Categories
የንባብ ፉክክር [rEADEING cHALLENGE]

ጭምቅ በ ዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ ላይ (ክ. ፩)

Dagnachew Werku’s Adefris Summary, (chapter by chapter) per the first round rEADING cHALLENGE @binyamhk.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 30th 2021 GC.,

[የመጽሐፍ ጭምቅ] ዳኛቸው ወርቁ፡ አደፍርስ
[BOOM SUMMARY] Dagnachew Werku: Adefris

ይህን ጭምቅ እና ተከታዩን ክፍል በአንድነት በ ተአዶ. (PDF) የአውርዱ፨ [አማራጭ አንድ Word] [አማራጭ ሁለት PDF-Google Drive]፨

ደራሲ፦ ዳኛቸው ወርቁ፤
Author:- Dagnachew Werku;

እርእስ፦ አደፍርስ፤
Title:- Adefris;

የመጽሐፍ አይነት፦ የአዋቂዎች ልብወለድ (የተረዳ)፤
Type of Book:- Adult Novel (Illustrated);

እትም፦ (1962)፤
Publication:- 1970;

አታሚ፦ ንግስ ማተሚያ ቤት፤
Published at:- Nigd Printing House;

ገጽዎች፦ 330፣ (ስድሳሠባት ምእራፍዎች)
Author:- 330, (Sixty Seven Chapters)

የንባብ ፉክክር ገደብ፦ የካቲት 18 እስከ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓም.፨
rEADING cHALLENGE Limits:- April 14, 2021 GC.,

ልቡሰ ጥላ የእምለው፣ ከአእምሮ ክፍልዎች በአነስተኛው ውስጥ የእሚገኝ ልዩልዩ ነገርዎችን ማየት — እና ማውጠንጠን ከጀመርንበት ጀምሮ የእሚጠራቀም — መያዣ መጨበጫ የሌለው የእሚመስል ምስቅልቅል ሁኔታ ነው።– ከቤተሰብእዎችአችን ይወረሳል። ከልዩልዩ መጽሐፍት ይዘራል።– (ገ.40)
….ልቡሰጥላ ሊያድግ ይችላል። …ተረት እና ታሪኮችን አዘውትሮ በመስማት መጽሐፍትን አዘውትሮ በማንበብ አዘውትሮ በማሰላሰል ሊያድግ ይችላል። ነገርግን እነዚህ ሁሉ ተዋህደው በሰውነቱ ካልሰረጁበት የሚያመጡበት ለውጥ አይታወቀውም። (ገ.45)[Book Summary] መጽሐፍ ጭምቅ
ሴራ/Plot

አርማኒያ ላይ፤ አስካለ በባለአባትነት በቆፍጣናነት እና አልበገርባይነት ታዋቂ ሆና ጭሰኛዎቿን እያሰራች ስትኖር፤ ብቸኛ ፍሬዋ እምትሰኝ ልጇን ጥቂት ከተሜነት ስታበዛ ከደብረሲና ወደ አርማኒያ ከስምንተኛ ክፍል በኋላ እንድትመለስ ተደርጋ አብረው ይኖር አሉ። በእየ ዓመቱ ወደ መንደሩ፤ ከ አዲስአበባ ከተማ ፍትህ-አካል ውስጥ ዳኛዎች ተልከው የድሀ ገበሬውን ክስዎች አዲስአበባ ከአልጠናበት በቀረ እንዳይመጣ በማለት እየጎበኙ በመመርመር ሲያገለግሉ፤ ሁሌም ወደ አስካለ ቤት እየተጋበዙ እሚቆዩ ሲሆን፤ በእዚህ አመት፣ ዋና ዳኛው ጥሶ ወደ አርማኒያ ብዙ ልዑኩን ከነቤተሰቡ ይዞ ለመክረም ሲመጣ፣ አብሮት የእህቱ ልጅ ከኅዋአዊከተማ ቅድመምርቃ በህዝብ አገልግሎት ምድቡ ደብረሲና በመሆኑ ቦታውን ለመልመድ ሲል አብሮ መጣ። በመንደሩ፤ ቤተሰቡ ሁሉ ወደ ዋና ዳኛው እንዲያማልዱ በብዙዎች ሲቀረቡ፣ አደፍርስ ግን በመምከር እና በማሰልጠን ችግርአቸውን በጋራ እንዲሁም በ አንክሮት አይቶ ያስተምር ብቻ ነበር።
በላይ አብሮ ልቡሰጥላ እያለ ስለጋብቻ ትንታኔው ሲያቀርብ፣ እየተከታተለ፣ አብሮ ይከራከረው እና አብረው በክብረት ፈረንሳይ ሄዶ በተመለሰው ሰዓሊ ስእል ይሳሉ፣ እና ከፍሬዋ ጋርም ይጨዋወት አሉ።
በሂደት፣ አሰጋሽ ወጣት ክብረት እና አደፍርስ እንግዳዎቹን ይጠሉ ጀመረ። ብዙ ሲቆዩ፣ ትተውአቸው ከጎርፉ ጋር ወደ ፍልውሃ ፀበል ሄዱ። እዛ ሲቆዩ ጎርፉ ፂዮኔን እንጋባ አላት። ደንግጣ እንቢ አለች። ጎርፉ በእዛው ጠፋ። ብዙ ሳይቆይ ጺዮኔን ጠልፎ ከጓደኛው ጋር ቢጠፉም፣ ሲደረስበት ትቷት ጠፋ። ሮማን ደግሞ ትሰረግ ጀመረች። አደፍርስን ይዘኽኝ ከተማ ጥፋ ስራ አሰጠኝ ብትልም አልቻለም። እንድትጠብቅ ሲነግራት ከተማ ለከተማ ወዘዋወረወ ጀመረች። ሰርጓ ሲቀርብ በመጥፋቷ ጎርፉን ለማግባት ፂዮኔ ተተክታ ታጨች። አቶ ጥሶ ስራ ጨርሶ ተመለሰ። እሷም እንደ ሮማን አምልጣ ደብረሲና መጣች። እዛም በሂደት ቆይታ አደፍርስ ቤት ተከራይቶ ከክብረት ጋር በመኖር ማስተማሩን ጀምሮ ሳለ ፂዮንን በማስፈርጠጥ ተጠርጥሮ ተያዙ። የውሸቷን ተናግራ ነፃ አድርጋው አልጋባም ብላ ተይዛ መገደድ አቅቷት ሁሉም ቀረ። ጺዮኔ ልቧ ተሰብራ ወርዎችን ብሎ አመት በማዘን ስትቆይ፣ አንድ ቀን አደፍርስ እና ክብረት መንገድ ዳር ሆቴል ሲጨዋወቱ ተማሪዎች ረብሻ ጀመሩ። እነእሱም ድንጋይ ከህግዘብዎች መወራወር ጀምረው አደፍረስ እና ክብረት መሀከል ቢገቡ፣ ተመትተው አደፍርስ ህክምና ተወስዶ ሞተ፤ በቀብሩ ወቅት ሮማን እና ጺዮን ከተማ ሊወስደን ነው ብለው ሰርግ እንቢ እንዳላሉ በማዘን ሳሉ፣ እጅግ የተከፋች ሮማን ቀድማ በማምለጥ፣ ከለቀስተኛ ተለይታ ሮጠች።

ትርክት ጭምቅ በእየምእራፉ [Story Summary by Chapter]


ምእራፍ አንድ

በሰሜንሸዋ ዞን፤ ይፋት እና ጥሙጋ አካባቢ ኑሮው፤ ከሌላ ሞቅ ያሉ መኖሪያዎች በተለየ፤ እጅግ ቅዝቅዝ ብሎ በህመም ላይ እሚገኝ ነው። መልክዐምድሩ በከባዱ አስቸጋሪ ሆኖ፤ አኗኗር እጅግ አርብቶ እና አርሶ አደርነት የሞላው እና ከእጅ ወደአፍ እንደሆነ የቀረ፤ በሀይማኖት እና ታሪክ ስነስርአት እና ሂደት የተተበተበ፤ በጠቅላላው እጅግ አስቸጋሪ፣ ያንቀላፋ እና የታመመ ህይወት ነው።
ምርት የአልተሳካለት፣ ጭሰኛው ገበሬ አቶ የየየየ ከ ወጣቷ ሮማን እናት ወ/ሮ አሰጋሽ ቤት እሚዘራውን ስላጣ በእሚዘራበት ወቅት እሚዘራው ፲፭ ቁና ማሽላ ዘንጋዳ ዘር በብድር ለመውሰድ መጣ። ጭሰኛአቸው ስለሆነ አምና ስራ አግዘኝ ብለውት ስላልሠራ ተቆጥተው ነበር። በቀላሉ ለጭሰኛአቸው ከማበደር ይልቅ፤ ስለብዙ ስብከትዎች እንዲቀበል እሚከራከሩት፣ እሚመክሩት፣ እና እሚዘበዝቡት ሆነ። በፍፁም ቢያምን እንኳ እና ቢቀበልም በቀላሉ ግን አይለቅቁትም።
“ነፃነት ቢኖረንም በአግባቡ ከአልተጠቀምንው፤ አምላክን ዘነጋን ስለእዚህ እንቀጣ አለን። አንተም ከሚስትህ አምላክ ተመሳጥሮ፣ ምርትህም ሳይሣካ ሀብትህ ስለሟሠሰ፣ ልትበደረኝ የመጣህው አምላክን ረስተህ እየተቀጣህ ነው።” “ገባኝ!” “አልገባህም፤ ቡትቶ ለብሰህ፣ የእጅ ፈለግ፣ የእግር ንቃቃት ይዞህ ያለህው ከእግዜር ስር ያለንህን አምላክ ያልተጣላንን፣ እኛን ባላባቶችህን እና ባለእርስቶችንም ስለማታከብረን ነው። ዝምብ ቢሰበሰብ ቋጫ አይከፍትም፤ የበላይ ማክበር ግዴታህ ነው።” “ገብቶኛል” “መች በተግባር አዋልከው! ለእዛ ነው አምላክ ቁንጢጥ እሚሰጥህ፤ አምና አጨዳ እና ውቂያ አግዘኝ ስልህ እንቢ የራሴንም አልሰራሁ፣ ብለህ ተኮፈስህ! እኔ አልጎደለኝም። ግን ለንጉሴ እናም ለአምላክ ታዛዥ እና አንገት ደፊ ነኝ። እግዜር አልጣለኝ ንጉሴም ፊት ሞገስን አሰጠኝ። አንተ ግን ኩራተኛ ነህ። በኩራት የተነሳ የጥበብ መንገድን ሳትህ፤ እንደ እኔ ለንጉሴ ትል ነኝ እያልኩ እንደእምሰራው አንተ ደግሞ ለእኔ መስራት ነበረብህ።” “መተሳሠብ የበዛበተወ የድሮው ዘመን ይሻል ነበር አይደል?” “አዎ! ባላባት እና ገበሬ ይተሳሠብ እንዲሁም፣ ገበሬም ዐመል ትቶ ያከብር ነበር።”
የጠየቀውን ፲፭ ቁና በብር ግዛ ቢሉት የለውም፤ ታህሳሥ በአይነቱ ከምርቱ መመለስ አስቦ ነበር። ፱ ቁና ፈቀዱለት፤ በታህሳሥ ፲፭ ሊመልስ።
“መንገድ ስንገናኝ እየለቀቅህ አክብረኝ፤ አሁን ስለቸገረህ አንገት አስደፍቶ በጥቂቱ የበረደልህን ኩራት አሁንም ቢሆን ማስተካከሉን መቀጠል አስታውስ፤”
ይከብደኛል ወለዱን ይቀንሱ ቢል “አራጣ አልፈልግም፤ ፲፭ ግን ግድ ነው። ካልሆነ ተወው፤” አሉ። ጨከኑ ቢል “ከፈለግህ ተወው እንጂ እኔ ጨካኝ አይደለሁም፤ ጀግና ነህ ስራ እና ክፈል፤ እኔም የየቆረንጮው ግብር ራስምታት ሆኖብኝ እያዞረኝ ነው፤ የመነኮሳት ድርጎ፣ የሮማን ሰርግም፣ አለብኝ፤ ብድር እና ዉለታ ደግሞ ይያዝህ፤ ስቸገር ይህን ያረግኩልህን አትርሳ!”
“ይሁና!” “ውለታ እንድታስታውስ ብድር ሳይሆን አሁንም ዉለታ ዋልልኝ፤ አዋሳኝህ ላይ ያለውን፣ ድርቆሽ ሰማንያ ሸክም ቢሆን ነው አጭደህ እዚህ ደጄ ስለእሚርቅ አላቻኩልህም በ ፲፭ ቀን እስከ ወር አግባልኝ!” ብለውት ተለያዩ።
(ጎርፉ) እሱም፤ ሆን ብሎ ሰው ሳያየው መደበቅ እንዲችል ከእየእረኛ እና ተጓዡ እያመለጠ እሚመጣው እና እሚመለሰው በከብትዎች እና እንሰሳዎች እንቅስቃሴ ወቅት ስለነበር፣ ከብትዎች ለመግባት አሁንም ሲንቀሳቀሱ እየተቻኮለ፤ ሮማንን በአጥርአቸው በኩል አገኘ። እህቷን ጽዮንን አምጪልኝ ላነጋግራት ሲል ኮሶ ጠጥታ ተኝታለች አለች። ሲለምናት ብዙ አከራክራው፤ አባቴን ሳልጠራ ሂድ ብትልም እነቢ ስላለ፤ አህያ ስትመጣ እሷው መጣችልህ ብላ ልቡን ሰቀለች። ግን እሚያልፍ ገበሬ እንጂ እሷ አልነበረችም፤ ተደስቶ እነዳልነበር፤ መልሶ ያን ሲመለከት ተናድዶ፤ በቅርርብአቸው መሰረት እየተጨዋወቱ ጭምር አልቆ፤ ኮሶ ስለታመመች ፍራፍሬ ያመጣላት የታመመች ጽዮንን ልትጠራለት እናቷን ተደብቃ ገባች።

ምእራፍ ሁለት
ኮሶ ውጣ ደክማ ከተኛችበት ተነስታ ተነጋገሩ። ደብረሲና ሄዳ የተማረችውን ጥልፍ መጥለፍ ልታሳየው ብትልም ቸኩሎ ስለነበር ይለፈኝ በማለት፤ ከደብረሲና ከመጣች ወዲህ ጥቂት ጊዜ ሲገናኙ አጉርጣ እምታየውን የሰሞኑን አተያየቷን የውስጡን እምትመለከትበት እየመሰለው ስለእሚያሸብረው እንድታቆምለት ለመነ። አተያየቷ ከከተማ ከመጣች ከተሜነት ለምዳ ስለመሆኑ እና ወደ አዳል ውስጥ ራሳ ወደእሚባለው ሀገር እንደእሚሄድ እና እነሱን መስሎ አሸርጦ ዓዋዲ ለዓዋዲ ደግሞ ስልብ ፍለጋ እሚመላለስ መሆኑን እንደእምታውቅ ነገረችው። እሱም እነእሱን እንደእሚወድድ አሳወቃት። በግልጽ ከእነሱ ውጭ ያለ ሌላውን ሰው ይከረፋል እንደእሚሉ እና እነሱን ግን ከእዚህ ከእሱ ጋር እሚሄዱትን እንደለመዷቸው ነገራት። ከተማ ብዙ ሰንብታ ስለመጣች እና እሱ ገጠር ቆይቶ አዳሎቹን ለምዶ ስለወደደ ምን ስለእሷ እንደእሚሰማው ጠይቃ፣ ጨዋታውን ወደ ያዘው ጠብመንጃ አዞረች። ጨቅጭቃው አቶደኝም ስትል “ገድሌ ይሙት” ብሎ እንደእሚወድ ምሎ አስተኮሳት። (ከእሚከስር ብሎ) ሙከራዎቿ ሲከሽፉ እራሱ ተኮሰው። እንደፈራው እናቷ ጭሰኞቼ ብለው ብለው በጥይት ይጫወቱ ጀመር ብለው በሮማን ጽዮንን አስጠሯት። እሷም፤ ጎርፉ አተያየቱን እንደለወጠ እና የተደበቀ ውጥን እና ምኞቶች ብዙ ነገርዎች በውስጧ እንደእሱ እሷም ደብቃ እንዳላት እና አዲስአበባ ከእዛ ቀጥላ ደግሞ ፈረንጅ ሀገር መሄድ እንደእምትፈልግ፤ እንዲሁም ዘፈን መማር እንደእምትሻ ህልምዎቿን ከአተያየቱ ተነስቶ ብቻ የአንጀቷን ገልጦ እንዳያቅባት እንደእምትፈልግ ነገረችው። የአረጋሽን ቁጣ ተናግራ እህቷ ስትጠራት የአመጣላትን የኮሶ እራቷን ሳይሰጣት ወዲያው ስትገባ ለሮማን አስረከበላት፤ እነእሱም በኮሶ ቅጠል የተከበቡ፣ እንጆሪዎች ነበሩ።
ወርዶፋ፣ እረኛው እንደለመደው በማምሻዎቹ ከብቶች አጉሮ ዋሽንቱን በመንፋት ሲለቅቅ፣ በነፋሻማው መንደር ይሰማ ነበር።
ስለ ፀባይ መለወጡ አስቦ እያወያያት ቆዩ። ሲጨላልም ከተመልካች በመደበቅ እያሰባበረ፤ ተመለሰ።

ምእራፍ ሦስት
እቤት ስትገባ፣ እናቷ የወርዶፋን ጎጆ መጣበቁን ቢያንስ ሲመሻሽ እንኳ ከሆነ እንድትተው እና እቤት ብትሆን እንዲያ የመቆየት ፍቅር ይኖራት እንዳልነበር ነግራ ወቅሳ፣ ጴጥሮስ ዋናውን አብዬ ወልዱን ጨምሮ ዳኛዎች እና እንግዳዎች ለሰርጉ ጥራ ተብሎ ስለጠራአቸው እና ስለእሚመጡ፣ የኅዋአዊከተማ (university) ተማሪ ዘመድዎችም ውስጥ ተያይዘው ስለእሚደርሱ፣ ከአዲስአበቤዎች የአነሰ በመሆን ገጠሬነትአቸው እንዳይነሳ እንድትዘጋጅ፣ የቆዩ የደበቀችባትን መጽሐፍዎቿን እና ደብተርዎቿን አቧራ ጠርጋ እንድታነብብ እና በተለይ እንግሊዝኛ አንብባ በመልመድ ከተሜ በእሚፎካከር ጉብዝና በእንግሊዝኛ እያዋራች እንድትቀበልአቸው ሠጠቻት። እሷ ግን በአምስት ስድስት ቀንዎች ምንም ረብያለሽ ነገር መገንባት እንደእማትችል አሳወቀቻት። በአጭር ወቅት፣ ሌት ከቀን አንብባ፣ ልባም ስለሆነች በቶሎ ሁሉን ጨርሳ እና ጉብዝናዋን ተጠቅማ፣ ሳይንስም ደብተርዎቿን አሳይታ ፣ ተምራ እንደተወችው እንጂ እምታቀው መሆኗን አረጋግጣ፣ አሰጋሽ ከባድ ወይዘሮ ልጇም ጺዮን ትንሽ እማትሰኝ እመቤት መሆኗን ልታረጋግጥ ወተወተች፣ አግጣጫም አቀረበች።

ምእራፍ አራት
ጽዮኔ የአሰጋሽ አዝራው፣ ብቸኛ ልጅ ናት። ትሁት፣ አርቆ አሳቢ፣ ረጋ ያለች፣ ብሩህ፣ ንፁህ፣ ሰው እማትገምት፣ ልዩ ሰው ናት። ማክበር እና የሰውን አለመንካት ትወድድ አለች። ሰዎች ግን አጠገቧ ጨዋታ እማታቅ እና ኩሩ ነች እያሉ እንደልብአቸው አይጫወቱም፣ እሷም ምንም የስሜት መለዋወጥ ቢገጥማት የመቻል ነገሯ አይጣል ነው።
ጎርፉ አብረለ አደጓ ዳዊት አብሯት ደግሞ፣ እስከ ስድስት ደግሞ፣ አርማኒያ መንግስት ትምህርት ቤት ተምሮ ፈቅዶ ሲያቋርጥ እሷ ደብረሲና የተማረው እና እውቁ ነጋዴ አጎቷ ወልዱ ዘንድ ሄዳ እስከ ስምንት ጨረሰች። አብራ ጥልፍ መጥለፍ፣ አገልግል መስፋት፣ እና ሙዚቃ ላይ በርትታ ደግሞ በክራር እና ሀርሞኒካ አጨዋወት እጅግ ጎበዝ ስቶን፣ አጎቷ እህቱ እናቷን ሲያገኝ፣ እሚነግረው ግን የትምህርት ጉብዝናዋን ነበር። ማታማታ ክራር መጫወቱን ማንም አይመስላትም። ቀንቀን በጄ አይለኝም እሚል ቋንቋ ነበራት። ማታ ስትጫወት የእናቷ ነብስአባት አዲሴ ክራር ሰምተው በመቆጣት መንፈስ ወስዷታል በማለት ተናግረው ወደ እናቷ እንድትመለስ አድርገው ስትመጣ፣ ስልጣኔ ፈጥና ትቀስም ስለነበር በቂ አውቃ በመመለሷ ጎርፉን ሰልጠን ያለ ማልበስ እና ንግሩን በማረም ታዘምነው ነበር።

ምእራፍ አምስት
አዘጋሽ ዝራው የነፍጠኛ ልጅ ሲሆኑ፣ ከታወቀ ዘር መንዝ ተወልደው በአርማኒያ እንደባላባትነትአቸው እያሳረሱ ኖረው፣ በትልቁ በታጠረግንቡ በተለየ ቤት ይኖራሉ። እልፍኙ ተደራራቢ፣ ባለብዙ ክፍልዎች ቤተንጉስ (castle) ነው። የሟች ባልአቸው ሻለቃ ይነሡ እቃዎች፣ የእሚያገለግሉ የቤት እንሰሣዎች፣ ልዬልዩ ቁሳቁስዎች፣ ወዘተ. ያሉት ባለብዙ ክፍልዎች ቤት ነው። ከውጭ፣ ሁለት ሰቀላዎች እና የገበሬዎቹ አለቃ እረኛው ወርዶፋ ያለበት ጎጆ አለ፤ ጺዮኔ ያንን ቤት የበለጠ እምትወድደው ነው። ከታጠረው ቤት ውጭ ጉድጓድ ሲኖር፣ እህል ያስቀምጥ አለ። ባላባቱ ጉድጓዱን ወንጀል መፈጸሚያ እዳይሆን እሚቆጣጠር ነው።

ምእራፍ ስድስት
በእየክረምቱ ዳኛዎች ከአዲስአበባ ወደእየአውራጃው በመምጣት ሰዎችን ወደአዲስአበባ በመመላለስ እንዳይንገላቱ እሚሰሩ ሲሆን፣ ከልዑክ ቡድኑ ጓዝ ለያዘ ኪራይቤቶች፣ ጓዝ ለሌለው የተሟላ የእንግዳ ማረፊያ በነፃ በቤትአቸው አድርገው፣ በደብረሲና እውቁ ነጋዴ አቶ ወልዱ ተቀብሎ ስለእሚያዘጋጅልአቸው፣ እዛ ሳሉ ጥሪ ማድረጉን አሰጋሽ በቀላሉ ያስከውኑታል።
አሁን የደረሱት አጭሩ እና እማይለዋወጥ ስሜት እና ፊት ያላቸው ዳኛ ጥሶ፣ ሚስትአቸው ከሞተች ወዲህ ከአስራሰባት አመቷ ልጅአቸው ፍሬዋ ጋር እያቀማጠሏት እና ቅብጥብጥ እያረጓት እሚኖሩ ናቸው። ሁለቱም፣ ወሮ. አካላት ታላቅ እህትአቸው እና ልጅአቸው አደፍርስ፣ ሠዓሊ ጓደኛ እና ገረድ ጭምር አብረው ይዘዋል።
ፍሬዋ ቀጫጫ፣ ቀኝ አይኗ እንደረጠበ ያለ በመሆኑ ለሰዎች እሚፍለቀለቅ መንፈስ ግንፈላ ያለባት እሚመስልአቸው ሆኖ ያላት፣ የፈረንጅ ሙዚቃ እሚኮረኩራት፣ ‘እችክ እችክ’ እሚያዛጋት፣ እንደእሳት እራትን ብርሀን ስቧት እንደእምትጠጋ ሁሉን ወጣት ወንድ እምትስብ፣ የዝናቡ ሀገርን አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትጎበኝ የጠላችው ናት። ይባስብሎ፣ አማላጅ ሁኝን እያሉ የገጠሩ ሰዎች በደንብ ስለእሚመጡባት፣ አባቷ ግን መማለጃአቸውን ከቶ እንዳትቀበል ተቆጥተው ስለእሚነግሩ፣ ህግዘብ (police) ከምጠራ ከእነስጦታአችሁ ተመለሱ እያለች መመለሱ አሰልችቷት አለ።
በእዚህ ነገር ልብአቸው አልጠናም እያሉ የነበሩት፣ አክስቷ ወሮ. አካላት ነበሩ፤ ብዙ ነገርተኛው ወደወንድሟ በእሷ ጋር ባልደርስ ኖር ብዙ ይፈረድብኝ ነበር እያለ ሲያወራባቸው በመሰማቱ ይጠረጠራሉ። እሳቸው፣ አምስት ሀብታምዎችና እና መኳንንት አግብተው ከሁሉም አንዳንድ ወልደው የሞቱባቸው ሲሆኑ፣ እየመረጡ የአገቡአቸውን ሀብትአቸውን ልጆቻቸው ወርሰው ይንደላቀቁበት አለ። ሰውም፣ መርጦ ማግባት እንደሳቸው፤ ባል መፍጀትም አንደኛ ናቸው እያለ ቢያወራብአቸውም፣ አሁንም፣ ሀምሳ አመቴ ስለሆነ ከስድሳ አመቱ ያላለፈ፣ ሀይማኖተኛ፣ ምራቅየዋጠ፣ ባገኝ አሁንም አገባዋለሁ፤ ዘር እና ማእረግ አልጠይቅም ይላሉ። ቢሆኑም፤ ሰሞኑን ግን ባልገፊ መባልአቸው በወሬ ሲበዛ የማግባት ፍላጎትአቸው እየቀነሰ፤ ባልምን ያረጋል እያሉ ነው። ልጅዎችአቸው አድገው እያገቡ ሀብተጀን ይዘው ሲለዩ፣ በሀብትአቸው ወቅት እሚጎበኘው እሚያረግደው እንግዳ እና እንክብካቤ ሁሉ ስለቀነሰ፣ አሁን ባልዎችአቸውን በትዝታ እንኳ እረስተው ሲሞቱ ያጋበሱትን ክብር ፍለጋ ወደ ጥሶ ወንድምአቸው ዘንድ በመጓዝ የእሱ አጀብን ይካፈል አሉ። ሰው አማልዱኝ ሲል እያወጉ፣ እየጋበዙት፣ መማለጃውን እየተቀበሉ፣ የድሮ አጀብአቸውን ይመልሱት አለ።
እሳቸውን በፀባዩ እማይመስለው፣ ልጅአቸው አደፍርስ፣ ፊተሰልካካው ባለሃያአራት አመቱ ወጣትን፤ ነገርተኛ ቀርቦ ሲከብበው እና ሲያደምጠው ደስ እያለው ምክር በተለይ በመስጠት ያስተናግድአቸው አለ። ከአዲስአበባ ለመጀመሪያጊዜ ወጥቶ አብሮ ደብረሲና የመጣው፣ ከኅዋአዊከተማ የአገልግሎት ምድብ በደብረሲና ስለወጣለት፣ ቀደምብሎ ደርሶ የከተማ ሁኔታውን ለመለማመድ ነበር።
አፍአዊ (ውጭአዊ) ሁኔታው እጅግ ግድየለሽ – አለባበሱ ዝርክርክ፣ ጸጉር አያያዙ ወጥነት የሌለው፣ ለማያስቸኩለውም እሚቸኩል አረማመዱ ብዙጊዜ መላቢስ፣ በጊዜአዊ እይታው ተመስርቶ ረዥምጊዜ ውጤቱን ሳያስብ ድርጊት እሚከውን፣ የመታየት እና የመታወቅ ፍላጎቱ ሁሌ ሰው ወደተሰበሰበበት ስለእሚመራው ለንግግር ተዘጋጅቶ እሚገኝ ሰው ነው። ከአልተግባቡት ደሙ እሚፈላ፣ በተለይ በተቃውሞ ሰልፍ ድጋፉ ከመጡበት እሚጋጭ፣ ነበር።

