Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የኢትዮጵያው ድኅረ-ኢህአዴግ ውጥንቅጥ እና የአሸለበው ጋዜጠኛነት እና መገናኛብዙሃንነት

About how poorest journalism and massmedia services in Ethiopia is one giant reason why Ethiopia cannot move easily in finding and discussing national and political challenges and build better civilization of modern world.


bY
binyam HAILEMESKEL Kidane, ግምቦት 29 ቀን 2013 ዓም፨


አቶ ሙሉአለም ካሳ፣ ደንዳና ጎልማሳ ግለሰብእ፣ (ገጣሚ) በእሁድ ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓም. ሰርክ ላይ ግጥም ተቀምጠው በ ኢሳት. ትመ (Tv) ገጽማያ (screen) በመቅረብ ሲያነብቡ፣ የኢትዮጵያን ወቅትአዊ ውድቀት በዘለፋ ዘረዘሩ። እንደ እነ ሶርያ እና ሊቢያ ልንሆን ቋፍ ደርሰን፣ ብዙ ተገዳድለን አለን፣ በእየመንደሩ ሰውን ከመግደል የተሻለ የሌለ አስመስለን አለን፣ ወዘተ. በማለት ሲያሳስቡ፣ ወደ አመክንዮ(ዎቹ) አሰሣ መጀመር ግድ ነው። በእድሜ አርጅቶ የአጠፋውን በአምላክ ሲቀጣ ለማየት ከመፈለግ ይልቅ አመክንዮዎቹን ስለአላሠሱ ያንን ስንከውን ብዙ እምንመለከትአቸው ምክንያትዎች ይኖሩ ይሆን አለ። ነገርግን፣ ምክንያትም የምክንያትም አፈላላጊ የሆነ መሣሪያም ወዲያው እንደአጣን ይገባን አለ። ያም፣ የእየስፍራው ዜጋዎች መገደል እና የእየትላልቅ ተባይ ጠብዎች፣ ግድያዎች፣ ወዘተ. መረጃዎችን ለማግኘት እንፈልግ አለን። ዳሩ የችግርዎቹን ምንጭዎች ለማግኘት አሠሳ ስናደርግ፣ እምንመለከተው ቢኖር እዚህ ግባ የእሚባል መረጃ አናገኝም። በሩቁ የተዘገበ፣ ወይም በፕሮፓጋንዳ ማውጫዎቹ የህዝብ መገናኛብዙሃንዎች የተሸፈነ የአልጠነከረ እና ነፃ የአልሆነ መረጃ እናገኝ አለን። ነፃ መረጃ በነፃ ተቋም እንጂ በመንግስት አገልጋይ መገናኛብዙሃን የእሚተላለፈው አይሆንም።
ይህ እውነት እሚቀስረው፣ አንድ ገሀድ አለ። የሀገር አደጋ፣ ተጨባጭ የህዝብ ምትክየለሽ ጉዳት፣ የእምንሸፍነው፣ በአሸለበ ጋዜጠኛነት እና መገናኛብዙሃንዎች ተቋምዎች ነው። የጠጠረ እና ተፅዕኖአማ የመረጃ አነፍናፊ እና አቀባይ የህዝብ እጅ ወኪል የሆነ ጋዜጠኛ እና መገናኛብዙሃን የለንም። የተለመደ መደበኛ ወሬ ከማንሸራሸር በዘለለ፣ የደረሰን ጉዳት እሚዘረዝር፣ መነሻውን የእሚያስስ፣ ባለሙያዎች እና ባለድርሻአካልዎችን እሚያካትት እና እሚያፋጥጥ፣ በህዝብ ወኪልነት እና ሙያአዊ ስነምግባር መሰረት የእሚሞግት፣ የተፈጠረውን ወሬ በሩቁ አቀብሎ ነገ ከመርሳት ሁሉ ሲረሳውም ጉዳዩን በመከታተል የተለወጠውን እና አዲስ የፀደቀውን ትርክት የእሚያቀርብ፣ ዝርዝርዎችን የእሚያስጨንቁት ሆነው ፈልፍሎ የእሚዘረግፍ፣ ለእረዥም ጊዜ የአገኘውን ሰድሮ የእሚያስቀምጥ፣ ወጥ ሆኖ በእነእዚህ ሙያአዊ ስኬትዎች የእሚያገለግል የለም ወምመ ለተፅዕኖ የበቃው እምብዛም ነው።
ኦሮማይ ልብወለድን በዓሉ ግርማ የቀመረው፣ በደርግ ዘመነመንግስት የነበረ ገሀድን ተመስርቶ ነበር። የጋዜጠኛው ዋና ገጸባህሪ በድንገት ጦርነቱን እየተከታተለ ሊዘግብ አብሮ ሲዘምት እና ከፊያሜታ ሲገናኝ እንመለከት አለን። ይህም፣የወቅቱ እውነት ነበር። በቀኃሥ. እና ደርግ ዘመነ መንግስትዎች የህዝብ ጉዳይ የእሚሆኑ ትልልቅ ጠብዎች እና ግጭትዎች፣ ብሎም ጦርነትዎች፣ በጋዜጠኛዎች ተካፋይነት እና ዘገባ አቅራቢነት ይሞሉ ነበር። ድህረ-ደግር በኢህአዴግ.፣ ይህ ተወግዶ የአለ እውነት ነው። ድህረ-ኢህአዴግ. በብልጽግና አስተዳደርም የአልተቋረጠ ብሔርአዊ ውድቀት ነው።
