Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የቋንቋ-ባህል እና አጠቃቀም-ማእከልአዊነት መታጣት በኢትዮጵያ ለአለመሠልጠን የአበረከተው ትልቅ ሚና

About how a making and practice of a language-culture and usage-centralization leads into a wider power of communication and psychological bondage between speakers; thereby causing development of the society.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, June 10th 2021

[ይህን መነሻ ጽሑፍ በ ተአዶ. (PDF) የአግኙት፨ በአማራጭ ማስፈንጠሪያ ከጉግል ድራይቭ ይጋሩ፨]

አንድ ማህበረ-ሰውዎች፣ ስምጥ ተግባቦት በቋንቋው ይቀጥር አለ። ግለ-ሰብእዎቹ አእምሮዎችአቸውን የአገናኙበት አለ። በቀረ ከቃበልላይ ለሆነው፣ ሌላውን ገልጠው በሀሳብ አንድ ይሆኑበት አለ። ቀጥሎ፦ አንድም፣ ተግባቦት ከሆነ፣ ወደ ቀረው ህይወት ይሻገር አሉ። ሁለተኛ ግን፣ ወደ ቀረው ህይወት ከአልሄዱ ቋንቋውን እራሱን ይመረምሩት ሆን አለ። ሁለተኛውን ለሁለት አመክንዮዎች ይከውኑት አለ። አንደኛ ተግባቦቱን ለማሻለል ሲሉ ቋንቋውን ለማሠልጠን ነው። ወይም ሁለተኛ በቋንቋ የአለውን ከቋንቋ በላይ የሆነ ወይም የአልታወቀ ምስጢር ከአለ እሱን የአስሱበት አለ። ሁለተኛው የጠለቀ ጥበብ ሲሆን ከቋንቋ ጥናት በላይ እየሆነ ወደሌላ ጉዳይዎችም የእሚገናኝ ሲሆን፣ አንደኛው ግን ቋንቋን አስፍቶ ቅኝስለመግዛት እና ተግባቦትን ስለማሠልጠን ስለሆነ፣ አንድ ሰፊ እና ጠቅላላአዊ አርእስቱን አንስተን እናወያየው። ይህም እጅግ መነሻ ሐሳብ ለማቅረብ እንጂ ከቶ እሚጨንቅ አይደለም።
መነሻ ሃሳቡ እሚፈለፈለው ከእሚከተለው የምናልቦታ (hypothesis) ቆረቆንዳ ነው። ቋንቋ በመጠነቃልዎቹ (vocabularies) እና ቅርፁ ሲደጋገም እና ዘወትር ሲለዋወጡት፣ አመለካከትን በእሚደጋገመው የቋንቋ ቃልዎች መሠረት የመጥረብ እና አንዳች ቅርፀ-ርእዮቱን የማጋለጥ እና ወጥ የማድረግ አቅም አለው። አንድ ህዝብ በአንድ ቋንቋ ልውውጥ ክወናው ይህ ማለት የቋንቋ ባህል የአበጅበት አለ ማለት ነው። አንዱ ህዝብ ለእራሱ በቋንቋው የአመለካከት መስመር ከተግባቦት ልማዱ የተነሳ ከአበጀ፣ ሌላውም ህዝብ ለእራሱ የግድ ተመሳሳይ ነገር ኖሮት እናገኘው አለን። ህዝብዎች በእየአሉበት የቋንቋ-ባህል ከአለአቸው፣ ከሌላው የቋንቋ-ባህል የተለየ የአመለካከት ቀለም፣ ይኖርአቸው አለ። ምርጥ፣ ማለትም የሰመጠ እና የላቀ የቋንቋ አቅም የአለአቸው እንደሆነ ቋንቋው የተሻለ አእምሮአዊ ስፋት ይሰጥአቸው እና ወልሰብእነትአቸው (የጋራ ማንነትአቸው) ወይም ስብእናዎችአቸው እና የበለፀገ ይሆን አለ። ያን መመርመር ለአሁኑ ገድፈን፣ በመቀጠል፣ የቋንቋን አቅም በእሚከተለው ጥያቄ ዙሪያ እንግባ። በጋራ የተናጋሪውን የአመለካከት አመሉን እና ወጥነቱን በኋላ ያንንም ማእከልአዊነት ሆኖ እምናገኘው ነው እንዴት እንደ እሚሰራ እንይ።
