Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

የዘመኑ መደበኛው የኢትዮጵያ ሙዚቃ፡ እርግማንዎች ምንጭዎቹን ስለመጨለፍ (መነሻ ጽሕፈት)

About the nearly drowned Ethiopian recent years (a decade+) flop of its music outputs.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ, May 04th 2021 GC.,


መነሻ
—,
ከ አፈጀው የሸንተረር እና ባንዲራ ጠቃሽ ፍቅረሀገር፣ ሰላም እና ብሔርብሔረሰብዎችን አወዳሽ ነኝ ባይ እንደ ታደሰ መክት እስከ ቴዲ አፍሮ፣ ከመንደር-ወለድ አንድ አሰልቺ ዘፈን ሞክሮ እማይመለስ ዘፋኝ እስከ አምባሰልን አርኪ አቀንቃኝ ወይም ጥላሁን ገሠሰ፣ ከተስፈኛ ባለተሠጥዖ በይዘቱ ከእማያረካው (ያሬድ ነጉ፤ ወዘተ.) እስከ የይዘት ምርጥ ሰባኪ (የከተማው መናኝ መጽሐፍ ላይ እንደ ሰፈረው ጂጂ ሙዚቀኛዎችን ለነገ በእሚጠቅም ሙዚቃ እንደቀየረችአቸው)፤ ከወዘተ. እስከ ወዘተረፈ.፤ የውድቀት እና የከፍታ ንጽጽሩ፤ በኢትዮጵያ ብዙ የሙዚቃ ዓለም ከፍተኛ ውጣውረድ የአለበት እውነት አለ። መንፈስ-ሰባሪ እና መንፈስ-አዳሽ – ለጆሮ እርግማን እና ገጸበረከት – እሚፈልቅበት ዓለመ-ሙዚቃው ውስጥ፣ መደበኛው ወይም ዋናጅረት ሙዚቃው በቅርብ ወቅትዎች (በተለይ ይህ ትውልድ = ዘመነ ኢህአዴግ ከእዛ ደግሞ እጅግ-እጅግ የበለጠ ድኅረ-ሚሊኒየም) ግን ህጸጽዎች እጅግ እየጎሉ እና አስከፊ አወዳደቅ በመከወን እየአሰለቸን እየመጣን ነው። በተለይ ከምርጫ 1997 ወዲህ አምባግነና በዝቶ በስመ-ብሄርብሄረሰብእ-ዕሪና የዘፈን ጥበብን በጎሳ አመለካከት እስርቤት ውስጥ ሸንቅሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ተስፋውን ወርውሮ አሽቆልቁሎ ግሉን አድጦ፤ ከቀደመው በአስጠላ መሽቀንጠር ወድቆ አለ። ያ እንደምን ሆነ? በአጭር፣ ደፈናአዊ፣ ጀማሪ-አሳሽ አድማጭነት በመንቀሳቀስ እውነታውን እንመልከት። መልስዎቹ እራስአቸው ችግርዎቹን ማየት በእራሱ ስለእሚሆን አብሮ መውጫም ጭምር በእዚህ ችግር ዳሰሣ አለ፨


ዐብይ ችግርዎች
ለመነሻነት የአክል ደፈናአዊ ጉዳይዎችን እንመልከት።


ዝማኔ እና ፈጠራ መጥፋት
