Categories
የንባብ ፉክክር [rEADEING cHALLENGE]

ጭምቅ በ ዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ ላይ (ክ. ፪)

Part 2 of rEADING cHALLENGE on Dagnachew Werku’s Adefris, (reader’s opinions on the novel).

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 13th 2021 GC.,

የግል አተያየትኤዎች [Personal Comments]

[ክፍል አንዱን እዚህ የአግኙ፨

[ወይም በደፈናው፤ በ ተአዶ. (PDF) የአውርዱ)]

አደፍርስ በደፈናው
፩) ከእነችግርዎች ምቹ የአዋቂዎች ልብወለድ፤

አደፍርስ በሂደቱ፤ ለአብዛኛው ክፍል፣ በጨጭ ባለ ወረቀት እና ጥቁር ቀለም የተፃፈ ሳይሆን፣ በዶሮ ላባ እና ሀር ጨርቅ እንደተበጀ ትልቅ ትራስ እሚደላ፣ የአዋቂዎች ልብወለድ ትርክት። አንጠልጣይ ሴራ ከቶ ሳይቀምርም፤ አንብበው ሲያቋርጡት ለንባብ ወዲያው ወዲያው እየጎተተ እሚመልስ፤ ትንግርተኛ ጣፋጭ ጽሑፍ ሆኖ እሚዘልቅ ነው።
) በመጨረሻ ፈሪ ትራጀዲ፤
አፈፃጸሙ፣ ግራ የተጋባ ነበር። አሯሯጡ አንድ ማስመልከቻው ነው። ቀጥሎ ግን፤ የበረታ፣ ወደፊት የተራመደ፣ ወይም ተስፈኛ አፈፃጸምን አልፈለገም። የፍፃሜ አተያዩ ፍትህ እና አመክንዮ የሌለው፤ እንደ ሴራ ሳይሆን እንደ አጋጣሚ ተከውኖ ልብወለዱን ለመቋጨት የአክል እሚቀርብ ነው። እጅግ ድራማ ፈላጊ ፍፃሜው፣ የሰነፈ እይታውን ከተስፋቢስ ፍላጎቱ ጋር የአከለበት እና የአራወጠው ነው።
፪) የአዋቂዎች (የአባትአዊ / parentis) ይዘት፤
በመጨረሻ፤ ከእሚጠለው ሀሳብዎቹ አንዱ፤ ሀገር ትለወጥ ግን የነበረንን ወግ፣ ቅርስ፣ ልማድ ወዘተ. ረጋ ብለን እንጂ የአለንን በሙሉ በመተው አንቀየር እሚለው ሃሳቡ ይህ ነው። ይህ መሀልሰፋሪነት፣ አንዳንዱ ስፍራ ላይ ተገቢ አንዳንዱ መስክ ላይ ቢጠይቁት ቀለል የአለ አቋም ቢሆንም፤ በደፈናው እርጋታ እና ክብርን ከስልጣኔ በማብለጥ በእርጋታ እንለወጥ ማለቱ አንድ ረጋ የአለ ሊያስብለው እሚችል ነው። የታየው ከመዳፈር እና አደጋን ከመፍጠር ረጋ ብሎ ማዝገሙን በመሆኑ፣ በብዛት እንደ ጎልማሳ ምክር እምንቀበለው ነው።
በደፈናው፤ የመለወጥ ተቆጥቋጭ ጭንቀቱ ከልብወለዱ ትርክት እየሳተ በእየምእራፉ በዝርው ሊቅአዊ (academic) ውይይት ቢጠመደውም፣ በተለይ ለዘመኑ ተደራሲ እንደ መነሻ ጉዳይዎች አወያይነቱ ከደግ ደረጃው ለመውረድ እማይቻለው፣ ነው።
ስለእዚህ በደፈናው ከሌጣ ልብወለድ በላይ፤ የአዋቂዎች ውይይት፤ ነው። የሰብእአዊ አኗኗር መሰረት ሀሳብዎችን ጭብጥዎቹ ያሽከረክሩ፣ ማእዶተ ማህበረ-ሰብእን በእርጋታ (አጥባቂ?) መንገድ እንድንከውን ያሳብቁ፤ እና ረጋ ብሎ መብሰልን ስለእሚሰብኩ፤ በሥነጽሁፍ አለባበስ የተገተረልን ዳግ-ጥናት (research) የአደርገው አለ።
፫) አፍጊት፤
እንደ መልካም አፍጊትነቱ ደግሞ፣ ፈገግታዎችን እሚያቀርብልን የተዋዛ አስተናጋጅአችን ነው። ምንም እንኳ አንዳንዴ ብቻ ቢሆንም፤ ምንም እንኳ ከአማካይ በላይ ብዙም ባይዘልግ፤ አንዳንዴ አፍጊት የሆነ ጠብታዎች አሉት። ሲገጥሙ ግን ደግነት አሉአቸው።
፬) የተሳካለት በመካከለኛ ደረጃ ቢሆንም ሁሉን አቃፊነት አሁንም እንደ አባትነት አለበት፤
የበዛ ወገንተኛነት በክርክሩ የለም። የአሉትን የተማሪ ወጣትዎች እና ወግአጥባቂ ጎራዎች ማስታረቅ ፍላጎቱ እንጂ መጣላት አይፈልግም። ኋላቀሩን ከመጥላት፣ ችግርዎቹን አይቶለት መገንዘብ፣ እንዲሁም አጥፊዎችን መመለስ፣ በእርጋታ ደግሞ እሚያምነውን ማቀበል፤ መሞከሩ ይህ ሁሉ የአዋቂ ዘዴነቱን ይጠቁመን አለ – እንደ አቀራረብ፤ በደግ የሀገር አባት (ሽማግሌ) የተፃፈ ነው። በመጨረሻ ቢያንስ እርጋታን አክብሮ ይዞ አለ። መታገስን እና አብሮ መሆንን ያስተናግደው አለ። ልክ ምእራፍ አንድ እንደተነሳው፣ የጭሰኛን እርግማን የመሰለ ህይወት እንደእርግማንነቱ ቀርፆ ያሳይ አለ። በሂደቱ፣ በእዛውም ምእራፍ ደግሞ፣ የበላይን አክብሮ እና እየተሳሰቡ መኖርን እስከ ንጉስህን ማፍቀር (ምእራፍ ፲፫ ጭምር) ይነግረን አለ። በዝባዣ-ተበዝባዥ ብሎ ከመንገር እና ነውጡን ከማሳየት፣ እሚነግረን፣ መሻሻል ያለበትን የእየወገኑን ጉዳይ ነው። ጠላትነት እንዳይፈጠር እና ለውጥ ብቻ እንዲታለም የአቀደ ነው። ንጉሡ የአመጡትን ለውጥ እንድናከብር እና እንድንጓዝ እንጂ እንዳንቃወም እረጋ እንድንል ይመክረን አለ። ጭብጥዎቹን ትተን፣ እንዲህ የቀረበበትን፣ መንገድ ስንመለከት፣ ሚዛንአዊ እና አርቆ አሳቢ እንደሆነ እንገነዘብ አለን። አባትአዊ የሽማግሌ አተራረክ ስልቱ የእሚረጋገጠው፣ ወጣት ተማሪዎቹ በዘመኑ የተፃፈ ይህን ልብወለድ ትተው ትግሉን በማብዛት የአመጡት ለውጥ ብዙም አልተሳካም። ረጋ ማለቱ እና ከንጉሱ መተባበሩ ለውጡን እንዳስቀጠለ ይገኝ ነበር እሚለው የእሱ እሳቤ መሆን አለበት። ያም፣ በተተካበት እሳቤ መክሸፍ ምክንያት ደግ እሚሰኝ እይታ ይሆንለት አለ።
በመጨረሻ ግን፤ ይህን ማስመልከት አልፈለገም። ለውጥ አምጪነትን እሚተጋበት አደፍርስ ተጠንቅቆ ለመማር እና ለማገልገል ሲዘገጃጅ በትርክቱ እንዲሞት ማድረጉ፤ የእዛ ሃሳቡን ይጣረስበት አለ። አመጣጡን በፍፃሜው አንመለከትም እና የአመጣጡ እርጋታ አፈጻፀሙ ላይ ይበንብን አለ። ለውጥን እማይፈልግ ሆኖ የጨለማ አኗኗርን በሰበከበት የአፈፃጸሙ ወቅት ድረስ ግን፤ እሚያደርሰን የመሀከል ላይ ጉዞ ነው።

ትርክት አቀራረብ
በደፈናው አደፍርስ የበለጸገው በቋንቋ አቅሙ እና በእርጋታ ሆኖ በእሚሰብከው የለውጥ ሂደቱ ሲሆን፤ ሁለተኛውን በመጨረሻ አፈጻፀሙ የካደው ስኬቱ ነው። ይህን እስክንደመድም እሚገጥመን የአጻፃፍ ገሀድ ምንድር ነው?
እንደቀነጨብንው በትርክት አፈሳሠሱ እጅግ ዘግየት እያለ እሚመጣ ነው። በሊቅአዊ ውይይትዎቹ እሚያዝ ስለሆነ፣ ሴራውን ለመሰብሰብ ከባድ ነው። ለምሳሌ፣ መቶ ገጽ ድረስ ተነብቦ እሚጠልለው ሴራ ምነም ነው ማለት ይቻል አለ። በላይ ፍሬዋን እንደወደደ፣ ጥሶ እና ቤተሰቡ አርማኒያ እንደመጡ፣ በተረፈ ኑሮ እዛ አስቸጋሪ መሆኑ ከመገለጹ በቀረ፣ ያን ሁሉ አንብበን ሴራውን ለመጎንጎን ግን አይቻለንም። ትርክቱ ላይ አተኩረን ግን አዋቂ ውይይትዎቹን እየተጎነጨን፣ ሞቅ ሞቅ በእሚያደርጉ አተያይዎቹ ለሰፋ የአንጎል መለጠጥ እንገደድ አለን። ቢሆንም፤ የትርክቱ አተራረክ ውበት፣ ከሴራው አለመፍጠን አንፃር እሚያነካካው ነገር ከአለ፣ ይህ በእርግጥ የትዝብት መስመር ነው።
ወደ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ፤ በተለይ የሠርግ ጉዳይ ሲጀመር አካባቢ እሚጀምር ከበድ የአለ የትርክት ሩጫ፣ እና መዝረክረክ አለ። የእማይገመቱ አካሄድዎች፣ የበዙ ጨለምተኛነትዎች፣ የተሯሯጡ እጥፋትዎች አሉ። በመጨረሻ አንድ ሴራ ለመጎተት ይከብደን አለ።

ገበሬው እና ሚስቱ ን በአጭሩ እንዲሁም የ አደፍርስ ከፍተኛው ክፍተት
አደፍርስ ሲጀምር፤ ጭሰኛው ድሃ ገበሬ ጎርፉ እሚዘራው ዘርን ለመለመን ወደ አሰጋሽ ባለጠጋዋ ሲሄድ፤ የ ተፈሪ ደረሱ፤ 1949 ዓም. አጭር የግጥም ትርክት፤ ገበሬው እና ሚስቱን ያስታውስ አለ። ልክ ያ ምእራፍ እንደ አበቃ ግን፤ ወደ እዛ ትርክት ክንፍ ዳኛቸው አልተመለሰም። ገበሬው እና ሚስቱ ላይ እዛ ተበድሮ፣ ሰርቶ፣ አግኝቶ በሚስቱ እርዳታ ጥቂት አጊንቶ ኑሮን አሻሽሎ እሚኖር ሆኖ እሚያልቅ፤ ሰርተህ-ተለወጥን-ሰባኪ ትርክት ነው። ጎርፉ ግነ ሳይሳካለት እሚቀር በመሆኑ፣ ፍፃሜው ባይገናኝም፤ ለአነበበአቸው የመመሳስልአቸው ነገር ግን አስገዳጅ ስሜት ነው። በእርግጥ ልብወለዱ፣ ጎርፉ ከተበደረ በኋላ የተበደረውን ሲያገኝ እንጂ ይዝራው፣ አይዝራው፣ ይሳካለት አይሳካለት፣ ይመልስ ብድሩን አይመልስ አይነግረንም። የተጀመረ ትርክትን አይፈጽምም። ይህም፣ ከትርክት ወይም ሴራ አቀማመሩ የእሚገኝ ስህተቱ ነው። የተዋጣለት ትርክት እና ሴራ የለውም። በመጨረሻም እየተራወጠ ይጨርስ አለ እንጂ የውይይትዎቹ ጉዳይዎች እንጂ የሴራ ጉዳይ እሚሳካ አይደለም። ያን ስህተት ግን ትልቅ ሆኖ አንመለከተውም፤ ቢያንስ የባሰ ሲገጥመን።
ምክንያቱም ከጅምሩ የእሚወስደን ውይይቱም ለነገሩ፤ በመጨረሻ በአልተሳካ ፍፃሜ ሊቋጨው በመፈለጉ ግራ የተጋባ ዜሮአዊት (nihilist) ሰባኪ ነው። እውቀትም ድንቁርናም ሞትን ካላስቀሩ የምን በእውቀት መጨነቅ ነው እሚል የፍፃሜ ወሬው እጅግ እማይቀበሉት አፈፃጸም ነው። ከአለማወቅ ማወቅ መሻሉን፤ መለየት የአቃተው አገነዛዘብ ምኑም እሚያነቃቃ አይሆንም። እጅግ መሰረትአዊ ክሽፈትን የአለው ሆኖ እናገኘው አለን። በየቱም መንገድ፤ ህይወት እሚቀየረው እንኳን በማወቅ ከማወቅ ቀጥሎ በትውልድዎች መሀከል በእሚከመር መስዋእትነት ሆኖ ሳለ፣ ይህን መሰል ስህተት አደፍርስ ማስመልከቱ እጅግ ተወቃሽ ነው።

