Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

የበላይ ማናዬ አዙሪት ዘአልፋ፡ ጨለምተኛው ልብወለድ አሁንም ቢሆን በደንብ ማስተማር ይቻለዋል

A fan review of Azurit Ze Alpha, a debut novel by Belay Manaye.

A potential murdered; so oxymoron it is. It is plotless plot. And, a no-story story. Quite self-contradictory and a theme that is too-archaic-and-full-of-fool-judgments. At its best no-that-much and nearly nothing-at-all tale. Itself as embarrassing illusion as the null illusion in it. Simply, and in conclusion, a-not-helping-at-all too outdated telling.

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 2013 ዓም፨ (ከእዚህ ቀደም ብሎ የተዘጋጀውን ሂስ እዚህ የአግኙ። ግን እሚመከረው ይኽኛውን የታደሰ ወይም ሁለተኛ አርትዖት (second edition) ፅሑፍ ማንበብ ነው።)

የበላይ ማናዬ፣ የ፪፼፭ ዓም. ልብወለድ፤ አዙሪት ዘአልፋ፣ እምቅ የድርሰት አጻፃፍ ክሂሎት እምቅአቅም እንደተደበቀ ያሳይ አለ። እንደአለመታደል፣ በአይነተኛነት ልዩነት-እማያመጣ፣ እና እማያግዝ፣ ጭብጥ፣ ከአልተጎነጎነ ሴራ ጋር በአበሳጭነት ተዳብሎበት የቀረበ ነው። እጅግ ቀላል አማርኛ አጠቃቀሙ እና የእማይከብድ – ስለእዚህ ዉብ – ስልተ አተራረኩ፣ ተወዳጅ ወይም ቢያንስ ተደጋፊ ቢሆንም፤ አረምነቱን ቢታገሱ እንኳ የማያድግ ትርክቱ እና ማቋቋም ስለአልሞከረው የማይገኘው ሴራው፤ በተቃራኒ-ትርጉም (reading the opposite) የሚያስጨብጠው ህያው የሆነ ጠቃሚ መልእክት ግን አለ። ከድል ብቻ ሳይሆን ከሽንፈትም – ከሌላው ዉድቀት – መማር ይቻላል በእሚል ብልሃት። ትልቅ አንድ ብሔርአዊ ችግራችንን እምንዳሥስበት እና እምንወያይበት ልብወለድ እናድርገው። ጭብጡ ቢያንስ ያንን ሲያስችለን፤ ዋና ባናደርግአቸውም፤ ሌሎች አላባአዊያንም አስተማሪ እና እንዲሁ መማማሪያ ስጦታ አልአቸው።
ቀድሞ፦ በአጭሩ ሴራው ሲቆነጸል። አብርሃም ምናለ፤ አዲስስአበባ ኅዋአዊከተማ (university) ውስጥ፣ በጭምት እና ቁጥብ ጸባይ የህግ ተማሪ ሆኖ፤ በመምህሩ ዶክተር አልፋ አስጨናቂ የሚመራ ሠላሳ አመትዎች የቆየ አዙሪት እሚሰኝ ህቡዕ ማህበር (secret society) ለስንት አመት እንደሆነ ባይታወቅም ተቀላቅሎት ግን የአግዝ አለ፤ ስውር ተቋሙ ለሀገር እንደ ደግ-አሳዳጅ (vigilante) ይንቀሳቀሣል።