ምእራፍ ሰባት
ደብረሲና አደፍርስ ትንሽ ከርሞ በመቀጠል ወደ አጎቱ ችሎት ወረደ። ብዙዎች የዋና ዳኛው እህት ልጅ በማለት ለምልጃ ይቀርቡት ጀመር። ዳሩ፤ ከማማከር እና ማውራት በቀረ ብዙ ማማለዱን አይከውንም ነበር። በተለይበቤተሰብ ጥል ዙሪያ እሚቀርበውን ወሬአቸውን ሲያደምጥ፣ ይሰለች ጀመረ፤ እና በመጨረሻ አንድ መልስ ለሁሉም እንዲሆን አድርጎ ማበጀት አስቦ የሁላችሁ ችግር ምንድነው? አሁን በብይን ብትጣሉም ብትስማሙም ሌላዎች መምጣትአቸው አይቀርም። ስለእዚህ የሁልአችን ምንጭ ችግር ምንድር ነው?
ወደ ስር ወስዶ እያየወያየ ይህን ጠየቀአቸው። ለምን ሴተኛአዳሪዎች በከተማ እና ገጠር በዙ፣ በሽምግልና መፋታትዎች ጨመሩ፣ ወጣትዎች ጋብቻን ፈሩ፣ ያ እንዴት ይሻሻል አለ፣ አብዛኛው ሰው ውቃቤ ራቀው፣ እንዴት እራስን አውቆ መኖር ይቻላል፣ ወዘተ. እያለ በመጠየቅ፣ መልስ ሲሠጡት ቆዩ እኔ አብራራለሁ እያለ በመዘርዘር ጠየቀ። የሁሉ መልሱን ለመተንተን ልቡሰጥላን እንወቅ ብሎ ማብራራት ሲጀምር ጉድፍ ሰይጣን ብለው አቂያቂያሉት።
ልቡሰጥላ፣ በድብቅ ጭንቅላትዎችአችን ከልጅነት ጀምሮ እሚጠራቀምብን እምናውቀውን እምናየውን እምንወድድ እእምንጠላውን ሁሉ የተሸከመ የመረጃ ቋት ነው። ያ፣ እሚገነባው ከልጅነት ጀምሮ በምንሰማው፣ እምናደምጠው፣ እምንመለከተው፣ እምናነብበው፣ ከቤተሰብ ዙሪያ ሳለን እምንመለከተውን በአብነት በመቅዳት ነው።
ስለእዚህ፣ ቤተሰብ እራሱን እንዳስመለከተው እቅጩን ልጁ መስሎ ያድግ አለ። በቤተሰቡ መልካም የተባለውን ሰው አይነት መስሎ ለጋብቻ እሚመኘውም ያንን አይነት ሰው ነው። ግን፤ ከቀዬው ከወጣ ልቡሰጥላው አዲስ መመዘኛ ይማር አለ።
በላይ መጥቶ ሰዎቹ ነገርአቸውን እሚያደምጥ ቀጥሎ እሚያማልድ እንደሆነ እንጂ እንዲያስተምር እንደእማይፈልጉ ነግሮት ያነሳው ሃሳብ ግን እንደማረከው ገልጦ ከፍሬዋ ጋር ሊስልአቸው እንደ እሚፈልግ ጋሽ ክብረት እንደጠራአቸው ገልጦ ቀድሞ አንድ ጥያቄ እንዲያብራራለት ጠየቀው። ከቀዬ ባይለቅቁም፣ ከቀዬ ውጭ ከአለ በመቀራረብ እና ወሬውን በመስማት፣ ሌላሌላ በማንበብ አዲስ ልቡሰጥላ ማግኘት እሚቻል ነው ብዬ አስብአለሁ፤ ጭራሽ ይህኛው አለቅጥ አድጎ ግለሰቡን እያበሳጨ በብቸኛነት እሚያኖረው እሚሆን ነው ሲለው አደፍርስ ተነስቶ በሉ ዋናዋናውን አጉርፌልአችሁ አለሁ፣ ሌላጊዜ እንቀጥል አለን በማለት ሲለይአቸው፣ ሁሉም ነገርአቸው ስላልተሰማ ባስተማረው ሳይጨነቁ እየተናደዱ ሳለ አንዱ የግድ አድምጠኝ ተቸግሬአለሁ፣ እምካሰሰው ከሀብታም ነው ሲለው እውነትህ ያሸንፋል አለው። አይሆንም፣ አቅም ያለው፣ ንግግር እሚያውቅ፣ ገንዘብ ያለው፣ ነው እሚያሸንፈው፣ ካልረዳህኝ ያሸንፈኛል ነገ ሲለው ጠበቃ አይደለሁም፣ ጠበቃ ቅጠር፣ እንጂ መሸነፍም ቢሆን አያስፈራህ ብሎ ከበላይ ጋር ከነገርተኛው በመለየት ይጓዙ አለ። በሂደት፣ ሲወያዩ በላይ ጥያቄውን አነሳ፣ ከለመዱ፣ ከሌላዎች ከመማር የተነሳ እምንማረው አዲስ ልቡሰጥላ አለ። በበፊቱ ልብስተ ጥላ መሰረት ወድደን ያገባናት ከቀረቡን አዳዲስ ሰዎች ከመማርአችን የተነሳ አመለካከት በመቀየርአችን ጊዜ አስጠልታን በአዲስ ልቡሰጥላ አምሳያአችን ስለማትስማማን በሌላ እምትሆነን ሴት እምንቀይራት እንፈልግ አለን እኮ ብሎ አማከረው።
አደፍርስ ያን ጉዳይ እንዳሰበበት ገልጦ፤ ቤተሰብ አካባቢ ነው ሁሉ እሚመሰረተው ብሎ ጀመረ። ግን ከሌላዎች ተምሮ፣ ደጋግሞ በማሰብ እና በመነጋገር በእርግጥ አዲስ ልቡሰጥላ ሊጀምር ይችል አለ። ዳሩ፤ በሰውነቱ ከአልሰረጀ እሚመጣው ለውጥ ለሰውዬው አይታወቀውም። ያን ማወቅ እሚቻለው እንዴት ነው ብሎ ሲጠይቅ፤ ከሰረጀ ውጋጋን ያስመለክት አለ ብሎ ቀጠለለት። ውጋጋኑን እሚያስመለክቱ ነገርዎች ሲቀርቡት ስሜት ከአልሰጡት አልሰረጀበትም ማለት ነው። የፍቅር ዜማ ሲያደምጥ፣ ስእልዎች ሲመለከት፣ ወዘተ. ልብስተጥላውን ስትንቀሳቀስ ማየት አለበት። ሌላም ሙዚቃ ሲሰማ ወዘተ. የልቡሰጥላ ጀግናው ሊታየው ይገባ አለ። በእውኑ እያጓጉት፣ በህልሙ እየመጡበት፣ ይሄድ አለ። ለአቅራቢዎቹ ፍቅሩ እየቀነሰ ለልቡሰጥላው እየበዛ እሚሄድ ነው። በሂደት ልቡሰጥላው በእሚያስመለክተው ቅርጻቅርጽ እና ልዩልዩ ነገርዎች እየተደሰተ ከሰው በመነጠል ይኖር አለ። ሰውነቱ ሁሉ ወደእዚህ ፍቅሩ ይሰራ እንጂ እንደተለመደው አይሆንም። ወሰንየለሽ ክብር፣ ውበት፣ ግርማሞገስ፣ ሀይል፣ ወዘተ. መሰል ጌጣጌጥዎች ሰጥቶ፣ የሰው ፍቅሩን ውስጡ ይውጥበት እና ከህልሙሴት (ሴት ከሆነች ከህልሟ ወንድ) አጋብቶ ያስቀምጠው እና በእውነቱ ደግሞ እድሜዘመን እማያገባ ይሆን አለ። ልቡሰጥላውን በግዙፍአዊ ወይም አፍአዊ ለውጥ በመቀበል የተነሳ በመለወጥ ጊዜ ሲበዛው እሚቀጥለው ነገር ቢኖር ልቡሰጥላው ተትቶ በገሀድ መቀየር ነው። ሚስት ፈቅዶ ያገባ ወንድ ልቡሰጥላውን እሷ ትወክለው እና ልቡሰጥላው አፍአዊ (እሷ) ስለእሚሆን፣ ህልሙ እውነታው ሆኖ እሚቀጥል ይሆን አለ። አንድአካል አንድአምሳል ተኮነ እሚባለው ጋብቻ ሲከወን ይህ ስለእሚፈጠር ነው አለው።
በላይ ተመስጦ የተናገርከው ረቀቅ ብሎብኛል፤ አስራሁለተኛ ክፍል ድረስ ብማርም፣ ገና ታስተምረኝ አለሁ አሁን ወደ ስእል እንሂድ አለው።

ምእራፍ ስምንት
እነበላይ ቤት በላይ እና አደፍርስ ሲገቡ ወሰራ ዶሮ እየኮኮለ፣ ሴቶቹን በመጋበዝ እና በማጥቃት ፊትለፊትአቸው ፋታአጥ (busy) ሆኖ ቆመው አየት አርገው ሰዓሊው ክብረትም ፀሐይ እየሞቀ ተቀምጦ ሲመለከት አገኙት። ስለዶሮዎቹ በእንግሊዝኛ እና አማርኛ እየደባለቀ ግርምት መከወኑን እና ነገረስራአቸው አስደናቂ እንደሆነበት አብራራልአቸው። ዶሮውን ሴትዎች በማመራረጡ እንደሰው አመለካከቱ ሳይቀየር አንዴ የወደዳትን እንደእማይቀይረው እሚፀኑ አለመሆንአቸውን በላይ ሲያነሳ፤ አደፍርስ ሰው ከውጭአዊ እይታ በላይ ውስጥአዊ እይታዎች እንደአሉት ጨምሮ ገለጠ። ልቡሰጥላው ያስመለከተውን ለመከወን እማይፈጥን፣ ዉሸት ቢሆንም ከጓደኛው ከተስማማበት ለመከወን እንደእማያቅማማ፣ ለእዚህ ልቡሰጥላ ጠንከር ብሎ ከሰውነት ተጣብቆ ያለ እንደሆነ እንጂ ትንሹ ነገርን ያለ እንዳልሆነ አብራራ። ክብረትም መሣል ጀመረ እና ንድፍ ይነትብ ጀመረ፤ እንዘጋጅ ሲሉት ከእዛ በላይ አልሻም በስሜት እንደሰመጥአችሁ ቀጥሉ እና ተጨዋወቱ እናንተ አዋቂ ወጣትዎች እኔ እስልአለሁ አለ።
አደፍርስ ቀጥሎ፤ ልቡሰጥላ እሚያሳየንን መቶበመቶ በምድርአዊ ህይወት አናገኘውም ግን በቂ ደረጃውን ፈልገን መኖር እንችል አለን። ለምሳሌ ጋብቻ አልሰምር እያለቢሆንም፤ እሚግባቡ ከተቀራረቡ ግን፣ ረዥምጊዜ መቆየት እሚችሉ እንጂ እንደዶሮው ሁሉም ተጋቢ እማይሳካለት ቀያያሪ አይሆንም ብሎ አብራራ። ክብረት እሚሞነጫጭረው እነሱን አልመስል ሲል እማነሳው እንደፎቶ አይደለም፤ እነእሱን ሲያይ እሚታየውን መሆን እንደአለበት ገለጠ። ሰው እሚወድደውን የልብስተጥላውን ሰው ካገባ አብሮ ይቆይ አለ። በቀረ ያገባውን ለመፍታት እሚቸኩል እንጂ እሚቆይ አይደለም፤ እሚወድደውን ፍለጋ ይጠመድ አለ እና። ፈቅዶ ያያገኛትን ግን ከምድር ሴትዎች ሁሉ አብልጦ እሚይዛት ይሆን አለ። በላይ አልስማማ ሲል ይሞግተው አለ፤ ለምሳሌ ሚስት ያገባ የሆነች ሴትን የወደደ ሰው መልሶ ሌላ ሲያይ የወደዳት መስሎት ይጋቡና ቶሎ ይፋቱ አለ። ያ፣ ሚስቱን በአይን እና ጆሮ ወደደ እንጂ በልቡሰጥላው ልክ ስለ አልወደደ እሚከሰት ነው።
ክብረት ‘እምስለው ስትከራከሩ እማየውን ፍቅር እንጂ ሌላጊዜ የሆናችሁትን አይደለም’ እያለ ክርክሩን ተቀላቅሎ ቀጠለ። ከስእል ሊያወዳድር ይህን አለ። ‘ልቡሰጥላው ሲጋቡ በደንብ ሳይስማማ ከነበር፣ ልቡሰጥላው አብሮ ቆየት አድርጎአቸው ለጊዜው እንደቆየ ግን ዋናው ልቡሰጥላ ሲነቃ ባል እና ሚስት መጣላት ይጀምሩ እና ከአለፍቅር ለመኖር ሲባል በመታገስ ይቆይ አሉ። ሲጠና መጠላላቱ መፋታት ይሆን አለ። ወንዱም ልቡሰጥላው ዘግይቶ ሲነቃበት ትኮሰኩሰው ይመስለው እና ሊጠላት ይጣጣር አለ። ለምሳሌ ሴቷን ቢስል ተጣልተው ሳለ የያዘችውን ሰውነት ሳይሆን የእሚንበለበለውን የውስጧን ማንነት እሚስል ነው’ በማለት መለሰ። ቀጥሎ፤ ሚስት በልብስተጥላ መሰረት ከተገባች፣ ልብስተጥላ በእድሜዘመን እሚጠራቀም እሚወድዱት ምስያ ስለሆነ በጣም ያፈቅራት አለ። ስለእዚህ ያገባትን እንደጓደኛ መመልከት አለበት። ያኔ እሚወዳት የህልሙ እመቤት ከህሊናው ወጥታ በአካል ያለችው ትሆንለት አለ።
ያንን ሲባባሉ የልቡሰጥላ እመቤትአችንን በደንብ ስለመተዋወቅ እንደእሚከብድ ተነሳ። አደፍርስ፤ አይከብድም ብሎ አብራራ። ሀያ ወይም ሠላሳ የሆነ የአክል፣ ስለ ልብስተጥላ እመቤቱ እንዲፅፍ እና እምታሟላ ከሆነች እንዲያጠና ያስፈልጋል ሲለው ክብረት እማትቀርብህ እና እማታወያይህ ከሆነችስ አለ። አደፍርስ፤ ወንድነቱን ባለማልፈስፈስ የተማረከባትን በደንብ ቀርቦ ማጥናት አለበት በማለት አብራራ። ከተስማማችው፤ የልቡሰጥላው እመቤት ሆነች። ማለትም፤ የውስጡ እመቤት የውጭዋ ሆነችለት። ከአንድ አጥንት መፈጠር፣ አንድአካል አንድ አምሳል መሆን ማለት በአጭሩ፣ የልቡሰጥላ ሴትን አጊንቶ ከህሊና ወደአካል መለወጥ ማለት ነው፤ በማለት አብራራ። እሱን አቅርባ አጥንቷት ወድዷት እሷ ባትሳብበትስ በመጨረሻ ሲለው፤ ስላዋራት ብዙ ስለተጨዋወቱ ጥቂት መዋደዷ አይቀርም። በሂደት ግን፣ እሱ በብዛት ስለተስማማችው ሲንከባከባት እየበለጠ ትወድድደው አለች። እሱ የልብስተጥላው መስታወት ስትሆንለት፤ እሷም የልብስተጥላዋ መስታወት ይሆንላት እና በሂደት የበለጠ ይቀራረብ አሉ። ክብረት አልስማማ ብሎ ከየት ይህን የህይወት አተረጓጎም ተማርክ ይለው አለ። እሱም ከኅዋአዊከተማ እንደተማረ መለሰ። ከኅዋአዊከተማ ገብቼ ያለሁት የተጻፈ መልሼ ለመናገር ሳይሆን፤ የችግርዎችን ምንጭ ለማሠስ እና እውነትን ለመፈልፈል ነው። እናም የድሮ አባትዎችአችን ይህን እንደተነተንኩልህ አይተንትኑ እንጂ የጋብቻ ስነስርአትአቸው እሚከተለው እንደነበር አውቅ አለሁ። በፊት እነእሱ ከቀዬ በረት ሳይወጡ በተመሳሳይ ልቡሰጥላ ይኖሩ ነበር። እስከ ቅድመአያትዎች ተመሳሳይ አመለካከት፣ ተረት፣ ሚዛን ይዘው በማደግ እሚያሳድጉትም ተመሳሣይ ልቡሰጥላ ነበር። የእሚመረጥልአቸው ባል እሚሆነው የተዋወቁት እና የወረሱት የአያትዎችአቸው ልቡሰጥላ ነው። ልብስተ ስጋ የሆነችው ሴትም ለወንዱ ልብስተ ጥላ ሴት አቻ ለእሷም እንደእዛው ሆነው እሚኖሩ ናቸው።
ስእሉን ሲመለከት ድንገት ልዩ ሆነበት። ግማሽፊቱ ስንጥብ፣ ግማሽ ፊቱ ሰው፣ ዓይን፣ ጆሮ እና እግር ለእየብቻው፣ የቀለም ቦግታ እሱም እንስራ የተሸከመች ሴት እሚመስል ነው፣ ሥለእዚህ ከቶ የተሰማህን አልሳልክም። ሴቷም ፍሬ አልመጣችም ከየት ሳልካት? የሳልኩት አሁን እምትኖሯትን ቄደረኛ ማንነትአችሁን እንጂ ከቶ እናንተን በቀጥታ አይደለም። የዘመኑ ቄደረኛ ወጣትን ለመግለጥ እሚሞክሩ ምስልዎችን እምናዘጋጅበት ነው። የቀለሙ መወራቸት የዘመኑን ድምፀታ ቀልብ ፍለጋ እና ጠቅላላ አየር እሚጠቁም ነው። ሲል በላይ ተቆጣ። እምፈልገው ከአፍንጫዬ ጀምሮ ሁሉም አካሌ እንዳለ እንዲሳልልኝ ነበር፤ ጊዜዬን አባከንክ። ከፈረንሳይ መሄድህ በፊት ስትስል ሰው ሁሉ ሰው መሆኑ አይታወቅ መልአክ አስመስለህው ነበር። መማር ክፉ ነው፤ እያበላሸህ ነው። እንዲያ እንደድሮ ነበር እንጂ መሳል። ክብረት ያ ዘመን አለፈ ብሎ ተከራከረ። አሁን ማንም የውሸት ቆንጆ መሆን አይፈልግም። ሰው ተራቅቋል፤ ፀጉር ሠንጥቋል አእምሮውን እሚያሳስበው ልቡን እሚያረካው እሚያሳስበው ነገር ይፈልጋል። ከእምታጎርሰው ሰርቶ እና እነዳሻው ሆኖ መመገብ ይሻለዋል። ህዝቡ እንዲያ ሰልጥኖ አለ። በላይ ተናድዶ፤ እኔ ህዝብ አደለሁም። የአልክው ስልጣኔ ሳይሆን ግልበት ነው ለእኔ። ክብረት ከፍሬዋ ጋር ስለሳይንስ፣ ጆግራፊ፣ ስነጥበብ ስትከራከሩ እንዴት አልዘመንክም ብሎ ሲጠይቀው ወደ አደፍርስ ሲዞር የለም። እጅግ ተናደደ እና በሩጫ ሊደርስበት ተፈተለከ፤ ‘ወደ ፍሬዋ መድረሻ ሰበብህ አመለጠህ’ ብሎ ለእራሱ አጉተመተመ፤ ስእሉን ፊቱን ሰየፍ ሰየፍ እያደረገ እየተመለከተ።

ምእራፍ ዘጠኝ
ፍሬዋን እቤቷ አጊኝቶ የአወራት ጀመረ። ስለተለያዩ የልጅነት አስፈሪ ትውስታዎቹ እንዲነግር በላይን እሚወድደው ወሬ ስለገጠመው አሁንም ጠየቁት። አስር አመቴ አካባቢ፣ ከባላገር ወደደብረሲና ሳንመጣ ገና ለድግስ ብቻ ስንደርስ እኔ አልመለስም እዚሁ ልደር ብዬ በማልቀስ እዛ ለማደር ተፈቀደልኝ። ቋንጣ ባለቤቱ ሰጥተውኝ ስበላ ጥርሴ ተሰንቅሮበት የዋጥኩት ሳይሰርግ አነቀኝ። ሌላው የራስአቸው ልጅ ሲጠራአቸው ማጅራቴን ቢሉኝ ዋጥኩት እና ከእዛ ይልቅ እሚተፋ ነበር ይገርም አለ መዋጥህ ብለው ሄዱ። አልበላም በመቀጠል ስል በኩራቴ ተገርመው ለልጅአቸው ሰጡት እሱም በልቶ እንደእማያውቅ አቀላጥፎ በላው። ፍሬዋ ስለሰይጣን ትውስታው እንዲያወራ ትጎተጉተው ጀመረች። እሺ እያለ የጀመረውን ይቀጥል ጀመረ፤ እናትየው ስለዳንኩ የእናትህ ውቃቢ አዳነህ ብለው መርቀው ከመተኛቴ በፊት ሳሙኝ። አጣሁ ወሮታ፣ እነአደፍርስ ቤት የኖረች የቤትሰራተኛ ተከትላአቸው ተገኝታ ወደ ሰይጣን ወሬው እንዲገባ እሷም ጭስያለበት ጓዳዋን ግንብ ተጠግታ ትጠይቀው ጀመረች። እሺ ብሎ፤ እየቀጠለ፤ ተኝቼ ድምጽ ሰማሁ እና ስነቃ ጌቶች ስምአይጠሬን ሊጠሩ ነው ሲባባሉ ጓጉቼ ልመለከት ስነሳ የሆነ ነገር ጎትቶ በደረቴ ወደታች አነጠፈኝ። ስምአይጠሬ መስሎኝ ላየው ፈራሁ። ስጮኽ ሁለት እረኞች አጠገቤ አየሁ። አደፍርስ ሳታየው ጨረስክ እጅግ ሰነፍ ነህ አበቃ ወሬው ‘ሞት እና ህይወት ድንቁርና እና ዕውቀት!’ ብሎ ሁሌ እሚጠቅሳትን አባባል አቀረበ። በላይ ግን ገና መጀመሬ ነው ብሎ ቀጠለ።
እና ማንም እንዳይወጣ ጌቶች ስራ ይዘዋል እና ማንም ወደበረንዳ እንዳይወጣ ብሎን ሌላው ሰውዬአቸው አለፈ። ለልጆቹ ስጠይቅ፣ በሹክሹክታ አባ ድብልብሌ እሚሰኝ የመንደሩ ለጋስ ንጉስ ቁጣውም ትልቅ ነው እኛም ልናይ ልንወጣ ነው ተደብቀን አሉ። ስለእሱ እማ ሰምቼ አውቅአለሁ ማየት እፈልግ አለሁ ብዬ ስነሳ ሌላው እረኛ መጣ እየሰማ ስለነበር ተራ ወሬ ነው ተውአቸው ሲለኝ አተያየተጀ አዘን ስላለልኝ ዝርዝር ጠየቅኩት። ሶስት የስምአይጠሬ አይነት መኖርአቸውን እና የጌቶች አባት እየጠሩ ያናግሩት ስለነበር ሲሞቱ መቀበር እንዳልቻሉ እና ሀጢያት እንደያዘአቸው ገለጠልኝ።
ደፍሬ ብንመለከትአቸውስ ስለው ወጥቶ ቀንበጥ ቀጥፎ አመጣ እና ለእኔም ለእሱም ይዘን በደረት እየተሳብን ወጣን። ጸያፍ፣ አስቂኝ ወይም መጥፎ ቢሰሩ አትሳቅ ብሎ አስጠንቅቆት ሲመለከቱ ሁለት ጥቁር እና አንድ ጠይም በጌታው ፊት አለፉ። ፍግ ላይ ቁስዎችን ቆለሉ። ሰውዬው ስም እየጠሩ ሲያነብቡ፣ ሰዎቹ ቀምበጥ ከመያዝ እና በሀፍረትአቸው ቅጠል ከማስቀመጥአቸው በቀረ ምንም ሳይለብሱ ራቁት በቂጥአቸው አካባቢ ይጨፍሩ አለ። አንዷ ሴት ስትመስል በጥርሷ ፊቷን ሸፋኝ ሙዳ ስጋ ይዛ አለች። ጥቁሩ በአፉ ወንበርቲ እንዲሁ ይዞ አለ። ሶስተኛው ደግሞ፣ በአጓጉል ዳንስ መደነስ በፊቱ የተለያዩ ምልክትዎች በመስራት እሚቆም ነበር። ይህኛው ሰው፣ ወዲያው እየጮኸ ጠጠር እና አፈር እየዘገነ ወደእኛ አግጣጫ ይወረውር ጀመረ። ወዲያው ወደሰውየው ሲቀርቡ፣ እየፈጠኑ ሲያነብቡ፣ እሚያጓራ ምንነቱ እማይታወቅ ድምጥ መጣ። ወዲያው ባለቤቱ ከእነመጽሐፍአቸው ወደቁ፣ ይዘውአቸው ሰዎቹ ገቡ፤ አልተሳካልአቸውም ዛሬ በማለት ነግሮኝ እረኛው ወደመጣንበት ተመለስን። ወሮታ በተለይ እየተመለከተች፣ እሚመስላት የጋብቻ ወሬ ሆኖ ስታደምጥ አደፍርስ ቀጠለ።
እና ገብተን ተኛን ነጋ፣ ስነቃ ባለቤቱ ሽማግሌ ሲያዋሩ ሰማሁ፤ እሚሉአቸው፣ በደንብ ሳይዘጋጁ ሰዓት እንዳያልፍ ደፍረው እንደተንቀሳቀሱ እና እንዳልተሳካልአቸው ነገሩት እና ሰማሁ። ያንን ሲል እነፍሬዋ ወሬውን ትተው ተለዩት፣ እሱም ሲያፈጥጥ ከአጥሩ ውጭ ተራራ እና ጭጋጉ አስፈራራው።

ምእራፍ አስር
ማታ ሁሉ ሲተኛ አስካለ እግሯን ታምማ ስለነበር እያሻሸችላት፣ አጣሁ ወሮታ ቀን የሰማችው የሰይጣን ጨዋታአቸው የጋብቻ ወሬ መስሏት ስለነበር ለአስካለ መናገር ጀመረች። አስካለ፤ ሁሉም ልጆች ናቸው ገና ለጋብቻ ፍሬን አይጠይቁም፤ ሰዓሊው ክብረት ከጠየቀ ደግሞ እሚገርም ነው በማለት ተወያዩ።

