Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

አብይ አንድ የኢትዮጵያ ቀውስ፡ የባህል አለመሰራት የትዳር እና ቤተሰብእ ጉዳይን እንደአበላሸው

About solving the Ethiopian societal problems through helps to the ailing family institution of the countrt.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 2021 GC.,

Take this on PDF here.

የኢትዮጵያው ማህበረሰብእ፤ አንድ ምሰሶ ችግር፣ የተዘነጋው የቤተሰብ ጉዳዩ ያም ውጥንቅጥ የሆነው ነው። ለልኮት የአክል፣ የ ቤተሰብ ጨዋታ ትመ. እይት (Tv. Show)፤ አሳላፊው እሸቱ መለሰ ሁሌ (አሁን ከአመት በላይ) ሳይደክም እንደእሚለው፣ ቤተሰብ ሲደመር ቤተሰብ ሀገር ነው፤ የማህበረሰብእ አላባአዊ – ስለእዚህ የሁሉ መሰረት – ነው። በትክክል፤ ይህን ተቋም ምን ችግር እየገጠመው ነው?
በሀገርአችን ዉስጥ፤ ቢያንስ በቅርቡ አስርታት (decades) ቤተሰብእ ልል ህላዌ ሆኖ አለ። በዋነኛነት የስነምጣኔ መደህየት፣ እና የስልጣኔ ግጭት፣ ወደ ቤተሰብእአዊ ድብዛዜ አምጥቶን አለ። ስለእዚህ፤ ህግ፣ መንግስት፣ ተቋምዎች፣ እምነትዎች፣ ባህል እና ልማድ ወዘተ. እጅግ ስስ ጥበቃ ለቤተሰብ ሰጥተው ከፍተኛ የአልጠነከረ ግንኙነት በቤተሰብ አባልዎች መሀከል እንዲፈጠር ሆኖ አለ። የተጋቢዎች መፋታት እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ፤ ፍርድቤትዎች፣ በዋነኛነት እሚመለከቱት ፍሬጉዳይአቸው የፍቺ እና ቀለብ ወይም ተያያዥ የቤተሰብእ ጉዳይዎች ናቸው። አንድ ቀልደኛ የታክሲ ወያላ እንደዘበት ሰርገኛዎች በመኪና ከአጠገቡ ሲያልፉ አዲስአበባ ላይ እንደ አለው፤ “መጋባት እኮ መፋታት ባይኖር ነበር፤” የአለውን እውነት እሚያሰኝ የጋብቻ ቅድስና የጠፋበት ዘመን ሆኖ አለ። ይህ ደፈናአዊ ዳሠሳ ነው።
በሌላ መንገድ፣ ደግሞ በላይ ማናዬ በሁለተኛ መጽሐፉ (ከአራት ኪሎ እስከ ስድስት ኪሎ) በግልጽ እንዲሁም በመጀመሪያው ልብወለዱም ቀንጨብ አድርጎ (አዙሪት ዘአልፋ) እንደገለጠው፣ ቤተሰብእ እጅግ የተፈረካከሰ ተቋም እንደሆነ እና ልጅዎችም ተምረው አንድአች ደረጃን ሲይዙ ዞረው ቤተሰብእ እንደእማይረዱ (በቸልታ ወይም ባለመቻል) ይነግር አለ።
