Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

አንድ እርምጃ ወደፊት ለኢትዮጵያ፡ የእምነት ተማሪዎች እና አባትዎችን ወደ ዘመንአዊ ትምህርት የማትመም ጉዳዩ

About how Ethiopia should take its religous education teachers and students into modern education system with easier approach on formality.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 27, 2021 GC.,

አሁንአሁን፤ በእዚህ አስርታት በተለየ፤ የተለያዩ ደግ መነሻ ለውጥዎች በ ሀገርአችን አሉ። አንዱ፤ የቤተክህነት ወይም ሌላ ሀይማኖት መምህርዎች ወደአለምአዊ ትምህርት መትመም ነው።
እስከ ቅርብ ጊዜ፣ መሪጌታ፣ ዲያቆን፣ ካህን፣ ዑስታዝ፣ ሼህ፣ ወዘተ. መባል የሀይማኖቱን ትምህርት በማወቅ ብቻ እሚያገለግሉት እና በእዛው እሚቀሩበት ነበር። ቢያንስ በደንብ በከፍተኛነት በነበረ ሀቅ። ዳሩ፤ በአለፈው አስርት፣ ብዙ የእምነት አገልጋይ የእምነት ትምህርት ምሩቃን ወደ ዓለምአዊ ትምህርት እየፈሠሱ ነው።
ዛሬዛሬ፤ “በሁለት በኩል የተሳሉ ሰይፍ” እያሉ እሚያስተዋውቁአቸው በአለምአዊ ትምህርት እና መንፈስአዊ ትምህርት አብረው በደንብ የተመረቁ ተማሪዎችን እንመለከት አለን። እነእሱም፤ በደንብ በሁለት የትምህርት ስርአተትምህርት የእሚወጡ እና እውቀትን እያሰባጠሩ በተሻለ አቅም ከአንድ ስርአተትምህርት ምሩቅ የተሻለ መብቃት ላይ የደረሱ ናቸው።

መንፈስአዊ ንቅአት ተይዞ የዓለሙን ትምህርት ሲማሩ ልዩጥቅም ከአለምአዊው ተማሪ የተሻለ የማግኘት እጅግ ግዙፍ ተጨባጭ እድል አለ። መንፈስአዊ ትምህርት የተማረው፣ የልቦና ንጽሕና፣ የመንፈስ ንቅዓት፣ የመንፈስአዊ አስተምህሮት ጥበብ፣ የመንታ ሚዛን ባለቤትነት፣ ወዘተ. ስለ እሚገኝ፣ በተሻለ እውቀትን ለማበጠር፣ ማመስጠር፣ ማነጻጸር፣ ማወዳደር፣ ማስማማት፣ ማግባባት፣ ማፍታታት፣ ማብላላት፣ መረዳት፣ ልብአድርጎት (internalization)፣ ወዘተ. በጠቅላላው በተሻለ ልህቀት ስለእሚያገኝ፣ በዓለሙ ትምህርት የመርቀቅ እድል አለው።
አብሮ ግን አንድአንድ ከፍተኛ እምቅአደጋዎች አሉ። አንደኛ የቤተክህነትም ሆነ የእስልምና እምነት ትምህርትዎችን መማር፤ ወደ መንፈስአዊ ስብራት እና ትጋትአማአዊነት (commitment)፣ ወይም ቅንአት የአመጣ አለ። ወደ የዓለሙን ትምህርት ሲገባ ዘመንአዊውን መናቅ ወይም ማንቋሸሽ ይኖር ይሆን አለ። ሁለተኛ፣ ከመንፈስአዊነት መጣላት፣ መንፈስአዊውን አለም መልቀቅ ወይም ግጭት ውስጥ ወይም ስነልቦና ቀውስ ውስጥ መግባት