Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የኢትዮጵያ ትልቁ አደጋ፡ እጅሰጪነት

About the utter failure to live like a sane human being in political and national life.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 30th 2021 GC.,

፩) ጠባቂአዊያን በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያው ማህበረሰብእ ዉስጥ ጠባቂአዊያን እሚሰኙ አባልዎች አሉ። “አንድ ቀን ኢትዮጵያ ትልቅ ትሆን አለች፤” እሚል መርህ ታቅፈው በመጠበቅ ይኖር አሉ። እንዴት ትልቅ ትሆን አለች? አይጨነቁም። ወይም መልስ ቢያበጁም፤ ዳሩ፣ እነእሱ ግን የትግል ወይም ሂደቱ አባል አይደሉም። የፍፃሜው እንግዳ ግን ናቸው። መጥተው ትልቅ ኢትዮጵያን ለመቀላቀል እሚሹ እንደሆነ እርግጠኝነት እንጂ ሌላ እሚያውቁትን አያብራሩም። አንድ ቀን፤ በትንቢት፣ በእምነት፣ በስልጣኔ፣ ወዘተ. ብቻ ሀገርአችን ታላቅ ትሆንልን እና ድንገት እኛም እዛ ውስጥ እንገኝ አለን። ሌላ አናውቅም። ስለ እዚህ፤ ጠባቂአዊያን ተባሉ።
ጠባቂአዊያን፤ የአልተሳሳቱት አንድ ቁምነገር ነገር ብቻ ነው። ያም፤ ሀገር ማደግ እና መለወጥ እሚችል መሆኑን ነው። መንገዱ፤ የሳቱት፤ ግን ጥበብ፣ እና ትግል ነው። ተዘርፍጦ እሚጠብቁት የክረምት ዝናብ አይነት የሀገር ስልጣኔ አይገኝም። የቱም ሀገር ያን አላገኘም።

