Categories
የንባብ ፉክክር [rEADEING cHALLENGE]

የ ከበደ ሚካኤል “ታሪክ እና ምሳሌ ፩ኛ መጽሐፍ” የመጽሐፍ ጭምቅ (Book Summary)

Kebede Micchael’ Amharic ተረት እና ምሳሌ፣፩ (Terete ena misale = Fable and Parable) summarised 64 pages into 5 pages with all contents present in Amharic.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, June 5th 2021 GC.,

ሁለተኛ እትም፦ 1992፤ በ ሜጋ ኃግማ.፤ ገጽዎች፦ 64 [በ ተአዶ. (PDF) ይህን ጭምቅ ከ አካዳሜያ አውርዱት ወይም ከ አርካይቭ ይጋሩ።

የኀይል እና ክብር ምንጭ
፩) ሀገር ነው። [ሀገር፦ የቀደሙ ወላጅዎች ኖረው የአወረሱት ስጦታ፣ የተሳሠረ ህዝብ የአለበት፣ ህዝቡ እሚያድግበትን በረከት እሚያገኝበት በረከት የአላት እናት ምድሩ፣ ውስጡ ከማደግ የተነሳ ስነልቦናአዊ ፍቅር የአለበት፣ አንድ ክፍለ ዓለም ነው።
፪) ህዝብ ነው። [አንድ መንግስት፣ ህግ፣ ሰንደቅ፣ ውስጥ የአለ ህብረተ ሰብእ፤ የአለፈ ታሪኩ የአስተሳሠረው፣ ለነገ በአበጀው አንድ ተስፋው የተሳሠረ ነው።]

፫) ሰንደቅ አላማ ነው። [የነፃነት ምልክት፣ የህዝቡ ማህተም፣ የህብረቱ ማሰሪያ ሀረግ ነው፦ ተመልከት አላማህን፣ ተከተል አለቃህን፣ ተብሎ ሰራዊት ሲተምም፣ ትእምርተ ኀይል እና መዊእ ነው።

ታሪክ እና ምሳሌ።
ኢትዮጵያዎች የግድም ቢሆን መፈጸም የአሉብን ሀሳብ ነገርዎች ዝርዝር፦ 1) ሀገር ከጥቃት መጠበቅ እና ማስጠቀምን እስከመስዋእትነት መፈጸም፤ 2) ሀገር መውደድ ሀገርን አስከባሪ ስራ መስራት ነው፤ 3) ሀገር ከእሚያስንቅ ስራ መሞትን መምረጥ፣ 4) በስራአችን ሀገር ትታይ አለች፤ 5) ሀገርህ ከምንም ትበልጥ አለች፤ 6) ሌላው ለሀገሩ እንደእሚሰራው አንተም ለሀገርህ ስራ፤ 7) አንድ ኢትዮጵያአዊ ሲነካ የተጠቃው ሀገር እናትህ መሆኗን እወቅ፤ 8) ሌላው ዜጋ ሳይደላው አንተ ቢደላህ የህልም ወርቅ ነው፤ 9) ከሀብት ይልቅ ለሀገር የሰራውን ታሪክ ሲያነሳው ይኖር አለ፤ 10) የሰለጠኑ ሀገርዎች ከደረሱበት ሀገርን ለማድረስ መታተር እና መድከም ይገባን አለ።

አንድ አመት 12 ወርዎች፣ 52 ሳምንትዎች፣ 365 (በአራት አመት ደግሞ 366) ቀንዎች፣ በወር 30 ቀንዎች፣ በሳምንት ሰባት ቀንዎች፣ በቀን 24 ሰዓትዎች፣ አሉን። ጥቢ፣ በጋ፣ በልግ እና ክረምት በተሰኙ ወቅትዎች ነን።