ሊኖር ይችል አለ። ከአልተዳደረ፣ ይህ ችግር ቀውስ ሊሆን እሚችል ነው። ሶስተኛ፣ ከመንፈስአዊ ትምህርት ወደ አለምአዊ ዳግምርምርዎች (reaearches) እሚገቡ፣ ከፍተኛ የሊቅአዊ (academic) ቅርጸት መላበስ ችግር ይገጥምአቸው አለ። ሊቅአዊ አለም የራሱ ስነልቦናዎች፣ ደንብ እና ወግዎች አሉት። ለምሳሌ ለሀሳብዎች ክፍት መሆን ሁሌ እሚያሻ ነው። ግን በመንፈስአዊ ትምህርት እሚመጡ አዳዲስ ሃሳብዎችን በክፍት እይታ ለማስተናገድ እሚቸግርአቸው እና የእምነት አስተንህሮቱ አንድ የተነገረ ነገርን ሌላ መሆን አይችልም ውጉዝ ነው እሚለው ሃልዎታ (attitude) ሊያስመለክቱ ይችል አሉ። ለምሳሌ፤ የግዕዝ ምሁርዎች አማርኛን እንደ ግእዝ ወስደው የመመልከት እና ከአለ ቋንቋአዊ አመክንዮ ፊደልገበታውን አትንኩት ብለው ይሞግቱ እና ተጨማሪ ማብራርያ ግን አናቀርብ ይሉ አለ።

በ ሚያዚያ 17ኛው ቀን 2013 ዓም እኩለቀን ስርጭት፣ ረጋ የአሉት፣ ባዬ ይማም (ሊቀልሂቃን) በ አዲሱ የ ኢሳት. ትመ. የንባብ ክሊኒክ መርሐግብር ለ አዘጋጁ መንግስቱ ታደለ ከተሞክሮአቸው እንደ አወያዩት፣ ከግእዝ ትምህርት መልእክተ ዮሐንስ አጥንቶ የመጣ የተሻለ የአለምአዊ ትምህርት መብቃትን የእሚለውን መሆኑን ነግረውት አለ። በተለይ፤ በእነእሱ ዘመንዎች፣ የመገናኛብዙሃን አንባቢዎች መልእክተ ዮሐንስን እና ሌላውንም በአራት ቀለም ድምጽዎች የቆጠሩ ስለነበሩ፣ ድምጽአቸውን ቀጥረው መረጃዎችን የማንበብ ጊዜአቸው እጅግ ለዛ የነበረው እና ተወዳጅ እንደነበረ ገልጠውለት አለ። በሌላው ጉዳይ ሊያበረታአቸው እሚችል እንደሆነ በመገመት ብቻ አልፈው በንባብ ክሂሎት ግን ግእዙን የአጠናው ቄማሪን እሚያክለው እንዳልነበረ ግን በቁርጥ ምስክርነት አድርገዋል። እሚገመተው ስለእዚህ፣ ዛሬም ይህንን ማስከወን እሚቻል እና ከግእዙ የእሚመጡትን በማገዝ የላቀ ጥራትን ለሀገር ማበርከት እንደ እሚቻል ነው።

ልዩጥቅም
የመንፈስአዊ ትምህርት ተማሪዎች፣ ዜማ፣ ፊደል፣ መጽሐፍዎች፣ ትርጓሜዎች፣ ምስጢርዎች፣ ቅኔዎች፣ ወዘተ. ተማሪዎች ናቸው። በትሁት ስነልቦና እና ፀሎት አብረው በመጠመድ፣ ይህን ሲማሩ አለእረፍት እና ለፍፃሜ ደረጃ በመብቃት እና ብዙ በማህደረትውስታ (memory) በመሸከም ነው። ስለእዚህ፣ በዓለሙ ትምህርት በአጭሩ የማወቅ እና ግላጤ ቶሎ የመከወን አቅም አሉአቸው።
በቋንቋም ቢሆን በብዛት ግዕዝ እና አረብኛ ስለእሚያጠኑ፣ የቋንቋ ብቃትአቸው እጅግ የበረታ እና ለትምህርት እውቀት አሰሣው ጠቅላላላ አእምሮአቸውን (IQ) እሚጨምርልአቸው ነው። በቶሎ ተምረው፤ በተሻለ ለስኬት የመድረስ አቅምአቸው ከፍተኛ ነው።

ቢማሩ ምን ጥቅምዎች አሉን?