በሌላ ጎን፣ ቤተሰብእ በእጅግ ፈጣን የዘመን ለውጥ መሀከል እሚበቅሉ ልጅዎችን በማሳደግ እና ሩቅ በእሚመስል ዘመን አድገው የደረሱ የቤተሰብእ አሳዳሪዎች (Guardians) አስተዳዳሪነት መሀከል ትልቅ ስውር እና ግልጥ ግጭት ሆኖ አለ። በደፈናው የስምንተኛው ሺህ ዘመን ልጅ እንደእሚባለው አረዳድ፣ በእንጣጢት (hyper) የዝማኔ እንቅስቃሴ እና አረዳድዎች የተወሳሠበ ስብእና በወጣትዎች እና ታዳጊዎች ኖሮ ከበላይዎች ጋር መጣጣም እየከበደ ነው።
በውጤቱስ? ልጅዎች በአልተሟላ የቤተሰብ ከባቢ አዳጊ ሆነው አሉ። ታዳጊ እና ወጣትዎችን ወደ ጠቢ (future) እሚመሩአቸው፣ የቤተሰብ ጠንካራ ተፅዕኖዎች ቀንሰው አሉ። በአሳዳሪ እና አዳሪዎች መሀከል ስነልቦናአዊ፣ ስነምግባርአዊከ ስልጣንአዊ፣ እና ተመሣሣይ ምትክ/ዋጋየለሽ ቅርርብዎች ትስስርአቸው ረግቦ ከነበረው መደበኛ ተፅዕኖው እንኳን እየወረደ ነው። ስነምግባር፣ አስተዋይነት፣ ለእራስ፣ ቤተሰብ፣ ሀገር፣ ወዘተ. አርቆ ማሰብ፣ ንቅአተ-ማህበረሰብእ እና ተሳትፎ፣ ቀንሶ አለ። አብሮታ በምላሹ አሽቆልቁሎ፣ የተጠያቂነት፣ ይሉኝታ፣ አንድነት፣ ጸረሙስና አኗኗር፣ ከዕፅ፣ በሽታ እና ቀውስ ንጹህ ዜግነትዎች ሸሽተው አሉ። የስነምጣኔ ቀውስ ችግርዎቹን በብዙ አባዝቶአቸው ይገኝ አለ። ወደ ግማሽ እሚጠጉት የኢትዮጵያ ታዳጊዎች የቀነጨሩ እየሆኑ፣ በአቅም ተገድበው፣ በከላይ እማበለጽግ ህይወት በማደግ ላይ ናቸው። የሰው ልጅ ትልቁ ስጦታ፣ ቤተሰብእአዊ አኗኗር ቀዝቅዞ፣ ህይወትም ደስተኛነትዋ በዓለም ከአሉ ሀገርዎች ትንሽ እሚባሉት ሀገርዎች መሀከል ሆና አለች።
በአጭሩ፤ ምን ይህን ሁሉ ፈጠረብን?
፩) የማህበረሰብእ ንቃተህሊና አለማደግ። ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም፤ የባህል እና ተጓዥጉብኝት (tourism) ሚኒስቴር እንደ አሉት፤ “የ ባህል ወረራ” ትድድር (management) አለመደረጉ አንዱ ችግር ነው። ንቅአተህሊና እና ብስለት በደፈናው በማህበረሰቡ የለም። ያ ኖሮ ህዝብ በአማካይ ብልሃቱ በርትቶ ሲኖር፣ ልጅዎችም እያንፀባረቁ የባህል እና አስተሳሰብ ብልሃትን በማንጸባረቅ እሚያድጉ ይሆን አሉ።
፪) የመንግስት እና የስርአተትምህርት ቸልታ። አመለካከት እሚጠነክርበት፣ ተግባር-ተኮር እውቀት እና ክሂሎት እሚገኝበት፣ አብሳይ ትምህርትአዊ እድገት ውስጥ ታዳጊዎች አያድጉም። በዓለም ሉልአዊነት እና ምጡቅ ዝማኔ የተነሳ፣ የእሚመጡ ብዙ የእየዘርፉ አማራጭዎችን አስተናግዶ በምላሹ በብልሃት ወደ ደግ ማንነት መዘመን እንጂ መጠቃት እነዳይከወን እሚያስችል ማብቃትን ከመንግስትም ሆነ ስርአተትምህርቱ መደበኛ ፍፃሜ ላይ እማይገኝ ሆኖ አለ።