ምእራፍ አስራአንድ
ዋና ዳኛ ጥሶ ከቤተሰብዎችአቸው አባላት ጋር እንደሁኔታው ማታማታ እራት ተበልቶ ሲያበቃ ጥላስር ውጭ የማውራት ልማድ አላቸው። ዛሬ፤ ከልጅአቸው ፍሬዋ ጋር ስለኢትዮጵያ መነጋገር የቀጠሉት ስለሀገር ማስተማሩን ሆኖ፤ መልካም ወግ፣ ልማድ እና ቅርስዎች ሀገርአችን እንዳላት እና ስልጣኔ የግድ ከውጭ እንደእማይመጣ መክረው ነግረው እስአቸውም በሀገርአቸው እንደእሚኮሩ አሳውቀዋት እንድታጠና አበረታቷት።

ምእራፍ አስራሁለት
በመንደሩ አምስት ሰው እጅለእጅ ቢያያዝ እማይጨብጠው ሰባ አመት አካባቢ እሚታወቅ ሰፊ ዋርካ ሲኖር ብዙዎቹ አምልኮ መሰል ነገር ይከውኑበት፣ ቅቤ ይቀቡት፣ ጨሌ ጨርቃጨርቅ ያስሩበት ወዘተ. አለ። ከአውራጃው ሹምዎች ሶስቱ፣ ሊያስቆርጡት ሶስቴ የሞከሩትን ሁሉ አሸንፎ ጥሎ አደገኛነቱን አስመስክሮ ያለ ነው፤ እየተባለ እሚወራለት ሲሆን፤ አጠገቡ ደግሞ ልዩ የድንጋይ ካብ አለ። በእዛ ከፍ ብሎ ወደ ደሴ እሚወስደው መንገድ ላይ፣ በመንገዱ እሚንቀሳቀስ ሁሉ በእጁ የገባውን ድንጋይ አንስቶ ሳይክብ አያልፍም፤ በመጪ ጉዞው ከአደጋ ያድነው አለ ይባል አለ። አጠገቡ ደግሞ አቡነ አረግአዊ ቤተክርስትያን አለ።
እሁድ አራት ሰዓት ላይ ከቤተክርስትያን መልስ በአድባሯ ስር የተሰበሰበውን ሰው አባ ዮሐንስ ከአዲስ አበባ የተላኩት ሲሆኑ፣ የትምህርት ቤት ክንፍ ማህበረሰቡ ገንዘብ አዋጥቶ እንዲገነባ የማስተባበሪያ ስብከት ከፃፉት በማንበብ ይከውኑበት አለ። ያኔ፣ ፍሬዋ ዛፏ ስር አንድ እግሯን ድንጋይ ላይ ሌላውን በወራጇ ውሀ ነክራ ተቀምጣ በላይ የፃፈላትን የፍቅር ግጥም በለሆሳስ ታነብብ አለች።
ሰባኪው አባ ዮሐንስ፤ አንድነት ላይ አተኩረው ይሰብኩ አለ። እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እና የሁሉ መነሻ እና አስፈላጊው አላባአዊ መሆኑን ይመክሩ አለ። ሰውን አጀግኖ ብቁ ለማድረግ፣ ለማበረታታት አንድነት አስፈላጊ ነው፤ ፍሬዋ ደግሞ ግጥሟ በአጭሩ፣ ታገስ ልቤ እምትወድድአትን ታገኝ አለህ ይላት አለ። ቄሱ እየቀጠሉ፣ ያልበቁትን ጥራዝነጠቅ ክፍለማህበረሰብዎች ማሻሻያው አብሮ ለመኖር አንድነት ነው ሲሉ፤ ቀጣዩ ስንኝዎች የሰውነት አካልዎቿን ያንቆለጳጵስላት አለ። ስብከቱ ቀጥሎ፤ በችግር እና ሀዘን በእየሁኔታውም ሰውን ሁሉ ከሰው አቻ እሚያደርገው አንድነት ነው ሲሉ፤ ግጥሟን ቀጥላ ፍቅሯ እንዳሳመመው እና መሀረቧን እንኳ ሰጥታው እንዲያስታግስበት ገለጠላት፤ አባ ዮሐንስ ደግሞ አንድነት ከሌለን መኖር እና መግባባት ሁሉ የውሸት ይሆን አለ ብለው ያብራሩ አለ። አንድነት ታጥቶ፣ የውሸት ስንቀራረብ እንደአዞ አጭበርባሪ ያደርገን አለ፤ አኗኗር መሰሪ ይሆን አለ፤ ተራርቀን በውሸት አለም የህልም መንግስት እየመራን ልክአችንን ሳናውቅ ከተፈቀደው በላይ እየገፋን፣ በስሜት እያረጀን እና በሀሳብ ረግረግ እየተጠመድን፣ ሰውን ከሌላው እያራራቀ በመጨረሻ ከክብሩ ዝቅ አድርጎ አጭር ዘመን እሚያኖር ነው። ግጥሟን ስታነብብ፣ ውበቷን አድንቆ ልፈወስብሽ ይላት አለ።
አባ ስብከት ቀጥለው፣ አንድነት ነፃነት፣ ሀገር፣ ስልጣኔ፣ መንግስት፣ ህይወት፣ ወዘተ. ማለት ሲሆን እነእዛ ሁሉም ደግሞ አንድነት ማለት ናቸው፤ ከአለአንድነት ከቶ የቱም አይሰራም እና። ፍሬዋ ስንኞቿን ዳግ-ስትጋበዝ እያንቆለጳጰሣት ነይ አንድ ሆነን እየተባበርን ብርሀን ሆነሽኝ እንኑር ይላት አለ። አባ ዮሐንስ ቀጥለው፣ ነፃነት ዘለአለምአዊ እና ሰማይአዊ ጭምር ነው። እሱን ለአለማጣት አንድነት መጥበቅ አለበት። ነፃነት እንደ ፀሐይ፣ ዉሀ፣ አየር፣ የጋራ ሀብትአችን ነው፣ የውሸት ከአደረግንው ይበላሽ አለ፤ ግን ዘለአለምአዊ ለማድረግ ማድረግ ያለብን፣ ሲሉ ግጥሟን ቀጠለች እና በድንገት እንዳፈቀራት እና ምንም አማራጭ ስለሌለው ሰሎሞን እንዳለው ፍቅር በድንገት ስለእሚፈጠር ተፈጥሮ አለ እና ፍቅር እንገንባ ይላት አለ። ማነሳሳቱ ቀጥሎ፣ ነፃነት በሰማይቤትም ዘላለም እንዲቆይ አንድነትን በሀዘን እና በደስታ፣ በማግኘት እና ማጣት፣ ወዘተ. መከወን ሲቻል ነው። አንድነት እና ነፃነት መንትያ ስለሆኑ አሰራርአቸው አይራራቅም፤ አብሮ እንዲሰሩ ማድረግ አለብን። በልዩ ትርጉሙ ብቻ ነው አንድነት ከነፃነት እሚለያየው፤ እሱም ከበዛ አስቸጋሪ ስለሆነ እንደማር ከበዛ እሚመር ሊሆን እሚችል ነው። ምንአልባት ይህ ልዩ ትርጉሙ እያሳወቀ አያናግር፣ አያሰራ፣ አያበረታታ፣ ደዌውን ተክሎብን ይሆን አለ። ምንአልባት ማን ያውቅ አለ ሲሉ ግጥሟን ፍሬዋ ትቀጥል አለች። ስለተራባት፣ ቢያንስ በዓይን እንዲገናኙ ይለምናት አለ። (ጺዮኔም በአይኖቿ ንባብ ቀጠለች)። አባ ዮሐንስ ቀጥለው፣ ሀገር አንድነት ከሌላት፣ ኑሮዋ ምኑም እማይጥም፣ መልክአምድሯ እማይዋብ፣ ምንቢኖር እና ከኖር እማይደላ ነው ብለው ገለጡ። ግጥሟ ቀጥሎ፣ ፍሬዋ ስታነብብ፣ አንድአፍታ ቤቴ ነይ ልይሽ ልቤ እየተጓዘ ተቸገረ ይላት አለ። አባ ዮሐንስ ቀጥለው፣ የወገን፣ ጎሳ ክፍፍልን በመተው አንድ ስነሆን ድል እናደርግ ይሆን ይሆናል፤ ማን ያውቅአለ መነሻአችን አንድ መሆን እንደሆነስ? ኧረ ማን ያውቅ አለ? እሷም ስታነብብ፣ የእኔ ላድርግሽ ባይ ስንኞቿ ቀጠሉላት። አባ ዮሐንስ አንድነት ኀይል መሆኑን አብራሩ። አንዱ ሲነካ ሌላው ከተከፋ፣ አንድነት አስተባብሮ ጉልበት እሚሰጠን ነገር ነው አሉ። ስለእዚህ በአንድነት ሁሉም ሰው በእራሱ መተማመን ይጀምር አለ። ያንን ሲሉ አህያ እሚነዳ አንቺን ከቶ አልረሳም እያለ እየገጠመ እሚራመድ ነጋዴ የተሰበሰቡበት ደረሰ። ከአህያዎቹ እየታገለ እንዲመለሱ ሲያደርግ አባ ዮሐንስ ቀጠሉ። ከእዛ መንገድ በቀረ፣ ሰው እራስገዳይ ጨካኝ ፍጥረት፣ እየሱስ ቢመለስ እማይተኛ ነው፣ እንዲህ ያለ አውሬነትአችንን ግን ማስወገጃው መንገድ አንድነት ነው። አንድ ሆነን፣ በአንድነት መንገድ ጫፍ ኀይልን እናግኝ ይሉ እና ወረቀትአቸውን ሲጨርሱ፣ የረሱትን ይጀምሩ አለ። የእየብሔረሰቡ እና ሀይማኖቱ ተማሪ ልጅ ሁሉ እሚማሩበትን ትምህርት ቤት ለማስፋፋት መዋጮ እንዲደረግ፣ ብለው ለአቶ ወልዱ ሶስት ብር ሰጡ። አብረው፣ የምስጢር ቤት ቆርቆሮ ስለበሰበሰ አሳድሱ የቻላችሁ እንደእዛው ዞሮዞሮ የእናንተው ነው ሲሉ፤ ሌላው ነጋዴ ካራማራ፣ እና ጅጅጋን እያሞገሰ በመግጠም ይሻገር አለ። ፍሬዋም ወረቀቷን ጨርሳ በወራጁ ውሃ እየከተተች በመጫወት በጣጥቃ ጣለችው።

ምእራፍ አስራሶስት
ማታ እራት በልተው፣ ዋና ዳኛ ጥሶ በበረንዳው ዛፍ ስር ተቀምጠው የምሽት አየር እየተቀበሉ፣ አደፍርስን ያወያዩት አለ። ፍደሳ በጎ እና ጎጂ ጎን እንደአለው አነሱለት። ፍደሳ፣ ቤተሰብ መስርቶ የሞቀ ኑሮ ስለመኖር ልጅዎችን ስለማበልጸግ እና አርሞ ስለማኖር፣ ያስተምረን አለ። ስለሀገር፣ ፖለቲካ እና ማህበረሰብም ጠቃሚ ነገርዎችን ይነግረን አለ። ቤተሰብአዊ አፋዳሽ እና ሀገርአዊ አፋዳሽዎች በጠቅላላው ስለዘርፉ ስኬት ቁልፍ ይነግሩን አለ። አደፍርስ የአጎቱ ነጥብን ተቃወመ፤ አፋዳሹ እራሱ ያንን እኮ አይኖረውም አለ። የሀይማኖት አፋዳሽ ደግሞ ስለእምነት ዝርዝርዎች በእሚገባ መርምሮ ያስተምርህ አለ። በእየሰለጠኑበት ዘርፍ፣ ለምሳሌ ስመገንዘብ፣ ፍቅር፣ ስልጣኔ፣ ትምህርት፣ ወዘተ. ያፋድሱልህ አለ። ወጥ ማፋደሻ ካላወቁ ደጋግመው እሚቀያይሩ አሉ። ግን፣ በተለይ ወጥ ዐዋቂ አፋዳሽ ጠቃሚ ነው። አደፍርስ ዞሮዞሮ ጎበዝም ሆኑ ሰነፍ አፋዳሽዎች እሚሰብኩትን እራስአቸው አይኖሩትም እና አምባገነን፣ የሀገር ሸክም ናቸው ብሎ መለሰ። ታግሰህ አድምጠኝ ብለው፣ እያወቁ ነው እሚያፋድሱት፤ እማያቋርጡበት ምክንያቱም ዘመንአዊ የእሚያሰኝ የኑሮ ግዴታ ሆኖብአቸው ነው፤ አሉት። አደፍርስ ለምን ግዳጅ ሆነብአቸው ብሎ ሲጠይቅ፣ ለእነሱ ፍደሳ የመልካም አነጋገር፣ አቋቋም፣ የዘመንአዊ ማህበረሰብነት መገለጫው ነው። ሰላምታ አሰጣጥ፣ አመጋገብ፣ አረማመድ፣ ወዘተ.አቸው የተመተረ የተጠና ነው። የእነሱ ጎሳ የሆነን እና የአልሆነን መለያአቸውም ይህ ነው። ደጉ ነገር ሁሉንም አያካትቱም እና ሁሉም ሰው በአልተለጎመ የዘመንአዊነት ፍላጎት ይቀቀል ነበር። ግን፣ የሀብታም እና ደረጃ ያለው ሰው በመሆኑ ሌላው ክፍለ ማህበረሰብእ ባህል የተጠበቀ ሆነ። ለሁሉ ልቅ ቢሆን ኖሮ፣ ሁሉም ለመለወጥ ሲሞክር ህግአዊ እና የተገደበ መሆኑ ቀርቶ ልማድ ይሆን ነበር። ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባሉት ሰዎች ዘንድ ሲወሰን ግን፣ ህግአዊ ሆኖ ከስርአቸው ያለውን እያርበደበዱበት እንዲቆዩ ያስችልአቸው አለ። አደፍርስ ለማጥራት፣ በጥቂት ሰዎች ሲከወን ፍደሳ ሊጠቅም ይችል አለ፤ እና ዐውቀው ስለእሚሰሩበት ከእሚያመጣው ጉዳት ይጠነቀቅ አሉ ነው እምትለኝ? ያ ግልጥ አይደል እንዴ! ታዲያ ግን ዐውቀውትም ችግሩን መከላከል ሲያቅትአቸው ስታይስ? ከጊዜ ብዛት ያሉትን ባይጀምሩትስ? የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን ሆነው ብታገኝአቸውስ? የአመኑበት እና ስራአቸው ሰማይና ምድር ያክል ቢራራቁ እና ብታይስ? ብሎ ጠየቀ። ጥሶ መልሰው፣ ማወቅ ያለብህ አፋዳሽ ለአፋዳሽ እሚተዋወቁ ናቸው፣ ከአንገት በላይ እንጂ የምር አይደሉም። ሁለተኛ ደግሞ፣ የእሚኖሩበት ማህበረሰብእ የተለየ ስለእሚሆን ማንም የመመዘን እድል አያገኝም። እርስበእርስ እሚተዋወቁት ደግሞ፣ ትዝብት አይደራረሱም። አደፍርስ እኔ ሲናገር የሰማሁትን አፋዳሽ ተከታትዬ መድረሻ መንገድ ባገኝስ? ብሎ መለሰ። ጥሶ አይጠቅምህም አለው። የከበበህ ማህበረሰብእ ዋሾ እሚልህ ነው። እሚያምን የለም እንደገናም ሰውዬውን መስዬ ልገኝ ብትልም እሚቀበልህ ማህበረሰብ የለም። ግን እውነቱን ሀገር ማወቅ አለበት ሲል፤ የግድ አይሆንም አሉት። አጉል አሰራር አይለውጠንም። ለቢሮ ወይም ኅዋአዊከተማ እሚሆን አሰራር ሳይሆን ስለሀገር ከአወራን ያ እምትለው አደጋ አለው። አንተ በእምትለው መንገድ ሳይሆን ዘዴ ያስፈልግ አለ። ህሊናአችን እማይቀበለው ተጠንቶ ነገሩን በእሱ መመስረት የአስፈልግ አለ። ለምሳሌ፣ ለእኔ አጉል የመሰለኝ የህዝብ መንፈስ ለእራሱ ለህዝበጀ ግን ዋጋ የአለው መሆኑን መርሳት የለብንም። ስለእዚህ ስትነግረው ግር ብሎት ከእማይቀበለው ሀሳብ ይልቅ፣ በእሚገባው መንገድ ንገረው። ለምሳሌ፣ በእምነትህ፣ በእርሻህ፣ በልማድህ፣ ወዘተ. አጉል ስልጣኔ መጣብህ በለው። ያኔ ሆብሎ ይነሳ አለ። ማንኛውም ለውጥ በእዚህ መንገድ ከአልሆነ ሊቋቋሙት አይቻልም።
አደፍርስ ተቆጣ፤ ማለትህ እኮ ኢትዮጵያአዊ ፊትአችን እራሱን የቻለ ነው እንጂ ግልባጭ አይደለም እሚለው ኢላማ ኢላማ አይደለም ነው። በእምነት፣ ጀግንነት፣ እንግዳተቀባይነት፣ በንብረት አክባሪነት፣ እምንታወቀው እኛ የአንዱን እንስሳ ዘር ፊት ከሌላው ተመሳሳይ መለየት እንደእማይችል፣ እንደውሻ ሙርሙር አይደለንም፣ ኢትዮጵያአዊ መልክአችን ለዓለም ይገለጥ ይመርመር ማለት አላማ አይደለም ነው እምትለኝ ሲል ተከራከረ። ጥሶ በእርጋታ ቀጠለለት። እኔ ያን ከቶ አላልኩም። ኢትዮጵያአዊ ፊትአችን አይታወቅ አላልኩም። እኔ እማምነው የኢትዮጵያ ፊት ይገለጥ ሳይሆን እንዲያውም ተመልካች ከተገኘ ተገልጦ አለ ብዬ ነው። ንጉስ ንጉሰነገስት እሚለው ማእረግ ስም በሌላው አለም ከአለው ፕሬዚደንት እና ጠቅላይሚኒስትርነት የበለጠ ግዳጅ እሚጠይቅ ነው። አንድነትአችን እሚገልጽ መልክ መያዝ አለበት። ጠቅላይሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት የመንግስት መሪ ነው። ንጉስ ግን ከእዛ ጊዜአዊነት በላይ ነው። ንጉስአችን ቅርስ፣ ወግ፣ ባህል፣ ምኞት፣ ወዘተ. ማንጸባረቂያ ኢትዮጵያአዊ ጭምር ነው። የንጉሰነገስቱ ግልአዊ ስራ ሁሉ እኔን ይመለከተኝ አለ። የአኔ ጭምር ነው። የጠቅላይምኒስትሩ እና ፕሬዚደንቱ አሠራር ግን ከይፋ ስራው ውጭ የግል እንቅስቃሴአቸው አይመለከተኝም። ንጉሱ በግል እና ይፋ ስራአቸው ሁሉ ኢትዮጵያአዊነቴን ማንፀባረቅ አለብአቸው። አጓጉል ነገር ስለእስአቸው መስማት አልፈልግም። በንጉሴ የመጣን ለማረም እና ለመንቀፍ የመጣውን እማላፈገፍግለት ጠላቴ ነው እማደርገው።
አደፍስ ቀላል ነው ብሎ ዋናው ነገር ንጉስአችን እንዲያብረቀርቁ በፀዳል፣ እኛ በየአለንበት ጥቂትጥቂት ፀዳል እንሁንአቸው ነው እምለው። ከአልሆነ ቅዳሴውን በቀረርቶ መሙላት የአክል ነው። ዋናው ማገዝ መቻልአችን ነው። ጥሶ መልሶ፤ ከአቅም በላይ አትጠየቁ እንጂ፣ እንደተቻለ ብርሃን እንድትሆኑ እማ ታስቦ ነው ትምህርትቤትዎች የታነፁልአችሁ ብለው መለሱለት።
እቤት ወይዘሮ አከላት በገና ይቃኙ ጀምረው አሉ። ጥሶ ወደ ውስጥ ሲገባ አደፍርስም ከኋላ ተከትሎት ገባ።

ምእራፍ አስራአራት
አሰጋሽ እጅግ ሀብታም ነበሩ። በግልአቸው፣ ዶሮ ወይም ማር አምጡ ማለቱ፣ እንጨት ማስለቀሙ፣ ከብት ማስጠበቁ፣ ዉሀ ማስቀዳቱ፣ የማሳረሱ፣ የማስገበሩ፣ የማዘዙ ስልጣን እና በግልአቸው የያዙት መሬት ደግሞ ሲደማመሩ ቀላል ሀብት አይደለም። ሀብታም ሁሉ እሚቀናበት የሀብት ስብስብ ነበር። ባልአቸው ሻለቃ ይነሱ ደግሞ ብዙ አውርሰውአቸው የበለጠ ናጠጡ። ሶስተኛ ደግሞ፣ አባትአቸውም የማያልቅ የእርስት ሀብት አውርሰውአቸው ሞቱ። በተለይ ክረምት በእርሻ እና ዘር ወቅት ላይ፣ ማሳረሱ፣ ማሳረሙ፣ ማሳጨዱ፣ ማስወቃቱ፣ ወዘተ. እጅግ ከባድ ሲሆን አለቃ፣ ሹም፣ መልከኛ፣ ሻለቃ፣ የእኔ ስራ ይሰራልኝ ባይ ሆኖ ጭሰኛው የራሱ ስራ ዞላ እየቀረ ቤቱን ችጋር ወርሶት ይኖር አለ። እራስአቸውን ለአጃቢነት፣ ተከታይነት፣ ግብርናው፣ ወዘተ. ሰጥተው፣ ልጆችአቸውን ለእረኝነት አዋጥተው፣ ሚስትዎችአቸውን ለፈጪነት እና ፈታይነት አስረክበው፣ ይኖር አሉ። በመጨረሻ ኑሮ አሳር ሆኖ፣ ቤተሰብ እስከመበተን ይደርስ አሉ። ወይም ጠቅልለው ለአለቃ፣ ሻለቃ ወይም የበላዩ ያድርአ አሉ።
አሰጋሽ፣ አሁን ለጴጥሮስ ብዙውን እንዲያስተዳድር ሰጥተውት ብዙም ሰው አያስቸግሩም፤ ሰው መንገድ እየለቀቀ ያክብረኝ እሚለው ሃሳብአቸው ነው አልጠፋ የአለው። አሁን ሁለት እረኛዎች አባትዎችአቸው ግብር እስኪከፍሉ እንዲያገለግሉ ተሰጥተው ቤትአቸው አሉ እንጂ ብዙም ሰው አያስቸግሩም።
አሁን ዛሬ የከፍተኛ ፍርድቤቱ ዳኛዎቹ ግብዣ ደርሶ፣ ጴጥሮስ እንደለመደው እየበረታ ግብዣ ድግሱን ጠብእርግፍ እያለ እያሰናዳ ነው። ሰው የአክብረኝ ወይም አስገዳጅ ሲሆን እንጂ ሰው ላክብር አይልም። ውርደት የፈለጉትን ማጣት እንጂ ፍላጎትን ለማግኘት ሲባል እሚደርሰው እርግጫ እና ግልምጫ አይደለም ባይ ነው። በመክሊትአዊነት ላይ የተመሰረተው እምነቱ ዘለቄታ ያለው የመኖር ፈትሕ ሆኖ አግኝቶት አለ።
አሰጋሽ ማልደው ተነስተው ሁለት ታዳጊዎች ፀጉር እና እግር ተካፍለው እያሰማመሩአቸው ነው። ዋናው እልፍኝአቸው፣ በእሚገባ የተዘጋጀ ሆኖ አለ። መብል፣ መጠጥ፣ ጽዳት፣ ዉበት፣ ሁሉም እየተሟላ ነው። ተኩለው፣ ተጊያጊጠው ጴጥሮስን ሁሉን እንደጣሉበት ነግረው፣ እንግሊዝኛ ሲሆን ለውጥ ባይኖረውም ብቻ በፈረንጅ እሚጠራአቸውን ምግብአይነትዎችም ሁሉ እንዲያሰናዳ አሳሠቡት። እሱም፤ በፈረንጅ ቋንቋ ጨረቃ ስለተደረሰ በፈረንጅ ቋንቋ መናገር ማእረግ አለው ግን ጨረቃ በእርግጥ መድረስ አይደለም፤ ቢሆንም በእርሶ ፊት በአማርኛ ቋንቋ እሞካክር አለሁ ብሎ ቃል ገባ። እሱ፤ ትግረ እና ትግሪኛ እንደእሚችል፣ ወንድምአቸው ወልዱ በእናቱ ትግሬ በመሆኑ እስአቸውም ትግሪኛ አውሩ ሲል፣ እናቱ ትግሬ የእሷ ግን አማራ መሆንዋን እና በአባት ወንድም እና እህት እንደሆኑ ገለጡለት። በእናቱ ወጥቶ ባህርማዶ ለባህርማዶ እንደእሚንከራተት ገለጡለት። ማስተናገዱን አደራ ብለው፤ እንግዳዎቹን ለመቀበል እንዲወጣ በእዛው እነ ሮማን እና ጺዮኔን እንዲጠራ አደረጉ። ሲመጡ ሮማንን፤ አደራ ብለው እሚከተለውን አሳሠቡ። አምሮብሽ ለባብሰሽ በርጩማ ይዘሽ ቁሚ፣ አይንሽን ማንቀዥቀዥ እና አስሬ ምራቅ መዋጥ አቁሚ። ጺዮኔም የአለቀውን የወጥ አይነት እያየሽ ፊትፊትአችን ማስቀመጥ የአንቺ ድርሻ ነው። እቃ ማጋጨት፣ እግር ማማታት፣ ሰው ላይ ማንጠባጠብ፣ በሰው ትከሻ ማምጣት፣ አፍ ሳትሸፍኝኛ ሰው ማናገር፣ ከአጎረሱሽ በእጅሽ መቀበል እና ጥቂቱን ብቻ በአፍ መጉረስ እንጂ እንዳለ አለመጉረስ፣ እንዳትረሽ።
ወደ ማፉድ ወደ እሚወስደው እና ወደ አሰጋሽ እሚወጣው መንገድ መጋጠሚያ ላይ ምስ ለመከወን በተስያቱ ሰዎች በቃሬዛ የታመመ ሰው እና ጥቁር በግ ይዘው ደረሱ። በጉን በሽተኛው ዙሪያ ሶስቴ አዙረው አርደውት ደሙን በበሽተኛው ግባር መስቀል ሰርተውበት በጉን ትተውት፣ በፍጥነት መጋጠሚያ መንገዱን ትተውት ሰይጣኑ ይመገባል ብለው በማመን ወደመጡበት ተመለሱ። ሰይጣኑ ሲመገብ ዞረው ከአዩ የአመመው ሰው መዳኑ ቀርቶ ተመልሶ በሽታው ይመጣበት አለ ብለው የአምኑ አለ። እነ ጥሶ እንደደረሱ ሰንጢ አውጥተው የበጉን ጆሮ እያማተቡ ከአዲስ ባርከው እድለኛ ነን በል እድሌን አስተካክለህ አምጣ ብለው ለአሽከርአቸው በማዘዝ፣ ወደ አሰጋሽ ቤት መንገድ ሲታጠፉ ጴጥሮስን አገኙት እና እንደ ደንቡ እጅ ነስቶ ተቀበለአቸው።

