Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የስልጣኔ ወሬ፡ እርፍ ይዞ ወደ ኋላ እና ንብርብረ-መፍትሔ ወይም እንዴት የኢትዮጵያ አለመሰልጠን ትልቅ ዝብ-መሠረቱ እንደእሚታደን

About fundamental Ethiopia’s failure in building a sustainability character in its attempts of civilization.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 28th 2021 GC.,

፩) እጅግ መግቢያ፡ ስልጣኔ መንገድ እና መዳረሻ ነው።


ስለ ጥበበ-ስልጣኔ ወሬው፣ በምድር ሁሉ ዳግምርምርዎች (researches) እና ቀጣይ-ውይይትዎች እንደተከወኑ ነበሩ። ሁሉም፣ ሁለት ጎራ ውስጥ ተለያይተው የተከማቹ ናቸው። ወገን አንዱ፤ የስልጣኔን አወላለድ መሰረትአዊያን እንደ ይዘት ወይም ፍሬነገር (substance) እሚነግሩ ትትረትዎች አለው። ይልቁንም፤ በሌላው ወገን፤ እጅግ አቻ ዉብ እና የግድ-ወሳኝ የሆነ ወሬው ደግሞ፣ የስልጣኔን ሂደትአዊ ስነስርአት (procedure) እሚገልጥ የጥናትዎች ሁሉ ዳግምርምርዎች አሉ።
በመጀመሪያው፤ እሚደረጉ ውይይትዎች ፍሬነገርዎች (ይዘት/substance) እሚመክሩት ለአብነት የአክል እንደ ንጽዉሳኔ (democracy) መገንባት፣ ትምህርትን ማብዛት፣ ስነምጣኔአዊ እርምጃዎችን አከዋወን፣ ወዘተ. እናገኝ አለን። በሁለተኛው ደግሞ፣ በይበልጥ ስነውሳኔአዊ (political) ባህልአዊ፣ እና የእቅድ እንቅስቃሴዎችን፣ እሚያበዛ ሆኖ፣ እናገኘው አለን። ለምሳሌ፣ ለስልጣኔው ጥበቃ መከወን፣ እርሱን የአለውን እና የተገኘውን ማስፋፋት፣ መጠበቅ ወይም ማስቀጠል መቻል ወዘተ. ዋናዎቹ ናቸው። በአጭሩ፤ ስልጣኔ መዳረሻ ከሆነ ያ መዳረሻ ሂደቱ (procedure) ነው። ዳሩ፤ ተቃርኖት የአለው ቢመስልም፤ የስልጣኔ መንገዱ ደግሞ ይዘቱ ነው። በይዘቱ መንገዱ ሲገነባ፤ ወደመዳረሻው እሚያደርሰው ደግሞ፣ ሂደቱ ነው ማለት ነው። አንድ ህዝብ ስለስልጣኔ ከተነጋገረ፣ ወሬው ሁሉ ስለእዚህ የስልጣኔን መንገድ ስለ ማንጠፍ እና ፍሬነገሩንም ስለ መከመር (መዳረሻ ስለ ማቆም) ነው።

፪) ንብርብረ-መፍትሔ፡ እንዴት የቅርቡ የኢትዮጵያው የስልጣኔ ሙከራ የአካሄድ መንገዱን እየሳተ ይዘቱን (መዳረሻውን) መከመር እንደ አቃተው


ንብርብረ-መፍትሔ። የኢትዮጵያው ማህበረሰብእ፤ ችግርዎቹን ሰብስቦ በነብስወከፍ እየፈታአቸው ይከምርአቸው። አንዱ ችግር ሲፈታ፣ ዝማኔ ይባል አለ። በሂደት፣ ስልጣኔን ይመሰረት አለ። የተነባበረው ዝማኔ አንድ ስልጣኔ ይባል አለ።
ይህን እነሆ ለመከወን በእሚመስል አያያዝ፣ ብዙዎች እየተነሱ ብዙ ባይሆንም በመሀከልአችን ለመከወን ይጣጣር አሉ። የስነውሳኔ ልሂቅዎች (political elites) ወይም ነን-ባይዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ዘፋኝዎች፣ ዳግ-ተመራማሪዎች (researchers)፣ ክብረትአምዎች (celebrities)፣ ወዘተ. እሚነግሩንን እንድንከውን እና በዘመንአዊ ጎዳና እንድንሰለጥን ብዙ ጊዜ ተነግረን ነበር። ጭራሽ ይህ የበዛ መስሎት እምቅ አቅም የለአው ጀማሪ፣ ኃይለእየሱስ ፈይሳ፣ “ፍቅር ተወደደ” ላይ እንደገለጠው፣


