ስለሌሉ፣ ችግሩን ማወቅ አይቻልም እና ህዝቡ እጅግ በገባበት መዓት አኗኗር ተጠምዶ የአጣውን እና የአለውን ስለእማያውቅ እና ማወቅም ስለእማይሻ በቀኑ ማምሻ ትንሽም አይጠዘጥዘውም። ወደ ዳግ-ተመለሰ የእዚህ ጽሑፍ አጭር ነጥቡ – ባህልአዊ ባይተዋርነት – ቀጥለን እንግባ – ያም የእዚህ የጠየቅንው ግድአለሽየለሽነት (carelessness) ድንዛዜ ከአከማቸው ደብረ-ችግር ለመውረጃው ቁልፍ ፍኖቱ ነው። የእዚህ አጭር ጽሑፍ ከቀደሙት ልዩነቱ፣ ትኩረቱ፣ ለምን የባህል ኦናነት/ባይተዋርነት በመሀከልሀገር ኢትዮጵያ በአለፉት አስርታት ተፈጥሮ አየን እሚለውን፣ ከማእከለ-ትውልድ-ትስስርዎች ላይ አስምሮ ማተኮር መፈለጉ ብቻ ነው።
እናስ! ዝርዝር የእምንገልጠው በሂደት ነው፤ ግን ይህ የባህል ባይተዋርነት የት ሰምሮለት በመሀከልሀገር ኢትዮጵያ በቀለ፣ አሁንስ ምንየአክል ሠግጎ አለ? ለአለመሠልጠንአችን ግብረመልሱስ?
ስናነፈንፍ ሁለት ቦታዎች ውስጥ አለ። አንደኛ፤ የአለመጣጣም እና በዓድነት፤ በኢትዮጵያ ከተሜ ህዝብ እና የከተማ ተራው ከተሜአዊ ስልጣኔ መሀከል አለ። ይብስ የሆነው ሁለተኛ ግን የስልጣኔ (በተለይ ከሠውዘር ሁሉ አንፃር) ክፍተቱ እንደ ሰማይ እና ምድር ሆኖ፣ ይህ ከገጠር-ኢትዮጵያ እራሱን ለይቶ ዘመንኩ እሚለው መሀከልሀገሬ ህዝብ እና ዘመንአዊ ስልጣኔው እማይተዋወቁ ዳሩ እንደ በዓድ እና እንግዳዎች ግን አብረው ተጠምደው መሀከልሀገሬው እሚደናበርበት እውነት ውስጥ ይህ የባህል ኦናነት አለ። መልሶ፦ ወደ እዚህ ዘረሰው ስልጣኔ ምንምአይሌ (fair) ተቋዳሽነት እንኳ ለመድረስ – ለማበርከት እሚለውን ፈንግለን ጥለን – መልሱ አንድም የእዚህ ባህል ብልጸጋ ነው። እንደ ሀገር-መሠልጠኛ እና ህዝብ-መግሪያ ሁሉ እንጂ ይህ ጉዳይ የባህል ምስረታ ወይም ማእዶት ቁምነገር ብቻ አይደለም። ከረዳን፤ ቀጥለን ወቅትአዊ አንድ ጉዳይ በመተንተን ወደ ከባህል ጋር የአለውን ጫወታ ለማገናኘት ሙከራን እንከውን።
በአለፉት ሁለት አመትዎች በኢትዮጵያ፤ ሀገርአዊ ውጥንቅጥ የወጣበት ነው። መገለጫው? በገሀድ የታየ ተገልሎ የአፈገፈገው ህዋሃት. እና ማእከልአዊ ወይም ክልልአዊ መንግስትዎች መሀከል የአሉ ግጭትዎች፣ በገሀድ ይነገሩ እንደ ነበረው ሀገርን የማዳን ጉዳይ ተሠኝተው ነበር። “የአስተዳደሩ” መገናኛብዙሃንዎች ነጋ-ጠባ ሀገር ልትፈርስነው በእሚል ዜጋውን (ገጠርም ከተማም)፣ ወደ ክተት እና መዋጮ ይጠመዝዙት ነበር። ውጭ ሀገር የአሉ ብዙ ኢትዮጵያዎችም፣ ሀገር አትፈርስም በእሚል፣ ህዋሃት. በመቃወም ማእከልአዊ መንግስት አስተዳደሩን ቸብቸብታ ለመሸለም ይንቀሣቀሱ ነበር። ብዙ ተቃውሞ እና ትእይንተ ሰልፍዎች ይከውኑ ነበር። ዞሮዞሮ፤ የእርስበእርስ ጦርነት እና ግጭትዎች፣ ንጹሐንዎችን በገፍ እና ግፍ በጨመረ በመቶሺህዎች ገድለው እና አፈናቅለው የሀገር ጉዳይን ወደ አደጋ አድርሰው እንደ አሉ ይነገር አለ። በተምኔትዮጵያ (UtoEthiopia)፤ ፍፁም ተደርጋ የእምትሳለው ኢትዮጵያ፤ ህዋሃት.ን ከውስጡ ዐብይ ከፈነገለው” (ገ.28)፣ በኋላ “የብልጭድርግም ለውጥ” (ገ.26)፤ አስመልክተው ሲያበቁ “ተረኞች” የተሠኙት መንግስት መሪዎቿ፣ ቢያንስ እንደ አስመለከቷት ከሆነ፤ በቋፍ ቆማ ታየች። እነእዚህን ሃቅዎች (facts)፣ ከተራ የታወቀው ደካማ የመንግስት አስተዳዳሪው ተቋም ብቃት፣ ከ”ህዋሃት. ወደርየለሽ ጭካኔ፣ ሀገር-ጋጭነት፣” (መስፍን ወልደማርያም፤ ዛሬም እንደ ትላንት? 2012ዓም. ገ.29)፤ ወይም የስልጣን ሽምያ እውነታ፣ ወይም ሌላ መነጽርዎች አንፃር መመልከት እሚቻል ነው። ግን፤ እነእርሱን ቸልታ ቸረን፣ ወደ ትውልድአዊ ቀውስ፣ ያም ከባህል-አልበኛነት የተነሣ ሆኖ እንደ ተመዘዘ ቆሻሻ ሀገርአዊ እውነት እንመልከተው።
ይህ ውጥንቅጥ፣ በአለፉት እየተደራረቡ እሚገኙ አስርታት (decades)፤ የጎረመሱ እድገትዎች እንጂ፤ በድንገት አበልቀለም። እዚህ እንዴት ተደረሰ?
በፍኖተ ዘመንአዊ ሥልጣኔ አለመራመድ ምርጫ-ውጭ መሆኑ ከታወቀበት ሁለትመቶ አመትዎች ገደማ ወደእዚህ፣ ብዙዎች የምእራብ ስልጣኔን ተውሰው እራስን በመቻል እንደ አደጉ እና ዛሬ በእራስአቸው የቆሙ ታላላቅ ሀገርዎች መሀከል እንደተቀመጡ ይታወቅ አለ። በኢትዮጵያም ይህ ትትረት፣ ዘግየት ብሎ፣ ከአፍሪቃ ግን በብዙ አያያዙ ፈርቀዳጅ እየሆነ በ ቀኃሥ. ዘውድአዊ ፈርምግባር (royal initiative) የተሞከረ እና በእማይናቅ መሠረት እየጎነቆለ ነበር። ያንን ለበለጠ ማሻሻል የተደረጉ አስተዳደርአዊ ተቃውሞዎች፣ ስርኣተመንግስቱንም ለውጠው፣ እንደ አለሙት ሳይሆን ጭራሽ ይከስም ጀመረ። ያ ማቆጥቆጥ በጉጉው ደርግ መቀጠል ሳይችል ቀረ። ያ እሳቤ ጭራሽ በህዋሃት.-መር ኢህአዴግ. መንግስት-አስተዳደር አፈርድሜ በመብላቱ፤ ብዙ ሀገርዎችን አንቅቶ ለማሠልጠን የቻለው የ “የቀረው አለም ርቆ ከሰለጠነብን እኛ ቅኝእንገዛ አለን” ፍራቻ፤ ዛሬ ለኢትዮጵያ ማንቂ መሆን አለመቻሉ ገሀድነቱ ታየ። በእርግጥ ብዙዎች እንደተቹት እና ግልጥ እንደሆነው የዲፕሎማሲ ከረፈፍነት እና የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ ተደረገ እንጂ ድህረ-ኢህአዴግ.