ምእራፍ አስራአምስት
የጥሶ አሽከር በጓን አርዶ በልቶ በቆዳው ቋጥሮ ጉዞ ሲጀምር፤ ትንሽ እረኛ ተደብቆ ባህሉ ግራ ስለተጣሰ ግራ አጋብቶት እየተከተለ ወደ አሰጋሽ ቤት ሲቃረብ እሮጦ ቀድሞት ጴጥሮስን ከሞቀ ጨዋታው አስጠራው። እንግዶቹ ገብተው በመመገብ ላይ ሳሉ አደፍርስ ቱግ ብሎ በስሜት እየተንተከተከ አባ አዲስን ሲከራከር መተውም መከራከርም ከብዶአቸው ብቻ ይመልሱለት አለ። ጥንት በህገ ልቦና፣ ቀጥሎ በኦሪት፣ ቀጥሎ በሀዲስ፣ ቀጥሎ በህገመንግስት ኢትዮጵያን አምላክ ትቷት አያውቅም ብለው ሲመልሱ፤ አደፍርስ ጠባቂ አጥታ ታቅ አለች አይደለም፤ እንደ ሀያኛው ክዘ. ግን ድሀ እና ሀብታም እኩል ተምሮ፣ እኩል እየተሾመ፣ እኩል እውቅና የአገኘበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም፤ ኢትዮጵያ እጅዎቿን ዘርግታም ሆነ አጥፋ አታቅም አሁን፤ በእሚገባ እና በእሚታይ መንገድ መስራት የጀመረችበት እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ ሳይሆን ወደፊት መገስገሥ የጀመረችበት ጊዜ ነው ይልአቸው አለ።
በቁጣ ሲናገር፣ መብል እየጨመረችለት ቢሆንም፣ እጅግ ተመስጣ ገሚሱ እየገባት የቀረው እሚለው ግር እያላት ጺዮኔ እየተመለከተችው፣ መሳብ ቀርቶ በስህተት አንዴ ስለአልተመለከታት፣ እጅግ እየተገረመች እና እየተናደደች፣ ቆየች። አባ ተናድደው፤ እጅዎቿን ትዘረጋ አለች እሚለውን ለማንቋሸሽ ነው ሀሳብህ፤ የልጅዎቹን ህብስት ለውሻዎቹ፣ አሁን ንጉሱ የማን ቢባል የማ እንደሆነ እማይታወቅ ሰው ሰብስበው አሳር እሚበሉ አይደል አንዴ? ሲሉት፤ ሰው በአምላክ አምሳል ከተፈጠረ መወዳደር የአለበት በጤነኛነት እና እሚያስብ ጭንቅላቱ ብቻ ነው። ጥበብን ለማግኘት ከየትም መወለድ አያስፈልግም፤ አያንጓልሉ፦ ከፍ ለማለት ዝቅ በሉ፤ ከድንጋይዎች መሀከል መሪ እና ተመሪ መፍጠር ለእግዚእአብሔር ይቻለው አለ የተባለውንም ቢያስጠላዎትም አንድፊት ብቻ ለአለመመልከት ሲሉ ያስቡ። አሰጋሽ፤ በአምላክ አምሳል ተፈጠሩ ተብሎ አሽከርዎቼን ከእኔ እኩል ላድርግ፤ ከሰው መርጦ ለሹመት እና ከእንጨት መርጦ ታቦት ነው፤ ሁሉ አይነት አለው ተብሏል ብለው ተቆጡት። ንስሀ አባቷ አግዘው፤ የቄሳርን ለቄሳር መች ይለን ነበር ሁሉ እኩል ቢሆን፤ ሲሉ፤ አደፍርስ ተቆጣ። ከቄሳር ጸር ሆነ እንዳይሉት እንጂ፤ የቄሳር የአልሆነ በገንዘቡ አይጠቀም ለማለት አይደለም፤ ብሎ መለሰ። አባ ትውልዱ አምላክ ስለፈጠረው የተፀፀተበት እንደነበረው አይነት እሚመስልአቸው ገለጡለት። አደፍርስ የእኔ ትውልድ ይሻል አለ እያሉን ነው ብሎ ጠየቀ። እነ ወልዱ እና ክብረት ለሁለቱም የተሻለ መናገር ሲችሉ ጸጥ ብለው ለጊዜው ያደምጡ አለ። ሁለቱም ተከራካሪዎች ለመደመጥ እነጂ ለመማማር የመጡ አይመስሉም ነበር። ቢያንስ ከእዚህ ትውልድ አናንስም ሲሉ፤ ወልዱ ከእየትውልዱ ዐዋቂም ደንቆሮም አይጠፋም አሉ። አባ ከፍሬአቸው ታውቁብአቸው አላችሁ ተብሎ የለም እንዴ? አሉ። አደፍርስ፤ አብረው የተናቀች ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነች የአለውንም ይጥቀሱ እንጂ ትውልዱ ዘማአዊ ብቻ መሆኑን አያንሱ አለ። አባ ጊዜው ነው፤ ባይሆን ኖሮ መች ‘ይከውኑክሙ ለእቅፍት’ ይባልበት ነበር ብለው መለሱ። ወልዱ፤ ቃልበቃል መተርጎም አደጋ አለው። በቀረእማ ባለፀጋ መንገስተሰማያት ከእሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ የተባለውን ቀጥታ በመውድ የትኛው የመስፍን፣ የንጉስ፣ የተሿሚ፣ የባላባት፣ ወዘተ. ልጅ ነው እሚፀድቀው፤ ሁለጀ ሲዖል ገባ አይደለም እንዴ? ብለው መለሱ። አደፍርስ፤ የእከሌ እማይባሉ የአሏቸው ናቸዋ እሚፀድቁት፤ ብሎ ጣልቃ ገባ።
ከቤቱ ዉጭ የቦረንትቻ ስጋ እመቤትአችን ቤት አይገባም ብለው፤ አሽከሩን በሰሙት ወሬ መሰረት በመከልከል ጭዳ ሊጥልብን መጣ በማለት ትንሽ ደብደብ ሁሉ አድርገውት እየተከራከሩ ነው። እነእሮማን ፍሬዋን ከእሚያስተናግዱበት ከወርዶፋ ጎጆ ወጥተው ሲያስረዳአቸውም፤ ብንቀበለው እቤት ያለንውን እና ከብትዎቹን ሁሉ በበሽታ ይጨርስብን አለ ብሎ ወርዶፋ ተቆጣ። ፍሬዋ ከአልገባ ስጋው ደብረሲና ልመለስ ስትል ሮማን አሰጋሽን ጠሩ እና ሰምተው አዲስ ሙክት ይታረድ እንጂ ቦረንትቻ አያስፈልገንም አሉ። ይግባ እና ፍሬዋ ተለይቼ ልመገበው እና በሽታ ከአመጣብኝ ይዯ ብላ ሞገተች። የሰው ጅኒ አላስገባም ስትል፤ ደብረሲና በመመለስ ዛተች። አባትሽ ይፍቀድ እንጂ እኔ ምንአገባኝ ስትል፣ ብዙዎቹ ወደክርክሩ ወጡ። አሰጋሽ ለአቶ ጥሶ ስታሳስብ፤ ምንአገባኝ፣ እዚህ ልሁን ብትል እንደ ሀገሬው ደንብ ትኑር አላዋጣኝም ብትል ትመለስ ስትል እንዳሻት መረን መልቀቁ ምን ነው? ብላ አሰጋሽ አባቷ ጥሶን ተቆጡ። አባ አዲሴ እምፍሬሆሙ ታእምርዎሙ፣ የዛሬ ልጅ አስቸጋሪ ፈጥኖ ሯጭ ፈጥኖ ጠፊ ነው ብለው መናደድአቸውን ገለጡ። በላይ ወደ ቤቱ ቦረንትቻ እማይገባበት አመክንዮ አይታየኝም፣ ከእሷ ጋር እሄድ አለሁ አለ። ጥሶ አዲስ ነገር የለውም፤ ከሙክት ቦረንትቻ ከበለጠ ምን ይደረግ፤ ዘመኑ ከእኛ እሚለይ የእራሱ አመለካከት አለው ብለው ስለነፃነትአቸው ሞገቱልአቸው። አሰጋሽ በላይን ሁለተኛ ሰበር ሰካ እንዳትል ፊቴ፤ ፍሬዋ ደግሞ አለልማዴ በአንዴ ወድጄሽ ገና በደንብ ሳልጠግብሽ በመሄድሽ አዝኜ አለሁ፤ ቦረንትቻ ስጋ ቤቴ ባገባ ሰራተኛዬ ሁሉ፣ ጴጥሮስም ይሄዱብኝ አለ አሉ። ፍሬዋ አሰጋሽን ስማ ለመጓዝ ሲነሱ አባ እንግዲህ ለእምነት፣ ባህል፣ ወግ፣ መቅናት ግድ ነው፤ አምላክ በአንድ ልጁ እንደ ደረሰልን፣ እኛም መስዋእት ከፍለን መጠበቅ የአለብንን መጠበቅ አለብን፣ እርሶ ባይወዱትም ይጡአቸው ይሂዱ፤ እናንተም ሰላም ድረሱ፤ ብለው ጸሎት እና ምርቃት አድርገው ተጓዦቹ ወጡ። የቀሩት ወደ ግብዣው ተመለሱ። አደፍርስ ወጥቶ ሲመለከት፣ መንገደኛ ሲዘፍን አግኝቶ፣ ቀን እስኪያልፍ እሺ በል ማለቱን ግልጥ ብሎ ለአፉ እንኳ እንቢ በል አይልም ግን ብሎ ጺወኔ ስትመጣ አብዝቶ ሳያያት፣ ብቻ ስለ እምቢኝ አሻፎረኝ እሚለው ሐረግ አነቃቂነት እንደ ሙዚቃ እና ከባድ እንደሆነ ነግሯት፤ የወርዶፋ ኦሮምኛ ግጥም ዝማሬን አድምጠው ተመልሰው ገቡ።

ምእራፍ አስራስድስት
ጺወኔን አደፍርስ ሲያወራ ሳይገባት ስሜቱን በማድነቅ ግን ታደምጠው አለች። ስለ ተጋብተው እሚፋቱ ሰዎች መብዛት፤ የልቡሰጥላአቸውን አቻ ፈልገው አለመጋባት መሆኑን ገልጦ ይገልጥላት አለ። በወረቀት ዘርዝረው እሚወዷትን ልቡሰጥላ አጥንተው ከማግባት በዐይነአዋጅ እያገቡ ስለሆኑ ናቸው። ተጋብተው በመፋታት ከተማ መጥተው ግራ የተጋቡትስ ለምን በዙ? እራሱ መለሰው። ምክንያቱም፤ የወላጅዎችአቸው ምስያ የሆነ ልቡሰጥላን መሰረት አድርገው ተጋብተው ሲኖሩ፤ ከተማ መጥተው ስለእሚያሳድጉት ነው። ለምሳሌ፤ ከከተማ የተመለሱ ጓደኛዎች እና ዘመድዎችአቸው ወይም ሰዎች በእሚያወሩት ወሬ ነሁልለው ልቡሰጥላአቸውን ያፈርሱት አለ። እነእሱም ከተማ ገባወጣ በማለት የተለየ እየተማሩ ይለወጥ አሉ። ድንገተኛ ልቡሠጥላአቸው የቀደመውን ያስለቅቀው አለ። ከቀደመው ጓድ አዲሱ ልቡሠጥላ ይጠላላ አለ። መፍትሄው፤ አዲሱን ልቡሰጥላ ማቋረጥ ነበር። ግን ዘመንአዊ ትምህርት ሳይማሩ፤ ልቡሰጥላ ብቻ ማሳደግ ጎጂ ነው። ስለከተማ የሰሙትን ነገር ጠንቁን ሳይተክል በእርጋታ ብዥብዥ እንዳለ ገና መከልከል የአስፈልግ አለ። የለውጥ ዘመን ላይ ስለሆንን በከተሜነት መጓጓት የለብንም። ቅሬነት እና አጉራ ዘለልነት እንጂ ከተማ በመሰደድ ሌላ አይገኝም። የይድረስ ይድረስ ኑሮ ደግሞ ሰፊ ደስታ አይሰጥም። ከተሜውም ሀገረሰቤውም እንደእየልቡሰጥላአቸው አግብተው መኖሩ ይሻልአቸው አለ። ከተሜዎች እንደእየልቡሰጥላአቸው ሲያገቡ፣ ከእየገጠሩ የተጓዙ ቅሬዎች ስራአጥ ሆነው ወደ ጎሬአቸው ይመለስ አሉ። ሊከተሉአቸው የአሰቡትም እዛወ ገጠር ይቀሯት አሉ። የአለአቸውን ለአለማጣት እንጂ የሌለአቸውን ለማግኘት አይጨነቁም። ወጣት ቆንጆው ሁሉ ከተማ እየፈለሰ በበሽታ መያዙ በዝቶ አለ እኮ፤ አላት።
ቤት ዉስጥ፣ እነ ጥሶ ሲጨዋወቱ፣ ስለ ባለውቃቢ እየነገሩ አሰጋሽ ጨዋታውን አሰፉ። አንድ ህፃን የገደለ ሰውን አውቆበት እንደአስያዘ እና ሰዎች አዋቂ እንድታተርፉ ግደሉ እያሉአቸው እንደእሚገድሉ እና የህፃንዎች ደምን እሚሸጡ መሆኑን ሁሉ ነገሩአቸው።
ውጭ፤ አደፍርስ ጨዋታውን ቀጥሎ፣ ባለሀገሩ ልጅዎቹ ተምረው እሚረከቡ ስለሆኑ የሀገርአችን ተስፋ ነው፤ ስለእዚህ እማይወልድ የአረጀው እየቀረ ወጣቱ መሰደድ የለበትም፤ ወጣቱ ባለበት መቆየት አለበት አላት። ለምሳሌ፤ ሀይማኖቱ፣ ገራገርነቱ፣ ንጉሡን አፍቃሪው፣ ሰላምአዊው፣ ሀገር-ወዳዱ፣ ስነምግባሩ፣ የአለው የገጠር ዉበት ላይ ዘመንአዊነት ብትጨምሪበት፣ ምንኛ በበዛ፣ ምንኛ በተራመደ፤ አያጓጓም ወይ በረዥሙ አስቢው! ሲል፤ ባለማወቅ አፏን ከፍታ ስታደምጠው ቆይታ በመመሰጧም ተገረመች። አጠገብአቸው፣ ሮማን እና ጴጥሮስ እየተወያዩ ሲያልፉ፣ ሮማን እስኪ ጣልያንኛ አስተምረኝ ስትል፣ አሰጋሽ አንቺን ባስተምር አትወድደውም ሲል ሀገርህ አትናፍቅህም ወይ አለችው። የልጅነቴ አስመራን ከመናፈቄ ክንፍ ቢኖረኝ በርሬ እሄድ ነበር አላት።

ምእራፍ አስራሰባት
ጺዮኔ ማምሻውን፣ በረት ሆና ፍዝዝ ብላ ሳለ አደፍርስ መጥቶ አይንዎቿን ከጀርባ በእጁ ሸፈነ። ጨዋታ መስሏት፣ ሮማን፣ ከእዛ ገረድዎቹ ፍቅርተ፣ ማሚቴ ብትልም አደፍርስ ነበር። ወንድ አያጫውትሽም ሲል፤ ከጎርፉ አብሯት ተምሮ በኋላ ዓለሙን ትቶ ከከተው በቀር ወንድ ጋር እንደእማትቀራረብ ነገረችው። አኮርዲዮን አምጥቶ አለመገልገሉ አስገርሟት ስትጠይቅ ገጠሩ በነገረስራው ሁሉ ዉብ ሙዚቃ መሆኑን ሲነግራት ለእሷ ስለተለመደ እንደሰለቻት ስትነግረው፤ ከመልመድ ስሜት ህዋስዎችም ይደነዝዙብን አለ ብሎ አኮርዲዮን በደንብ ሲጫወት ሁሉም ገረድዎች ጭምር መጡ። አሰጋሽ ቢጣሩ፣ እሚሰማ ጠፍቶ ወጥተው ወደ በረት ሲሄዱ ሙዚቃው አስደመመአቸው።
ወዲያው ጺዮኔን ሲጠሩ፣ አባ አዲሴን በሙዚቃው ሲወዛዘወዙ አይተው ተገረሙ። ጺዮኔን ለአቶ ጥሶ ክራር ተጫወች ብለው ለጴጥሮስ ክራሯን አስወርደው አስበጁላት። ሰራተኛዎቹም ተበሳጭተው፣ ጺዮኔም ከክራሯ ጋር ሲገቡ፣ አባ ለአሰጋሽ ከ ቅዱስ ያሬድ በላይ የለም፤ ግእዝ፣ ዕዝል አራራይ ውህደት በላይ ሙዚቃ አለ ማለት ዘበት ነው። በግእዝ አነሳስቶ እና ጀምሮ፣ በዕዝል ደርቦ እና ጨምሮ፣ በአራራይ አሳዝኖ፣ ልብን መስጦ እና አስደስቶ በማራቀቅ በማሳመር ከማቅረብ ወዲያ ሙዚቃ የለም፤ ሲሉ አሰጋሽ እርስዎ ደግሞ ሙዚቃ የሌጊዮን ነው እያሉ ቅድም ግን ሊደንሱ ሲዳዳዎ ታይተው አለ፤ አያያዝዎ የአስፈራ አለ አለችአቸው። መስማትን ሰምትአችሁ ልብ አትሉም፣ ተብሎ አለ፤ እንኳን እኔ የተሰወሩትም ብቁ አይደሉ፤ አሏት። ክራሩን ለመጫወት ቀንቀን በጄ አይለኝም ብትልም ሁሉም አደፍርስን ትቶ ተሠበሰበ። በንጋታው፣ ጥሶ ደብረሲና ተመለሱ።

ምእራፍ አስራስምንት
ሮማን አደፍርስን ስለ አኮርዲዮኑ አድንቃው በገጠሩ እንዲያ እሚጫወት አለመኖሩን ስትነግረው ተደስቶ ጎርፉ አባትሽ ነው ሲላት አንመሳሠልም እንጂ አዎ አለች። የጉንጭሽ አጥንት ይመስል አለ ሲላት ትመሳሳልአልአችሁ ለእሚል ሁሉ በነፃነት ቀርባ እንደእምታወራው በደስታ ተሞልታ ቀረበችው። ጎርፉ ዋሽንቱን እባብዎች ከድንጋይ ወጥተው ነው እሚሰሙት፣ የእርሶን አኮርዲዮ ወድዶት አለ፤ ስትል አቋርጧት ስለእናቷ ጠየቀ። የስልጤ ጉራጌ ቆንጆ እነደነበረች፣ መሞቷን እና እሷን ትመስይ አለሽ ብሎ ጎርፉ አንዳንዴ እቅፍ ከሚያደርገኝ በቀር አላቃትም አለች። ጠይም መሆኔ አያስደስተኝም ስትል፣ ቆንጆ ነሽ አሁንም አላት። ሹሩባ ልሰራ ስትል ባትሰሪም ቆንጆ ነሽ አላት። ቅልጥልጥ የቤት ስሟ እንደሆነ ተወያዩ። እግርዎች ያምር አሉ ሲል ተደስታ ሰዎች ጺዮኔን እንደእሚለክፉ እና እንደእሚተዋት ስትነግረው ልትጋቢ አይደል አላት። አይቼው እማላውቀው ሰው ስለሆነ በትሬንታ እጠፋ አለሁ እንጂ አላገባም አለችው። የባላገር ማደሮ አንገፍግፎኝ አለ እና አስመራ እጠፋ አለሁ ስትል፣ አዲስአበባ አይቀርብም ሲላት፣ አባቴ ሊያገኘኝ ይችል አለ፤ አያዝንም ሲላት እሱም የባላገር ማደሮ አንገፍግፎት አለ መሄጃ አጥተን ነው አለችው። አዲስአበባ ብትሆኝ ፈረንጅ ቤት ገረድም ሆነሽ እንድትገቢ እንረዳዳ ነበር ሲላት ከወሰዱኝ እሰራ አለሁ ምንም ስራ አለች። ጲዮኔ ድንገት መጥታ ሳያዩዋት ያንን ሲባባሉ ማድመጥ ጀመረች። አደፍርስ ወደ ዉኀ ትቷት ሲወርድ ስለሰርጓ ሂደት ሮማን በሰፊው ሰምጣ ትቃዥ አለች። ስለሰርጉ መሰረግ እና ማምለጥ ስታወራ ወዲያው፤ አደፍርስ ከውኀው ሲመለስ በጣቱ ሲነካት ባንና በመፈንጠር ስትጮኽ እየተገረመ አያት፤ ከጎርፉ የተሰቀለች ጎጆ ጺዮኔ ከቤት ደግሞ ክብረት እና አሰጋሽ ወጡ። አሰጋሽ ለክብረት አመም የአደርገው አለ? ስትል እሱ ደግሞ እጅግ ተደስቶ በመጮኽ አናገረአቸው፤ እነዲህ የአለ ሙዚቃ፣ የተፈጥሮ ዉብ ድምጽ፣ ስትጮኽ ሰማችሁት? አለ። አሰጋሽ፤ አአይ፣ የሆነ ድንገተኛ አመመም እማ እሚያደርገው የአደርገው አለ። ከተልከስካሹ፣ ከአይነጥላው፣ ከድንገተኛውም፣ ከሁሉም ቅጠላቅሸል አዘጋጅተን ሳይበዛ በአፍንጫው ቁር እናደርግለት አለን፤ እሚታኘክም እናበጅለት አለ፤ ደያሉ ቅጠላቅጠል ቀነጣጠቡ።

ምእራፍ አስራዘጠኝ
ጺዮኔ ሙዳይ ስትሰፋ ጎርፉ ቤት ጎን ሆና ፍሎቤር ይዞ ሲወጣ አገኘችው። ስትጠይቀው፤ ለአካል እንቅስቃሴ እና ለአደን እንደተነሳ አሳወቃት። መሳሪያው ደግሞ ትምህርት የአላሻሻለው የአውሬነት ባህሪዬ ምን የአክል ውስጤ እንደቀረ ልለካበት ነው ሲላት፣ አውሬ አይደለሁም ስትል፣ በተፈጥሮ ሁልአችንም አውሬ ስለሆንን ደም ለማፍሰስ ወይም ሲፈስስ ለማየት እንሻ አለን ሲላት የዶረለ ደምም ማየት አያጨክነኝ አለች። ድሮ አባትዎች ወንድነት ለማሳየት ወይም መብል ፍለጋ አደን ይከውኑ እንደነበር ገለጠላት። አጎቱ ጋሞ ጎፋ ድረስ ዝሆን ፍለጋ ይሄድ እንደነበር ሲነግራት አንተ ምግብ አላጣህ፣ ወንድነትህም የጥሶ እህት ልጅ እውቅ በእዛ ምሁር ስትለው፣ ለደስታ ነው፣ እንሰሣ ሲገድሉ ደስታው ትልቅ ነው ብሎ ሰበካት። ከሳምንት በላይ ሳቅህ በስቃይ አትደሰትም አለችው። ሞክሪው የሚነገር እና እሚገባ አይደለም አለ። እምለፈልፈው እንዲህ፣ ግድየለሽ ስለሆንኩ ነው፤ ሰዎች ከተማ ውስጥ ግን ራስወዳድ ስለሆንክ ነው ብለው ራስወዳድ ይሉኝ አለ፤ በደንብ ስለእማያውቁኝ። እራስ ወዳድ ሳልሆን፤ እኔ ግን አማራጭ በሌለ ጊዜ ብዙ ሰው ሲወድድሽ አንዱን ለምሳሌ በዳንስ ወቅት ተሰብስበን ለመምረጥ ስትገደጅ ራስወዳድ ስለእሚሉ ነው። ባለፈው አባ ዮሐንስ ብር ለማሰባሰብ ሲሰብኩ የተናገሩት ስላልጣመኝ ለብቻአቸው ከእዛ ደግሞ በምስክር ፊት ተከራከርኩአቸው። እነእሱ እዩኝ በኋላ ደብቁኝ ባይ ናችሁ ብቻ እንጂ እሚረባ አምተናገሩም። እራስ ወዳድ መስዬአቸው እንደሆነ አላቅም፤ ለአንቺም እንዲያ ብመስል ይቅርታ ሲል፤ ከቶ እንዲያ አለመሆኑን ነግራ ለሰጣት መጽሐፍ እና ብዕር አመሰገነች። እንዳመጣልኝ ተቀመ አልተቀየመም ሳልል ሰውን እማናግር ነኝ እና አትቀየሚኝ ሲል እኔ አልቀየምህም እንዲያ አላይህም። እምትመስለኝ ብዙ ሃሳብ ያለህ ልብህ አንድ ቦታ የአላረፈ ተዟዟሪ አይነት ሰው ነው እምትመስለኝ፤ ስትል፤ ብቻ የጊዜው ሰው፣ የአለም ሰው አትበይኝ ብሎ አስምሮ መለሰላት።
ስለ ጎርፉ ከተዋደዱ ቀጥሎ ጠየቃት። ከብዙዎች አብልጦ ይወድደኝ አለ ብዬ በማመን እወድደው አለ፤ ያሳስቀኝ እንደገናም አውሬ ሲሆንም ይማርከኝ አለ። ልቡሰጥላአችሁ ተስማምቷል ታፈቅሪዋለሻ ሲል አዎ አለች። የትምህርትቤት ጓደኛዎቼንም ጭምር ይወድድአቸው አለ፤ ሮማንንም ይወድዳት አለ። እኔን ግን የአበልጥ አለ።
በአለፈው ስናወራ ስለአደል መግደል፣ ጥይት ተኩስ፣ አዳም ከብትዎች ጠረን፣ ወዘተ. አንድሰዓት ሙሉ አወራኝ። እንደ እኅቱ ይይዘኝ አለ። ሮማን እና ሌላዎቹን ቢሆን ያን ያክል አያወራአቸውም ነበር። በሃሳብ ባንግባባም መቀራረቡ ግን አይቀርልንም። በአጭሩ ትወድጅው አለሽ ብሎ ፍሎቤሩን አንግቶ ወጣ።

ምእራፍ ሃያ
አደፍርስ አደን ማሳለማሳ ከውኖ ይስት እንጂ አልተሳካለትም። በመጨረሻ ወደ ስምንት ሰዓት ወደ መንደር ቀረብ ብሎ ቆቅ መግደል መሞክሩን ሲያያዝ፣ ጺዮኔ የተቀቀለ ባርማሽላ ወሰደችለት እና ጠየቀችው፤ እየተኮሰ መሳቱን ቀጠለ። የገበሬ ሚስትዎች ወጥተው ዶሮ በስሙኒ ግዛን መግደል ከአቃተህ በእማይገኝኛ ጥይት አትልፋ አሉት። ሲወተውቱት የመታ የአክል ወደ ቋጥኙ ሄደ። የጸሎተኛዋ ጲዮኔ ገድ ነው። ከደግ ዘር ነች፣ ከአለው ተጠጋ ወእም ተወለድ ነው ሰዎቹ ተባባሉ።
ጲዎኔ ወደቤቷ ተረተር ስትደርስ ትንፋሽ ለመሳብ ብትዞር ይፋት ተንጣልሎ ታያት። የአዳል ጋልዎች፣ ዘላን አዳልዎች፣ የወላስማዎች መዘዋወሪያ የነበረው ይፋት፣ ሰፊነቱ እንደአለ አንድ ሰው እያንጎራጎረ ይንቀሳቀስበት አለ።