የኢትዮጵያ ሙዚቃ፣ በአለፈው ሠላሳ አመትዎች በስልት፣ ደፈና አቅሙ፣ አቀራረቡ፣ ብዝሃ-ተፈጥሮው፣ ዝግመቱ፣ ወዘተ. የተስተካከለ ሂደት አንመለከትም። አንዱ ዘውግን ብንነቅስ እዚህግባ ተባይ ዝግመት በቅርብዎቹ እጅግ ጥቂት አስርታት አንመለከትበትም።


ድግግሞሽ ጥበብ
በስልት፣ ሙዚቃ ምት፣ ዜማ፣ አዚያዚያም፣ ድምጽ አወጣጥ፣ ተም. አሠራር፣ ወዘተ. የተደጋገመ አሠራሩ እጅግ የበዛ እና የአታከተ ነው። መኮራረጅ፣ መመዘኛ የአለ ይመስል መመሣሰል፣ ከአጀማመር እስከ አጨራረስ አንድ መሆን፣ ወዘተ. የበረታ እና ቋሚ ችግር ሆኖ እንደ ግንባርስጋ ይታይ አለ።
የጥራት ጉዳይ መሽቀንጠር
በደፈናው የተደጋገመ ስራዎች፤ የህትመት ብዥታዎች (የድምጽ አለመጥራት እና መሰማት፤ የውህደት (mixing) አለማማር፣ ወዘተ. የችግርዎቹ ምንጭዎች ናቸው)፣ የግጥምዎች ውበት፣ የዜማዎች መብሰል፣ የተም. (ተንቀሳቃሽ ምስል) ማራኪነት ወዘተ. የጠፉ ወይም በከባዱ የቀነሱ ናቸው።
ቀላል የመንደር ምርት እና ገበያ እና ጆሮ ተሻሚነት
ዕድልዎች መልካም ጎንዎች አሉአቸው። እድል የአጣውን አጋጣሚ ይሰጠው አለ። በተቃራኒው ከእድል መብዛት የተነሳ የጥራት የለሽ ምርትዎች ይገጥሙን አሉ።
ዘመኑን በሙዚቃው ከእሚገልጡ ነጥብዎች አንዱ፣ ትርኪምርኪ ምርት ከእየጉራንጉሩ መውጣቱ አንዱ ነው። እኛ ባንመርጠው እንኳ፣ የጠራ ግጥም፣ ዜማ፣ ቀረጻ እና ውህደት፣ ወዘተ. የሌለው ምርት በመገናኛብዙሃን አሰልቺ ቃል “ዜማ ግብዣ” ተከትሎ፣ መጓጓዣ፣ በመዝናኛ ሰፈርዎች፣ ወዘተ. ስንጓዝ ይገጥመን አለ።
የተስተካከለ ምርትዎችን ለማግኘት፣ እንዳንችል፣ ትኩረት እንድናጣ፣ ወዘተ. ከአንድ ቢበዛ ሁለት ወይም እጅግ ጥቂት ሙከራዎች በቀር በእማይቀርቡን ግን በልበሙሉነት በትንሽ ጥረት ለመንቀሳቀስ በእማይመለሱ ግለሰብእዎች፣ ገበያው እጅግ የተጨናነቀ እና ጥራቱን የአጣ ሆኖ አለ።
የንቁ አድማጭነት መሠወር
አምራች ዘርፉ እንደ መቀዝቀዙ፣ አድማጩም የአነሰ ዴንታ አምራች፣ በህይወት አገነዛዘቡ ለጥበብ የሠነፈ፣ አዲስ ትውልድ ድርጅት (አትፓ.) (party) በ ኢትመ. (ETV) ሚያዚያ 26 ኛው ቀን በከተሜነት እና መሰረተልማት ዙሪያ ለ 2013 አም. ስድስተኛ ብሔርአዊ ምርጫ ሲፎካከሩ አንድ ተወካዩ አንዲት ጋዜጠኛ ጠየቀችኝ ብለው እንደተናገሩት፤ አዲስአበቤ ጭልጥየአለ ድባቴ ላይ እና ድንዛዜ ላይ ነው ብለው ነበር። መንግስት ኑሮ በማስወደዱ፣ መኖሪያ እና መጓጓዣ በመወደዱ ወዘተ. ብለው ስነውሳኔአዊ (political) ወቀሳአቸውን ቢያቀርቡም፣ ደፈናው የእኛ ልኮት (reference) ግን፣ ህዝቡ እንደ ቀደመ ትውልድ በንቅአት በምንም ነገር አይሳተፍም እሚለው ነው።
በአኗኗር መድከም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እሚታማ ነው። ባህሉ ላይ ከመዘመን አንፃር ክፍተት አለበት። ያም፣ ባህልን በገጠር አኗኗር እንድንገድበው እና አሳንሰን እና አዛብተን እንድንረዳው በአምባገነን መንግስት ስለተደረግን በተለይ በከተማ አካባቢዎች የባህል ክፍተት የአለበት ህዝብ በኢትዮጵያ አለ። ህዝቡ ከመሰባጠሩም የተነሳ፣ ወጥ የአኗኗር ዘይቤ መቋቋም አልተቻለውም።
አንዱ የእዚህ እውነት መገለጫው፣ የሙዚቃው ዘርፍ ነው። ከቴዲ አፍሮ በዘለለ፣ በትውልዱ የተመረተ እንደቀደመው ትውልድ የበረታ ብሉይ (classic) ዝነኛ ሲመረት አይገኝም። ዘርፉ በትንንሽ ጥረትዎች ጠግቦ የአለው፣ የሙዚቃውን ዓለም ከቁብ ቆጥሮ እሚከታተል ተደራሲ በመቀነሱ ነው። የሙዚቃ ሂሰኛዎች እንኳ ቀንሰው እና ጠፍተው እንመለከት አለን። በከተሜነት እና ሀገርአዊ እድገት ያ እንዲቀየር እምናስብ ቢሆንም ያ ግን እውነት አልሆነም።
በትችት፣ በንቅአት ተሳትፎ፣ በሠለጠነ አመለካከት፣ ውይይት እና ኩነና፣ ህዝቡ ሙዚቃን ሲቀበል እና ዘርፉን ሲነዳው ወይም ተፅዕኖ ሲያሳርፍበት ቢያንስ ብዙም አንመለከትም። የተደረሰበት ሙከራ እንዲሁ ይደመጥ እና ይሽቀነጠር አለ። አብሮ ከውጭ እሚመጡ ዘፈንዎች በቀላሉ ተደራሽ በመሆንአቸው፣ እምብዛም የበዛ አትኩሮት ለተዘነጋው ዘርፍ ከህዝቡ የለም።
ሥነውሳኔአማነት (politicization)
መንግስት አምባግነናን ወደ ጥበብ አምጥቶት ተመልክተን አለን። ይህም፣ ህዝቡን ወደ አልተፈለገ ትልም እንደ ወሰደው ሙዚቃውን ወደ መዝቀጥ አምጥቶት አለ። በብሔርብሔረሰብእዎች አዘፋፈን ላይ ከፍተኛ የስነውሳኔ ትርፍ ታቅዶ ድጋፍ በመደረጉ፣ ዘፈንን ሲያደምጡ እና ሲያወጡ ከጥበብ እና ውበቱ በመፋታት፣ ወደ እዚህ የመንግስት መርኅ መቃረብ ልማድ ሆኖ አለ። መንግስት እና ውሳኔዎቹን እንጂ ሙዚቃውን በልዩነት ማጣጣም ትዝ እማይለን ወይም እሚጎዳብን ጉዳይ ሆኖ አለ። የብሔረሰቡን ማንነት ማንቆለጳጰስ ብቻ እንጂ ጥበብን ማስመልከት በሙዚቃው የለም። የተጨቆኑት አሁን ተንፈላስሠው ዘፈኑ እሚል አንደምታው እንጂ ዉበቱ አያቃጭልም። ምንም ደህና ሙዚቃዎችን ብንመለከትም፣ ይህ የስነውሳኔ በጉዳዩ መጥለቅ ግን ዘርፉን አፍራሽ አናሽ ጉዳይ ሆኖ አለ።
የዘርፉ ድጋፍ እና ዴንታ-ተጋሪነት መቅረት
በመደበኛነት ብዙ ሙዚቃዎች ይመረት አሉ። እነሱን ለማግኘት እንደ አሻ መንቀሳቀስ አይቻልም። መግቢያ መውጫ የለም። ዘርፉን በበላይነት እሚቆጣጠር እና አገልግሎቱን እሚያመቻች የለም። በእተእይንተመስኮቱ እና በእየመስኮተድምፁ (radio)፣ የተገኘውን ዜማ በመልቀቅ፣ በበይነመረብ አገልግሎትዎች የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ፣ ወዘተ. እንጂ በተቋምዎች፣ ከምርአዊ አያያዝ በያዙ ቡድንዎች፣ ግለሰብእዎች፣ ነጋዴዎች፣ ጥበብ አፍቃሪዎች፣ መንግስት፣ ወዘተ. የሙዚቃውን አለም በርትቶ መረጃ ሲሰድር፣ ማህደር ሲያስቀምጥ፣ ዜና እና ጥናት-ምርምሩን ሲከውን፣ ሲያስከውን፣ ተደራሽ ሲያደርግ፣ ወዘተ. አንመለከትም። የእምንሻውን በትግልም እምብዛም አናገኝም። የብሔርብሔረሰብእዎች መዝሙር የተሰኘውን የሁለተኛው ሚሊኒየም አካባቢ የተለቀቀ የቆሸሸ አላማ ቢይዝም ዜማን አስውቦ የአቀረበ ዜማ በበይነመረብ ቢፈልጉ ደራሲውን እና ዘፋኝዎቹን ግን አያገኙም። ቢያንስ በከፍተኛ ደጋግሞ በስልት በመዘርዘር፣ የተገኘ ውጤት የለም። ይህን ስጽፍ፣ በቆየ ወቅት፣ የ ወቅቱ የ ኢትመ. ኢትዮጵያን አይዶል አንድ ዳኛ በግሉ ልጆችን ሰብስቦ እንደ አሰራው የተናገረበት አጭር
የዘርፉ በፍራቻ መናጥ
በስነውሳኔ፣ ማህበረሰብአዊ አኗኗር እና የአልተለመደ መንገድ አፈንግጦ መቅረብ በዘመኑ መደበኛ ሙዚቃ የለም። የመሳብ፣ የማነሳሳት፣ የመማረክ፣ እና መሰል የሙዚቃ ኢላማዎች ከምርትዎቹ ተገንጥለው አሉ።
እንደ ቀደመ ትውልድ፣ በመተቸት፣ በማነሳሳት፣ በመቃወም ወዘተ. መዝፈን ወይም በጥበቡ መንቀሳቀስ ቀርቶ አለ። ወይም ሟሽሾ አለ።
ከዳሌ፣ መደዴው የሀገርፍቅር አብይ ጭብጥዎች አልፎ እሚደመጥ ጠቃሚ ጭብጥ በሙዚቃው ዘርፍ እምብዛም ጉዳይ ተብሎ ተወስዶ የእሚገኝ አይደለም።
የአልተገቡ ጡረታዎች እና ስደትዎች