እግዚእአብሔርን መፍራት የሁሉ መጀመሪያ፤ ከማዘዝ ቀድሞ መታዘዝ፣ ጥሩ ነገርን ከልክ አለማሳለፍ፣ ትእቢት እና ውርደት አካል እና ጥላ እንደሆኑ ማወቅ፣ መጽሐፍዎች የመንፈስ ምግብ ናቸው፣ ከበላይህ በሆኑት ከመቅናት ከበታችህ በአሉት መጽናናት፣ በወደቀ እና መከራ በገጠመው አለመፍረድ፣ ብትሰራም አትመካ፣ መልካም ነሩን ከሀገሩ እንደ አገኘ ሰው ለሀገሩ መስዋእት መሆን አለበት፣ ቃል ለሰው ሃሳብ ሊገልጥ ሳይሆን ሊሸፍንበት ተሰጠው፣ ከሰነፍ ሰው በቀረ ይቅርታን ለማንም ስጥ፣ ጦርነት ብትጠላ ለውጊያ ተዘጋጅተህ ኑር፣ ጌታነት እና ድኽነት ጎንለጎን የአሉ እንጂ የተራራቁ አይደሉም፣ የአልሰራህውን የሰራህ መስሎህ እየታበይህ አትኑር፣ ቅን ሰው ደግ አውርሶ እሱንም ይሰዋ አለ፣ ሰው በማሰብ፣ መናገር እና መስራት ሶስት ሙያዎች አሉት (አንዱን ወይም ሁለቱን ብቻ ከማወቅ ሶስቱንም የተካነ መሆን ግድ ነው)፣ ደስታ ማለት ጤንነት ነው ጤንነት ማለት ሁሉም ነገር ነው፣ በአለም ላይ ትልቅ ነገር የእሚሰራው ሰሪው እና አሰሪው-(የተመቸ)-ጊዜ ሲገናኙ ነው፣ ተንኮለኛዎች እና ክፉዎች ትልቅ ቦታ መድረስ እሚችሉበት አለምም ነች፣ የአለም ሁኔታ ቢከፋንም ቢያስደስተንም ከመቀያየሩ እኛ አናስቆመውም፣ ማንኛውም ሰው በሰፊዋ አለም ፊት ኢምንትነው እና ነብሱ ያንን አውቃ ትኮማተር ዘንድ ይሁን።

ብረት ድስት እና ሸክላ ድስት [ግጥም]፦ ሸክላ ድስትን ብረት ድስት ጓደኛነት ጠይቆት ሲጓዙ ንፋስ አጋጭቶአቸው ሸክላ ተሰባበረ፣ ሽርክና ከእኩያ እንጂ ከበላይ ከሆነ የበላይ ጎጂ ይሆን አለ)።
እብደት፦ እብደት ከሁሉ የበለጠ በሽታ ነው ሰውን እንስሳ አእምሮ የአደርገው አለ እና። ካሊጎላ የተሰኘ የሮም ንጉስ በጭካኔው የተነሳ የታወቀ ሲሆን እብድ ነው ብለው ተረድተውት ነበር።
አስቸጋሪ ፍርድ፦ በአንድ ሀገር ብቸኛ የሆነ ቀጥቃጭ ሰው ገድሎ፣ ሞት ተፈረደበት፣ ማህበረሰቡ ተሰብስቦ ሊገደል ሲል ሁለት ሸማኔ አለን መግደል ግድ ቢሆን በእጣ አንዱን ግደሉ፣ እሱ ቢሞት ማረሻ፣ ዶማ ሰሪ የለንም ብለው አቤቱታ አበዙ፣ ዳኝነት ጣጣው ብዙ ነው።
ረኀብን እሚሻ ሃብታም፦ ተረቦ እማያውቅ ሀብታም ብራብ ብሎ እንደ ተመኘ በመንገድ ሲጓዝ ተራብኩ መጽውቱኝ እሚል ቢመጣ ብዙ ሳቀበት እና መራብን ፈልጌ አንተ ትሳለቅበት አለህ ብሎ ተቆጥቶ ሳይመፀውተው አለፈ።
ደራሲ እና ሌባ፦ የተራበ ድኻ ደራሲ ቤቱ ተኝቶ ሳለ፣ ሌሊት ሌባ መጥቶ ልብሱን እና ቤቱን ቢበረብር ብር አጣ፣ ቁጭ ብሎ ሲመለከት የነበረው ደራሲ ሳቀ እና በሌሊት ቀርቶ በቀን ብርሀን ብር አላገኘሁም እርቦኝኛ አለሁ አለው።
[ግጥም] ሁለት አፍ የአለው ወፍ፦ ሁለት አፍ ይዞ እሚኖርን ወፍ አንድኛው አፍ ሁሌ የተገኘውን ቀድሞ እየበላ የአሳዝነው ነበር፣ ቢመክረውም እንቢ እየአላ ሲያናድደው፣ አንድ ወቅት በመርዘኛ ዛፍ ሲያርፍ የተበደለው አፍ በላው ሌላውም አትዋጠው ይገድለን አለ ቢለውም እንቢ አናድደኽኝ አለህ ብሎ ዋጠው እና አብረው ሞቱ፣ የተናደደ አፍ ነብሱንም ትቶ ልጉዳ ሲል ስግብግም የጋራ ንብረትን ይጎዳ አለ።
