Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ዞሮ ብርቅ ዘመንን ማደን ብርቅ ጠቢ መስራት ነው[Hunting Back Fabulous Age is Making Future Fabulous]

About special attention Ethiopia needs to give through specialized researches and studies for its recent attempts to modernize during the last emperor and Dergue ages so that history is recorded better and more importantly so that the nation re-learns how to modernize faster.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane., March 31st 2021 GC.,

የ ደርግ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ልዩ ነው። ወጣት ህዝቡ፣ የተገነባው፣ አደፍርስ ላይ ዳኛቸው ወርቁ እንደ ተናገረው፣ በእሚፈራ ንጉሥ በማመጽ ነበር። ያን የአደረጉት ወ/ሮ አሰጋሽ፣ እንደአሉት ንጉሡ ሁሉን ሳይመርጡ ስለ አስተማሩት ነበር።
ያ ዘመን ግን፤ በደፈናው፣ በትልልቅ ልብዎች የተሞላ ነበር። ለነፃነት እና ህዝብአዊነት፣ ለህገገዢአዊነት (republicanism) እና ሌላ ልዑል እሳቤዎች ብዙ የተከወነበት ነው። ጠሚ. አብይ አህመድ (ሊቀምሁርዎች) ለ “ቸ” እና “ሸ” መገዳደሉ ይቁም ብለው ለ አሜሪካ-ኢትዮጵያአዊያን ጥሪ ሲሠጡ፤ የ ፍኖተ-ዲሞክራሲ መስኮተድምጽ (radio) ታታሪ አዘጋጅዎች (የ ኢህአፓ. መገናኛብዙሃን ነው)፤ “በ ቸ እና ሸ ተጋደሉ?” በእሚል አጭር መልስ እንደገለጡት፣ ለልዑልአዊ እሳቤዎች ህዝቡ ብዙ የከፈለበት ዘመን ነው።
በ ንጉሡ የተደረጉ ለውጥዎች የወለዱአቸው ምርጥ ምሁርዎች የፈለቁበት፣ ስለ ቋንቋ እና ስነጥበብ፣ ስለ ሀገር እና መጪ ጊዜ ብዙ የተሞከረበት ዘመን ነበር። ምንም ጥቂት እርጋታ እና ብልሃት የጠፋበት ዘመን ቢሆንም፣ ዘመኑ ግን ታላቁ የጥቁር ህዝብ ልዩ ታሪክ የተፃፈበት ዘመን ነው። ማህበረሰብእአዊት ዘመም ሀገር ከመገንባቱ በአሻገር፣ እጅግ ዋናው ነገር ግን፣ የባህል ለውጡ ነበር።
ጎንደርን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአያት፣ የማእረግ (class) እይታን ታጭር አለች። ህዝቡ እጅግ ኩሩ ነው በፊቱ ያም የፈሰሰ እና የተገለጠ ነው ይል አሉ። ቤተመንግስት ዘ ፋሲለደስን ሲጎበኙ ደግሞ አስደሳቹን ቅጽበት በቃልዎች መቀመም ከባድ ነው። የጎንደር ክብር ከፍታው ታላቅ ነው። ዳሩ፤ ልክ ወደ ከተማው ሲገቡ፣ የፋሲለደስን አገነባብዎች እና የህዝቡን ኩራት አቻ ዉበት በአኗኗርአቸው አይገኝም። የ ዐፄ ቴዎድሮስ ሀውልት የተገነባው በጣሊያን አስተዳደር በተገነቡ ቤትዎች ዙሪያ በተዘጋጀ አደባባይ ነው፤ ያንን አንድ ስነቃል ላይ (እቅጭ አርጌ ባላስታውሰውም) እየፎከሩ፣ ተረክበን “ገባንበት” በአሉት ቤትዎች ነው። የአፍሪቃ ዘመንአዊ የመጀመሪያ ከተማ እንደሆነችው የአክል፣ የእራሷን ዉበት አስቀጥላ ከተማዋ አላደገችም። ዉበትን የከወነችው በግርማሞገስ ሃልዎታ (attitude) እንጂ፣ ገሀድ ግን ጭው የአለባት ናት። አደፍርስ ላይ፤ ዳኛቸው ወርቁ፣ እንደተናገረው፣ የገጠሩ ሰው እጅግ ኩሩ ነው፣ እንደከተሜው እንዲማር ከተደረገ፣ ትልቅ ለውጥ እንደእሚገኝ ይናገር አለ።