፩) በአሁኑ ሰዓት ለሀገር አንድ ሸክም፣ የተማሩ ዜጋዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ነው። የተማሩ ብቻ ሳይሆን በላቀ መንገድ የእሚወጡ ምሁርዎችን ቶሎ ማጋበስ እሚቻል ነው። እዚህ ላይ ለአስተዋለ፤ አብዛኛው ተፅዕኖአማ የሀበሻ ምሁር ከሃይማኖት ትምህርት የወጣ ነበር። እነ ሀዲስ አለምአየሁ፣ አያልነህ ሙላት፣ ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ቶማስ ወልድ፣ በአሉ ግርማ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ በዕውቀቱ ስዩም፣ ይስማእከ ወርቁ፣ ሮዳስ ታደሰ፣ እጅግ እና እጅግ ብዙ በእየሙያው በአቅምአቸው ለሀገርአቸው የተጠበቡ፣ በመንፈስአዊ ትምህርት የተሻገሩ እና ወደ አለምአዊ ትምህርት የመጡልን እንቁዎች ናቸው። በተለይ፣ ከቀኃሥ. እና ደርግ ዘመን የነበሩ ምሁርዎች እጅግ ከፍተኛው ቤተክህነትን የአልዘለቀ አይደለም ነበር። የተማረን ዜጋ ከማፍራት የጥራት ምሁርን ማፍራት የእሚታቀድ ነው። እምንመለከተው የተሳካለት የልሂቃንዎች ዝርዝር ደግሞ በብዛት መንፈስአዊ ትምህርቱን የከወነ የአለምአዊ ምሁሩን ነው። ስለእዚህ፤ ይህን ሀገር በጠቢው ለማሻሻል፣ አንድ የምር ትልምአግጣጫ (series policy) በእዚህ መሰራት አለበት።
፪) ሀገርበቀል እውቀት እና ስልጣኔን፣ ወግ እና ልማድን ሰይለቅቁ ወደ ዝማኔ ለመምጣት እማይሞከረው የውይይት አይነት የለም። ምንአልባት አንዱ ይህን ማሳኪያው መንገድ፣ በቀጥታ ዘመንአዊ ትምህርቱን የተማረ ትውልድ ከመፍጠር በተለየ ደግሞ፣ የመንፈስአዊ ትምህርቱን የተማሩትን ማካተት ነው። እነእርሱ ዘንድ ሀገር የመጠበቁ ጉዳይ አብሮ ጭራሽ ከሀገርአዊ ቅርስ እና ጥበብ ጋር ስለእሚገኝ፣ ዘመንአዊውን ትምህርት ቢማሩ፣ ሲመጡ እሚሰጡን ውጤት እንደ ሮዳስ ታደሰ (ሊቀምሁርዎች) ለምሳሌ ሀገርአዊ የጥንት እውቀትዎችን የእሚያያይዝ ወይም ቢቢያንስ ባለመዘንጋት እሚያነሳ የሆነውን እንጂ ቀጥታ የውጭ ትምህርቱን አይደለም። ስለእዚህ፤ ሀገርአዊነትን ለስልጣኔ ለማላበስ በእሚለው ወደተግባር ጠብአልል ለአለ ፍትጊያ መፍትሄ አንዱ ይህ ሀገርበቀልነቱን የተካኑትን ወደ ዓለምአዊ ትምህርት ማቅረቡ ነው። ያ፤ ወደ አለም ትምህርት ሲያቀርብአቸው፣ የመንፈስአዊ ትምህርት ተመራቂዎቹን ወይም ተማሪዎቹን፣ አብሮ የጠራው ሀገርበቀልነትአቸውን ጭምር፣ የእኛን አንድ ጭንቀት ነው። ሀገርበቀልነትን መርጃ አንድ መንገድ ይህ ነው።

የመንግስት እና ሀይማኖት ትምህርት ተቋምዎች ምን ይከውኑ፤