ተቋሙ፤ የህዝብ ድምጽ በስነውሳኔ ምርጫዎች (political elections) እንዲከበር ለማድረግ በደርግ ፲፱፻፸፭ ይመስረት እንጂ፣ በዘመንዎቹ የአደረገው፣ ምንም ሳይገለጥ ብቻ አሁን ግን፤ አልፋ በመንግስት የደህንነት ሠራተኛ አቶ እርገጤ በላቸው ‘ድብቅ ድርጅት ይመራ አለ’ ተብሎ መነፍነፍ ይጀመርበታል። እጅግ በቅርቡ፤ የግብፅ ሰላይ ኢትዮጵያ ሲገባ በማጥመድ ወደ ካይሮ አዙሮ የተደበቀ ተቋሙ በመመለሡ፤ የተሰረቀ ዕርዳታ-ስንዴ ከእነሙሠኛዎቹ በማሰር በህግዘብ (police) እንዲያዙ በማቀነባበሩ እና ምንም ዝርዝሩ እማይገለጥ ግድያዎች በድንበር አካባቢ በመከወናቸው ይህ ምስጢርአዊ-ግን-የሀገር-ረዳት-ተቋም አለ ብሎ እርገጤ ሲያነፈንፈው፤ አልፋ እና አባል ተማሪዎችአቸው መሸበር ጀመሩ።
ለሀገርአቀፉ ስነውሳኔአዊ ምርጫ ፪፼፭ የህዝብ ድምፅ መከበር እንዲኖር አዙሪትዎች ሲዘገጃጁ፤ እርገጤ ደግሞ መምህሩን ከምርጫው ቀድሞ ለማግኘት ከእልህ ጋር ቆረጠ። አብዝተው እና ሁሌም እንዳደረጉት፣ የመንግስት ሰራተኛዎችን ለእራስአቸው እንደእሚቀጥሩት፣ የእርገጤ አለቃን ለድርጅቱ በመመልመል አዘሩትዎች በመልስምት ተዘጋጁ። ዳሩ፤ አዙሪትም ሆነ መስራች መምህሩም ማንንም ኢትዮጵያአዊ አንጎዳም-አንነካም እሚል ምሠሶ መርኅአቸውን ጥሰው፤ እርገጤ በመጨረሻ መምህሩ ላይ ደርሶ ለማሰር ጥይት ሲደገን፣ ተቋሙን ፈልግ የአለው አለቃው ለ አዙሪት በማገዝ እኩል ተከትሎ ታዛዡ እርገጤን በመክዳት ጥይት ደግኖበት ከመታሰር መምህሩን በማስጣል በኩራት አስመለጠው። እና በንጋታው ምርጫ ተከውኖ ውጤቱም አምሮ ሴራው ተፈጸምኩ ይል አለ።
ልብወለዱ፤ የተጠቀሱት ቀኝ ጎንዎች አሉት። አንደኛ፤ ቀላል የአፃፃፍ ስልት አለው። በንፁህ እና የአልተወሳሠበ አማርኛ ፍሰት እሚከበር ስኬት እንደያዘ ይጠናቀቅ አለ። አጫጭር አረፍተነገሮችን ተፈናጥጦ ኮለል ብሎ ወደ ትርክቱ በቀላሉ ይጋብዘን አለ። ወጥ አድርጎት ብልህ አማርኛ አቀጣጠሩ፤ በምንምአይሌ (fair) ደረጃ ይማርካል። ተደራሲ ባለማስጨነቅ ትርክቱ እንዲረከበን የአቅሙን ለልብወለዱ አበርክቶ ሌላ አላባአዊዎቹን እንዲያሰምር ደራሲውንም ይጋብዘዋል። ኋላ እንደ እምናየው ሴራው ሲመጣ ያንን የቋንቋ ስኬቱን የአጠለሽ አለ እንጂ አይጠቀምበትም። ሁለተኛ ስኬቱ፤ የትርክት ገጸእይታ (story framework) አቀማመሩ ላይ፤ በ ብልጽግና አስተዳደር የተዘጋው ጣቢያ አስራት ትመ. ላይ ይሰራ የነበረው ደራሲው፤ ተመሣሳይ እምቅአቅሙን የሳለበት ስኬቱ ነው። በተጨማሪ፤ ስነውሳኔኛ (politician) ሳይሆን የ Ethiopian