Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ለኢትዮጵያ አዳኝ-ሚናው

About how English is important for Ethiopians to attain mental excellence as a benefit from knowing two languages. Given Amharic and other domestic languages except Geez are too poor, and English is already fine and family, questions of excellence to be attained from knowing more than one quality languages can be balanced in this approach.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 28 of 2021 GC.,

ሁለት ቋንቋዎች መልመድ ከሁለት አንደበት ክሂሎት በላይ ነው። ሁለት ቋንቋዎች የእብስልስልታ (intelligence) መጠንን ማተለቂያ መንገድ ነው። ያ፤ እጅግ ከፍ የአለ መጠን ነው።
አንድ ቋንቋ እሚያውቅ ሰው ሁለት ወይም በላይ ቋንቋዎችን ከጨመረ ሰው፤ የተሻለ ዓለምን እና እራሱን የመረዳት አቅም አለው። እንዴት?
ቋንቋ ከመግባቢያነት ቀድሞ እሚያስተምረን እብስልስልታ (intelligence) ነው። ያም በእርግጥ ስውር (hidden) ነው። ያ ከጀርባ እሚከሰተው ቋንቋን ሲለምዱት፣ እንድንግባባበት ሰዋሰው እና መጠነቃልዎች (vocabularies) ከማስተማሩ ቀድሞ፤ ነገርዎችን ሁሉ እንዴት መገንዘብ እንደ አለብን ይነግረን አለ። ለምሳሌ፤ የጊዜ እውነትን ቀድመን እንገነዘብ አለ። ጊዜኃላፊ (past tense)፣ አሁንአዊ፣ እና ጠቢአዊ (future tense) አረፍተነገርዎችን ይነግረን አለ። ያንን ስንለምድ፤ የተማርንው፤ ጊዜን እንጂ ቋንቋን አይደለም። ጊዜን አጥንተን በቋንቋ መግለጥ ከእዛ መግባባት እንችል አለን።
ስለ ሰዋሰው ስንማር፣ አእምሮአችን ጊዜን፣ ነገረስራን ወይም ህላዌን (existence) በድርእናማግ (fabric) ደረጃ ማስተሳሰር እና መረዳት ይማር አለ። የጸባይ (behavior) እና ገጸባህሪ (character)፣ ስነልቦና፣ ወዘተ. ልዩነት ከአልሆነ በስተቀር፣ ሰው እሚያውቀውን ሁሉ እሚያስተምረው ገና አንደበት በቋንቋ ሲፈታ እሚከወነው የእዚህ ስውር ትምህርት መማር ነው።
ቋንቋን ስንለምድ፤ ስለነገር ሁሉ አገነዛዘብ አሰራር ወይም እይታ (perspective) እንለምድ አለን። ያን ብልሃት አፍመፍቻ ቋንቋ ከአስተማረን በኋላ፣ ሁለተኛ የቋንቋ ስጦታው ደግሞ፤ ተጨማሪ የአመለካከት መስፋት ሲሆን፣ ያም ተጨማሪ ቋንቋ ስንለምድ ነው።
ሁለተኛ ቋንቋ መልመድ፣ የአመለካከትን አድማስ ዳግመኛ እሚጠርብልን ነው። አንደኛ፤ የተማርንውን ሰዋሰው በማገለባበጥ፣ በተለየ መንገድ የመከወን እድሉ ስለእሚበዛ፣ ነገረስራን ከአዲስ የመማር እና በእዛ መከሰት ስነአመክንዮአዊነት (reasonableness) በበለጠ ስፋት እምንማር ይሆን አለ። ሁለተኛ፣ በመጠነቃልዎች መማር ደግሞ፣ የአሰያየም ትንግርትን እንመለከት አለን። የበለጠ የበራ አመለካከትን እናገኝ አለን። ለምሳሌ፣ በአንድ አሰያየም የተረዳንው ነገር ወይም ስም፣ በሌላ ቋንቋ በተለየ አግጣጫ ታይቶ እንደ ተሰየመ ስንማረው፣ ስለነገሩ የበለጠ የማወቅ እንችል አለን። በአጭሩ፤ ሁለት ቋንቋ ሁለት ዓለምን መመልከቻ የመሆን እድል አለው። አንድ አይን እና ሁለት አይን እንደ ማለት ነው። ይህ፣ በስውር ከአእምሮአችን ጀርባ ወይም በተፅዕኖ እሚገኝ፣ ስለእዚህ በሂደት ወይም ሳናስተውለው ብልህ እሚያደርገን ነው።
ሶስተኛ፣ የቋንቋዎቹን ተናጋሪዎች አመለካከት እንቀስም አለን። ለምሳሌ፣ በአማርኛ፣ ዋንጫ በላ፣ ደህና ደሞዝ ይበላል፣ ሰርግ አበላን፣ ወዘተ. እሚለው በእንግሊዝኛ ዋንጫ አሸነፈ፣ ደህና ደሞዝ አገኘ፣ አገባ፣ እንደቅደም ተከተልአቸው ሲሆን፣ ሀበሻዎች ነገርን ሁሉ ከመብል እንደእሚያገናኙ ምንም ማህበረሰብእአዊ ጥናት ሳንከውን በቋንቋአቸው ብቻ እንማር አለን።