የበእውቀቱ ስዩም፣ “የፍቅር ቀዶጥገና” አሀድ-ግጥም በምእራፍ ፲፫
አንድነት ሰውን ከአውሬነት ጸባዩ እሚያስለቅቀው እንደሆነ ይነግረን አለ። አንድ ከአልተኮነ፣ አውሬነት በዝቶ አምላክን መሸጥ ድረስ ሲያደርስ፣ አንድ መሆን ግን ሰውነትን ይመሰርትልን አለ። በእውቀቱም፤ ፍቅር የሰው ልብን አስተምሮት፤ ለአፍቃሪው ቀዶጥገና አድርጎ ከአውሬ አካልዎቹ ቅጥያው እንደእሚያላቅቀው ይነግረን አለ። አንድነት ያለፍቅር ደግሞ ውሸት ነው አይሳካም ብሎ እንዲሁ፤ ሰባኪው አባ ዮሐንስ ይነግረን አለ። በመፋቀር፣ አንድነት ሲገኝ፣ በሁለቱም፣ አውሬአማ ክፍለ ማንነትአችንን ማስወገድ እንደእሚቻል ይነግሩን አለ።

የአደፍርስ ስርአተነጥብ ጉዳይትምህርት ከአለን
አደፍርስ በእየአካባቢው፣ የስርአተነጥብ አጠቃቀሙ፣ የበዛ ነው። በተለያዩ መንገድዎች፣ የአጭር ሰረዝ እና ረዥም ሰረዝዎችን እሚጠቀሙ አንቀጽዎቹ አሉ። እንዲሁም ሌላዎች አሉ። እነእዚህ ሁሉ፣ ለምን እና እንዴት እንደአገለገሉ በማጥናት፣ የተለያዩ አገልግሎትዎችን ማግኘት እሚቻል ነው።
በቀጥታ እምንመለከተው የአደገ ስልተ አጠቃቀም ላይሆን እሚችል ነው። ዳሩ፣ የተሻለ ፈርቀዳጅ አቀጣጠር እሱ ከተገለገለ፣ በእዛ መሠረት አገልግሎትዎችን ወደደንብነት ተጠቅሞ የቋንቋውን ቀላል ደረጃ ስርአተነጥብ አቀጣጠር፣ ወደ ተወሳሠበ ስለእዚህም የተሻለ የተግባቦት አቅም የአለው አካባቢ መውሰድ እሚቻል ነው። በዋነኛነት የተለያዩ የሰረዝ አይነትዎቹ፤ ወደ መጨረሻም የተጠበብአቸው ነቁጥዎች አሉ። ሰረዝዎቹ፤ በእየአይነትአቸው፣ ምንአልባት አረፍተነገርዎችን ወደ አንቀጽነት ስንለውጥ ከአንድ አንቀጽ በአነሰ መከፋፈል መክፈል እምንችል እንደሆነ እሚጠቁም ይመስለኝ አለ። ቢያንስ አንዳንዴ። አንቀጽ አንድ ወጥ ሃሳብ ቢይዝም፤ ሰረዝዎቹ የበለጠ ወደ አነሰ ክፍል ሊቀንሱት ይችል አለ። አንዳንዴ ደግሞ የአንቀጹን ፍሰት ለመቆራረጥ እና ለተሻለ ተግባቦት የተጠቀመብአቸው ይመስል አለ። ዞሮዞሮ፤ ለመመርመር እሚፈልግ፤ ከሃሳብዎቹ ከቋንቋው ወዘተ. ውጭ አንድ ነቁጥ ነው።

