Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ቋንቋ አማርኛ ፈጣሪነትን አይጠላውም

How Amharic has to make use of creativity count in its transformation.


ባለቤትነቱ የመሀከልሀገሩ የሆነው ቋንቋ አማርኛ፣ ከገጠሙት ቁልል መመሰቃቀልዎች አንጻር እምንመለከተው አንድ እማያጠራጥር ነገር፣ ፈጠራ ከአገኘ እሚጠላ አለመሆኑን ነው። የትእምርተጥቅስዎች፣ ቃልዎች፣ ሰዋሰው፣ በግልጥእንደእሚታወቀው ገበታፊደልዎች፣ ወዘተ. ችግርዎችን ለማስተካከል ወይም ለማሻሻል ወይም ታካይ ለማድረግ እሚያስችሉ ነገርዎችን ማከል አስፈላጊ እና አንድ ስምሪት ነው።
ለምሳሌ፤ ይህን እርእስ በተይ ሰንጥቆ የአስነፈሰው (get it inspired)፤ የ ዳኛቸው ወርቁ ተወዳጅ-አማርኛ-ልብወለድ አደፍርስ ነው። በልብወለዱ እሚገኘው የአማርኛ ደግ መጠን ውበት እንደአለ ሆኖ፣ ለእዚህ ነቁጥ፣ መነሻ የሆነው የሰረዝ (ጭረት) አጠቃቀሙ ደግሞ አለ። ሠረዝ በአደፍርስ በከፍተኛ ድግግሞሽ የእሚቀጠር ሲሆን፣ አንዳንዴ ከለመድንው አገልግሎቱ የሰፋ ሆኖ የቀረበ ሊመስለን እንገደድ አለን። ያን፤ ለአረፍተነገሩ ፍሰት የተዋበ የመንቆርቆሪያ አማራጭ ሲሠጠው እንድንጠረጥር ስለእሚጋብዘን ነው። ይህ ከፍተኛ ዋጋ ለአማርኛው ውበት ቀኝአውሶት ለመመልከት እንገደድ አለን።


…. (የተሻለ ዝርዝር በልብወለዱ የጭረት አጠቃቀም እና ለቋንቋው አቀጣጠሩ የወለደለትን ልዩነት በተሻለ መርምሮ ለማቅረብ መመለስን እስክንከውን በመጠቆሙ ብቻ እንገታ) …


ይህ ከሆነ፤ አማርኛን በእንዲህ የአለ ፈጠራ ለማገዝ መሞከሩ ትልቅ ዋጋ እንደእሚያስገኝ ለመመልከት ተገድደን እንሳብ ዘንድ ነን። የአደፍርስን አፃፃፍ ለማጥናት በሰፋ መንገድ ለማወቅ እንዲቻል እና ተጠሪ ማለትም ግልጽ ጽንፀሃሳብ ለመውለድ ጥሪው እንሆ በእዚህ ተጋብዞ፤ ወደ አጭሩ የውይይት ሃሳብ ድምዳሜ እንመለስ። ይህም፤ አማርኛ ቋንቋ በከፍተኛ የልህቀት ደረጃ ገና የአልተዘጋጀ ነው ከእሚለው የእሚነሳ ነው። የመሀከልሀገር የዛሬው አማርኛ የተለመደው በመደበኛ ውይይትዎች፣ ልውውጥ እና ለደንበኛ ምርምር ወይም ውስብስብ አገልግሎት ስለአልሆነ የቋንቋ-ጉልበቱን በደግ ደረጃ አልመሰረትንም። ይህን አወዳደቅ ለማገዝ አንድ ዐቃፊዣንጥላአማ (overarching) ክፍተት እንመለከት ዘንድ ጉልህ ነው። ያም፤ በብዙ ዘርፍዎች፣ አዲስ ልህቀት – ልክ እንደ ደረጃ (standard)፣ ዝግመት፣ ወዘተ – ለቋንቋው ማበጀት እሚፈለግ መሆኑን ነው። ከእነዚህ መሀከል አንዱ እና ዋነኛው የቋንቋ ባህል እና የአጠቃቀም ማእከልአዊነት ማበጀት ነው። ያንን እንዲከተል ደግሞ፣ የቋንቋ ቀለም ከእየተገልጋዩ ሊበጅ እሚችል እንደሆነ ሁሉ፤ እንደ ዳኛቸው ወርቁ ደግሞ ፈጠራንም ማሰብ አንድ ጉዳዩ ሊሆን እሚቻል ነው። የቀለም ነገሩ፤ የቋንቋ የግል አቀጣጠር ነው ብንል፣ ሰው እንደ አንድ ልማድ አማርኛን ደጋግሞ ከቀጠረ፣ እምንመለከተው የቅንጅት እና አቀራረቡ መደጋገም የአማርኛው ቀለም ነው። ያ ለቋንቋው እድገት አንድ ገፀበረከት ሊያመጣ እሚችል ነው – የተሳካለት ብስለትን ከአስመለከተን። ያ ሌላ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ዳኛቸው ምሳሌአችን እና አነሳሽአችን በአደፍርስ በተለይ መጀመሪያ አጋማሽ የቀጠረው አማርኛ እንደ እሚያጠምድ ውበት ማራኪ ነው። የግሉ የአማርኛ ቀለም ልንልለት እንድንችል እነስብሃት ገብረእግዚእአብሔር እንኳ መስክረውለት አለ። የእኛ ነጥብ ግን ያ እንደአለ፣ አማርኛውን በግሉ መብቃት እንደተገለገለው፣ በእዛም አብነት ሆኖ እንደቀረው፣ የፈጠራው ነጥብ ደግሞ ንጥል ስኬቱ ነው። ያም፣ ለአማርኛ የተላከ ስጦታ ሊሆን ነው። ተገልጦ ሊመረመር አስገዳጅ ነው።
አማርኛን በፈጠራ የአገዘ ልክ እንደእዚህ የተገኘ እንደሆነ፣ ነገረስራውን መመርመሩ፣ ጠቃሚነቱ ደግሞ ከተስተዋለ ለሰፊ እርባታ እና ለቋንቋው እገዛ ወይም ይፋ ቀጠራ ማምጣቱ ክወናው የእሚቀጥለው ስራ ነው። ምንአልባት፤ አማርኛ የሊቅ ቋንቋ እንዲሆን በተለይ፣ ወይም የቀለለ እና የተመቻቸ መደበኛ ቋንቋም እንዲሆን ከአስፈለገ፣ ፈጠራዎችን አምጥቶ ወደ ልሙድ ደረጃነት ማሳደግ አስፈላጊው ቀጣዩ እጅግ ትንሽ ቤትስራ ሊሆን እሚችል ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s