ቋንቋ ሀሳብ ማቀያየሪያ ጥበብ ነው። ስኬታማ እና ፈጣን እንዲሆን፣ የመለዋወጡ መንገድ እየተደጋገመ ይፈጠር አለ። ያ ወደ ወጥ ቀለም ቋንቋውን በአመሉ የአደርሰው አለ። ጊዜ እየቀያየረው ቢኖርም፣ በተገደበ ጊዜ ግን ወጥ የሆነ ቀለም ይዞ ይኖር አለ። በወጥ ከመገልገል የተነሳ ቋንቋው የተለያዩ አማራጭዎች ቢኖሩትም በአንድ የተለመደ አግባብ ተጠባቂአመል (convention) የእሚሆን ቋንቋአዊ ወጥነት ይመሰረት አለ። ከአለው የአእምሮዎች በተደጋገመ መንገድ መግባባት መፈጸም የተነሳ እሚቀሰቀስ ተፅዕኖ አለ። ያም፣ አንድ ንቃተህሊና፣ አንድ አብሮታ፣ አንድ ስነልቦንታ (psyche) ወይም ወልሰብእነት (human-commonness) አንድ ስልተ ልኮት (style of reference) እና በእሩቁም ሆነ በቅርብ እንደ አእምሮው ቢለዋወጥም በተጨባጭ ደረጃ ግን ተመሣሣይ የአመለካከት አግጣጫ እንድናበጅ ይረዳን አለ። ተመሣሣዩ የቋንቋ አቀጣጠረደ መንገድ፣ ህዝቡን የእሚያስማማ እና የእሚገልጠው ይሆን አለ። ያም፣ ህዝቡን ማእከልአዊ የቋንቋ ባህል ይሆንለት አለ። በአገላለጡ እሚሰጠው ልኮት፣ ስልት እና ነገረስራ እጅግ የተመሣሠለ ይሆን አለ። የቀለጠፈ አገላለጥ፣ በተሻለ መንገድ የተስተካከለ አለዋወጥ፣ የእሚቀላጠፍ የልውውጥ ውበት፣ ወዘተ. ይፈጠር አለ። ያም ቋንቋው ጠንካራ እንደሆነ ግን ቀድሞ በመገመት ነው። ሁለተኛ ተፅዕኖው ደግሞ፣ የሃሳብ ክፍተት፣ ድግግሞሽ፣ አለመጣጣም፣ በተለይ መደጋገምን የማከም እድል አለው። ዛሬ አንዱ የገለጠውን፣ ሌላው መጥቶ በተለየ ቋንቋአዊ አቀራረብ አያመጣትም። የቋንቋው ወጥነት የእሚያግዘው ቢኖር፣ አንድ አመለካከትን በአንድ መንገድ የማቅረቡን ስልት ጠጠር ሆኖ ማቆም ነው። በመጨረሻ፣ እጅግ የተሳለጠ ማህበርአዊ ተግባቦትን ይከውኑበት ዘንድ ለህዝቡ ስልጡን ቋንቋአዊ መስተንግዶ ያፈልቅ አለ።
ይህን ቅንጭብ ሃሳብ ከአየን፣ የኢትዮጵያውን ዛሬ ዳብሮ የእሚገኘውን ተግባርአዊ አውድ መመልከት ቀጣዩ ነጥብ ነው። እዚህ ህዝብ መሀከል፣ አማርኛ ለምሳሌ የስራ፣ ንግድ፣ ህግ እና ይፋ መለዋወጫ ቋንቋ ሆኖ እሚገኝ ነው። በመደበኛነት እሚዘወተር፣ ለጥበብ ምርትዎች፣ ትምህርት እና መዝናኛነትም የእሚቀጠር አንደበት ነው። ታዲያ የቋንቋ ወጥ ባህሉ እና የማእከልአዊነት አቅሙ የት ጋር ነው?