የኋሊት ስልጣኔአችን ሲገለጥ፡ ዛሬ እማይሰራው የአደፍርስ ልብወለድ ምእራፍ ፲፪
ምእራፍ ፲፩ የአደፍርስ ልብወለድን ለያዝንው ዘመን እማይሆን ያደርገው አለ። ቢያንስ በደፈናው ዘጠና እጁ፣ ዛሬ እማይሰራ ነው።
ምን አለው? አጭሩ ምእራፍ፣ ዋና ዳኛ ጥሶ ለልጅአቸው ፍሬዋ ስለኢትዮጵያ እንደለመዱት እሚያስተምሩትን ቁምነገርዎች እሚነግር ነው። ስለኢትዮጵያ ትልቅነት ቅርስ፣ ወግ፣ እና ልማድ፣ በጠቅላላው ባህል ይሰኝ አሉ፤ ብለው ሁሉን እየከፋፈሉ ያስተምሯት አለ። በአጭሩ እሚሏት፣ ልማድ ክፉ እና ደግ አለው። ክፉ ልማድ፣ አለእድሜ ጋብቻ፣ ጥንቁልና፣ በጋለ ብረት መተኮስ አይነት ህክምና፣ ወዘተ.። በጎ ልማድ፣ የሰው ንብረት ማክበር፣ ስልጣን እና የበላይነትን መታዘዝ እና ማክበር – ለምሳሌ በአባት፣ በሀይማኖት፣ እና መንግስት ላይ ክብር አለን። ቤተክህነት እና ሹማምንት ስለሰላም የማክበር ልማድም አለን። ለእነ ዐፄ ዮሐንስ፣ ቴዎድሮስ እና ምንይሊክ ዘመን ትግል ምስጋና ይሁን እና፣ መንግስት እና እምነት በግብጽ የእምነት መሪዎች መከፈሉ ቀርቶ በሙሉ በኢትዮጵያአዊያን ተይዞ እሚያገለግለን፣ ልክ ንጉስ ሰሎሞን እንደነበረው በመንፈስአዊ እና አለምአዊ ብቃት ባለው መሪ እምናምን ሆነን ሞዓ አምበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ እምንል፣ ተሰባስበን በመወያየትም በጎ ልማድ ያለን (በእድር፣ እቁብ፣ ሸንጎ፣)፣ በማህበር የመስራት ልማድ፣ በወንፈል፣ ጊሶ፣ ደቦ፣ መተባበር፣ መሰባሰብ እና መገባበዙ ደግሞ በሰርግ፣ ማህበር፣ በለቅሶ፣ እንዲሁም የሰው ስብእና ክብርአችን ደግሞ ትልቅነቱ፣ በመወለድ ጊዜ በክርስትና ማንሳት፣ ክርስትና ስም መስጠት፣ በጋብቻ በመቁረብ፣ በሞት ጊዜ በቁምነገር በመፈታት፣ ሰውነትአችንን እናከብር አለን። ወግ ደግሞ፣ ደንብ ሆኖ እሚነግረን ስለ ሰላምታ ስንሰጣጥ፣ አቀማመጥ፣ አበላል፣ አለባበስ፣ አረማመድ፣ ወዘተ. ላይ አለን። ስለ ቅርስ ደግሞ፣ ልዩልዩ የልብስ አሠራርዎችአችን፣ የፈረስ አጊያጊያጥአችን፣ (ጥብጣብ፣ ካባ፣ ላንቃጎፈር፣ ለምድ፣ እጀጠባብ)፣ የበቅሎ፣ ግብርና፣ ሙዚቃ፣ ቤትአሠራር፣ ምስል፣ ሀውልት፣ ወዘተ. ላይ ልዩልዩ ቅርስዎች አሉን።
ይህን ነግሯት፣ በእነእዚህ ከአለም የተሻልን ከሆንን ስተረጠይቀው በአዎንታ ይመልስላት አለ። አንዳንዴ ጭራሽ እንሻል አለን፤ ህንፃዎችአችንም ጊዜ ወስደው ይገንቡ እንጂ እንደ ግሪክ እና ሮምአዊያን እሚፈራርሱ አይደሉም። ብሎ አከለ። በመግለጥ ወደኋላ ከቀረን ብላ ስትጠይቀው፣ ለቅሶ፣ ሳቅ፣ ቡጢ ወይም ዱላ ናቸው ስሜት መግለጫ፤ አሉን ሁሉም፤ ብሎ መለሰ። ከምር ነው ስትለው፤ ፍቅር እና መሀላ በፈረንሳይኛ፣ ስድብ በጣሊያንኛ፣ ስልጣኔ በእንግሊዝኛ ካላወራን፣ አልሰለጠንንም አይባልም። ያያንን ሲላት፣ አዲስ መከላከያዋ፣ ስልጣን ወይም ሀብት ሀገርህም መንግስትም ሳይሰጡህ ለምን ትከላከልልአቸው አለህ? ስትል፤ ስልጣን በቃኝ በማለቴ ነው፤ ሀገር ደግሞ የትም ብሄድ ብረማመድ በነፃነቴ አፍንጫዬን ሰቅዬ በኩራት እየተነፍኩ እማርፍበት ስለሆነ እንደ እርስቴ ነው፤ የግል ሀብቴ የአክል ነው ሀገሩ ሁሉ፤ እያለ ያወያያት አለ።
እነእዚህን፤ በመመልከት፤ ዳኛአቸው፣ በጥሶ በኩል የአቀረበው በዛይቱ ኢትዮኦእያ እምብዛም እማይገኝ ነገር መሆኑን እምንመለከት እንድንሆን እውነታው ይጋብዘን አለ። በእዛ መሰረት፤ ዛሬ ባህልአችን ወጥነት፣ መሰረት እና ብስለት የጎደለው ሆኖ አለ። ለነገሩ፤ በደፈናው እንጂ ባህል አልተብራራልንም። ወደ ልማድ ስንሻገር፣ በጎ ልማድዎቹ ቀርተው አሉ ማለት እሚቀልል ነው። ወግዎችም እንዲሁ፣ እማይገኙ ናቸው። ቅርስዎችንም በተመለከተ፣ ጥቂት የባህል ልብስ ከመገልገል በቀረ እምብዛም እማይገኝ ነው። የሀገር መንግስትም፤ እሚመራው በብቁ ምሁራን ሳይሆን በካድሬዎች ሰንሰለት ነው። አባት፣ ሀይማኖት፣ መንግስት፣ ወዘተ. እሚከበሩ እና እሚታፈሩ መሆንአቸው እጅግ የደበዘዘ ነው። በመንቀሳቀስ መብትም፤ ሰዎች በሀገርአቸው እንደልብ ዛሬ አይዘዋወሩም፤ መፈናቀል እና በመዟዟር የተነሳ እንደ ሁለተኛ ዜጋነት መታየት ያለ ነው። የሀገር ስነምግባርአዊ አኗኗር መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን፣ በጋራ መስራቱም ለሀበሻ እማይሆን እንደሆነ እና በጋራ ከመብላት አብሮ ወደመስራት እንዲለወጡ ህዝብ በመሰበክ ላይ ነው። ዛሬ፤ የአደፍርስ ልብወለድ ምእራፍ ፲፪ ቁጭት ብቻ እንጂ የእኛን መቼት አያንፀባርቅም። ቢያንስ በመሀከልሀገር እና በአለፉት ሠላሳ አመትዎች።

ገጸባህሪዎች
ለእኔ ከገጸባህሪዎች አሣሳሉ፤ ከፍተኛውን ስኬት የአገኘው በአሰጋሽ አሰራሩ ነው። የ አሰጋሽ አሠራሩ እጅግ ድንቅ ነው። የነገርበምሳሌ አጠቃቀሟ ወጥነቷን ከጅማሮ እስከ ማብቂያ ማስቀጠሉ መቼም እማትዛነፍ አድርጎ እሚስላት ትልቅ የገጸባህሪ አሣሳሉን ከቋንቋ አቅሙ አስተሳስሮ እምንመለከትበት የስኬት ጫፉ ነው። ሌላዎቹም ወጥ ናቸው። ዳሩ፤ እጅግ የበረታ የቋንቋዋ ወጥነት፣ ከወግአጥባቂ ስብእናዋ አሰጋሽን የእምትስብ የአደርጋት አለ።
በቀረ፤ ሌላዎቹ ደህና ናቸው። በመጨረሻ ግን፣ ደርሶ እሚራወጥ ትርክት እና ግጭትአቸው ግራ የተጋባ ፍፃሜ በገጸባህሪዎች እንድንመለከት የአደርገን አለ።