Herad ጋዜጠኛ ሳለ ይህን የፃፈው ደራሲ ሦስተኛ በጎ ጎኑ፤ የብሔረሰብዎች ተዋፅዖ በገጸባህሪዎቹ ለመፍጠር እና አንድነትን ለማሳበቅ መሞከሩ ነው። ለዘርፈዘርአዊ (multiracial) ሀገር ተደራሲ፣ የቀኝ መልእክት ብልሃት ሆኖለት አለ። አራተኛ፤ ዳሩ ከቶ ከመሳካት ቢሽቀነጠርም፣ የወረቀት አርትዖት ጥንቃቄው ወይም ጉጉቱ፣ ብሎም የስርአተነጥብ አንድ ፈጠራው፣ በተለይ ከሌላ የዘመኑ ብዙ የልብወለድ ጭምልቅልቅ የህትመት ስንዱነትዎች አንፃር፣ እጅግ የአልኮሠሰ “IQ” እንደአለው ያሳይአለ – መበረታታት የአለበት ነው። ሳያበቁ የተጀመሩ ዐረፍተነገሮች መቋረጥ፣ ወጥ-ህዳግ (justify) አለመደረግ፣ የቃልዎች ዝብ-ትየባ፣ የቁምፊዎች ቋሚነት ማጣት፣ የቁምፊ ቁመት (font size) መንዠዋዠው፣ ወዘተ. በአስገራሚ ሁኔታ ከዕድአዊ (manual) የለቀማ ወደ አሃዝአዊ ህትመት ዝማኔ፣ ዘርፉ ቢሻገርም፣ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ምርትዎች ግን እራስአቸውን የኋሊት ማዳጥ አናዳጅ ገላቢ’ ገጸ-ባህሪይአቸው ሆኖ አለ። አዙሪት ዘአልፋን ደራሲው በአልተጨማለቀ መንገድ አሳትሞ ማቅረብ ለመሞከሩ ተገቢ ድጋፍ ይገባው አለ።
እነዚህ ድል የረታብአቸው አዎንታአዊ እውነትዎቹ ልብወለዱን ቢደግፉትም፤ በምንም ልል መስፈርት እንኳ፤ የልብወለድ ጠቅላላ አቅርቦት መሆን አይችሉም። ከእዛ ብቸኛ-ገንቢነት እነእዛ የራቁ ናቸው። ምንአልባት በቀረ ዘርፉን ለእሚያጠናው ወይም ሃያሲ፤ የአለውን አቅም አሟጥጦ መዘርገፍ ከሌለ፤ እምቅአቅምን ማስመልከት ምንም ትርፍ ከአንባቢ አይመዠርጥም። ጭራሽ ቀጣዩን ስራ አላነብብም እንጂ ሌላ ምላሽ አይኖርም፤ እና ለእምቅአቅሙ እምቅአደጋ (Risk) የመሆን ኋኝነትአዊነት (Possibility) አለው።
በእንዲህ እንደአለ፤ ቀጥለን፤ እንደ መነሻ የችግሩ ነቁጥ፤ ሴራውን ብናይ እራሱን የጠረሰ፣ ከምር መደዴ፣ (Mediocre) ይሆንብናል። ለመጀመር የአክል፤ አዙሪት ህቡዕማህበሩ በመላሀገሪቷ ከቶ ከማንም የተሰወረ ምጡቅ ሽልፍኖትአዊ (technologically advanced) ነው። በእየዋሻዎች እና ከርሰምድር ማእከልዎቹ በልዩ-ዘመንአዊ አሠራር እንደ እፀመሰውር የተደበቀ ነው። ንደአልንው ምን ሲያደርጉ እንደነበር አይነገረን እንጂ ፍፁም ተሠውረው ሠላሳ አመትዎች የቆየ ተቋም ነው። በተጨማሪም፣ በእየመንግስት መስሪያቤትዎች እና ጠቅላይሚኒስትር ጎን እሚያማክሩ ጭምር ብዙዎችን መልምሎ ባለስልጣንዎች ተደብቀው እሚሰሩለት ተቋምም ነው። ደካማ ሴራው ግን እሚንጠለጠለው አንድ ከፍተኛ የአሆነ የደህንነት መስሪያቤት ሰራተኛ – እርገጤ – የተከወኑትን ስለሠማ ያለበቂ መረጃ (ገ.147፣ 149) አዙሪትን ሊያገኘው ሲነሣሳ ማስመልከቱ ነው። ይህ እጅግ አጭር ሆኖ በረዥሙ እሚያንከራትተን ዋናው ሴራ ሲደመደም፣ በልብወለዱ እጅግ የቀደመ ወቅት ገና ኩርማን ሂደቱ ጀምሮ (ገ.108፣) ተደጋግሞ የተነሳው (ገ.106፣ 178፣ 190) እና እርገጤን በአለቃው በኩል ወይም በቀጥታ እራሱን በአንድ መንገድ የማስቆም ሀሳብ፤ ያም በመደጋገም “አይሆንም መርኅአችን አይደለም” የተባለ ነበር፤ ብቻ ዞሮዞሮ ሲፈጸም ግን ተደርጎ እምንመለከተው ነው። ዘግይቶ ወደ አነሳው ሀሳብ እሚመጣ በዔሊ ደምብ የተንቀራፈፈ ሴራ፣ ምንም አስተንጋሪ አለመሆን (un-surprising)፣ እና እራሱን ተጣራሽ ነው። አመክዮአዊነት (reasonableness) ያጣ ስለእዚህ “ሴራ እማይሆን ሴራ” ነው። ያ ብቻ አይደለም ሁለተኛ ሴራ ህጻጼ (plot fallacy) አለው። አልፋ መምህሩን ደህንነቱ እርገጤ ቢይዛቸው ወይም መርህ ጥሰው እሱን በአለቃዎቹ ከእሚያስይዙት አርፈው ቢያዙለት፣ እርገጤ ተራ ፍንጭ እንጂ ምንም ማስረጃ አልነበረውም። አንድ ቤቱን ሲደርሱበት እንኳ ቢሄዱ (ገ.175) ቢበረብሩት በረቀቀ ስወራ የተደበቀ በመሆኑ (ገ.98)፣ ምንም አያገኙም። “ከቶ አዙሪት እሚባል ነገር አላቅም” ቢል እጅ ነስቶ እሚተዋቸው ነው። እንኳን ስውር ድርጅቱ፤ ቤተሰቦቹም የት እንዳሉ በደህንነቱ ተደጋግሞ ቢመረመርም ምንም ከቶ አይታወቅም (ገ.58፣ 98፣ 131፣ 148፣ 178፣ 182) ሲቀጥል፤ ሶስተኛው ግልጥ ክፍተት፤ ስውር ድርጅቱ እና እንቅስቃሴው (ገ.30፣ 43፣ 164) በአሰራሩ እሚከፍተው ማስረጃ ስለሌለው እስከ ጀነራል ድረስ ያሉት የ አዙሪት የመንግስት ሰዎቹን ተጠቅሞ እርገጤ ክትትል እንዲተው ማስደረግ ይችላል፤ ልክ ቀደም ሲል አለቃው አቋርጥ እንዳለው (183)፤ ያም ቀላሉ የአላበደ አመለካከት ነው። ሴራው ቀውሶ ግን፤ ተቋሙም መምህሩም መርኁን (ገ.37፣ 107፣ 178) አክሽፈው፤ አንነካውም የአሉትን መንገድ ነክተው፣ ከቶ በማንም ተደርሦበት ለማይገለጥ ድርጅቱ፤ እርገጤን ይነሱበት አሉ፤ ሴራው ፍላጎቱን ጥሶ እርስበእርስ ሀበሻዎችን ሲያነካካ አሳይቶ ይቋጫል።
ይህን፤ ክፍተቱ እና የእሚዳስሳቸው ብዙ የፍሬነገርዎች ላይ ያለው አስተሣሰብ አለመጠንከር እንዲሁ፤ እሚከብድ ዉድቀት ነው። ለምሳሌ በህግ-በላይነት፣ ንጽውሳኔ (democracy)፣ ማህበረሰብእአዊ ንቅዓት እና ተሳትፎ፣ ወዘተ. ዙሪያ እሚነሡት ሀሳብዎቹ እጅግ ያልተብላሉ እና ዝብ ናቸው። በምሥጢርአዊ ድርጅቱ፣ በሀገርአቀፍ ደረጃ ያለው መሰረትአዊ ንጽውሳኔአዊ (democratic)፣ እና ህግየበላይነት ስነስርአት አይጠበቅም። ጥንትአዊው የንጽውሳኔ እና