፣ ዓለምአቀፍ ጫና በኢትዮጵያ በተለየ መልኩ የልተከወነም። ዞሮዞሮ፤ የሰለጠነው አለም ጫና ሀገር ለማፍረስ እሚያስችለውን ጎንዮሽ ተጽዕኖ በባህል-ክፍተት-ሞዪ-ሚና ግን እንዲጫወት ግብዣ እና ተገቢ መስተንግዶውን ሰጥቶት አለ። ይህ ሃቅ ወደ ባህል ክፍተት ውይይቱ የአስተሳስረን አለ። በተጠቀሰው መጽሐፍአቸው መስፍን ወልደማሪያም “የትውልድ መገፋፋት” እንደ አሉት፤ “የትውልድ ቅብብሎሽ መሠላል በደርግ ተሰብሮ፣ በወያኔ ተረጋግጦ አለ” (ገ.113 – 118)።
በሀገር በወጥ መንገድ መሠልጠን አለመቻል የተነሳ፤ ታዳጊ እና ወጣት ኢትዮጵያዎች ከወላጅዎች የእሚወርሱት የአኗኗር ዘዴ ወይም ወቅቱን የእሚጣጣም ስልጣኔ አላገኙም። ስለእዚህ፤ የትግል እና የስንፍና አኗኗር ለወጣቱ ተትቶለት አለ። እንደ አላደገች ጭራ ሀገር ገና ብዙ መመስረት የእሚገባው ሳለ፣ በደፈናው ከሠለጠነ አለም እሚገኝ ዝማኔ ጫፍጫፉ ግዝግቤት (import) በቸልታ ተከምሮበት፣ በአሠቃቂ መጠን አለሁልህባይየለሽ እና ተቆጣጣሪየለሽ ትውልድ ተፈጥሮ አለ።
በግንቦት 30 ቀን 2013ዓም.፣ “‘የህፀፅ ቅብብሎሽ’ መጽሐፍ ወግ” በእሚል አርእስት በ ዳግ-ቀረበ “ሰበዝ” የ አፍሪሄልዝ ትመ. (Tv.) መርሐግብር ውይይት ላይ የቀረቡት፣ ደራሲው ጌታቸው ታደሰ ወጣት እና ታዳጊ የዘመኑን ሀበሻ ለአሰናጇ ቤተልሔም “እንዴት ነህ ሲሉት እሺ! ብሎ እሚያልፍ ነው፣ ቆሞ አያናግርም። ብርድ ነው፣ ልበስ ወይም ይርብህ አለ ብላ ሲባል ‘ችግር የለም!’ ብቻ እሚል ነው። ‘እሺ!’ እና ‘ችግር የለም!’ ብቻ የዘመኑ አማርኛ ሆኖ አለ!” ብለው ነግረዋት ነበር። በመሰረቱ፤ ወጣቱ ምስኪን መሆኑን፣ የእድሜ በላይዎቹም በማቅረብ ከፍራቻው ገፍፈው መግራት እና ከእራስአቸው ማመሳሰል እንደ እሚገባቸው በደፈናው መልእክት ሰጥተዋት ነበር። ይህ በጠቅላላ፣ በታሳቢነት እና በተግባር በእሚተካኩ ትውልድዎች መሀከል ተከፍቶ የተለጠጠውን አስጨናቂ የባህል ክፍተቱን አስመልካች ነው።
ስለእዚህ፤ የአባትአዊ ሀገርነት እሳቤ በኢትዮጵያ የምእት አካባቢ ውድቀቱን በከፍተኛ መጠን – በተፅዕኖ (virtually) ግን መቶእጅ – የአስቀጠለ ሆነ። መስፍን ወልደማሪያም፤ “ትውልድ እና ታሪክ ቅብብሎሹ መፋለስ…የዛሬው ኢትዮጵያ ዋናው ችግር ነው” ብለው እድሜውን ወደ ኩርማን ምእት የአወርዱት አለ፤ (ገ.24)። የገጠሩን ትተን በመሀከልሀገር የአሉ የኢትዮጵያ ጎልማሳዎች ሽልፍኖትዎችን (technologies)፣ ከተሜነትን፣ ዝማኔን፣ ወዘተ. አያውቁአቸውም። ያ ሌላው ችግር ነው፤ የህጸጽ ቅብብሎሽን ሲታረም የእሚያደናቅፈው ሌላ ህጸጽ፣ ጎልማሳ እና አዛውንት እሚሰኙት ልዕለብዙሃን (super-majority) ከወጣቱጎጎ እኩል እውቀት የለውም፤ መግባባትም አይችሉም – ያ ግን ሌላ ትልምአግጣጫ ይጠራ አለ እንጂ በችግርነቱ ማሸነፍ የለበምት። ምንም አዳዲስ ባህልዎች እና ቁስአዊ ስርአትዎች አፍንጫዎችአቸው መሀል እየአደገ ኢትዮጵያን ቢያጥለቀልቅም፤ የኢትዮጵያ ጎልማሳ-ዜጋዎች፣ እምነት መሪዎች፣ ምሁርዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ ባለሀብትዎች፣ ውጭሀገሬዎች (Diasporas) – እነእዚህ ሁሉም ለየቱም ሀገር አባትዎቹ ናቸው – ግን የመኖር ዘዴአቸው ደካማ እና እጅግ ውሱን እንደሆነ ቀረ። እንደ ተጠቀሰው የአለምአቀፍ ጫናው ግን በረታ። ለምሳሌ ከተሜነት አስገዳጅ ለውጥ ሆነ። ስለእዚህም፤ ከውጭ ስለንግድ ብቻ በእሚል ተሸራርፈው በእሚገቡ ግንባታ እና ከንቲባአዊ እውቀት እና ጥበብዎች፣ ቁሳቁስዎች፣ ወዘተ. ኢትዮጵያ በእማታውቀው አኗኗር ውስጥ ለመግባት ብሎም የሀገርነት ማእከልዎቿን ለመመስረት በቃች። መሀከልሀገር ከ ሀገረሰቤ በእሚል ሀገር እና ህዝብ ለመሠንጠቅ እና ሀገረሰቤን እንደሁለተኛ ዜጋ እምትመለከት የአክል ለመሆን በቃች። መቶእጅ ሀገረሰቤ የነበረች ኢትዮጵያ በመቶ አመትዎች የሶስትሺህ ዘመንዎች ታሪኳን ሁሉ ገፍትራ አዲስ ማንነት በከተማዎች ለማፍራት ተሯሯጠች። መሠረቷ ሀገረሰቤ ሳለ፣ ሀገረሰቤ የአልተቆጣጠረው ለውጥ፣ ሀገረሰቤን የአላነጣጠረ ጅማሮ፣ ሀገር መክዳት ሆኖ ተጀመረ – ከቀደመው ታሪክ እና ስልጣኔ፣ ባህል እና አመጣጥ ተጣጣሚ ለውጡን ከዴንታ ውጭ አደረጉት። ምንም በ ቀኃሥ. ጥረቱ ሀገርበቀልነትንም ለማኖር እና ጃፓንን ለመኮረጅ የታለመ ቢሆንም፣ እንደ ተባለው ፈጥኖ በደርግ ተቀልብሶ፣ የአልዘለቀ አዲስ ማህበረሰብእአዊት ሙከራ ቆየ። ያም “መራር ዘመን” (ገ.28) ጭምር ነበር። በተለይ በቀጠለው አስተዳደር ግን ነገረ ሀገር ተሽቀንጥሮ፣ የቸልታው መጠን በመብዛቱ ወደ አለንበት ስንነሳ የዘከርንው የሀገር ውጥንቅጥን ደርሶ ማየት ግድ ሆነ። ያ ሲተነበይ የነበረ ነው። ሌቋሆ. (ሌላነገርዎች ቋሚ ሆነው)፤ ይህ አካሄድ እጅግ አደገኛ ነው፣ ገና ነገም ከፊ ነው። ለልጅዎች ማስተማር የእማይችሉአቸውን አኗኗር ዘዴዎች፣ የኢትዮጵያ አንጋፋ ዜጋዎች ተቀብለው ወደ አልተማረ ትውልድ አዘነቡ። አሁንም መቆጣጠር የእሚችሉት ባህል እና ስልጣኔ በፊትአቸው በአሉ ልጅዎች አይሮጥም፤ ከአቅምአቸው ውጭ የአደረጉት እንጂ። የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም (2012ዓም. አንድ መድረክ ላይ) እንደ ገለጡት የሀገር ባህል ወረራው ቸል እሚባል የአልሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ አለ። ዳሩ፤ ሀገር እየአተራመሰ ለአለው በዓድ የባህል እንቅስቃሴው ምንም አቻ እርምጃ ከአረዳዱ ጎን የለም። ማንም ፈርቀድዶ የአላስተማረውን አኗኗር ዘዴ ታዳጊ እና ወጣት ገብቶበት እሚደናገርበት ሆነ። በመጨረሻ፤ ገብረህይወት ባይከዳኝ እንደ አሳሠበው፤ እውቀት የበዛበት ኣለም እውቀት ወደ ሌለበት ሀገር የስራዎቹን ዋጋ ልኮ ሀገሩን የአጠፋው ዘንድ ወደ እሚያስችለው መንገድ እንዲነዳው፤ የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ሁኔታው በእራስሰር በቀላሉ ተቀነባበረ። ይህ የባህል ክፍተት አንደኛ ደረጃው ሆነ። የአልተቀደመ የዝማኔ እና ከተሜነት ዘዴ፣ እንደ ትንግርት ለታዳጊዎች እና ወጣትዎች ይሆኑ ዘንድ እንጂ በተሞክሮ እና ልምድዎች እሚቀላቀሉት መሆን ሳይችል በመቅረቱ፤ አኗኗር ባህልን የግድ ይይዝ አለ እና የባህል ክፍተት በአኗኗሩ ገጠጠ። ሁለተኛው ችግር የስልጣኔው መወሳሠብ ሲሆን፣ በእውቀት እና ማእዶት የዜጋዎች አለመበልፀግ፣ ከዓለሙም ሆነ፣ ከእራስአቸው ጋር እንዳይኖሩ አደረገአቸው። የባህል መኖር ህዝብን የአስተሳስር እና በአንድ የአኗኗር ፍኖት ይከትት አለ። ወጥ ባህል የገባውን ዝማኔ እየመራ በ አለመጠንከሩ፣ ህዝብን ግድየለሽ እና በሂደት የተነጠለ አድርጎ ሊያስቀረው በቃ። በፊትም ዛሬም ሀገረሰቤ እደእሚኖረው፣ መሀከልሀገሬ ግን በአንድ ባህል አይኖርም።
የስነውሳኔ (politics) እና መንግስትአዊ አስተዳደር መጨቅየትን መርጦ፣ ጭራሽ ይህን የባሀል ኦናነት ይገለገልበት አለ። የህዝብ ንቃተህሊና አለ ማደግ እና ወድዶ ሳይሆን አለም በላቀ በመሰልጠኑ የተነሳ ስነምጣኔውን ከውጭ ሀገርዎች በመጣ እውቀት እና ንግድ ጥቂት አሻሽሎ እሚኮፈስበት እንጂ ሀገር እየተወረረ የአለበት አንዱ ፍኖት መሆኑንም አይመለከቱትም። ስነውሳኔአዊ አቅለሽላሽ “መሸጦነት፣ ሆድ-አደርነት፣ እና ሀገር-ጋጭነት” (መስፍን፤ ገ.19፣ 28፣ 40)፤ ከእዚህ የተዝረከረከ ስነምጣኔአዊ አረዳድ እና አያያዝ ተደምረው፤ እነእዚህ ሁለቱ አባሽ ችግርዎች ሆነው፤ የባህል መጥፋቱን አጨብናኝ ችግር አደረጉት። ከእዚህ ውጥንቅጥ በተጨመ ምን ስጋት ከእዚህ የተነሳ በኢትዮጵያ አለ?