ምእራፍ ሃያአንድ
አደፍርስን ጲዮኔ አጊንታ አደን ሳለ ስለመጣችበት ይቅርታ ጠይቃ አኮርዲዮን ተጫወትልኝ ስትል እንቢ አለ። እሺ ክራር ልጫወትልህ ስትል እንቢ አለ። አትችይም ብሎ ተከራከራት። ሌላው ሲቀላምድ ነው ትችይ አለሽ እሚለው ሲላት ሁሉ የሰማኝ ይወድደኝ አለ፣ አንተም ባለፈው ስትሰማ ወድደህ ነው የሄድከው ፊትህን አይቼ አለሁ ብላ ፊቱ ላይ ሌላም እንደአየች ነገረችው። ምን ሲላት፤ ስትደብቀው እንባ አየሁብህ ስለመንግስት፣ ኃይማኖት፣ ቤተክርስትያን፣ ወዘተ. እያወሩ ወንደዎች ሲባሉ ስሜትአቸውን ለመደበቅ እንደእሚታገሉ እና ምን እንደእሚያሳፍርአቸው እማታውቅ መሆኗን ነገረችው። እንባውን ሲክድ አጉል ኩሩ አለችው። አልስማማም አልኮራሁም ሲላት፣ ኩራት ራት ነው፤ ሁሉም ሰው አለው። ለነገሩ አንተ ኩራት የለህም ስትለው ክው ብሎ ተቆጣት። አፌ አምልጦት ነው ከአንተ መቃለድ አይገባም ብላ አዘነች። ማስጨነቂያ ምክንያት ስላልነበረው ስትከፋ አጽናናት። ጎርፉ ቢኖር ይረዳኝ ነበር ምላሴ ይስትብኝ አለ ስትል አፍጥጣ ስታየው አፍጥጦ በመተያየት ቆዩ። የአልሽውን እማያምን የለም ሲል ምንም ብትም እሚያምናት መሆኑን መናገሩ ገርሟት አረጋግጥልኝ አለችው። እሚለው አጣ። ቆይተው ምን ለአጠፋሁት ልክፈልህ ስትለው፤ ምንም ሲል አንተ አኮርዲዮን ተጫወትልኝ አለችው። ድንገት ሰውነቷ ማርከለት ወደቤት ሲገቡ፤ አሰጋሽን ክብረት እየሳላት ነበር።
ሳቅ እና ምንድነው ቤት የአፈርስ አለ ሳልስቅ ሳለኝ አሉት። ተነስተው ሲያዩ ጎጆቤት ስለተመመከቱ፤ ተናድደው እግር አሻሸከአቸውን ልጅ አዲሴን እጀጠባብ ልብስ አልብሰውት፣ ሮማንን ዣንጥላ አስይዘው በመቀመጥ፤ በል አሁን ሳለኝ አሉት።

ምእራፍ ሃያሁለት
ሮማን ኩሬው ጋር እግርዎች ታጥባ፣ እንሰወራ ሞልታ ስትመለስ አባቷ ቤት ጎን በግርምቡድ፣ ጺዮኔ እና አደፍርስ ተቀምጠው አሉ። ስታልፍአቸው፤ ስለ ሮማን ብትማር የተሻለ እመቤት የመሆኗን ነገር ነገራት። ምላሽ አትሰጠውም። አመለካከቷ ሩቅ እሚያይ ጎበዝ እና ልቧ ትልቅነት አስገራሚ መሆኑን አብራርቶ፣ ድሀ ብትሆንም ሙጃሌ እንኳ እማያቃት የአልታመመች መሆኗንም እንደነገረችው ሲነግራትም ጸጥ አለችው። እሷ አድምጣ ሌላ ወሬ ስለ እናቷ ስእል ነገረችው። ደህና ሳልኩት ቢልም፣ እማይረባ እና የአልተወደደ እንደሆነ ገለጠችለት። በውቃቢሽ ከአልተወደደ ወደ ድብኝት ክተችው አልኳት ስትለው ሮማን ዳግመኛ እንስራ ይዛ ስትወጣ፣ እና ስታልፍአቸው እሱን እማ ከአነሳሽ የልቡሰጥላ ነገር ነው፤ እሱን እማ መከተል ነው እያለ ወደ ሮማን ተከትሎ ሄደ።

ምእራፍ ሃያሶስት
ሮማን ስትቀዳ አደፍርስ ተደብቆ በመቅረብ ሲጣራት ደንግጣ ሽክና መቅጃዋን ጣለች። አጠገቡ አህያ ቀድማው ስትራመድ መጣራቱን ቀጥሎ አስደነገጣት። አህያዋ ወደ ዉኀው ስትመጣ የበለጠ ተደናገጠች። ወዲያው እሱም ወጥቶ ቀለደ። አልደነግጥም፤ ይልቅ ጺዮኔ እኩል ቤት ረገጥሽ እሚል ፈሊጥ አምጥታ ማኩረፍ ጀምራ አለች ብላ መለሰችለት። ለመጨዋወት ወደ ቤት ገልብጬ ልመለስ ብላ ተለየችው። ከእራሱ ጋር ሲወያይ፤ አሁን አካልዋን ብነካካት ባቅፋት እሷም እራሷ አታኮርፍም የምሯን ነው? አኩርፋ ገና ሄዳ ትናገር ነበር። ጺዮኔ ምን ትል ይሂን ብትሰማ? የጎርፉን ልጅ እንጂ እሷን በደንብ ሳልቀርብ ቀርቼ ወደእሷ ባለማዘንበሌ ይሄኔ ሃብታም ስለሆንኩ ብላ ትገረም ይሆን አለ እያለ አሰበ። ቀጥሎ አላገባም እንጂ ባገባ ግን ማንን እመርጥ አለሁ? ጺዮኔ ሙዚቃ ወዳጅ ነች እኔም እንዲያው፤ ሮማን ደግሞ ባይወደድም ድምጼን ጭምር ወድዳልኝ አለች። ሲጨዋወት፤ ጴጥሮስ ከጀርባዋ እየተከተለ ተመለሰች። አታኮርፍ ከሆነ ሲጠይቃት አዎን በማለት በመበርታቷ፣ ጡትሽን ብነካውስ ብሎ እየረቻኮለ አላት። አላኮርፍም አለች። ንካ ብላ ገልጣ ነክቶ ፈራ። አደፋፍራ አስነካካችው። እሚተናኮል እንስሣ አለ ወይ ሲላት ጥንድ ስለእምንሆን የለም አለችው። ሰው እረኛ ሲላት አንቀመስም እና አይጠጉንም አለች። ጴጥሮስ ጡቷን ሲነካካው አይቶ በመናደድ ጲዮኔን ጠራት። እሷ ስትሄድ ወደ ጎርፉም ሮጠ። ጲዮኔ ደግሞ አይታ ወዲያው ተመለሰች። ሮማን ዉሃዋን ሞልታ ስመለስ እንጨዋወት አለን ብላ ተለየችው። ስትመለስ ጴጥሮስ እንስራዋን ሰበረባት። በሩጫ ወደ አደፍርስ ስትሮጥ ዉጥንቅጥ ሆኑ ታሰሩ። አሰጋሽ ሮማንን ተቀብላ እያዳፋች ወደ ቤት በማስገባት ምናሳብአለን አፍጥነው እንዲጠሩላት ላከች፤ ድንግልና ከጠፋ ወይም ከአለ እምታውቅ መድሃኒተኛ ነበረች። ቁርዝ አውርደው እየደበደቧት ተናገሪ ይሰማ ማለት ጀመሩ።

ምእራፍ ሃያአራት
ወልዱ አደፍርሰን ከአቧራው ተጣጥቦ ሲጨርስ ገሠፁ። ትባልግ አለህ ብዬ ሳይሆን፤ ሰርጓ እየተደገሰ ከአለ ልጃገረድ መጫወት እንኳ የለብህም፤ የሀገሬውን ባህል ማክበር ነበረብህ። አውሬዎች ናቸው ሲል ያንን ከአወቅህ ምን አናደደህ፤ ለማንኛውም ዳኛህ አሁን ምናሳብአለ ናት አሉት። ጎርፉን በዐድ አምልኮ ትቶ በዋሽንቱ ስራ እንዲያገኝ፣ ለሌላዎቹም ብዙ ቃል ገብቼ ነበር እንዲማሩ እንዲሰለጥኑ ሲል ወልዱ ለእነእሱ እሚበሉት እሚጠጡት እና እሚጨብጡት እንጂ ሌላው ሁሉ ህልም ነው ዴንታ አይሰጡትም። ይግባህ አሉት።

ምእራፍ ሃያአምስት
ወልዱ አደፍርስን እየአጫወቱት፣ እንደ አንተ የአለውን አስተሳሰብ እና አካሄድ እሚይዝ ሰው ተማሪ ሳለን ስንቀልድ ፊልጶስ እንለው ነበር፤ መቼም የማርትሬዛ ገንዘብ ባለቤት የኦስትሪያ መሪዋን እና ልጇን ታሪክ አልተማርኩም አትልም፤ ብለው ነገሩት። ተምሬአለሁ አላስተዋልኩትም ሲል ቀጥለው፤ እናትየዋ ድሀን ድሀ የሾሙትን ሀብታም አድርገው በእማይለወጥ መደብ ያኖሩት ነበር። ህዝቡ በልጅ ልጅ ከድህነቱም ወይም ሀብታምነቱ አይለወጥም ነበር። በአለበት ረግቶ የበላይየበታችን አንቀጥቅጦ እየገዛ ሲኖር እናቱን የወረሰው ፊልጶስ ግን በዕሪና (equality)፣ ነፃነት፣ ወንድምአማችነት መንፈስ ሁሉን አቻ ሊያደርግ መሳፍንቱን ጋበዘ። ሲመጡ አሰረአቸው እና ርስት እና ሀብትአቸውን ለእየበታችዎቸሠአቸው አከፋፈለ። የእናቴ ቅልብዎች እያለ ይጠራአቸው ነበር፤ ክፍያው ግን እኩል ስለአልነበር መለያየት ተፈጠረ። ወዲያው የከፋ ሀብት ልዩነት ድሀውን አላኖር ሲለው አመጸ። መሳፍንቱን ፍታልን አሉት ግን ስለአልተማራችሁ ነው ትምህርትቤትዎችቻ ገንብተን ትለምዱ አልአችሁ ቢል እና መመለስ አይቻልም ሲል አምጸው አስቸገሩ። አንድ ቀን ቤተመንግስቱን በመውረር አጠቁት። አራት መሳፍንት አመለጡ። ከእነእሱ በመተባበር ደግሞ አብረው በመበርታት፤ ተመልሰው ወጉት። አልቻለም። ንጉሱን በማስወጣት፣ በግዞት እና ስደት ቆይቶ ኖሮ እስኪሞት ዳረጉት።
እኛም እዚህ ሀገር እነዲህ ነን። ዕሪና፣ ነፃነት፣ ወዘተ. አይመቸንም። አንደኛ ተበላልጦ ኑሮ እንወድድ አለን። ሁለተኛ ደግሞ ደልዳልነት ነው እሚስማማን። እንደአሻን ለመኖር ደህንነት ይኑር እንጂ ነፃነት እና ዕሪና ምኑም አይደለም። ነፃነት ደልዳልነትን ከነካበት ህዝቡ ምንም ነፃነት አይፈልግም። ሚስት፣ ንብርት፣ ሀይማኖት፣ ጠብቅ እሚለው ደልዳላነት እሳቤውን እሚገልጥለት ነው። ወንድምአማችነትን ደግሞ ከፈረንሳይ መጣ ሳትሉ በነፃነት ሰበብ ደልዳላነቱን ከአልነካችሁበት በእንግዳ ተቀባይነቱ ልማዱ የቆየ ስለሆነ በቀላል ግንጥል ጌጥ ሳይል ተቀብሎ እሚያሟላው ነው። ነፃነቱን ደግሞ የአንተ መሬት እንዲከበር የሌላውን አክብር፣ እንደአሻህ መሬት ገዝተህ አከማችተህ ሌላውን አታስቀይም ያ ማለት ነው ቢሉት እንዲሁ ነፃነትንም ግንጥል ጌጥ ሳይል ይቀበለው አለ። ስለእዚህ የዘመኑ ልጅዎች፣ ነፃነት ወዘተ. በማለት ከሌላ አለም እንደመጣ እንደአልተሰማ እንደአልታየ ነገር ስትሰብኩት መቀበል ቀርቶ እናንተንው እብድ ብሎ መጥቶ እሚወጋ ማህበረሰበእ ቢሆን አይግረምአችሁ ብለው አስተማሩት። ወሰን የሌለው ነፃነት ደግሞ የህልም እሩጫ መሆኑን ልታውቁት ይገባ አለ።
አደፍርስ ሮም ስትሆኑ ከቶ ሳትጠይቁ እነእሱን ምሰሉ፤ ቁንጣን ይዞአችሁ ስትጓዙ ተርቦ ሊሞት የደረሰ ስታዩ እንደተራበ ለመሆን አንድ ጉርሻ ቢያገኝ ንጠቁት እና ጎርስአችሁት ተመሳሠሉ።፤ ባህል ውስጥም እሚመሳሠል ፈልጉ እንጂ እንደወረደ ስልጣኔ አታምጡ ነው አይደል፤ ሲል አዎን፤ እኔም ፈረንሳይ ሄጄ ተምሬ ስመለስ እንደ ችግር ስታይ ስለነበር እማወራህ ችግርህን አውቄ እንደ እራሴን ማዋየት የአክል ነው። ከባድ እንደሆነ ተምሮ መሬቱ አልቀበል ሲልህ እምገነዘበው ነገር ነው አሉት። በእርግጥ፣ ኑሮ (ግብረገብ) የአስተማረው መጽሐፍ ከአስተማረው እሚበልጥ ነው ሲል፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለደልዳላነት (ሚስት፣ እምነት፣ ወግ፣ ዉሎ ገብቶ ማደር) በቂ አለው፤ ዘመንአዊ ነገር ሁሉ አለው፤ ፈረንሳይ በደም መፋሠስ የአገኘችውን መማክርት እንኳ እዚህ በነፃ አግኝተን አለን። አደፍርስ በአጋጣሚው ቀጠለበት፣ እና፣ ደም ስለአልከፈለ ህዝቡ እንደውም ቸላ ብሎ አይመርጥ፣ ተመራጩ ቢቀር ባይሰበሰብ ግድአይለው በግብርይውጣ እሚተወው እና ንጉሡ ብቻ ይኑሩለት እንጂ ግድ እማይለው አይሆንም ነበር። መልሰው፤ የመሐይም ህዝብ መሪ መሆን ችግሩ ይህ ነው፤ እሚፈልገውን አያውቅም፣ ጥቁር ወተት ነጭ ኑግ ይሰጠኝ፣ ፀሐዩ አቃጠለኝ ብሎ በስንፍናው ምትክ ይናገር አለ። ሰንፎ ባለመስራት መሪ እሚያስጨንቅ ህዝብ ነው። አባ አዲሴ ይሄኔ ገብተው ጨዋታውን ስለትውልድዎች ልዩነት መሆኑን ነግረውአቸው ተቀላቀሉአቸው።
ትውልድዎቹ እበዮች ዕልውና ናፋቂ ናቸው ሲሉ፤ ወልዱ ያ ሳይሆን ጨዋታአችን የኢትዮጵያ ህዝብ ከኀልያት ይልቅ በተአምር እሚያምን ነው ነው ስል የነበረው። አባ አዲሴ ተስማምተው፤ ከገነት የወጡት በኀልያት ስራ ነው፤ በኀልያት ፍትሕ አይገኝም፣ መመራመርን አምላክ አይፈልግም ሲሉ፤ ወልዱ ህዝቡን ታዲያ ለምን ገና በተአምር አማኝ ነው እንጂ ኀልያትን እመን ማለት አያስፈልግም እኮ ሲሉ? ገና ለምን አሉ? ወደፊትም አምላክ የመጨረሻ ነው ሲሉ፤ ትተውት ወልዱ ቀጠሉ ሁለተኛ ደግሞ፤ ህዝቡ በ ኦቶሮቴ እንጂ በ ቮሎንቴ ለመተዳደርም ገና ነው ሲሉ አባ አዲሴ አማርኛአችን አልተገጣጠመም ልጄን ላግኝ ሲሉ፤ የለም ህዝቡ በጉልበት ‘በመባህት’ እንጂ እራሱን ገዝቶ በነፃ ፈቃድ መተዳደር አያቅም ነው እምሎት አሉ። አባ አዎን፤ ልጄ አሰጋሽ ጋር ከልጅ እና ሚስትዎችአቸው ጋር የእሚያድሩላት ይኸው ለእራስአቸው መሆን አቅቶአቸው አይደለም እንዴ? ልጅዎች ለተላላኪነት፣ ለእረኛነት፣ ለተከታይነት፣ ወዘተ. ስታውልአቸው፣ እናትዎቹን ለአረም፣ ወፍጮ፣ ፈትል፣ ጉልጓሎ፣ ወዘተ. ወንድዎቹን ለገበሬነት እምታውልአቸው፣ እርስትአቸውን አፍርሰው እሷ ጋር እየመጡ አይደለ? መባህቱን በእሚችለው ሰው ተካትቶ የመተዳደር የአክል ቀላል ነገር የለም። አባ ቀጥለው፣ በእራስ ሲኖሩ ጨው፣ ልብስ ሲሉ በእዚህ ደግሞ መብል ቤት ሲሉ ተችሎ አይኖርም። ሰው ስር መኖር ሃሳብን ሁሉ ጥሎ እሚበጀው ነው አሉ። ወልዱ፤ እንግዲህ የእኛ ህዝብ በግፈራ እንጂ በምናብ ደስታ የመኖርን ደስታ አልደረሰበትም። ‘ሬቫ’ እንጂ ገና በህዝቡ መንፈስ የለም። ‘ራሳዚዬይ’ ብቻ። አባ መልሰው መጀመሪያ የመቀመጫዬን፤ ሰው የበላበትን ነው እሚመስለው ተብሎ አለ። አደፍርስ በእርሶ አተያይ በቃ እማይዋጥ ነገር ሲሳይ አይደለም አለ። ወልዱ፤ እንዳይካረር፣ የአሉት ያን ሳይሆን ለመብሉ ብቻ አይደለም፤ ለነብስ እያለ በመጨነቅ ጭምር ነው እሚኖረው ነው የአሉት። አዎን ሰይጣን በጎበጎ እያስመለከተ ከአለልክ ተስፋ ሰጥቶ እንደተዋረደው እንድትዋረድለት ይሸውድ አለ ያ ነው ሲሉ አደፍርስን መሟገት ወልዱ እየአስተወ አስጨረሰአቸው። ልጄን ሰላም አደርሰሽ ልበል ብለው ወደ ጎተራው ሄዱ።

ምእራፍ ሃያስድስት
ወልዱ እና አደፍርስ ተዋስኦት ሳይጨርሱ አባ ተመልሰው ሲደርሱብአቸው ተገርመው ወደ እልፍኙ አለፉኣቸው። ወልዱ እንዲህ በ ‘ሚስቴር’ እሚያምኑትን በአንዴ ወደ ‘ሬዞን’ መመለስ አይሆንም ነው።
አደፍርስ ቢሆንም በረዥሙ ሊለወጥ ስለ እሚችል፣ እጅ አጣጥፎ ከመቀመጥ፣ መበርታቱ አይሻል ወይ ብሎ አብራራ። ተማሪቤት በእየስፍራው በውድ ድንጋይ ሳይሆን በርካሽ እንጨት እና ጭቃ መገንባት፣ ዘመንአዊ እና የመንፈስ መምህሩን ሁሉ በመቅጠር፣ ሁሉም መጻፍ እና ማንበብ እንዲችል ማስተማር፤ ከእዛ፣ የተሻለውን ኑሮ አኗኗር እሚያስተምሩ መጽሐፍዎች ተርጉሞ አሳትሞ ህዝቡ እንዲያውቅ ማድረግ ማንያውቅ ለ ያኔ ህዝቡ አስተሳሠቡ ይለወጥ ይሆን አለ።
ወልዱ፤ ልጄን እረኛነት እንጂ ተማሪቤት አልልክም፤ አንድ ሳንቲም ለአንድ መጽሐፍ ከማውጣት ወደ አራት ብርሌ ጠጅ እሄድባት አለሁ፣ የጡት ማስጣያ ቋንቋዬ ትግሪኛ፣ ወላይትኛ፣ ጉራጊኛ፣ ወዘተ. ነው አማርኛ የተጻፈን ለልጅዎቼ አልፈልግም የአሉ እንደሆነስ? ሲል አደፈርስ መለሰ፦ ጡትማስጣያ ቋንቋን እንዲተዉ በአንድ ቋንቋ ዉብ ስራዎችን መስራት አስገዳጅ ነው። እነእንግሊኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ መስኮብኛ፣ ተወዳጅ ቋንቋ የሆኑት በተለያዩ ውድውድ ጸሐፊያን ምርጥ ምርጥ እና ሳቢ መጽሐፍዎች ስለተጻፉ ነው። ሼክስፒር፣ ሞልየር፣ ሚልተን፣ ቶልስቶይ፣ አይነት ደራሲዎች ቋንቋዎችአቸውን እንደአስወደዱ፤ እዚህም ብሔርአዊ ቋንቋ ብቻ በማለት ምንም ለውጥ አይመጣም። እርግጥ ቋንቋው እንዲለማ፣ እነ ብላቴንጌታ ኅሩይ፣ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፣ ነጋድረስ አፈወርቅ አለቃ ታዬ፣ ደክመው አለ። ሌላዎችም በእዚህ ዘመን በጥቂቱም ቢሆን እሚሞክሩ አሉ። አሁንም አጓጊ በማድረግ በመጻፍ ብዙ ማስተማር ይቻል አለ። ጡትማስጣያ ቋንቋ የጎሳ ስርአት ነው ያንን የአብላሽብን አለ ብትባልስ ደግሞስ? ብለው ወልዱ ጠየቁት እና መለሰ። በብዛት የልማድ እና አኗኗር ልዩነት የለንም። የቋንቋ ልዩነት እንጂ ለምሳሌ አማርኛ እና ትግሪኛ ቢለያዩም፣ ለምሳሌ ትግሬ እና አማራ ግን በአኗኗር እና እምነት ልዩነት የለአቸውም። ስለእዚህ፤ የተለየ ቋንቋ መማሩ ልዩነት አያስተምርም። ትምህርት በሰልዎች (experts) እንደተነገረው ህፃንልጅ እስከ አምስት አመቱ መልመድ የእሚገባው አንድ ቋንቋ ብቻ ነው፤ በቀረ ጎጂ እና ጭንቅላት ዘገምተኛ አድራጊ ነው። ቀጥሎ ስለ ሀገሩ ህዝብ ቁጥር እና ብሔርዎች የአገኘውን መረጃ ደማምሮ፣ አማርኛ ብዙ ተናጋሪ እንደአለው አረጋግጦ፤ ህዝብ ቁጥሩም እጅግ ጨምሮ ከጣሊያን ወቅት አምስት ሚሊዮንነት አሁን ወደ ሃያሰባት ሚሊዮንዎች መድረሱን እግረመንገድ አሳወቀአቸው። ቀጥሎ፤ ከህዝቡ ስድሳ በመቶ አማርኛ መናገር እና መስማት እሚችል መሆኑን ገልጦ፤ ብዙ ቋንቋ የአለበት ሀገር ስለሆነ እና አርባ እጁን ማንጓለል እንዳይሆን በቋንቋው አስተማሪ እና መጽሐፍዎች ለማዘጋጀት ደግሞ ስነምጣኔአዊ አቅም ስለሌለ መደረግ የአለበት፣ አማርኛን እንደ አንድ ትምህርት እያስተማሩ በጎን ደግሞ አንድ ሶስቱን መርጦ መገልገል ሲል ወልዱ ስለ ብርሌ እና እረኝነቱስ ሲሉት፤ እረኛነቱን መስኖ እያበጁ ከብትዎችን አንድላይ በማቆየት እስከ ስድስተኛ ክፍል ደግሞ በግድ ለማስተማር ደንብ በማውጣት ለብርሌው ደግሞ ከብርሌው ጠጅ የጣፈጠ በመጻፍ እንዲሳቡ ማድረግ እንጂ በእርግጥ ብርሌውን ማስጣሉ ከባድ ነው። ይሄኔ አባ እየፀለዩ አደፍርስን ሊረጩ ከውስጥ ወጥተው ሲጠጉት ሊያመልጥ ሲል ሊያቸችሩት ሆነ፤ እሱንም አምልጦ እየሮጠ ሲያመልጥ ወልዱን አቸቸሩት። ጺዮኔ እየተመለከተች ከነበረችበት፤ ሌጊዮንን አባረሩት እየአለች ሳቅበሳቅ ሆነች። አደፍርስ አልሰማትም።

ምእራፍ ሃያሰባት
ጎርፉን ወይዘሮ አሰጋሽ ቤትአቸው ድረስ አስጠርተውት አለ። ሮማንን ውሃ መቅጃው ድረስ እየሄደ በሳምንት ወይም በሁለት እንደእሚያገኛት እና ተነጋግረው እንደ እሚለያዩ ሰምተው ሮማን ከጋብቻ ቀድማ ጎድፋ ብትገኝ የአሰጋሽ ቤተሰብ ስሙ መበላሸቱ ስለእሚያንገበግባት አባ አዲሴ አጥምቀው ሲሄዱ እንኳ ልብ ሳይሉ፤ ለጎርፉ እሚሉትን አሰብ እያረጉ ተዋጡ። ሴት እና ወንድ ጭር ባለ ስፍራ መሆንአቸው አጓጉል ነው፤ ወዘተ. ልበለው፣ መቼም አላገኛትም ከአለ ጴጥሮስ አይዋሽም እና አንዳንድ እህል ቢሠራርቅ ወይም ከጭሰኛዎቼ ሙስና ቢሰራ እንጂ እሚዋሽ አይደለም አሉ። እና ቅር ቢለውስ? ይበለዋ። እኩል አይደለንም። እነግረው አለሁ፤ ቢቀየም ይቀየም እንጂ አሉ።