አስተዳደር ፅንሠሀሳብ የታወቁ መርኅዎቹ ግልፀኝነት፣ ንቁ ተሳትፎ፣ ድብቅ ማህበራትን ማጥፋት፣ ጠንካራ ተቋምዎች መገንባት፣ ወዘተ. ናቸው። እነእዚህን በመገንባት ላይ አዙሪት ተቋሙ ቢሳተፍ፤ ወይም በምናብቴ (fantacy) ዘውግ የተለመደውን ከእነእዚህ ስርአቶች ዉጭ አልፎም እሚከሰት ኢፍትህአዊነትን ቢዋጋ መልካም ነበር። ዳሩ፤ ንጽውሳኔን ህዝብ ሳይሣተፈው፣ ጠባቂ ተቋምዎች ሳይመሰረቱለት፣ አመለካከት እና ሩህአማነት (consciousness) ሳይዘምን እና ቅድመንቃትአዊ (proactive) ንቁተሳትፎ ሳይከወን፣ በተደበቀ አንድ ኦዲት እማይደረግ ተቋም እኔ አመጣዋለሁ አስተዳድረው እና እቆጣጠረዋለሁ ማለቱ፤ ከእራሱ ከንጽውሳኔ መነሻሀሳብ ከቶ እማይጣጣም የፍሬጉዳይ ዝብ-አተያይ ያደርግበታል። በመጨረሻ፤ መርኁን ጥሶ እርገጤን እንደ ተነሳበት፣ ተቋሙ ተጠያቂነት ወይም ውክልና ስለሌለው፣ የንጽውሳኔ የበላይ ጠባቂ መሆን አይችልም። ማንም በተደበቀ ድርጅት የሀገር ንቁ ስነውሳኔ ተሳትፎን አይደግፍም። የተደበቀ ተቋም፤ የንጽውሳኔ እና ግልጥ እና ተጠያቂ ስነስርአት ጸር ነው። ያም፤ አለምአቀፍ እሳቤ እና ድርድር እማያውቅ ነው። የምርጫ ጉዳይን ደግሞ፤ በተስተካከለ መንገድ ስለመከወን እና ህዝብአዊነትን ስለማሳደግ ከመስበክ ይልቅ የሀገር ችግርን ወደ ተሳሳተ አግጣጫ በጭብጡ እሚያመጣ ነው። እንኳን የአራተኛው ብሔርአዊ ምርጫ፣ አመት የዘገየው የ፪፼፲፫ ስድስተኛው ብሔርአዊ ምርጫ እንኳን በብዙ ደም ጥቂት እንዲሻሻል ቢገመትም፣ ዞሮ በሰነፈ ማህበረሰብእአዊ ተሳትፎ እና የኃላፊው አስተዳደር ተቃዋሚዎች እስራት፣ የእራሱ የደራሲው የትእይንተመስኮት ጨምሮ የብዙ መገናኛብዙሃን መዘጋት፣ ሰላም እና ደህንነት መጥፋት፣ የምርጫ ተወዳዳሪዎች እስራት እና ግድያ፣ የህግበላይነትየለሽነት፣ እማይጠየቅ እርምጃ በአስተዳደር እንኳ እሚወሰድበት፣ ወዘተ. የተስፋፋበት ኢፍትህአዊ ዐውድ ሆኖ አለ። ይህን መሰል መሰረትአዊ ችግር እሚንበለበልባት የአምባግነና ሀገርን፣ በስነስርአትዎች ስለማቋቋም እንደመሞከር፣ ችግርን ወደ ሰነፈ ተልካሻ አግጣጫ ወስዶ ንጽውሳኔው እና ንቁ ተሳትፎው ቀጥሎ ይመጣ አለ በማለት ማለፉ ስለጉዳይዎቹ የአለው አመለካከት ገና ሀሁውን የአልጨረሰ እንደሆነ የስመሰክርበት አለ። የነቃ ማህበረሰብእ፣ በትግሉ ስነስርአትን ለትውልድ የአስጀምር አለ፣ አዙሪት ዘአልፋ ያንን መረጃ ስቶ፣ እሚሰጠው አማራጭ የአልጎለመሰ-ሰው እይታ ነው። ማንም ሊቀበለው እማይቻለው ድሃ እና ዝብ መነጽር።
ወደ እሚያያዝ፣ ወደ ዋናው ዉይይት እንምጣ። ታዲያ ይህ ልብወለድ፤ ከወደቀበት አብይ ሴራው እና ሰነፍ ጭብጡ፤ ለምን ረብሰጪ ምክክር አናፀድቅበትም?
