Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የጡረታ ዘመንን አስነጠቦ ኢትዮጵያአዊ አኗኗር እና ስልጣኔን ስለመርዳት

About how Ethiopia is not awake in considering pensioners and elderlies in a productive and constructive methods; elderliness should have been taken as a part of great life portion of one’s lifespan where many roles and attempts must be made instead of mere pension-finishing and aging days.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 25th 2021.,

በ ገዳ ስርአት ሁሉንም የዕድሜ እርከን መሰረት የአደረገ ክፍፍል የአለፈ ነዋሪ፣ ጡረታ ሲወጣ፤ ሉባ ተብሎ በእድሜ ይፍታህ መደብ ይሰየም አለ፤ በውስጡ ለቀዘቀዘ ቢሆንም ለተረጋጋ እና ጠቃሚ አገልግሎት ይዘጋጅ አሉ። ያ፣ በእርጅና እስከ ፍፃሜ ድረስ ስራ ከማጣት አስገዳጅ ባይሆን እንኳ የ አማካሪነትን ሚና እየገጫወቱ እንዲኖሩ አስቻይ ጉዳይ ነው። ጡረታው ለብቻ ተገልሎ ከመኖር፣ ንቅአተ ህሊናን እንደያዙ ለመቆየት እሚያግዝ ነው። ሲደመር፤ ለጎልማሳ እና ወጣቱ ደረጃ፣ እረጂ እሚሆን ምክርአሰጣጡም አለ።
ሰብእአስተኔ (mankind)፣ በማህበረሰብእ ሲኖር፣ የእድሜ ጉዳዩ አንድ ገሀዱ ነው። ከልጅነት እስከ እርጅና፤ በተለያዩ በተጠባቂአመልዎች (conventions)፣ ደንብዎች፣ ሚናዎች፣ ወዘተ. እሚመሰረት ህላዌ ነው። ዳሩ፤ የእድሜ ጉዳይ በሰው ልጅ ኑሮ ሲመዘን፤ ብስል እና ጥሬ አያያዝዎችን እንመለከት አለን። በደግ ማህበረሰብእ፣ እርጅና ዋጋ አለው። ጡረታ መውጣት፣ የእራሱ አዲስ ክፍለ ህይወትን መክፈቻ በር ነው። ጡረታ በተለየ እቅድ፣ በአልሚ አያያዝ፣ በተለይ በመዝናናትዎች፣ በተለያዩ በጎፈቃድዎች፣ የመጨረሻ ፍላጎት ስራዎች፣ ወዘተ. እሚጠምድ ነው።
በጡረታ ዘመን በቁጠባ መሰረት ዓለምን እየዞሩ መጎብኘት፣ ተሞክሮን በመሰደር ለትውልድ በማስቀመጥ፣ ከስራዘመን ውጭ በተለየ መንገድ ሀገር ለማገልገል በመቁረጥ፣ ወዘተ. እሚያያዙት ነው። ያ፤ እንደ ደንብ ነው። በእርጅና መብሰል እና የህይወት ውጊያን መከወን አለ።
የኢትዮጵያው ማህበረሰብእ፤ እርጅና እና ጡረታን ግን የአልተጠቀመበት ነው። እርጅና እና ጡረታ ማፍጀት-ቤትም መክተት በእሚል መርኅ እሚተረጎም ነው። ሲደመርበት፤ ወግ ማእረግ መመልከት እና ዓይን በአይን መመልከት ትልቁ መደበኛ አተያዩ፣ ፍላጎቱ እና ህልሙ ነው። በተለይ እርጅና እንደእሚፈለገው ብቻውን ከመጣ አምላክን አመስግኖ ተቀምጦ መኖርን እሚመኙበት ገላጭ ክፍለ እውነትአችን ነው።
አንደኛው መነሻ መፍትሔ ጡረታ እሚለውን ቃል ከአውዱ ማስወገድ ነው። እርጅና እየተጦሩ እሚኖሩበት እና ከመመጽወት በቀረ ምንም እሚከውኑበት እንዳልሆነ አስመልካች ነው። እርጅና ግን የእድሜዘመን መቋጫ ተብሎ ከተወሰደ ብዙ ፍልሚያ እሚከወንበት እንጂ እሚከስሙበት አይደለም። ስለ ሀገር፣ ስለ መጪ ትውልድ፣ ስለቤተሰብእ፣ ስለ አዲስ ክፍለ ህይወት ወዘተ. እሚንበለበሉበት ነው። ጤናን ለመጠበቅ እና በርትቶ ለመኖር እማይሰንፉበት፣ እጅ ሳይሰጡ ከግኘታ ህግ እሚሟገቱበት ነው።