ምእራፍ ሃያስምንት
ጎርፉ በፊት ሮማንን ሲያናግር የለበሰውን እንደለበሰ መጥቶ አሰጋሽ ደጅ ላይ ጠብመንጃውን ለጠባቂአቸው ልጅ ሰጥቶ ገባ እና እጅ ነሳ። ከወደቀበት ጫማ ሲስም አንስተው ሳሙት። ጠፋህ አትጎበኘኝ ምነው ብለው ገሠፁት። ሰኔ ሚካል ከአባቱ እና ከእሱ ከተያዩ ወዲህ መራራቅአቸውን ነግረው እሱም ቅርብ ቢሆኑም አለመመቸቱን ሰው እጅ ንሱልኝ እያልኩ ነበር ግን ብሎ ነገረ። ዘመድ ተውኩ በል አሉት። ስለእግርአቸው ሲጠይቅ እየተሻሻለ እየመጣ እንደነበር ገልጠውለት፣ ክታብ በብዙ መልኩ ዘርዝረው በሰውነትአቸው እንደአስገጠገጡ ጭምር ነገሩት። ከአልፈቀደው አምላክ አይሰራም ሲል አዎን ግን ዝክር አላቋረጥኩ ዳስ ጥዬ ቶሎ አይወርድ ሲሉት፣ አዎን ወዳጁን አበዛብዎት ሲል አባቴም ያንን አሉኝ፤ ብለው ኮራ ሲሉ፤ ለመቀየር ጨዋታ፤ ቢልም መልሰው ምነው አትጠይቀኝም ስትመላለስ እዚህ ሲሉት፤ አንዴ ሮማን ሳልፍ አየሁዋት እንጂ አልመጣም ወዲህ አለ። አወራችሁ አደል ሲሉት አዎ አለ። አባቷ ቀጥቶ የአሳደጋት አንድ ልጅ ነች። ለምን ብቻዋን ታዋራለህ ሲሉት አብረን አፈር ፈጭተን ኖርነ እንጂ ወርዶፋም ቢያየኝ ሳላዋራው አላልፍ ሲል ቢሆንም ጋኔል ያሳስት አለ ለብቻ መገናኘቱ ክፉ ነው አሉት። ጋኔል የት አውቄ ሲል አዎ አኮርዲዮን ላይም አድሯል አሁን ቤቴ ገብቶ ሲሉ ክራር እማይፈቅዱ ምንው አኮርዲዮን ሲል የአስተናገድኩት ዳኛ አጎቱ ሆኖ አብሮት ስለመጣ አስራአምስት ቀን ትላንት ስለ አለፈው ነው። ዩንቨርስቴ የገባ አስቸጋሪ ስለሆነ ምን ይደረግ፤ አንድ አባት ልጁን ከዩንቨርስቴ አውጥቶ መግደሉን ሰማሁ፤ ለንጉስ አንታዘዝ ብለዋል ሲባል ደንግጦ ተቆጥቶ ነው የገደለው አሉ፤ ድሀ ዐመል ድሀ ሰው ሰብስበው ንጉሡ ተማረሩ፤ አህያ ማስዋብ የአክል ሆነብአቸው፣ ብለው ተጨዋወቱ። አንዱ አደን አድን አለሁ አንዱ የሀገሬን ስእል አነሳ አለሁ ብለው ነው ተከትለውት ዳኛውን የመጡት። ሰዓሊወን የሚካኤል ምስል ሳል ብለው እሺ እያለ ተረተሩ ስር አጠገቤ የእሚኖሩ መቶ አስር አመት የሆነአቸው ቀጫጫ አጅቤ እሚባሉ ሽማግሌ ዘንድ ሄዶ እየዋለ የአመጣውን ምስል ለአባ ስሠጥ አይተው ደነገጡ። ስናየው፤ የሚካኤል ምስልን ጠየም አድርጎ የአጅቤን አስመስሎት፣ የዳቢሎስን ፊት ቀላ አድርጎ የእኔን አስመስሎት፣ በሚዛኑ እሚገኙትን ነብሳት የእነ ሮማን እና ፍሬዋን አድርጎ ሳለው። አሻሽለው ስንል እንቢ ብሎ ለአዳል ቤተክርስትያን ሰጠው፣ እኛም የአልተማረ የአልቀበጠ እናስል አለን ብለን ተውንው። አንድ ባህትአዊ አሉ ወደእነእርሱ እሄድ እና ሰው እየፈወሱ ነው ነገሩን አጫውት አለሁ። ቶሎ ቢሄዱልኝ በወደድኩት። እማይቆዩትን ልጅዎቹን ወልዱ ነው ፏፏቴ አደን እያለ በእየቦታው በእየእርስቱ እየወሰደ ቶሎ እንዳይሄዱ እሚያደርገው። እስከ ነገወዲያ አሁንም አይቼ ከአልሄዱ ዘመድ ጥየቃ ብዬ ልጅዎቼን አልተውም ይዤ ነው እምጠፋው አሉት።
አብዬ ወልዱ ንግድ ትተው አሉ እንዴ ሲል፤ አሽከር ንግድ እሚያሰሩ እንጂ ከመቆጣጠር ውጭ እራስአቸው አይሰሩም አሉት። ቄደር አስጠምቀውት እንደነበር አባቴ ነግሮኝ አለ፤ ካቶሊክ ከሆነ አላየውም ብለው ሲል፤ ዘጠኝ አመት ሆነው እንግዲህ አንተያይም ሀገርህን አትረግጥም ብዬ የእነሱን ልብስ አስወልቄ አስጠመቅኩት። አዎ፤ እምነት በስንዝር አይለቅቁ እርስዎ፣ ፍቅርአችሁም የተመለሰ አስቀኝ ነው፣ ሳትጣሉ በመሬት መካፈል ሳትተሳሠቡ የአፈራውን በመካፈል ብቻ እምትኖሩ ናችሁ ሲል አዎ፣ ዳሩ አንዳንዴ እንጣላ አለ፣ የባህርማዶ ነገሩ እየመጣ ከወጣትዎቹ እንደ ፈረንጆች እየተነጋገረ፣ ሳገኘው እምቆጣው ነው። ፀበል ከአልክስ ፍልውሃ ፈልቋል ለእሚቆረጣጥመኝ ሲሉት አበረታታአቸው። በል አስጠምቀኝ፣ ከእነእዚህ የዩንቨርስቴ ልጅዎችም ታላቅቀኝ አለህ አሉት። መንገድ እሚመራኝ ሸንቃጣ ሰው ስለሆንክ ሰው የለኝም ሌላ ብዬ ነው የጠራሁህ አስጠምቀኝ እና አገልግለኝ አሉት። ለጉዞ እሰናዳ አለሁ፤ ሀሙስ መጥትህ አድረን አርብ በሌሊት እንጓዝ አለን። ወላጅዎችህን ሰላም በልልኝ አሉት።

ምእራፍ ሃያዘጠኝ
አደፍርስ ጸበል አምልጦ ሲጓዝ በቀደም የተመታበት ቦታ እሚወስደውን መንገድ ሳያስተውል ገብቶ ተራመደበት። ወደ ዉሀው አደረሰው። ጭር የአለውን ባዶ ስፍራ እየተመለከተ አጠና፤ ሲፈጽም ዉሀውን ተመለከተ፣ አይጥ አሳዎችን እያየ ቆየ። አጠገቡ አህያ እንደ ቀደመው ወጣች፣ ወዲያው ዉሃውን በ በጠጠርዎች ሲመታ ሲጫወት የአስራአራት አስራአምስት ኮረዳ መጣች። ዉሀ ቀድታ ሳትመለከተው በቅጡ ተመለሰች። ደግሞ መጫወቱን ቀጠለ። ደግማ መጥታ ስትቀዳ፣ ይሄኔ ሊፈትኑኝ ነው እሚልኳት እያለ ጠጋ ብዬ ብይዛትስ? ትጮኽ ይሆን ወይስ አባቷ በቅር እያረሰ ነው መቼም ሲል ተንጠራርታ ተፍታ ሄደች። ክብረት ከዛፍዎቹ ወጥቶ ተፍታብን ተመለሰች እኮ ጎበዝ አለ። አደፍርስ የአሰበውን ሲፈጽም አይቶ ቢሆን ኖሮ እሚያፍር መሆኑን አስታውሶ ፋደት ፋደት ሸትተናት ይሆን አለ አለው። ትንሽ ሸራውን ዘርግቶ፣ ዛሬ ቀንቶኝ አለ መሰል፣ የኢትዮጵያን ውበት በእዚህ ንድፍ መሰረት ሳልጨርስ አልቀረሁም አሁንስ አለው። አደፍርስ ኢትዮጵያአዊ ውበት የለም፣ ድንበር፣ ቀለም፣ ወዘተ. የለውም አለው። ማንም ደርሶበት ጨብጦት በዘፈንም ሆነ ቅርፃቅርጽ ስለአልተመለከትህ እንጂ እሚያዝ ውበት እንኳ እዚህ አለ ለአገኘው ብቻ ነው ግን አለው። የአማረ ቅርጽ፣ ፈገግታ፣ የዋህነት፣ ጠየም የአለ መልክ፣ ወዘተ. የኢትዮጵያአዊነት ውበት መገለጫዎች አይደሉም። እና ሲለው፤ የኢትዮጵያአዊነት ውበት በእሚንቀሳቀስ የህይወት ውበት ላይ የሰፈፈ ነው። ነብስ ስታልፍ ስታገድም የእሚታይበት ነው። በሸራ፣ በቅርፃቅር እማይያዘው በደንብ ለእዛ ነው።
ክብረት እሚሆንልኝ መልክ ከአገኘሁ፣ የነደፍኩት ብታይ ኢትዮጵያአዊ ውበትን ይይዝልኝ አለ ሲለው፤ አደፍርስ ኢትዮጵያአዊ ውበት የለም ውበት ድንበር አያውቅም አለው። ክብረት፤ ኢትዮጵያአዊ መልክ ከአለ ኢትዮጵያአዊ ውበት አለ፤ አንተን የአጠራጠረህ በቀራፂ፣ ጸሐፊ ወይም ሰዓሊ ገና ስለአልተጨበጠ ነው አለው። በእርግጥ፣ በዝለት፣ በጥንካሬ፣ በእንቅስቃሴ፣ በአቋቋም፣ በመልክ፣ ወዘተ. የእሚገለጥ ግርማሞገስ የአለው ኢትዮጵያአዊ ዘልአለምአዊ ውበት የለም። በቆንጆ ሴት ስእል፣ በነዳፊ እይታዋ፣ የህፃን ፈገግታዋ፣ ውብ ደማም ፊት የአየን ከሆነ ዉብ ኢትዮጵያአዊነት የለም። ዉብ ኢትዮጵያአዊነት እማይጨበጥ ሆኖ በህሊና ብቻ ነው፤ ከሆነ ደግሞ፣ ዉበቱ የለንም እምትለው ራስማታለል ነው አለ። ክብረት፤ ኢትዮጵያአዊ ዉበት የአሰፈፈው፣ እሚንቀሳቀስ ህይወት ላይ ነው፤ ነብስ ስታልፍ ስታገድም፣ ነው እሚያሳየው፤ ለመሳል እና መቅረጽ የአስቸገረው ለእዛ ነው። የእኛ ዉበት ቆራጥነት እና ልበሙሉነት፣ ሲፍለቀለቁ፣ ኅሊና የአልተቀበለአቸውን ረቂቃን ሲዛዛቱ መስሎ ለመኖር የሚደረጉ ቸልተኛነት፣ ቻይነት እና ኀይለ ስሜት ሲዋጉ፣ የተደበቁ ደስታዎች እና ብሶትዎች – ጠቅላላ የሃሳብ ነጸብራቆች – እምቅ ጭምቅ ከእሚለው ልብ እያውገነገኑ ሲወጡ የእሚታይበት መነሳንስት ነው። እንደ ፎቶው ቤት ሁሉ የተመራረጡ የሀበሻዎች ህይወትየለሽ የተሰቀሉ ስእልዎች አይደሉም፤ እነእሱ የኢትዮጵያ ስብእናን አይገልጡም። ስራ እና አሳየኝ አለው።
ሶስተኛ ጊዜ መጥታ ልጅቷ ቀድታ ስትሄድ ልታጠምደን እንዳይሆን አለው። እኔ ስቆይ ብዙ ተመላልሳ ነበር፣ ጠላ እየሞላች ቢሆን ነው አለው። ደግሞ አንተ ምንህ ይጠመድ አለ ሲለው የአገኘኝ ጡጫ ቢገጥምህ ይህን ባላልክ አለው።

ምእራፍ ሠላሳ
ሰኞ ሌሊት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ሲዘንብ ቆይቶ፣ አደፍርስን አንዲት ጥጃ እየተከተለችው ስትወጣ ጺዮኔ አብራ ሳትታይ ተከተለችው። ጸበል በአመለጠበት ማግስት በጤዛው እየተጓዘ ቆይቶ አንዳች ቦታ ላይ አሳብሮ ወደ ጢሻ ሲገባ ተከትላው በመቅረብ አስደነገጠችው፤ ደንግጦ እየተርበተበተ ቀረባት። ርቃ ብቻዋን ስለመጣች፣ ሲቆጣ የኔ ጉዳይ ነው፣ ሮማንን ማየትም አያስደስትህ ብዬ በመገመት ነው አብሬያት የአልመጣሁት፣ ብቻችንን ስንሆን ደስ ይለኝ አለ አላልክም ወይ ደግሞ ስትለው እዛው ቤትቤት ስንሆን ነበር አላት። የወይራ ቀንበጥ ቀጥፋ ወደጫካ እንግባ ስትለው ሰው ካየ፣ ስትጠፋም ከተቆጧት በእሚል ተቆጣት። አትጨናነቅ ብላ እየጎተተችው ብዙ ስላልለበሱ እሚሰጣት አጥቶ፣ ወደጫካ ገቡ። አርብ ጀውሃ እንዲሄድ ጋበዘችው። አርብ እና ቅዳሜ እዛ አብሮአቸው ቆይቶ እሁድ ደብረሲና ለመውጣት ስትለው ደብረሲና በጊዜ (አርቡኑው) ልውጥ አለ፣ እንቢ ብላ አሳመነችው። እንመለስ ሲል፣ ቅጠልዎች አንስታ በመበተን እየተጫወተች እንቢ ስትል፣ በእናቷ ገንጋኝነት (ተጠራጣሪነት) መመለስ ግድ ነው ሲል፣ ጥጃዋን ለቅቄአት ነው፣ ፍለጋ ነው የወጣሁት አስሬአት አለው ውጭ አለች። ስራ ስለእማይፈቅዱልሽ መውጫ ምክንያት የለሽም፣ ግን ታስራ በአሽከርዎቹ ብትገኝስ? ስለ ንጉሡ ለዩንቨርስቲነት ስለሠጡአቸው እንዲነግራት ጠየቀች። ጨዋታ እንቢ ብሎ ሲመለስ እየተጫወተች በእየቅጠሉ፣ ጥጃዋን አገኘ። ተቀምጣ አጫውተኝ ስትል፣ ካፊያ ጀምሮ በሽታ ይይዘን አለ መድኃኒት በሌለበት ሃገር እየአለ እንቢ አለ። ተለይቷት ሄደ።

ምእራፍ ሠላሳአንድ
ለሀሙስ አጥቢያ ሲዘንብ አድሮ፣ በንጋታው ያው ነበር። ብርድብርድ እያለ ጤናአጥ ሆና ረቡ ለት ስለ አደፍርስ ጺዮኔ የተሰማት ግብት ግራ ገብቷት አለ። ለትስብኤ ሀቅረት አላት። ህይወቷ በእማይታወቅ ምያኔ እሚቀር ይመስላት አለ። ሰው እማይሰማው ህሰም የአለባት ይመስል ባርባርታ ይዟት ትረበሽ አለች።
ጎርፉ እንደተቀጠረው፣ መጥቶ አደፍርስን አግኝቶ አብረው ወደ አሰጋሽ ቤት ደረሱ። አሰጋሽ ደምበሾ እህል ሲያስወጡ ስለነበር ጺዮኔ ተቀብላ አስቀመጠችአቸው። አደፍርስ ላጫውትህ እሻ ነበር ስለአገኘሁህ ደስ አለኝ አለ። ጺዮኔ እማገናኝህን ቀድሜ ስትል፣ አንቺ የአለምክንያት ሰው ስለእማትወድጂ ሲል ከወደደችህ በፊትም ኩሩ አሁንም ኮራሃ አለው። ስለመዋደድ አደፍርስ አይነትዎቹን አንስቶ፣ ሲዘረዝር ለጊዜው የፍትወት መዋደድ አለ፤ በተፈጥሮ እና በመዋደድ እሚመሰረት አለ ልክ እንስሳ የራሱን ዘር እንደእሚወድደው፤ እንዲሁም አብሮ ከመላመድ እእሚመጣ መዋደድ አለ ልክ ድመት እና ዉሻ እንደ እሚላመዱ እና እሚዋደዱት፤ ከትንሽነት ወደ ትልቅነት የአሳደጉትን ነገር ሁሉ የመውደድ አይነትም አለ፣ የአሳደጉትን ሲነኩበት እሚወድድ ማን አለ?
አደፍርስን የእኔ እና ጎርፉ መዋደድስ የቱ ነው? ስትለው ልቡሰጥላአችሁ ይወስነው አለ፤ አንተንም እወድድህ አለሁ ስትለው፤ ያ እንደ ድመት እና ውሻ ነው እሚሆነው መቼም አላት። አይመስለኝም ብላ ወደ ቀደመ ምያኔዋ ስትሰርግ ጎርፉን አደፍርስ የሀገርቤት ጨዋታ አምጣ አለው። እንቢ ሲል ጺዮኔ ተረትተረት ጀመረች። ስስታም ጅብ ከልጅዎቹ ጋር አህያ አድለ ለብቻው በልቶ ጠግቦ የአህያ ባለቤቱ ሲመጣ ማምለጥ አቅቶት ሲሞት ነገረችአቸው። አደፍርስ ተነስቶ እጇን ነካ። ምን ተሰማህ ስትለው እኔ እንጃ አላት።

ምእራፍ ሠላሳሁለት
ጎርፉ ተነሳስቶ፣ እኔም ተረት ልንገር ብሎ አስፈቅዶ ቀጠለ። አስራሶስት ጅብዎች አንድ አንበሳ ጋር ጓደኛ ሆነው ሲኖሩ ለአደን አንድ ቀን አረው ወጥተው ተበታትነው ሳለ አስራሶስቱም ጅብዎች አንዳንድ ወይፈን ቀንቶአቸው መጡ። አንበሳውን አፈራ አንድ ጅብ፣ ለአንበሳው አንድ ቀንሰን እንስጠው ብሎ አንድ ብቻ ወስደው አስራሁለቱን ለአንበሳው ሰጡ እና ሲመለሱ እንጀራአባትአቸውን አጊንተው ነገሩን አጫወቱት። ተናደደ። እያቅራራ፣ እየፎከረ፣ አንዱን እንመልስ የቀሩትን እንቀበል ብሎ ሄደ። ሲደርስ ግን አንበሳው አስደነገጠው። ተጨንቆ፣ ይቺን ለምን ወሰዱ ብዬ በልጆቼ ተቆጥቼ ነው እንኩ ይቺንም ብሎ የቀረችውን ታዳኝ አስክቦ ባዶእጅ ተመለሱ።
ስለእንሳሰት ደግሞ አጫውቱኝ አለ አደፍርስ። ጠቃሚ (በግ፣ በሬ፣ ሶረኔ፣ ዶሮ፣ አህያ…)፣ መርዘኛ (ጊንጥ፣ እባብ፣ ዘንዶ…)፣ እማይጠቅም (እንሽላሊት፣ ገበሎ፣ እንቁራሪት፣ ቢራቢሮ…)፣ እሚጎዱ (ቀበሮ፣ ወማይ፣ ጎሴ፣ ነጎዴ፣ ግልገል-አንሳ፣…) ናቸው። በተማሪቤት ደግሞ፣ በብዙ መንገድ ከፋፍለው የአስተምሩ ነበር። አንዱ ደንደስ የአለው ደንደስ የሌለው ብለው ይከፍሉልን አለ። ያ ሰነፍ አጠናን ነው፣ ምን ይረባን አለ? ለአደን ወይም ለአመራረት አይረባንም አለ።
ቀጥለው፤ ጎርፉ የተማረ አያስቀናኝም የአሳዝነኝ አለ አለው። ለምን ሲል፤ የተማረ በእግር አይራመድ፣ ዶማ ቢይዝ እጁ እሚላጥ፣ ንጉሡ የበከሮ ስራ በቃኝ አርስአችሁ ብሉ ቢሉ ገጠር ቢገባ ሙያሌ፣ ቁንጫ፣ እንቅፋት፣ አትችሉ…አለ። አደፍርስ፣ መጫሚያ፣ መኪና፣ ትራክተር፣ መድኃኒት፣ ለተውሳኩም መግደያ መድኃኒት፣ አይጠፋም ሲል፤ ጎርፉ መድኃኒት ሰውን አላድን እየአለን ባለፈው ታምማ የሄደች አልተኛ ብላን መድኃኒት አላስተኛ አላት፣ እነተባይዎችም መድኃኒት ይሸትትአቸው እና አይበሉ የበሉትም አይሞቱ ለምደው፣ ማረሻመኪናም ለመልክአምድሩ ከቶ አይሆንም፣ አሉ። ለትንሹ ነገር ብዙ መስራት እምትወድዱ፤ ጭራሽ ተኩስም አትችሉ፣ ታሳዝኑ እማ እናንተ የተማራችሁት አላችሁ እንጂ፤ አንድ የተማረ ቆቅ ለመግደል ጥይት አባከነ ብዙ ሲሉ ሚካኤል ስወርድ ሰማሁ፣ ግን የቆለኛ የአልተማረ ተኳሽ አንዲት ቀለሃ አያባክንም፤ ሲለው፤ አደፍርስ እሱ እንደሆነ ስለአወቀ አፍሮ ተኩስ እንወዳደራ አለው። እሺ ሲል፤ ፍሎቤሩን አውጥቶ ቅል ገትረው ሁለት ሁለት ሲተኩሱ አደፍርስ ጨረፍ አደረገ። ጥይትህ አትመችም አለው ጎርፉ እና የእራሱን አስመጣ፣ ቀለሃ ውድ ነው እዚህ እየአለ አንድ ቀለሃ ሰጠው። የተመታ ቀለሃ በዝናሩ ለመሙላት የአክል ከትቶ ስለነበር ሲከሽፍ ጎርፉ ደነገጠ። የአልተተኮሰበት ታገኛለህ ሞካክር ብሎት ቀጠለ። በሶስተኛው አጊንቶ ሳተ። ጎርፉ ቀጥሎ ከአንድአንድ አገኘ እና መታው። አደፍርስ ለማንኛው የተማረ እማይችል አታድርግ አለው። ወደ እልፍኝ ተመለሱ።

ምእራፍ ሠላሳሶስት
ሲመለሱ ምንም የተማረ ሰው የተለየ እሚከውነው እንደሌለ ጎርፉ ገለጠ። በትንሹ በአለው እየተደሰተ በጎጆ ኖሮ ድሮ መደሰት ለእኛ በቂ ነው አለ። እሱም፣ መጎብኘትስ ሲል እማያቁት አይናፍቅ አሉት። ልብስም በትንሹ ቁምጣ እምረካ፣ ወንድ ከሆንኩ ከእምማር ሰርቼ ሳበላ እምረካ ነኝ በቃ ሲል፤ ወልዱ እና ክብረት አሰጋሽ ደምበሾ የተበላሸ ከአልተበላሸው አስለያይተው ሲመለሱ አጠገብአቸው ደርሰው ክብረት የሚካኤል ቤተክርስትያን ስለታየው እዛው በእርሳስ ብቻ ስሎት የሰጠአቸውን አሰጋሽ ይዘው በጥርጣሬ ቢሆኑም እራሱ ክብረትን ለማናገር እስመዋለሁ አልጋዬ አናት አድርጌ እያሉ ገቡ። ጎርፉን ሲያዩ ተደፍቶ እግር ስሞ ተቀበለአቸው። አደፍርስ ይሄ መሳም ላይ፣ የተገኘውን ነገር ሁሉ አጥብቆ መሳሙን መች ነው እምናስተካክለው አለ፤ ነገር ሊያመጣ ብለው አሰጋሽ ሰጉ። እግር፣ ቤተክርስትያን፣ ወዘተ. መሳሳሙ ባክቴሪያ ያመጣ አለ ሲሉ፤ ባህል አይቀርም ቅር ቢሉት አሉት። እኔ እግር ታጥቤ ከአልተሳመ አልታጠብኩም ነው እምለው።
ወልዱ ትርኪምርኪውን ተዉ ብለው አስቋርጠው ቁምነገር ይወራ አሉ። ነገ ከሄድሽ ባዶቤት እኛ ምን እንስራ? እኔም ትምህርትቤቱን ለማስገንባት መዋጮ በእሚል እሁድ ስብሰባ አለኝ፤ አሉ። አደፍርስ ከእነጺዮኔ እኔም አለሁ ሲል እኛ ለጠበል ለሁለት ቀንዎች ዘመድ የሌለበት ተቸግረን ከአለማረፊያ ነው እምንሄደው ሲሉት አሰጋሽ ጎርፉ እንዳንበዛ እኔ ልቅራ በቃ አለ፤ ብትተካ ኖሮ መች አለፋሁህ ቀርን አሉት። ጺዮኔም እኔም ልቅር ማረፊያ ከሌለ ጤነኛ ነኝ ፍልውሃ አልሄድም አለች።
ፍልውሃ ከአለማ፣ ከደብረሲና ከሰው ጋር መጎብኘት ነው እንጂ አለ ክብረት፤ ወልዱ ሊያስጎበኙ ቃል ገቡ። ሁሉም ሲወጡ ጺዮኔ ልትከተል ስትል ድርቆሽ አብጂ አኮርዲዮ አያቅብጥሽ አሏት።

ምእራፍ ሠላሳአራት
ጎርፉ እኔ እግር ባልስም አታስፈልግም ተባልኩ ሲል ወደ መኝታ ወደ ወርዶፋ ገጆ እየሄዱ ወቀሰ፤ ወልዱ አባባልአቸው ሰው የአስቀይም አያስቀይም ስለእማይሉ እንጂ አንተ አታቀውም እሚያውቀው ሰው ይሻለኛል ለማለት ነው አሉት። እየተጨዋወቱ፣ ሰው ልብቡ መሆን አለበት፤ አስቀይም ይሆን ወይ ማለትእማ አለበት ክርክሩ ሁሉ በእየፍርድቤቱ ቸልተኛ በመሆን ጭምር ነው ሲሉት፣ ወልዱ አዎ የእኛ ዘመን ችኮ ይባል ነበር። ተከራክረን ብንሸነፍ ልብ ቢያቀውም አጉራ አጠናኝ አንላትም ነበር። አሁን ግን የእናንተ የተማረውም ትውልድ እየታማ ነው አሉት። የትምህርት ተጽዕኖ ነዋ ሲል፤ አይደለም ኦብሲቲኔት ናቹህ፤ ሂፖክራትዎች፣ ፍደሳ እና መድልው የበዛበት ትምህርት ነው የእምትወስዱት አሉት። እና ዘመንአዊነት ማሳያ ነው ሲል፤ አይ የ ‘ፊኔስ’ነት ምልክት ነው ፈረንሳይዎች እንደእሚሉት አሉት። አደፍርስ የተማረ ብዙ አለም የተመለከተ ገጠር ምን ይሰራ አለ ብሎ ጠየቀ።
ነበርኩ፤ የታወቅሁ ብዙ የአየሁ ሰው። በፓሪው ወልዱ ነበር ቅጽል ስሜ። እንደእኔ ደናሽ፣ ለባሽ እና ታዋቂ አልነበረም። ብዙ አደረግሁ። በ1919 ጃንሆይ ራስ ሳሉ ከመኳንንትዎችአቸው ጋር አንዴ ፈረንሳይ መጥተው ነበር። እዛ ተቀብለንአቸው በሽርጉድ ሳለ፤ ሲመለሱ አንዱ ቅርብ ሰውአቸው ከመንዘላዘል ለሀገር ወገን ሁን ብሎ አስቸገረኝ። በስብከቱ ተረታሁ። እሱ ችሎኝ ተመለስኩ። ነጋድራስ አድርገው የሀገሬ ልጆች ተከተሉኝ ከአሉት ጋራ ከመጣው ሁሉ ሰው እንደ አንዱ ስልጣን ተሰጠኝ። ሀገርቤት ደርሼ ልመለስ ስል ወዲያው ተፈቅዶልኝ በቅሎ ውሰድ ተባልኩ። ስንዞር ያየኋትን በቅሎ ስጠኝ ስለው ከት ብሎ ሳቀ። የጌቶች ናት ብሎ ድሃ በህልሙ ቅቤ ሲለኝ ተናደድሁ። ወዲያው ብዙ ሳልቆይ የገንዘብን ዋጋ አይቼ አልጨፍር አላባክን ከአልሁ አገኘዋለሁ ብዬ ፈረንሳይ ተመለስኩ። በስዊዝ ካናል ስድስት ጊዜ ተመላልሼ አለሁ። በመጨረሻ መጣሁ። አዲስአበባ ደግሞ ሰለቸኝ። የሰው ባሪያ ከመሆን ለእራሴ ባሪያ የእራሴ ጌታ መሆን ፍልስፍና ለኑሮዬ አድርጌ በግሌ እሰራ ጀመርሁ። እዚህ ደብረሲና መነገዱ በቀዝቃዛ ንጹህ አየር፣ በአልተጨናነቀ ከተማ ይሻል አለ ብዬ መረጥሁ እንጂ ስኳር እንደ አየ ጉንዳን አዲስአበባ አዲስአበባ እያሉ መሰብሰቡ አይመቸኝም። ሁሌ ጌታ ባለወሆን አጋር እኩያዎቼ ጋር ግን እሰራ አለሁ። በረዥሙ አጫውተው አሉት። ነገ በሌሊት እንውጣ ሲል፤ አንቸኩል፣ እስኪ ሌሊት ከሄደችእማ እህቴን እንሰናበት ብለው ወጡ።

