Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

እያሙ ወዳጅ፡ የቅኔ አኗኗር እንደ አኗኗር ቅኔ

About Andaegachew Tsige’s inspiring insight regarding Ethiopian psychology based on Qine that has probably led the nation to have no single or clear color of understanding of life.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, መጋቢት ፳፩ ቀን ፪፻፻፲፫ ዓም.፨

ክብረት፤ ኢትዮጵያአዊ ዉበት የአሰፈፈው፣ እሚንቀሳቀስ ህይወት ላይ ነው፤ ነብስ ስታልፍ ስታገድም፣ ነው እሚያሳየው። የእኛ ዉበት ቆራጥነት እና ልበሙሉነት፣ ሲፍለቀለቁ፣ ኅሊና የአልተቀበለአቸውን ረቂቃን ሲዛዛቱ መስሎ ለመኖር የሚደረጉ ቸልተኛነት፣ ቻይነት እና ኀይለ ስሜት ሲዋጉ፣ የተደበቁ ደስታዎች እና ብሶትዎች – ጠቅላላ የሃሳብ ነጸብራቆችእምቅ ጭምቅ ከእሚለው ልብ እያውገነገኑ ሲወጡ የእሚታይበት መነሳንስት ነው።

ከ ዳኛቸው ወርቁ፣ አደፍርስ (1962)፣ ገ.161 የተጨመቀ፥ አስተኩሮት (emphasis) የታከለበት።

አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አንድ የ ፪፻፻፲፫ ዓም. የተከወነ ተጨማሪ ትልቅ ሰዎች በተወያዩበት መድረክ ላይ፤ ተገኝቶ በተለመደ ግድንግድ ቁምፊ (font) ፊደልዎቹ የጻፈአቸውን አረፍተነገርዎች በፈጣን ሽርተታ (scrolling) እያነበበ አቅርቦ ነበር።
ወደ ኋላ ላይ፤ እንደዘበት ስለ ኢትዮጵያ (እና ኢትዮጵያአዊነት ንጥረነገር) ሲናገር፤ ስለ ሁለት የህላዌ (existence) አረዳድ ወይም የአገነዛዘብ መንገድአችን፣ ወይም አተያይአችን ቀንጭቦ አነሳ። ቀጥሎ፤ ያ ቅኔን ፈጠረልን ብሎ፣ የቅኔ ህዝብ ስለሆንን፣ አንድ ተናግረን ሌላ እምንከውን፣ ሰዎች መሆንአችንን እና መተማማትም እሚቀናን እንደአደረገን ገለጠ።
ይህ ብርቅዬ ኢትዮጵያአዊ አንክሮት ነው። ሃሳቡ፣ የመነጨው ነጥሮ አካባቢአዊ (local) ጉዳይ ላይ ነው። ሀገርበቀል እውቀት አይደለም። ዳሩ፤ የሀገር ብርቅ እውቀት ነው።
እርግጠኛ፤ ስምጥ የአመለካከት ባህር በእዚህ እይታ ተከፍቶ አለ። እሚመረመር ስነሰብእአዊ ወይም ማህበረሰብእአዊ ወይም የሀበሻ ስነልቦናአዊ ጉዳይ በእዚህ ነጥብ አለ።
የሀበሻ መደበኛ ስነልቦና፣ ቅኔ ነው። ሀቀኛነት የለበትም። ቅኔ ነገር መሸፋፈን እሚያውቅ የተግባቦት ዘዴ ነው። ሀበሻ ከእራሱ አእምሮ እና ከወገኑ እሚገናኘው ግን፣ በቅኔ ነው። ቅኔው ማታለል የሆነው፣ ቅኔውን መኖር እሚቻል ስለአልሆነ ነው። ለምን?
አንደኛ፣ የህዝብ መብዛት፣ የስልጣኔዎች ግጭት፣ አዳዲስ ዝማኔ፣ ወዘተ. ቅኔን እየአስተወ፣ ቀጥተኛነትነ እየአስተማረን መጥቶ አለ። ከዓለም ተፅዕኖ መላቀቅ እማይቻል ሆኖ አለ።
ሁለተኛ፣ የቅኔ አኗኗር በእራሱ እየአረጀ መጥቶ አለ። በታሪክ ጥናት፣ ዋናው የኢትዮጵያ መግባቢያ ቅኔ እንደሆነ እንገነዘብ አለን። አዝማሪ እና ስስኝዎቹ የሌሉበት የንግስና ዘመን አልነበረም። ኖሮ አያውቅም ማለት ቀላል ነው። ተክለጻድቅ መኩሪያ የመጀመሪያ መጽሐፍአቸውን እንኳ ከ ዐፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀኃሥ. ሲጽፉ በመግቢያ እንደ አሰፈሩት፣ የእየዘመኑ ታሪም ቅኔዎችን የእሚያውቁ አባትዎች ማነጋገር አንዱ ስራአቸው ነበር። ንጉስዎች እንኳ እሚወያየጀት እና ዕዝ ወይም አድማ እሚከውኑት በቅኔ ነበር። ይፋ እና ንግስናአዊ (royal) መግባቢያው መንገድ ቅኔ ነበር። ይህ ሁሉ፤ ዛሬ ክስም ብሎ፣ ቅኔ ከመንግስት ቋንቋ ስልትነት ተፋትቶ አለ። በዘመንዎች፣ ወደ ቤተክህነት እና እረኛዎች ዘንድ የተሰደደ ስልተ አኗኗር ተደርጎ አለ።

በእርግጥ የቅኔ አኗኗር ክፉ ነበር?
ፈጽሞ እሚገርም ልእልና (class) በእዛ የአኗኗር ስልት እና ዘመን ነበር። በቅኔ ሲኖር ግጥጥሞሹከእዚህ ዘመን የተጨናነቀ አኗኗር ጋር ስለአልነበር፤ ክብር እና ኩራት ጋር ነበር። ከመጨናነቅ ውጭ፣ ሲኖር፣ ቁሳቁሱም ስለእማይገኝ፣ ስልጣኔውንም መናቅ የተለመደ ስለነበር፣ ይህ ክብር እና አለመጨናነቅ የበዛ ነበር። ስለግሉ ሁሉም፣ ትልልቅ አገነዛዘብ ነበረው። እራሱን ዝቅ እሚያደርግ የለም። በእራሱ አመለካከት እንኳ ቢሆን ክብር የአልተገባው የለም። ያ እየደበዘዘ ቢገኝም ዛሬም በሀገረሰብእ ኢትዮጵያ የእሚታይ ስብእና ነው። በቅኔ ሲኖር ይህ ስብእና በስፋት አለ። በዘመነ ቅኔ፣ ስብእና ከኩራት እና ከሀበሻ እራስ አክባሪነት የተሳሠረ ነበር። የ አበራ ጀምበሬ የእስርቤቱ አበሳ (1966-74) እሚሰኘው መጽሐፍን የአነበበ፣ አንድ እሚሰማው ነገር ቢኖር እጅግ እራስን አክብሮ በአለማሳነስ የእሚጠየቀው የእንክብካቤ ፍለጋ ነው። ሁሉም፣ መከበር ይፈልግ አለ፤ የህግ መብቱንም ይጠይቅ ዘንድ ግልጥ ነው። ዳሩ፤ አበራ ጀምበሬ የእሚጽፉት በህግ ቋንቋአቸው ወይም ሙያአቸው ብቻ አይደለም። የአተራረቅ ቀለምአቸው የመጣው ከእዛ የዘመኑ የግል እና ማህበርአዊ አመለካከት ነው። ያም እጅግ እራስን አክብሮ ቅንጣት የተዛነፈ አለመከበርን እሚገሥጽ ዘመን ነው። ዛሬ፣ ያ አተያይ የለም። ክብርን ትቶ፣ አሰራር እና ንግድ ወይም ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ወይም በደፈናው ተጨባጭ የአልሆነ ግንኙነትን ከቶ መዘንጋት ስለአለ፣ የክብር እና እራስን ማግዘፍ ስነልቦና የለም። ብንሰደብ ወይም ብንተች ምንም አይመስለንም፣ ተጨባጭ ስራው ከቀጠለ። (ለነገሩ፣ ብዙ የእዛ ዘመን መጽሐፍዎች ያንን መሰል አተያይ ወይም ርእዮት ስለ ግልአረዳድ ነበረአቸው። ሰዎች በዘመኑ ክብርአቸውን በእሚያስጠብቁ ነገርዎች እንጂ ጥቅም በእሚያገኙበት ትልም እና አረዳድ እሚፈስሱ አልነበሩም። ነገረስራ ወይም አኗኗር ሁሉ ስለእዚህ ሰውን በክብሩ፣ ማእረጉ፣ ወጉ የአዟዙረው ነበር እንጂ በገንዘብ እሚገኝበት፣ ስልጣን በእሚጨበጥበት፣ ወዘተ. ሰፈር እና ትልም ለመፋለም እሚያራውጠው አልነበረም።)
ቅኔ እየደበዘዘ፣ አዲሱ ዘመን በተለይ በኢህአዴግ. አስተዳደር፣ በቁሳቁስዎች እና በቸልተኛ ስብእና እየተተካ መጥቶ አለ። አንዱ፤ የሀበሻ የባህል ክፍተት፣ ይህ ስህተት የወለደው ነው። ማንም አዲስ ባህል አላዳበረም። በግድየለሽነት እና በአያገባኝም ስሜትዎች ደግሞ፣ ህዝብ የተራራቀ እና አብሮታው አቅመቢስ የሆነ ሆኖ አለ። የኑሮውድነት እና አነሁላይ ግለአታሎት መከወኛ የመዝናኛ አማራጭዎች ደግሞ፣ የለየለት የባህል መጥፋቱን ከውነው አሉ። ሲደመደም፣ በቅኔው ዘመን፣ ቢያንስ እንደ ጎንደርዎች በኩራት እና በማእረግ ሲኖር፣ ለእራስ ክብር የመስጠቱ ጉዳይ ከፍተኛ ነበር። በሂደት ግን ያ፣ የቅኔው ጥቅም ደብዝዞ እየቀረ መሆኑ ተቋቁሞ አለ።

