Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የስልጣኔ ልዩነት፡ የዘረ-ሰው ነገር ሁሉ መሠረት በ ዳኛአቸው ወርቁ አደፍርስ እንደተደረሰበት

How Dagnachew Werku’s novel Adefris has tapped on the fundamental topic of any modern civilization’s – the mind.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 11th 2021 GC.,


የ ኢትዮጵያ መሠልጠን ጉዳዩን፤ ብዙዎች ሠርገው ጫፉ ድረስ በአንክሮት ሳይነካኩ – ይልቁንም እንደ ብሔርአዊ መገለጫአችን በዜሮ-ጀማሪነት ደጋግመው የተደገመውንም ደጋግመው – ላይላዩን እንደ አወሩት ነው።
ጥንት፤ አንዳንድዎች አንዳንድ መስኩን በተግባር ጀማመሩት። ብዙ ሳይቆይ ለረዥም ዘመን ያ ከሽፎ ኖረ። ሀገር መምራት፣ ድንበር በጥቂቱ መጠበቅ፣ ከእዛ በቀጠለ ግን ግብር እየበሉ ሀገር ለተተኪ ሳያቀኑ ማለፍ እንደ ሆነ ቀረ። ዛሬ ድረስ፤ እንደ ረዥሙ አክሱም ሀውልት መቆም አቅቷት በስልጣኔዎች ክንፈዘመን (era of civilization) የወደቀች እና የአለም ጭራ ኢትዮጵያ አለች። ከመጨረሻው የምእራብ ስልጣኔ የመተዋወቅ ትትረት ጀምሮ፤ እስከ አሁን የምእራብ ስልጣኔን መጸየፍ፣ ተጠያቂ እና አባላጊ ማድረግ፤ የመንግስትዎች ሙስና፣ እውቀት-የለሽነት እና አምባገነንነት ከምንም የመሻሻል ጎዳና ሀገሩን የአለማውጣት እውነትን ከወኑ። የመሰልጠን ወሬ በሀገር ሁሉ አንደበት፣ መንግስት፣ ተቃዋሚዎች፣ የህዝብ መሪ አካልዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ወዘተ. እንደተሞከረ፤ ከስኬት ግን ከቶ እንደተራቀ የኢትዮጵያው ሀገር አለ።
በብዙ መንገድዎች፣ ስልትዎች፣ ጥበብዎች፣ አማራጭዎች፣ ደምዎች እና መስዋእትዎች፣ ትውምድዎች፣ ወዘተ. ከወጥመድ መዳኽ እና መቀየር አልተቻለም። የአወዳደቁ አመክንዮ(ዎች) ብዙ ወይም ጥቂት ቢሆኑ፤ አንድ የድርናማግ መሰረት ግን ከቶ የሁሉም ንጣፍ ነው። የህግ፣ የባህል፣ የስነውሳኔ (politics)፣ ስንምጣኔ፣ ትምህርት፣ ወዘተ. ጥረትዎች ሁሉ፣ እሚካቡት እና ሀገር እሚያቀኑት በእዚህ በብዛት ከስነልቦና የተያያዘ ጉዳይ ጋር ነው። ይህ ጉዳይ፤ የስልጣኔዎች ልዩነት እና መሰረት ነው። የአልሰለጠኑት፣ በእዚህ ጉዳይ የደከሙ ሲሆኑ፤ የሠለጠኑ ህዝብዎች ደግሞ፣ እጅግ በእዚህ ጉዳይ የላቁ እና የተመሰረቱ ናቸው። ይህንን ማንም ሊያስተባብለው እማይቻለው ገሀድ በኢትዮጵያ ውስጥ እምብዛም በተለይ በከተማዎች በተለይ የቅርብዎቹ አርባ አመትዎች ከቶ የእማናገኘው ሆኖ አለ እና እንመልከተው። አሁንም፤ የሀገር መሰረትን እሚሠራ እና የወደፊት ተስፋ እና ብሩህ ገሀድን የተሸከመ ወለል ነው።

