Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የስልጣን ባሪያ ስነልቦና፡ መንግስትአዊ አስተዳደርን በምርጫ መለወጥ አይቻልም እሚለው ስሜት እንደ ኢትዮጵያአዊው የስነውሳኔ መሰናክል

About the typical Ethiopian political Psychology of Stockholm Syndrom in power and administration that dictates since no power transfer was made that it might not happen even by now.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, May 2021 GC.,


የብልጽግና ድርጅት ተወካይ ዛዲግ አብርሃ፣ በሚያዚያ ሁለተኛ ሳምንት መነሻ 2013 ዓም. ማብቂያ በ ኢትመ. (ETV.) ትመ. ለ 2013 ስድስተኛ ብሔርአዊው ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻ ፉክክር ሲያቀርቡ፣ ከአነሱአቸው ሰነፍ ነጥብዎች አንዱ ቀልብ መሳብ የእሚገባው ነው። ያም፤ ለተቃዋሚዎች ተወካይዎችአቸው በፊትለፊትአቸው ተቀምጠው ለነበሩት ሁሉ የተናገሩት አንድ ጉዳዩ ነው። እናንተ ብትመረጡ እንደ ብልጽግና ሀገር ማስተዳደር እምትችሉ ናችሁን? አይመስለኝም። ብቃቱ ወይም ዝግጅቱ የለአችሁም፤ አሉአቸው።

የኢትዮጵያ ስነውሳኔ (politics) አንድ የአልቀመሰው ተሞክሮ በምርጫ መንግስትአዊ አስተዳደርር መቀየር ነው። አምባግነና እና ንጉስአዊው የአንቀላፋ ረዥም አመጣጥ አገዛዝን፣ ወደ ንጽውሳኔ ቁልፍ (ምርጫ) መቀየር እርግጥ አንድ እርምጃ ነው። ይህ እንዲከወን ሁሉም መረባረብ አለበት። አብይ አህመድ ደጋግሞ ይህን ለመከወን መዘጋጀቱን ሲናገር ተደምጦ አለ። በምርጫ የአሸነፈን ቁልፍ ሰጠቼ አስረክበው አለሁ እንደ አለ እዚህ ተደርሶ አለ። ዳሩ፤ ብልጽግናዎች ሲከራከሩ ግን፣ መንግስት አስተዳደርን መቀበል የእሚችል ማንም የለም የማለት በኢህአዴግ. የተለመደ ተመሳሳይ ማስፈራሪያን በማቅረብ ክህደት በተፈጸመው ቃል ይፈጽም አሉ።
የምርጫ ለውጥን መከወን የአልቻለ ህዝብ እና ሃገር ቢኖር እንኳ፣ አንደኛ፣ በእዛ ሂደት ገዢው ድርጅት ትብብር ማድረግ እንጂ ማስፈራሪያነት ማድረግ አይገባውም። የዘመንአዊ ሀገር ምስረታ ሀገርአዊ ዝግመቱን አለመውደድ እና ማደናቀፍ ነው። ሁለተኛ፣ በምርጫ አሸናፊ እና መንፍስት መስራች አዲስ ድርጅት ቢገኝ ህዝብ እስከመረጠው ስለህዝብ ብሎ በማገዝ እና በመደፈፍ እና እርዳታ ማድረግ እንጂ ማስፈራራቱ ተገቢ እሚሆን አይደለም። ሶስተኛ፣ መንግስትን ብልጽግና ማስተዳደር እንደአልቻለ እና የሰላም እጦት እና የኢህአዴግ ዘመን ችግርዎች መቀጠል መብዛቱ፣ ለምን እንደሆነ፣ ሲጠየቁ ዋና መልስአቸው አንዱ ገና ብልጽግና ሁሉን የአልተቆጣጠረ እና በኢህአዴግ አመራር እሚሰራ መሆኑን ከሁለት አመትዎችም በኋላ ይናገሩ ነበር። ብልጽግና እራሱ ለውጥን ከውኖ፣ ህዋሃትን ከበረሃ አጥፍቶም፣ ገና መንግስትነት አልመሰረትኩም ጊዜ የአስፈልገኝ አለ እሚል ከሆነ፣ እራሱም መንግስት የመሆን አቅም የሌለው ሆኖ እስከ ፉክክሩ ቀን የተገኘ ተጨባጩ ወዳቂ መንግስት-መር ነው። አራተኛ፣ ኢትየዮጵያ ለውጥ ላይ ናት። ከብልጽግና እኩል እንጂ የአነሰ የአልሆነ ተቀራራቢ እድል ለሁሉም አለው። ምክንያቱም ገና የተመሰረተ አዲስ ድባብ የለም። ለማንም ሆነ ማን መንግስትነቱ አዲስ አስተዳደር መፍጠር ነው። አምስተኛ፣ የአምባግነና ስነልቦና እናእንጂ ተጨባጭነት የሌለው ነጥብ ነው። አንድ መንግስት አስተዳዳሪ ከተለየን ገደል ገባን መሰል አተያይ ከስቶኮልም ሲንድሮም አይለያይም። ስድስተኛ፣ የመንግስት እና ድርጅትን ልዩነት ጠንቅቆ አለማወቅም ነው። መንግስትን እሚነካው የለም። ምርጫ የመንግስት አስተዳደሩን እሚቀይር ነው። ያ ደግሞ በአንዲት ቀን እና ጥቂት ሳምንትዎች እሚከወን ነው። የቱም አለም ስልጣን ማስረከቡ ይኑር እንጂ፣ ማስተዳደር የተለመደ ቀላል ሂደት ነው። ሰባተኛ፦ ህፃጼአማ (fallacious) ነጥብነቱ መንግስት ለመመስረት ውጣውረድ አልፎ የቀረበ ድርጅት አቅም እንደ አለው አምኖ የቀረበ በመሆኑ ተፎካካሪነት በመሰረቱ መነሻው የማስተዳደር አቅም ታሳቢነት በመሆኑ ይህን የሳተ ነቁጥ ይሆን አለ።
ለረዥም ዘመንዎች የሰረፀ አምባግነናአዊ አመለካከትን በማሸነፍ፣ እንዲሁም አዲስ ልማድን በመፍጠር፣ መንግስትአዊ አስተዳደርን የመለወጥ ባህልን ሁሉም ተጋግዞ ለመገንባት እና ሀገር ለማቅናት መሞከሩ እጅግ አስፈላጊው ወቅትአዊ ጥያቄ ነው። ሁሉም ተባብሮ መገንባት ደግሞ ህግአዊ፣ ሀገርአዊ እና ሞራልአዊ ግዴታው ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s