ልጅዎች፣ ወጣትዎች፣ አዋቂዎች፣ ወዘተ. ነፃነትን እንደፈለጉ በመረዳት፣ ቤተሰብ ጎጂ ነገርንም መከወን እሚያሻ ከሆነ መከወን እሚመክሩ እሚከውኑ ሆነው አሉ።
፫) ሽልፍኖትአዊ (technollgical) ትውልድነት። ጠቃሚነቱ ቢበዛም ትድድሩ ከብዶ፣ ሽልፍነለትአዊ አማራጩ በደንብ ለአልነቃ፣ ለአልተማረ፣ እና በወላጅዎች ለእማይመራው ትውልድ፣ እጅግ ፈጣንነት፣ ስንፍና፣ ግልብነት (ጥራዝ ነጠቅ)፣ ወዘተ. አምጥቶት አለ።
የመውጫ መንገድዎች
የ አደፍርስ ልብወለድ አንድ ነቢብ አለው። ልቡሰጥላአችን ከእሚስማማው ግለሰብእ እጅግ ተጠናንተን በመጋባት ማህበረሰብእን ባለጠንካራ ጋብቻ ባለቤት እናድርገው ይል አለ። ለእዚህ ደግሞ፣ የባህል እና አኗኗር ለእየአካባቢው ተስማምቶ እንዲቆይ እና ተረጋግቶ በመሰልጠን እንድንበረታ ይናገር አለ።
የ መስፍን ጎንለጎን (ቢንያም ኃይለመስቀል) ልብወለድን በእዚህ የአስታወሰ ነው። በእዛ ስነልቦናአዊ ትርክት የእነ እማዋይሽ ቤተሰብእ አባትአቸው፤ እንደ በዕውቀቱ ስዩም ክንፋም ህልምዎች ከገጠር፣ ወደ ቀጣይ ከተማ ከእዛ ወደተሻለው በመንቀሳቀስ በተሻለው አኗኗር ይነሆል አለ። በመጨረሻ ደግሞ፤ ከቤተሰቡ ይፋታ አለ። ቤተሰቡ ሁሉ እሱን አጥቶ በቀውስ ሲዋጥ፣ አስጨናቂውን ነገር ለመጋፈጥ ሲገደዱ እንመለከት አለን።
አደፍርስ እሚመክረው ዋና አንዱ ነጥብ፤ ሀበሻ በከተማ እና ገጠር መሀከል ተለያይቶ እሚኖረው በሰፋ ልዩነት ስለሆነ፣ በእርጋታ ለውጥዎችን ይያዝ ከአልሆነ መፋታት ይበዛ አለ ብሎ የነበረው ገና በንጉሡ ዘመን ነው። ዛሬ ያን ችግር ቢመለከተው ኖሮ፣ እጅግ ስለእሚበዛ የበለጠ ይደነግጥ ነበር። ከተሜነት እና የበለጠ ከተሜነት፣ የበዛ እንቅስቃሴን ስለእሚከውን መፋታቱ አይሎ አለ።
አንድ ምላሹ፤ ሀገረሰቤነት እና መሀከልሀገርን፣ ማስተሳሰር ነው። መንግስት እና እንደ አደፍርስ እሚጨነቅ ጠቢብ፣ ባህልን በከተማ እና ገጠሩ አንድ ወጥ አድርጎ ከአኗኗር ዘዬ በቀረ እምብዛም መለያየት እንደሌለ እና ለምሳሌ የቤተሰብእ ተቋሙ ከቶ አንድ እንደሆነ እና ያ ከምንም እንደእሚበልጥ እያስተማረ ህዝቡ በከተሜነት እና በሀገረሰቤነት የተነሳ እሚደርስበትን የባህል ግጭትዎች በብልሃት እንዲያሸንፈው ብዙ የደርሶ ማስተማር እና ማንቃት ተግባርዎችን መከወን እሚገባ ነው። ሀገረሰቤ እና ከተሜ፣ ገና ከአሁኑ እንዲህ በልዩነት ከእሚሰፉ፣ የሠመጠ ዉይይትዎች፣ የማህበረሰብእአዊ ተሳትፈለዎች እና ንቅአተህሊና ክወናዎች በመተግበር፣ ይህንን መዋጋት እሚቻል ነው።