የ ዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ ልብወለድ፣ አንዳንድ ነቁጥዎቹ የአልበለጸጉ አንዳንዱ ወቅቱን የአኖሩ፣ አንዳንድዎቹ ግን በቀንዎች እማይቀየሩ ህያው ናቸው። ከእነእዚህ ከሁሉ ወርቅ የሆነው ሃሳቡ፣ በ ልቡሰጥላ ሰይሞ የአቀረበው አስገዳጁን መሠረተ ስልጣኔ ነው።

[የገጠሩ ነገረተኛ ተሰብስቦ፣ ችግርዎቹን እየዘበዘበ፣ አደፍርስን የዋና ዳኛ አቶ ጥሶ ዘመድ ነህ አማልደኝ ሲል፤ የችግርዎችአቸው ምንጭ ተነቅሶ ለማህበረሰቡ ሁሉ ከስሩ ከአልተፈታ እነእሱ ዛሬ ፍትህ ቢያገኙም ነገ ሌላዎች እንደ እሚጣሉ እና ችግር እንደ እሚሆን ገልጦ አሁንም ቢሆን የቤተሰብእዎች በህግ ተካስሶ መለያየት መነሾውን እንዲገልጡለት ጠየቀ። የተለያዩ አመክንዮዎችን አነሱ። ተወያዩ። በመጨረሻ፤ ሁሉም የአሉአቸው የላይ ላይ መልስዎች እንጂ፤ የአልሰረገ ዳሠሳ መልስ እንደ አልሆነ መልሶልአቸው፤ የችግርዎቹን ምንጭ ነገርን ከስሩ፣ ውሃን ከምንጩ በእሚል በአንክሮታ (critically) ለማብራራት ይጀምር አለ። (ገ. 41)]
“…ከልቡሰ ጥላ እንጀምር አለን።”. …
ልቡሰ ጥላ የእምለው፣ ከአእምሮ ክፍልዎች በአነስተኛው ውስጥ የእሚገኝ ልዩልዩ ነገርዎችን ማየት — እና ማውጠንጠን ከጀመርንበት ጀምሮ የእሚጠራቀም — መያዣ መጨበጫ የሌለው የእሚመስል ምስቅልቅል ሁኔታ ነው።– ከቤተሰብእዎችአችን ይወረሳል። ከልዩልዩ መጽሐፍት ይዘራል።– (ገ.40)
….ልቡሰጥላ ሊያድግ ይችላል። …ተረት እና ታሪኮችን አዘውትሮ በመስማት መጽሐፍትን አዘውትሮ በማንበብ አዘውትሮ በማሰላሰል ሊያድግ ይችላል። ነገርግን እነዚህ ሁሉ ተዋህደው በሰውነቱ ካልሰረጁበት የሚያመጡበት ለውጥ አይታወቀውም። (ገ.45)