ተስፋሰጭ ዘፋኝዎች እና ባለሙያዎች፣ ወደ እውቅና እንደመጡ በስደት ወደ ውጭ ሀገርዎች ሄደው በመሰወር ይቀሩብን አሉ። ወይም እራስን ከሙያው በመነጠል የገቡበት ይጠፋ አለ።
የፈረንሳይ አሳሽዎች (አካሌ ዉቤ) ፈልገው ከ25 ዓመትዎች መጥፋት በኋላ ወደ መቅረጫ በመውሰድ የዳግ-ቀረጹት (re-record$) ቃልዎችን አስደማሚው አቀንቃኝ ግርማ በየነ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ መዝፈኑት ትቶት ነበር። እንደ ከአዲስ እንደ ተቀረጸ ግን ውበቱ ሁሉን አስደምሞ ተመልካች ተዋዳጁን (fan) አስደስቶ አለ፤ ይህ ሙከራአቸውም እንደ እሚቀጥል ተጠቁሞ አለ።
ብዙዎች ግን ይህንን ትተውት አሉ። በቤተሰብ በመመስረት፣ በስደት ኑሮ በመስመጥ እና በመመቻቸት፣ በቸልታ፣ ወዘተ. ደግ ከዋኝ ሆነው ይጠፉ እና ይቀር አሉ። ከላይ የአልንው የህዝቡ አድማጭነት በመሟሸሹ፣ የዘርፉ ነጋዴዎች አለመበራከት እና አለመብዛት በመሆኑ፣ የሰነፈ ጥረት ከሌላው ወደ ተለዩን ደህና ሞካሪዎች ሳይደርስ ይቀረን አለ። አሳታሚዎች፣ ተቆርቋሪዎች፣ ተዋዳጅዎች፣ ነጋዴዎች፣ ተቋምዎች፣ ክበብዎች ወይም ማህበርዎች፣ ሃያሲዎች፣ ጋዜጠኛዎች፣ መገናኛብዙሃንዎች፣ ወዘተ. ተፅዕኖ መከወን ላይ ስለእማይገኙ የአጠረ ትትረት እዚህ ችግር ዙሪያ ሀገር እየጎዳ እንመለከት አለን።

ዝርዝርዎች
ዝማኔ እና ፈጠራ መጥፋት
አምባገነን መንግስት እንደእሚታመጽበት፣ አብዮት አስተዳደርን እንደ እሚቀይረው፤ ሙዚቃ በአብዮት የእምትናወጥ ናት። አንድ ዘውግን በብዙ መንገድዎች ማዘመን የተለመደ ዓለምአቀፍአዊ ጉዞ ነው። ከመሳሪያ፣ ከአረዳድ፣ ከአጨዋወት፣ ከአዘፋፈን፣ ከአዚያዚያም፣ ግጥም ሁሉ፣ በተም. (ተንቀሳቃሽ ምስል)፣ ወዘተ. ሙዚቃ ከስሩ እየተመነገለ እየተለዋወጠ በማያቋርጥ ዝማኔ እንደተጓዘ ነው።
ይህን፤ በሌላው አለም እንመለከተው አለን። ሀጀድነቱ ጉልህ ፍንትው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን፣ ለውጥ አለ ቢባልም ይህ ዝግመት የኋሊት ነው። ከንጉሡ ጀምሮ ወደ ደርግ ከተደረሰ በኋላ ወደፊት የተራመደ እንቅስቃሴ አንመለከትም። እንደ ታሪክ ብናጠናው ዘርፈ-ሙዚቃ አፈግፍጎ እሚገኝ ነው። ይህ ለምን ተፈጠረ? አንኳር አመክንዮዎቹ ምንምን ናቸው?