የጋብቻ አብሮ ቆይታዎችን አብዝቶ መሸለም እና ማበረታታትከ ፍቺዎችን ደግሞ አብዝቶ ማዳከሚያ ትልምአግጣጫዎች (policies) መጠቀም እሚገባ ነው። ለአዋቂ ግለሰብእዎች ከአለብን ኃላፊነትዎች የበለጠ ለነገው ሀገር (ልጅዎች) የበለጠ ኃላፊነትዎች አሉብን። የተራራቁ ወላጅዎችን በእዚህ ውጥንቅጥ ድጋፍ ፈላጊ ዘመን ለልጅዎች መተው እጅግ ከፍተኛ የረዥምጊዜ ቀውስ እና እዳ እሚሰጠን ነው።
የባህል እና ስርአተትምህርት ንቅአት እና ዝማኔ እጅግ እሚያሻን ነን። በተሻለ አቅም እንዲጎለብቱ፣ በቋንቋዎችአቸው እንዲማሩ፣ የበለጠ ፍሬ ገርዎች እና ተግባርአዊ እውቀትዎችን እና ክሂሎትዎችን እንዲያሳድጉ፣ እሚያስችሉ ትምህርትዎችን እና የባህል ስራዎችን ከእየዘርፉ መከወን እሚያስፈልግ ነው።
ነገርዎችን ወደ ላቀ (advanced) መስተካከል ስናመጣው፣ የቤተሰብእ ነገረሁኔታው የስልጣኔ ሁሉ መሰረት ነው። እንደ ገዳ ስርአት፣ ሁሉም አዋቂ የሁሉም ታዳጊ ወላጅ ሆኖ፣ የጠበቀ ማህበረሰብእ ከኖረን እሚገባ ነው። የመተባበር፣ መተሳሠብ፣ አብሮነት፣ ወዘተ. ስነልቦናውን መመስረተጀ የስልጣኔ መነሻ ነው። የቱም እድገት ከአለ ቅብብል እና አብሮታ ከቶ መንፏቀቅ አይቻለውም እና። በቀጣይ የላቀ ደረጃው ደግሞ፤ የ boko haram ፍልስፍናን ማብረሻውን የህፃንዎችን ህይወት በበለጸገ እና ዝሙን መጽሐፍት እና ክሂሎት የሞሉአቸው አስተዳደግዎችን መከወን እና ስልጣኔን በተቀላቀለ መንገድ እንዲያድጉ ማድረግ እሚቻል ነው። መጽሐፍዎችን እና ጥበብን በትምህርትቤትዎች ብቻ ሊያውም በበዐድ ቋንቋ ገና በልጅነት እንዲጋፈጡ በማድረግ፣ ማወቅን እሚጠጥር ቤትስራ አድርጎብአቸው፣ አውቀው ሲለወጡም ሀጢያት ከማስመሠል፣ አብረው ከእውቀቱ ጋር በማደግ፣ በመማር ወቅት አንድም የበዛ ለውጥ ባለማስመልከት በቤተሰብእ ፍቅር እንዲፀኑ ሁለትም በቀላሉ የልጅነትን ህይወት ሁሉም አድጎ ስለእሚኖር በእውቀት የተቀረፁ ህፃንዎች የአወቀ አዋቂ የመሆን እድልአቸው እንዲጨምር ማድረግ ይቻል አለ። የትምህርትን በዐድነት በከፊል ማስወገጃው መንገድ ያ ሲሆን፣ ኩርማን ምላሹ ደግሞ ሀገር እና ማህበረሰብእ የተማሩትን በህይወትአቸው በመኖር የለወጡት ወቅት እሚመጣ ነው። ብቻ፤ ቤተሰብእን በሰፊ ጉዳይዎች በመንከባከብ የልጅዎች ጠቢን መቅረጫ ማእከል ማድረግ እና በምላሹ ደግሞ የስልጣኔን ትትረት መመገብ እሚቻል ነው።