በ ዓይንአችን ትመ. (Tv) መርሐግብር የህዘብ ሃብት ብክነትዎችን እየመረመሩ በመርማሪ ጋዜጠኛነት አንዳንዴ ጥቂት ዝግጅትዎችን እንመለከት ነበር። በቀረ፣ መርማሪ ጋዜጠኛነት ሲቀርብ አልተመለከትንም። እጅግ በቅርቡ፣ ሶስት እና አራት መርሐግብርዎችን የአቀረበ የ ኢሳት. ትመ. ጎልጉል ዝግጅት ሲቀርብ ከማየት በቀረ፣ ሌላ መርማሪ የመገናኛብዙሃን መስተንግዶ ሲገጥመን አንመለከትም።
ይባስ ብሎ፣ በመገናኛ ብዙሃንዎች መብዛት የተነሳ፣ ያም በይዘት ባይበዙም በአጭር አመትዎች ግን በቁጥር ስለጨመሩ ነው፣ የእሚገኙ መገናኛብዙሃንዎች የእሚያቀርቡአቸው ዜናዎች የመገናኛ-ብተና (press release) ናቸው። የተላከልን ፕረስ ሪሊዝ፣ መግለጫ፣ መልእክት፣.. ያንን የአስረዳ አለ ወዘተ. እሚሉ መቋጫዎችን ማድመጥ የተለመደ ነው።
የግጭትዎችን ስምጥ ዘገባ ቀርቶ፣ የአዘቦት ቀን እልፍ ኢፍትህአዊነት፣ ኢተጠያቂነት እና ሙሰኛነትዎችን፣ የእሚመረምር እና እሚያቀርብ እምብዛም የለም። አንዳንድ ሙከራዎች ለምሳሌ በ ኢሳት. ትመ. እና በተከፈተ ወቅት ብዙ ሳይቆይ በመንግስት በተዘጋው አስራት ሚዲያ. የተለመደ አንድ ጥረት ምርጡ ሆኖ እናገኘው አለን። ያም፣ የተበደሉ መጥተው በመገናኛብዙሃኑ በደል አልቅሰው (ብዙ ጊዜ በእንባ እየታጠቡ) ፍትህ ብለው በመለመን ያበቃ አለ። ይህ ዝግጅት ሌላ ነገርን ሲያደርግ አናየውም። የተከሰተውን መርምሮ፣ የእሚመለከተውንም ጠይቆ የተሰደረ መረጃ አቅራቢ የለም። ዞሮዞሮ፣ ያንንም መንግስት በማዳከም ሊሰልበው፣ አስራትን በማስጠንቀቂያ መስጠት ወዲያው ቀነገደቡ ሳያልቅ ደግሞ በአዲስ ውሳኔ በመዝጋት አጥፍቶት፣ አለ።
የተሻለ መረጃ አቅራቢ ተቋም እና ጋዜጠኛ አይገጥሙም። በአንድ ወቅት እየበቀሉ ደግሞ እሚሰወሩ እንዲሁ አነስ የአለ ቁጥር የደሉአቸው እንደ ቤተልሄም ታደሰ የአሉም ይገጥሙ እንጂ አይቆዩም። መደምደሚያው፣ የሀገር ችግርዎችን ለመመርመር እምንገደደው ተገቢ መፍትሄ ስንፈልግ ነው። ዳሩ፣ ዋናው መደበኛ የእዚህ ምንጭ ነፃ እና ገለልተኛ መገናኛብዙሃን እና የጋዜጠኛነት ሙያ አገልግሎት ነው። ያንወ ግን በኢትዮጵያ ለማግኘት አንችልም። ስለእዚህ የችግርዎችአችን አንዱ ችግር በአብይ ደረጃ ይህ እራሱ የመረጃ መርማሪ እና አቅራቢው የአለመኖር ችግሩ ሲሆን፣ የመፍትሄው ፍፃሜም የመፍትሄው መድረሻ ጎዳናውም ነው። በሙያአዊነት፣ መስዋእትነት እና መብቃት ህዝብን አገልጋይ ጋዜጠኛዎች እና መገናኛብዙሃንዎች፣ እነእሱን አበርቺ ተቋምዎች እና መአድ.ዎች (መንግስትአዊ የአልሆነ ድርጅት)፣ ወዘተ. አስገዳጅ መስተጋብር በመከወን ህዝብን መገንባት አለብአቸው። ከመንግስት አስተዳደር ነፃ እና ገለልተኛ ተቋምአዊ ሽፋን ህዝብ ሳያገኝ፣ የሙያ ጥራት ድጋፍ ይገኝብህ ማለት ከባድ ነው። አንድአርግአቸው ፅጌ አምና እንደተናገሩት፣ የክልል እና በዘር የተደራጁ መገናኛብዙሃንዎችም እራስአቸው እንኳ፣ የመንግስት እና አገልጋይ እን የህዝቡ አገልጋይዎች አይደሉም እንደ አሉት፣ የእነእርሱ ችግርነትዎች እንደአለ፣ የተሻለ ትትረትን መከወን ዞሮዞሮ አስገዳጅ በመሆኑ፣ የግል እና ማህበር መገናኛብዙሃንዎች ይህን ክፍተት መከላከል መቻል አለብአቸው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s