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ አንዱ ትልቅ ችግር፣ ከቶ ቢዘነጋም፣ በመሀከልሀገር የባህል መጥፋት ነው። መሀከልሀገር፣ ከአለፍልስፍና እሚራወጥ ነው። በብሔርብሔረሰብእዎች ስብጥር የተገነባ አንድ ወግ እና ልማድ የእሚከተል ስለአልሆነ አይደለም። በተለያዩ ህዝብዎች መሀከልም፣ ወጥ ባህል መፍጠር እሚቻል ነው። ባህልን አዛብቶ መገንዘብ እና፣ አለመማር፣ አምባግነና እና ከድህነት የተነሳ ስብእናን አዝቅጦ ጥቂት ከተገኘ እና ሰላም ብቻ ከሆነ ይበቃል ባይነት፣ ወዘተ. ባህልን በመሀከልሀገር አብዝቶ አጥፍቶት አለ። ከተማዎች እጅግ የቆሸሹ እና የአልተገነቡ፣ ሰቅጣጭ እና ጭንቅንቅ የአሉ በመሆንአቸው፣ ሰብእአዊነት ከመስተካከል ወደ መዝቀጥ ሄዶ አለ። ባህል ደግሞ የአኗኗር ደንብ በመሆኑ፣ የክፍተት ተጠቂዎች እና ባህልየለሽዎች ሆነን አለን። መንግስትን እና ማህበረሰብእአዊ ችግርዎችን እሚመለከቱ አይንዎች የሉንም። ምንም፣ የአስጨንቀን አለ ማለት ከባድ ነው።
በእዚህ መሀከል፣ ወደ ጀርባ አርባ ሀምሳ አመትዎች ስብዞር፣ ይህን ተውቦ እንመለከት አለን። ኢትዮጵያ በባህል የተንበለበለች ከክፍተት ውጭም ነበረች። (ገና ባህልነ ለመገንባት በእሚደረግ ጥረት የባህል ባለቤትነት ተሳክቶ ነበር።) በአፍሪቃ የአልታየ እና አሁንድረስ የአልተደገመ የህግየበላይነት ፍለጋ፣ የስብእና ልእልና፣ የማህበረሰብእአዊት አብሮነት፣ እኩልነት፣ ወዘተ. ይሞከር እና ጫፉ ሰግጎ የታየበት ነበር። ባህልአዊ ስንጥቃቱ ተደፍኖ፣ ጭራሽ የእሚጨበጥ የባህል (የሀልዎታ ምላሽ = answer to existence) የታየበት ነበር። ይህ፣ በሀገርአችን ታሪክ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ዘመንአዊ ባህል ቅጽበት ነው። ህዝብ፣ በአንድ ትልም ይፈስስ ነበር። ምሁርዎች እና ሌጣዎች፣ በሰፋ ጨዋታ ይገናኙ እና አንድ አመለካከትን ለማሳደድ፣ ይራወጡ ነበር። በህዝቡ ውሥጥ፣ የህዝብ አኗኗር መንገዱ እንደ አንድ የታወቀ የቀለም አይነት ነቅቶ (actively) ይታይ ነበር።
በስነውሳኔ (politics) ሂደቱ፣ የወታደሩ ጭካኔ ለታሪክ እይታ ቢሰግግም፣ ከእዛም የቀደመው ትውልድ ግን ከፍተኛ ስራን በእዛ የከወነ ነበር። አንድ ምሁር እንደመሰከረው፣ ከ ኢህአዴግ. ንጽውሳኔ (democracy) ወይም በተለይ ምርጫ፣ የ ቀኃሥ. ዘመን ለምርጫ እሚደረግ ጥንቃቄ እና ስኬቱ እማይገናኝ ስኬት ላይ የነበረ ነው። መርህዎችን የአስተናገደ ሂደት በምርጫወች ይከወን ነበር።
ይህ ሁሉ የገጠሩ ክብር የአለው የግልአወከነት አረዳድ፣ በዝማኔ እየታጀበ፣ በደግ ባህል እና ስልጣኔ ግንባታ ላይ ዳዴ ይሞክር ነበር።