ምንአልባትአዊ አስተውሎት በምእራፍ ፲፮
የበእውቀቱ ስዩም፤ ለንጹህ ህፃንዎች የጭራቅ ተረትን ፈቃጅ ግጥሙን በእዚህ ምእራፍ፣ አሰጋሽ ለወንድምአቸው ወልዱ እና ዋና ዳኛ ጥሶ ሲያወያዩ እንሰማ አለን። ያም፤ ስለ ህፃንዎች መገደል እና ለጥንቆላ ፍጆታ መሆንን እሚተርኩበት ነው። ዳኛቸው ወርቁ ለህፃንዎች የአስፈሪ ትርክቱን በእዛ መንገድ አቀነባብሮ ከትቶ አለ። አሸባሪ ወሬን ነግሮ፣ ስለ ጨካኝ መሞት መተረኩ፣ እንደ ጨለማ ዘመን የአልሰለጠነ መንገድ፣ አንዱ መፍትሄ ይመስል አለ። ዳሩ፤ በተሻለ ትርክት እያመራመሩ፣ የልጅዎችን ንፁህ ቀልብ በአልሚ መንገድ መኮትኮት እሚገባ ነው። አስፈሪ ተረት ወይም እንደ ወይዘሮ አሰጋሽ የአለ ትርክት ከመንገር በእዛም ሽብር ናፋቂ ስነልቦናን እና እሚያያዝ አናሽነትን በልጅዎች ከማስረጽ በእንቆቅልሽ እና ምርምርከ ትንግርት እና ተግባርአዊ ቤትስራዎች፣ ስነምግባርዎች፣ ወዘተ. የበለጸገ አስተዳደግን መከወን እሚገባ ነው። ይህን ቅንጭብ ትርክት፣ ደራሲው በአልሰለጠኑት የገጠር እመቤት እሚነገር የአደረገው ምንአልባት፣ መቅረት እሚገባው አጉል ልማድ እንደሆነ ለማስተማር ይሆን አለ። በምትኩ፤ በስነፈለክ ወይም ስነንጥረነገር፣ እሚብስልስል ህፃንን ለማሳደግ፣ አቅሙን እንደ በጎ አባት በማሸበር ትልም ከመልቀቅ፣ ወደ ብስል እና ወደፊት ቀኝአዊ እና አረቦት ክፍያ እሚያቀርብ መንገድ መውሰዱ እሚሻለው ነው። ይህ የተሻለ የመሆኑ ምስጢር ስለወደፊቱ በማሰብ ብቻ አይደለም። ስለ አሁንአዊ አስተዳደግ ጭምርም፣ ህፃንዎችን ወደ ንቁ፣ አፍቃሪ፣ እና ሙሉ ስነልቦና ይዞ እሚያድግ ሰው አድርጎ ለማሳደግም፣ አሁንኑም ቢሆን መከወን እና ማትረፍ እሚችል ነው። አስፈራርቶ፣ የልጁን አውሬአዊ ገጸባህሪን አርክቶ ከመደለል፣ ጥቂት የአደገ ማህበረሰብእ በመሆን፣ አቅሙን እንደተገለጠው በቀና መንገድ መውሰድ እጅግ የመዘመን መገለጫ እና ይዘት ነው። ይህ ቅንጭብ ትርክት፣ ዳኛአቸውን በእዚህ እሳቤ ከከተተው፣ ብቸኛ በደንብ እሚያስወቅስ ሊሆን እሚችል ነው።

ባህልአዊ መንቃት፡ የበላይ ማናዬ አዙሪት ዘአልፋ ልብወለድ ዋና ገፀባህሪ አብርሃም እና የ አደፍርሱ አደፍርስ
ልብወለድዎቹን ለአነበበ፤ እጅግ እሚመሳሰል ነገር አለብአቸው። በትርክት አወቃቀር ጭፍግግ ሆነው ሁለቱም ልብወለድዎች ነገርን የተመለከቱ ናቸው። ኢፍትህ እና ፍርሃት ለልብወለድዎችአቸው ትራጀዲ መምረጥን አስተምሮአቸው አለ። እንደ ዋና ገጸባህሪዎቹ አያያዝ ደግሞ፤ አብርሃም እና አደፍርስ ተመሳሳይነት አሉአቸው። ክብረት እና ቀልቤሳ (ኢትዮጵያአዊው ማርክስ)፤ የአደፍርስ እና የአብርሃም አጋርገጸባህሪዎች (side kicks) ሲሆኑ በሃሳብም እሚመሳሰሉ እና ዋና ገጸባህሪዎቹን እሚግዙ ናቸው።
አብርሃም እና አደፍርስ፤ ለእማይማርክአቸው ሰው ትኩረት አይሰጡም። ሁለቱም፤ አጠገብአቸው የአለው ሰው ስሜት ዴንታ አይሰጥአቸውም። እሚመስልአቸውን እውቀት ከመዘክዘክ በአሻገር፤ ስለሌላው ቢወደዱ እንኳ አይጨነቁም። ለዐብነት የአክል።
አደፍርስ ጺዮኔን ደጋግማ ስትመለከተው እንጀራም ፊቱ ስትቆርስ እና ስታቀርብለትም ከቶ አይመለከታትም፤ ያም ይገርማት አለ፤ (ገ.100)።
ጺዮኔ መጥታ ስትቆም ጎኑ አይገድደውም ዝምብሎ ግን ያወራት አለ፤ (ገ.106)።
ሲያዋራት ሃሳቡ ግራ ገብቷት ስለስሜቱ ብቻ ታደምጠው አለች፤ (ገ.107)።
አዙሪት ዘአልፋ ውስጥ፤ ከቶ አንድአይነት ገጸባህሪው እንደ አደፍርስ ዋና አቀንቃኝ ነው። ለዐብነት የአክል።
አብርሃም ክፍል ውስጥ ተቀምጦ፣ አጠገቡ የአሉትን እንደሌሉ በመቁጠር በሃሳብ ይነጉድ አለ (ገ.14)።
ጓደኛው ብታፈቅረውም እምትለው ምንም የማይመስለው የፍቅር ጉዳይ እማይጨንቀው ልቡ ለፍቅር የተዘጋ ሰው ነው። (በመደጋገም በብዙ ገጽዎች እምንመለከተው ነው።)
በደፈናው፤ እንዲህ አይነት ሰውዎችን መገንዘብ እንደእሚያስፈልግ ሁለቱም ልብወለድዎች በወጥ አተያየትአቸው ይመሰክር አሉ። ሰውዎችን በእየጸባይአቸው መገንዘብ አስፈላጊነቱን እና ሆደሰፊ እና አእምሮ-ሰፊ በመሆን የመገነዛዘብ ነገረሁኔታዎችአችንን የአስገነዝቡን አለ።

የፍፃሜው ሩጫ
አደፍርስ ከፍተኛ ደግ ጎንዎች አሉት። አብሮ አሉታአዊ ክፍልዎች አሉት። ምንአልባት አንዱ፣ የትርክት ፍፃሜው ሩጫ ነው። ወደ ማብቂያ፣ በተለይ ከምእራፍ 58 ጀምሮ ሩጫው ትርክቱ ላይ ብቻ ነው። እየተዝናና መምጣቱ በእርግጥ ስለ አስተያየትኤዎች (commentaries)፣ እና የሃሳብዎች ውይይት ነው። ያም፣ የትርክቱን ፍሰት አዝግሞ እንደወሰደው እሚገኝ ነው። ከእዛ ምእራፍ በኋላ ግን ትርክቱ ለመፈጸም ብቻውን ይንቆረቆር እና ይፋጠን አለ።
እያነበቡት ሲመጡ ለረዥም ገፅዎቹ ከለመዱት የልብወለዱ አፈሳሠስ ወይም አቀራረብ እማይስማማ ነው። ረጋ ብሎ የአመጣን ትርክት ሲራወጥ፣ ያ ስልት፣ ጥቂት ቢሆን እንኳ ሁለት መጽሐፍዎችን የማንበብ ስሜት የአክል ይጭርብን አለ። ለልብወለዱ ወጥ ቅመሣ መሠናክል ነው።
በቅርብ ከገጠሙኝ፤ የ ይስማእከ ወርቁ ከፊል-ምናብቴ (semi-fantacy) ልብወለድ ደህንነቱ እንዲሁ አይነት የትርክት ነገራ ቅርጽ (story narration structure) የያዘ ነበር። ግማሽ ወይም በላጭ ክፍሉ የስነውሳኔ ትችት (political critique) ሲሆን፣ ቀሪው የተቀነጫጨበ ትርክቱ ሆኖ ከትችቱ ጎን ኩስኩስ እያለ እሚጓዝ ነው። በመጨረሻ ትችትዎቹን ዘግቶ በትርክቱ ፍፃሜ ላይ አተኩሮ ይራወጥ አለ። ልክ አደፍርስ እንደ አደረገው።

