Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

Introducing Child Psychology And Homeschooling within the Ethiopian Society: As A (and the) Way Out በ ኢትዮጵያው ማህበረሰብእ ደቂቅ ስነልቦና እና ቤትትምህርትቤት ስለማስተዋወቅ፡ እንደ መውጫ (እና አንዱ መውጫ)ው መንገድ

barrbarreAbout how Ethiopians shall consider homeschooling and child psychology as a way of, or alternative for, patching the barren education system.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 5th 2021 GC.,

የአንቀላፋ የኢትዮጵያ ስርአተትምህርት እና አንድ አማራጩ

የገዳ ስርአት፣ የዜጋዎቹን ህይወት እሚወስደው በህይወት ንብርብርአዊ መሰላል እና ሚና ነው። ከተላላኪነት እስከ ሉባ፣ ዜጋዎችን ሸንሽኖ፣ በእድሜ ሚዛን እሚዳኝ ነው። የገዳውን ስርአት የእሚያንፀባርቅ የትምህርት ስርአት ደግሞ በሀገርአችን አለ። እድሜዘመንን በመሰላል ለማሸጋገር የአክል በቁንጽል አስተምህሮትዎች በእየዘመን እያሸጋገረ ወደ ኅዋአዊከተማዎች (universities) ይደረስ አለ። ከእዛም በእማያበቃ ትትረት፣ ወደ ስራ ፈላጊነት መሸጋገሩ ደንበኛው እውነታ ሆኖ ሰላሳ አመትዎች አካባቢ ተቆጥሮ አለ። እድሜዘመንን በትምህርትአዊ ሚና በመከፋፈል ማራመድ እንጂ፣ እውቀት ደረጃን ማብሰል አይከወንም። በውጤትም፤ የተማረ ጉልበት በሀገር ደረጃ ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ብዙዎች እማይደግፉት እና እሚሳለቁበት ሀገር ሆኖ አለ። እሚመስለው እንደ “ኢጋሊታሪያን” ማህበረሰብእ መገለጫው ገዳ ስርአት፤ እመሜዘመንዎችን ለማደላደል እንጂ ለልህቀት የእማያደርስ የስርአተትምህርት እንደከበበን የአለን መሆኑ ነው።

አማራጭ እውነታዎች መሀከል፤ እማያወላዳው የትምህርት ጥራት በስነስርአቱ፣ ይዘቱ እና ከምርቃ በኋላ በአለው አኗኗር መከወኑ አንዱ ትልም ነው። ያንን፤ በብዙ መንገድ በብዙ ይዘት እሚመለከቱት እንደአሉ፣ እሚቀንስ ጉልበት እና ተዘውታሪነት የአለውን መረሳት የእማይገባውን አንድ መንገድ ግን ለመቅደድ እዚህ እንነጋገር – ቤትትምህርትቤት (home school)።

ቤትትምህርትቤት ምን፣ ለምን እና እንዴት?

ቤትትምህርትቤትን ሀገር ውስጥ እሚገደደውን ክብር እና ጆሮ እንኳ ሲሠጥ አንመለከትም። ቢበዛ ቤትአስጠኚ (home tutoring) ትልቁ የቅርብጊዜ ወሬአችን ነው። ከእዛ መስገግ እና መንዘርፈፍ እሚችል ሃሳብ፤ ከእዛ በተሻለ ውጤት እና አቅምሙም፣ እሚያቀርብልን ሆኖ ቤትትምህርትቤት አለ።
ቤትትምህርትቤት ማለት ቅጽአዊ (formal) ስርአተትምህርት ይዘትን እና ሂደትን በቤት ውስጥ፣ ኢመደበኛ (non-regular) በሆነ ግልአዊ (privet) አያያዝ መከወን እና ልጅዎችን በእራስ ምርጫ ልህቀት (excellence)ን ማስተማር ነው። ለምን ይብለጥ?
በተለይ ታዳጊው ልዩጎበዝ (prodigy) ከሆነ፤ በሰነፍ የስርአተትምህርት እያንቀራፈፉ፣ ማባከን ተገቢ እና ፍትሕአዊ አይሆንም። በበለጠ መብቃት ህፃኑን ለማሳደግ ይህ እሚፈቀድ ስራ መሆን አለበት። ሁለተኛው አመክንዮ፤ ልጁን በበለጠ ኃላፊነት ወስዶ ወደ ልዩ ጉብዝና ለማምጣት እሚከወን ጥረት እና ምኞት ነው። ሶስተኛ፣ የአካል ወይም አንድአች ችግር ወደ መደበኛው ትምህርት በቀላሉ እማያመላልሰው ከሆነ፣ በቤትትምህርትቤት ማሳለፍ እና ብቁ ማድረግ እሚመከር እና አማራጭ ነው።
በደፈናው፤ በቤትትምህርትቤት አያያዝ፤ የተሻለ አቅም እና ብስለትን፣ ቀድሞ በእድሜ መዘጋጀትን፣ ከእዚህ አያያዝ ማግኘት እሚቻል ሲሆን፣ በልዩ ስብእና ወይም ልዩአዊነት (specialization) አስተኩሮ ለማሳደግም እድል አለው።