ቋንቋው ወጥ አቀራረብ እና ማእከልአዊነት የአጠረው ነው። ቋንቋውን በእርግጥ አስፍቶ የመገልገሉ ብልሃት የእማይገኝ ስለሆነ፣ ከመጥበቡ የተነሳ የተደጋገመ እና እማይቀየር የአቀራረብ መንገድ ይኖረው አለ ተብሎ ይገመት ይሆን አለ። በአንድ መንገድ ያ እውነት ነው። ለምሳሌ በእየመንግስት መገናኛብዙሃኑ የተለመዱ ቃልዎችን በፕሮፓጋንዳ አያያዝ የተነሳ ደጋግመን እናደምጥ አለን። ያም ለቋንቋው በአንድ መንገድ ስለእሚደጋገም ማእከልአዊነት የአጠራቀመለት ይመስለን አለን። ግን፣ የተገደበ እና እንደ ፕሮፓጋንዳ እንጂ በመደበኛ ልወውጥ የእማይደጋገም ሲሆን፣ የረባ የቋንቋው መለኪያ ባህል ሆኖ አይገኝም። ፕሮፓጋንዳ የወለደው የቋንቋው ባህል መሆኑ እሚታወቀው ቋንቋውን በድርጅት አመራር እና መንግስትአዊ አስተዳደር ሂደትአዊ ስነስርአት ውስጥ የእሚውለው ቋንቋ ስለሆነ እና በመስሪያቤትዎች እንጂ በሌላቦታ የእማይደመጥ ስለሆነ ያም በመገናኛብዙሃንዎች ስለእሚፈስስ፣ የተለየ የቋንቋ ክፍል እንጂ የእውነተኛ መደበኛ የአማርኛ ክፍል አለመሆኑን እንገነዘብ አለን። ስለእዚህ ሁሉን የአማርኛ ተናጋሪዎችን፣ ከተመራማሪ እና ተማሪ፣ ከጥበብ እና ሂስ፣ ከመደበኛ ቋንቋ እስከ ገለልተኛ መገናኛብዙሃን ወዘተ. እየተሰናሠለ እሚገኝ ሆኖ አናገኘውም። ማለትም፣ አሁን አማርኛ፣ ምንም የበረታ የቋንቋ ባህል እና መሪ የሆነ ማእከልአዊነት፣ ከፕሮፓጋንዳ ባህል ውጭ የለውም። በድርጅትአዊ ቋንቋ ባህሉ ያም ባለማቋረጥ ወደ ህዝብ የእሚቀርብ ነው ስናደምጠው፣ ለምሳሌ የተለያዩ ወጥ ሀረግዎችን፣ መጠነቃልዎችን፣ ቅርፀትዎችን እናገኝ አለን። ለምሳሌ፦ "…የእንዲህ/ንዲያ ስራ ተሰርቷል።"፤ "ይህ/ያ አግባብነት የሌለው ሆኖ ተገኝቷል"፣ ወዘተ. እሚሉት ዐነ.ዎች ውስጥ የተለመዱ ድግግምዎሽዎች ሲገኙ፣ የቋንቋው ባህል እንዳይሆሙ ግን ከካድሬዎች፣ የድርጅት ልውውጥዎች እና የህዝብ መገናኛብዙሃንዎቹ ውጭ አይደመጡም። በእዛ የተነሳ፣ የአደጉ የአማርኛ ቋንቋ ወጥ ባህልዎችን ተፈረካክሰው እና በእየፊናአቸው እንጂ ጠጥረው እንዲሁም አንድ ሆነው አንመለከትም።