ዳኛቸው ወርቁ ብሉይ (classic)፣ በ አደፍርስ ላይ ሰዓሊው ገጸባህሪይ ክብረትን፣ የአናገረው የልዩ ኢትዮጵያአዊ ውበት መገለጫ መግለጫው፣ ገሚሱ የቅኔ ስነልቦና የአልንው ነው። ለ ክብረት ግን የውበትአችን መገለጫ ሆኖ ታይቶት ነበር። ቢሆንም፤ መገለጫአችን እንጂ ውበትአችን ነው ማለቱ ከበድ የአለ ነው። ድብቅነት፣ ቸልተኛነት፣ መጠራረሱ፣ ከህሊና መሟገቱ፣ በሁለት አፈታት ወይም ቅኔ አኗኗርን ከመልመዱ የተነሳ ነው። ከውበቱ ጉዳቱ በእዚህ ዘመን በተለይ ጠፍቶ አለ። ሲመረመርምእንደሃሳብ እንኳ፣ የሰነፈ አያያዝነቱ ጎዪ ነው፤ ተቃርኖ ህሊናን እሚያራውጠው ለምንድነው? አንድ ወጥ ነገር እና ምላሽ ጠርቶ ስለአልተያዘ አይደለም? ወደ አንድ መንገድ መግባት ተአስገዳጅ ነው ማለት ነው፤ ግን ያ አልተከወነም ለእሚለውም ማረጋገጫ ነው። ኢትዮጵያአዊነት፤ በተጨባጭ ሲታይ፣ ከሆነው መሀከል አንዱ፤ ይህ በቀውስ ውስጥ የመኖሩ እውነታ ነው። ውበት እንደ አለው ገና አለመጥራትንም አስመልካች ነው። እየተጨነቀ ሲያውገነግን ነው ሀበሻ በውበቱ እሚታየው የአለው በመጨረሻ ተገቢ ቅጥያ ነው። ያም እሚያሳየን መጨነቅ የእኛ ስነልቦና እንደሆነ ነው። የእማይጨነቅ ኢትዮጵያአዊ ኢትዮጵያአዊ አይደለም ማለት ነው። ከመጨነቅ እና ፍቺ መመስረት ከአለመቻል ውስጥ ስንብሰለሰል እምንገኝ መሆንአችን ግልጥ ነው ማለት ነው፤ በእዛ አመለካከት። መብሰክሰክ ነገር ከአላጠራ ሰው ወይም ህዝብ እሚገኝ እንጂ ከሠለጠነ ሰው አይጠበቅም።

ቅኔ በስነልቦናው ዛሬ ጉዳቱ የበዛ ነው። ዘመኑ እየተቋቋመ የአለው በግልጠኛነት እና በአዳዲስ አሰራርዎች ነው። ይህንን መግለጥ እሚችሉ ቅኔዎች የሉም። ስለእዚህ ዝርውነት እየተላመደን ነው።
ደግ የሆነ ክፍል ይህ አካሄድ በእርግጥ አለው። ግን፣ ትጉህ ትብብር ከእየአንዳንድአችን ይፈልግ አለ። አብሮታ የግድ ነው። ሀቀኛነት እማይነጠል ውህድ ነው። ግልጠኛነት መንገዱ ነው። ሁሉን ገሀድ መሰተር እና በእኩልነት መረባበር አላባአዊዎቹ ናቸው። ቅኔ በእሚያርቀው ትውልድ፣ ያ ተተኪ መንገድ ስለአልተደረገ የአኗኗር ክፍተት እና የስልጣኔ አቅም መቀነስ ተከስቶ፣ መንግስትአዊ አምባግነና እና ክሽፈት እየተተካካብን ነው።