በደፈናው፤ የትውልድዎች ወጥ ቅጥያ መጥፋቱ፤ ባህል ከነበረበት ዘመን ከ አለንበት ትውልድ ላገናኘውም። ባህል ከነበረበት ወይም ከአዲስ ተሠርቶ ወይም በመዳቀል ተፈጥሮ (ከድሮው እና ከእሚፈለገው)፣ ከአሁኑ ህዝብ ከአልተገናኘ፣ ህዝብ በመሀከሉ እንደ ጠንካራ ሀገር አይገናኝም። ባህል ህዝብን አስተሳስሮ ከማኖሩ በዘለለ፣ በስነውሳኔ እና አስተዳደርም ቀጥተኛ አዎንታአዊ ተፅዕኖ የአበረክት አለ። ለስነምጣኔም የእማይነጣጠል አበርክቶት አለው። ሠላም እና ደህንነት፣ የሀገር መቆየት እና መሠልጠን፣ ሁሉም በወጥ እና ጠንካራ ባህል የእሚታገዙ እና በእርሱ ወለል የእሚካቡ ናቸው። ይህ ሁሉ መሰረተ ሀገር ግን ከባህል ውጭ ቢገነባ የእማይቆም ነው ማለት ነው። ያ ሰምም ወርቅም ነው – አማራጭ የለውም። አሁን የሺህ አመትዎች ታሪክ እና ወደ ጥቅም የእማይመነዘር ኩራት (ባዶክብ (overrated) ታላቅነት) በነተበ መንግስትአዊ አስተዳደር እና እማይዝል ቸልታ ሀገርን ከመቅጽበት ወደ ልትፈርስ ነው/አትፈርስም ወሬ እና ጠመንጃ-መር እንቅስቃሴዎች አውጥቶአት አለ። ይህ በመሰረቱ የስነውሳኔ እና ሀገር አስተዳደር ውድቀት ከፍተኛ መለኪያው እንደሆነ፤ የባህል ጉዳዩ የእሚያቃጥል ነጥብ የሆነበት ወቅት ነው። ባህልን፤ በግድአለሽነት፣ በትጉህ፣ ጥንቁቅ፣ አርቆ አሳቢ፣ ግልጽ፣ ተጠያቂ፣ ሀገር-ህዝብ-ወዳድ፣ ከምንም በላይ ስልጣኔ ላይ ንቁ ገጸባህሪዎች ዙሪያ ማበልጸግ እና ማሳደግ የመጨረሻ እድሉ ላይ የአለ ይመስል አለ፤ ሌቋሆ.።
ብዙ ህዝብ እና ሀብትዎች፤ ወደ እድልዎች መቀየር ሲችሉ፣ ወደ “ሀገር ማፍረስ” እየደረሱ የአሉት፤ በእየዘርፉ በአሉ እዚህ ለማድረስ የግድ የእሚበቁ ስህተትዎች እንደሆነ ግልጥ ነው። አሁን በእዚህ ዳሠሳ ግን የአለው የባህል አለመገንባት ነቁጡ በሁሉም ዙሪያ የእሚገኝ ዣንጥላ አጥዪ ቅድመሁኔታ እና የሂደቱም ምሠሶአዊ አባል ነው። በዘመንዎች የእሚራራቁ ኢትዮጵያዎች፣ ተፈጥሮ ያንን አድርጎብአቸው አለ። ነገርግን፤ በባህል ከተራራቁ፣ በአንድ ሀገር አልኖሩም። አንድ ህልም፣ አተያየት፣ ፍልስፍና፣ ወዘተ. የሉአቸውም። የሀገር በዘመንዎች ወጥ ንብርብር ማግኘት እውነታ ሳይሳካ በመቅረቱ፤ የሀገር ጉዳይም የመፈረካከስ እውነቱ በቀላሉ ተመዥራጭ ነው። እንደ ሆነው።