አንዲት አህያ ርኅራኄን አስተማረች፦ በመንገድ ሲያልፉ ሁለት ልጆች እንቁራሪቷን አይተው በድንጋይ ለመግደል እያለሙ ሲወረውሩ አህያ ከፊትአቸው አለፈች፣ እንቁራሪቷን ልትረግጥ ስትል ተጠንቅቃ ዘልላ አለፈቻት፣ እነእሱም ከአህያ የበለጠ ርኅራኄ የለንምን ብለው ትተዋት ሄዱ።
መልካም ምላስ ቁጣን ታበርድ አለች፦ ህፃንን በኮክ ዛፍ እየወጣ ሲመገብ እንዳይወድቅ ደጋግማ እናቱ ብትቆጣም ዛሬም ወጥቶ አገኘች እና ከጓዳዋ ስትመለከተው፣ ጠራችው። ልትመታው ስትል እመኚኝ አልወጣሁም ብሎ ተከራከረ፣ ብወጣም በቃ ከወደድሽኝ ውውሸቱንም እመኚኝ በእሚል ሃሳቡ ተማርካ አቅፋ ሳመችው።
ከባለቤት የአወቀ ቡዳ ነው፦ ሰው ስራ በዝቶበት ለአሽከሩ ማንም ቢመጣ የለም በል ብሎት አሽከሩ ብዙ ፈላጊውን ሲመልስ ውሎ፣ አንድ ፈላጊው መጥቶ የለም ሲባል በመስኮት ሰውየውን አየ እና አየሁት ጥራው አለ፣ ገብቶ አሽከሩ ሲናገር ባለቤቱም ወጥቶ የለሁም ብሎ በንዴት በሩን ዘግቶ ተመለሰ።
[ግጥም] አንድ ሀብታም እና ድኻ ሰው፦ ጫማ ሰፊ ድኻ በማለዳ በአማ ድምጽ ሲዘፍን ጎረቤቱ ሀብታም ሰው እየሰማ ሲደሰት አንድ ቀን አስጠርቶ ጠየቀው። እሱም ድኻ ነኝ ሲል ከረጢት ወርቅ ሰጠው፣ ቤቱ ወስዶ ቀበረው። ሌሊት ይጨነቅ ጀመረ፦ መሸለሜም የሰማ ገድሎ እሚቀማ ቢመጣብኝስ ብሎ አለእንቅልፍ ብዙ ዋለ አደረ። በመጨረሻ ለሀብታሙ ወርቁን መልሶ በድኽነቴ ልዝፈን ብሎ ተለየው። ሀብት ሁሌ ደስታ የለውም።
ሰነፍ ተማሪ፦ ተማሪውን ሀሁ ማስቆጠር አልተቻለም። አልቅሶ የአገኘው መንገደኛ ሲጠይቀው ሀ ብዬ እስከ ፖ ጨርሼ ነበር። ግን፣ ጣው አያልቅም፣ ከአዲስ በለው ይይሉኝ አለ አለጥፋቴ ብሎ መለሰ። ሰነፍ ተማሪ ፊደልን ተራራ የአደርጋት አለ።
ታማኝነት ከሁሉ የበለጠ ነገር ነው፦ የንጉስ ግምጃ ሰራተኛ እየሰረቀ ብር አጠራቅሞ አንድ ቀን ጠብቆ ከእዚህ ወጥቼ ልነግድ ፍቀድልኝ ሲል አለቃውን አስጠርቶ እንዴት ይሰራ ነበር ቢለው የጎደለውን ነገረበት ንጉሱም ባዶ ጠርሙስ ወተት የአገኘ እንስሳ ገብቶ ጠጣው እና ሊወጣ ሲል ሰውነቱ ጠጠረበት ምን የአድርግ አለው? ወተቱን መልሶ ይውጣ ሲል አንተም የአው ነህ ብሎ መልሱን ሰጠው። መታመን ከሙያ በላይ ነው።
ስካሮን፦ ባለቅኔው ስካሮን ብዙ ዘመኑን በስቃይ ታምሞ ተኝቶ ኖሮ ሲሞት በድንጋዩ የአዘዘው አጭር ግጥም ተፃፈለት፣ ያም በአጭሩ በእርጋታ እለፉ እንጂ ከድካሜ ልረፍ እሚል ነበር።