የልኮትአማ እና ትርክት-ከተት አተራረክ ስልትዎች
የፍፃሜ ሩጫ ችግር ተረከዙን ጎትቶ እሚወጣ ጉዳይ አለ። ያም የአማራጭ አተራረክ ስልት ነው። ትርክት ስንመሰርት፣ ሙሉ ትርክቱ፣ ለምሳሌ እንደ ፍቅር እስከ መቃብር፣ የትችትአችን አካል መሆን እሚችል ነው። ያ፣ ትርክቱ በገጸባህሪያቱ ዉጣውረድ ሲቀርብልን ከትርክቱ አፈንግጦ ትችትን ለማቅረብ የአለውን አጋጣሚ ይዘጋልን አለ። ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ፣ በልኮትአማ የአተራረክ መንገድ ማካተት ነው። ያም፣ ገጸባህሪዎቹ በትርክትአቸው ውጣ ውረድ መሀከል እና በደራሲው አተራረክ መሀከል ጥቂትጥቂት እየአደረገ አስተያየትዎቹን በጎን ይነግሩን አለ። በደፈናው ከትርክቱ እንደ ደህንነቱ ወጣ ብሎ ወይም እንደ አደፍርስ በገጸባህሪዎቹ ውይይት ትችቱን ከማስተላለፍ ይልቅ፣ በትርክትአቸው ሂደት ሲጋጩ እና በፍሰቱ ሲኖሩ ከእሚገጥምአቸው ተጨባጭ ጉዳይ በመነሳት ሊያወሩን ይችል አለ። የተነጠለ ትችት ሳይሆን፣ የትርክቱን አካል እናነብብ አለን። ይህን ትርክት-ከተት አተራረክ እንበለው። ትርክቱ ሲዘረገፍ፣ ከትችት ወእም አስተያየት የተነጠለ ጽሑፍ አይሰጠንም። ያም፣ በሁለት መንገድ (በደራሲው እሚነገረን ወይም በገጸባህሪዎቹ ከትርክትአቸው ውጭ ተቀምጠው ውይም እየተራመዱ በማውጋት) እሚነገረን ነው። ይህን ሁለት መንገድ፣ በትርክቱ መዋቅር መጨመር ወይም ትርክት-ከተት አተራረክ ፈጥሮ ማቅረብ እሚቻል ነው። አደፍርስ፣ ከእዚህ ውጭ ሆኖ፣ እንደ ብዙው የኢትዮጵያ ልብወለድ ስልት፣ ትችትዎቹን ሲያስኮመኩም የእሚዘልቀው ከመነሻው ጀምሮ እስከ ማብቂያው አጀማመር ከትርክቱ ውጭ ለተደራሲ በገጸባህሪዎቹ አንደበት በመናገር ነው። ያም፣ በፍፃሜው ትርክቱን ለመቋጨት የተለመደውን ጥድፊያ እንዲከውን አደረገው። ያም ሲከሰት፣ ልብወለዱ የመጣበት ስልት ጋር አልጣጣም ብሎ፣ የአልንውን ሁለት ልብወለድዎች የማንበብ የአክል ጭላንጭል ወይም እማይዘነጉት የአክል ስሜትን የፈጠረ ሆነ።

አብይ የኢትዮጵያ ቀውስ፦ የባህል አለመሰራት የትዳር እና ቤተሰብ ጉዳይን እንደአበላሸው
የኢትዮጵያው ማህበረሰብእ፤ አንድ ምሰሶ ችግር፣ የተዘነጋው የቤተሰብ ጉዳዩ ያም ውጥንቅጥ የሆነው ነው። ለልኮት የአክል፣ የ ቤተሰብ ጨዋታ ትመ. እይት (Tv. Show)፤ አሳላፊው እሸቱ መለሰ ሁሌ እንደእሚለው፣ ቤተሰብ ደግሞ፣ የሀገር አላባአዊ – የሁሉ መሰረት – ነው። በኢትዮጵያ ግን በትክክል፤ በእዚህ ተቋም ምን ችግር እየገጠመን ነው?
የባህል መቃወስ፣ የስነምጣኔ አቅም መኮሠስ፣ የስነስርአት (discipline)፣ ትምህርት እና አቅም ጉልበታ፣ ወግ እና ልማድ፣ ወዘተ. ጉልበትዎችን ቤተሰብእ የአባክን አለ። ወላጅዎች በአላደጉበት እና በእማያውቁት ከባቢ እሚገኙ ናቸው። ስለእዚህ፤ ልጅዎችን ተቆጣጥረው አንጸው እና መርተው ለሀገር አያስረክቡም። አቅም እና የመንግስት ቸልታ ጥላውን በቤተሰብእ እና ታዳጊዎች ጥሎ፤ ሀገር እየባሰ የመጣ ትውልድን በማከታተል ላይ ናት።
አደፍርስ እሚመክረው ዋና አንዱ ነጥብ፤ ሀበሻ በከተማ እና ገጠር መሀከል ተለያይቶ እሚኖረው በሰፋ ልዩነት ስለሆነ፣ በእርጋታ ሆኖ ቤተሰብእ እየአደገ እንዲዘምን ነው። ይህም ዛሬ ድረስ አንዱ መንገድ ነው። በሌላ ቋንቋ ማለት የፈለገው፤ ወጥ የአኗኗር ባህልን በመላ ሀገርአችን ማኖር አለብን። በሰው ደረጃ፣ እምንግባባ እና እምንነቃ ከሆንን፤ የልቡሰጥላ ለውጥ በከተማ ፍልሰት መኖሩ ይቀንስልን አለ፤ ቢያንስ። እስከእዛ፣ የ አደፍርስ እይታ ዋጋ አጊንቶ ቤተሰብእን በተማረ ደረጃ መመስረት እስክንጀምር፤ በበዙ ፍቺዎች እና ቀውስዎች ማህበረሰብእአችን ይታመስ አለ። [የበለጠ ማብራሪያውን ከእዚህ ያግኙ]

