Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የኢትዮጵያ ስነውሳኔአዊ ምርጫ ወቅትዎች ደገኛ ውድቀት፡ ሰፊው ስልጣኔን አለመመልከት

About how shortsighted contents of political parties in election campaigns in Ethiopia can potentially hamper political parties capacities and the nation’s future.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 25th 2021 GC.,

የስነውሳኔ ምርጫ (political election)፣ በኢትዮጵያ ቅርብ ዘመንዎች አንድ ሀቅ አለው። የመንግስት ስልጣንን በደፈናው ለመውሰድ እሚደረግ መናኛ ፉክክር ነው። ገዢ ድርጅትዎችም ሆኑ አዲስ መጪ ተፎፎካካሪዎች፣ መንግስትነቱን ፍለጋ አላሚ ናቸው። የተሻለው ደረጃ አንዳንዴ እሚገጥመን፣ የሀገርምስረታ ጉዳይንም የማካተት ፍላጎቱ ነው። ከመንግስት ስልጣን ተሻግሮ፣ የሀገር ተገቢ ምስረታ እንደሌለን እና ከ ፊውዳል ስርአት ውዥምብር ገና የአልጠራ አኗኗር እንደ አለን እሚመለከቱ አንዳንድዎች ይገጥሙን አሉ። ለምሳሌ፤ መራራ ጉዲና (ሊቀምሁርዎች) ደጋግመው ከአዲስ ማህበረሰብእ ውል (social contract) ገና መጀመር አለብን እሚሉ ናቸው። በተለያየ መንገድ በእርግጥ ብዙ ስነውሳኔኛዎች (politicians) ይስማሙብአቸው አሉ።
ሀገርን የያዝንው፣ ከንጉስአዊ ስርአት ወርሰን ሲሆን፤ ህዝብአዊነትነት (republicanism) በ ኢህአፓ. ትግል እንጂ ጭራሽ የተሞከረም መጠነኛ እንኳ ታሪክ የለውም። አመጽዎችም መንግስትአዊ አስተዳደርዎችን ሲለውጡ፣ ስርአትን ግን ወደ ህዝብአዊ ልዑዋላዊነት፣ አርነት፣ ዕሪና እና አዲስ ሀገርነት እሚመልሱ አይደሉም። ሀገር በኢህአዴግ. እና ብልጽግና መንግስትአዊ አስተዳደርዎችም ፍፃሜዎችአቸው፣ መንግስትአዊ ትድድር ብቻ ሲሆን በካድሬ-ሰንሰለት እና በፍፁም አስፈፃሚ ክንፈ መንግስት የበላይነት እሚሮጥ እውነታ እንጂ ከስሩ የእሚመሰረት አይደለም።
የድህረ-ንጉስአዊ ስርአት ከፈረሰ አዲስ ህዝብአዊት (republican) የሀገር ወይም ስርአተ-ሀገር ምስረታ እሚያስፈልገን እንደሆነ ብዙዎች አይጨንቅአቸውም። ዴንታአቸው የመንግስት ስልጣኑ ብቻ ነው።