[ግጥም] አውራዶሮ፣ ድመት እና የአይጥ ግልገል፦ ግልገል የሆነች አይጥ ከእናቷ ተለይታ ስትጎበኝ ደገግጣ ተመልሳ ለእናቷ የገጠማነን ተረከች። የአማረ እሰሳን አጊንታ ስትቀርበው ሌላው ሲርገበገብ ደንግጣ መጣች። እናቷ የአማረው ጠላት ድመት ሌላው ዶሮ ነው ብላ ፊት ታይቶ በመልክ፣ ከጠባይ መመርመር ውጭ ማንንም ማመን አይገባም አለቻት።
የአንድ አዋቂ መልስ፦ አንድ አዋቂ በመርከብ ከአሻጋሪው ጋር ሲጓዝ ማእበል መጣ እና ደነገጠ፤ ምሁር ሆነህ ከኔ ደነገጥህ ሲለው ብሞት አለምን አጎድል፣ አንተ ብትሞት ምንም አለም አይጎዳ፣ ብሎ አሳፈረው። ሞት ፊት ሁሉ እኩል፣ እና ሁሉ መፍራት ቢገባውም፣ አዋቂ የተማረ ግን መልስ አያጣም።
መልክ እና መስታወት፦ አስቀያሚ ሰው ፊቱን በያስጠላል ሀሜት እንጂ በመስታወት ሳያይ ኖሮ መስታወት ድንገት አንድቀን ሲያገኝ እራሱን ተመልክቶ ባለማመን ሰበረው። መልክ ክፉ አመል፣ መስታወት ሀቀኛ ጓደኛ ችግርአችንን ነጋሪ ነው። ክፉ አመሉ ሲነገረው አምኖ ሊለውጠው እሚቀበል እጅግ ጥቂት ነው።
ትክክለለኛ ዳኛ፦ የተካሰሰ ሰው ወደ ጓደኛ ዳኛው ሄዶ ነገ መምጣቴ ነው ጓደኝነትህ ለመቼ ነው በል አድላልኝ ሲለው ተቆጥቶ አበላሽቼ እንዳልፈርድ ከአላገዝከኝ ለህሊናዬ ከአላገዝከኝ ጓደኛነትህ ምንላይ ነው፤ በገንዘብ በሌላ አቅሜ እንጂ በአምላኬ እና መንግስቴ ፊት በሃቄም ፊት አላደላልህም ብሎ መለሰለት።
የዱባ ፍሬ እና የሾላ ፍሬ፦ አንድ ባላገር በገጠር ሲጓዝ ደክሞት ሾላ ዛፍ ስር አረፍ ብሎ ሾላው ትልቅ ዛፍ ፍሬዎቹ ትንንሽ ሆነውበት፣ አጠገቡ ዱባ ተጋድሞ ፍሬዎቹ ተልቀውበት ተመለከተ። በመደነቅ፣ አምላክ ተሳስቶ አለ ፍረሀዎቹ መቀያየር ነበረብአቸው ብሎ ፈርዶ እንቅልፍ ወሰደው። ሾላ ፍሬ ወድቆ አፍንጫውን መትቶት ደምቶ ተነሳ፣ ዱባ ቢሆን ጨፍልቆ አናቴን በገደለኝ፣ አምላክ አይሳሳትም ለካ ብሎ ከአንተ የተሟገተ መሸነፉ አይቀርም ለሁሉ ምክንያት አለህ ብሎ ተነስቶ ሄደ።
ሶቅራጥስ፦ ሶቅራጥስን ከመታወቁ የተነሳ የመቄዶኒያ ንጉስ አርኬላዎስ ና እና በቤተመንግስቴ አክብሬ ላኑርህ ሲለው እኔ በሀገሬ ውሃ በነፃ መብልም በርካሽ አገኝ አለሁ፣ ለመልካም ሀሳብህ አመሰግን አለሁ አልመጣም ብሎ መለሰለት። ምን ቢደላ ከውጭ ከመኖር በሀገር መኖር ጥቂት ከአለ በቂ ነው ማለቱ ሲሆን፣ ከመረመረ እና ከአጠና በኋላ ተማሪው ቢጠይቀው እሚያውቀው አለማወቁን መሆኑን ነገረው።
ኤዞፕ፦ ኤዞፕ በመንገድ ሲጓዝ ኬለኛ መዳረሻውን ሲጠይቀው አላቅም በማለቱ ተናድዶ አሰረው። መልሶ ተናገር እና ልልቀቅህ ቢለው የትአውቄ፣ አሁን እዚህ እስርቤት መግባቴን አውቄው ነበርን? ሲለው ይሄስ ቀልደኛ ነው ብሎ ለቀቀው።
ተጫዋች ሰው፦ ነገር በሆዱ የገባ ሰው እያሰላሰለ ሲሄድ አንድ ተጫዋች ሰው አይቶት በመሳሳት ሰላም አለው መልሶ ይቅርታ ሌላ የማውቀው ሰው መሰልክኝ አለው ተጓዡም እኔም የሆነ ሰው መስለኽኝ ነበረ ሲለው፣ ተጫዋቹ በል እኔም እኔ አይደለሁ አንተም አንተ አይደለህ ብሎት አለፈ።
እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት፤ እጅግም ብልሃት ያደርሳል ከሞት፤ እድሜዘመንአቸውን መጽሐፈ ጥበብዎችን የመረመሩ ሶስት ሰዎች አሁንስ ወጥተን ለእውቀትአችን እሚገባ ስራ እንስራ በማለት ወደ ቤተመንግስት ለመጓዝ ወጡ። ከጓዙ አንድ የአልተማረ በተፈጥሮ አስተዋይ ተከተለአቸው እና ወዲያው ጫካ ደርሰው የአንበሳ አጥንት አጊንተው አንዱ በሉ እንወዳደር ብሎ ጥቂት ደግሞ የተበታተነ አጥንቱን ሰብስቦ አንድ አደረገው። ሶስተኛው በመፎካከር ነብስ ሊሰጠው ሊደግም ሲል የአልተማረው በትር እንጂ የለንም ምን ማረግአችሁ ነው አንተ ደንቆሮ የአስነሳንው አይበላንም ምን አገባህ አሉት እና ዛፍ ላይ ተሰቀለ። ነብስ ሲሰጡት ሁለቱን ነረሃቡ።የተነሳ በልቶ አንዱን እየጎተተ ወደ ዋሻ ወሰደው። እጅግ የበዛ ነገር አይበጅም፣ መልካሙም በፉክክር ከተደረገ ደግሞ ይጎዳ አለ።
[ግጥም] ጽጌረዳ እና ደመና፦ ልትደርቅ የአለች ጽጌዳ ዳመናውን ውሃ ስትለምነው ስመለስ አዘንብልሽ አለሁ ብሎ ሄደ። ሲመጣ አዘነበ ግን ደርቃ ስለነበር አላዳናትም። ሰውም በህይወት ሳለ መረዳዳት እና ማዳን እንጂ ሲሞት ተዝካር ለቅሶ ተሰብስበው ቢለፉለት አይረባውም።
በአንድ ባለጠጋ በረት የሆነ ሁከት፦ በአንድ ባለጠጋ ብዙ ከብትዎች ሲገኙ እጅግ ሌሊቱን ይታወኩ ነበር። አንድ ሽማግሌ ሲያማክር ሌላ በረት ሰርተህ ለሁለት ከፍለህ አሳድርአቸው አለው። ያንን ሲከውን አንዱ በሰላም ሌላው በመታወክ አደረ። ያንን ሲያዋይ የተረበሸውን ደግሞ ሁለት ክፈለው አለው ያንን እያደረገ ከብዙ ሺህ ከብት በስድስት በረት ከፋፍሎ ደቂት እየተረበሸ እሚያድር በረት ላይ ሲደርስ፣ አሁን ቆመህ ተመልከት ሌሊቱን አለው። ሲከውን፣ አንድ ወይፈን እየሮጠ ሁሉን እየወጋ እሚያውክ ሆኖ አገኘው። እረደው ወይም ሽጠው አለው። ሲወጣ ሁሉ ሰላም አደረ። መልሶ በአንድ ትልቅ በረቱ አኖረአቸው። ሰው መሀከልም ችግር ጨማሪዎች አሉ፣ በብልሃት ግን ይገኝ አሉ።
የክፉ ሰው ስሙ ምንጊዜም መጥፎ ነው፦ አንድ ቤተሰብ፣ ዘመድ ጭምር የአገኘውን ሁሉ እሚያጣላ ሰው ሞተ። ሰዎች ሰይጣን መቼም ለኩነኔ ጥቂት ሃጢያት ስራ እንጂ እንደአሻህ ስትከፋ ኑር አላልኩም እንደ እሚለው አይጠረጠርም እያሉ ተጨዋወቱበት። ልጆች ሆይ ክፉ ሰው ሲሞትም ስሙ ክፉነቱ አይቀርም እና ተጠንቀቁ።