ይህም፤ ለኢትዮጵያ መሠልጠን አስፈላጊ የእሚሆነንን እና የሥልጣኔ እትብትን ማየት ነው። አዙሪት ዘአልፋ በአተያየቱ ድክመት፤ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ ፀር የሆናትን ጎዳና ተራምዶበታል። ለሀገር ግንባታ፤ አንዱ ይበጅ፣ ሌላይ አይበጅ ብሎ እርስለእርስ መስዋእት መደራረግን እሚያስመለክተን ነው። እርገጤ ምንም መረጃ ባይዝም እንኳ ብቻ ስራውን ለመስራት እና ሀገሩን በደህንነት ለመጠበቅ በታገለ፣ ጥይት በአደባባይ እሚደገንበት እና እሚከዳው፣ ብዙ አማራጭ ትልምን በመተው “ዶክተር አልፋን ሀገሬ ትፈልጋቸዋለች” (ገ.207) በእሚል ሰበብ ነው።
ይህ የልብወለዱ ከፍተኛ ውድቀት ለእኛ ግን ዉድ ስጦታው ነው። አንዱን ተፈላጊ፤ ሌላውን ተቃራኒ ማድረግ፤ ይህ እቅጩ፤ ያልዘመነው የልብወለዱ ከሁሉ የከበደ ዉድቀቱ፤ ለአለን የመከዳዳት እና እኩልአዊ (egalitarian) ማህበረሰብ ያለመፍጠር ኋላቀርነት ትክክለኛ ተጠያቂው ብሔርአዊ ችግር ነው።
አውሮፓ ዉስጥ የዘመንአዊ የዓለም ታሪክ ፈር መቅደድ በጀመረ ወቅት፤ ምንአልባትም ቀደም ባለ ጊዜ ራሱ፤ የህግ የበላይነት፣ የዜጋአዊያን (civilian) አርነት እና እኩልነት፣ እና ለሀገር የሁሉም እኩል ዋጋ መያዝ፤ በተግባር የተጀመሩ ሀሳቦች ነበሩ። ዛሬ በዘመነ ሉልአዊነት፤ እነእዚህ ከቶ አይነኬ እና ህዝብ-መንቀጥቀጥ (public shoke) እሚያመጡብን ዋስትናዎች ተደርገው በባህልነት የተያዙ ናቸው።
ሀገራችን፤ ዘግይታ በመሰረተችው ማህበረሀገራት (The League of Nations) ሳቢያ፣ ዜጎቿን ከባሪያ-አሳዳሪነት አሥጥላ ይህን ረዥም የዘመነ ሀገር በእኩልነት እና ንጽውሳኔ የመገንባት ጎዳና ሀ ብላአለች። መሬት ለጭሰኛ በደርግ ቢመለስም፤ ተፈግፍጎ መሬት በባለቤትነት እሚናፈቅበት፣ በዘውግ ስነውሳኔ መብዛት የተነሳ ብዙ ሀበሻ በሀገሩ እንደሁለተኛ ዜጋ እሚስተናገድበት እውነታ እና ወል ስነልቦንታ (common psyche) የነገሰበት፣ አንዱን እሚያገሽሽ እና በእጅ አዙሪት የአለንጽውሳኔ በአምባግነና እሚኖርበት፣ የብሄረሰብ የበላይነት እና ታናሽነት በግልጥ ስነውሳኔ እሚሰግግበት፣ በብዙ ሚዛን ዝማኔው እና ስነውሳኔው የደከመ እና ድሮ-ቀር እንደሆነ ባለማቋረጥ የተመሰከረበት ሀገር እንደሆነ ብዙ ዳግተመራማሪዎች (researchers)፣ ተቋማት፣ ተቃዋሚ ስነውሳኔኛዎች፣ የየዘርፉ ሀያሲያን እና ዐምድአዊያን (columnists)፣ ወዘተ. እሚመሰክሩበት ነው።