ሌላው ዋና ነቁጥ፣ ሁሉም ሲደመደም፣ ባህልን ማጠንከር ነው። በደፈናው፣ የባህል ክፍተት በሀገርአችን አለ። አንድም፣ የስልጣኔ ወደእኛ ሀገር መግባት የከፈተው አደጋ ሲሆን አንድም ከስብጥርነትአችን የተነሳ አንድ ወጥ ልማድ ይዘን መኖር ባለመቻልአችን፣ የከተማ ስፍራዎች በተለየ የባህል ክፍተት እሚገኝብአቸው ናቸው። ቤተሰብእዎች በመሰለአቸው መንገድ እንጂ በአንድ ወጥ ልማድ አመሳስለው ልጅዎችን አያሳድጉም። ሀገርአችን በደፈናው አንድ ወይም ተቀራራቢ የአኗኗር ዘይቤ የሌለባት ናት። ከገጠርዎች ወደ ከተማ፣ ከከተማ ወደ ላቀው የከተማ ክፍልዎች፣ የአሉት ልዩነትዎች ሰፊ ናቸው። በስነእናኪነጥበብ፣ መገናኛብዙሃንዎች፣ ይፋ ግንኙነት መንገድዎች፣ ወዘተ. ስከ ልብ ትርታው ድረስ ማህበረሰቡ እራሱን ለእራሱ ተገላልጦ ወደ አንድ የህላዌ (existence) ደንብ አልቀረቡም። ሀገርን በአንድ ወጥ ወይም ተቀራራቢ መንገድ ማኖር ሲቻል፤ ዘይቤው ተተንባይ በመሆኑ ቤተሰብእንም እንዲሁ በታወቀ መንገድ ማስተካከል እሚቻል ነው። የአኗኗር ጥበብአችንን፣ አንደኛ ቢያንስ በግልጥ ማሳየት እና የማያጠራጥር ወይም ክፍተት የሌለው በማድረግ፣ እንዲሁም ሁለተኛ የቀረውን በማሟላት እና በማስተካከል፤ የባህል ጥንካሬ እና የቤተሰብእ ተቋም ስኬትአማነትን ማስተካከል እሚገባ ነው። ከእዛ ውጭ፤ የቱም የሀገር ብልጽግና ዉሸት ነው። ጠቢአችንም ሠነፍ እና ሙሉ እማይሆን፤ ዕዳ ማብዛቱም እማይቀር ነው።
በቀኑ መጨረሻ፤ የስልጣኔ ትድድር (Management of civiliation) አንድ ዋልታው ይህ ነው። የስንምጣኔ፣ ባህል፣ ማንነት፣ ስነውሳኔ (politics)፣ ህላዌ፣ ሉልአዊነት፣ ወዘተ. ላይ ተፅዕኖዎችን እሚያቀርብልን የድልአድራጊነትአችን እና ተሸናፊነትአችን አንድ ቁልፍ የአለበት ዘርፍ ነው። ከአጥፊ የስነውሳኔ ጉልበትነት፣ ከማልማት አቅም ውጭነት፣ አማራጭ አጥቶ ከዘር እና ቡድን ጎሬ አሳሽነት፣ ከአለም እና አህጉር መድረክዎች ሩቅነት፣ ወዘተ. ተለውጦ፣ ወደ ቀኝ ስልት በመጓዝ፣ የተሳካለት ማህበረሰብእን ለመፍጠር፣ ይህን የቤተሰብእ ጉዳይን መመልከት እና በምርአዊ የመንግስት ኦዲት ማካተት እነ መንቀሳቀስ አንዱ ትልቅ ቤትስራ ነው። ቤተሰብእ የሀገር እጅ እና እግር ከሆነ፤ እንክብካቤ እና አያያዙም አቻ ሆኖ መገባቱ አስገዳጅ ይሆን አለ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s