የሀገር ማህበረሰብእአዊ ምርታማነት (social productivity) መጠቁምን እሚያፋፋ አላባአዊ ነው። የእርጅና ዘመንን አትብቶ መገልገል መቻል ሀገርን እንዲበለጽግ ከልምድ እና ተሞክሮ እንዲገለገል፣ ትውልድአዊ ትስስር እና ውርስ እንዳይነፍስበት እና በጥብቅ ቁርኝት እንዲከወን፣ በእንዲያውደፈናው ደግሞ ማህበረሰብእን በተጋ መስተጋብር እና ስነምግባር ወይም ወጥ ሀገርአዊ ቀለም ለማቆየት፣ ወዘተ. እሚያገለግል ነው። የሀገር እድሜጣራን እሚያዘምነው ነው። እርጅና እና ጡረታ የትግል ዘመን መደረጉ፣ ቁምነገር እሚታፈስበት እና ገና እሚጠበቅበት መደረጉ፣ ማህበረሰቡን እሚያግዘው በብዙ መንገድዎች ነው። ጤና መጠበቅ፣ መበርታት እና እራስን ዋጋ መስጠት በአረጀን-ባይ ዜጋዎች ስለእሚሠርጽ፣ ጠንክረው መኖርአቸው ህልም እና እቅድን ከህይወት አለመገፍተርአቸው፣ እረጅም እድሜ ይሰጥአቸው አለ፤ ሌቋሆ. (ሌላ ነገርዎች ቋሚ ሆነው።) ያ፤ ሀገርን ዘርፈብዙ ጥቅም አስታቅፎ እሚሸኛት አካሄድ ነው።
የቀረው ክፍለ ማህበረሰብእ፤ ከልጅ እስከ ጎልማሳ፣ ጡረታን በአዲስ ስነልቦና መመልከት መጀመር አለበት። ማርጀት ቤት ከመከተት ይልቅ እሚብረቀረቁበት ዘመን መደረግ አለበት። ብዙ ነገርዎችን ከአረጁ መጠበቅ ተገቢ ሀገርአዊ የመብሰል ማመካኛ ነው። የሰባ አመት ግለሰብእ፣ በእርግጠኝነት፣ የአለፈበት የልጅነት ዘመኑን ለማሳወቅ ብእር፣ መቀቢያ፣ መቅረጫ፣ ወዘተ. ማንሳት አለበት። እሚገመተው፣ አንድ የበሰለ ሀገር በአንድ የአረጀ ሰው እንደ አለ መሆን አለበት ነው። የአረጀን ከመናቅ ወደ ማርቀቅ መመለስ ግድ ይል አለ። ስነህዝብ እንዲበለጽግ፣ ፣ጡረታ የወጣ ከሀገር ስነምጣኔ ገንዘብ ወይም ሀብት መጨረስ እንዳይሆንበት አማራጩ ነው።
አብሮ ስለትውልድ ተፅዕኖ ስናሰፋ፣ ዘጠነኛ መጽሐፉ ተልባ እና ጥጥ ላይ የፃፈውን ደራሲ ታገል ሰይፉ ሲያብራራ፤ በ ቅዳሜን ከሰዓት፣ ኢቢኤስ ትመ. መርሐግብር ላይ፣ ሚያዚያ 16 ቀን 2013 ዓም. እንደተናገረው፣ ኢትዮጵያን ዛሬ ወደአቃወሳት ከአምስት የማህበረሰብእ ውድቀት ምንጭ ምሰሶዎችአችን መሀከል አንዱ የአዋቂዎች የስነምግባር መሪነት መጥፋት ነው። ሌላው የቤተሰብ ልጅዎችን አንፆ የአለማሳደግ ነው። ምንአልባት ቀጣዩ፣ የትምህርትቤትዎች ስነምግባር አራሚነት መጥፋቱ ነው። በእነእዚህ ዙሪያ፤ አዛውንትዎች በነቃ እና ከጡረታ በዘለለ ቀጥተኛ ተሳትፎአቸው ሀገርን ማስተካከል እሚችሉ ናቸው ማለት ነው። ቢያንስ እርጅናአቸውን ለማንበልበል፣ ወደ ወጣትዎች እና ህፃናት ተማሪዎች፣ ክበብዎች፣ መርሐግብርዎች፣ ወዘተ. በመቅረብ በመጎብኘት፣ በበጎፍቃድ አገልግሎት፣ ወዘተ. ልጅዎችን ማገልገል መቻል አለብአቸው። ስነምግባር፣ ብልሃት፣ ትምህርት፣ የእድሜ-ልዩነት-የለሽ አብሮታ ወዘተ. ማስተማር አለብአቸው። የአዛውንትዎች፣ ጡረተኛዎች፣ እድርዎች፣ ወዘተ. አሰራርዎች እንዲህ የአሉትን ማመቻቸት አለብአቸው። በደንብ እና ህግዎች እነእዚህ ደግሞ መስመር መከተት አለብአቸው። በተያያዘ፤ ማህበረሰብእአዊ አብሮታአቸውን እንደ ተጧሪ ክፍለ ማህበረሰብእ ሳይሆን እንደ በላጭ ትርጉምአማ ክፍል በማጠንከር በመምከር፣ በመጻፍ፣ በመገናኛብዙሃንዎች በመውጣት፣ ወዘተ. የእድሜዘመን ትሩፋትዎችን ማስመልከት አለብአቸው። የኢትዮጵያ አዛውንትዎች በሁሉም ዜጋ እሚደመጥ፣ የእሚገኝ፣ የእሚረባ፣ የእሚፈራ፣ የእሚያከብሩት፣ የእሚያስጨንቅ፣ ኑባሬን ማቋቋም ይገባአቸው አለ። ዕርጅና ከተገለለ ህበረሰብአዊ እና ዕድሜዘመንአዊ (ግለታሪክአዊ) መጋረጃ መግቢያ ሳይሆን፤ ማህበረሰብእን እንደ ሽማግሌ መምራት እሚገባበት ስፍራ ነው። እንደ ታገል ተገቢ እይታከ ሀገር እምትተረማመሰው አዛውንትዎች፣ በተጧሪነት ስም ከጥርስ መድከም እኩል የኑባሬ መድከምን ስለእሚያመቻቹ ነው። ያ፣ ሀገርን እንደ ከዱ አስመልካች ነው። ሀገርን ማቅናት እድሜ እእሚገድበው አይደለም። በተለዋዋጭ ሚና ከማብቃት ውጭ እሚጓዝ ነው። ሀገርን ለማቆም የአዛውንትዎች መንበልበል አስፈላጊነቱን ከ ገዳ ስርአትም ቀስሞ ወደ መሀከልሀገር እንኳ ማጓጓዝ እጅግ የስልጣኔ ጥያቄ አንዲት ቁንጽል – ግን ግዙፍ እና ግዑዝ ውጤት ያዢ – ነው።
የአረጁት፣ እንደ በርኒ ሳንደርስ፣ ጆይ ባይደን፣ ወዘተ. ከሰባ አመት በኋላ (በህግ በጡረታ ከእሚገለሉበት መደበኛ እድሜ በኋላም) ሀገር ለማስተዳደር እሚመረጡበት ዘመን መሆን አለበት። ያንን መሰል የተባ ማህበረሰብእአዊ ትስስር፣ ሀገርን የአረቅቅ አለ። ማእከለትውልድአዊ (intergenerational) መጣበቅን፤ ወልዶ ሀገርን የጠበቀ እና ብርቱ የአደርግ አለ። በእዛ የተነሳ የሀገርአዊ ትርጉም-ሰጭ ኑባሬ መነደል አይንጠውም።
አንዳንድ ወቅት ደግሞ፤ በእርጅና መንደድ ለሀገር የመሠልጠን አላባአዊ ከመሆኑ ይልቅ፣ ለግለሰቡ ተመሣሳይ ስጦታ እንደአለው በሌላ መንገድም እሚነገር ነው። ይህም፤ ለምሳሌ፣ በመጨረሻ እድሜህ በርታ እና ታገል እንጂ ነገረስራህን አታድክም አትናቅ፤ በቀረ ግን ዘመንህን ዋጋቢስ ታደርግ አለህ እሚል ፍልስፍና አለ። “Do not go Gentle into that goodnight” እሚለው የአየርላንድ ገጣሚ፣ DYLAN THOMAS, ልብነኪ ግጥም፤ በእድሜጣሪያ፣ እጅሰጪ ስንሆን፣ መልሱ ከሞት በኋላም እየጎዳን እሚገኝ ሊሆን እንደእሚችል ይነግረን አለ። (CHRISTOPHER NOLAN, Interstellar 2014 ፊልምን መመልከቱ ደግሞ የበለጠ ያንን አጉዪ ነው)።
ቢያንስ፤ እምንተወው ቤተሰብእ እና ህዝብን እንዲታገል፣ እንዲጣጣር፣ እንዲበረታ፣ የእኛ የመጨረሻ ዘመን ትግል ምስጢር አስመልካች እና የአረጀው ሲበረታ በገሀድ ስለምንመለከት ከስር ለአሉት ዜጋዎች እሚያሸማቅቅ-ተፅዕኖም አመንጪ ስለእዚህ አንፋሽአማ (inspirational) ነው። ስለእዚህ ሀገርን፣ እራስንም ማዳን በእርጅና አለ። ከሆነ፤ እነሆ እርጅና አዲስ ዘመነ-ህይወት ወይም ክንፈ ኑሮ መክፈቻ እንጂ አጥፊ አካሄድ እሚከወንበት እና በቸልታ አካልአዊ ዝግመትን እሚቀላቀሉበት ብቻ መሆኑ ይቅር። ከስነልቦና እና አመለካከት መጣፈጥ አንፃር እንጂ ከመገርጀፍ ብቻ መታየቱ ጉዳቱ በእየዘርፉ ነው። ሀገር ከእዚህ አገነዛዘብ ብዙ ይትረፋት፤ ውጤቱ ብርሃን እንጂ ሌላ አይደለም እና።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፤

አለፈው ጥረታችንን ሳስታውሰው ትዝ ሲለኝ 
ከሰራነው ነገር ይልቅ ያልሰራነው ነው የሚቆጨኝ! ሁላችንም ሽማግሌዎች በእድሜአችን መዝጊያ መዕራፍ ትልቅ ጋቢ እንፈትላለን። ግን ሳንቋጨው እንሞታለን። አዎን እኔንም እንዳባዎቼ የአልቋጨሁት ነገር ይቆጨኝ አለ፨

ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፤ ጦቢያ መጽሔት ጋር ቃለመጠይቅ፣ 1997 ዓም.