ወደፊት እንደርስበት አለን፡ ጉዞ-መካንጊዜ ትርክት የመቀመር አቅም በዳኛአቸው አደፍርስ
የ አደፍርስ ትርክት እና ሴራ አቀራረብ ስልት ዘመንአዊ ነው። እስከአሁን በአማርኛ ተጽፈው ከአየሁአቸው ጥቂት መጽሐፍት በእዚህ አንደኛ ነው። ጭራሽ ከ Indiana Jones: Raiders of the Lost Ark ጀምሮ በአዲስ ሴራ የመቀመር መንገድ የሆሊውድ ፊልም ዘርፉ እንደተመነደገበት እና እንደእሚያንጸባርቀው አዲስ (የድህረ-)ዝማኔ ሴራ አጎናጎን ስልት፣ እጅግ የ2021 እኤአ. ስኩ blockbuster ፊልም እንደመመልከት እሚያስቆጥር ሴራ አጎናጎን የአለበት ነው። የበረታ አቅም በውስጡ ሲገኝ በኋላ ወይም ይልቅ አሁን እምንመዝዘው እንጂ ባናጠና የማንመሳሠለው ስኩት ሲሆን፣ እየመሰለ እሚገኘው አንድ ነገርን ነው። ይህም፤ ምንአልባት፣ ዳኛቸው ወርቁ ልብወለዱን በአማርኛ የፃፈው ነው እንደተባለው፣ በ1960ዎቹ መነሻ አይደለም። በ2200 ዓም. የተፃፈ ልብወለድ ሲሆን በጉዞ-መካንጊዜ (time travel) ወደኋላ ተሽቀንጥሮ የተገኘልን ነው። የጉዞመካንጊዜ ጽንሰሃሳብ በአንድ ጎኑ እንደእሚያረካን፣ ለማነሣሳት እና ለለውጥ አስተማሪነት ሲባል በአማርኛ ቋንቋአችን በደከምንበት ዘመን ለመነሣሳት ከወደፊቱ የተላከልን እሚመስል ነው። በሌላ ቋንቋ፣ በእነእዚህ አይነት የአማርኛ ቋንቋ እምርታዎች ተርታ ለመግባት፣ ዛሬ በዘመኑ ብዙ መሠራት እሚገባው ነው። በአማርኛ ቋንቋ፣ የተፈተነ ሴራ አጎናጎን እና ትርክት አፈሣሰስ እንዲሁም፣ ቋንቋውንም በተቻለ አቅም በደግ መጠን የመጠቀም ጉዳይን ከአሁኑ ይልቅ የአሳካ በመሆኑ፣ ከወደፊቱ እንጂ ከወደኋላ እሚመዘዝ አይመስልም። ይህን በስፋት ከታች እናብራራ።

ትርክት የማቀናበር ስልቱ፣ እጅግ የዘመነ ነው። እንደ ወቅቱ አንዳንድ ልብወለድዎች፣ እንደ ፍቅር እስከመቃብር ወይም እንደ ወንጀለኛው ዳኛ፣ ፈጽሞ ወጥ የትርክት ፍሰትን አይከተለም። ለልብወለዱ እራሱ ይህ ዉለታ ውሎለት አለ። አንደኛ፣ የውስብስብ ትርክት እና ሴራ ፈሠሳ መፍጠሩ፣ አነጋገር ጥበቡ ከሴራው በአሻገር በአተራረክ ስልቱ ብቻም እንዲሁ ትንግርት፣ ልብጥንጠላ፣ ወዘተ. እንዲጨምር አድርጎት አለ። ሁለተኛ፣ የዘመንአዊ ልብወለድ አጻጻፍ ወይም ትርከ ነገራ ጥበብን የተከተለ ሆኖለት፣ ዛሬም እጅግ የጠራ መልካም ደረጃ ትርክት አቀነባበር እና ሴራ አቀራረብ ውስጥ አንድ ተጠቃሽ ልብወለድ እንዲሆን አድርጎት አለ። በእርግጥም ዛሬ እንኳ ተቀራራቢ አግኝቶ በሀበሻ ስነጥበብ ገበያው እምብዛም እማናገኘው በደንብ ዘመንአዊ እሚሰኝ አተራረክ ስልት ያቀረበው ሴራን የተሸከመ ልብወለድ ነው።

እንደ አባይ የማይቋጩ መጠነቃልዎች፡ በቀረ አማርኛ መዝገበቃልዎች ጸሐፊው ወይም አናስነብብአቸውም እንጂ የሰሜንሸዋ ሀገረሰብእ ተደራሲዎች፣ በእርግጥ የደስታ መከራ (ተራራ) የሆነ ልብወለድ
የቋንቋው ነገር፣ ሲጀምር ባለው ምእራፍ፣ እጅግ ግርምታ ነው። ከምኑም እንደቁንዲ እሚሰግገው በተለይ በባሰ እርግጠኝነት ዛሬ በመሀከልሀገር አማርኛ የእማንለምድአቸውን ቃልዎች በሠፊ መጠነቃልዎች (vocabaries) በመክተት እሚያቀርብልን ነው። እውነት ለመናገር ደግ መዝገበቃላት በአቅራቢያዬ ስላልተገኘ፤ አብዛኛውን አዳዲስ የሆኑብኝን ቃልዎች እንዲሁ በደፈና በመገመት አለፍኩ እንጂ መረዳት አልተቻለኝም። ይህም፤ የልብወለዱን የመግለጥ አቅም ማግኘት እንዳንችል ያደርገን አለ።
በሂደት በተለይ የአካባቢውን፣ ሁኔታ እና የመጀመሪያውን ምእራፍ ከገለጠልን በኋላ ስስመለከት፣ አማርኛውን እየወደቀ እምናገኘው ሲሆን፣ ጭራሽ አንዳንዴ ግን ዘቀጥ ሁሉ ይል አለ። ለነገሩ የቋንቋ ሁኔታውን ከአፃፃፍ ስልቱ አገናኝተን መመልከቱ ይሻል አለ።
የቋንቋውን አፃፃፍ ስልቱ ወጥነት ሁሌ አናገኝበትም። ለምሳሌ ገጽ 37 ላይ እጅግ በወረደ አገላለጽ ሲገለገለው እምንመለከት ሲሆን ከምእራፍ አንድ የመጠነቃልዎች ብልጭታ ከመፋታቱም ባሻገር የአረፍተነገርዎች ቅርጹ እየዘቀጠ መጥቶ ግስዎችን በአረፍተነገሩ ማብቂያ እንመለከት አለን። ያ፤ በተለመደው መንገድ ሲታይ፣ አማርኛን አቅለሽላሽ አድራጊ ነው። ጭራሽ ደግሞ ግሱን እሚሰጠን በጭረት ገፍትሮት ከአረፍተነገሩ አስወጥቶ በማባረር ነው – ልክ በቅጹ መበላሸት ያልበቃ ይመስል። ለምሳሌ፤ “ሀያአራት አመቱ ነው – ከተወለደ” ሲልን ቀጣይ “ከእዛ ግን ሳይቆይ – ተሠደደ” ወዘተ. በማለት ገና እሚቀጥል እንጂ እሚቋጭ አይመስልም። ይህ የአረፍተነገርዎች ምስረታ የአቀነባበር ቅርጸት እጅግ የአማርኛን ጥቅምየለሽ የቅል መሰል ጩኸት አድራጊ ነው። ምንም ለአመለካከት ንቅአት አበርካች አይደለም። አብዝተን ባለማግኘትአችን ደግ ነው። ግን፣ አማርኛውን እጅግ እዚያ አጎንብሶበት እነመለከት አለን። በተረፈ ወጣገባ በእሚለው የመጠነቃልዎች እምብሽብሹ መደበኛ የመሀከልሀገር የዘመንአችንን ተደራሲ እሚያስገርም፤ በአንዳንድ ምእራፍዎች ደግሞ እንደ ምእራፍ አንድም ባይሆን እሚያስደምመን ሆኖ እሚጓዝ ነው።