ይህን የሀገር ውድቀት ለማስተካከል ከቅርብ መቼት (space-time) ወዲህ፣ በብዛት እና ስፋት ጥረት ይደረጋል። ዳሩ፤ የልብወለዱ የእዚህን ሰፊ አረንቋ አንድ እሾኽ ነቅሦ ማስተናገድ ቢጨበጨብለትም፤ እረጂ የሆነ መፍትሄን ግን አያቀርብም፤ የለሽረብ ነው። አንድነትን፣ ፍትህን፣ ተገቢውን የአካሄድ-መንገድ፣ መፈየዱን አላሳካም። ጭራሽ፤ ከፊ ነው። እርስበእርስ መነካካትን በሀገራችን እናብቃ ብሎ ለተተኪው አዙሪት አባሎች ሁሉ ያወረሰው መርኁን (ገ.101) ደንበኛ ግለ-ተፃርሮት ፈጽሞበታል።
በተሻለ ጎዳና በስሎ የሀገር ችግር እና ችግር-መፍትሔዎችን በማሻሻል እሚከተል የኢትዮጵያ ኪነእናስነ (fine art) ወራሽ ትውልድ ያስፈልገዋል። የዘርፉን ዐውድ እንደቀደመው “ለመዳኽ የሞከረ ወርቅአማ” ዘመን ማሞቅ ባይቻለንም፤ ቢያንስ እንደቀደመው ትውልድ ምርአዊ-የሀገር-ችግርዎች-ፍተሻ ከዋኝ የልብወለድዎችአችን ጭንቅዎች ሆነው መንፀባረቅ አለባቸው። ያን ዘመን በአቻ ንጽህና አለመከተል ሀገርአዊ የስነእናኪነ ዉድቀትአችንን ለመሸፈን ከእሚደረግ አልፎአልፎ ትትረት መሀከል በሀሴት ብናካትተውም፣ አዙሪት ዘልፋ ግን ጭብጡ ፈር-እሚሰነጥቅ ዘመንአዊ ለመሆን ቀርቶ ጎህ እሚያሽሸብረው እና ወደ ጅራቱ ቢዞር እንደ ግማሽ ዕድሜ እንደ አረጁት ልብወለድዎች እንኳ በርታ ያለ አይደለም። ምንአልባት፤ ከጭብጥ ስንፍና እና አወዳደቁ የተነሣ እምንመኘውን ኢትዮጵያ በጥበብስራዎች ከእሚገልጡልን ልብወለድዎች ዝርዝር መሀከል ድርሽ አርገን አናነሣውም።
አዙሪት ዘአልፋ ከ አደፍርስ ልብወለድ አባትአዊ-ታጋሽ ስኬት አንሶ እየተሳደበም ቢሆን ስለ ማህበረሰብእ በሂደቱ ለመምከር መሞከሩ አንድ ነቁጡ ነው። ግን፣ እንደ ዳኛቸው ወርቁ፤ ተስፋ የእማይታየው፣ ዘመንዎችንም አልፎ መዘመን የአልቻለ ጭራሽ ከእዛ የረገበ ነው። ወደ መሠልጠን ሀገር እንዲመጣ፣ የሉት ስነስርአትዎች ከማስመሰል ወደ ሀቀኛነት፤ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ሊቀምሁርዎች) እንደ እሚለው ህዝብም ከዴንታቢስነት እንደ ተረከበው ትልቅ ሀገር መጣኝ ሆኖ በጥበብ ጎዳና እሚጓዝ እንዲሆን እንጂ፣ ቆሞአሸልቦ እንደ አዙሪት ዘአልፋ መቅረት የለበትም።
መደምደሚያው፤ መሆን እማንፈልገው ብልሹ ጠቢአችን (our erroneous future) መሀከል እርግጠኛ አንዱን ሆኖ በማስመልከት ግን፣ እምንቆጥረው የልኮት (reference) አገልጋይ መሆን እሚችል ልብወለድ ነው።

One reply on “የበላይ ማናዬ አዙሪት ዘአልፋ፡ ጨለምተኛው ልብወለድ አሁንም ቢሆን በደንብ ማስተማር ይቻለዋል”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s