ቤትትምህርትቤትን ለመከወን፤ እሚያስፈልገን ምን አለ? ቀድሞ የስነልቦና ዝግጅት እና መቁረጡ ነው። ተከትሎ፤ ስርአተትምህርቱን ማበልጸግ ነው። በመጨረሻ፤ በትጋት እና አመቺ መቼት ማስኬዱ እና መቆጣጠሩ ነው። ወደ ቅጽአዊ (formal) ትምህርት ለመክተት ቢሞክሩ ግን፤ የትምህርት ሚኒስቴር በ2013 ከአወጣው፤ ትምህርትብርሃን ፈርምግባር (initiative) በቀረ፣ አማራጭ የአለ አይመስልም። ያም፤ አራተኛ ክፍል በቀጥታ ለመግባት እሚያስችል የፈተና ስርአተደ አይነት ነው። ለልእለሊቀጎበዝዎች (super genius) እሚሆን የተለየ ስርአት ኖሮ ከፍ ወደ አለ ክፍል መዛወር እሚችሉበት መንገድ ከአለ አይታወቅም። ልህቀት እና ርቀት

ለኢትዮጵያ እሚሆን ከሆነ?

አንዳንድ በሀገረሰቤ ማህበረሰብእ ውስጥ እሚበቅሉ ህፃን ልጅዎች፣ እንደ በዛብህ ቦጋለ – የ ሀዲስ አለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር እንደ አለው፤ በ ለጋ ዕድሜአቸው የቤተክህነት ትምህርትአቸውን ጨርሰው በልዩ ትጋት እና ብስለትአቸው ቶሎ በመማር ትልቅ ማእረግ ይቀበል አሉ። በእርግጥ የመንፈስቅዱስ ፈቃድ ጭምር ቢሆንም፤ ይህን አኳኋን መገንዘብ ግን ለማንም የተገለጠ ነው። ገና በአስር-አስራአንድ ዓመት አካባቢ፣ ቅስና እና መርጌታነት በማእረግ እሚያገኙ ታዳጊዎችን ወደ እየደብሩ ስንሄድ እንመለከት አለን። በጭሩ፤ በለጋ እድሜ በትምህርት በስሎ በመንጠር ትልቁን መሰላል መርገጥ አንድ የተለመደ ገሀድአችን ነው – በቤተክህት ብቻ ተወስኖ እምናገኘው አውድ ቢደረግም።
በአሳለፍንአቸው ሁለት አመትዎች ገደማ፤ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ የአስተማረው አንድ ፍንጭ፣ ልጅዎችን ከልጅነትአቸው ከስርአተትምህርት ውጭ ለምጥቀት ሲባል ማስተማር መሞከር እንደ እሚቻል ነው። ደግ ግርምት ልጅዎችን ለ ናሙና አምጥቶ በተለያዩ መገናኛብዙሃንዎች አስመልክቶ ነበር። እውቀትአቸውን እሚያለማው፣ በመደበኛው ትምህርት ሳይሆን፣ በላቀ ጥረት ነበር። እርግጥም፤ እሚያበረታታ ናሙና ውጤት ማስመልከት ጀምሮ ነበር። እንደእሚቀጥል እና ገና እንደጀመረው ተናግሮ አለ። ለ ነገሩ፤ ይህ የሆነው ጠቢ-ኢትዮጵያን በእዚህ መንገድ የእምስላት ስለሆነች እና ስለእምተጋ ነው ብሎ ያንን ስለከወነ፤ ተመሳሳይ ኢላማ ያላነጣጠረ፤ ይህን መከወን እሚችል አይሆንም።
በደፈናው፤ ለታዳጊዎች እሚሆን የተለየ ፈጣን እና ይዘትአማ ትምህርትን ማዘጋጀት እሚቻል እና ተቀራራቢው መሀከልአችን እሚገኝ ነው። የሞከሩ፣ እውነትም ቤትትምህርትቤትን የአዘጋጁ ዜጋዎች ከአሉ አይታወቅም።

