Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ስለ የ ቋንቋ እንግሊዝኛ ትምህርት በተሻለ ፍኖት እንዲሰጥ ማሠብ

About how Ethiopians shall revisit their education system to start new ways to teach English language in a better way, such as intensively for a whole and secluded year.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, August 7th 2021

በአለፉት የተከማቹ አስርታት ኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት ውስጥ፣ እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት እንደ ተለመዱት ይዘት ትምህርትዎች እለትከእለት ተታክኮ ይሰጥ ነበር። አሁንም። ነገርግን፤ በቂ ክሂሎት ለተማሪዎች አይሰጥም። ምንአልባት አማራጭዎች መሀከል፤ አንዱን ብቻ እንቀንጭብ።
በአንዳች የታዳጊነት ዘመን ላይ፤ ቋንቋ ትምህርትዎችን፣ በግለት (intensively)፣ ማስረከቡ የእሚመከር ነው። የእማይጠየቅ አንድ አስከፊ እውነት አለ። እንግሊዝኛን ከ A B C እና መወጠኛ ተግባቦት ክሂሎትዎች አንፃር፣ እስከ አራተኛ ክፍልዎች ይማር አሉ። እጅግ መሰረትአዊ እንግሊዝኛን የእሚላቀቁት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሲገቡ ወይም ሲያጠናቅቁ አካባቢ ነው። ዳሩ፤ መሳለመሳ አስቀድመው መወጠኛ እንግሊዝኛ ሲማሩ እና አምስተኛ ክፍል ሳሉ የተወሳሠበ ይዘትአዊ ትምህርትን በእንግሊዝኛ ይማር አሉ። ለምሳሌ፤ social studies, basic science, maths, civics, sport, ,ወዘተ.። የአምስተኛ ክፍል እንግሊዝኛ በእራሱ ተራ መነሻ ክሂሎትዎችን የእሚሰጥ ሆ ሳለ፣ ሙሉበሙሉ ትምህርት በእንግሊዝኛ ይቀበል አሉ ተብሎ ታስቦ አለ።
በመሰረቱ፤ ቋንቋ ትንሽ ጉዳይ ነው። በየቱም ቢማሩ ዋናው ይዘት ወይም ቁምነገሩ ነው። ነገርግን፤ የእሚያውቁትን መግባቢያ ይዘቱ ሊፈስስበት ከአልተከተለ፣ ትምህርቱ በቁምነገሩ ይበደል አለ። ተማሪዎቹ ተመርቀው በእውቀት ግን ጎደሎ ይሆን አሉ። ይህን አለመስማማት ከቋንቋ ግጭት ለማስታረቅ፤ አንዱ አማራጭን እንይ። ይህም፦ እንግሊዝኛን በጋለ አቀራረብ አስቀድሞ መስጫ መንገዱን ማመቻቸት ነው። አራተኛ ክፍል የጨረሱ ተማሪዎች፤ ሙሉ ግማሽ አመት በእንግሊዝኛ ጥናት እንዲቆዩ እና በከፍተኛ መጠን እንዲያልፉበት ማድረግ አዳኝ መፍትሔ ሊሆን እሚችል ነው። ወይም አመቱን በሙሉ የቋንቋ ትምህርትዎችን (አማርኛ እና እንግሊዝኛ) በማስተማር፤ በቀጣይ አመትዎች የቀለለ ተግባቦት በመከወን፣ ይዘትዎችን በተፋጠነ መንገድ ለማድረስ እሚቻል ነው።
አሁን የአለው ተገቢ የእማይመስልን መንገድ ለማስተካከል፤ ይህን ወይም ይህን መሰል መንገድ መከተል የድሚገባ ነው። ይህ አማራጭ የለውም። የተሻለ ጥራትን ከተማሪዎች ለማግኘት፣ እንግሊዝኛን በተለየ መንገድ ማስተማር ተገቢ ይሆን አለ። እእግሊዝኛ፤ እንደ አንድ ብሔረሰብእ ቋንቋ በኢትዮጵያ አይነገርም። በትምህርት ተቋምዎች እና አለምአቀፍ ግንኙነትዎች እንጂ፣ የበዛ ህላዌ የሌለው ቋንቋ ነው። በልጅነት ልጅዎችን ከትምህርትቤት ውጭ የእማያገኝአቸው ቋንቋ ነው። ይህ ከሆነ፤ የእሚሻለው፤ የተሻለ ትልምአግጣጫ (policy)፣ ለቋንቋው መፍጠር ይሆን አለ። በታዳጊነት አመትዎች አንድ ዘዴ በመፍጠር፤ እንግሊዝኛን ለብቻው በበለጸገ መንገድ ማስተማር አስገዳጅ ከሆነ ትርፉ ብዙ ይሆን አለ። አስራሁለት አመትዎችን አንድ ቋንቋ ለመልመድ ተማሪዎችን ማስቸገር ስነአመክንዮአዊ አይደለም። ቋንቋን በአጭር ጊዜዎች ለመልመድ የእሚቻል ነው። ይህ ከተከወነ፤ ለምሳሌ እስከ ስድስተኛ ክፍል በአለው ወቅት በጋለ አቀራረብ እንጊዝኛን የእሚማሩ ከሆነ፤ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ እንግሊዝኛ በተለየ መንገድ ተወሳስቦ መቅረብ ይችል አለ። ለምሳሌ፣ የቋንቋ እና ስነጥበብ፣ English and Literature, Ethiopian Literature in English, ወይም ሌላ ተዛማጅ እና አእምሮ አበልጻጊ ትምህርትዎችን በመስጠት መጓዝ የእሚቻል ይሆን አለ። ያ፤ የእንግሊዝኛ አቅም መወሳሠብን ከተጨማሪ ትምህርት እና አስተሳሠብ መጎል አያይዞ ይቸር አለ።
እንግሊዝኛ አቀራረቡን ዳግ-መመልከት አለበት። በመሰረትአዊ ክሂሎት ደረጃ 12 አመትዎች ተሰጥቶ ሳያልቅ በጊዜ ወደኋላ ጉዞ በመከወን ተመልሶ ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ በማድፈጥ ከአማርኛ በቀረ ለሁሉም ትምህርትዎች እውቀት ማስተላለፊያው መንገድ ይሆን አለ። በእንግሊዝኛ ብቻ ስለተወሳሠብ ጥበበምርምር (science) – ለምሳሌ “environment, population, geographical and so on studies” – አምስተኛ ክፍል ሲማሩ፤ እንግሊዝኛ ግን እንጭጭ ክሂሎቱን በጎን ይሰጥ አለ። ይህን እማይመስል እና ከምንም በላይ የአላተረፈ አካሄድን ዳግ-መቃኘት በቋንቋስ ብቻ ሳይሆን በተሻለ የይዘት እድልም እንደ ተገለጠው ሊመጣ የእሚችል ስለሆነ ጉዳዩ መንታ አገልግሎት አለው። ኢትዮጵያ በትምህርት ስርአቷ፤ ቋንቋን አሻሽላ በማቅረቢያ መንገድ በመዘየድ የይዘት ምቾት እና የተጨማሪ ይዘት ክፍተትንም ማበጀት ትችል ዘንድ አለች፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s