፩) በቅርቡ፤ እስከ ሶስተኛ ክፍል አዋቂዎች ወይም ኢመደበኛ በሆነ መንገድ የተማሩ ሰዎች መጥተው በመፈተን ከአለፉ የ ሶስተኛ ክፍል አቻ ዉጤት ማረጋገጫ እንዲያገኙ እሚያስችል ሂደት – “ትምህርት ለብርሃን” የተሰኘ ተግባሬት (project) – ተግባራዊ ተደርጎ፣ የእሚመለከተው ተቋም በማስፈጸም እንደእሚገኝ ተገልጦ ነበር – በ መሀንዲስ ሊቀምሁርዎች ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ምኒስቴሩ። አንድ የሀገርአችንን ነባርአዊ ሀቅ የአገናዘበ እና ሀገርበቀል ችግር እሚፈታ እርምጃ በመሆኑ ይመሰገን አለ።
በእዛ መሰረት፣ ያንን በተለይ ወደ ቆሎ ተማሪዎች፣ ዲያቆንዎች፣ ሃጂዎች፣ ቄስዎች፣ ወዘተ. በመውሰድ፣ እድሜአቸው ስለገፋ ተስፋ ከመቁረጥ እና ከመቅረት ወደ ዓለምአዊው ትምህርትም እንዲገቡ እንዲደረግ ማገዝ የአስፈልግ አለ። ተፈትኖ ሶስተኛ ክፍል አቻ ዉጤት መቀበል የተፈቀደበትን አሰራር በጥቂት ሞጁልዎች በማገዝ፣ በአንድ እና ሁለት ቀንዎች ትምህርት አጭር ክለሳ አብሮ በማገዝ በቀላሉ መፈተን እና መመዝገብ ቢቻል ደግ ነው። ከመፈተኑ ቀድሞ፣ የማንበብ እና ማስላት ፈተናዎቹን ጥቂት የማገዝ እና መመዘኛ (standard) የማሳወቅ አጭር ሂደት ቢቀድመው ይመረጥ አለ።
ሁለተኛ፣ ለቆሎ ተማሪዎች እና መሰልዎችአቸው፤ እስከ ስድስተኛ ክፍል በርቀት በአሉበት ቢያነብቡ እና መጥተው ቢፈተኑ ስድስተኛ ክፍል ፈተናን እንዲፈተኑ አስቻይ ተመሳሳይ ስርአት ቢዘረጋልአቸው እጅግ አልሚ ነው። የእውቀትአቸው ልክ እና የእይታአቸው አድማስ ከመተለቁ የተነሳ፣ ተፋጥነው እና ተበረታትተው እንዲፈተኑ ያንን መፍቀድ ተገቢ ነው። አብሮ እና ቀድሞ ግሞ ግን፣ የእዛ ፈተና አጭር ሞጁልዎችን አዘጋጅቶ በእየቤተክርስትያኑ፣ መስጂዱ፣ ገዳም እና አድባራቱ ማከፋፈል እና ሁሌም የስርአቱ አካል ማድረግ አስፈላጊ ነው። በርቀት የአሉ ቆሎ ተማሪዎች እስከስድስት ለመማር አጭሯን ሞጁል አንብበው በቅተን አለ ሲሉ መጥተው በጠራ ደረጃ ተፈትነው ማለፍ ከቻሉ ወደ ሰባተኛ ክፍል ለማስገባት እንዲቻል ይህ አጋዥ እና ጠሪ ነው። አመክንየለው፤ እጅግ የረቀቁ ምሁርዎች በእየእምነቱ መገኘትአቸው ነው። እነእሱን ከአንደኛ ክፍል ወይም ከሶስትም ቢሆን ጀምሩ ከማለት፣ ቢያንስ ሰባተኛ ክፍል እንዲገቡ ትልም ቢፈቀድ፣ በአጭሩ ወቅት ተበረታትተው በመዘጋጀት ወደ ትልቅ ነገር እንዲደርሱ አጋዥ ነው። የአሉትን ሊቅዎች፣ ወጣት፣ እስከ ጎልማሳ በመማር ፍቅር ግን ከ አንድ በመጀመር ስንፍና በአሉበት እንዳይቀሩ ይህ ትልቅ መንገድ ነው። መታወቅ የአለበት፣ ተምረው ከአልቻሉ እሚወድቁ እና በግልአቸው ወደ ቀጣይ ክፍልዎች እሚሄዱ ስለሆነ፣ የጥራቱ ጉዳይ እንደእማያሳስብ ነው። ዋናወወ ጉዳይ፤ ለኢትዮጵያ ማህበረሰብእ እሚሆን ገሀድ እስከ አለ በእዚህ መሰል አያያዝ ልንጠቀምበት እና የብዙዎችን ህይወት አሻሽለን ሀገርም ልንጠቅምበት እሚገባው መሆኑን ነው።