የ ዳኛቸው ወርቁ አመለካከት በእዚህ መንገድ መቅረቡ እንደሆነው ሁሉ፣ የእራሱ መንገድ ነው። ዳሩ፤ በደፈናው፤ አመለካከትን በማስመጥ እና በማስፋት፣ ትልሙን ወደ ተፈለገ አግጣጫ በመውሰድ፣ የዜጋዎችን አእምሮ በስልጡን መንገድ መቅረጽ የስልጣኔ ሁሉ መሰረት ነው።
አደፍርስ ላይ እንደተሞከረው፤ ልጅዎችን በተፈለገ ተረትተረትዎች፣ ስነምግባርዎች፣ ፍቅረ-ሰብእ፣ ተፅዕኖ፣ አንክሮታ፣ ከባቢ፣ ወዘተ. በማሳደግ፣ የዘመነ ሀገርን ከዘመነ ትውልድ ወዲያው ማብቀል እሚቻል ነው። አደፍርስ ላይ ዳኛቸው የገለጠልን በአጭሩ፤ ከልጅነት ጀምሮ የዜጋዎች አእምሮን በመቅረጽ የእድሜዘመን ስኬት ማግኘት እንደ እሚቻል ነው። ይህን፤ ሀዲስ አለምአየሁ፣ በ ፍቅር እስከ መቃብር እንደገለጡት፣ በዛብህ ለስቃይ እና መከራ የተዳረገው ቤተሰቡ ገና ሳያድግ ህይወቱን መርጦለት ከፍ ብሎ ሲኖረው የአልተስማማው ሆኖ ስለነበር ነው። ይህን ምስቅልቅል እምንመለከተው የቤተሰብእ ጫና ወይም አቅም ርዝመቱን እና ከተሳሳተ እመጣውን ስህተት ነው።
በደፈናው፤ አንድ ታዳጊን በሰለጠነ መንገድ መቅረጽ ከተቻለ፣ ትውልድን በሙሉ እንዲሁ በተሻለ መንገድ መፍጠር እሚቻል ነው። የስነልቦና እና አእምሮ ብልጽግና፤ ለየቱም ፍላጎት ወይም አዝማሚያው፤ ለዜጋው ስለእሚሆነው፣ ምጡቅ ሀገር የማልማት አቅም የአበረክት አለ።
ከልጅነቱ ጀምሮ ይጽፍ የነበረው ዳኛቸው ወርቁ አስምጦ በእዚህ ልብወለዱ ይህን ብርቅ ሀገር-አድን/መስርት እሳቤ አይጎረጉረው ስለእዚህ ደህና የተሠናሰለ ነገር ይዞልን አይወጣ ይሆን አለ። ዳሩ፤ መሰረቱን አጊንቶት አለ። በእዛ መሠረት፣ የስልጣኔ የአልተቋረጠ መሠረቷ፤ አእምሮ ላይ ስራ ነው። ዉስጡ፤ ትልቅ ምላሽ አለ። ያም፤ የተፈለገውን ትውልድ የመፍጠሩ ነው።
ለነገሩ፤ የ ቀኃሥ. አላሚነት (visionaryness)፣ ትምህርት እና ስነምግባር ወዳድነት የደርግ (ሀገር ወዳድ) ትውልድን (በብዛት የያ ትውልድ እሚሰኘውን ትውልድ)፣ የ ኢህአዴግ. አምባግነና እና ሀገር ጠልነት ሀገር ልበታትን ባይ፣ በብዛት የቀነጨረ፣ እራሱን ነፃ ማውጣት የአልሆነለት ተሸናፊ ትውልድን አምርቶ አለ፤ (በላይ ማናዬ፤ ይህ ትውልድ ከአራት ኪሎ እስከ ስድስት ኪሎ ብሎ በመቀንጨብ ጭንቅዎቹን የአስተጋባበት እና ይህ የአለው ትውልድ)። እንደ በዛብህ ቦጋለ አብዝቶ ትውልዱ አላመጸ እና አልታገለም እንጂ፤ በእርግጥ ይህ የ ኢህአዴግ. ትውልድ እና የአልሰክን የአለው (ዳኛቸው ወርቁ ቀድሞም በ አደፍርስ እንደ መከረው ሳይሳካለት እንደ ቀረው)፣ ዞሮ ዞሮ ትውልድን በሩቁ እንኳ በተፈለገው መንገድ መቅረጽ እንደ እሚቻል ይህ ሀገር ተመልክቶ አለ።
በሠለጠነ አያያዝ፣ በተጋ እና በእማይመለስ አኳኋን፣ ትውልድን ለመቅረጽ ዛሬም፣ መልሱ ልጅዎች ናቸው። ቤተሰብእ፣ ከባቢ እና ከማንም በላይ ታላቁ ተቋም መንግስት፣ ከማንም እና ማንም ልጅዎችን እያበለጸገ ከአመረተ፤ ወረት የአለው የአልራቀ ምላሹ እውቅ እና እሙን ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s