አንድ ፈላስፋ፦ አንድ የአረጀ አባት ሶስት ሣጥንዎች አሽጎ ለጎረቤቱ ሰጥቶ አስተምረህ ሲያድጉ ስጥልኝ አለው። አሳድጎ አስተምሮአቸው ሲጨርሱ ሲሰጥአቸው ትልቁ ወርቅ፣ ትንሹ ኩበት፣ ትልቁ አፈር አገኙ። እኛ ተበደልን አካፍለን ብለው ታላቅአቸውን ጠየቁ፣ እንቢ ሲል ዳኛ ፊት ወስደው ከሰሱት። ይህ ከባድ ነው፣ ምስጢር ከሌለው እኩል አይደለም እና ፈላስፋ ጋር ሂዱ አሏቸው። ሲጓዙ የደከመች ውሻ ልትወልድ ውሾቿ በሆዷ ሲራወጡ ደክሟት አዩ፣ ሲጓዙ የጠገበ ፈረስ ሲፈረጥጥ አዩ፣ ሲጓዙ ሌላ እንስሳ ተደብቆ ሳር ሲግጥ አዩ። ፈላስፋው ደጅ ገብተው ሲጠይቁት የአፈጀ ሆኖ ወደ ታላቄ ሂዱ እኔ አልገባኝም ሲል ታላቁ እንዴት ይጃጅ ብለው ሲሄዱ ጎልማሳ ነበር። እሱም ሰምቶ ወደ ታላቄ ሂዱ ሲል ተገርመው ሲሄዱ ወጣት ተቀብሎ ተገላቢጦሽ እድሜው እሱ ስለእማይናደድ እና ወጣቱ የበለጠ ስለእሚቆጣ፣ መሆኑን ነገሮ የአዩትን ጠየቀ። ውሻዋ እና ልጆቿ አውቅአለሁ ባይ የስምንተኛ ሺህ ልጅዎች ናቸው አለ። ፈረሱ የስምንተኛው ሺህ የእሚነሱ መሬት ጠበበችን ብለው ከድህነት ተነስተው ሰው የእሚያፋጁትን ወካይ ሲሆን የቀረው እንስሳ የስምንተኛው ሺህ ቀማኛ ነው። አባትአችሁ ብልህ እንጂ ሊያበላልጥ አልነበረም። ወርቅ የተሰጠህ ነጋዴ ሁን ስስትጀምር አትቸገር ሲልህ ነው። ኩበት የተሰጠህ በሬ አርባ ሲልህ ሲሆን አፈርማው ገበሬ ብትሆን ያዋጣህ አለ ሲልህ ነው አለአቸው። ተገርመው ተደስተው የተባሉትን ጀመሩ በአጭር ጊዜ ስኬትአማ እና ሀብታም ሆኑ።
ፋኖስ እና ብርጭቆው፦ እሳት ፋኖስን እምጠቅም እኔ እንጂ አንተ አደናቃፊ ነህ ብላ መስታዋቷን ስትሰድብ መስታዋት ጥሏት ሄደ እና ወዲያው ንፋስ አጠፋት። ሰውም የእሚጠቅመውን እና እሚጎዳውን ሳይለይ ከቀረ በእራሱ በአሳ የአመጣ አለ።
ቮልቴር፦ ስራን አብዝቶ እሚሰራ ቮልቴርን አንድ ወዳጁ አረፍ እያልክ ሲለው ሰው ሲሞት እስኪታክተው የአርፍ አለ፣ እስከእዛ ሊሰራ ነው የተፈጠረው።
[ግጥም] አዝማሪ እና ዉሃ ሙላት፦ አንድ አዝማሪ ዉሃ ዳር በማሲንቆ ሲዘፍን መንገደኛ መጥቶ ለምን ለውሃው እንደእሚዘፍን ሲጠይቀው እንዲያሳልፈኝ እራርቶ እንዲጎድልልኝ ነው ሲለው የሰማው ትቶህ ሲሄድ የአልሰማህ እየመጣ በችኮላ ጥሎህ ከከነፈ መቼም አይሳካልህም አለው። ሰምቶ እሚስተካከል ከሌለ አራሚ ተናጋሪ ቢበዛ ዋጋቢስ ነው።
[ግጥም] እሮሮ፦ አንድ ጣሊያንአዊ ለአንድ ኢትዮጵያአዊ ትክክለኛ የሆኑ ጉድለትዎቹን እያስመለከተ እጅግ ደንቆሮ ህዝብ መሆኑን እና ክብር እሚገባው እንደ አልሆነ ይገልጥለት አለ። ጣሊያን ግን ለአለም ብዙ የአደረገ እና የጥበብ ሀገር እንደሆነ ነግሮት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አለው የአለ ህዝብ ግን ምንም የእሚገባው ክብር ባለመኖሩ ሲሰደብ አይክፋው አለው። ሰው ተገዢ ሲሆን የአለበትን እዳ የእሚያመለክት ደግ ትርክት።