ምእራፍ ሠላሳአምስት
አደፍርስ፣ እና ፍሬዋ የእሁድ ረፋድ ላይ የአባ ዮሐንስ ሁለተኛ ገቢማሰባሰቢያ ፍለጋ ሲሰበስቡ፤ ከፍሬዋ ጋር ቀደም ብሎ ከፊትከፊት ወደ መሰብሰቢያዋ ዛፍ እየአመራ ይከራከር አለ። ከሁሉም ስታወራ እኮ አይቼህ አለሁ። አይበቃም ስትለው የተለያዩ ናቸው ክርክርዎቼ አለ፤ አንደኛ በፊትም ወደፊትም ይመጣሉ እሚባሉትን መሪ እና ጻድቃን አልቀበልም ሲል ተቆጥታ እኔ ሳልማር ታሪክአችን በጻድቅዎች እና ታሪከኛዎች እንደተሞላ አውቅ አለሁ። አልቀበልም በል ብትፈልግ አለችው። እነ አቶ ጥሶ፣ ወልዱ እና አከላት እየቀረቡ ተቀላቀሉአቸው። ወለ ኢትዮጵያ ጻድቅዎች ሲናገሩ፣ ሁሉም አሳመኑት። ብዙ ጻድቅዎችን ከክርስትና ሰጡ። አብረው ከእስልምና የታወቁትን አቀረቡ። ታዲያ ከግብጽ እና ከአውሮፓ በመጡ ጻድቅዎች እናምን አለ ሲል ጠየቀ። ድንበር በእምነት የለም ብለው ሌላ መከራከሪያዎችንም እየሰጡት ቆዩ። በመጨረሻ፤ ስለቃልኪዳንአቸው ስለቅዱሳኑ ሲናገሩ መጨረሻ ቅድስት እማሙዝ የተሰኙት ያዘመመ ቤተክርስትያንአቸው እስከአለም ፍጻሜ እንደእሚቆይ ነገሩት፤ ኒሊንግ ታወር ኦፍ ፖዛ አለና ሲል፤ ኒልታውፒዛ አሎጣኝም ብለው አባ ዮሐንስ በማብራራት ጨረሱ።

ምእራፍ ሠላሳስድስት
በዛፏ ስር ሲሠባሰቡ፣ በመጨረሻ፣ ፍሬዋ እንደልማዷ አንድ እግር በውሃ ነክራ አንዱን ውጭ አድርጋ ውሃን ፍዝዝ ብላ እየተመለከተች ቆየች። ወልዱ ከጎኗ ሆኖ በሃሳብ ሲወሰድ አባ ዮሐንስ ስብከቱን ተያያዙ።
ዱር እየመነጠሩ፣ አውሬ እያባርሩ እሚኖሩበት የድካም ዘመን ድሮ ቀረ። ሰው ልኩ ቆላ እና ደገኛ ተብሎ እሚታወቅበተወ ዘመንም ቀረ። ትምህረወት በእሚሉት መልእክተኛ ተጭኖ ሀገርአችን ገባ ስልጣኔ።
የረዘመውን የእሚያሳጥር የአጠረውን የእሚያስረዝም ምትሃት ትምህርት የእሚሉት ትምህርት ተስፋፋ በሃገርአችን — ሻካራውን ለስላሳ ጉጣጉጡን መዘዞ፣ ወልጋዳውን ሰተቶ ጠማማውን መለሎ የእሚያደርገው ትምህርት። ልማት እና ስፋት ውበት እና ጽዳት የእያንዳንዱ ኢትዮጵያአዊ አላማ ሆኖ አለ ሲሉ አህያ ነጂው ነጋዴ ዛሬም ሱማሌን ዞረሽዞረሽ ምንገኘሽ እያለ እየገጠመ ከአህያው ጋር ወቅ አለ። አውሎነፋስ መጥቶ ልብሱን ሲመነትፍ፣ እነፍሬዋንም ነክቶ በላይ ጭን ላይ ጣላት እሱም አናቱ መታት። ተስተካክለው፣ ጭኑ ላይ ስታፈጥጥ እኔ እስከአስራሁለት ተምሬ ሲል ፍሬዋ ኮሌጅ ባትቀጥል እደኔ ብትወድቅ ኖሮ ዲግሪ ታገኝ ነበር አለችለት። አባ ቀጥለው በእየቀበሌው እንደ ሰርዶ ተማሪቤት ተተክሎ አለ የፈለገውን መስዋእትነት ባንከፍልለት አደጋ ነው አለ። ሁሉም የአቅሙን ሲያዋጣ፤ ነጋዴውም ያዢኝ እንደ አመሌ እያለ ነጎደ።

ምእራፍ ሠላሳሰባት
ወልዱ፣ አደፍርስ እና አቶ ጥሶ ከስብሰባው በኋላ ስልጣኔ ከሀገርውስጥ ከአልጀመረ ይጎዳ አለ ተባብለው ክርክር ቀጠሉ። አቶ ጥሶን ለመቋቋም አደፍርስ እየፈለገ ሳለ ወልዱ፤ ንብ እና ወባ እኩል አበባ ቀስመው ንብ ማር ወባ መርዝ አበጅተው ይቀርቡን አለ ሲል፣ አደፍርስ፤ ስልጣኔ እንደ ተቀበለው እሚወሰን ነው፣ ማርም መርዝም መስራት ይቻል አለ። የለም፤ እኛ ጋር የተቀበልንው የውጭ ስልጣኔ መርዝ ነው የአስሰራን፣ ማር አይበዛም በሰራንው ሲል እንመዝነዋ አለ አደፍርስ።
እኛ ሀገር የገባው ስልጣኔ ሀብት ወይም ማእረግ እሚያስጨምር፣ ድህነት የአጨራመተውን አስተምሮ አስፈትኖ ወደ፣ ስራ መቀጠር እሚያደርስ፣ ወደ ምእራብዎች ባህል እሚያስገባ በር ከፋች፣ በብዙውን ክፍሉ ስለእማይተገበር የቅዠት አኗኗር በቀለም እሚያስተምር፣ ልዩመቀመጫው ከተማ የሆነ፤ ምእራብአዊ ስልጣኔ በመባል ብቻ ተወዳጅ ወይም ተፈሪ የሆነ ማለት ነው አለ። በእርግጥ የገጠሩ ደጅ ስላልደረሰ ይህ ደግ ነው፤ ገና የመምረጥ አቅም የለውም፣ ያንን እስኪያገኝ ይዘግይለት፤ አስር እጅ ከተሜ ህዝቡም ገና ብዙ ይፈልግ አለ ሲሉ፣ አቶ ጥሶ ድሮ ሀገር ተከላክሎ የአቆየልን ቆራጥነት እና እምነት ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ከዘመንአዊው ስብእና መዋጥ እሚያድነን ተቆርቋሪው እና ደንቆሮነትአችን ነው አሉ።
አቶ ወልዱ አብዝተንው ብንይዘውም ብዙ አይገባንም የምእራብ ስልጣኔ ሲጀመርም፤ አሉ። በደፈናው ጎዳን ነው እምትሉት፤ እጅግ ጠቅሞን አለ፣ መጓጓዣው፣ መድሃኒቱ፣ ሰራዊት ድርጀታው፣ እውቀቱ፣ ወዘተ. ሲል፣ ሳይገባን አልቀረንም አሉት። እምንለው፣ ለማኝ እንኳ ተዘጋጅቶ አቁፋዳ ይዞ እንዲወጣ እኛም ቀድመን የአለንን እንመልከት፣ የጎደለንን ብቻ እንለምን ነው አሉት። በመዘውር እሚሄድ ስብእና ነው የአለን ያኔያኔ በእርግጥ፣ ከውጭ ሀገር የእሚኖሩት የእኛ ሰዎች ቤተሰብ የተቃወሰብአቸው ወይም ከአንድ አሳዳጊ የአልኖሩ ናቸው። ሲሉ፣ አዎ ደግሞ ጉዳትም አለ፤ እምነት እና ወላጅ መዳፈር፣ ብቸኛነት እና መገለልን ማብዛት፣ እንደእስስት መለዋወጥ እና ቋመከ ስብእና ማጣት፣ ቀለም እንጂ ስብእና እማያስተምሩ መምህርዎች መብዛት እና ክፍተቱን ማሳየትአችሁ፣ የማይጠቅመውን ከድሮው በእሚጠቅም ተክቶ መጨረስ የአቃተአችሁ ናችሁ ይባል አለ አሉት አቶ ጥሶ። እርሶስ ሲልከ እኔ በመቻቻል አማኝ ነኝ። ብትማሩ እንድትጮኹ እና ወደስራ ስትገቡ ለስራ የአልሆነውን ለመተው ስለእምትገደዱ መማርአችሁ አይከፋኝም። ለምሳሌ ጓደኞቼ መሀከል እኩልነት፣ ነፃነት እንዳላሉ ስንማር ሲመረቁ ስልጣን ሲያገኙ ፀጥ ነው የአሉን አሉተደ።
አቶ ጥሶ፣ ምን ቢሞቅአችሁ ለአስር እጁ እንጂ ለዘጠናው እጅ እንደማትሆኑትም እወቁ አሉት። አልዋጥም በትንሹ እጅ፣ ተምሬም ስወጣ አልበገርም እሚል ሲመጣስ አለ አደፍርስ? ደህና አሉት።
እየተነሱ አቶ ጥሶ፣ ማደጉ መልካም ነው። መለወጡም እንደአየንው እየረዳን የአለው ጎን አለው። በስብእና እና መከባበር፣ በባህል እና ወግ እምናጣውም አለ። ግን እንድንድን፣ የእኛ ሃሳብ ከምእራብ ስልጣኔ መላቅ ይገባው አለ። ምንም ኒውክለር፣ ኅዋ ምጥቀት፣ ወዘተ. እና እኩልነት ከአደጉት ብናገኝ፣ እራስአችንን ግን በመሰዋት አካሄድ፣ አለባበስ በመቀየር መሆን የለበትም።

ምእራፍ ሠላሳስምንት
ሮቢት ወርደው አሰጋሽ ሲጠመቁ ሰንብተው ቀለል ቢልምአቸውም ጨርሶ አልዳነም። ከቆዩ ግን እንደእሚድኑ እርግጠኛ ነበሩ። ግን ሙቀቱ አልተቻለአቸውም። ተመልሰው ጧትም ገብተው አሽከርዎቹ የበሰለ እንዲሰጡ ሢጠይቁ ገና እየበሰለ ነው አሉአቸው። መብረር መብረር አሰኝቶኝ አለ እየአሉ ሙቀቱንም አማረሩት።

ምእራፍ ሠላሳዘጠኝ
ጎርፉ እና ጺዮኔ ሮቢት ወርደው የተለያዩ ፍራፍሬዎች ተክልዎቹን ተመለከቱ እና ጎበኙ። ሎሚ ለመቅጠፍ ስትታገል የተሻለችዋን ቀጥፎ ሰጣት። ወስዳ፣ እየተራመዱ አብረኸኝ ስቶን ከደፍርስ የአነሰ ነው እማምንህ አለችው። ይቅርታ ስላላመጣሁት ብቀር ቢመጣ ደስ ባለኝ ከመጣን ዝምታ። አበዛሽ አጫውችኝ አላት። አላምንህም እንደ እሱ እሱ ጨዋታ አዋቂ እና ተወዳጅ ነው አለችው። እሱም፣ እንደ እሚወድደው ነገራት።
እየተራመዱ አላምንህም አንተ ጋር አንድክፍል ብንሆን፤ አደፍርስን ግን አምነው አለ አለችው። አልቀይምሽም እኔም አንቺ ጋር አንድ ክፍል አልሆንም ብሎ ተራመዱ። ቆየት ብላ አይክፋህ፤ አብሮ አደጌን አምንህ አለሁ፤ ቀልዴን ነው አለችው። ጥቀከት ሲጓዙ ቆይተው ደፍሮ ጎርፉ፤ እንጋባ አላት። አፍጥጣ በድንጋጤ እየፈጠነች ተመለሰች። እሱም ብሶት ይዞት፣ አዳልዎች ሲታጠቡ ተመልክቶ በወንዙ ዙሪያ ሆነው በመተቸት እየመረመረ ተመለከተአቸው።

ምእራፍ አርባ
ጺዮኔ ጎርፉን የአሰጋሽ ልብስን እንዲያጥብ ስትነግረው ለመጠመቅ በሄዱበት እያወለቀችላት፤ ከፍቶት ከእራሱ ይሟገት ጀመረ። እሚለው፤ የከተሜ ተረት ወዳድ አታለላት፣ እኔ እያለሁላት ደህና ሰው፣ ቆይ አንድ የተሻለ የጀግና ስራዬን ባልሰራ እና ባልወስዳት አለ።
በኋላ ሲጠመቁም፣ እሚላት፣ ሳያስበው እንደተናገረ እና እንደገረመው ነበር። ተወው ግድየለም ስትለው አልሰማ እያለ ይደጋግምላት ነበር። ሲወጡም እየተከተለ ደግሞ እውነት ቢሆን እሺ እየአለ ይደጋግምላት አለ።

ምእራፍ አርባአንድ
ከኋላዋ እየተከተለ መደጋገሙን ቀጠለ። እውነቴን ቢሆንስ እሺ ሲላት እየተበሳጨች፤ በቃ እሳልሃለሁ እሺ አለች። ቀንበጥ ስትጥል እያነሳ እያስተዛዘነ ሲከታተላት ስትራመድ ከስርስሯ በመለቃቀሜ ነው ብሎ ተናደደ። ወዲያው፣ መሄዴ ነው ቤት ብላ ወደሌላ መንገድ ገባች። እንባ ሊፈነቅል ከአንጀቷ ይታገል ነበር።

ምእራፍ አርባሁለት
በሳተችው መንገድ ስትገባ እና በችኮላ ስትረማመድ፣ እየተከተለ ስተሻል አላት። ጸጥ ብላ ስታመልጠው ደረሰባት። እየተነጫነጨች ተጨቃጨቁ። ለምን ታናድደኝ አለህ ስትል፣ አላናደድኩሽም፣ ዉሸቴን ነው እየተባባሉ ተከራክረው ጎጆአቸው ሲደርሱ፣ እሷ ተለይታው ስትቀመጥ አሰጋሽ ሰምተዋት እየወጡ የምን ዉሸት ዉሸት ነው፣ እውነትአችሁም ዉሸት ነው ዉሸት ዉሸት በሉ እና ቀርቶ፣ ብለው ጎርፉን ጥሪው አሏት።

ምእራፍ አርባሶስት
በማግስቱ ማታ ጎርፉ ልብስ ለማጠብ ጀውሃት ወምበርቲውን ብቻ ታጥቆ እንደወጣ ጠፋ። አሰጋሽ ደንግጠው ቀኝአዝማች ልጄን ቢለኝ ምን ልል ነው አምጥቼ የሰው ልጅ ብለው ተጨነቁ። የሃምሳአለቃ ተጠርቶ ተነገረው። የቤቱ አከራይ ውረድ እየው ሲባል ልብሱ በደንብ ሳይታጠብ ተሰቅሎ እንደአገኙት ገለጡ። ምልክት አለመገኘቱም አሳሠበአቸው። አዳል ወስዳው እንዳይሆን ሲሉ፤ በቃ ለማንኛውም ጎርፉን አውቀስ አለሁ ነጭለባሽ ተደርጎ ሳለ አውቀው አለሁ። ጠፋ ብል እማይነሳ ሽፍታ የለም ብለው አረጋጉ።

ምእራፍ አርባአራት
ከእራት መልስ አቶ ጥሶ አደፍርስ ጋር ጠለላው ስር ተቀምጠው እየተከራከሩ ይቀመጥ አሉ። የድሮ እና የአሁን ሙግት ይለያይ አለ ሲሉት አይስማማም። የድሮውም የዘመኑም አንድ ነው ገና አልተሻሻለም የተበላሸ ነው ሲል እስአቸው በዳኛነት የአሉበት ከበፊቱ ስርአት ተሻሽሎ አለ በማለት አይደግፉትም። ለምሳሌ ነገ እሚሰቀለው ገዳይ በሽተኛ እንጂ ወንጀለኛ አይደለም አላቸው። ስለ ጊደር መጥፋት በ በላልበልሃ ግጥም አንድ የድሮ ሙግት አሰሙት። አደፍርስ ታዲያ ውብ ነው እኮ ሲል፤ ውብ እውነት የአስገኝ አለ ማለት አይደለም አሉት። የኢትዮጵያ ህዝብ እሚፈልገው እውነትን ነው፤ ከአልሆነ እርስት፣ እምነት እና ንብረቱን ዋጋ አይሰጠውም አሉት። እውነትን ከአጣ ይህ ሁሉ አይረባኝም ባይ ህዝብ ነው። እውነትን የአጣ እና የአገኛት ጊዜ ግን የበደለውን ወዲያው ገድሎ ቢሆን እንኳ እራሱን የአረሰርስ አለ እንጂ ገደልህ ቢባል እና ወዲያው ቢያዝ አይጨንቀውም፤ ትክክለኛ ፍትህ የአለውን በህይወቱም ገዝቶ በአመለካከቱ መሰረት ይጸድቅ አለ እንጂ ትቶት ገሃነመእሳት እሚገባ መስሎት አይኖርም።
የበደለን በመግደል እውነት አይገኝም፤ ውሸት ዘለአለምአዊ ትሆን አለች እንጂ አለ አደፍርስ። በህይወት ባለመቆየቱ ውሸት ትኖር አለች አብራው አትሞትም አለ። እውነት በሰውየው አእምሮ ነው በአነወጓለለው ህሊና የአለው? አለ አደፍርስ። ጥሶ በሁለቱም ቢሆንስ ሲለው እንዲያማ ግድያውን በእሱ መበየን ወንጀል ነው፤ ውሸት ከእውነት ለይቶ እማያውቅ ህፃን ነው። በሽተኛ ነው። አትግደሉት እንጂ ብትገድሉት ጥፋቱ በገዳይዎቹ ነው አለ። የአካባቢውን እውነት ነዋ እምታስተምረው አለ ጥሶ፤ አዎ ሲለው ዘለአለምአዊ እውነት የለም ማለትህ ነው ሲለው፤ በሳይንስ ይኖር ይሆን አለ በህብረተሰብእ አኗኗር ግን የለም። አኗኗር የመሰረተው እውነት ነው የአለው አለው። በቦታዎች እውነት ይለያይ አላ ሲለው አዎን አለ። እና ብትገድለው እውነትን አልገደልክም ጊዜአዊ ችግር ቀነስህ፣ እውነትንም ለህብረተሰቡ አስተምረህ ማቋቋም ትችል አለህ አሉት አቶ ጥሶ። እውነትን እምንሰራው እና ተከተሉት እምንለው በብዛት መጠኑ እኛው ነን። ስለእዚህ ስትገድለው የእኔን እውነት ካድህ ብለህው ነው። ሀሳቤን አዘበራረቅህው እባክህ በቃ የድሮ ሙግት ንገረኝ እና እናቁም አለው። አንድ በላልበልሃ ተናግሮ፣ እንደ ዘመኑ በማስተዳደር በመያዝ መጎበዝ እንጂ ሌላ አማራጭ የለም አለው።

ምእራፍ አርባአምስት
ሰኞ እና ሀሙስ መንዝ እና ይፋት እሚገናኝበት ገበያ ላይ ሰው ከተፈረደበት እሚሰቀልበት ጭምር ነው። አሁንም ዳኛዎቹ፣ ወልዱ፣ አደፍርስ፣ ፍሬዋ…ሁሉም ተሰብስበው ሰባት ሰዓት ሲል ጀምሮ የተዘጋጀውን መታነቂያ ይመለከት አሉ። ገበያው መሀከል ሌላውም ለመመልከት ሲመጣ አንዳንዱ ሳይጨነቅ ሲገበያይ፣ ሰባት ተኩል ሆነ። ዘቡ ገዳዩን አስሮ መጣ። ገዳዩ አስቸግሮ ዘቡን ገፈተረው። ኃይለስላሴ ይሙት፣ ብለቀቅ እገድለው ነበር እየአለ ዛተ። እብድ ሴትም ስለጀግንነት እየፎከረች ገበያውን ታራውጥ ነበር። እኛው ስንሞት ከአልተነሳን እኛ በድን ነን እየአለች አትስነፉ በእሚል ጭብጥ እና ጀብድ ስታቅራራ ስትፎክር፣ ገዳዩ ተይዞ ድጋሚ አጓጉሉን ታስሮ ወደ መሰቀያው ቀርቦ ወንጀሉ እና ፍርዱ ተነበቡ። ገዳዩ ማቅራራት ጀመረ እሱም እንደ እብዷ። እያቅራራ ገዳይነቱን በእየገደለበት ስፍራው እየገለጠ፤ ሲፎካክር በመጨረሻ እዚህም ገዳይ ብሎ ዘቡን በእግረጀ ረግጦ ክፉኛ ጣለው። የወደቀው ዘብ መነቃነቅ አልቻለም፤ ገዳዩ እራሱን አንገቱን በገመዱ ከትቶ የወጣበትን ጥሎ ሰቀለው። ዘቡም ንቅንቅ ሳይል እንደወደቀ ቀረ። እብዷም፤ ተነሱ ተነሱ እሚል አንሸነፍ እንዋጋ እሚል ፉከራዋን አውልቀው ሱሪህን ምን የአደርግልህ አለ፤ በሴትዎች መሀከል አንቀው ይገድሉህ አለ፤ እየአለችም ቀጠለች።

ምእራፍ አርባስድስት
አቶ ጥሶ የብዙሰው ጥፋት የአንድ ሰው ቅጣት ይሆን አለ ብለው ከባልደረባዎችአቸው እና ወልዱ ጋር እየተወያዩ ከገበያው ወደ ፍርድቤት መመለስ ጀመሩ። አቶ ጥሶ ተናድደው አያገባኝም ባይ ያናድደኝ አለ። ትነሽ ስህተት እንኳ የተመለከተ ከአልተሟገተ ያ ትክክል አይደለም አሉ። አንዱ ሌላ ዳኛ፣ ጭራሽ ንግዱን እንጂ ሰው ተገፍትሮ ሲወድቅ እንኳ ምንም የአስጨነቀው አልነበረም። ሰውየውን ጥሎ ሲገድለው ትንሽ ተሰበሰበ እንጂ ህዝቡ ከመጤፍም አልቆጠረን ብለው ተናገሩ። አዎ፤ እነዲህ የአለው ነገር እንኳ፣ ምንም አይመስለው፣ ተስፋ አይሰጠው አያስቆርጠው፣ አያስደስት አያሳዝነውከ አይበርደው አይሞቀው የሆነ ህዝብ ነው። እኛ ስራአችን ሆኖ እንኳ ብዙ ቅሬታ አሳድሮብን የአውቅ አለ አሉ። ወልዱ እንዲያማ ከሆነ አበቃ፣ ሰው መግደሉ እንኳ ለማስተማር ነበር፣ እሚማር የለም እኮ፤ ሰላሳ ሚሊዮን እማንሞላ ህዝብ አንድ ሰው ብንገድል ብዙ እያጣን እኮ ነው። እና ዛሬ ህዝቡ ምን ተማረ ይላሉ ብለው ሲጠይቁ፣ እኔ የሰማሁት፣ ሞተ አይባልም ሰርግ ነው፤ የወንድ ወንድ ነው፤ መውለድ ይህንን አይነቱ ነው…ሲሉ ነው አሉ። ያ ማለት ሁሉም ገዳዩን መሰል ወንድ ፈላጊ እና ወዳጅ ነው፤ ሴቷም እንደ እዛው እነዲህ የአለውን መውለድ ወእም መዛመድ መፈለጓን ነው የተማርኩት አሉ። የአየሁት እንባ እንኳ የኩራት እና የደስታ እንጂ የሀዘን ወይም የመማር አይደለም። እና፤ የመገረፍ የመስቀሉ ነገር እሚያስተምረው ምን እንደሆነ እንጃ፤ የብሔርአዊ ስሜቱን ነው ደግሜ የአየሁት አሉ። ከሆነ እንደ ውጭ ሀገርዎች መግረፍ መስቀሉ ቀርቶ ይታሰሯ ሲባል አይሆንም አሁንም የእኛ ሀገር ወንጀል ከፍተኛ እና እስርቤቱ ሁሉ የተጨናነቀ ነው ተባለ።
ጨምረውም፤ የአምላክ ሀገር ስለሆነ በእየእምነቱ ሰው ፈሪሀ-እግዚእአብሔር ስለአለው፣ በርትተን ማስተማር፣ የጠንቋይዎች በእየገጠሩ እሚያታልሉትን ቀጭ ሸንጎ በሽማግሌዎች ማዘጋጀት፣ ከተቻለ ወንጅልን በብዛት መቀነስ እሚቻል ይሆን አለ። በውጭ ሀገር የአለው አኗኗር፣ ወንጀልን በብዙ መንገድ የአሥከውን አለ እኛ ጥቂት ከበረታን እንሻሻል አለን ተባባሉ።

ምእራፍ አርባሰባት
ፍሬዋ እና አደፍርስ ገበያ ሲዟዟሩ ቆይተው፣ ወደ ወልዱ ቤት ጎራ ብለው ስለ ተገደለው ሰው ሲጨዋወቱ፣ የባለቤቲቱን ወሮ. ማለፊያን ጨሌ ተመልክቶ እሚያመልኩበት እንደሁ ሲጠይቅ አዎን ሰው እንደ አባዜ ልምዱ አይደል አሉት። እርሶን ያህል በላይን የአክል የተማረ ሰው የአደረሱ ትልቅ ሰው ግን ያንን ቢተዉስ ብሎ መለሰ። ከቅድመ አያቴ ወደ አያቴ ከእሷ፣ ወደእናቴ ከእዛ ወደ እኔ የመጣች ናት፤ አልተዋትም ይቺን ጨሌ፣ እኔን ቤተሰቤን ንብረት እንስሳዬን ጠባቂ ደግ ናት ብታይ አሉት። ፈርተው እንደሆነ ሲል፤ አይደለም አልፈራም እናቴን እንቢ ብል አያቅተኝም ነበር አሉት። ፍሬዋ አንተ እምነት የአለህ ይመስል ስትለው አለኝ ብሏት ዶቃውን ልጣልሎት ሲል እሞት አለሁ አለችው። ዶቃ ስለተጣለ አይሞቱ እኔም ምንም አሎን ሲል፣ ቅርስ ሀብቴ ነው ተራ ዶቃ አይደለም አለችው። በጎን ፍሬዋ እራስክን አታታልል፣ እምነት የለህም አንተ ስትለው አለኝ እሚገርመው የተማረ ወልዱ እናት በዶቃነማምለክአቸው ነው ሲል እኔ እሚገርመኝ ከእሷ ይልቅ የአንተ እምነት አለኝ ባይነት ነው አለች። አንቺ ቦረንትቻ አልበላሽም፣ እኔንም አይገድለኝም ሲል እኔ በፍቅር እና ክብር አስፈቅጄ እምነትአቸውን ሳልነካ ወጣሑ በላሁ። አንተ በግድየለሽነት ከማክበር ውጭ ወስጄ ልጣል አልክ አክብርአቸው አለችው። ስለ አምልኮቷ አቅልሎ እንዲያይ ነግራው ለውጥ ከውጭ በቀጥታ ከእሚመጣ ቀጥታ፣ ወግ፣ ክብር፣ ፍቅር፣ መግባባት ቀድሞ የአስፈልገን አለ፤ አታንጓልል፣ ቀድመህ ረጋ ብለህ ተለወጥ እንጂ አለችው። አቶ ጥሶ ገደልማሚቶ አበጁ። የራስሽ ሀሳብ አብጂ ሲል እርጎ እንዲጠጡ አስተናጋጇ አሰናድተው እማወርሳት የልጅ ሚስት በአገኘሁ ወድቆ ዶቃዬ ባልቀረ እያሉ እርጎውን ስትሰጥአቸው አደፍርስ እንዳልበላ የአደርገኝ ነው ብሎ ምሳ ሲጠብቁኝ አሉ ብሎ ተሰናብቶ ወጣ።