አንድ ጉዳይ ሲገጥመን ተመሳሳይ ቃል አንጠቀምም፣ ተመሳሳይ ፈሊጥ አይሰሙም፣ ወጥ የሆነ የምላሽ ቃልዎች ብልጭ አይሉም። ውጤቱ ደግሞ፣ በተሰናሠለ መንገድ በአእምሮ ትስስር (meeting of minds)፣ እንዳንተሳሠር የአደርገን አለ። ግንኙነትዎችአችንን በሰብእአዊነት እና ልማድ ደረጃ እንዲቀር እንጥለው አለን። ቋንቋአዊ ወጥ ትስስሩ ቢኖር የበለጠ እንደ ህዝብ ተዋህዶ በበለጠ አብሮነት እና አንድ ስነልቦና ለመገናኘት የአግዝ አለ። በእየመገናኛብዙሃኑ፣ የዘመምነት ልዩነትዎች እንደ አሉ፣ በእየትምህርቱ እና መደበኛ ግንኙነቱም፣ በመንግስት እና አስተዳደርም ውስጥ፣ ተቀራራቢ እና ወጥ የሆነ ብሎም በእየቋንቋ ዘርፍዎች የተዘረዘረ (በፈሊጥዎች፣ ምሳሌዎች፣ ተረትዎች፣ ወዘተ.) ስለእዚ የበሰለ የቋንቋ ወጥነት፣ ማእከልአዊነት፣ እና ባህል-መሆን ሊኖር ይችል አለ። ያ፣ ተመሳሳይ ጉዳይዎችን በወጥ የአገላለጥ መስመር ስለእሚደጋግምልን፣ አመለካከትዎችአችንን፣ ተቀራራቢ እና በቋንቋ የተነሳ የአልተራራቀ አድርጎ ወደ ቀጣዩ የማህበረሰብእ እድገት ወይም ማእዶት ደረጃ የአወጣን አለ። በአልተዘበራረቀ የቋንቋ ባህል እና ማእከልአዊነት የእምናቀርብአቸው ሃሳብዎች ወጥ እና በቀጥታ ግልጥ የእሚሆኑ ይሆንልን አለ። ማለትም፣ ተግባቦትአችን የፈጠነ፣ የአልተፈረካከሰ፣ ግንባርስጋ፣ ይሆን እና ችግርዎችን ለመወያየትም አንድ ሃቀኛ አንደበት ይነለረን አለ ማለት ነው። በሌላ ቋንቋ፣ አንድ ቋንቋ መነጋገር፣ ከአንድ የቋንቋ ባህል ውጭ የእሚከወን ከሆነ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪነቱን የእሚያከሽፍ ነው ማለት ነው። ምንም አንድ ቋንቋ የእሚጠቀም ህዘብ ቢኮን፣ ወጥ፣ ብስል፣ እና ሁሉም በተቀናጀ ደረጃ በአንድ አካሄድ የእሚቀጥፍለት ማእከልአዊነት ከሌለ፣ የልውውጥ ባህሉ የቋንቋውን ጉልበት ገርዞ ትልቅ ክፍሉን አይገልጥልንም። የአልተላጠ ፍራፍሬ እንደመገልገል የአልተቀናጀ ቋንቋ መጠቀም እማያረካ ነው። የቋንቋ አገልግሎት አለማርካቱ ደግሞ በአእምሮ አለመብሰል እና የህዝብ ጭንቅላት አለመረስረስን ስለእዚህ አለማደግን የእሚያመጣ ነው። በመሆኑም፣ ቋንቋን በመነጋገር ብቻ እሚለዋወጡት የግድ አንድ አሳብ አለአቸው ማለት አይደለም። በሃሳብም ልወውጥ ይከውኑ እነወጂ በሃሳብ ፈጣን ልውውጥ እና እድገት ይበለጽጉ እና ወደፊት ይራመዱ አለ ማለት አይደለም። በመደበኛ የአንድ ቋንቋ ተግጋይነት በመደበኛነት ሰው ሲግባባ፣ ቋንቋውን መግባባቱን ደግሞ በአንድ የተጠረበ ትልም ውስጥ ጨምሮ ቢነጋገርበት የተሻለ የሃሳብዎቹን መሳለጥ እና የበረታ ልውውጥን ከቀደመው በላይ ይከውንበት አለ። ቋንቋው በስነልቦና በማስተሳሰር፣ ወደላቀ ተግባቦት በመጋበዝ፣ ከባህል እና ሰብእአዊነት በዘለለ ህዝቡን አብሮታ ውስጥ በማስረግ፣ ህዝቡን ለማሰልጠን እጅግ ትልቅ መነሻ ይሆን አለ። ይህ ግብአት፣ ስልጣኔውን አንድ አድርጎ በህዝቡ የተግባቦት መመሳሰል የተነሳ ወደ ላቀ አንደበት፣ ያም የእውቀት አመቻች ነው፣ ወስዶ ይረዳው አለ።