ሎሬት፣ ዳኛአቸው እና ስብሃት ገብረእግዚእአብሔር፦ ማን በአማርኛ አቅም ይበልጥ አለ?
በእርግጥ፣ ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚእአብሄር እንደገለጡት፣ በአማርኛ መጻፍ እሚቻል አይመስለኝም፣ በእንግሊዝኛ መጻፍ ጀምሬ ነበር፤ ይህን አደፍርስ የተሰኘ ልብወለድ ሳነብብ በአማርኛ መጻፍ እንደእሚቻል ተመለከትሁ እንዳሉት፣ ይህ ልብወለድ፣ እጅግ ከበዛው በመሀከልሀገር (አሁንአዊ) አማርኛ የአልተለመደ አማርኛ መጠነቃልዎቹ (vocabularies)፣ አንድ የቋንቋውን እምቅ አቅም አስመልካች ነው። አሁንም፤ የቋንቋ የመጠነቃል መብዛቱ ሳይሆን፣ የቋንቋ አጠቃቀሙ ያንን ሃሳብ መለወጥ እንዳነሣሳአቸው መገመት እሚቻል ነው። መጠነቃልዎች ግን አናሽ ስኬት ናቸው። የቋንቋ ስኬት ላይ እሚበልጠው ቁምነገር የአለው የአገላለጥ አቅም ነው። ያንን ደግሞ፤ በእርግጥ ፍፁም አንደኛ ባይባልም፣ በደግ መጠን የአሳካ ልብወለድም ነው። ለነገሩ፤ መጀመሪያ አካባቢ የአሉ ምእራፍዎቹ እንደ አሉት፣ ይህ ልብወለድ በአገላለጡ ትልቅ እንደሆነ አይቀጥልም።
ስለእዚህ አነሳሽ የመሆን አቅም በእርግጥ ሊሰጥ ይችል አለ እንጂ ፍፁም ግን አለመሆኑን እና በደግ መጠን ከእዛ መራቁን ግን ማስተዋል ችዬ አለሁ። እንደውም፤ በመግለጥ አቅም፤ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድሕን አማርኛን መመልከት እጅግ እሚመስጥ ነው። ከ አደፍርስ የተሻለ አማርኛ የጠራ የአገላለጥ አቅሙን አፍስሶ ወደ ትንግርትአዊ ንቅዓተህሊአዊ ድንበር ሲያደርሰን የሎሬትን አማርኛ እንመለከት አለን። ዳኛቸው፤ በቋንቋ አቀጣጠርአቸው፣ እጅግ ውበትን እሚያሳዩን ሲሆን፣ ወደ አዲስ ንቅአተህሊናአዊ ድንበር እና መገለጥ ሊሰበስቡን ግን በሎሬት ደረጃ ከቶ አልተሳካልአቸውም። ልብወለዱ ሲጀማምር ግን፤ ሎሬት የጻፉት አማርኛን ይታከከው፣ ይመሳሠለው አለ። በወጥ አቅም አለመቀጠሉ ለተደራሲ እና አማርኛ ቢዘምን ለእሚል ተቆርቋሪ እሚያበሳጭ ነው። በመደምደሚያው እጅግ የአልበሰለ መላምት ላቅርብ። ስብሃት ገብረእግዚእአብሔር በቋንቋ አማርኛ የተማረኩት በዳኛቸው አማርኛ ብቻ ሳይሆን ምንአልባት ምንአልባት በአተራረክ ስልቱ መጠጠር እና መዘመን ነበር። በእርግጠኝነት ፈርቀዳጅ እንጂ የተስተካከለው በወቅቱ (በአሳዛኝ ሀቅ ዛሬም) ስላልነበረ ነው። እንጂ፤ የዳኛአቸው አማርኛ በሰመጠ ደረጃ አነሳስቶ እሚያስመለክት እንጂ እስከፍፃሜው እሚዘልቅ አይደለም። ሁለተኛው መላምት፤ አማርኛን ከመጀመሪያዎቹ ምእራፍዎች ብቻ በትልቅ አቅሙ ተመልክቶት፤ አነሳስቶት አለ ማለት ነው።
ብቻ፤ ሎሬት ከተመለከትንአቸው አማርኛዎች ጥግ ዳኛቸው ደግ አቻ ለቅጽበት የነበረ፤ ስብሃት ደቀመዝሙርነትን የከወኑ ነበሩ ማለት ነው። ምንም ዳግምርምሩን (the research) ባልከውነው፤ ብዙዎች በዘመኑ ከአደፍርስ ይማሩ ይነሳሱ እንደ ነበር መገመት አያቅትም።

አደፍርስ ዛሬ
አደፍርስ የተቸአቸው ነቁጥዎች፤ ዛሬ ከሃምሳ አመትዎች ጀርባ ሆነንም፣ በእሚደንቅ ሁኔታ የያዝንአቸው ብዙ ህጸፅዎች አሉን። ተምረን እንገኝ አለ የተባልንአቸውን የአልተማርንአቸው ነገርዎችን አግጥጠው እናሳይ አለን። ቢሆንም፤ ከአደፍርስ በሰመጠ እና በሰፋ መልኩ ነገርዎች ተመርምረው ተወያይተው ስለአሉ፤ የሰረገ እና የሰፋ የእውቀት ደረጃን ማሠስ መከወን አለብን።
አንድ መማር እምንችለው እውነት መማር አለመቻልአችንን ሆኖ፤ አደፍርስ ዛሬ ያንን ቢመለከት፣ ጥቂት ሃሳቡን እሚቀይር ይመስል አለ። በዝግታ እንለወጥ ብሎ ሳንለወጥ የያዝንውንም ወግ እና ቅርስ ስለቀነስን እና ስለተውን፣ ከሁለት የአጣን ሆኖ የአገኘን አለ ስለእዚህ፤ አንዴ እንሰልጥን በቃ የማለት እሳቤውን እሚይዘው ይመስል አለ፨
———– & ————

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s