፪) ለጠባቂአዊያን እሚደረግ የመንግስት ደስተኛ ድጋፍ እና ሲጀመርም አባትነት
ግን፤ የእዚህ ጎራ-ጠባቂአዊያን በሽታ አጭር አይደለም። በብዙ መንገድ የታወኩ ናቸው። በ 2010 ዓም. ጠሚ. አብይ አህመድ (ሊቀምሁርዎች) ሲሾም ጮቤ እረግጦ (ሽፋኑ መለስ ዜናአዊ፣ ሳጥናኤል ቦታ ሆኖ ሚካኤል ቆሞበት፣ አጠገቡ ፈቅ ብለው በመለስ ስቃይ ሳይጨነቁ እነ አብይ አህመድ (የእሱ ቡድን እሚሰኙት እነ ለማ መገርሳ፣ ወዘተ.) የሠራዊት ልብስ ለብሰው ቆመው እያዩን እሚያሳይ ነው – የ ዳኛቸው ወርቁ ብሉይ (classic) አደፍርስ ላይ ክብረት የሳለው የቅዱስ ሚካኤል ምስልን የአስታውስ አለ (ገ.164)) የታተመ መጽሐፍ፣ ኢትዮጵያ በክፉ ድብቅ ቡድንዎች እምትታደን ናት ብሎ ‘ካርዶ አብ ኬዎ’ (From Chaos, Order) እሚሰኝ ነቢበ-ሴራ (conspiracy theory) በመተንተን ይጀማምር አለ። ዋና ሃሳቡ ሁሉንም ህዝብ አስጨንቅ፤ ሲጨነቅ ለጥ ብሎ ይገዛልህ አለ እሚል ነገርን እሚከተሉ ህቡዕማህበር (secret societies) እያስጨነቁ አለሙን ይዘውት ኢትዮጵያንም መቆጣጠር ይፈልግ አሉ ይል አለ። ይህ የ ህቡዕማህበር መርኆዎች ብቻ አለመሆኑን እና የ ኢህአዴግ. ጭምር እንደሆነ ይነግረን አለ። ያ፤ በአጭሩ ደግሞ፤ የምስጢር አሰራር ሳይሆን፤ የአምባግነና መንገድ ነው። በ ኢህአዴግ. አስተዳደር ስር ሳይሆን በአብይ አህመድ አስተዳደርም (ብልጽግና) ጭምር የእሚገኝ ነው። በስነውሳኔ ዳግ-ምርምር (political research) ደግሞ፤ ሰላምሻጭነት በእሚል ተተንትኖ አለ። ሰላምሻጭ መንግስት እራሱን ተፈላጊ ማድረግ አይችልም። መንግስትአዊ ብቃት የለውም። ስለእዚህ፣ በምትኩ ሰላም ይነሳ አለ። ቀጥሎ፤ ሰላም ይቸበችብ አለ። ሰላም ስለተወደደ፤ የስነውሳኔ ገበያው ላይ ልቅ ዋጋ ይዞ በህዝብ ይሸመት አለ። ሌላ መስራት እሚቻለው ስለሌለ፣ ይህ አስተዳደር፣ ሰላሙን አስወድዶ (ሰርቆ) በመልሶ መሸጥ የዉሸት ፍላጎት አስመርቶ የውሸት መልስ በመስጠት፣ እውነተኛ የመንግስት ስራውን ይዘነጋ አለ። በሰላም ማስከበረጀ ሂደት እና ስም ደግሞ የአሻውን አምባግነና እና አፈና ይፈጽም አለ። ከጭንቅ እና ሰላም ማጣት የተነሳ ሁሉም፣ ሰላምን እጅግ ይፈልጋት አለ። ከእዛም ሰላም ይነገድ እና ሌላ ልማት ከመጠየቅ ይልቅ ገብተን እንውጣ ከእዛ በቃን እሚሰኝ ወሬ ይናፈስ አለ። ከጭንቅ መደበኛነት ይወለድ አለ። From chaos comes order.
ይህን፤ ወጥመድ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ. እጅግ አስምጦ ተክሎት አለ። አብይ አህመድም ከቶ ከማስተካከል ጭራሽ እረድቶ እና አጠናክሮት አለ። በአጭሩ፤ መንግስትን መሪ ተቋም ወይም ድርጅት፣ በሺህ ዘመንዎች የተመደበለት አመክንዮ-ዘ-ህላዌው (reason d’etre)፣ ሰላምን አለማስነካት ነው፤ እንጂ አስጨንቆ ወይም ለጭንቀት ጋብዞ ሰላምን መልሶ መሸጥ የዘመኑ መንግስትነት መገለጫ አይደለም።
የኢትዮጵያ የአለፉት ሰላሳ አመትዎች መንግስት ህዝብን እሚስተዳድረው በማታለል ነው። ሰላምን አናግቶ (በሽታ ፈጥሮ) በመድኃኒት መሸጥ (ሰላም ማስጠበቅ) ዘዴአማአዊነት (strategy)። ያ፤ ለጠባቂአዊያን አንድ ድጋፍ ነው። ምንም የመሰልጠን ሃሳብ እና ትልም ከመንግስት አይቀርብልአቸውም። ስለእዚህ፤ ነገ የተሻለ ነው እሚሆነው በእሚል ዛሬ ውሎ በማደር እሚረኩ ሆነው አሉ። በሌላ ቋንቋ፤ ሰላም በማግኘት ውሎ የማደር ነገር ከተረጋገጠ፤ እድገቱ ግድየለም ይቅርብን ማለት የጠባቂአዊያን መገለጫ ነው። አንድ ቀን እናድግ አለን ብሎ ገብቶ መተኛት፣ ነገም ተነስቶ ያንን ተናግሮ መተኛት፣ በእዛ መንገድ ዘመንዎችን መኖር፣ ፍችው፤ ማደጉ ይቅር፣ ሰላሙ ብቻ ይሁነኝ እንደ ማለት ነው። ማረጋገጫው፤ የሆነ ወደፊት ላይ ሀገር ከአደገች፣ ያንን እሚከውነው ሌላ ትውልድ ነው ማለት ነው። እስከ እዛ፣ ማደጉን እኔ አልከውነውም እሚል ግልጥ እንደምታ (overt implication) እንመለከት አለን። ተስፋየለሽነት፤ የአምላክ ስጦታ የግልአችን እና አብሮን የተወለደ ሰላምአችንን ስንነጠቅ፣ ግድየለም በሀገርአችን ቢሆንም እንግዛው አስብሎን አለ፤ እዚህ ጎራ ከተገኘን። አባትአችን አስጨንቆ የያዘን እና የወለደን ይህ አምባግነና፤ ሰላምሻጭ መንግስት ነው ማለት ነው። ዛሬ መሰልጠን ስለአቃተን ማደጉን ባንችልም፣ ተሸነፍን ለአለማለት እና ለአለመሸነፍ በኢትዮጵያአዊ መገለጫ ወኔአችን “የሆነ ቀን እንለወጥ አለን” ብልን ግለአታሎት እንከውን አለን ማለት ነው።