ሁለት ቋንቋ ማወቅ በሁለት ቋንቋ መግባት ብቻ አይደለም ብለን ጭንቅላት እንደእሚያበስል በጠቋሚ ቁንጸላ አየን። ቀጥለን እነእዚህን ሁለት ቋንቋዎች እንይ።
እምናስበው፣ አማርኛ እንደእምናውቅ ነው። ስለእዚህ፣ ቀጣዩ ቋንቋ ምንድር ነው? የተሻለ አቅም የአለው ቋንቋ፣ የተሻለ ብስለት ከጀርባው ይሰጠን አለ።
አማርኛ እጅግ የልህቀት ተጻራሪ እና ኋላቀር ቋንቋ ነው። ሁለተኛ ቋንቋ ስንለምድ፣ አንዳንዴ አንደኛ ወይም አፍመፍቻ ቋንቋ እንደመልመድ የአክል ብዙ አሉታአዎ ተጽዕኖዎቹ ይደርሱብን አለ።
በደፈናው ግን፣ ግእዝን አይነት እጅግ የረቀቀ ቋንቋ ከአላጠናን፣ የተሻለው አማራጭ እንግሊዝኛ ነው። የቱም የኢትዮጵያ ቋንቋ፣ ስለሽልፍኖት (technology)፣ ነገረጥበብ፣ ወዘተ. በስምጥ መንገድ አያስተምረንም እሚል ቅድመግምት እንውሰድ።
ተረፈን አማራጭ፣ ግዕዝን መመርመር እና ወደ አንድ ከቶ እሚደንቅ ልህቀት መምጣት ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ወይም አፍሪቃ የአለው አንደኛው ስምጥ ቋንቋ እንደ ሆነ በማመን ያ እሚያገለግለን ቢሆንም፣ (በቋንቋው የተፃፉ ትልልቅ መጽሐፍዎች እውቀት ሳይሆን እንደ ቋንቋ እራሱን መልመዱ)፣ በደፈናው ግእዝን ግን ማጥናት እምብዛም ለመደበኛ ዜጋዎች የተዘጋጀ ስርአት ስለሌለው አይሆነንም።
ቀሪው ወደ ውጭ ሀገር በመዝለል፣ የተሻለውን ቋንቋ መምረጡ ነው። ቀላሉ፣ ለሁሉም እሚበጅ፣ አቅሙ የበዛው፣ በኋላ በብዙ መንገድዎች እሚረዳው እንግሊዝኛ ሆኖ እናገኘው አለን። እንግሊዝኛን፣ በጥራት ለማወቅ ምቹ ሁኔታዎች አሉን። እምንማረውም እንደ ሀገር በእዛ ቋንቋ ሲሆን በስራም አለም ከአማርኛ ጥቂት ዝቅ ብሎ ዐብይ መግባቢያአችን ነው።
እንግሊዝኛን ለኢተዮጵያአዊያን ስለእዚህ በትምህርት፣ መዝናኛ፣ እና ስራው ዓለም ማብዛት እና ማስተማር ብልህ ትልምአግጣጫ (policy) ነው። ከቋንቋዎች ማወቅ በላጭ እብስልስታ (intelligence) እሚገኘው እውነት ለኢትዮጵያዎች እንደጠነከረ እንዲገኝ፣ የቋንቋው መስፋፋት ጠቃሚ ነው።
አብሮ፣ ሁለት አማራጭ ድምዳሜዎች አሉን። አንደኛ፣ የሀገርውስጥ ቋንቋዎች አቅምአቸውን በማፋፋት፣ ተፎካካሪ የእንግሊዝኛ ምትክ ለመሆን ቢሰሩ ገሀድ የወጣ እውነት ነው። ሁለተኛ፣ ከእንግሊዝኛ ውጭ፣ ሰፊ ቋንቋ ለምሳሌ እንደ ጀርመንኛ እና ፈረንሳይኛ ማጥናቱም እሚመከር ነው። የቋንቋ ምሁርዎች የተሻለ አእምሮን እሚያነቃ አቅም የአለውን የቋንቋ ዝርዝር ሊመሰክሩልን ከቻሉ እነእዛንም መከተል ገሀድ ነው። እስከእዛ፣ በአማርኛ መውደቅ ከቀረበን የከፋ የአእምሮ አለመንበልበል ነገር፣ የእንግሊዝኛ ቀኝ እጅ እንደ መዳኛ እና ብልህነትን ማመጣጠኛ ይሁነን። ይህም፣ አማርኛ እንደ ሙሉ ቋንቋ ብርቱ በአለመሆኑ፣ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እንግሊዝኛን መልመድ በእርግጥ ከባድ ነው። ገና እንደ ትክክለኛ አንደበት መክፈቻ እምንማረው ነው። ቢሆንም፤ ብልሃትን ለእራስ ከቋንቋ እንደእሚገኘው ለማስተማር፣ በየቱም መንገድ፣ እንግሊዝኛን እንገልገል፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s