Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የምርጫ ቀልድ ፪፤ የቢያንስ የጀመርኩትን ልጨርስ ፉክክር

The folly of prosperity party in the coming Ethiopian six national election campain of Ethi

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, April 07th, 2021 GC.,


ብልጽግና ድርጅት፣ ለ 2013 ምርጫ ከሰቀለአቸው ትልልቅ ህትመትዎች፤ አዲስ አበባ ከተማ፤ ከአውቶብስ ተራ ወደ ልደታ ሲመጣ እሚገኝ የ አብይ አህመድ (ሊቀምሁርዎች)፣ ምስል አንዱ ነው። ጠሚ.ሩ ሲናገር እሚታይ ሲሆን፣ ከስሩ ” የተናገረውን የእሚያደርግ የጀመረውን የእሚጨርስ ፓርቲ ብልጽግና ነው።” ይል አለ።
በ ጠሚ.ሩ የእሚመራው የ”ለውጥ አስተዳደር” ኢህአዴግ.ን ከተቀበለ ጊዜ ጀምሮ፣ እና ጥቂት ቀደም ብሎ፣ በብዙ ድፍን ስሜት ወሬዎች እርካታን እና ተስፋን ያጭር ነበር። ብዙዎች ነሁልለው ነበር።
በሶስት አመትዎች ሲደመር፤ የዲናው መንግስቱን “ኮሎኔልዎች በአፍሪቃ ስልጣን በመጨበጥ እሚችልአቸው የለም” የአለበትን ትንተና (Children of the Revolution), የእሚያረጋግጠው፣ ኮሎኔሉ ጠሚ.፣ ወደ ርእሰ መንግስትነት ሲቃረብ እና ስራውን ሲቀበል፣ ከተናገረአቸው የተከተለው – ዛሬ ድረስ – የትየሌለ ቁንጽል አዎንታ እና እማይፈጸም አሉታአዊ ቅርስ ነው።
በአንድ ጊዜ፣ ሀገርበእሚቀይሩ ስር ነቀል ነገርዎች መከወን ሲችሉ፤ በሶስት አመት ሲመት በዓል እለት እንኳ የተለመደ ኩርማን-ሺህ ንጹህ ዜጋአዊን (civilians) በእማይጠየቅ አካል ተገድለው ለተከታታይ ዘገባ በቅተው ነበር።
የ ፳፯ ዓመትዎች አምባግነና ትግል ከጠራው ጥቂት ለውጥ በቀረ፣ (ለምሳሌ የተቃዋሚዎች ከውጭ ወደ ሀገር መመለስ)፣ በሂደት ይህ ህዝብአዊ መስዋእትነት የቀጠረው ለውጥ እያፈገፈገ ከጀመረው ሁሉ ተቀንሶ አለ።
በሂደት ግን፣ ተጨማሪው አሉታ እየበዛከ ውስጠ-ሀገር መፈናቀል፣ ሽብር፣ ሁከት፣ ወንጅልዎች መብዛት፣ ስራ አጥነት፣ ድህነት ኑሮ ውድነት፣ ብሄርተኛነት፣ እርስበእርስ ጦርነት፣ ወዘተ. በዝቶ ብዙ ውድቀት ተግባሩን አስምሮ ገልጦት ነበር።
ይህ ሲሆን፤ የቀረው ተስፋ፣ ሶስት አመትዎች ቀድሞ የኢህአዴግ. ሊቀመንበርነት ሲቀየር የተደመጠውን አሟሟቂ ወሬ ዞሮ መደገፍ አንዱ የቀጣይ ጉዞ ስልት ሆኖ ተገኝቶ አለ። በሶስት አመትዎች ተስፋ ሳይንጨላጨል፣ ለአምስት አመት ውል፣ ማሳመኛው የመጀመሪያው ወሬ ይጨረሳል ነው። ያም፤ ሌላ አፍጊት፤ ገሀድ ግለ-አቂያቂይነት (self-ridiculing) ነው። እንደ “ስንገባ የአወራንውን እንጨርስ ምረጡን” መሰል ትልቅ ይሁን-አይሁን እንጃ እንጂ ሌላም ቀልድ አይጠፋም። በሶስት አመትዎች የተተከሉ ዛፍዎችን፣ ወይም ዉሃ እማይደፉ ወይም ቀዳምአዊነት (priority) እማይገባአቸው ለውጥዎች፣ በ አምስት አመትዎች እረዝመው፤ ሞት፣ ስደት፣ መፈናቀል፣ እርስበእርስ ጦርነት፣ ዘረኛነት፣ ሙስናው-በእየዘርፉ፣ የአልጠራ እና ነገን እማያገናዝበው የተለመደ ቆሻሻ ግንባታ ያም የወደፊት ትውልድ ወጪ ወእም የሀገር እዳ ነው፣ ዘረኛነት፣ ወዘተ. በሌላ መንገድ ይቀጥል አለ ማለት ነው። የታየው እስከአሁን የ፳፯ አመት አመጽ ፍፃሜውን እሚያንፀባርቅ ጥቂት ለውጥ እንጂ፣ በጎኑ ዝብ-ትድድር (mismanagement) የአቀናው ብዙ ውድቀት ሆኖ፣ ይህን ለማስቀጠል፣ ማሰብ ትልቅ ክስረት ነው። ክስረቱ ላይ መደመር የከወነው ደግሞ፣ ብልጽግና ከአስተዳደሩ ቅያሬ ቀድሞ ቅያሬ ወደ ደረሰበት የነበረው ቤተመንግስ ሲገባ የሰበከውን አስታውሱ ከእዛ እሚሻል ዛሬም የለም ማለቱ ነው፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “የምርጫ ቀልድ ፪፤ የቢያንስ የጀመርኩትን ልጨርስ ፉክክር”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s