ሠነፍ ይከስራል ሰራተኛ ይከብራል፦ አንድ ግለሰብእ ምን ሰርቼ ልኑር ሲል፣ የአባቱ እርስት እና ሰራተኛዎችን ተገልግሎ መሬቱን በእርሻ እና ከብት እርባታ አልምቶ፣ ሊኖር አስቦ ሰራተኞቹ በነፃ በመብል ብቻ እየአደሩ ስለእሚሰሩ እየላከ እንዲሰሩ አስቦ ያንን ጀመረ። እሱም ይልክአቸው የነበረው ጧት ሆኖ ስሩ እና ኑ ሲል እሱ ፈንጠዚያ ውሎ ማታ ይመለስ ነበር። ሶስት አመት ስራውን አሰርቶ አላተርፍ ሲለው ሰራተኛዎቹም እየተራቡ ሲመጡ፣ ከፍሎ አከራየው። የተከራየው ቶሎ አትርፎ ኪራይ ጨረሰ እና እባክህ ልግዛህ ወይም አከራየኝ ብሎ ለመነው። እንዴት አልክ ሲለው አትርፌአለሁ አለው። እንደ አንተ ሰራተኛዎቹን ጧት ኑ ሂዱ አልልም። ኑ አብረን እንሂድ ነው እምለው። እነእሱም ሄደው እኔን እያዩ ስሰራ ጠንክረው ይሰራ አሉ። የአለገመውን ደመወዝ እቀጣ እና እየአበረታሁ ስንሰራ እጅግ አተረፈን። አንተ ሂዱ ብለህ ስትጠጣ ስትውል እሚማሩት ማልገም ነው። ሄደው አይሰሩም ነበር። ባይሰሩም ስለእሚበሉ ምን አስጨነቀአቸው አለው። ኑ ስራ ሂዱ ከማለት ኑ ስራ እንሂድ እሚሻለው ነው ብሎ መለሰለት። እሱም ተገርሞ በከፊሉ ሊሰራ ከፊሉን ሸጠለት።
[ግጥም] ክፉ ሰው፦ ክፉ ሰው ሁሉ መልካም ሲያደርግ፣ ጧት በክፋት ይነቃ እና ምንም ደግ ሳይከውን በክፋት ለመዋል የአቅድ አለ፤ የእሚውልበት ስፍራም ወዮታ የአለበት ነው።
[ግጥም] የሰራተኞች ዋጋ፦ አንድ መኮንን ገበሬን በመንገድ ይዞ ሲደበድበው ንጉሱ አይቶ አለፈ። በኋላ እልፍኙ አስጠርቶ ምሳ እንዲበላ ላከው፣ አሽከሩን ከእንጀራ ውጭ ወጥ ስጡት አሉ። መኮንኑ ወጣወጥዎች አቅርቦ ጠፋ። በመቆየት ሰልችቶ ሲወጣ ንጉሱ አግኝቶ ምሳ እንዴት ነበር አለው። ከእንጀራ ውጭ ምኑን ልብላ ተርቤ ነበር ቀረ ሳልበላ ሲል፣ እንግዲህ እንጀራ አምራች ገበሬ ጤፍ ነው ከአልተንከባከብንው እንዴት ይሆንልን አለ አሉት። ሰራተኛ ሁሉ የሃብት መነሻ እርካብ ነው።
[ግጥም] አስተዋይ ተማሪ፦ መምህሩ ሰው ከእንስሳ ይበልጥ አለ ሲል፣ ተማሪ ሰው ሲሰክር ማንም እንስሳ አይሰክርም ሲለው መልስ አጣ። አስተዋይ ተማሪ የጠየቀው ጊዜ፣ አቤት የመምሀር አባዜ።
[ግጥም] ፈሪ ጦረኛ፦ ናፖሊዮን አንቀጥቅጦ ሲገዛ፣ እጅግ ፈሪ አንድ ጦር መሪ ነበረው። ሁሉም በፍራቻው ይተርትበት ሳለ አንድቀን ከሰው ተጣልቶ ተታኩሶ ሆዱ ተመታ። ለናፖሊዮን ሲነገረው፣ በምግብ ተሳስቶ አብሮ በልቷት እንጂ የምር ተመትቶ አይሆንም አጣራ ሂድና ብሎ እሱም ቀለደበት።
[ግጥም] ሞት ሁሉን እኩል የአደርጋል፦ ድኻ እና ሃብታም ጎንለጎን ሲቀበሩ ተጣሉ፣ ተከታዩ ለቀደመው አትዳፈረኝ ሄደህ በእማይረባ ቦታ ተቀበር ሲለው የቀደመው እኔ በድህነቴ መሬት ነው ልማዴ አንተ በተመቻቸ ቤትህ ተኛ አትረብሸኝ አለው። ሞት ሁሉን እኩል አድራጊ ነው።