በ ፋና ትመ. ለ ፮ኛው (ሚያዚያ 2013 ዓም) ብሔርአዊ ምርጫ፤ ምረጡኝ ፉክክር ሲከወን፣ የ ኢዜማ መሪ. ብርሃኑ ነጋ (ሊቀሊቃን)፣ እንደ ተናገሩት፣ የሀገር ምስረታ ስራውን ብንመረጥ እምንከውነው ሲሆን የድርጅት ጉዳይ አይደለም፤ ተቋምዎች፣ ህዝብ እና ልሂቅዎች መሳተፍ እና መከወን እሚገብአቸው እውነት ነው ሲሉ፤ ብንመረጥ ወደ እዛ እንገባ አለን እንጂ ገና ዛሬ ሀገርን እንዲህ አድርገን እንመሰርታት አለን አንልም ብለው አለ። በተጓዳኝ፣ ሌላ ስነውሳኔአዊ ድርጅትዎች፣ ሀገርን ለመመስረት የአቀዱብአቸውን መንገድዎች አብረው አቅርበው ይፎካከሩ ነበር። (ለምሳሌ ህብር ኢትዮጵያ እና እናት ድርጅትዎች፣ በአዳዲስ ክልልዎች ህዝቡን ከአዲስ አዋቅረን ሀገርን ከአዲስ እንመሰርታት አለን ሲሉ ተሰምተው ነበር።)
በደፈናው፤ የኢትዮጵያ ስነውሳኔአዊ እና ታሪክአዊ ገሀድ፤ የቋሚ ህዝብአዊት ስነስርአት የአልተመሰረተበት፤ ከንጉስ ስርአቱ ተከትሎ ማህበረሰብእአዊትነት (socialism)፣ ቀጥሎ ዘር-ወለድ ስርአት ሀገርን የሰራበት እውነት ነበሩ። ዛሬም፤ ድህረ-ንጉስአዊ ረዥም ታሪኩን ተከታይ፣ ስልጡን እና ወጥ ሀገርአዊ መሰረት የለም።
መደምደሚያው፤ የመንግስት ምስረታ ምርጫ ፉክክርዎች፣ አስተዳደርአዊ ጉዳይዎችን ብቻ እሚፎካከሩብአቸው አይደሉም እሚለውን ነቁጥ መነሻ የአደረገ ነው። መንግስት የመመስረት ጥያቄ በኢትዮጵያ የአለው ብቸኛ የስነውሳኔ ጥያቄ አይደለም። ሀገርንም በወጥ መንገድ የመመስረት እና ህዝብአዊትነትን የመከወን መንገዱ ገና አልተነካም። ይህንን አንዳንድዎች እሚነካኩት ነው።
ወደ ሶስተኛው መንገድ ደግሞ እንሻገር። መንግስትነትን መመስረትከ ሀገርንም እነዲህ-እንዲያ መቅረጽ የኢትዮጵያ ጥያቄዎች ማብቂያዎች አይደሉም። ጥንትአዊቷ እና የድሃድሃዋ ሀገር፣ የመሰረተ ስልጣኔም ሶስተኛው እና ከመንግስት ቀጥሎ ከሀገር ምስረታ ቀጥሎ እሚጠብቃት ገጣጣ ጥያቄዋ ነው። መሰልጠንን በረዥም እቅድ የእሚያልም ስነውሳኔአዊ የምረጡኝ ፉክክር ደግሞ፤ ይህንን ሶስተኛው ጥያቄን ማሰብ እና መመለስ አለበት። በቀረ፤ ተራ አስተዳደርአዊ እድል ፍለጋ እና ቆይታን ማለም እንጂ፣ ትርጉምአማ ለውጥን ማምጣት እሚፈልግ ወይም እሚችል ወይም እሚያውቅ ትረት አይደለም።
መንግስትነት ምስረታውን ማሰስአቸው ለድርጅትዎቹ በደፈናው፣ የስነምጣኔ ምንደጋ እና እድገት (economic growth and development)፣ መመስረት ከመሆን ይልቅ፣ ሰፊዎቹ ጥያቄዎችን ማለትም ሀገር መስርቶ ወደ አለም-ደረጃ ስልጣኔ ማምጣት መሆን አለበት። ትልቁ የስነውሳኔ ፉክክር ውድቀት ስለእዚህ እሚሆነው፣ ትልቅ ጥንትአዊ ታሪክ ከትልልቅ ወቅትአዊ ቀውስዎች እና ተቃርኖትዎች ተጣምረው የአለባትን ሀገር፣ የወቅቱን ችግር ተመልክቶ እየአከሙ ለማስተዳደር ከመምጣት ወደ ፍቱንአዊ (የረዥምጊዜ) ምልከታ መዞሩ ነው። የረዥሙ ታሪክ እና ረዥሙ ጠቢ ተቆራኝተው የሀገር ምስረታውም ሆነ መንግስት ምስረታው አናሽ ጥያቄዎች ተደርገው፣ ወደ ትልቅ እይታ እና ስለእዚህ ትትረት መገባት አለበት። መነገር እሚገባውም፣ የወቅቱ ንዑስ ግን ቸላ ስለተባለ እንዲሁም በረዥሙ መመልከት ስለአልተለመደ፤ የገዘፈ የመሰለንን ችግር ለማከም ብቁ ነኝ ምረጡኝ ከማለት፣ በላጩን የረዥም ታሪክ እና ረዥም ጠቢ ውብ መስተጋብር ኢላማው የአደረገ እንቅስቃሴን ማቅረብ መቻል አለበት። በቀረ፣ አጭር ጉዳይ እንጂ ረዥም መፍትሄን ማቅረብ አልቻልንም።

በደፈናው፤ የኢትዮጵያ ብዙዎቹ ስነውሳኔ ተቃዋሚዎች፣ እሚከተሉት የሃሳብ እና ርእዮተ-ኢትዮጵያ፣ ህጸጽ የአለበት እና ስነውሳኔአዊ መብቃት ላይ የደረሰ አይደለም። ለምሳሌ፤ በደፈናው፣ ሰላም ሻጭነትን ለማስወገድ እንሰራ አለን። ሰላም እናመጣ አለን። ሃብትአዊ ፍትሕ እንፈጥር አለን። ወዘተ. እሚሉ ደፈናአዊ ጉዳይዎች አሉ። እነእዛ ከቶ ዋናው መፍትሔዎቹ አይደሉም። ላይላይ እሚታዩ ጉዳይዎች ናቸው። የሳቱት ሁለንተናአዊነትን የእሚፈጥር ርእዮት ክወና ነው።
ይባስ ብሎ፣ ጥቃቅን ነ ይዘን አለ እንመረጥ ብለው ደግሞ ለታናናሽ ነገርዎች እንደ እሚጥሩ ይናገር አሉ። ለምሳሌ፣ የእናት ድርጅት ተፎካካሪው አንድ ተወካይአቸው፣ በ ኢትመ. (ETV) የከተሜነት እና መሰረተልማት ርእስ ላይ በተደረገው የሚያዚያ 26 ኛው ቀን 2013 ስርጭት ላይ ለስድስተኛው ብሔርአዊ ምርጫ ምረጡኝ ዘመቻው ቀርቦ የነበረ አንድ ነጥቡ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እንጦጦ መናፈሻ መግቢያ ዋጋው ፪መቶ ብርዎች በመሆኑ ደሃውን አይደግፈውም፣ ስለእዚህ እኛ ብንመረጥ እናኗንቀንሰው አለን እሚል ነበር። በመሰረቱ የከፋ ኢላማ አይመስል ይሆን አለ። ዳሩ፤ የቀረው ወሬ እምብዛም የረባ ነጥብዎችን ስለ አላቀረበ፣ ይህን ልንነቅፍ እንገደድ አለን። በኢትዮጵያ የከተማ እና መሰረተ ልማት ጉዳይዎች፣ ተቆጥረው አያልቁም። ገና የአልተመሰረተው ከተማ፣ ከተመሰረተው ደግሞ ዝማኔ እና ሙያአዊነት የያዘው፣ ለረዥሙ ጠቢ ደግሞ እሚታቀደው የትየሌሉ፣ ሶስት መጽሐፍአዊ (እጅግ አብይ) ነጥብዎች ናቸው። ከእነእርሱ ጋር ደግሞ እማያልቁ እሚመስሉ ተያያዥ ጉዳይዎች አሉ። ከገጠር ሲወጣ መቋቋም የአለበት እና ኢትዮጵያ የእማታውቀው የባህል ወይም ከተሜነት ወጥ ፍልስፍና፣ የስነምጣኔ፣ ወዘተ. ጉዳይዎች አሉ። ይህ ሁሉ ሳለ፣ ገና የአልተመሰረተ ሀገር ተይዞ፣ የመናፈሻ መግቢያ ዋጋ ማስተካከያ ቃልመግባት ትልቅ ሆኖ መቅረብ እሚገባው ነጥብ አይሆንም።