ዛሬ አዲስ ዘመን እንፍጠር ቢባል፤ ትውልዱ የአነሰ አቅም ላይ እሚገኝ ነው። ሰነፍ አኗኗር ላይ ነው። የአንቀላፋ እና የተገፋ፣ ዞሮም የእሚገፋ ነው። ፱ ሺህ፣ ተከታታይ አፍጊት (sitcom) መግቢያ ሙዚቃው እንደ አለው፣ ለእማይጠቅመን እና ለእማንጠቀመው ነገር እምንጣላ እና ለአለን እንክብካቤ አድርገን ማደግ ስንችል በአናሽ አመለካከት ወደ ትልቅነት እማናልፍ ሆነን አለ ይል አለ። ቀናው መንገድአችን ችኮላ እና አስተዋይነት-አጥነት መሆን ከሆነ፣ ግራአችን አምባግነና፣ ዘረኝነት፣ አለመማር፣ ስንፍና፣ ወዘተ. ከሆነ፣ ስደት እና ፍልሰት ወዘተ. ሁሉም አስቸጋሪ ጉዳይ ሆኖብን ከባህል እና መሻሻል የተፋታን እንሆን አለን። እን ሆንንው።

ወደፊት ደህና አኗኗር ቢቋቋም፣ ሀገር ቢዘምን፣ ወደ እዚህ ስልጡን አያያዝ እንመለስ አለን። ዘፈንዎች፣ ከሽንጥ እና ዳሌ ወደ ዋይዋይ ሲሉ፣ እናንተ ሾካኮች፣ ሌላውም ስነእናኪነጥ. ከዝቅታው ወደ ማህበረሰብእአዊ ቁስል አሰሣ እና ህክምና (እንደ-እነ አደፍርስ፣በፍቅር እስከ መቃብር፣ ከአድማስ ባሻገር (ከውድ ምግብቤት ወጥታአችሁ መንገድ ዳር በተኙ ሰው እምታገሱ ወዘተ. እየአለ እንደእሚናገረው)፣ ሁሉም ወይም በብዛት ወደ ማደግ ይመለስ አለ። ህገገዢነት፣ እኩልነት፣ አርነት፣ ወዘተ. እሚኖር ይሆን አለ። ቀድሞ ግን ነገሩ ሲፈጠር፣ እሚከወነው፣ ወደ እዛ ዛመን መመለስ ወይም መመሳሠል ይሆን አለ። በመዘመን ሂደት ሁሌም፣ ወደ እዛ መመለስ ከአለ፤ አንዱ መንገድ ቀድሞ ወደ ተዘጋጀው ያ ዘመን መመለስ ነው። ያም፣ የቀኃሥ. ብጁው ዘመን ነው። በታሪክአዊ ስህተት እራስአቸውን የጣለው እና ቀጥሎም የታገለው፤ ዋጋም የከፈለው፤ በቀሩ ጥቂትዎች ደግሞ ለአምባግነና ሀገሩን የአስረከበው፤ ግን ጫፍ የባህል ጅማሮ የካበው ትውልድ። በእዚያ፣ ባህል እና አኗኗርን መመልከት እሚቻል ነው።

በ ማማ በሰማይ፣ The Beautiful Things that Heaven Bears, ወዘተ.፣ በዘሪቱ ከበደ የደርግ ዘመን መቼት ፊልም፣ ወዘተ. በዘፈንዎች፣ ወሬዎች፣ ወዘተ. እሚተው አይደለም። በተሻለ ስፋት ያንን ዘመን በልዩአዋቂነት (specialization) ማጥናት ለኢትዮጵያ አስገዳጅ ነው። ስለ ትግል፣ ስህተትዎቹ፣ መማር ስለአለብን፣ መድገም ስለ ሌሉብን ነገርዎች፣ ስለ አንዣበበው ባህል አወላለድ እና አመጣጡ፣ ብዛቱ እና ስፋቱ፣ ዘርፍዎቹ፣ መስተጋብርዎቹ፣ ወዘተ. በጥልቀት መመርመር እሚገባው ብዙ በደፈናው አለው።
የአስገረመ ዘመኑን ከአልተነተንነው፤ እምንደርስበትን አናውቅም። ያ ዘመን እመርታን ቀድሞን ከሞከረ፤ እኛም አሁን ኋሊትአዊ ዝግመት ከፈጸምን፣ መመለሱ እንዲሰምር እንዴት እና የት ወደእዛ እንደተደረሰ መመርመር እና በነቢብዎች ሁሉን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው። የቅርብ ታሪክ፣ የአሁኑ እጅግ የቅርብ ቅጥያ ከመሆኑ በላይ፣ የወደፊቱም ኋላ ነው።
ወደነገ ለመድረስ፣ ትላንትን መመልከት በመደበኛነት ይነገር አለ። ታሪክም ያንን የእራሱ መሰረት የአደርገው አለ። ይህ ግን ከታሪክ ትምህርት በላይ ነው። ወደፊት መራመድ ሲሳካ፣ እሚደረስበት ጀርባ ነው። ወደኋላ መመለስ፤ ወደፊት እንደመሄድ እሚሆንብአቸው ሁኔታዎች ውስጥ ነን። በተለይ ኢህአዴግ. እጅግ የአንቀላፋ አምባገነን ስለነበር፤ ወደፊትአችንን ከቀኃሥ. ጀርባ አሽቀንጥሮት አለ። ደርግ እንኳ በነበረበት ቢቀጥል፣ ዛሬ የብራዚል ስንምጣኔ ይኖረን እንደነበር እሚናገሩ አሉ። መደምደሚያው፤ ዛሬ እጅግ እንደ ሀገር ከወረድን፣ የአለንው በፊት ተወጣጥተን የተውንውን ነው። እምናዘግመው፣ ወደእዛ ወደከሸፈ ከፍታ ነው። ያ፤ የኢትዮጵያ ድህረ-ድል/ነፃነት ትውልድን እስከ ኢህአዴግ. አጥንተን ለመመርመር አንድ ስርአተ ትምህርት/ዳግ-ጥናት ክፍል እሚያስፈልገው እንደሆነ እሚያስመለክተን ነው። ወደፊትን፣ እንደ ሀገር ከኋላ እንጨልፍ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,