Categories
የንባብ ፉክክር [rEADEING cHALLENGE]

አታሚ ከ አሳታሚ፡ መነሻ ፍቺዎች እና ግራአጋቢ የህግ ትርጉምዎችአቸው በኢትዮጵያ

About defining publisher and printer in Ethiopia in a very basic way, which seem to have in fact a legal blurry definition realm.

በንባብ ፉክክርዎችአችን፤ ጠብጠቢትዎች (temples) ለጭምቅ መጻፊያ አዘጋጅተን አለ። ያም፤ መነሻው ላይ ስለ እሚነበበው መጽሐፍ አታሚ እና አሳታሚዎችን ስለመጽሐፉ እንዲሰፍር ይጠይቅ አለ። አታሚ እና አሳታሚ፤ ምንምን ማለት ናቸው?

አታሚ ማለት፦ መጽሐፉን በወረቀት ህትመት አውጥቶ በመጠረዝ መጽሐፉን በአካል አምርቶ በተፈለገው ቁጥር መሰረት እንደዉሉ እሚያስረክብ ተቋም ነው። መጽሐፍን በአሃዝአዊ ደረጃው (digital form) ተቀብሎ (በፊት በለቀማ ህትመት = manual printing ወቅት ደግሞ አንድ የደራሲውን እጅ ወይም ብቻ ጽሕፈት ቅጅ ወስዶ) በበዙ ቁጥርዎች በማተም በተፈለገው የመጽሐፍ ቁጥር መሠረት እሚያስረክበው ተቋም ነው። የህትመት አንቀሳቃሽ (Machine) የአለው ሲሆን፤ ቀለም እና ወረቀት ተገልግሎ እምናነብበውን የተደራጀ ወረቀት እሚያበጅው ነው።

የተሻረው የመገናኛብዙሃን እና የ መረጃ ነፃነት አዋጅ ቁ. 590/2000 እሚከተለውን ይል ነበር።

“አታሚ ማለት የህትመት ስራዎችን ለማተም በአሳታሚው የተሾመ ወይም ከአሳታሚው የተዋዋለ ማንኛውም ሰው ነው።”

አንቀጽ 2 (13)

በቅርብ የመጣው አዲስ አዋጅ፤ 1238/2021

“አታሚ” ማለት በየጊዜው የሚወጡ ህትመቶችን ለማተም በአሳታሚው የተመረጠ ወይም ከአሳታሚው ጋር የተዋዋለ ማንኛውም ሰው ነው፤”

አንቀጽ 2 (32)

የአዲሱ አዋጅ አታሚን ወደ በእየጊዜው እሚወጣ ህትመት (periodical) አታሚነት ብቻ ሲአሽቆለቁለው፤ የተሻረው ህግ ደ የህትመት ጉዳይ (print matter) ብሎ በሠፋ መንገድ ይተረጉመው አለ። ቀደም ብሎ ደግሞ የህትመት ስራ ወይም ጉዳይን ይተረጉምልን አለ። ስም ጠፍቶ በሐረግ የተገለጠው (በፍቺው) በእየጊዜው እየታተመ እሚወጣ (periodical) አንዱ የህትመት ስራ ነው። በአዱሱ አዋጅ ግን ብቸኛው የህትመት ስራ ነው። ይህ ሰፊ ዳግ-ምርምር (research) የአደረግኩነት ባይሆንም፤ በእዚህ ትርጓሜው ግን ገሀድ ክፍተት ነው። በተፅዕኖው፤ አታሚ ለመሆን ያንን መስራት ብቻ ፈላጊ ከሆነ እጅግ አስጊ ነው። መጽሐፍ አታሚ ለምሳሌ፤ የት ሊገባ ነው? በመጽሐፍ ህትመት አታሚ መሆን ከአልቻለ፤ ተከታታይ ህትመት ብቻ ማተም አለበት ባይ ነው። ግራ አጋቢ፨

አሳታሚ ማለት፦ ደራሲዋ የጻፈችውን ተቀብሎ በመግዛት፣ ወይም በአንዳች ውል መሰረት የመጽሐፉ አታሚ ፈልጎ አሳትሞ የመሸጥ እና ስርጭቱን የመቆጣጠር ወይም እንደ ውሉ የተለያዩ መብትዎች ወስዶ ለደራሲው እና አታሚው መሀከልአካል (intermediary) በመሆን ያንንው ሚና ከ መጽሐፍ አከፋፋይዎች መሀከል ሆኖ እሚከውን ነው። ደራሲውን ወደ ህትመት መሯሯጡ ከመሻገር እሚያሳርፈው፣ የተሻለ የማሳተም እውቀት፣ የማከፋፈል እና ማስተዋወቅ አቅም የአካበተ፣ ከደራሲው ወደ አታሚ እና ሻጭ አድራሽ ተቋም ነው። ተቋሙ፤ አርታዒዎችን ገዝቶ፣ መጽሐፉን አስመርምረው፣ እርማትዎችን አስከውነው፣ ለገበያ እንደእሚመቸው አድርገው የአዘጋጁት አለ። ለምሳሌ፤ እርእሱን ከደራሲው ምርጫ ውጭ እንዲቀይር ሊነግሩት ሁሉ ይችል አሉ። የመቀደሻ ልብወለዱን፤ ኢትዮአሜሪካአዊው ዲናው መንግስቱ ለምሳሌ ከፃፈ በኋላ የአብዮቱ ልጆች ብሎ ሰይሞ በእንግሊዝ ውስጥ አሳታሚው አታሚ ፈልጎ አሳተመለት። ወደ እንግሊዝ ለህትመት ሲሄድ ግን፣ እዚያ የአገኘው አሳታሚ (RANDOM HOUSE) አሜሪካዎች እሚወድዱት እርእስ አይደለም፣ በእሚል ከ ስነውሳኔ (politics) ውጭ የሆነ እርእስ ስጠው አሉት። ለእዚያ ነገርዎች እሚሰጥአቸው ውብ ነገርዎች” ተብሎ ታተመ። በአጠቃላይ፤ አታሚ የተሰጠውን ሳይመለከት ሲያትመው፤ አሳታሚ ግን ሽያጩ ስለእሚመለከተው እና ቀጥተኛ ስራው ስለሆነ መጽሐፉን በደንብ ፈትሾ፣ በአዋቂም አስፈትሾ፣ ተፈላጊ አድርጎ አሳትሞ፣ ሸጦ፣ ትርፉን ይካፈል ወይም ይወስደው አለ (ሙሉ ለሙሉ ገዝቶት ከሆነ)፤ እንደ ውሉ መሰረት።