የሐይማኖት ትምህርቱን አስተማሪዎች ደግሞ፣ አብረው ይህን ስርአት መከራከር፣ ማገዝ፣ ማበጀት፣ መጽሐፍዎቹን (ሞጁልዎችን) ማራባት፣ ማንበቢያ እና መፈተኛ ጊዜ ማቅረብ፣ ወዘተ. እሚገባአቸው ነው። ከስርአቱ ተሳስረው፣ በማገዝ፣ ተማሪዎችአቸው በዘመንአዊ ትምህርቱም እንዲገፉ እድሉን ለማቅረብ ጉዳዩን መመርመር እና ማስመር’ አለብአቸው። ልጅዎችአቸውን በሁለት መንገድ ቀርፆ እንደለመዱት አንድም ለሀገር አንድም ለእምነቱ ማዘጋጀት እና ቀጣዩን ሀዲስ አለምአየሁ ዘመንአዊ ትምህርት ከራቀአቸው ታዳጊዎች ማትረፍ እንዲችሉ ማሰብ ቢችሉ መልካም ይሆን አለ። የሐይማኖት ትምህርቱን የተማረውን አረጋግጦ በመፈተን፣ በአለምአዊ ትምህርት ከአልተመዘገበ፣ በእድሜው መግፋት ከእሚቀር አለምአዊ ትምህርቱን ፈትኖ ክፍያ እሚያቀርብ ማዳንን መከወን እሚቻል ነው።
በደፈናው፤ ዳኛአቸው ወርቁ አደፍርስ ላይ (ገ.161) እንደጠቆመው በኋላም ደርግ እንደተያያዘው መሰረተ ትምህርት ጉዳዩ፣ ትምህርት በእድሜ እንዳይነጻጸር እና ከመማር እንዳይቀር፣ በመዘናጋት፣ ቸልታ እና ምንያደርግልኝ ደለ በማለት በእድሜም መግፋት፣ መማሪያ አማራጭ እና አቅም በማጣት፣ ተስፋ በመቁረጥ፣ ወዘተ. ከአለምአዊ ትምህርት እሚፋቱትን ነገርግን ይህን እድል ቢያገኙ፣ ትልቅ ደረጃ ላይ እሚደርሱትን መድረስ እና ለሀገር መገልገያ ማድረግ የአስፈልግ አለ።
ብዙዎች ከመርጌታነት፣ ዲያቆንነት፣ ወዘተ. በዘገየ እድሜ ወደአለምአዊ ትምህርተመጥተው በተለያዩ ደረጃዎች በአለምአዊ ትምህርት ትልልቅ ስኬትን በአንፃርአዊነት በማግኘት አገልግሎት በተሻለ ደረጃ ለመስጠት ሲበቁ በብዙ ስፍራዎች ተመልክተን አለ። ይህንን፣ በብዙ ከተማዎች እየታየ የአለ እና እየተሻሻለ የመጣ ሀገርአዊ እውነታ በእራሱ የሀገርአዊ የእውነታ ስሪትነቱ (version) በአዲስ አውድአዊ መልስ በመንከባከብ ውጤት ማግኘትን መከወን እሚቻል ነው። በእርግጥ፤ ሀገርበቀልነት በውይይት ደረጃ ተደጋግሞ በተነሳበት ዘመን ይህንን መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ፤ ዘመንአዊ ምሁርነትን ማብዛት እና ሀገርበቀልነትን ማደላደል፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s