… የቆላውም መቶ እምዬ ይላትአል፣
የደጋውም መጥቶ እምዬ ይላትአል፣
ጣልያን አልወረረ ተኩስ አልተተኮሰ፣
በግልአችን ጉዳይ ቤትአችን ፈረሰ…


ብሎ አለ። እኔ የሀገሬን ችግር የመረመርኩ፣ መደረግ የአለበትንም የእማውቅ ነኝ፤ ሀገሬ ይህን አድርጊ-ታድርግ እየአሉ በእርግጥ ብዙዎች ይነግሩን አለ፤ ህዝብም የተለያዩ ጎራዎችን እየያዘ እርስበእርሱ እየተጣላ አለ። ታዲያ ለምን ሙግ. (ሙዚቃግጥም/lyrics) ያ የከፋ ሆኖ ሸተተው? የእዚህ ጽሑፍ ጽንሰሀሳብን የገለጠልኝ መስሎኝ በተረዳሁት መንገድ ወስጄው ለልኮትነት (reference) የወደድኩት እንደእሚከተለው የእኛ ስልጣኔ ጉዳይ እውነታው ስለሆነ ነው።
የተለያዩ አካልዎች፣ ይህ ይደረግ፣ እኔ ይህን ላድርግ እናንተ ተከተሉኝ እሚል ነው። ግን፤ ያ በራሱ ችግር አይደለም። ችግሩ፤ ያ ሂደት መደጋገሙ እና ንደ ተግባር አለመራመድአችን ነው።
በሌላ ቋንቋ፣ የስልጣኔአችን ግንባታ ጥረት፣ ሂደቱ በላይጠባቂ የለውም። መሰልጠን እሚቻልበትን ሁኔታ እሚነግረን እንደመብዛቱ፣ የተነገሩትን፣ የተከወኑትን፣ የአልተሳኩትን፣ ጥቂት የተራመዱትን፣ ወዘተ. ግን አብጠርጥሮ በማመሳጠር እሚይዝ እና እሚያመሳክርልን የለም። አንዱ መፍትሔ ተጀምሮ፣ ጥቂት ከተራመደ፣ ወዳቂ ይሆን አለ። ከአስር አመት በኋላ በእዛው መንገድ አንዳች ነገር ሲጀመር፣ እንደ አዲስ ነው። እሚያስታውስ፣ እሚያመሳጥር፣ እሚያነጻጽር፣ እሚያፎካክር፣ ወዘተ. የለም።
ስለእዚህ፣ ንብርብረ-መፍትሔን ከማንም አናይም፤ ማለትም የትም አንመለከትም። በፊት እንደ አልንው ስልጣኔ አትንጠለጠልም። ታሪክ እየሆነ እሚያልፈው ትውልድ አጠገብአችን ሳይሆን ለአንዴ እንደ ራቀ የአክል እሚለየን ነው። ከአለ እዛ ስንንቀሳቀስ ደግሞ፤ የየችግርዎችአችን ወሬ ድግግሞሽ፣ የየመፍትሔዎች ድግግሞሽ ብቻ ያጮለን እንጂ ወደ እሚነባበር የጠቢ (future) መነባበር መራመድ አይሳካልንም። በሌላ ቋንቋ፣ በካድሬዎች ቋንቋ፣ የትውልድ ቅብብሎሽ፣ እሚሰኘው ሀገር ግንባታ ንፋስ እንደሆነ ይቀር አለ።
የስልጣኔዎችአችን ውይይትዎች (discourses) እና እርምጃዎች፣ ልፋት እና ዉጤትዎች፣ በአለመገኘትአቸው፣ አዙሪት ቀላል ሆኖ አለ። ከ ቀኃሥ.፣ ደርግ፣ ኢህአዴግ.፣ ብልጽግና፣ ድረስ መንግስት ግልበጣ እና ሌላዎችም ለምሳሌ አማርኛ ይሻሻል፣ ኢትዮጵያአዊ እድገት ይመስረት፣ ወዘተ. ጥያቄዎች እየተደጋገሙ እሚሰሙ ናቸው። እንጂ፣ ወደ ቀጣዩ ምእራፍ እሚደርስ አንድም ነገር አንመለከትም። መቶ አመት በኢትዮጵያ ታሪክ ለምሳሌ፣ አማርኛን ለማሻሻል ተጥሮ አለ። መቼም አልተሳካም። ያ ከገረመን እና ውስጡን ከአየንው፣ መቼም መቶ አመት ስንንቀሳቀስ በተጀመሩ ጥናትዎች እየጨመርን አለመግፋትአችን ተጠያቂነቱ አይጎላም? ነገ እሚነሳው ተከራካሪ፣ ወይም ተሟጋች፣ አንድም ስሜትአዊ ብቻ እና የአለፈውን እማይፈልግ፣ አንድም ቢፈልግም በቀላሉ የተዘገበ እና ከምንበላይ ተደራሽ ነገር እማያገኝ ነው። ከአዲስ እየቧጠጠ፣ ለምን አማርኛ ወደ ተሻሻለ ደረጃው መለወጥ እንደአለበት በግሉ መመራመር እና በፊት የተከወነውን የመድገም ኃላፊነት አለበት።wordpressምዎች፣ መንግስት፣ መገናኛብዙሃንዎች፣ የስርአተትምህርት ይዘት፣ እንደ ከሁሉ አዲሱ (newest) ግኝት አይንቀሳቀሱልንም። የአለፈውን አይዘግቡ፣ በአለፈው አይቀጥሉም። ዛሬ የመጣ እና የተደረሰበትን ቸላ ማለት፣ ነገን የታሪክ መረጃየለሽ ፍትጊያ ማድረግ ነው። ንብርብረ-መፍትሔን አለመከወን፤ ነው። ያ፣ ዝማኔን ሁሉ በመርሳት ስልጣኔን አለማገዝ ነው።