የተሻረው ህግ ተከታዩን ይል አለ።

“አሳታሚ” ማለት መገናኛ ብዙሃኑን የእሚወክል ወይም መገናኘ ብዙሃኑ ባለቤት የሆነ በድርጅቱ ውስጥ የጎላ የባለቤትነት ጥቅም የአለው ወይም የድርጅቱን የስራ አስተዳደር የእሚመራ ማንኛውም ሰው ነው፨

አንቀጽ 2 (12)

አዲሱ አዋጅ ቁ.1238/2021 ከስር ይህን ይለን አለ።

“አሳታሚ” ማለት በየጊዜው የሚወጣ ህትመትን ወይም የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን የሚያሳትምና ለስርጭት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ነው፤”

አንቀጽ 2 (32)

የተሰረዘው አዋጅ የበለጠ ስፋት ሲኖረው ተኪው፤ እንደ ቀደመው ንዑስአንቀጽ አታሚን እንደ ገደበው አሳታሚንም ገድቦት አለ። አሳታሚ መጽሐፍ ለምሳሌ ለማሳታም እማይፈቀድለት ይመስለን ዘንድ እንገደድ አለን። በእየጊዜው ታትሞ እሚወጣ ከአልሆነ ለማሳተም የእማይፈቀድለት ነው ማለት ነው። ይህም ከቶ ግራ አጋቢ ነው። ተከታታይ ህትመት ከአልሆነ፤ ወይም የበይነመረብ ህትመት ከአልሆነ፤ አሳታሚ መሆን አይቻልም ማለት ነው።

እነሆ እንዳለጌታ በ ሰም እና ወርቅ መጽሔት እንደመሰከረው ከማሳተም እስከ ማንበብ ድረስ የአለው እንቅስቃሴ በወንጀልዎች እና በተበሳሰኩ እውነትዎች የተሞላው ዘርፈእንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ለረዥም ዘመንዎች አለ። ይህ ክፍት የሆነው አዋጅ ደግሞ ያንን ክፍተት እማያግዘው እና ከፈቃድ ውጭ እሚንቀሳቀሱ አሳታሚዎች እና አታሚዎችን፣ ጭራሽ አታሚ እና አሣታሚዎች አይደልአችሁም በእዚህ ህግ አካትቼ እናንተን አልጠይቅአችሁም እየአልአቸው ነው። ዳሩ፤ ያ ብቸኛ እውነቱ ባይሆንም፣ ትልቅ ክፍተት በአዋጁ ግን የተወለደ ይመስል አለ፨

በግልጥ እንደ እሚታየው እጅግ አነጋጋሪ እና ትንግርት ትርጉም በአዲሱ ህግ እሚገኝ ነው ማለት እንችል አለን፤ ቢያንስ የሠረገ ዳግምርምር ስለአልሆነ በምንአልባትም ቢሆን። በደፈናው ግን አሁንም ቢሆን፤ በኢትዮጵያ የመገናኛብዙሃን ተሞክሮ መሰረት፣ አሳታሚዎች እምብዛም የሉም። ግለ-አሳታሚነት (self-publishing) የበዛው ተሞክሮ ነው። ደራሲው እራሱ እሚሰራው ስራ እና ተሯሩጦ እሚጨርሰው ስራ፣ የአሳታሚውን ጭምር እንጂ የደራሲነቱን ብቻ አይደለም። ማስመረቅ እና ማከፋፈል ድረስ በብዛት የተለመደው ነገር፣ ይህ መሆኑ ደራሲዎችን ስለእሚከብድአቸው፣ እንዳለጌታ ከበደ፣ ደራሲ እና ሀያሲ፣ “የአንድ ኢትዮጵያአዊ ደራሲ ህመም ከድሮ እስከ ዘንድሮ” በአለው አጠር የአለ ጽሑፍ የመረመረው አብይ ችግር ይህን የአሳታሚዎች አለመገኘት ነበር።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s