ወደ እነእርሱ ለመቀላቀል ግን ሁለት ነገርዎች የአስገድዱን አለ። አንደኛ መደበኛው ትምህርት የወደቀ በመሆኑ ነው። በአስራአምስት አመት እና በላይ ከአለመውደቅ ክፍልዎች እየተረማመዱ መማር፤ እንግሊዝኛን እየተጠቀሙ ሆነለ እንኳ በቅጡ ቋንቋውን በቅጡ እማይጽፉ፣ እና እማያነብቡ ልጅዎችን አፍሪ እየሆነ እንደተመለከትንው ነው። በይዘትም አያበስልም። በስነምግባር እና ሀገርበቀልነት ጉዳይዎችም ስረወአተትምህርትአዊ ክለሳ እና ክፍተቱ ቋሚ ወሬ እንደሆነ ነው። እነእዚህን ሁሉ ማሸነፊያ አማራጭ ልጅዎችን በቤትትምህርትቤት ማበልጸግ ነው። የፈለጉትን መራርጦ ማስተማር በመፍቀዱ ይህ እረጂ ነው።
ሁለተኛ፣ ሊቅ እና ፈጣሪነትን በልጅዎች ለመክተብ ነው። ከመንግስት ትምህርት ስርአት የወጡ ዜጋዎች ትልልቅ ደረጃዎች ሲደርሱ መመልከት ዘበት እየሆነ ትውልድ በማለፍ ላይ ነው። በግል ትምህርትቤትዎች መስፋፋት ጥራት ከመጣ በእሚል ብዙ ተስፋ ማህበረሰቡ ተስፋ የአደረገ ቢሆንም፤ በሃያታት (two decades) ከፍተኛ የግል ትምህርት ንግዱ አድጎ አለ። ግን፤ የልዩነት ፈጣሪነቱ በይዘቱ ሳይሆን ቀርቶ ተመልክተን አለ። ወለእዚህ፣ የመንግስት ቸልታ ተቀርፎ ቢያንስ ፍቅር እስከ መቃብርን እሚያውቅ ስድስተኛ ክፍል ተማሪነት እድል እስኪመሰረት እንኳ፣ በግል በማስተማር ልጅዎችን በቤት ማበልጸግ አንዱ አማራጭ ነው።
ተደራራቢ ሽልማትዎች አሉ። ከስነምግባር፣ ከእሚውሉበት ስፍራ ወዘተ. የተነሳ ከመበላሸት እሚቆጥብ ስልትም ነው። ልጅዎችን በጠበቀ ቅርበት እንደ ታቀደ አሳድጎ የማግኘቱ እድል ይበረታ አለ።

መነሻው ወይም ራስቻይ አማራጭ

አንድ ሌላ እውነታ የእዚህ ትትረት አካል አለ። ይህም ደቂቅ ስነልቦና (child psychology)ን ማስተሳሠሩ ነው። ልጅዎች ከአስተዳደግአቸው እራስን ለመሆን ተበረታትተው እሚያድጉበት ልማድ በአማካይ ማህበረሰቡ የለም። ያንን ማከም አስገዳጅ ነው። ያ ሲሆን ቤትትምህርትቤት ኢላማን አጋዥ ወይም መጋቢ ጅማሮን እንረከብ አለን።
ህፃንዎችን በአእምሮ አቅም ዝግጅት አበልጽጎ ለማሰናዳት፣ ለብቻአቸው በበዛ ጊዜ በመተው፣ ከንክኪዎች በቀነሰ እና ከመጋለጥ በተቻለ አቅም በሰወረ መንገድ እስከ ሶስት እና አራት አመትዎች ማሳደግ፣ አእምሮአቸውን ከፍቶ ብልህ አድራጊ ክሂሎትአማአዊነት (technique) ነው። ቢያንስ በእዛ ደረጃ ወደ ትምህርትቤት ማስገባቱ፤ ለተሻለ ብስለት እድል ይሆንአልአቸው አለ። ከተበረታ ደግሞ፣ ወደ ቤትትምህርትቤት በማሻገር፣ በበረታ ደረጃ ልጅዎችን ማሳደግ እና ሀገርን በልሂቅ ዜጋ ምርት ማገዝ እሚቻል ነው፤ ከቤተሰብአዊ ስኬቱም በተያያዘ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s