ንብርብረ-መፍትሔ ለምን አልከሰት አለን? ከአለመከሰቱ የተነሳ ምን ችግርዎችን በጎን እየተመለከትን ነው? ይህ በሌላ ቋንቋ ብናሻሽልአቸው ምንምን ነገርዎችን እስከአሁን ከእነችግርነትአቸው ይዘን አለ እሚለውን ይነግረን አለ።


፩) ዜሮ ጀማሪነት፤ እንደየቱም ሀገር፣ የኢትዮጵያው ስልጣኔ ፍለጋው ከችግርዎቹ አሰሣ እሚነሳ እና ወደ መፍትሄዎቹ ዛሬ ተጠንስሶ በትውልድዎች እሚያዘግም ነው። ግን፤ ነገርዎችን ከአዲስ የመመስረት አባዜ ወይም አዙሪት አለብን። ታጥቦ-ጭቃ። የታጠበውን፣ የተሻሻለውን ወይም የተጀመረውን ወደ ኋላ ወስዶ ከ አላጨቀየን እና እኛው ከአላጠብን እሚሰራው ሁሉ የተሰራ አይመስለንም። መፍትሔውን መቀጠልን ወይም ማነባበሩን ልክ ከአዲስ እንደመመስረቱ አንጨነቅበትም፤ ወይም አናውቅበትም።
፪) እንቅስቃሴ አለመቻል ወይም መፍራት፤ መፍትሔዎች ሲጀመሩ፣ በእነእሱ ጨምሮ መቀጠል ከባድ ይመስለን አለ። መፍራቱ እንደ አለ፤ የአቅተንም አለ። አንደኛ ስልጣኔን ማንጠልጠል የለም። እንደ ቀረው የበሰለ አለም የሰራንውን እሚቀጥልበት የለም። አንድ ግኝት ሲገኝ ቀጣዩ ማስፋፋት ሳይሆን ወይም መተው ወይም ደግሞ ከአዲስ መመለስ እንጂ ማወሳሠቡ ይከብደን አለ። ከእርሻ እና እርባታ መሻገር እሚያቅተው ለእዛ ነው። አንዴ የተደረሰበት ስልጣኔ፤ ደግሞ ከአልተጨመረበት፤ ማደጉ አይከወንም። መፍራቱ ወይም አለመቻሉን ማቋረጥ አስፈላጊ ነገር ነው።
፫) በእናቅ(ልህ)አለን ባይዎች ተታላይ ወይም ተበይዎች መደረግአችን፤ ብዙዎች መፍትሔ ፍለጋ እሚነግሩንን ብንከተል እንጂ ሌላው አያስጨንቅአቸውም። ስለእዚህ እሚነግሩን ትንንሽ ወሬዎችን እና የእኛን የመከተል ፍላጎት መቀስቀስ እሚያስችልአቸውን እንጂ አንክሮትአዊ እና ስርነቀል ነገርዎች አይደሉም። በአጭሩ፤ ከቅርብ ወቅት ወደእዚህ፤ የስነውሳኔ አውዱን ማንም እንደአሻው እሚራወጥበት ሆኖ አለ፤ የአዋቂነት ማህበረሰብእነት አብሮን ስለሌለ፤ እጅግ የወደቅንበት መስክ ሆኖ። በማህበርአዊ ትስስር ድረገጽዎች እና የኢህአዴግ. አእምሮ እጥበት የተነሳም፣ በአጫጭር ትርኪምርኪ ወሬዎች ገንኖ መውጣት ተችሎ አለ። ገጣሚ ጌትነት እንየው፣ የተሻለ አንጻርአዊ መርቀቅ የአለጅት ላይ፣ በ መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓም. በተሰራጨ የ አርትስ ትመ. አየር እንደአቀረበው ግጥም “ይድረስ ለእኛ ለእኔ እና አንተ” በአለው ግጥሙ፣ የተማርን ወይም የምንመራ ለእምንል ለእኛ አደጋን እያመጣን ለአለን ግለሰብዎች፣ ደም እና እምባ እያፈሰስን ታሪክአዊ ሀገር እያቆሸሽን ነው እንጠንቀቅ እንደአለበት ግጥሙ፤ የዘመኑን አዋቂ-አጥ ስነውሳኔአዊ ገጸባህሪ እሚያስመለክት ነው። እንዲህ እሚገሠጹ መሪመሆንፈላጊዎች፣ ስልጣኔን አነባብሮ ለማለፍ ቀርቶ ሰብእአዊነትን መገንዘብ እሚችሉ አይደሉም እና አንዱ ችግር አዋቂዎች እና አዋቂ ስርአት አለመመስረትአችን ነው።