ሰው ለመሆን ብትፈልግ፦ [ሩድያርድ ኪፕሊንግ ታላቁ ሰው ይህን መከረ] የከበበህ ሰው ናላው ዞሮ ሃላፊነት ቢጥልብህ ሳትደናገጥ ተቀበለው። ሰው ሲጠረጥርህ ቅሬታ አይሰማህ መተማመንህን ብቻ ቀጥል። ወደፊት እሚሆነውን በትእግስት ጠብቅ እንጂ በከንቱ ጉልበትህን አታባክን። ሰው ሲጠላህ ቂም አትያዝ፤ ደግነት እና ልምምጥ አታብዛ (ራስህን ታዋርድ አለህ እና)። ምኞትን ተመኝ፣ ባሪያው አትሁን። አስብ፣ በሃሳብ ውሥጥ ብቻ አትቅር። በመጠን ተቀበልአቸው እንጂ ደስታ እና መከራ አታብዛ፣ ፈንጠዚያ እና ደስታ አታብዛ። የእድሜዘመን ስራህ ቢፈርስ ተስፋ ሳታጣ ተነስተህ በደከመ መሳሪያህ ስራህን ከአዲስ ጀምር እንጂ አትተወው። ስትነግድ የሰራህው ሁሉ ቢከስር፣ ከአዲስ ጀምረህ ነግድ። ሃሳብህ፣ ደምስር፣ ስጋህ እንቢ ቢልህ፣ በልብህ ከአመንህ ሁሉም ይመለሱልህ አለ። ለተመልካችዎች ሙያህን ስታሳይ አትደናገር፣ ንጉስም ፊት ብትቀርብ አትደናገጥ። ወዳጅ እና ጠላት ቢጎዳህ ልብህን አይክፋህ። ማንም ሰው ከአለመጠን አይተማመንብህ። ትንሽ ሳትል አንዲቷን ደቂቃ አክብረህ ሰርተህ ከአለፈች እንጂ አትተዋት። ይህን ሁሉ ብትከውን መሬት እና መልካሙ የእሷ የሆነው ሁሉ የአንተ ናት።
[ግጥም] አንድ ሰው እና ዝንጀሮ፦ አንድ ዝንጀሮ ጓደኛዎቹ መሀከል ተስፋ አጥቶ፣ ለብቻው ሲሄድ፣ ሌላው ሰውም ተስፋ በሰው መሀከል ሲያጣ ሊመንን ወጣ። ወዲያው በመንገድ ተገናኙ እና ጓደኛምዎች ሆኑ። ዝንጀሮው ሲጠብቀው ሰውየውን እጅግ ይዋደዱ ነበር። አንዴ ሰውየው አርሶ ሲጨርስ ሲተኛ ዝንጀሮው ሊጠብቀው ቁጭ ሲል በአፍንጫው ዝንብ ተቀመጠች እና ዝንጀሮው በዱላ ሲመታት አብሮ ሰውየውን ገደለው። ጥንትም ሲተረት፣ ከደንቆሮ ወዳጅ የተማረ ጠላት ተብሎ አለ።
[ግጥም] የፈላስፎች ንግግር፦ ተቃርኖት አይቀሬ ነው፦ ነገር ይገለባበጥ አለ፤ የአማረ ማስጠላቱ፣ ጎበዝ መሸነፉ፣ ወዘተ. እውቅ ነው። *** ፍሬ ወድቆ ከቆየ ሰውም ገንዘብ አግኝቶ መክበር ከጀመረ መበላሸትአቸው አይቀርም። *** አንድ ፈላስፋ እጅግ ሰውን መርምሮ ግብር አጥቶበት ይንቀው ጀመረ። *** ደንቆሮ እድለኛ ነው፣ ሳያብብ የአወቀ ይመስለው አለ። *** ሊቅ ሲጨነቅ ሲኖር ሃሳብ የለሽ በትራሱ ተጠቅልሎ ይተኛ አለ። *** ኩራት እና ትእቢት የሞሉት በጎራዴ እንደተመተረ መሬት መንከባለሉ አይቀርም። ገንዘብ ለሰው አገልጋይ ነበር፣ ግን በመስገብገብ ባሪያ መሆን በዛ። *** እውነትን ደብቀው የሀሰት ወገንዎች ሲታገሉ፤ እሷ ስትበረታ ሁሉም ወደቁ እየተሸነፉ። *** ማእረግ እሚሰኝ ደረጃ ላይ ሰው ሁሉ ሲወጣ እና ሲወርድ፣ ዳር ሆኖ ለተመለከተው ምንኛ ደስ ይላል። ***

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s