አዲስአበባ ውስጥ መጓጓዝ፣ መዋልማደር፣ መጠለያማግኘት፣ ሰላም ወይም ደህንነት ማግኘት፣ አገልግሎትዎችን በፍትሕ እና ቅልጥፍና መገልገል፣ ሌላ እማይቆጠሩ መሰረተልማትዎችን ማግኘቱን እንዲያመቻቹ ቃል እንከለ መግባቱ እምብዛም የተፎካካሪ ፍፃሜ መከራከሪያ መሆን አይገባውም። ችግርዎቹ እንደ አሉ ይታወቅ አለ። መፍትሔው እነእሱን ዘርዝሮ አስተዳዳሪውን ድርጅት ማሳጣት አይደለም። ሲበዛም፣ የለእነእዚህ የተሻሻለ ነገር ለማቅረብ መዘርዘሩ አይደለም። መፍትሔው፣ ስር መቅረብ እና ስር መትከል እንጂ የአገጠጠውን ችግር መንቀስ እና ህክምናውን ማቀድ አይደለም። ተጨማሪ ለምሳሌ፤ በኢትዮጵያ በወቅቱ ከተደጋገመው አንኳር እና ጥቁር ችግሩ – ዜጋዎችን ከብሄርተኮር ግጭት በተከተለ መፈናቀል እና ሞት መቀጣት – ከመደጋገሙ ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት፣ ብዙ ተቃዋሚዎች እሚናገሩት ሰላም እናመጣ አለን እናስታርቅ አለን ወዘተ. ነው።
ይህ እጅግ አስደንጋጭ ነው። አንድ ወቅት በቅርቡ፣ ይህ ችግር ሲንበለበል ከነበረበት ወቅት በአንዱ በወለጋ የአማራ ጎሳ ተብለው የአካባቢው ሙሟሙ ትውልድ የሆኑትንም ጭምር አሸባሪ የተሰኘው የኦነግ ሸኔ ነው በተባለው በተከወነ ጥቃት፣ ብዙዎች ሲሞቱ እና ሲዘረፉ፣ ከኢትዮጵያ-ብሔርአዊ-ሽማግሌዎች ቁንጮው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እንደተቆጣው …እኛ መሬት ላይ አመለካከትን ስለ እምንከውን እየተጋደል የአለንው በመሬት የተነሳ ሆኖ አለ። ግን ዘመኑ መሬት ለማግኘት እምንገዳደልበት ሳይሆን፣ የሰውዘር መሬቱን ጥንት ለቅቆ አየሩን እና ኅዋውን እየኖረበት እየነገደበት ስለሆነ፣ እኛም ከመሬትተኮር አመለካከት ወደ ዘመነ አመለካከት መምጣት አለብን…።
በአጭሩ ነጥቡ፤ መሬትን እንደሁሉ ነገር መሰረት አድራጊ አመለካከት ችግሩ ከሆነ፣ መፍትሔውም ያው ይሆን አለ ማለት አይደለም። ያንን የወለደ መኖሩ አይቀሬ ነው። ችግሩ እጅግ ጥንትአዊ ነው። ታላቁ ሯጭ ይህን የተናገረው ስለእዛ ነበር። እንዲህ ከሆነ፤ መፍትሔው ፉክክር በተርታው ችግር ዙሪያ መሆን የለበትም። የእምንመለከተው ችግር የበረዶው የሰገገ ጫፍ ነው። ከስር ዋናው ችግር አለ። ያንን መንግሎ በመንቀስ መጥለቅ አስገዳጁ ጉዳይ ይሆን አለ።