ይህን ለማግኘት እና ምርጡን የቋንቋ መንገድ ለመቀየስ እንገዲባን ለማመን፣ ፕሮፓጋንዳን እንመልከት። እውነት ሲደጋገም ውሸት እንዲሆን፣ የቋንቋ መደጋገም ደግሞ ደግሞ አንድ አእምረፐን ስለእሚወልድ፣ ይህም በስነልቦና የታወቀ ነቁጥ ነው፣ አንድ ቋንቋን ደጋግሞ በመንገር ወጥ እና ማእከልአዊ የቋንቋ ባህል ለማዳበር በመሞከር መንግስት ህዝብን ተገዢነቱን የአመቻች አለ። እንዲሁ፣ በሰለጠነ ሃገር፣ ህዝብ በነፃ እና ሰፊ ቋንቋ እየተገለጓ ያም ቋንቋ ማእከልአዊነትን እንዲገነባ ተደርጎ የቋንቋ ባህሉ የእሚያበለጽግ ይሆን አለ። ከእዛ በላይ እንደ አልንው የማስተሳሠር አቅሙ በስነልቦና የማዋሃድ እውነታው ወይም ተፅዕኖው የተነሣ ከፍተኛ ተጨማሪ ግብአትነት ለእድገተ-ህዝብ የታወቀ ነው። የቋንቋ ማእከልአዊነት እና ባህል ሰፍቶ በወጥነት ከተገኘ፣ ወደፊት ህዝብ የማራመድ እድሉን አብሮ ይሰጥ አለ።
ይህ ቢሆንስ፣ በምን ይህን መከወን የእሚቻል ነው እሚለውን ማወቅ ጠቃሚ ነው። ቋንቋ በተለመደ መንገድ የአግባባን አለ። ያም ስልጣኔ ከሌለን ወይም ሰፋ የአልን ህዝብ ከሆንን፣ በመደበኛ መንገድ እንጂ በስብ መንገድ አይሆንም። የተቀራረቡ ሰዎች ሁሌ ተመሳሳይ እንዲነጋገሩ እና እንዲለምዱ፣ አንድ የቋንቋ ተግባቦትን ዘልለወወ አንድ የቋንቋ ባህል አበለፀጉ ማለት ነው። ምክንያቱም ቋንቋውን እየተገለገሉ በመግባባት ሆነውም፣ የቋንቋውን ባህል ለወጥ ለማድረግ አንድአቸው ይህን ቢከውኑ፣ ቋንቋአቸውን እየተግባቡበት ባህሉ ስለተነካ ግን ግራ ይጋቡ አለ። ማለትም፣ ቋንቋ አግባብቶ ከአለቀ በኋላ፣ መልሶ ደግሞ አንድ ማእከልአዊነት በመፍጠሩ ከአብሮመኖር በላይ የበለጠ መተሳሠር እና ስነልቦናአዊ ወጥነትን አምጭ ነው። ይህ እሚደፈርሰው ሰፊ ህዝብ ቋንቋውን ከተነጋገረው እና በማእከልአዊነቱ መጠን ግን አናሳ አቅም ከእዛ የተነሳ የአገኘ ሲሆን ነው።