፫) የባሰ ዝቅታ፣ እጅ ሰጪነት
ተስፋ ትልቁ ዋጋአማ ጉዳይ ነው። የ አሌግዛንድር ዱማስ፣ The Count of Monte Cristo፣ እፎይታ ተብሎ የተተረጎመልን፣ ማብቂያ አረፍተነገሩ እንደ ሴራው ውብ ነበር።
“ፍላጎት ተሟልቶ እፎይ እስኪባል ድረስ የሰውልጅ ብልሃት በሁለት ቃልዎች የታጨቀ ነው፤ ትእግስት እና ተስፋ”
አንዳንዴ፤ መሸነፍ እንደሆነው፤ “ቢያንስ ነገ እናድግ አለን” እሚለው የጠባቂአዊያን ግለአታሎት፤ በአንድአንድ ዐውድዎች ተስፋ መስሎ ይገኝ አለ። አመክንዮው፤ እጅግ የዘቀጠ ኢትዮጵያአዊ ስነልቦንታ (psyche) አለን – እጅ ሰጥቶ መኖር። ጠባቂአዊያን እጅ ሰጥተው እሚኖሩ ናቸው። ግን፤ እማያሳድዱት ተስፋ አልአቸው። እጅሰጪዎች ግን፣ ሰላም ገዢዎች ከሆኑ በኋላ፤ ማደጉ አይመለከተኝም፣ ወደፊት እናድግአለን አልልም ባይ ናቸው። ልክ እንደሆነው፣ ለአፍ የአክል እንኳ፣ አያገባአቸውም። በመሸነፍ፣ ምኑም ምኑም አይመለከተኝም ባይ ናቸው።
እነእሱን እንደ ዜጋ እንኳ ለመቁጠር አይቻልም። ሰነፍ ቋሚ ነዋሪዎች (permanent residents) ናቸው። አይመለከተንም ከአሉ በኋላ የምር አይመለከትአቸውም፤ ምኑም አያገባአቸውም። ዉሎ ማደር ስኬትአቸው ጫፉ እና መነሻውም ነው።
ኃይለእየሱስ ፈይሳ፤ ከዘፈንዎቹ አንዱ እሚስብ ትግበራ የከወነበት፣ “ፍቅር ተወደደ” እሚለው ነው። ሀሳቡን በደፈናው እንደ ለሀገር ተጨነቀ ሰው እምንመለከተው ነው። ዳሩ፤ ብዙዎቹ የቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈንዎች እንደሆኑት የጠባቂአዊያን ጎራነትን ግን ስቶ ወደ ዝቅጠተ-ዝቅታ እራሱን እሚያሽቀነጥርበት ስንኝዎች አሉ። ምርር የአለው የሀገር እና ህዝብ ሁኔታውን ተችቶ መፍትሔ ስላላገኘ ግን፣ የሰሎሞን እና ዳዊት ትንቢት አለሽ ታላቅ ትሆኝ አለሽ አንድ ቀን ከማለት ቦዝኖ ችግሩ ስለጠና እንሰሣአዊነቱን ተቀብሎ የተናገረው ይህ ነው።


“አንድ እንጀራ እራቴ ተቀመጭ በቁና፣
ማታ እበላሽ አለሁ እራቤ ሲጠና፣
እራቴን ከበላሁ ደጄን ከዘጋሁ፣
ሰላሙን ከ አገኘሁ፤
ሌላ ምን እፈልግ አለሁ፤”


እንደእዚህ እጅ ከመስጠት፤ እና ወደ ቀለምአማ ጠቢ (colorful future) ከመፋታት የበለጠ መውደቂያ መንገድ የለም። ይህ ስንኝ በእርግጥ በመልካም ዘፈን እና ሙግ. (ሙዚቃግጥም / lyrics) መሀከል የተገኘ ስህተት ነው። ግን፤ ያቺን አንድ እንጀራ እንዴት በቁና አስቀመጣት? ከየት መጥታ ነው? ለመተኛት እሚያስበው ያቺን እንጀራ ማን ሰጥቶት ነው?
የአምባግነና ቃልአቀባይነቱ የአልተወላዳው ኢትመ. (ETV)፣ ቱልቱልቴን (propaganda) እንደለመደው ሲያቀርብ፣ እሚለው አንድ አዲስ ስልት በ ብልጽግና አስተዳደር እንኳ የአልተዛባው የመለወጥ ፍላገለት ወሬ በመጋቢት ፳፩ ቀን ፪፻፻፲፫፣ ዓም. እንደ እሚከተለው ተነብቦ ነበር።

MP3 (ዘገባውን ለማድመጥ)