የውይይቱ መቋጫአችን ተጨማሪ ተግባርአዊ ነገር (practical case) ውይይት ይሁን። የኢትዮጵያው ማህበረሰብእ ከስነውሳኔ ገበያ ተፎካካሪዎች ዘንድ ትርኪምርኪ መፈለጉ ወይም አለመፈለጉ አይደንቅም። በስልጣኔ እና ስነውሳኔአዊ ግድየለሽ ህዝብነቱ የታወቀ ነው። በተለይ ሀገረሰቤው፤ እሱም የመንግስት ሚና እና ጥቅም የአልደረሰለት ስለሆነ አይደንቅም። ህዝቡ የአንቀላፋ መሆኑ የተማረው እና ውሃእሚነሳ ንቃተህሊና የአለው ቁጥር አናሽ ከመሆኑም የተነሳ እሚገመት ነው።
ታዲያ ለእዚህ ህዝብ፣ ቀላል ወሬ አነሁላይ፣ የአልተመዘነ ስብከት አሳሳች መሆኑ አይደንቅም። ለምሳሌ፤ የ ህዋሃት፣ የእረዥም ጊዜ ብሔርብሔረሰብእአዊነት የተመሠረተው እና የተሳካለት በህዝቡ ንቃተህሊና አለመመስረት የተነሳ ነው። የስነምጣኔ እና ስነውሳኔ ዓለሙ ውስብስብ ጉዳይ ለሀገረሰቤው አይገባውም። ያም፤ ማንነትህ ተነካ፣ ብሔረሰብእነትህን አክብሬ ልያዝልህ ወዘተ. በእሚሉ ስብከትዎች የተሸነፈ ሆኖ ቀርቶ አለ።
ዛሬም፤ የፈነገለውን ህዋሃት. ብሔር ብሔረሰብአዊነት ፍልስፍና የቀማው ብልጽግና፣ በእውቁ እና በተዛባ መልእክት ተወዳጅ ዘፈን በሆነው የብሔርብሔረሰቦች ዘፈን በታጀበ ምረጡኝ ቅስቀሳአቸው (ሚያዚያ 26ኛው ቀን 2013 ዓም፤ እረፋድ በ ኢትመ. የተሰራጨ) ላይ ተቃዋሚዎችን የብሔረሰብእ መብትዎች ጨፍላቂ አድርጎ በማሳበቅ ዝግጅት አቅርበው ነበር። ዘፈኑ የህዋሃት ትግል እና መስዋእትነትን አንቆለጳጳሽ፤ ብልጽግና ደግሞ የእነእዛ ታጋይዎች አታስፈልጉም ወንጀለኛዎች ብሎ ደምሳሽ ነው። ዳሩ፤ ምንም ግለ-ሃፍረት የለም። አምባግነና እና ስነምግባር ተቃራኒ ናቸው። ያ እንደ አለ ግን፤ የአነሳንው ነጥብን ስንቀጥል ይህ አስተማሪ ነው። ይህ በእየጉራንጉሩ ከዓለም ተሸርፎ እሚገኝ ሀገረሰቤን አቃቤነት ልቆምልህ ነው ብሎ ምረጠኝ ባይ የምርጫ ፉክክር ሀገር አይገነባም፤ ስልጣኔ አያቋቁምም አይመሰርትም። እንዲህ ባሉ ትርኪምርኪ ነጥብዎች በድሃድሃዋ ሀገር ተቀዳሚ ጉዳይ ተደርጎ የድርጅትዎች ፉክክር መከወን አይገባውም። የድርጅትዎች ፉክክር፤ ከጨለማ ድህነት ሀገር አሠልጥኖ ፈር ቀዳጅ ስለመሆን እንጂ፣ በጨቀየው ሀገር ከፋፍሎ መብትዎችን ለመጠበቅ በእሚለው ቅኝግዛትአዊ ጭንቅ ዙሪያ መንቀሳቀስ አይገባውም። ብዙ ችግርዎች ተነባብረው በአሉበት፤ በትናንሽ – ዝብ ጭምር – ጥያቄዎች አቅምን ማባከን ሀገር እና ታሪክ ሰባሪ ነው። ማንም ባይገመግመኝ እንኳ እራሴን ልግዛ ከእሚል ግለ-ስነምግባርአዊ ደግ ርእዮት ይህ ሀገር እና ጠቢው ይጠቀም አሉ። እስከ እዛ፣ የምባግነና ክፉ ታሪኩን ሲቀጥል፤ መልሰን መገንዘብ የአለብን፤ እሚያስፈልገን ላቂው ፉክክር ያም ሀገር እና ጠቢ መስራች እንጂ ሌላ አይደለም፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s