ይህ ጉዳይ በመሀከል ሀገር ለምን አተኮረ? አንደኛ፤ የመሀከልሀገር ባህል የሌለው የሆነው ከዳር ሀገር ወይም ገጠር-ኢትዮጵያ ስለተራራቀ ነው። መብራት አልባው ኢትዮጵያ፤ ምንም የተለየ ስልጣኔን ስለአልሞከረ ባህሉ ጥቂት ተነካካ እንጂ በነበረበት አለ። በእሚያመልከው “ሰላም”፣ ወግ፣ ልማድ፣ ዘዴ፣ ከመንግስት እና ከተሜ-ሀዘኔታ ርቆ፣ ተደብቆ፣ በነበረበት እንደነበረ አለ። ለወደፊት ቢያሰጋው እንጂ፣ ባህሉ “ጌጡ” ወይም የህላዊው ፈረስ ሆኖ እየጋለበው የእማያውቀውን የጊዜ ሽግግር በቸልታ እየአለፈበት እንደ ነጎደ አለ። ሁለተኛ፦ “ከተሜ” ኢትዮጵያ፣ በእማይያዝ እና እማይጨበጥ አኗኗር፣ በአልተገባ ትግል ባርነት በመሠለ የአኗኗር ቸልታ ከእዚህ ነጭ ኢትዮጵያ ተሰንትሮ ለብቻው ቀርቶ አለ። የእራሱ እውነት በዝቶ እየተለየ መምጣቱ ተቋቁሞ አለ። የስነውሳኔ፤ ስነምጣኔ፣ አስተዳደር፣ “መዘመን”፤ ጉዳይዎች ሁሉ የአንዣበቡት በእዚህ ክፍለ ኢትዮጵያ ነው። የሀገር ባህል ከገጠር ባህልነት ተፋትቶ አለ። ያ የግድ ለመሆን እሚጠበቅም ነበር፤ እንደ ሆነው። የሀገር ባህል ከገጠር እንደ ህዝቡ ሳይፈልስ፣ ከተሜነት አዋጪ ባህል ሳያዳቅል ወይ ሳይፈጥር፣ የተዳከመ ብሔርአዊ ዝግመት በተጨባጭ ግልጥነት አለ። ብሔርአዊ አባትአዊነት – ጠቢ ትውልድ እሚከተለውን እሚከተለውን ዘርፈ-ሙሉ ሀገርአዊ እና ኑባሬአዊ (existential) እንቅስቃሴዎች ፈለግ አስማሪ እና ተዪ እውነት – የዘመንን ጎህ እየቀደደለት ለትውልዱ አያስረክብም፤ አያልፍም። ግድየለሽነት መልህቅ እስኪጥል፤ ባይተዋር ታንኳዋን መሰሏ ሀገር በገብረህይወት ባይከዳኝ ለዛሬም ዘመን-አይሽሬ ትንቢት በሆነው (ም.፦ ፕሮፍ. አለምአየሁ ገዳ፤ “የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ መሰረታዊ የኢኮኖሚክ አስተሳሰቦች (ገ.19፤) እና ) ትንቢት እንደ ወደቀችው ወደ በለጠ ውድቀት ትሄድ አለች። ከብዙዎች መሀከል፤ የአልተገናኘውን ከአልተገናኘ የእማያገናኝ የሆነውን ባህልን ከህዘብ እና ጠቢው ማገናኘት የሺህመትዎች ታሪክ የአስረፈደው እውነት ነው፨

———-&———

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s