፬) እውቀትን እና ክሂሎትን በበቂ የአልከወኑ መሪዎች ማብዛትአችን፤ በዳዴ የተራመደ የችግርዎችአችን ምልከታ መከወን እንኳ ብዙ የእሚያስተምረን ዘመን ላይ ነን። መወለድ ቋንቋ ነው፤ ከእዛ በላይ ግን፤ በእዚህ ዘመን መወለድ ብቻውን የብዙ ዕውቀት ባለቤት አድራጊ ነው። እንደ ቀደመው ዘመን ድምጸመስኮት (radio) ገዝቶ ግርታ አድርጎ ስለእርሱ መልመድ የለም። ከልጅነት ጀምሮ በሰቤዎች (androids) ተከብቦ መኖር ግድ ነው። ስለ ብሔረሰብእዎች እኩልነት ሲነገር መጠራጠር ሳይኖር፣ ሁሉ እኩል እየተያየ ሲያድግ የእሚታደግበት ዘመን በመሆኑ ብዙ መመራመር እማይጠየቅበት ነው። በአጭሩ፤ ብዙ በትውልድዎች የተገነቡ የስልጣኔ ውብ ውጤትዎች – ወሮታው በዛብህ (ሊቀምሁርዎች) በመጋቢት 19 ቀን 2013 ዓም፤ አሀዱ ትመ. እንደተናገረው፣ 3000 ጥበብዎች በእየግለሰቡ ተገንብተውልን ቆጥረን በእማንጨርሰው የሰውልጅ ጥበብ ውጤትዎች የተከበብን ነን – እንጂ ብዙ እምንማር እና ከአዲስ እምናጠና የቆየ ትውልድ ውስጥ የአለን አይደለንም። ስለእዚህም፤ መሰረትአዊ ነገርዎች እንኳ እናውቅ አለን ተብሎ ይጠበቅብን አለ።
ዳሩ፤ አወቅን ብለው እሚነሱ እና የወል ነገርዎችን እንምራ ብለው እሚነሱልን ግለሰብእዎች የሰመጠ ነገርዎችን እሚያውቁ አይደሉም።
፭) ወደ ጠቢ ለመራመድ ስርነቀልነት እማናይ መሆንአችን፤ እምንመለከተው የ አፍንጫ-ስር-አፍንጫ-ስሩን ብቻ ከሆነ፤ እርቀን በስልጣኔ ጎዳና መራመድ አንችልም። ስርነቀልነት ወይም አንክሮትአዊነት እጅግ አስፈላጊ የመፍትሔ ቁልፍ ነው። በቀረ፤ እምንጓዘው አጭር መንገድ እና ስንቀጥልም እማይቻለን በመሆኑ ወደ አዙሪትነት እንጂ ቀጥታ መስመርነት አይሆነንም።

በደፈናው፤ ስለመሰልጠን ስንነጋገር፣ የተሞከርንውን ሁሉ ስህተት እንኳ ቢሆን፣ ዛሬ ድረስ ሊታወቅ እና ሊገኝልን እሚገባ ነው። በተገኘው የአኗኗር መንገድ ሁሉ፣ ወደ አሁኑ ቀን እምንደርሰው የአለፈውን እያሰስን መሆን መቻል አለበት። ያኔ፣ ወደፊትም እምንጓዘው የዛሬውን አለም ገጠመኙን እንደ መረጃ ለወደፊትአችን እየካብን ነው። ያ፤ የስልጣኔ ፍሬነገር አይደለም። የንብርብረ-መፍትሔ ገሀድ፣ የስልጣኔ ሂደት ወይም ጉዞ ነው። ሳንጓዝ፣ አንደርስም፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s