በቅኔ ስብእና (ስነልቦና) ለመኖር፣ ደፋርነት፣ እራስን ቻይነት እና አይበገሬነት አስገዳጅዎች ናቸው። እነእዚህን መመዘኛዎች ደግሞ አጥተን አለ። ያ ከሆነ፤ በምትኩ አብሮነት እና ዝማኔ መተካትአቸው አንዱ ግድ የሆነ አማራጭ ነው።
በንቅአት ያንን እስክንከውን፤ የድሃድሃዎች፣ አስመሳይዎች እና ከአንገት በላይ ነዋሪዎች፣ እያሙ ወዳጅዎች፣ በደፈናው አንድ ስብእና እና ወጥነት የጎደለን ነን። የእራስአችን ጠር እራስአችን ነን። እራስአችንን እምንጥል እኛው ነን። እቤት ለልጅ አትዋሽ ብለን ከመንግስት በውሸት እምንሰርቅ ነን። በደበዘዘ የቅኔው የላላ አኗኗር ልማድአችን ተሸብበን በተቃርኖት እምንራወጥ ነን። ወንድምአገኝ ጋሹ፤ በ ኢሳት እለትአዊ፤ መጋቢት 22 ቀን 2013 ረቡዕ ስርጭትአቸው እንደ አለው፤ ወደ ሃምሳ ንጹሕዎች (ህፃንዎች ጭምር) ሰዎች በቀደመው ቀን ተገድለው ማንም ምንም አላለም። ማንም ምንም አላገባውም፣ አውጋዥም እንከለ የለም – ያን አይነት ዜና በጥሞና ሰምቶ፣ በዝምታ መዝለል ለምደን ደንዝዘን አለ። ምን አልባት ከቅኔው አኗኗር ወደ ገሀዱ ስንመጣ፣ ሌላው ስጦታ ገሀድን አለማለባበስ ነው እና የድንጋጤ አላባአዊ (shock element) ያበቅልልን አለ። በቅኔው መፍረስ፤ አስገዳጅ ገሀድን መጋፈጥ ስለአለ፤ የአልተዛነፈ ገሀድ ይቀርብልን አለ። ያኔ እንደ ሀገር መንቃት እንችል ዘንድ እንቀሰቀስ አለን። ከቅኔ ወደ ገሀድ መጋፈጥ ሲመጣ፣ ከባዱን ገሀድ ለማሸነፍ ፍልስፍና ወደመጀመር፣ ከእዛም አንድ ላይ ስለሆንን በእየግልአችንም የእምንኖር ሆንን ብለን፤ ወደ መሰረትአዊው የስልጣኔ ወለል ግንባታ እንዞር አለን። አንዱ ለሁሉ፤ ሁሉ ለአንዱ ወደ መሆን፤ ለመጨረሻው አንዱ ሀበሻ ደራሽ ሀገር እና ህዝብ ወደ መሆን እንሻገር አለን። እኛው ለእኛው ለመሆን ግን፤ እሚያስተፋፍረን፣ እሚያታልለን፣ ግልጥ እና ሀቅን እሚቀማንን፣ ከአንገት በላይ እሚያኗኑረንን፣ የቅኔ መሰል አያያዝ እንጠነቀቀው አለን። ቢበዛ በአለን ወግ፣ ዘመንአዊነትን ማከል እንጂ፣ ወደ ዘመንአዊነት አለመሻገርን አንከውንም። እንደ ህንድዎች፣ ኩራትአችንን ከገጠር ወደ ዘመንአዊው አለም አላጓጓዝንም። ዛሬ፤ ከአንድነቱ ተፋልሰን፣ ከቅኔውም ተራርቀን፣ በዝማኔም ሳንበረታ፣ በተለየ ወግ ዓለሙን ግን እንዲሁ እንሻው አለን። ያም ማንም የአጠናልን እና የአቋቋመልን አዲስ አኗኗርአችን አይደለም። ገበያ እና ንግድ፣ ሉልአዊነት፣ በተለይ ከአስተዳደር እና መንግስት ደግሞ አምባግነና እና ሙስና፣ በተዘነጋ ስነአኗኗር የተፈጠረ ቸልታ የተከበብን ሆነን አለን።
አዲስ ባህል እስክንለምድ፣ ወይም ወደ ዘመነ ቅኔ አለም ዳግ-እስክንመጣ፣ አማራጩ፣ እራስን ባለማታለል፣ በምርአዊነት፣ በይሉኝታየለሽነት፣ በግልጠኝነት፣ በጀግንነት፣ በህብረት፣ በአርቆ አሳቢነት፣ አዲስ ባህልን መፍጠር እሚገባን ነን። የአስረጀንው ቅኔአዊ አኗኗር፣ የአኗኗር ቅኔውን አይበርዝብን። አንድ ወጥ ስብእና እና የማንነት አቀራረጽ መንገድ ከድህነት እና ጭለማ እንዲያወጣ ይደግፈን፨

One reply on “እያሙ ወዳጅ፡ የቅኔ አኗኗር እንደ አኗኗር ቅኔ”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s