የችክችክታ መዘመን አለመቻል እና እጅግ አሰልቺ አዘማመን
አቢ ላቀው፤ አንድ የጎነደርኛ (ሆዴን ሰው እራበው) ዘፈን ስትለቅቅ ምቱ መነሻ ፈጠራ የአስመለከተ ነው። በተለምዶ፣ የጎንደር ሙዙቃ ስልተምቱ እጅግ ከፍታ የአለው ድምድምታ (የከበሮ በባህላዊው ስልት) የበዛበት ነው። ይህን በሙያአዊ ቋንቋ ለመግለጥ ጥናትአዊ አገላለጥዎችን እንደልብ ወይም ከቶ አናገኝም። በአጭሩከ በመደዴ ቃል ስንገልጠው ግን፣ የተለመደው ገበያ፣ ጎንደርኛን ሲሠጠን ከጥንት ጀምሮ ፈጣኑ የጎንደር ሙዚቃ ምት በከፍተኛ ድምድምታ ይንቆረቆርልን አለ። ይህ የአቢ ላቀው ዘፈን ግን በደግ መጠን አዲስ ጆሮ ነው። ስልተምቱ ዘመንአዊ እና የተሰወረ ነው። ጎንደርኛ መሆኑን ዘግይቶ መረዳት አጋጣሚው ሊሆን ይችል አለ። ይህ በዝግታ የጎንደሩን ሞቅ-የአለ ምት እሚከትብ ስልተ ምት ደግ ፈጠራ ሆኖ አስደማሚነቱ ለገበያው አዋቂ የአየለ ነው።
እንደ እዚህ፤ እምንመለከተው አዲስ ፈጠራ ቢያንስ በእርግጠኝነት እምብዛም የለም። የጎጃም ትልቁ ልሙድ ምት፣ ዛሬም ያው እና የተለየ አይደልም። የዝግታ ሙዚቃዎች ከአታካች የአደረጉት ከ ሣክስፎን ምትአቸው ውጭ አይደርሱንም። እጅግ አሳዛኙ እውነት፣ ሙዚቃው በአቀራረብ እና ስልቱ የተነሳ ከመደጋገሙ መሳሪያውን እንዲያቅለሸልሸን እስኪሆን ሆኖ አለ።
በ ችክችክታ ዘፈን፣ ሀገር የታወቀ ነው። ዳሩ፣ ምንም ረብያለሽ ዝግመት ዘውጉ አያስመለክትም። ወይም እዚህ ግባ እማይባል ደካማ ሙከራ ቢሆን ነው እንጂ ሰጋጊ አይሆንም። ሀገርን የአጥለቀለቀው መደበኛ ምትን፣ በዝማኔዎች ፈቅ ማድረግ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ነው።
ቺጌ፣ አዲስ ምት ፈጠራ የተሰኘ አንድ ወቅት እንደ ተሰማ (እንደ ተባለው) ችክችክታውን መለዋወጥ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።
እማይሰበር ክፉ የመሳሪያዎች ሚና እና ባህል
ሌላው ተያያዥ ችግር፣ የመሳሪያዎች ወጥ አጠቃቀም ነው። አንድን መሳሪያ በተለያዩ ዘውግዎች እምንመለከት እንድንሆን እንፈልግ አለን። ዳሩ፤ ሙዚቃ መሳሪያው አንድ የተለመደ ሚና ከመጫወት ውጭ አዲስ ልማድ ላይ ወጣ ብሎ አንመለከተውም። ለምሳሌ እንደ አነሳንውከ ሣክስፎን እሚደጋገመው በዝግታ ዘፈንዎች ሊጮኽብን መሆኑ አተለመደ ሆኖ አለ። በብዙ መንገድ ልንመለከተው ግን እንችል ሆነን ሳለን ያ አይደረግልንም።
በዘርፉ ለውጥን ስለእዚህ አንመለከትም። ድግግሞሽ የአሰለቸን አለ። በአንዱ መሳሪያ ፋንታ ሌላው ለጆሮ ግርምታ በእሚል ለውጥ እንኳ ተተክቶ አይቀርብም።
የሙዚቀኛዎች ልዩአማአዊነት (specialization) መጥፋት
ሙዚቃውን ለማስተካከል፣ ዐብይ መፍትሔ ወጥ ልምድ በአንድ መንገድ ማልመድ መቻል አንዱ ይመስል አለ። ለአንድ መንገድ የተስማማ አካሄድንም በእየዘርፉ ከመበተን እና ከአለመመንደግ፣ አጥብቦ በመጓዝ መንገዱን መሙላት ወይም መስገግ እና ለጆሮ መቅረብ እሚቻል ነው።
ይቀጥል አለ፨

((( ይህ ጽሑፍ ረቂቅ እና የአልዳበረ ነው። አልተቋጨምም። ይመለስ አለ።))

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s