ስለእዚህ፣ የበለፀገ ብሔርአዊ ተግባቦት በቋንቋ ደረጃ ለማግኘት፣ የቋንቋ ግንኙነት ወጥ ሆኖ በአንድ ተቀባይ መንገድ መኖር አለበት። መገናኛብዙሃንዎች፣ ጥበብ፣ ትምህርት፣ መደበኛ ልውውጥ፣ ወዘተ. ወጥ የሆነ ቋንቋ መገልገል አሉብአቸው። ለምሳሌ፣ የተለመደ ቅርፀት፣ እውቅ ምሳሌዎች፣ ተረትዎች፣ ፈሊጥዎች፣ ሀረግዎች፣ ወዘተ. መለመድ አለብአቸው። ነገርግን ፍፁም ወጥነት ማለት አይደለም። መነሻ እና ጠጣር የሆነ ማእከልአዊነት ነው እንጂ፣ ልዩ-የቋንቋ-ባህልን ግን አይጨምርም። ለምሳሌ ዳግ-ተመራማሪዎች (researchers) እና መደበኛ መንገደኛው አንድ አይነት ቋንቋ ቢያወሩም ከቶ ተመሳሳይ የቋንቋ ባህል ይኖርአቸው አለ ማለት አይደለም። በልዩ-ቋንቋ-ባህል እነእዚህን እንይዝአቸው አለን። ወይም ቀበልኛ፣ የታዳጊዎች፣ የወጣትዎች፣ የአራዳዎች፣ ወዘተ. ቋንቋ የተለያየ ሊሆን ይችል ይሆን አለ። ግን፤ ሁሉም እሚግባባበት ወጥ የሆነ የቋንቋው ደረጃ ከፍተኛ መሆን አለበት። የተራረቀ እና የተጋነነ ልውውጥ ማእከለግንኙነትዎችን ለማህበረሰቡ እማይቸር በመሆኑ፣ በአንድ ቋንቋ ስር ሳሉ ከአለጠና ተግባተት ተራርቆ የመኖሩ ጉዳት ይከሰት አለ። ይህ ከሆነ፣ ማእዶት አይሳለጥም። አብሮነት፣ አይንበለበልም። ስለእዚህ፤ ቋንቋን በመግባቢያነት ደረጃ በመተው በሩቁ መገልገል ለስልጣኔ አያበቃም። በሰፊ፣ ወጥ እና ብልህነቱ የበዛ የቋንቋን አጽንቶ በማሰራጨት፣ በጥልቅ ትልምአግጣጫዎች (policies)፣ ህግዎች እና አስተዳደር፣ ቋንቋን በደግ ደረጃ ማዘመኑን መንግስት መወጣት አለበት። ለምሳሌ፦ አንዳንድ መንግስትዎች ቋንቋአቸውን ለማሳደግ እጅግ የበዙ ደንብዎችን ደንበው፣ በወጥመንገድ እንዲገለገሉት ይጣጣር አሉ። ለምሳሌ የሀገሩ ቋንቋ ቃል ከአለው፣ እንግሊዝኛ አትጠቀሙ በማለት መገናኛብዙሃንዎችአቸውን በእየቀኑ በመመርመር ይቀጡ ወይም የአበረታቱ አሉ። ቋንቋው የእሚበለጽግ እና የእሚሰፋ ሲሆን፣ በሌላ መንገድ ነፃነት እና የመንግስት ቋንቋ ባለመኖሩ፣ በሀገር ቋንቋው ከፍልስፍና፣ እስከ ኪነእናስነጥበብዎች እና መደበኛ መገናኛው ወዘተ. ስለእሚከወን፣ የተሻለ የማደግ እድል እየተገኘ ነው፤ ሌቋሆ.።
ይህም በመሆኑ በህዝብ ፊት አንዱ ግለሰብእ ሲቀርብ፣ ሃሳቡን እሚቀርጽበት የቋንቋ ቅርጽ እና የቃልዎች፣ ምሳሌዎች፣ ተረትዎች ወዘተ. መንገዱ ወጥ እንዲሆን መታገል ተገቢ ነው። ማእከልአዊ የተደረገ ቋንቋ፣ የስልጣኔ መሰረት ከሆነ፣ አማርኛን እና ሌላ ቋንቋወፐችንም፣ በተቻለ ሁሉ ወጥ ባህል አስይዞ ለማሳደግ መስራቱ የኢትዮጵያ አንድ ግዴታ ነው፨

One reply on “የቋንቋ-ባህል እና አጠቃቀም-ማእከልአዊነት መታጣት በኢትዮጵያ ለአለመሠልጠን የአበረከተው ትልቅ ሚና”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s