ምእራፍ አርባስምንት
በማለዳ ተነስተው ወንዝ በመውረድ ጎርፉን መፈለግ ጀመሩ፤ አሰጋሽ፣ ሮማን እና ጺዮኔ። እረፋዱ ድረስ ምንም የለም። በመጨረሻ፣ ፀሐይ ሲበረታ አንቺ ተመለሽ እኔ ልፈልግ ሲባባሉ ሲነጋገሩ ቆዩ እና ሮማን እና ጺዮኔ ሊፈልጉ ቁርጥማት እንዳያምማት አሰጋሽ ደግሞ ሊመለሱ ወሰኑ። ሁለቱ እየፈላለጉ ቆይተው ፀሐዩ አናት ሲወቐ ከብዶአቸው ወደ ጥላ ለእረፍት ገቡ። ከራቀ ከመንደሩ ጩኸት ሲሰሙ ተሯሩጠው መንገዱን ይዘው ወጡ። ጺዮኔ ቀድማ ስለነበር ሮማን ሳታይ ሁለት ጎረምሳዎች ጺዮኔን በቡልኮ ከመንገዱ መሀከል እሩጫውን አስጥለው ጠቅልለው በጀርባ በመያዝ ሁለቴ ተኩሰው ወደሰማዩ ይሮጡ ጀመሩ። ሮማን ስትደርስ እየጮኸች ተከተለች። ማንም አይመጣም። በመጮኽ ኡኡታውን ስታቀልጥ ስትሮጥ ሰው ሳይደርስ መንደር ገብታ የሆነውን አሰማች። አሰጋሽ መጀመሪያ የጮኽኩት እኔም ስገባ ዝናር እና መሳሪያውን ጎርፉ ከአስቀመጠበት ሳጣ ነበር አለች።
መንደሩ እነእሱን በማሳደድ ተኩሱ ቀለጠ። እየተታኮሱ ርቀው ጭራሜዳ ላይ ተደረሰብአቸው። እዚያ ጺወኔ ፈዝዛ ስትገኝ ጎርፉ ከጓደኛዎቹ ጋር የገቡበት ጠፋ። አጠገቡ የተሰረቀ ታቦትን ሌላው ቄስ ሊያስጥል ሲፋለም ሌላኣኣ ገበያተኛ የማንንም ታቦት ማንም አይነካ ብለው በጨርቅ ተሸክመው ሳይታዩ ወደ ቤተክርስቲያን ወረዱ። ሰርቆ አዲስአበባ ሊገባ የነበረው ቄስ ከሌላው መረማረም ግን ቀጠሉ።

ምእራፍ አርባዘጠኝ
አሰጋሽ ጎርፉን ስለእሚያውቅ ሃምሳ አለቃውን ገሰጹት። ምንም ግንኙነት የለኝ እሱ ጀግና ሆኖ ነው የአመለጠ ጎበዝ ነው እኮ ብሎ ተከራከረ። በመጨረሻ ተጠንቀቅ ለአቶ ጥሶ ነግሬ አብረህ እንዳትታሰር አሉት። ሁለት ብር ለጠላት ሰጡት እና ተደሰተ። ሁለተኛ ፍልውሀ ብዬ ብመጣ አሉ።

ምእራፍ ሀምሳ
አደፍርስ እና አቶ ጥሶ እየተጨዋወቱ እናት ለልጇ መድኃኒት ቀምሳ እምታቀርብለት ለምንድነው ተባባሉ። አይቷት በመተማመን እና ቢመረውም ስለቀመሰች ላለማነስ ብሎ እንዲጠጣ ነው ተባባሉ። ለፍቅር እና መስሎ ለመታየት ሲባል፣ የእማትፈልገውን ትከውን አለህ ማለት ነው፤ ሲል አደፍርስ፣ የእማትፈልገውን ስለ ፍቅር እና እምነት መከወን አለብህ፤ ብሎ አቶ ጥሶ አሳሠበ። ለአደፍርስ፣ ስለ ጨሌ ማውራት ቀጥለው አቶ ጥሶ፤ ዘምኖ ፈጥኖ ሌላውን ለመለወጥ ከማሰቡ ቀድሞ እራስአችሁ ተለወጡ ብለው እንለውጥ እሚለው ትውልድ ረጋ ብሎ እንዲያከብር ነገሩት። ህዝብ ዋጋ ለእሚሰጠው ነገር የግድ የእኔ ሀሳብ ብሎ መጫኑን እንደ እማይገባ ነገሩት። ፍሬዋ ወደ ውይይቱ መጥታ ምሳ እንቢ ብሎ እርጎም አልጠጣም ብሎ ትልቅ ሰው ሲጠይቀው እንቢ የአለ ነው ብላ ገስጻው ወደ ቤት ሲገቡ ተውስኦቱን ለማስቀጠል አደፍርስ ተከተለ።

ምእራፍ ሀምሳአንድ
አደፍርስ አቶ ጥሶን መጫወቱን ቀጥሎ ስለ ንጉስዎች ሰሎሞን ዘርነት ከአመኑ ጠየቀአቸው። አምን አለሁ ሲሉ መረጃ ሲል ለማመን መረጃ የለም ግን መላምት አለኝ አሉት። የዛሬ ኢትዮጵያ አንድ ደመን የታላቋ ኢትዮጵያ አካል ነረበች። የሳባ፣ ሳብዓን፣ ናምሩድ፣ ተከታይ የነበረው የኩሽ ልጅ አቢስም ነበር የአቢስንያ መጠሪያ። ግሪክዎች እና ሃዋርያት የጻፉላት ኢትዮጵያ የዛሬዋ ሳትሆን ትልቋን ነበር። ከኑብያ እስከ ሕንደኬ ከሜሶፖታሚያ እስከ ሱዳን ግርጌ የተዘረጋው ስልጣኔ የኢትዮጵያ ጭምር ነው። ግን አንደኛ የደረዘርክው ሀገር ሁሉቧ ባለቤቱ ጭምር ነው። ሁለተኛ ለታሪኩ ወራሽነት ብቁ ነን ወይ ነው ዋናው ሲለው ጥሶ ምን ማለት ነው አለ። አደፍርስ፤ የእዚያን አይነት ታሪክዎች ነን የእሚሉት እንዲህ የአለውን አሳፋሪ ነገር የእሚሰሩ ናቸው ከመባል የአልደረሱ ሆኖ መገኘት አለው።
የሰሎሞን ጥበብ የክርስቶስ መንገድ አብዝቶ እሚይዝአቸው ለፍትህ እና ሀቅ እንጂ ለሌላ እማይሸነፉ እንደ ኢዛና፣ ላሊበላ፣ ምንይልክ የአሉ ነበሩን። አሉን ይኖሩን አለ። በእየእምነት ፍላጎትአችን ተተብትበው እንጂ አሉን። ይመጣሉም አሉት። እመን ብለው ጥቂት አመነ፣ ስለእዚህ ጨምረው ተነጋገሩ።

ምእራፍ ሀምሳሁለት
አሰጋሽ ከሮቢት ተመልሰው ደብረሲና ሳይሄዱ አርማኒያ የሮማን ሰርግ ስለደረሰ ዝግጅቱን በመብል መጠጡ ሲረዱ ቆዩ። ሮማን ሰርጓ ሳምንት ስለቀረው ተጨንቃ ለመጥፋት ትሞክር አለች። ጴጥሮስ ይዟት ለመጥፋት ቃልገብቶ እስኪቆርጥ ቀኑን ስትጠብቀው ሀሳቧ እሚታያት ከተማ ገብቶ ካቲካላ ነጋዴ ዘንድ እንድታሳድራት ለምና በንጋታው ነጋዲቷ ከስካር ስትመለስ አኑሪኝ ማለቷን ነበር።

ምእራፍ ሀምሳሶስት
አቶ ጥሶ ስራአቸውን ፈጽመው ከልጅአቸው ጋር አስካለችም ከአሽከርዎችአቸው ጋር አዲስአበባ ለመክረም አቶ ጥሶን ተከትለው ተመለሱ።
አደፍርስ እስኪፈፅም ስራውን ደሴ እሚወስደው መንገድ ላይ ከአለ ሆቴል ክፍል ገብቶ ቤት እስኪከራይ እየቆየ መቀጠል ሲያያዝ ክብረትም አብሮት ረብቶ ነበር። ስለ እሚአምፁ ተማሪዎች ማመፅ፣ ድንጋይ መወርወር፣ አድማ መያዙ፣ ሰላምአዊሰልፉ፣ ወዘተ. እሚያረጉትን ሳያቁ ነው ባይ ነህ? በጎ ጎኑም ይታይህ ሲለው ክብረት አመፁን ለመንግስት ለቤተሰብ ብሎም ለከተማ ህግዘብ (police) እንቢ ስላሉ ነው፣ ወታደር ከደብረብርሃን የሄደው ያም ሰላም ሰጠን ሲለው አደፍርስ ወታደር መላኩ ተግባቢ አይደለም ብሎ ተከራከረው።
ስለ ቢል እሚባል ሠላም-ጓድ ነገረው፤ አሁን ፍርፋሪ እሚመግብአቸው ተማሪዎች እየተከታተሉ ይገላምጡኝ አለ ምን አስበውብኝ እንደሁ እንጃ። እና እንግሊዝኛ ማስተማር ስጀምር፣ አንድ ተማሪ ለ Ethiopian Herald የፃፈውን አርምልኝ ብሎ አረምኩለት። የሰላም ጓዱን ነጭ አይቶ አንተም አርምልኝ ሲለው፤ ከማረም ይልቅ የራሱን ሃሳብ ጽፎ፣ እንዲህ ነው እሚፃፈው አለው። ሲያገኘኝ የተሻለ መታረሙን ነግሮ ሲያሳየኝ የእሱ ሃሳብ ጠፍቶ ነበር። ያንን ብነግረው አይደለም ከእሱ አትሻልም አለኝ። ከአፍ ፈቺ ቋንቋ የበለጠ አንተ አጥንተህ መብለጥ አትችልም ወይ እሚለው ገና እየተጠና ነው ግን እግሊዝኛው የእራሱ ነበር። ብቻ ሳይሆን፣ በደፈናው በቋንቋአቸው እሚሰብኩን የእራስአቸውን አመለካከት ነው። በቋንቋ ውስጥ የእኛን ሃሳብ ትተን የእነሱን እንድናጎለብት ይተጉ አሉ። በእዚህ ስልት ቅኝገዢነቱን መቀጠል ይሹ አሉ።
ክብረት የፈለጉትን እስኪያገኙ በብልሃት መቅረብ ነው እንጂ አለ። አደፍርስ ተማሪዎቹም ያንን ብለው ፈረንጆቹን መስለው ቁጭ አሉ እንጂ እንዲያ አማራጭ ነበር አለ። አሁን ሰላም ጓድዎች እንግሊዝኛ ሲያስተምሩ፣ እሚነግሩት አገላለጥህ የተለመደ የእኛው ከሆነ ያስለውጡህ እና ቻልህ ይሉህ አለ። ለምሳሌ፣ ቤቢ፣ ሃይ፣ ወዘተ. ከአላልክ ሰላምታው ሰላምታ አልቻልክ እሚባልልህ ነው። የእነሱን ባህል ስትይዝ ማለት ነው። አሁን ሰብእናአችን እየተነካ ስለሆነ መሬትአችን ቢያዝ አናስመልሰውም መቼም። ድሮ መሬትአችንን የአስመለስናት ሰብእናአችን አንድ ስለነበር ነው። አሁን ምንም ተስፋ የለንም አለው።
ስለተሳለው ስእል እየተመለከተ ክብረት ሲናገር ቆይቶ፣ በመጨሻከ አሳላፊዋ ቢራ ስለጨረሱ ጊዮርጊስ ቢራ ሰጥታ ስእሉን በማብራራት ቀለደች።

ምእራፍ ሀምሳአራት
ሮማን የገባችበት ጠፍቶ፣ አሰጋሽ እየጨሱ ሳለ፣ ሶስቱ ሽማግሌዎች ለሰርጉ እየፈሩ እየቸሩ ገቡ። ሮማን ብትጠፋ ብታሳፍርም እሚጋቡት ሰዎች ከአንድ ባህር ነው እና እርሶን መድፈር አይሁን ብቻ የተደገሰው ከእሚበላሽ አቶ ጎርፉ ከጺዮን ይጋቡ ብለው እነ አባ አዲሴ ጭምር ተናገሩ። አሰጋሽ ለልጄ ከእዚህ የበለጠ ሰርግ ነው በመላ ኢፋት እማዘጋጀው ሲሉ፣ ግድየለም ይስተካከል አለ። ቀን ጨምሩ ጥቂት ብለው አስራአምስት ቀን በኋላ እንገናኝ እና እንየው ተባባሉ። አስተናጋጅ አሽከርዎች ለጺዮኔ ወሬውን ነገሩ።

ምእራፍ ሀምሳአምስት
ነጋዲቷ ሮማንን ተቀብለው ካቲካላ ቀን ከሌሊት ሲያሰሯት ደክማ፣ ወዟ ተመጥጦ ሳለች እሷ ግን ስለስራዋ ተወደደች። ሮማን ሰርጓ ሲደርስ ሳይበላ አልፎ ጺዮን ልትዳርበት ተቃርቦ ሽማግሌዎቹ ሊመጡ አንድ ቀን ሲቀር ደንግጣ ጠፍታ ደብረሲና በላይ አጎቷ ጋር ገባች። ተቀብሎ ልጅአገረድ ሁለት ተማረከዎች ከአሉበት ኪራይ ቤትአቸው ጓደኛ ስለነበር አስቀምጧት ስድስት ቀንዎች ቆየች። በሰባተኛው ቀን አደፍርስን ከአላገኘሁበሞሞቼ እገኝ አለሀጀ ስትል አስጠራላት።

ምእራፍ ሀምሳስድስት
የዩንቨርስቲ ስራውን አደፍርስ ጀምሮ አፍላ የስራው ወቅት ስለነበር እንቢ ማለት ነበረበት። ግን በላይ ሲጎተጉተው ተጨንቆ፣ ብመክራት ብትመለስ ድንገት ብሎ እሺ ብሎ መጣ። ይዘኽኝ ጥፋ አለችው። እንቢ አለ። መክሮ በሮማን መጥፋት የአዘነች እናቷ ሳትጎዳ እንድትመለስ እንድታስብ ስለእናቷ ሲነግራት እንቢ ገጠር ብመለስ እሞት አለሁ ለሮማን ስራ ልትፈልግ ነበር ለእኔም ፈልግልኝ አለችው። ጎርፉን ትወድጂ አለሽ አግቢው እኔ ስራ ለአንቺ አልፈልግም። አመት ገጠር እምቆይ ከእዛ ወዳጅ ሀገር ቀጥሎ ለመማር ወይም ለስራ ከሆነም ገና ያኔ እምቀመጥ ነኝ። አሁን ምንም አላረግልሽ ሲል፣ እግሩ ላይ ወድቃ አለቀሰችበት። እኔ አልወድም እነጎርፉን፣ ልቡሰጥላአችን አንድ አይደለም፤ ስትለው ስለእሱ አታቂም ወይ ዩንቨርስቲ መች ገባሽ ሲል ወልዱ ገቡ። ከውጭ ኡኡታ ሆነ። ህግዘብዎች መጥተው ወሰዱአቸው።

ምእራፍ ሀምሳሰባት
ህግዘብዎች፣ አደፍርስን ቃል የአሰረች ልጅአገረድ ከሀገር አስኮበለልህ በእሚል ክስ ይጠየቅ ጀመረ። ካደ። እሷም ስትጠየቅ አላስኮበለለኝም እምጋባ አልነበርኩም አለች። በመጨረሻ አሰጋሽም ከህግዘብዎቹ እየጮኸች ጠየቁ። በመጨረሻ አደፍርስ አይደለም ጎርፉን ላለማግባት መጣሁ፣ ወልዱ ደግሞ አስገቡኝ አሉ። አደፍርስ ተማሪዎቹን እያባለገ ነው እሱ ነው የአመጣሽ ሲሉ አይደለም ብላ በመከራከር አሳመነች። ክብርሽ አለ የለም ሲል ህግዘቡ የለም ብላ አሰጋሽ ደነገጡ። አደፍርስ ሊያዝ ሲል እሱ አየደደለም አርማኒያ ውሃ ስቀዳ ነው አለች። አሰጋሽ አውቀሽ ነው አንቺን እዛ እሚነካ የለም። በአኮርዲዮ የመጣ ጋኔን ነው አሏት። አይደለም ስትል እራስ እንደ መሳት ብለው ረገሟት። ስሞት እንኳ አጥንቴ ይውጋሽ አጠገቤ አትድረሽ እናት አባቴ አያትዎቼም አፍረዋል አትቅረቢኝ አሏት። ህግዘቡ አደፍርስን ለቀቀው። ሲወጣ በታላቅ ንዴት፣ የነደዱ ሁለት ሻማዎች አጊንቶ እንዲህ የአለ ነገር በሰውነትሽ አለ ብዬ አላስብም ብሎ ነግሯት ወጣ።

ምእራፍ ሀምሳስምንት
አደፍርስ ቤት አጊንቶ ተከራየ። እናቱ አከላት እና አጣሁ ወሮታ ሰራተኛዋ ተመልሰውለት አሉ። እምብዛም አይጨዋወት ተቆጥቦ አብዬ ትምህርትቤት አማርኛ እና እንግሊዝኛ እየአስተማረ፣ ሳለ ሮማን እየመጣች በመደበቅ ተወያይታው በተመቻቸ ጊዜ ተመለሽ ሲላት ከካቲካላ ቤት ወጥታ ወደ ደብረሲና ሄዳ ቡናቤት ትቀጠር አለች። በላይ አስራሁለተኛ ክፍል ተፈትኖ ወደ ዩንቨርስቲ አለፈ። ጺዮኔ ክብሯን ለአደፍርስ ሰጠች ብሎ ጎርፉ በመናደድ ጠባሴ ወጥቶ ውትድርና ተመለመለ። አሰጋሽ አርማኒያ ተመልሰው፣ በእርጅና ትንሽ ቢጫጫኑም፣ ልብአቸው አላረጀም። የአሉት እየተፈጸመ በደንብ እየተቆጣጠሩ ከኖሩ፣ አቶ ወልዱን ቄደር አስጠምቀው፣ ጺዮኔን ደግሞ ምን እንደእሚያስጠምቁ ይወያዩ ነበር።

ምእራፍ ሀምሳዘጠኝ
ጺዮኔ አጎቷ ጋር ተቀምጣ አለች። አለሙ ቀፍፏት ቤተክርስትያን መመላለስ ስራዋ ሆኖ አለ። አደፍርስ በአሰጋሽ እንዳይጠላ እና እንዳይሰደብ ብላ ክብሯ ሳይነካ ተደፍሮ አለ ብላ መዋሸቷ እየከነከናት መጥቶ አለ። የከፈለችለትን መስዋእት ሳያምን መቅረቱ አሳስቧት በምን ከእነክብሬ መኖሬንስ ልግለጥለት ብላ ተጨነቀች። እቤት እየዘጋች ማልቀስ ጀመረች። አባ ዮሐንስ እየመጡ አንዳንዴ የአጽናኗት ነበር። እየዳሰሡ በመስበክ የአረጋጓት ነበር። ወይም —

ምእራፍ ስድሳ
ከማህጸን መረጥኩህ እሚል እንደ አለው፣ አንቺም ከማህፀን የተመረጥሽ ነሽ። ለሰው ብለሽ ክብረንጽሕና የለኝም ብለሽ መስዋእት የሆንሽ ነሽ፣ አምላክ ለጽድቅ ይፈልግሽ አለ። በርቺ እና ወደ ገዳም ግቢ፣ የተመረጥሽ ፃድቅ ነሽ፣ አሏት። ወይም —

ምእራፍ ስድሳአንድ
አንድ ጊዜ መናኝ በደግ ደረጃ መንኖ ሲኖር፣ እከብርባይ ልቡና ቤቱ መጥቶ አንተን መሳይ ከተማ ተምሮ ሰው እየረዳ ይኖር አለ እንጂ የት ይደርስ እንጂ አይመንንም አለው። ንጉስ ቤት ላስቀጥርህ ሲለው ደግ ሃሳብ ነበር፣ ግን መንኖ ጥሪት እና ኀዲገ አብያት ተከትለውኝ አይሄዱም አለው። ዲያብሎስ ፍትወትን አዝዞ ከተማ እስካዘጋጅለት ሂድ ይዘህው ና ብሎት በፍትወት መዳራት መጠጥ ወዘተ. ሃሳብዎች ይዞት ወጣ። ጎርፍ እያሳሳቀ ይወስድ አለ።

ምእራፍ ስድሳሁለት
አጎቷ አቶ ወልዱ ደግሞ እራት ከተበላ በኋላ የእራስአቸው ድግግሞሽ ልማድ ነበረአቸው። ይህም አጠገቧ ተቀምጦ፣ ሲመክሯት ሁሉ እንደወደዱት አይገኝም፣ የለመዱትም ይለዋወጥ አለ። ምን ይደረግ ብለሽ ነው፤ ሳትደሰች ተደስተሽ፣ ምንም ሳትሆኚ የእምታዝኚበት አለም ነው አሏት። ወይም ደግሞ —

ምእራፍ ስድሳሶስት
እናትሽ እምትለፋው፣ እምትንቀሳቀሰው ለአንቺ ነው። መንገድ ፈልገሽ ታረቂ። ማለፊያ እዚህ ፈልጋሽ ባትለዪኝ ብትልም አራት ወርዎች እኛ መመለስ እና የአባትሽን ንብረት በመሰብሰብ በመመዝገብ እርጃት እንጂ። በመቀመጥ ማታ ስታጫውችኝ እኔም ማታ ማታ እማወጋሽ ሆነሽ ለምጄሽ አለሁ፣ ማለፊያ ከማጀት አትወጣ መርመጥመጥ ነው እምትወደው። ግን ሂጂ እባክሽ አሏት።

ምእራፍ ስድሳአራት
ወይም ደግሞ አንዳንድ ታሪክ በማውራት —
በ ኮንስታንቲኖፕል አንድ ፈታል እና ወሮበል ነበር። የፈቱትን መተኛት፣ እየሰረቀም መኖር እውቅ አድርጎት ሲኖር፣ የአልፈቱትን መተኛት ጀመረ። ተረጋግቶ አግብቶ መኖር የፈለጉ ጠሉት እና ሁለቴ ግድያ ሁሉ ተሞከረበት። ቀጥሎ፣ አሜሪካ ተሰደደ። እዛ በተመሳሳይ ስራው ቀጥሎ ሀብት አካበተ። ግን ከሀገሬው የበለጠ ሀብት አላገኘም፣ በደንብ አልተከበረምም። ሀብቱን ይዞ ኮንስታንቲን ተመለሰ። ሰው ሁሉ አላወቀም። አላመኑትምም። ስሙ ፈታል እና ወሮበላ የነበረው ሰው አምሮበት ከመጣ እየተጠራጠሩ አንዳንዱ ብቻ በድፍረት እሱ ነው እየተባባለ ቆይቶ በመጨረሻ አንዱ ደፍሮ መጣ እና በእምነበረድ ጠረጴዛው አጠገብ ማነህ አለው ደፍሮ። ታውቀኝ አለህ፣ ስታማኝ ነበር እዛ ጋር ከሰዎች ሆነህ አለው። አላማሁህም አለው። አበረታታው፣ ከእዛ ስምህ ፈ…እና ወ…ብሎ እሚጀምር አይደለም እንዴ አለው! ነው አለ። ፈታል እና ወሮበላ። ፃፍ እምነበረዴ ላይ ስደበኝ አለው። ፃፈ። የባንክ ደብተሩን አውጥቶ ጫነበት። አየህ ሃብቴ ትልቅ ሆኖ ስድቤን ሸፈነ አለው።
አንቺም ጺዮኔ ሀብት አለሽ ሂጂ ተመለሽ። ሀብት ላይ የአለሽ አመለካከት ይስተካከል፣ አትናቂ ገንዘብ ብዙ የአደርግ አለ ሲሏት፣ አልፈልግም እኔ አለች።

ምእራፍ ስድሳአምስት
ሮማን ከደብረብርሃን ተመልሳ ቤተክርስቲያን ጺዮኔን አጊንታ ሲያልፉ ከክብረት ጋር አደፍርስ ሆቴሉ ሆኖ ተመልክቷት ተደብቃው ስለመጣች ተናደደ። ክብረት አብሮአደግ እህቷ ናት አብራት ትሁን ተዋት አለው። ከእሷ አልይሽ ብያት ቃሌ አለመከበሩ ገርሞኝ ነው። እሷን ብሎ ቤተክርስትያን ሳሚ። ስትዞር ከርማ አሁን ደግሞ ቤተክርስትያን ትል አለች። መቼም ወርዶፋ ልጁን እንዳስቀመጥህ ቢሰማ ሲለው ይስማ አለው። ቀድመህም የአስኮበለልካት ናት ቢልስ ሲለው ይምሰለዋ አለው። አደፍርስ አልተጨነቀም። የጉድባውን አጋጣሚ ዘነጋህው ሲለው አደፍርስ እባክህ ለማንኛውም፣ ሌላ እየተጫወትን ቢራአችንን ብቻ እንጠጣ አለው።
አጠገቡ፣ መንገድ ዳር ላይ ተማሪዎች ወረቀት አንግበው በመቃወም ለሰልፍ ሲመጡ ተመለከቱአቸው።

ምእራፍ ስድሳስድስት
ጺዮኔ አደፍርስ አመት ሲሆነው እንዴት ሆንሽም አለማለቱ፣ ሮማንን ቢወድድ ነው ብላ ተበሳጨች። እና ከተገናኘን ጀምሮ እሷንው እንደወደደ ነበር ማት ነው? አይሆንም። እያለች መበሳጨት ጀመረች። በክፍሏ እያለቀሰች እየተከዘች መኖሩን ተያያዘችው።

ምእራፍ ስድሳሰባት
የተማሪዎቹ ሰልፍ ህገወጥ መንገድ ይከተል ጀመረ። ድንጋይ ውርወራው ተጀመረ። ተማሪዎቹን ለማስቆም፣ አደፍርስ እና ክብረት መሀከል ገቡ። ውርወራው ሲቀጥል፣ ሁለቱም ተመትቱ። አደፍርስ ግን ተጎድቶ ወደቀ። ጩኸት ኡኡታ በዛ። አስር አለቃው መጥቶ “ሞት እና ህይወትን ላያራርቁ፤ ጌታዬ እውቀት ምን የአደርግ አለ፣ እውቀት በአፍንጫአችን ይውጣ!” እየአለ ከክብረት ጋር ይዘው ሃኪምቤት ወሰዱት። ማታ አደፍርስ ሞተ።
ጺዮኔም ብዙ ሳይቆይ ሞቱን ሰማች።

ምእራፍ ተከተሏት።
ወደ ቀብር እየሄዱ፣ አቶ ጥሶ ሲያለቅሱ፣ ሮማን እና ጺዮኔ ግን የበለጠ እያነቡ ነበር። ሮማን ሲያጽናኗት በመናደድ በመሀከል ጉዞ ሳሉ አምልጣ በመለየት ሮጠች። ወርዶፋ ሲከተላት፣ አባ ዮሐንስም

ክፍል ሁለት ቀጥል አለ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s