እንደ አሉት፣ (ተሳካ-አልተሳካ ሳይሉ) እስከ መጨረሻው ህቅታ በመጋደል መኖር፣ እርግጥ ምትክ የሌለው እና የስልጡን ማህበረሰብእ አስገዳጅ አላባአዊ ነው። እንደ አሉት፤ የአባትነት ምስክሩ እድሜ ሳይሆን እስከ ፍፃሜ መታገሉ ነው። እንደ አሳበቁትም፤ ማብቂያ ዘመን ድረስ እሚቀመጥ ኢላማ አይጠፋንም እና ለማሳካት መሞከሩ ግዴታ የሰብእአዊነት ክፍል ነው።

በደፈናው ጽንሰሃሳቡ፤ አንድ እርጅናን በጡረታ ከማድቀቅ፣ በዝማኔ በማንበልበል፣ ሀገርን ማዳን፣ ለእራስም የተሻለ መከወን ለኢትዮጵያ አንዱ መነሻ መንገዷ ነው። መንግስት እና ልማድዎች፣ ያንን በማንፀባረቅ ከአላስመለከቱን፤ ያንን ኢላማ ባህል ማድረጉ ከበድ ያለ ይሆን አለ። ቢንያም በለጠ ዘ ሜቄዶኒያ፣ የሰበሰበአቸው የኢትዮጵያ አዛውንትዎች መሀከል ብንገባ፣ ነገርን ሰድረን ማውረስ እንደ ቀደሙ አባትዎችአችን የአልቻልን የዛሬዎቹ እኛ ስንት-ስንት በአገኘን፣ በአተረፍን። የአዛውንትዎች መጠለያ ቤት የሆነው ሜቄዶኒያም፣ ወይም ሌላዎችም፣ ይህንን ሁኔታ መመልከት ከቻሉ መልካሙ ይሆን አለ። ለአዛውንትዎችአችን፣ ትርክት እና ግለትርክት ፀሐፊዎችን መመደብ፣ እንዲተውልን ስለፈለጉት ነገር ሁሉ እሚያስተርፉልንን የዘመን ቅርስ-ስጦታ መተዉያ መንገድዎችን ማመቻቸት ቢቻል ለበጎአድራጎት ድርጅትዎቹ ሁለት ወፍ በአንድ ድንጋይ ይሆን አለ። ጥቂት ክፍለ መጽሐፍዎች-ቤት፣ እና አንድ ሁለት አጋዥ ግለሰብእ ኖሮ ይህንን ትድድር (management) መከወኑ፣ ትልቅ ጉዳይ ነው። የተረገመ ምድርነትአችንን ለመፋቅ ጥቂት ስንዝርዎች ሄደው የእድሜ ታላላቅዎችን የሰበሰቡ ተቋምዎች፣ ሀገር እንደ አዳኑ እና አበረቱ፣ ውርስም አያያዞ ማስተረፍ ቢችሉ፣ መጽሐፍዎችአቸውን፣ ትርክትዎችአቸውን፣ ወዘተ. ቢከውኑልአቸው፣ ሌላ ስጦታ ለጠቢ-ትውልድ ማስተረፍ እና የውለታውን አረቦ ማግዘፍ ነው፤ ሀገር በቀጥታ-ተግባር ከማዳን ወደ ቀጥታ-መገንባትም ገብቶ ነገን መካፈል ነው። በመንግስት እና ሀገር ባህል ጡረታ የተሰኘ ክፍለ-ገሀድን ማስነጠብ፤ የስልጣኔአችን ክፍተት የአኗኗርአችን አለመዘመን አንድ ትልቅ ጎዳናው ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s