የተቀረጸውን ባይተይብም፣ የተነበበው ዘገባ በአጭሩ ግን፣ የ ታኢህግ. (GERD)፣ ለድሃድሃ የእንጦጦ አካባቢ እንጨት ለቅመው እንጀራ በመሸጥ እሚተዳደሩ ኢትዮጵያአዊያን እናትዎች በዘጋቢ ጉብኝት ተደርጎልአቸው የተናገሩት ሲሆን፣ የጋጋሪዋ አይንዎች እንጀራ ለማምረት በመሰቃየት እንደሆኑ እንባ ቀረብ አድርገው በመቅረጽ እያስመለከቱበት እሚቀርበው ነው። ሌላው ሁሉ ሰብእአዊ ልእልና ቢቀር፤ አንድ እንጀራ በልቶ ሰላም ከሆነ በቃኝ እሚል እንዴት ከብልጽግና ቱልቱልቴአዊ ዘገባ እንኳ የአነሰ ይሆን አለ። መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ሊቀምሁርዎች) እንደእሚሰድበው (ታች እንደ አለው) የዜጋ አይነት ከመሆን ወደ አምባገነኑ አስተዳደር ተጠይነት መዛወሩ የከበደ ውድቀት ነው።
በእርግጥ፣ ዘፋኙ ይህን ግድየለሽነት፤ የ ሰላም-ገዢነቱ አኗኗርን አስገድዶት እንደ ከወነው የአስመለክተን አለ። ጸሐፊውን እንደጠቀስንው፤ ህዝብ በስንፍና ፣ መንግስት እና ተቋምዎች በአምባግነና አስጨንቀውት ከጭንቀቱ እጅሰጪነቱን (order from chaos) አግኝተው እነእሱ ግን ከሰላም በላይ በፈላጭቆራጭ እና ሙስናአዊ ደስታ ሰክረው አሉ። ቅሬታዎቹን ዘርግፎ ዘርግፎ፤ እጅዎች እግርዎች እንደበቀሉለት ፍጥረት እንዲህ ላድርግ በቃ ከማለት፣ በቀኑ መጨረሻ ሆዱ ብቻ እንደ አሳሠበው፣ በሰላም ከአንድ እንጀራ ጋር ከተገኘ በቃኝ-በቃኝ መልካም ኑሮ ብሎ ትግሉን ይቋጭ አለ።
አኗኗሩ፤ ከመስነፉ የተነሳ እንጂ፤ ሮዳስ ታደሰ ደጋግሞ እንደአሚገልጠው፤ ይህን መልእከት እሚሰድበው ይሆን ነበር። እኛ የባጃጅ አቀስቃሽ (motor)፣ ኢትዮጵያ የቻይና-ትራክ (Cino-Truck) አቀስቃሽ ፈላጊ ነን፤ በልተን ከአደርን እንደ እንስሳ እምንደሰት ከሆንን ምርጧ ኢትዮጵያን አንመጥንም…እየ አለ ብዙ ጊዜ ይናገር አለ፤ (ባላገሩ ትመ./Tv አንድሮሜዳ መርሐግብር፤ ከ ስራ-ጓደኛው እና አብሮ-ጸሐፊው (co-authour) ጌትነት ፈለቀ (ሊቀምሁርዎች) ጋር፤ መጋቢት አጋማሽ እንደተናገረው)።
ይህ ከሰብእአዊነት የመነጨ ቁጣ፤ ለተሻለ ስልጣኔ በእሚታትሩ እሚነገር ብቻ አይደለም። መደበኛ ሰብእአዊነትን መለኪያ መስፈርት ነው። ከእዛ የአነስ ህልም እና ተስፋ ወይም ላጎት መያዝ ሰውነትን እሚያመክን ነው። እጅሰጪነት። ኢትዮጵያ ከእምትፈልገው እልፍ ነገርዎች መሀከል እማትፈልገው አንድ ነገር ሊበልጥ ይችል አለ ከተባለ፣ በእርግጥ ያንን አይነት አንድ እንጀራ እንደመና የወረደለት መስሎት ሌላ ምን እፈልግ አለሁ እሚል እጅሰጪነት ነው። አሳዛኙ ነገር፤ ነገ ሲነቃ በሽታ የአቃወሳት እንጀራ ጋጋሪ በግብፅ መጉዳት እና መጋገር አለመቻሏ መረጋገጡ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲያ በመተኛት እና በግድየለሽነት በመኖር፣ መሬቱም ጤፍ አብቃይነቱ ወይም ጤነኛ ጤፍ አብቃይነቱ እሚቆምበት ጊዜም እያንዣበበ እና በንቅአት ከአልታገሉ፤ ሲበላው የነበረውም እራሱ ጤነኛ ጤፍ ስለመሆኑ ምንም አለመታወቁ ነው። የመጨረሻው የእኛ ዝቅታ፤ በድሃድሃነት ጀርባ ተሽቀንጥሮ እሚገኝ ነገር፣ ጠባቂአዊነት እንኳ የሌለበት እጅሰጪነት ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s